G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
on novel" የሚለው statement ግን ምክንያት ጠቋሚ ቃል አልተጠቀም። ከዚህ ምን እንረዳለን?

ሁለት እና ከሁለት በላይ premises ካሉን እና እነሱን በ ምክንያት ጠቋሚ ቃል(premises indicator words) መግለፅ ብንፈልግ አንደኛውን premise ብቻ በ ምክንያት ጠቋሚ ቃል መግለፅ እንችላለን ወይም ደግሞ ሁሉንም premises በምክንያት ጠቋሚ ቃል መግለፅ እንችላለን።
👇👇👇👇 ተመልከቱ

" Given that Moby Dick was written by sheksper and Moby Dick is a science fiction novel" ማለት እንችላለን።

ወይም ደግሞ፡

"Given that Moby Dick was written by sheksper and Given that Moby Dick is a science fiction novel"

👆👆 ሁለቱም ይቻላል።

🌷Conclusion indicator words.

Conclusion ማለት ማስረጃዎችን መሰረት በማድረግ ወይም ማስረጃዎችን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት ማለት ነው።

🤔 ታዲያ ማስረጃዎቹን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ስንሰጥ ፡ ድምዳሜውን ለመግለፅ ድምዳሜ ጠቋሚ(አመልካች) ቃላቶችን መጠቀም እንችላለን።

😊ድምዳሜ ጠቋሚ ቃላት ማለት በ እንግሊዝኛው conclusion indicator words ማለት ነው።

😁 ስለዚህ በ argument ቱ ውስጥ ከሚገኙ statement ቶች መካከል ድምዳሜ ጠቋሚ ቃላቶችን የሚጠቀመው statement conclusion ነው ማለት ነው።

🤔ለመሆኑ ድምዳሜ ጠቋሚ ቃላቶች የሚባሉት እነማን ናቸው?

Conclusion indicator word

🎈 Therefore
🎈 Wherefore
🎈 Hence
🎈 Whence
🎈 As a result
🎈 Thus
🎈 Consequently
🎈 Accordingly
🎈 it must be that
🎈 it follows that
🎈 implies that
🎈 Entails that
🎈 We may infer
🎈 We may conclude

👆👆እነዚህ በሙሉ ድምዳሜ ጠቋሚ ቃላት ወይም conclusion indicator words ይባላል። ሁሉንም ያዟቸው!!

✏️ ስለዚህ በ argument ቱ ውስጥ ካሉ statement ቶች መካከል ከላይ የተዘረዘሩትን ቃላት የሚጠቀመው statement conclusion ነው ማለት ነው።

😋 ምሳሌዎችን እንመልከት።

🔷 Example 1

" Easter is always on a Sunday. Consequently, the day after Easter is always a Monday".

የትኛው ነው Conclusion?
የትኛው ነው Premise?

Conclusion ማለት ማስረጃን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት ነው። ድምዳሜውን ለመግለፅ ደግሞ ድምዳሜ ጠቋሚ ቃላትን መጠቀም እንችላለን። ስለዚህ በ argument ቱ ውስጥ ካሉ statement ቶች መካከል ድምዳሜ ጠቋሚ ቃላትን የሚጠቀመው statement conclusion ነው ማለት።

በዚህ ምሳሌ መሰረት ድምዳሜ ጠቋሚ ቃል Consequently የሚለው ነው።

Consequently የሚለውን ጠቋሚ ቃል የተጠቀመው statement ደግሞ👇👇

"The day after Easter is always a Monday."

ስለዚህ ይህ ነው👆Conclusion የሚሆነው።

🔷 Example 2

"All banks are financial institutions. Awash Bank is a bank, it follows that Awash Bank is a financial institution."

😉 ስለዚህ በዚህ ምሳሌ መሰረት it follows that የሚለው ድምዳሜ ጠቋሚ ቃል ነው።

it follows that የሚለውን ድምዳሜ ጠቋሚ ቃል የተጠቀመው statement ደግሞ👇👇

"Awash Bank is a financial institution"

ስለዚህ ይህ ☝️ conclusion ነው ማለት ነው።


😋ፈተና ላይ እንዴት እንደምትፈተኑ ደግሞ ልንገራችሁ።

🔥 Which one of the following is/is not premise indicator word?

🔥 Which one of the following is/is not conclusion indicator word?

ተብሎ በ ምርጫ መልክ ፈተና ስለሚወጣ ሁሉንም ጠቋሚ ቃላቶች ልትይዟቸው ይገባል።

ወይም ደግሞ

Argument ቱ ውስጥ indicator word ሰጥተው የትኛው ነው premise የትኛው ነው conclusion ተብሎ ትጠየቃላችሁ። ምሳሌ ፡

" Because many movie actresses are millionaires and Angelina Jolie is a movie actress, it implies that Angelina Jolie is probably a Millionaire."

💥 Write the premises and conclusion of the above argument?

ተብሎ ፈተና ሊወጣ ስለሚችል በሁለቱም መንገድ ተዘጋጁበት።


🌹2ኛው) inferential claim

በ Argument ውስጥ የሚገኙትን premises እና conclusion ማወቅ ከምንችልባቸው ዘዴ አንዱ inferential claim or inferential link ነው። ይህን ዘዴ የምንጠቀመው በ argument ቱ ውስጥ የሚገኙት statement ቶች indicator word ከሌላቸው ነው።

🤷‍♂ indicator word ከሌላቸው እንዴት አድርገን ነው premises እና conclusion ኑን መለየት የምንችለው?

🤷‍♀ መለየት የምንችለው በ premises እና በ conclusion መካከል ባለው inferential link ነው።

🙋‍♂ inferential link ማለት ደግሞ በ premises እና በ conclusion መካከል ያለው ዝምድና ወይም ግንኙነት ነው።

ዝምድናቸው ምንድን ነው🤔?

🌿 Premise - ማለት ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የምናቀርበው ማስረጃ ነው።

Conclusion - ማለት ደግሞ ማስረጃዎቹን ተጠቅመን የምንሰጠው ድምዳሜ ማለት ነው።

😁 ዝምድናቸው ልክ እንደ እናት እና ልጅ ነው። ምክንያቱም premise የ conclusion መገኛ ነው።

ስለዚህ indicator word ካልተሰጠን፡

Argument ቱ ምንድን ነው ለመግለፅ የፈለገው? የተጠቀመው ማስረጃ ምንድን ነው? ማስተላለፍ የፈለገው ሀሳብ ምንድን ነው?

እነዚህን ጥያቄዎች ራሳችንን በመጠየቅ የትኛው premises እንደሆነ እና የትኛው conclusion እንደሆነ በቀላሉ መለየት እንችላለን።

🔷 Example

" Paying off terrorists in exchange for hostage is not a wise policy , this action will only lead them to take more hostages in the future."

👆 አያችሁ አይደል ይህ argument ምንም አይነት indicator word አልተጠቀመም። ስለዚህ premise ሱን እና conclusion ኑን ማወቅ የምንችለው በ inferential link ነው። እስቲ እናንተ ሞክሩት።

በስተመጨረሻ የምነግራችሁ logic የሚያጠናው argument ከመደበኛው argument ይለያል። ማለትም ክርክር የሚለው አይደለም።

"Aristotle is the father of Logic"

©A+ tutorial class.
G-Tutorialclass
Channel name was changed to «ወቅታዊ ሹክታዎች🎤 👁👁👂»
የብዙዎቻችሁ ምርጫ ትምህርቱ በኖት እንዲሰጥ ነው። ስለዚህ ዛሬ የ ሎጂክ ኖት ከጥቂት ደቂቃዎች በሗላ ይለቀቃል። የሎጂክ ትምህርት ብዙ ማብራሪያ እና ምሳሌ ስለሚያስፈልገው የምንለቅላችሁ ኖት ረዘም ይላል። ስለዚህ የምመክራችሁ ነገር ለማንበብ እንዳትሰለቹ ኖቶቹ ይጠቅሟችሗል። በ እንግሊዝኛ የተፃፋትን ገለፃዎች ያዟቸው። በአማርኛ የተፃፈው ደግሞ ለማብራራት ነው ስለዚህ ተመስጣችሁ አንብቡት።

🙌 ከዛ ኖቱን ካነበባችሁ በሗላ ያልገባችሁን ማንኛውን ጥያቄ በውስጥ መስመር ላኩልኝ። ጥያቄዎቻችሁን በ ድምፅ ለማብራራት እሞክራለሁ።

ይህን ቻፕተር እንደጨረስን worksheet አዘጋጅቼ እሰጣችሗለሁ። ከዛ ፈተና ይኖራችሗል።
Eshi..ቡ negn ke AAU ....ewunet lemenager ...mejemeria akababi manbeb kebed blogn neber mkniatum le gbiw adiss sleneberku gn demo alama neberegn le alama sil yechalkutin yakil anbibialew yetebekutin wutet aginchalew...so


Ene emnagerew neger mejemeria alama yinuren new alama kalen leza alama sinil mnm neger sacrifie madreg alebin...kenguadegna gar meznanat.....social media....online game ..manmn temariwoch sitekemu eyayu bzu sew follow yaregachewal...keza final lay regreet yadergalu.....regreet madrg mnm tkm yelwum gbi yemetanew memar eskehone dres memar new arif grade kelele kefelegnew department megbat kebad slehone

I think...manignawum sew alam kalew ena lenalamaw eminor gbi lay yalen challenge malef enchilalen so mejemeria alamaye mndn new blen erasachin endamt elalew

Amesegnalew🙏

©A+ tutorial class
በዚህ ሳምንት ከተማርናቸው የተወጣጡ ጥያቄዎች👇👇

🖇Psychology
1. Perception is the process that detects the stimulus from the Env't.
A. True
B. False

2. Which of the following can be another name for Absolute threshold?
A. Difference Threshold
B. Relative Threshold
C. Stimulus
D. Limen

3. Which of the following definition expresses "Sensory Adaptation"?
A. It is the tendency of our sensory receptors to have increasing response to unchanging stimulus
B. It is the tendency of our sensory receptors to have decreasing response to the changing stimulus
C. It is the tendecy of our sensory receptors to have increasing response to the changing stimulus
D. It is the tendency of our sensory receptors to have decreasing response to the unchanging stimulus

🖇Maths

1. Suppose the truth value of p and q is True & that of r is False, then find the Truth Value of p=>(q^r)?

A. True
B. False

2. Which of the Following is #NOT an open statement?
A. X+5=9
B. He is Freshman student
C. Mr X was your math teacher
D. Two plus two is four

3. Check whether the following proposition is Valid or not?
(Assume that all premises are true)
👉P=>q, p |- negation of q

መልስ መላክ ከፈለጋችሁ
@Ucan_scorebot

©A+ tutorial class
❗️ፈተና ላይ ብዙ ጥያቄ ስለሚወጣበት ይህን part በአግባቡ ልትረዱት ይገባል።

📕 Chapter Two

📖 Basic Concepts of logic

📚 Types of Argument

✏️ There are two main types of argument: these are 👇👇

📍 Deductive argument
📍 Inductive argument

ለአሁን dedeuctive argument እንመልከት።


🎈Deductive argument

Deductive ማለት from General to specific ማለት ነው እየተባላችሁ ተምራችሗል Biology ትምህርት ላይ ምናምን።

Logic ላይ ያለው Deductive ግን ይለያል እስኪ እንየው።

🌷 Deductive argument - is an argument in which the premises are claimed to support the conclusion in such a way that it is impossible for the premises to be true and the conclusion false.

🌷 Deductive argument - is an argument in which the conclusion is claimed to follow "necessarily" from the premises.

😊 Deductive argument የ argument አይነት ነው። argument ማለት ደግሞ ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት ማስረጃ ወይም ምክንያት የማቅረብ ሒደት ነው።

🤔 ታዲያ የምናቀርበው ማስረጃ(premises) ስለ አንድ ነገር የምንሰጠውን ድምዳሜ(conclusion) ሙለ በ ሙሉ የሚደግፈው ከሆነ ፡ በሌላ አባባል የምናቀርበው ማስረጃ ለ ድምዳሜው ሙሉ በሙሉ ዋስትና(Guarantee) ከሆነው Deductive argument ይባላል።

🤔 ይህ ማለት ደግሞ Deductive argument ላይ ያለው premises(የምናቀርበው ማስረጃ) true ነው ብለን ብናስብ ፡ እና true ነው ብለን ያሰብነውን ማስረጃ(premises) ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው conclusion(ድምዳሜ) false መሆን አይችልም። ምክንያቱም ያቀረብነው ማስረጃ ለ ድምዳሜ ዋስትና ስለሆነ። so,

😴 in Deductive argument, " assume the premises is true , it is impossible for the conclusion to be false."

❗️ እዚጋ ማስተዋል ያለባችሁ ነገር " የምናቀርበው ማስረጃ(premises) true ነው ብለን ብናስብ" ማለት ማስረጃው የግዴታ ነባራዊ ሀቅ(general truth or fact) መሆን አይጠበቅበትም። የሚቀርበው ማስረጃ ነባራዊ ሀቅ ቢሆንም ፡ ባይሆንም ፡ እኛ በአምሮአችን true ነው ብለን ነው የምናስበው ወይም assume የምናደርገው። ስለዚህ

🌿 Deductive argument ላይ የቀረቡት premises (ማስረጃዎች) true ናቸው ብለን assume እናደርጋለን ፡ ማስረጃዎቹ ደግሞ ለ ድምዳሜው(conclusion) ሙሉ በ ሙሉ ዋስትና ስለሚሰጡት ፡ ድምዳሜውም true ይሆናል ማለትም false መሆን አይችልም።

🔷 Example 1

➡️ All planets do not revolve arround the sun.
➡️ Earth is a planet.
➡️ Therefore, Earth do not revolve around the sun.

🥺 ተመልከቱ ይህን ምሳሌ። ፕላኔቶች በፀሀይ ዙሪያ አይዞሩም የሚለው ማስረጃ ከ ነባራዊ ዕውነታው ጋር የሚጋጭ ነው ማለትም ውሸት ነው በትክክለኛው አለም። ነገር ግኔ እኛ በ አምሮአችን እውነት ነው ብለን ነው የምናስበው። ስለዚህ ፡

😊 "ስለዚህ ፕላኔቶች በ ፀሀይ ዙሪያ አይዞሩም እና መሬቶ ፕላኔት ናት" ብለን ያቀረብናቸው ማስረጃዎች ዕውነት ናቸው ብለን assume አደረግን ፡ ያቀረብናቸው ማስረጃዎች ደግሞ " መሬት በፀሀይ ዙሪያ አትዞርም" ብለን ድምዳሜ ለመስጠት ሙሉ ለሙሉ ዋስተና ስለሚሆኑ Deductive argument ይሆናል ማለት ነው።

🤔 እንዴት ነው ዋስትና የሚሆኑት?

ተመልከቱ😳

" ሁሉም ፕላኔቶች በ ፀሀይ ዙሪያ የማይዞሩ ከሆነ ፡ መሬት ደግሞ ፕላኔት ከሆነች ፡ ስለዚህ መሬት በፀሀይ ዙሪያ አትዞርም🤷‍♂።"

🔷 Example 2

➡️ All freshman courses are simple.
➡️ Logic is a freshman course.
➡️ As a result, Logic is simple.

👆 Deductive argument ነው። እናንተ ተንትኑት።

🔷 Example 3

"Mount Kilimanjaro is higher than mount Ras Dashen and Mount Ras Dashen is higher than Mount Entoto, we certainly conclude that Mount Kilimanjaro is higher than mount Entoto."

👆 Deductive argument ነው። እንዴት?

"Kilimanjaro ተራራ ከ Ras Dashen ተራራ ይበልጣል እና Ras Dashen ተራራ ከ Entoto ተራራ ይበልጣል" ብለን ያቀረብናቸው ማስረጃዎች true ናቸው ብለን assume አደረግን።

ስለዚህ Kilimanjaro ተራራ ከ Entoto ተራራ ይበልጣል ብለን የደመደምነው ሀሳብ ውሸት መሆን አይችልም ምክንያቱም ማስረጃዎቹ ለድምዳሜው ዋስትና ስለሚሆኑት ፡ ምክንያቱም

" ኪሊማንጃሮ ከ ራስ ዳሽን ተራራ ከበለጠ ፡ ራስ ዳሽን ደግሞ ከ እንጦጦ ተራራ ከበለጠ ፡ ስለዚህ ኪሊማንጃሮ ከ እንጦጦ ይበልጣል🤷‍♀"


🙌 እሺ አሁን ደግሞ አንድ argument Deductive መሆን እና አለመሆኑን መለያ ዘዴዎችን እንመልከት። 3 ዘዴዎች አሉ።

🎈 1) the actual strength of the inferential link between premises and conclusion.

🎈 2) the occurrence of indicator words.

🎈 3) form of argument

💁‍♂ የመጀመሪያው ዘዴ ከላይ የነገርኳችሁ ነው። ማስረጃዎቹ ድምዳሜን ሙሉ በ ሙሉ የሚደግፋት ወይም ዋስትና የሚሰጡት ከሆነ Deductive argument ነው ማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ያቀረብናቸው ማስረጃዎች ነባራዊ ሀቅ ቢሆኑም ባይሆኑም ፡ ዕውነት ናቸው ብለን assume እናደርጋለን። ማስረጃዎቹ ደግሞ ለ ድምዳሜው ሙሉ ዋስትና ስለሚሰጡት ድምዳሜ false መሆን አይችልም።


🔥2) Indicator words

አንድ Argument Deductive መሆኑን ለማወቅ ከምንጠቀምባቸው ዘዴዎች አንድ indicator words ን በ መጠቀም።

⭐️ Deductive argument ማለት ማስረጃዎቹ ለ ድምዳሜው ሙሉ ዋስትና የሚሰጡበት ሒደት ነው ብለናል። ታዲያ ማስረጃዎች ለ ድምዳሜው ዋስትና መሆናቸውን ለመግለፅ የምንጠቀማቸው ጠቋሚ ቃላት(Deductive indicator words) አሉ። ታዲያ እነዚህ ጠቋሚ ቃላት ምን ምን ናቸው🤔?

Deductive indicator words

🌱 Necessarily
🌱 Absolutely
🌱 Certainly
🌱 Definitely

ስለዚህ እነዚህን☝️ጠቋሚ ቃላት ድምዳሜው ላይ የሚጠቀም argument Deductive argument ነው።

🔷 Example 1

" Anyone who is above the age of 18 has the right to vote and Abel is above 18, therefor
e it absolutely follows that Abel has the right to vote."

🔷 Example 2

" Mekdes is the mother of Saba and the sister of Leul. Accordingly, it definitely implies that Leul the uncle of Saba.

ስለዚህ ☝️እነዚህ ሁለት ምሳሌዎች Deductive argument ናቸው። በቀላሉ የተጠቀሙትን indicator word ማየት በቂ ነው።

🔥3) form of argument

አንድ argument deductive መሆኑን ከምናውቅባቸው ዘዴዎች መካከል አንዱ form of argument ነው። form of argument ማለት ደግሞ argument ቱ የቀረበበት መንገድ ማለት። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት argument በሙሉ deductive argument ናቸው።👇👇👇👇

A) Argument based on mathematics.
B) Argument from Definition.
C) Categorical syllogism.
D) hypothetical syllogism.
E) Disjunctive syllogism.

📍እያንዳንዳቸውን እንመልከት።

A) Argument based on mathematics :

is an argument in which the conclusion depends on some purely arithmetic or geometric computation or measurements.

📌 Argument based on mathematics ማለት maths ን ወይም ደግሞ የ maths ህጎችን እንደ ማስረጃ ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት ማለት ነው።

ታዲያ እንዴት ነው argument based on mathematics deductive argument የሆነው🤔?

😎 ማትስ ወይም የማትስ ህጎች already proved and measured የሆኑ ስለሆኑ ፡ ለድምዳሜው ሙሉ በሙሉ ዋስትና መሆን ይችላሉ። ማለትም እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ማትስ ወይም የማትስ ህግ true ነው ፡ ስለዚህ የማትስ ህጉን እንደ ማስረጃ ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው ድምዳሜ false መሆን አይችልም።

ምሳሌ ፡ አንድ ነጋዴ 4 ማንጎ ና 3 አፕል😋 ዘንቢል ውስጥ አስቀመጠ። ከዛ ከዚህ ዘንቢል ውስጥ 7 ፍራፍሬዎች አሉ። ብሎ ድምዳሜ ቢሰጥ የነጋዴው argument deductive ነው። ምክንያቱም መደመር የተባለውን የማትስ ህግ ተጠቅሟል።

🍎 ስለዚህ ዘንቢሉ ውስጥ 7 ፍራፍሬ አለ ብሎ ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀመው 4 እና 3 ን መደመር ነው። ስለዚህ ዘንቢሉ ውስጥ 4 ማንጎ እና 3 አፕል መኖሩ 7 ፍራፍሬዎች አሉ ብለን ድምዳሜ ለመስጠት ዋስትና ነው። ማለትም 7 ፍራፍሬ አሉ ብሎ ነጋዴው የሰጠው ድምዳሜ false መሆን አይችልም።

🔷 Example 2

"Because triangle A is congruent with triangle B and triangle A is isosceles triangle, it follows that triangle B is isosceles triangle."

☝️ ይህም የማትስ ህጎ ነው። ስለዚህ deductive ነው። ሁለት triangle ሎች congruent ከሆኑ ምን ምን ዝምድና እንዳላቸው ማትስ ላይ ተምራችሁታል። ይህን የማትስ ህግ ተጠቅመን ነው የደመደምነው። ተንትኑት።

B) Argument from Definition :

is an argument in which the conclusion is claimed to depend merely up on the definition of some words or phrases used in the premises or conclusion.

Argument from Definition ማለት እንደ ማስረጃ ከ ተጠቀምነው ዐ.ነገር(statement) ውስጥ የሚገኘውን ቃል ፡ የዛን ቃል definition ድምዳሜ አድርጎ ማቅረብ።

🔷 Example

"Abebe is Mendacious. Therefore, Abebe tells lie."

ተመልከቱ እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው "Abebe is Mendacious" የሚለው። እንደ ማስረጃ ከተጠቀምንበት ዐነገር ውስጥ "Mendacious" የሚለው ቃል ትርጉሙ ውሸት የሚናገር ማለት ነው። ስለዚህ የዚህን ቃል ትርጉም conclusion አደረግነው። argument from Definition ማለት ይህ ነው።

ታዲያ እንዴት ነው argument from Definition Deductive የሆነው 🤔?

ተመልከቱ ፡ Premise ስሱ ላይ ያለውን ቃል definition ነው ቀጥታ ወስደን conclusion ያደረግነው። ይህ ማለት premise ስሱ ዕውነት ነው ብለን assume እናደርጋለን ፡ premise ስሱ ደግሞ ዕውነት ከሆነ የ premise ስሱን ቃል definition ቀጥታ ወስደን conclusion ስለምናደርገው conclusion ኑ false መሆን አይችልም። ማለትም Premise ስሱ ለ conclusion ኑ ዋስትና ይሆነዋል።

3) Categorical syllogism

Syllogism - is an argument that always contains exactly two premises and one conclusion.

💥 Categorical syllogism - is an argument in which each statement begins with one the words "All", "some", "no".

Categorical syllogism ማለት ሁለት premises እና አንድ conclusion ያለው argument ሲሆን ሁለቱ premises እና አንደኛው conclusion የሚጀምሩት "All", "some", "no" በተባሉት ቃላት ነው።

😉 ስለዚህ argument ቱ ሁለት premises እና አንድ conclusion ያለው ሁኖ ሁለቱ premises እና አንደኛው conclusion የሚጀምሩት በ "All", በ "some", በ "no" ከሆነ argument ቱ Deductive ነው። ፈተና ላይ ብልጥ ሁኑ🤓

🔷 Example 1

No Concise member is silly. Some people are silly. Thus, some people are not Concise members.

🔷 Example 2

All books are interesting books. Some books are fictions. Hence, some interesting books are fictions.

ስለዚህ ☝️ ሁለቱ ምሳሌዎች Categorical syllogism ናቸው። በሌላ አባባል Deductive argument ናቸው።

D) Hypothetical syllogism

is an argument having conditional sentence for one or both of its premises.

Hypothetical syllogism ማለት ሁለት premises እና አንድ conclusion ያለው argument ሲሆን ሁለቱም premises ሶች በ conditional sentence የሚገለፁ ከሆነ ወይም ደግሞ ከሁለቱ አንዱ premise በ conditional sentence የሚለፅ ከሆነ Hypothetical syllogism ይባላል።

ስለዚህ☝️ ከላይ ያለውን የሚያሟላ Deductive argument ይባላል።

🔷 Example 1

If it rains , then I will not go to school.
It rains.
Therefore, I will not go to school.
🔷 Example 2

➡️ If electricity flows through a conductor, then a magnetic field is produced.

➡️ If a magnetic field is produced, then a nearby compass will be deflected.

➡️ Therefore, if electricity Flows through a conductor, a nearby compass will be deflected.

☝️ ሁለቱ ምሳሌዎች Hypothetical syllogism ናቸው ። በሌላ አባባል Deductive argument ናቸው።


E) Disjunctive syllogism

is an argument that contains "Either.....or...." statement for one of its premises.

Disjunctive syllogism ማለት ሁለት premises እና አንድ conclusion ያለው argument ሲሆን ከሁለቱ premises መካከል አንድኛው premise በ "Either.....or...." የተዋቀረ ዐነገር ከሆነ ።

😉 ስለዚህ argument ቱ ሁለት premises እና አንድ conclusion ያለው ሁኖ ከ ሁለቱ premises አንድኛው "Either.... or...." statement ካለው argument ቱ Deductive ነው ማለት ነው።

🔷 Example 1

➡️ Either Daniel or Elias will come to the party.

➡️ Daniel do not come to the party.

➡️ Therefore, Elias will come to the party.


🔷 Example 2

➡️ Either X or Y.

➡️ Not Y.

➡️ Therefore, X.

☝️ሁለቱ ምሳሌዎቾ Disjunctive syllogism ናቸው። በሌላ አባባል Deductive argument ናቸው።

🙌👐🙌 አለቀ የዛሬው ክላስ።

ይህን ትምህርት ማንኛውም ተማሪ ሳይገባው ማለፍ የለበትም። ስለዚህ ያልገባችሁን ማንኛውንም ጥያቄ በዚህ👇👇 መጠየቅ ትችላላችሁ።

@Inquiry_receving_bot

©A+ tutorial class
ሰላም እንዴት ናችሁ🙌

ዛሬ እንደተለመደው Psychology
Course እንቀጥላለን! በተቻለኝ መጠን ግልፅ ለማድረግ ጥሬያለሁ😇

የሚገርማችሁ ያዘጋጀዉላችሁ ኮርስ ግማሹ Clear ሆኖብኝ😭 በችኮላና በንዴት ነበር እንደገና ያዘጋጀውት፣ ነገር ግን አንድም ያስቀረሁት የለም😊
ግልፅ እንደሚሆንላችሁ ተስፋ አለኝ። ኖቱ እንዳይበዛባችሁ ስላሰብኩ ግማሹን ጠዋት የቀረውን ከሰዓት እንለቃለን።

በርቱ! አንብቡ!

©A+ tutorial class
📚PERCEPTION

በዚህ Sub-Chapter Major
Charecteristics of Perception የሆኑትን👇 እናያለን

📌Selectivity of Perception
📌Form Perception
📌Depth Perception
📌Perceptual Constancies
📌Perceptual illusion

እነዚህን ዘርዘርን መንዝረን አንድ በአንድ እናያቸዋለን፣ ነገር ግን ውስብስብ ስለሚመስል አንዱን ስትይዙ ሌላው እንዳያመልጣቹ😇

1⃣Selectivity of Perception (Attention!)

Note that at any given time, our sense organ is bombarded by many stimuli.
🖇እንደምታውቁት ሁልጊዜ የስሜት ህዋሳቶቻችን ከተለያዩ ብዙ ክስተቶች ጋር ይገናኛሉ፣ ነገር ገን እኛ attention ሰጥተን Response የምንሰጠው ለጥቂቱ ብቻ ነው።

ይሄ አንዱ ላይ Focus አድርገን ሌላውን stimuli ደግሞ ignore የማድረጉ ነገር(Selective Perception), #Attention ይባላል።

What does this selectivity of perception imply?🤔

🌹Selectivity of Perception imply የሚያደርገው, የልምምዳችን ሁኔታ ከየትኛውም ነገር በላይ ሁለት ነገር ላይ ነው የተመሰረተው።
📌Focus
📌Margin

🖇Events or Stimuli that you percieve clearly are the #focus of our experience.

🖇Events or stimuli that you percieve dimly or Vaguely are #Margin of our experience.
ይሄ ምን ማለት እንደሆነ ላስረዳችሁ ለምሳሌ በDSTv ቤት ሆናችሁ የሰዎች ጫጫታ ብርድ ባለበት ስፍራ ሆናችሁ የኳስ⚽️ ጨዋታ እያያቹ አይናቹ የሚከታተለው ኳሱን የያዘው ሰውዬ ላይ ነው፥ ይሄ Focus ይባላል። ነገር ግን Still የሰዎቹ ጨጫታ፣ብርዱ ምናምን አለ፣ ነገር ገን እናንተ ለእነዚህ ነገሮች ሙሉ ትኩረት አልሰጣቹም፤ ማለትም በቃ Dimly/Vaguely ነው ትኩረት ያረጋቹት እንዲህ ሲሆን #Margin ይባላል።

ልብ በሉ👆ጫዋታው ካለቀ በኃላ ግን ቅድም ትኩረት ያልሰጣቿቸው ነገሮች አሁን ትኩረት ማድረግ ትጀምራላችሁ።(ምንድነው ብርዱ ምንድነው ጫጫታው ትላለህ😺)

So, አያቹአ ቅድም Focusአቹ የነበረው(ኳሱ) አሁን ሲያልቅ ብዙም ትኩረት ስላልሰጣቹት Marginአቹ እየሆነ መጣ። ደግሞም ቅድም #Marginአቹ የነበሩት አሁን Focusአቹ ሆነዋል። 🤚ይሄ ምንድነው ሚያሳየው Attention Constantly shifting እንደሆነ🤷‍♂

What factors do you think determine your attention?
ሰው ለምንድነው በአንድ ነገር ትኩረቱ የሚሳበው?🤨🤨

🌹Paying attention is in general a function of two factors: factors external to the perceiver and factors internal to the perceiver.

External Factors የሚባሉት
📌Size and Intensity
📌Repitition
📌Novelty(Newness)
📌Movement
🔸Size and intensity👉 Bigger and Brighter የሆኑት ነገሮች ከsmaller እና ደብዛዛ ከሆኑት ነገሮች ይልቅ ትኩረት ሳቢ ናቸው። ለዚያኮ ነው፣ Bolded የሆኑ Letters እንዲሁም ነጭ ልብስ የለበሰ ሰው ትኩረታችንን የሚያገኘው።

🔸Repitition👉repeatedly or frequently የሚደረገው ድርጊት አንዳንዴ ትኩረታችንን ይስባል። ለዚያ ነው መፈክሮች(Slogans)፤ Advertisements የሚደጋገሙት።
❗️ነገር ግን አንዳንዴ ነገሩ ምንም ያክል ትልቅ ቢሆን ነጭ ቢሆን ቢደጋገም ትኩረት ላንሰጥ እንችላለን😒 ምናልባት ይሄ የሚሆነው ነገሩን Adapt ስላደረግነው ይሆናል፣ This is Called Sensory Adaptation[Habituation]. ባለፈው አይተናታል እቺን😎

🔸Novelty(Newness)👉ይሄ ማለት አንድ ነገር በEnvironmentኡ ውስጥ ካሉት ነገሮች ጋር Contrast ሲያደርግ ትኩረታችንን ያገኛል። ለዚያ ነው ቤት ውስጥ ካሉት ሰዎች ይልቅ ህፃን(First born) attentionአችንን የሚያገኘው😘

🔸Movement👉እንደምታውቁት Moving objects ከNon-moving/stagnant objects በላይ ቶሎ ትኩረት ይስባሉ። ለዚያ ነው ቢራቢሮ🦋 ወዲህ ወዲያ ስትል የምንመሰጥባት😁

Internal Factors የሚባሉት
📌Set or Expectency
📌Motive or needs

🔸Set refers to the idea that you may be "ready" and "primed for" certain kinds of sensory input.
ህፃን ልጅ ያላት እናት👩‍🦱 ሁሌ የምትጠባበቀው "ልጄ አለቀሰ ወይስ አላለቀሰም" የሚለው ከሆነ..የሚያለቅስ የህፃን ድምፅ በሰማች ቁጥር ልጄ ነው ወይ ትላለች😍😍 Because እየተጠባበቀችው ስለሆነ እንግዲህ ይሄ ነው "Set" ሚባለው።

🔸Motive(Needs):- ሰው ትኩረት የሚያደርገው ውስጥ ባለው ፍላጎትMotive ላይ ተመስርቶ ነው። ለምሳሌ የራበው ሰው Focus የሚያረገው Food ላይ ነው፣ አሁን እናንተ የመማር ፍላጎት በውስጣቹ ስላለ ነው፣ ለዚህ tutorial ትኩረት የሰጣቹት።

2⃣Form Perception

🌷The meaningful shapes or patterns or ideas that are made perhaps out of meaningless and discrete or pieces and bites of sensations refer to form perception.

🖇ይሄ meaningless ከሆኑ ነገሮች ማለትም ከምናያቸው፣ ከምንሰማቸው..ነገሮች ትርጉም ያለው ነገር መመስረት ነው Form perception የሚባለው።
ለዚህ ደግሞ Objectኡን[figure] ከSurroundingኡ[Ground] መለየት ያስፈልገናል።

Figure-Ground Perception
በግድግዳ ላይ የተሳለ ስዕል ብንወስድ፦ ስዕሉን እንደ figure ግድግዳውን ደግሞ እንደ ground ነው የምንወስደው ሌላ ደግሞ በመሬት ላይ የፃፈ ፁፍ እዚጋ ደግሞ መሬቱ እንደ Ground ሲሆን ፁፉ ደግሞ እንደ figure ነው🤷‍♂

የሆነው ሆኖ How Can we separate the figure from the general Ground and Form Perception?
ለዚህ 2 ዘዴዎች አሉ😊
📌Contours
📌Organization

Contours in Form Perception

🔰Contours are formed whenever a marked difference occurs in the brightness or color of the background. Figureን ከground ለይታችሁ የምታውቁት Contourኡን ስታውቁ ነው!
ለምሳሌ በጥቁር እስክሪብቶ🖊 Blackboard ላይ ብትፅፉ፣ ጥቁሩን ፁፉ ከblackboardኡ የለያችሁ ጊዜ Contourኡን ታገኛላችሁ። ከዚያ በኃላ ፁፉ Figure, blackboardኡ ደግሞ ground እንደሆነ ማወቅ አይከብዳችሁም👍
ሌላ ምሳሌ፣ ጥቁር ሰው ጥቁር ልብስ ለብሶ አስቡት🙈🙉 ሰውዬውን ከልብሱ የለያችሁ ጊዜ Contourኡን ታገኛ
1. 4 📚Set Theory

🔖እዚህ ስር ሶስት ነገሮች በዋናነት ታጠናላችሁ፦
📌Concept of set
📌Description of set
📌Operation of sets
1⃣Concept of set ማለት ያው የSet definition እንደማለት ነው። by the way "set"ን ከአምስትኛ ክፍል ጀምረን ነዋ የተማርነው🤨። ስለዚህ የሚከብድ ነገር የለሁም። Handout page 26 ላይ ታገኛላችሁ!

2⃣Description of Sets
ይሄ ማለት ደግሞ Set Describe የሚደረግበት (የሚገለጽበት) መንገድ ነው።
There are four different ways for this!
1. Verbal method
2. Roster Method
3. Partial listing method
4. Set builder method
📔ግልፅ በሆነ መንገድ ሞጁሉ ላይ
ተብራርቷል፣ ደግሞ ከPage 28-31 ያሉትን 11 የExercise አትለፏቸው! ሞክሯቸው!

3⃣Set Operation and Venn Diagrams
📔Set Operation is just the process of forming new set, it may be taking:
common elements
[intersection የሚባለው],
Non-Common elements
[Relative Complement የሚባለው]
Putting all together
[Union የሚባለው]

እና በእነዚህ ሶስት መንገዶች ተጠቅመን አዲስ Set ስንፈጥር ነው Set operation የሚባለው።

Theorem 1.1 and 1.2 ላይ ያሉትን Properties እዩዋቸው።

Elementary ትምህርት የሆነው Venn diagram እዚህ ላይም አለ😁...የሚገርማችሁ Math ላይ በጣም ቀላል የሆኑ ትምህርቶችን ሳይ እናደዳለሁ😁

ከPage 36-38 ላይ ያሉትን 13 ጥያቄዎች ምክሯቸው!

በሚቀጥለው Chapter 2
The real and Complex number system እናያለን😊

ጥያቄ ካላችሁ @Ucan_scorebot ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ🙏

©A+ tutorial class
😊 ሰላም ቤተሰቦቻችን እንዴት ናችሁ ግቢ ለመግባት ዝግጅት እንዴት ነው አይዟችሁ በርቱ።

😊 ዛሬ የ logic and Critical thinking ትምህርት ይኖረናል። ከጥቂት ሰአታት በሗላ ኖት ይለቀቃል። ዛሬ የምንማረው ትምህርት ሁሉም ግቢዎች ላይ ፈተና ይወጣበታል። ስለዚህ በአግባቡ ተረዱት።

😊 እሁድ ወይም ሰኞ የ logic ትምህርት chapter 1 & 2 ከ 30% ፈተና ይኖራችሗል። 93% ቱ ከ chapter 2 እና 7% ቱ chapter 1 ነው።

😊 እንደተለመደው ከ 1 እስከ 5 የወጡ የካርድ ሽልማት አለው። ፈተናውን የሚደፍን ተማሪ ደግሞ ለየት ያለ ሽልማት ተዘጋጅቶለታል። አንብቡ ተዘጋጁ😎

ሎጂክን በተመለከተ ጥያቄ ወይም አስተያየት ካላችሁ👇

@Inquiry_receving_bot
📚 Chapter Two.

📖 Basic Concepts of Logic.

📕 Evaluating Arguments.

📗 Validity and Soundness

📚 Types of Deductive Argument.

😎 በባለፈው ትምህርታችን deductive argument ምን እንደሆነ አይተናል።

🤓 ዛሬ ደግሞ የ deductive argument አይነቶችን እናያለን።

🌹 There are two types of deductive argument.

📍1) Valid deductive argument or valid argument.

📍2) Invalid deductive argument or invalid argument.

😁 እስቲ ሁለቱንም ለየቅል እንመልከት።

📍Valid Argument

🌀 Valid Argument - is a type of deductive argument such that the premises are assumed true, it is impossible for the conclusion to be false.

🌀 Valid Argument - the conclusion follows with strict necessity from the premises.

😊 እስቲ ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት እንሞክር።

😎 ማስረጃዎቹ(Premises) እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የማይችል ከሆነ ወይም በሌላ አባባል conclusion ኑ 100% እውነት ከሆነ argument ቱ valid argument ይባላል።

🥺 ታዲያ እዚጋ ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው ማለት፡

👉 ማስረጃዎቹ በነባራዊው አለም እውነትም ውሸትም ሊሆኑ ይችላሉ። እሱን እኛ አያገባንም። በነባራዊው አለም እውነትም ይሁኑ ውሸትም ይሁኑ ፡ እኛ ግን በ አምሮኣችን እውነት ናቸው ብለን እናስባለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ሆኑ🤗

👉 ታዲያ ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የማይችል ከሆነ valid deductive argument ይባላል። ምሳሌዎችን እንመልከት፡

🔷Example 1

All football players are Americans.
Tedy Afro is a football player.
Thus, Tedy afro is an American.

🥺 ተመልከቱ ይህን ምሳሌ።

All football players are Americans እና Tedy Afro is a football player የሚሉት premises ናቸው።

🤔 በነባራዊው አለም ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው እንዴ አይደለም።

🤔 በነባራዊው አለም ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ናቸው እንዴ አይደሉም።

😁 አያችሁ አይደል ሁለቱም ማስረጃዎች በነባራዊው አለም ውሸት ናቸው። እኛ ግን አያገባንም🙅‍♀🙅‍♂። እውነት ናቸው ብለን ነው assume የምናደርገው። ስለዚህ እውነት ናቸው🤗

👉 ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ከሆኑ
👉 ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ከሆነ
👉 ስለዚህ ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው።

😊 ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው የሚለው conclusion ፈፅሞ ውሸት መሆን አይችልም። ምክንያቱም ቴዲ አፍሮ በሁሉም ኳስ ተጫዋቾች ውስጥ ነው ያለው። ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች ደግሞ አሜሪካዊ ናቸው። ስለዚህ ቴዲ አሜሪካዊ ነው።

😋 So, the argument is valid deductive argument.

አሁን ደግሞ invalid argument ን እንመልከት።

📍Invalid argument

Invalid argument - is a type of deductive argument such that the premises are assumed true, it is possible for the conclusion to be false though it is claimed to.

📍Invalid argument - the conclusion does not follow with a strict necessity from the premises.

😎 እስቲ እናብራራው።

ማስረጃዎቹ(premises) እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የሚችል ከሆነ argument ቱ Invalid deductive argument ይባላል።

🥺 ታዲያ እዚጋ ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው ማለት፡

👉 ማስረጃዎቹ በነባራዊው አለም እውነትም ይሁኑ ውሸትም ይሁኑ ፡ እኛ በአምሮኣችን እውነት ነው ብለን assume እናደርጋለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው🤗

👉 ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው conclusion ኑ ውሸት መሆን የሚችል ከሆነ invalid argument ይባላል። ምሳሌ እንመልከት😎

🔷Example 2

All football players are Americans.
Tedy Afro is an American.
Therefore, Tedy Afro is football player.

🥺 ተመልከቱ ይህን ምሳሌ፡

All football players are Americans እና Tedy Afro is an American የሚሉት premises ናቸው።

😟 ከላይ የቀረቡት ሁለቱም premises በነባራዊው አለም ውሸት ናቸው። እኛ አያገባንም ፡ እውነት ናቸው ብለን assume እናደርጋለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው🤗። ከዛ ፡ ተመልከቱ😊

👉ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ናቸው።
👉 ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው።
👉ስለዚህ ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው።

ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው የሚለው conclusion ውሸት መሆን ይችላል። እንዴት

እዚጋ በደምብ ተከታተሉኝ ውዶቼ

ለምሳሌ በአለም ላይ 1000 ሺህ ኳስ ተጫዋቾች ቢኖሩ እና በአለም ላይ 5000 አሜሪካውያን ቢኖሩ። እንዲሁም ቴዲ አፍሮ አሜሪካዊ ነው።

ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች ማለትም 1000 ሺዎቹም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካዊ ከሆኑ ፡ ይህ ማለት ከ 5000 አሜሪካውያኖች 1000 የሚሆኑት ኳስ ተጫዋች ናቸው። 4000 የሚሆኑት አሜሪካውያን ኳስ ተጫዋቾ አይደሉም ማለት ነው። ስለዚህ ቴዲ አፍሮ ከ 4000 አሜሪካውያኖች መካከል ሊሆን ይችላል። ማለትም ኳስ ተጫዋች ላይሆን ይችላል። ስለዚህ ቴዲ አፍሮ ኳስ ተጫዋች ነው የሚለው ውሸት መሆን ይችላል።

ከዚህ ምን እንረዳለን

ሁሉም ኳስ ተጫዋቾች አሜሪካውያን ናቸው ማለት ሁሉም አሜሪካውያን ኳስ ተጫዋቾች ናቸው ማለት አይደለም።

ገባችሁ ኣ በጣም simple ነው😂

ተወዳጆች ሆይ ከ Example 1 Example 2 ምን ተረዳችሁ? የሆነ formula ማግኘት ትችላላችሁ። እስቲ ሞክሩት። አስፈላጊ ከሆነ ቡሗላ ላይ እነግራችሗለሁ።

ስለዚህ deductive argumentvalid እና invalid ብሎ መፈረጅ ወይም መክፈል validity ተብሎ ይጠራል።

ስለዚህ ከምሳሌዎቹ መረዳት እንደቻልነው Validity(valid or invalid) ማለት premises እና conclusion በ ነባራዊው አለም እውነት መሆናቸውን ወይም ውሸት መሆናቸውን የሚገመግም ሳይሆን premises እና conclusion ያላቸውን የምክንያታዊነት ዝምድና ፡ መደጋገፍ የሚገመግም ነው። ስለዚህ

Validity is not determined by the actual truth and falsity of the premises and the conclusion.

👆 ያዙት True/false ላይ ብዙ ጊዜ ይወጣል።

ማንበቡ እንዳይሰለቻችሁ ቀጣዩን ኖት ከሰአት እለቅሏችሗለሁ።

©A+ tutorial class.
1
📚 ግቢ ላይ የት የት ቦታዎች ማንበብ እንችላለን

በ Concise English(@Aconcise) ቻናል ተዘጋጅቶ የቀረበ።

📍በ ሁሉም የግቢ ተማሪዎች ሊባል በሚቻመልኩ በግንባር ቀደምነት ተመራጭ የሆኑ የመቸከያ ቦታዎች መካከል፡

📖 1ኛ) ላይብረሪ
📖 2ኛ) ስፔስ
📖 3ኛ) ዶርም

📚 ላይብረሪ

👩‍🏫👨‍🏫 12 አመታትን በትምህርት ላሳለፈ ተማሪ ስለ ላይብረሪ መናገር ልጅ ለ እናቷ ምጥ እንደ ማስተማር ነው😁። ነገር ግን ግቢ ላይ ስላለው የ ላይብረሪ የአሰራር ስርአት አንዳንድ ነገር ማወቁ አይከፋም😊

📖 ላይብረሪ አያሌ በሆኑ የግቢ ተማሪዎች ተወዳጅ የሆነ የመቸከያ ፡ የመሰገጫ ፡ የመፍለጫ ቦታ ነው።

👨‍🏫 ታዲያ ላይብረሪ ሔደን ለመገልገል ልንተገብራቸው የሚገቡ ደንቦች ና መመሪያዎች አሉ። በ ሁሉም ግቢ ተፈፃሚነት ያላቸውን ደንቦች ና መመሪያዎች ጠቅለል ባለ መልኩ እንመልከት።

📍 የ ግቢ መታወቂያ ካር ወይም ID Card መያዝ ግዴታ እና ግዴታችሁ ነው ላይብረሪ ስትሔዱ። 😎 ሰሞኑን ግቢ ልትገቡም አይደል ፡ እንደገባችሁ ከ 2 እና ከ 3 ቀን ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የ ግቢ መታወቂያ ካርድ ይሰጣችሗል። ስለዚህ መታወቂያ ካርድ መያዝ ግዴታ ነው ላይብረሪ ስትሔዱ።

📍 ጠሽ ጠሽ የሚል ሸበጥ ጫማ መልበስ ፈፅሞ የተከለከለ ነው። ቋ ቋ ቋ የሚል Hill ጫማ መልበስ የተከለከ ነው👠። እንዲሁም ውስጥ ላይ ማስቲካ ማነክ አይቻልም።

📍 Ear phone በፍፁም የተከለከለ ነው☹️። አደራችሁን የምላችሁ ነገር Ear phone አድርጋችሁ ወደ ላይብረሪ እንዳትሔዱ ፡ ላይብረሪ ውስጥም እያነበባችሁ ear phone በፍፁም እንዳትጠቀሙ። ቅጣቱ አይጣል ነው😩። ገጠመኝ ስላለኝ በዚህ ጉዳይ።

📍 አሁን ዘመኑ የ ኮሮና ም አይደል Mask መልበስ ግዴታችሁ ነው።

👆 እንግዲህ ከሞላ ጎደል መሰረታዊ የሚባሉት መመሪያዎች ናቸው።

👨‍🎨👩‍🎨 ታዲያ የ ላይብረሪው መግቢያው በር ላይ የ ላይብረሪ ዘበኞቾ፡ ተቆጣጣሪዎች አሉ። ልክ ከ ላይብረሪው መግቢያ በር ስትደርሱ Id card አውጥታችሁ ለ ተቆጣጣሪዎቹ ማሳየት ይኖርባችሗል። መመሪያዎቹን ካላሟላችሁ ይመልሷችሗል። ምንም ርህራሔ የለም😟

😎 ደንብና መመሪያውን ካማላችሁ ግን Sanitizer 🤲 አድርገውላችሁ በክብር ወደ ውስጥ እንድትገቡ ይፈቅዱላችሗል።

🔐 Ok አሁን ተቆጣጣሪዎችን አልፈን ወደ ላይብረሪው ውስጠኛው ክፍል እና ግብዳ ግብዳ መፅሀፍ በ ስርአት ወደ ተደረደሩበት ቦታ እያመራን ነው። እስቲ ተከተሉኝ፡

📚 እሺ እንግዲህ ላይብረሪው ውስጥ ከገባን በሗላ የምንፈልገውን መፅሀፍ እንዴት ነው ማግኘት የምንችለው🤔

🤗 በሁለት አይነት መንገድ ማግኘት እንችላለን።

🎈1ኛው) Open book ነው።
🎈2ኛው) በ ላይብረሪስቶች አማካኝነት።

📚Open book

Open book የሚባለው ምን መሰላችሁ😊

📖 የ እያንዳንዱ ኮርስ ወይም subject መፅሀፍቶች ስርአት ባለው መልኩ ተደርድረው ፡ ከመድረደሪያው ላይ የኮርሶቹ ወይም የ ሰብጀክቶቹ ስም በ ማርከር ተፅፎ ተለጥፏል።

📖 ስለዚህ እናንተ ከተደሩት መፅሀፍ መካከል የምትፈልጉትን መፅሀፍ መርጣችሁ ታወጣላችሁ። ከዛስ🤔

ከዛ ያወጣችሁትን መፅሀፍ ይዛችሁ ቀጥታ ወደ ላይብረሪስቶች ወይም አስነባቢዎች ትሔዳላችሁ። ከዛ ID card ኣችሁን ለ ላይብረሪስቶች ትሰጣላችሁ። ID card ከሰጣችሁ በሗላስ🤔

ከዛ መፅሀፋችሁን ይዛችሁ ብትፈልጉ ground ላይ ሁናችሁ ብትፈልጉ ፎቅ ላይ ሁናችሁ ፡ ብትፈልጉ tension box ውስጥ ሁናችሁ ብትፈልጉ ከ tension box ውጭ ሁናችሁ ፡ አሪፍ እና ምቹ ወንበሮች አሉ ከዛ ቁጭ ብላችሁ መሰገጥ መቸከል ነው። ከዛ አንብባችሁ ከጨረሳችሁ በሗላ መፅሀፋን ካነሳችሁበት ቦታ ትሔዱና በስርአት መልሳችሁ ታስቀምጣላችሁ። ከዛ ከላይብረሪስቶች ሒዳችሁ ID card ኣችሁን ትቀቡሉ እና ትወጣላችሁ ማለት ነው። ከዛ ፈተናውን ድፍን😋። መድፈን ይቻላል ውዶቼ።

📚ላይብረሪስቶች

ሁለተኛው መፅሀፍ የምናገኝበት ዘዴ በ አስነባቢዎች ወይም በ ላይብረሪስቶች አማካኝነት ነው።

እንዴት መሰላችሁ ውዶቼ🤔

📖 ላይብረሪ እንደገባን ቀጥታ ወደ አስነባቢዎቹ እንሔድና የምትፈልጉትን የመፅሀፍ ስም ትገሩታላችሁ/ትነግሯታላችሁ፡ ከዛ እኑሱም መፅሀፉን አምጥተው ይሰጧችሗል። መፅሁፉን ስትቀበሉ ID card ኣችሁን ለአስነባቢዎቹ ትሰጣላችሁ። ከዛ መፅሀፋችሁን ይዛችሁ አሪፍ እና ምቹ ወንበሮች አሉ ከዛ ቁጭ ብላችሁ መቸከል ነው። አንብባችሁ እንደጨረሳችሁ ፡ መፅሀፋን ለላይብረሪስቶች አስረክባችሁ ID card ኣችሁን ተቀብላችሁ ትወጣላችሁ ማለት ነው።

📚 እንግዲህ አንዳንድ ላይብረሪዎች ላይ የምትፈልጉትን መፅሀፍ የምታገኙት በ open book አማካኝነት ነው። አንዳንድ ላይብረሪዎች ላይ ደግሞ የምትፈልጉትን መፅሀፍ የምታገኙት በላይብረሪስቶች አማካኝነት ነው። ስለዚህ እንደ ላይብረሪው የአሰራር ስርአት መገልገል ትችላላችሁ።

📚 ታዲያ ላይብረሪ ውስጥ ስናበብ ፡ ሰላማዊ ሌሎች ተማሪዎችን ሊረብሽ በማይችል መልኩ መሆን አለበት። ከ ተቁነጠነጣችሁ ፡ ማን አለብኝ ብላችሁ ዘራፍ የምትሉ ከሆነ ተቆጣጣሪዎች ስላሉ ጓ ይሉባችሗል።

📚 ግቢ ላይ ላይብረሪዎች 24 ሰአት ሊባል በሚቻል መልኩ ክፍት ናቸው። ከ ጧቱ 12:00 ሰአት እስከ ጧቱ 2:00 ሰአት ብቻ ነው የማይሰሩት። ስለዚህ በፈለጋችሁበት ሰአት ሒዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

📚 እዚጋ ግን ለ ሴቶች እህቶቻችን የምነግራችሁ ነገር ቢኖር ፡ ሌሊት ላይ ላይብረሪ ሔደሽ ማንበብ የምትፈልጊ ከሆነ በፍፁም ብቻሽን እንዳትሔጂ። 3 ወይ 4 ሁናችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ነው መሔድ ያለባችሁ። መደፈር የሚባል ነገር አለ😓። ገጠመኞችን ስለማውቅ ነው። አንዱን ገጠመኝ በትንሹ ልንገራችሁ።

👩‍🏫 ልጅቷ ሰቃይ ተማሪ ናት ። Cumulative 3.96 ነው ያላት። እና ልጅቷ ቀን ቀን ማንበብ አትወድም። ከ ሌሊቱ 5 ሰአት በሗላ ነው የማንበብ ልምድ ያላት። እና እንደተለመደው ሀገር ሰላም ነው ብላ ሌሊት 5 ሰአት አካባቢ ላይብረሪ ሔደች። ከዛ እሷም ማንበቧን ተያያዘችው።

ከሌሊቱ 10 ሰአት አካባቢ ግን
ያልጠበቀችው ዱብ ዕዳ ሰይፍ በነፍሷ ሊያልፍ ሆነ።

📚 በርካታ ተማሪዎች ላይብረሪውን ጥለው ወጥተዋል። ላይብረሪስቶች ወይም አስነባቢዎቹ የሰውነት ባህሪ አሸንፏቸው ለ እንቅልፍ እጃቸውን ሰጥተዋል። አስነባቢዎቹ ደማሚት ቢፈነዳ እንኳን መስማት በማይችሉበት ሁኔታ ለ ሞት በተቃረበ በሚመስል እንቅልፍ ተጠምደዋል።

📚 ወዲህ ደግሞ፡ ስሜቱ ያሸነፈው ፡ በፍትዎት ልቡ የታወረ የዚቺን ሰቃይ ተማሪ ተስፋ ና ልፋት ገደል ለመክተት ፡ ወደዚች ሰቃይ ተማሪ ያመራል።

😁 ልባችሁን አንጠለጠልኩት መሰል። ብቻ ልጅቷ በ ተአምር ከ መደፈር አደጋ ተረፈች🙏። አሁን ልጅቷ GC ናት የማዕረግም ተመራቂ ናት👩‍🎓

📚 ተወዳጆች ሴቶች ሆይ እና ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ፡ ምሽት ላይ ላይብረሪ ስትሔዱ ብቻችሁን አትሒዱ ፡ በቃ በጨለማ ራሳችሁን በሚያጋልጥ መልኩ አትንቀሳቀሱ ምክንያቱም ብዙ አይነት ባህሪ ያለው ሰው ግቢ የሚገባው።

😊 ለዛሬ ይብቃን። በቀጣይ ደግሞ ስለ space እና dorm ሹክ እንባባላለን።

📌 Join and share 👇👇

@Aconcise
@Aconcise
#inbox_የተላከልን

በጣም አሪፍ ጥያቄ ነው። በጣም አሪፍ ነው የማመሰግነው። 🤔ግን እናንተ ይህ ጥያቄ በአምሮኣችሁ አልተመላለሰም?

Hello teacher I have one question 🙋 previously you defined deductive argument as "DA is an argument in which the premises are claimed to support the conclusion in such a way that it is impossible for the ቀpremises to be true and the conclusion false " እና ዛሬ ደግሞ invalid deductive argument define ስታረግ "invalid argument is a type of deductive argument in which if the premises are assumed true it is possible for the conclusion to be false"🙄🙄 thoug`h`` i`t is claimed (እዚጋ underline ከሆነው መሰለኝ ምስጢሩ ) ጥያቄየ ምንድን ነው invalid deductive argument ወስጥ ከተካተተ እንዴት ነው ሁለቱ ሀሳቦች ሚስማሙት አይቃረኑም ??
#እና_ደግሞ if premises are assumed to be true it is possible for the conclusion to be false (invalid ) በዚ definition መሠረት invalid deductive argument ከ inductive argument በምን ነው ምለየው አባክህን መምህር እዚጋ በደንብ ያስረዱኝ 😁 10Q ስላነበብከው
Observational ነው Learning ነው፣ ማለት የኔ ሞዴል ነው ከምንለው ሰው የምንማረው የLearning አይነት ነው።

🖱Because of its reliance on observation of others, a social phenomenon; the perspective taken by Bandura is often referred to as a social cognitive approach to learning.

Bandura identifies three forms of reinforcement that can encourage observational learning.

Direct Reinforcement
Vicarious Reinforcement
Self Reinforcement

Bandura mentions four conditions that are necessary before an individual can successfully model the behavior of someone else.

1. Attention: the person must first pay attention to the model. መጀመርያ ያ ሞዴል ለሚሆነን ሰው ትኩረት መስጠት አለብን።

2. Retention: the observer must be able to remember the behavior that has been observed. ከዚያ ያ ሞዴላችን ላይ ያየነውን/ያስተዋልነውን ባህሪ ማስታወስ መቻል አለብን።

3. Motor reproduction: is the ability to replicate the behavior that the model has just demonstrated. ከዚያ ደግሞ በሞዴላችን ላይ ያየነውን ባህሪ ደግመን ደጋግመን መለማመድ መቻል አለብን።

4. Motivation: This means that learners must #want to demonstrate what they have learned. ይሄ ደግሞ የውስጥ ተነሳሽነት ሊኖረን እንደሚገባ የሚገልፅ ነው።

Educational Implications of Social Learning Theory

🌱Students often learn a great deal simply by observing other people.
🌱Teachers should expose students to a variety of other models.
🌱Modeling provides an alternative to shaping for teaching new behaviors.
እና የመሳሰሉት ናቸው፣ ያው ግልፅ ስለሆኑ ነው በአማርኛ ያልተረጎምኩት😊

Cognitive Learning Theory

It is about understanding how the human mind works while learning.
ስለዚህ ይሄ ካለፉት ሁለቱ (Classical and Operant) ለየት የሚያረገው በአይምሮ አጠቃቀም🧠 ላይ ትኩረት ማድረጉ ነው።

Cognitive learning may take two forms:

🔖Latent learning
🔖Insight learning (gestalt learning or perceptual learning

1. Latent Learning
እንደምታውቁት "Latent" ማለት በራሱ "ድብቅ" ማለት ነው።
ስለዚህ Latent Learning ማለት የምናውቀው ነገር ሆኖ ነገር ግን ምቹ ሁኔታ አግኝቶ እስኪገለጥ ድረስ የተደበቀ ማለት ነው።
ለምሳሌ አንተ ቤተሰቦችህ ወጥ ሲሰሩ እያየህ ከሆነ ያደከው፣ ወደፊት ላጤ👨‍💼 ስትሆን ሳትወድ በግድህ ወጥ ትሰራለህ😁 ይህ ማለት ቀድሞ ባንተ ውስጥ ተደብቆ የነበረው ወጥ የመስራት እውቀት አሁን ተገለጠ፥ ስለዚህ Latent learning ለዚህ ለዚህ ይጠቅማል።

latent learning is learning that occurs but is not evident in behavior until later, when conditions for its appearance are favorable

2. Insight Learning

It is a cognitive process where by we reorganize our perception of a problem.
It doesn't depend on conditioning of particular behaviors for its occurrence.

ይህ ማለት ደግሞ ሞካክረን ያቃተን ነገር ግን በድንገት በአንድ ጊዜ መፍትሄውን ስናገኝ ነው።
ለምሳሌ ቀን ላይ አጥንተህ አጥንተህ🥵 ያልገባህ ነገር ለሊት ተነስተህ ስታጠናው በአንዴው ከገባህ፦ "aha😃 እንዲህ ነው እንዴ ምናምን ብለህ...ይህ Insight learning ይባላል።

Human beings who solve a problem insightfully usually experience a good feeling called an 'aha' experience.

የዛሬውን በዚህ አበቃን!
ሰላም ሁኑ! ደግሞም አንብቡ!

All Rights Reserved!
©A+ Tutorial Class
1
curs after some average number of responses but the number varies from reinforcement to reinforcement.
ይሄ ደግሞ እንደየResponsኡ የሚያበረታታው ነገር (reinforcer) የተለያየ ሲሆን ነው። ለምሳሌ ልብሱን👕 ባመረቱ ቁጥረ ዛሬ 2dollar ከሰጧቸው ሌላ ቀን ደግሞ የሚጨምር ወይም የሚቀንስ ወጋ መክፈል፣ አንደዚህ ሲሆን አሁን አሪፍ ነው።

3⃣Fixed- Interval Schedule- occurs only if a fixed amount of time has passed since the previous reinforcer.
ለምሳሌ የመንግስት ሰራተኞች ለሚሰሩት ስራ ደሞዝ (reinforcer) የሚከፈላቸው በየወሩ በቀን 25 ከሆነ ይሄ Fixed interval ነው።

4⃣Variable- Interval Schedule- occurs only if a variable amount of time has passed since the previous reinforcer.
ይሄም ደግሞ ለምሳሌ ደሞዝ ዛሬ ተከፍሏቸው ከዚያ የዛሬ ሶስት ሳምንት ከተከፈላቸው፣ ከዚያ ደግሞ በሁለት ሳምንት ምናምን እያለ በተለያለ ሰዓት ከተከፈላቸው ነው።

❗️የአራቱን ልዩነት አያቹ አ
የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ የreinforcer ልዩነት ላይ ነው የተመሠረቱት
የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ደግሞ የሰዓት ልዩነተ ላይ ነው

🔖Punishment
Is a stimulus that weakens the response or makes it less likely to occur again.
ቅጣት አንድ መጥፎ ነገር ደግመን እንዳናደርግ የሚያደርገን ነገር ነው።

Like reinforcers, punishers can also be primary or secondary.

➨Primary punishers: such as pain, extreme heat, cold and the like are inherently punishing.

➨Secondary punishers: such as Criticism, demerits, bad grades,...

Both primary and secondary punishers can be positive or negative.

Positive punishment ማለትም አንድ ሰው መጥፎ ባህሪ ካለው ያንን ባህሪውን እንዲያቆም መልሰን መጥፎና ያልተገባ ነገር ስናደርግበት ነው።

➨Negative punishment
ማለትም ያ ሰው ያንን መጥፎ ባህሪውን እንዲተው የሚወደውን ነገር ስንቀማው ነው።

The pros and cons of Punishment

ያው የReinforcement እና
Punishment ልዩነት ገብቷቿላ።
በአጭሩ Reinforcement የሚፈለግን ባህሪ ለማምጣት ሲሆን Punishment ማለት ደግሞ የማይፈለግን ባህሪ ለማጥፋት ነው።

Advantage And DisAdvantage of Punishment

📝Immediacy: When punishment follows immediately after the behavior to be punished.
ልክ የማይፈለገው ባህሪ እንደተከሰተ መቅጣት ማለት ነው፣ ለምሳሌ አባት ልጁ እንደሰረቀ ካወቀ ቶሎ ሲቀጣው ማለት ነው።

📝Consistency: When punishment is inconsistent the behavior being punished is intermittently reinforced and therefore becomes resistant to extinction.
ይሄ ደግሞ ቅጣቱ ቀጣይነት ያለው ካልሆነ እንደ ሽልማት ሊቆጠር ይችላል። ማለትም ሌባ ሰርቆ ካልጠቀጣ ወይም አንዴ ተቀጥቶ ሌላ ጊዜ ሚተው ከሆነ እንደ ጥሩ ቆጥሮት ሌብነቱን ሊቀጥል ይችላል። ስለዚህ Punishment ቀጣይነት ያለው (consistent) መሆን አለበት።

📝Intensity: In general terms severe punishments are more effective than mild ones.
አንዳንድ ጊዜ ቀለል ካሉ ቅጣቶች ይልቅ ከበድ የሚሉ የተሻሉ ናቸው፣ እንደየ ሁኔታው።

ጥቂት የPunishment disadvantage ደግሞ እንይ እስኪ👇👇👇

📍Most behavior is hard to punish immediately.
📍People often administer punishment inappropriately or mindlessly.
📍The effectiveness of punishment is often temporary, depending heavily on the presence of the punishing person or circumstances
📍The recipient of punishment often responds with anxiety, fear..

Shaping

🌷Shaping is an operant conditioning procedure in which successive approximations of a desired response are reinforced.
Shaping ማለት ደግሞ ያን የሚፈለገውን ባህሪ ለማምጣት በዚያ ሰው ላይ ለውጥ እየታየ በመጣ ቁጥር እያበረታቱ መምጣት ነው። ሌባው ሌብነቱ እየተወ በመጣ ቁጥር በርታ፣ ጎበዝ እያልን reinforce የምናደርግበት Process ነው Shaping የሚባለው።

🌱The responses that you reinforce on the way to the final one are called successive approximations.

Application of the theory of operant conditioning

1. Conditioning study behavior
እዚህ ስር አሁን ለምሳሌ፣ ቅድም ያየናቸው የreinforcement schedules Apply ሊደረግ ይችላል ማለትም ለምሳሌ አስተማሪው Variable-interval እየተጠቀመ ፈተና ቢፈትን፣ ተማሪዎቹ በጥናታቸው ሁሌ ዝግጁ ይሆናሉ።

2. Conditioning group behavior
እዚህጋ ደግሞ ለምሳሌ ተማሪ አስተማሪውን ቢሰድብ ለአስተማሪው ጥሩ ስሜት አይሰጠውም! ግን ክላስ ውስጥ ሲሳተፍ ምናምን አስተማሪው ደስ ይሏል። (ማለትም Reinforced ይሆናል) ስለዚህ Operant conditioning ለዚህ ለዚህ ጠቃሚ ነው።

3. Managing Problem Behavior
Operant conditioning is a behavior therapy technique that shape students behavior. To do this, teachers should admit positive contingencies like praise, encouragement etc. for learning.

እና Operant Conditioning እነዚህን ጨምሮ ሌሎች ነገሮች👇 ላይም Apply ሊደረግ ይችላል [ማለትም ለብዙ ነገር ጥቅም ይኖረዋል]

4. Conditioning and Cognitive Processes
5. Shaping Complex Behavior
6. Conditioning and classroom behavior

Social Learning Theory (observational learning) theory

🖱According to Bandura, a major part of human learning consists of observational learning, which is learning by watching the behavior of another person, or the model.

ይሄ Theory ከስሙ እንደምትረዱት፣ አብዛኛው ሰው ለመማር የሚጠቀምበት የመማር አይነት
Operant Conditioning Theory

The term "operant" emphasizes this point:
The organism operates on its environment to produce a desirable result.
ወይም በአጭሩ "Operant" ማለት "Response" /ምላሽ ነው ማለት እንችላለን።

🌷Operant conditioning is learning in which a voluntary response is strengthened or weakened, depending on its favorable or unfavorable consequences.
መጀመሪያ ላይ እንዳየነው Classical conditioning Involuntary ነበር Operant ግን Voluntary ነው፣ ማለትም አስበንበት የምንሸጠው ምላሽ ነው። ለምሳሌ አንድ ተማሪ ጥሩ ውጤት ማምጣት እንደሚያሸልም ካወቀ በደንብ ሊያጠና ይችላል። አያችሁ አ ለመሸለም🏆 ለሚለው Consequence በደንብ ማጥናት የሚለውን ምላሽ ነው የሰጠው። ከዚያ በደንብ እያጠና በመጣ ቁጥር Behaviourኡ እየተለወጠ ሊመጣ ይችላል። ይህ አይነቱ የLearning type Operant Conditioning ይባላል።

The behaviour is followed by a consequence, and the nature of the consequence modifies the organisms tendency to repeat the behaviour in the future.

Classical ላይ እንደምሳሌ Pavlov Experiment ማየታችን ይታወሳል፣ እዚህጋ ደግሞ የSkinner Analysis [B.F Skinner was American Psychologist] እናያለን።

Skinner ምን አለ መሰላች የሰውን ባህሪ ለማወቅ የዚያን ሰው ውጫዊ የባህሪው ምንጭ እንጂ የውስጡን የባህሪ ውጤት ማወቅ የለብንም! ቆይ በኃላ በምሳሌ ነግራቿለው!
"To explain behavior, he said, we should look outside the individual, not inside."

In Skinner‘s analysis, a response (operant) can lead to three types of consequences:

📍 a neutral consequence
📍 a reinforcement
📍 a punishment.

🔖A neutral Consequence is the consequence that does not alter the response. ውጤቱ ለምላሻችን ምንም አይነት አስታዋፆ ከሌለው።
ለምሳሌ የሆነ ነገር ሰርተህ ሰርተህ ምንም አይነተ encourage ወይም discourage የሚያደርግ ውጤት ሳታይ ስትቀር።😶

🔖 A reinforcement is the consequence that strengthens the response or makes it more likely to recur. ለምሳሌ አንድ ተማሪ በደንብ አጥንቶ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ከተሸለመ፣ እና ሽልማቱ ከጣመው🥰#ደጋግሞ_ያጠናል

There are two basic types of reinforcers or reinforcing stimuli.

➨Primary reinforcers: is in general, have the ability to strengthen a behavior without prior learning. Eg. Food, water, light, comfortable air, etc እነዚህ ነገሮች አንድን ሰው ሊያበረታቱ ይችላሉ።

➨Secondary reinforcers: These reinforce behavior because of their prior association with primary reinforcing stimuli. Eg. Money, praise, applause, good grades, awards, and gold stars are common secondary reinforcers.
እዚህጋ ቅድም ያየነውን የተማሪውንና የሽልማቱን ምሳሌ መውሰድ እንችላለን።

Both primary and secondary reinforcers can be positive or negative.

➨Positive reinforcement is the process whereby presentation of a stimulus makes behavior more likely to occur again. ለምሳሌ አንድ ሰው መልካም ነገር ሰርቶ ከተመሰገነ፣ ያ ምስጋና ያን መልካም ነገር ደጋግሞ እንዲሰራ ሲያደርገው positive reinforcement እንላለን።

➨Negative reinforcement is the process whereby termination of an aversive (የሚያስጠላ) stimulus makes behavior more likely to occur.
ለምሳሌ አንድ ሰው አጥኑ ብሎ
ከጨቀጨቃችሁ፣ ከዚያ ልክ እሺ
ስትሉ ጭቅጭቁ የሚቆም ከሆነ
ጥናታችሁን በደንብ ታጠናላችሁ።
አያቹ አ ጭቅጭቁ አሁን Negative reinforcer ነው😇
ማለትም ጭቅጭቁ በደንብ እንድታጠኑ ያደርጋችኋል።
የሚገርማችሁ እኔ ግን ተቃራኒ ነኝ አጥና ብለው ሲጨቀጭቁኝ ጭራሽ ይብስብኛል🚶‍♂🚶‍♂😁😁

Negative Reinforcementም ለሁለት ይከፈላል። የሚከፋፈል ነገር በዛ አ🤧

➤Escape Conditioning: Behaviour is reinforced by the elimination of expected event from happening
➤Avoidance Conditioning: Behaviour is reinforced by preventing an expected event from happening.

👆ሁለቱም የሚመሳሰሉ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ትንሽ ልዩነት አላቸው። አጥኑ ተብላችሁ ከተጨቀጨቃች፣ ጭቅጭቁን አስወግዳችሁ በደንብ ምታጠኑበት ሁለት መንገድ አለ፣ የመጀመሪያው እሺ🙏 ማለት ነው [Escape]..ሁለተኛው አትጨቅጭቁኝ😡 ማለት ነው [Avoidance]

Schedules of reinforcement

🔖When a response is first acquired, learning is usually most rapid if the response is reinforced each time it occurs. This procedure is called continuous reinforcement.
ለምሳሌ፦ ጎበዙ ተማሪ ሁሌ ከፍተኛ ውጤት ባመጣ ቁጥር ሲሸለም በደንብ እያጠና ይመጣል። ግን ከተደጋገመና ሽልማቱን ከለመደው😐 የልጁ በደንብ የማጥናት ልማድ እየቀነሰ ይመጣል።

🔖 If it is rewarded on an intermittent (partial) schedule of reinforcement, which involves reinforcing only some responses, not all of them. This is called intermittent reinforcement.
ይሄ ደግሞ ተማሪዉ ሁሌ ከፍተኛ ውጤት ባመጣ ቁጥር አለመሸለም፣ አልፎ አልፎ ማድረግ።

There are four types of intermittent schedules.

1⃣Fixed-ratio schedules- Occurs after a fixed number of responses. It produces high rate of responding.
ይሄ ደግሞ ለምሳሌ የልብስ ፋብሪካ ውስጥ ሰራተኞቹ አንድ ልብስ👕 ባመረቱ ቁጥር (response) 2Dollar (reinforcer) ሲከፈላቸው፣ ነገር ግን በጣም ብዙ ካመረቱ ብዙ ብር ስለሚያገኙ😋 ስራቸው ሊቀንስ ይችላል።

2⃣Variable-Ratio Schedule- Oc
Channel name was changed to «ልዩ ነው ይመቻል 👌👌»
Channel name was changed to «G---Tutorial ልዩ ነው ይመቻል 👌👌»
Channel name was changed to «G---Tutorial ይመቻል 👌👌»