G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
ከታረዱ በሬዎች ወርቅ ተገኘ‼️
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከንባታ ዞን ሺንሺቾ እና ዱራሜ ከተማዎች በትናትናው ዕለት ለመሳላ በዓል ከታረዱት ሰንጋ በሬዎች ሆድ ዕቃ ውስጥ ወርቅ ተገኘ፡፡

የከንባታ ዞን የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ለኢቢሲ ዶት ስትሪም እንደገለፁት፤ ለበዓል ከታረዱ 2 በሬዎች ውስጥ የተገኘው ማዕድን ወርቅ መሆኑ ተረጋግጧል።

በትናትናው እለት በከንባታ ዞን ሺንሺቾ ከተማ በአካባቢው ባህል  ሼማታ ተብለው የሚጠሩ ማህበሮች 8 ሆነው በመደራጀት ሰንጋ በሬ  ገዝተው እንደነበር አስታውሰዋል።

የእርድ ሥነ ሥርዓት  በሚያከናውኑበት ወቅት ከበሬው ሆድዕቃ ውስጥ ለጊዜው ግራሙ በውል  ያልታወቀ ወርቅ መገኘቱን አስረድተዋል።

የተገኘውን ወርቅ ከ80 ሺህ ብር የገመቱት ሰዎች መኖራቸውንም ጠቁመው፤ ባለቤቶቹ ግን ከዚህ በላይ ያወጣል ማለታቸውን አንስተዋል።

በተመሳሳይ በከንባታ ዞን ዱራሜ ከተማ ለመሳላ በዓል ከተገዛው ሰንጋ በሬ 12.5 ግራም የሚያወጣ ወርቅ መገኘቱን አቶ ዳዊት ሀንዲኖ ተናግረዋል፡፡
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ቡታጅራ ምን ተፈጠረ
ከትናንት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ በቡታጀራ ከተማ ግጭት ተቀስቅሷል።
የግጭቱ ምክንያት ደሞ ለዘመናት በመስቃን ወረዳ እንቦር ቀበሌ ይተዳደርበት የነበረው የስናኖ ሴራ  የዞኑ አስፈፃሚዎች ስናኖ ሴራ የእንቦር ቀበሌ አደለም የዶቢ ቀበሌ ነው ብለው በመወሰናቸው እና ዛሬ በመስቃን ወረዳ ዋና ከተማ ቡታጀራ ሴራና አዳራሽ ላይ ዝግጅት በማዘጋጀታቸው የተነሳ ሲሆን ይህም በተደጋጋሚ የመስቃን ወጣቶች ሽማግሌዎች ይሄ ልክ አደለም "ባህል የማጥፋት ተልዕኮ ነው " ብለው የመስቃን ወጣቶች ትናንት ምሽት መስከረም 17/2018 ዓ.ም ጀምረው በቡታጅራ ከተማ ወደ አደባባይ ወጥተው የተቃውሞ አመፅ ማንሳታቸውን ምንጮች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
በከተማዋ ሆቴሎች፣መኪኖች እና መገልገያ ንብረቶች ላይ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
ዛሬም ድረስ አመፁ የቀጠለ ሲሆን በከተማዋ መደበኛ እንቅስቃሴ ተስተጓጉሏል ብለዋል።
ችግሮች በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድረግ ይልመድብን።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍21
ትምህርት ሚኒስቴር የ2018 የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና ምዝገባ ከመስከረም 20 እሰከ 25 እንደሚካሄድ አስታወቀ‼️
በ2018 የትምህርት ዘመን የድህረምረቃ ፕሮግራሞች ለመማር ፍላጎት ላላቸው አመልካቾች የሚሰጠው የድህረምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ ከመስከረም 20 እስከ 25 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት አመልካቾች የመመዝገቢያ ቅጽ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት በ https://ngat.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን ፈተና የሚሰጥበት ጊዜም በቀጣይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

አመልካቾች ከምዝገባ ጋር ተያይዞ ለሚኖራቸው ጥያቄ ዘወትር በሥራ ሰዓት በ0920157474 ወይም 0911335683 እንዲሁም በኢሜይል አድራሻ ngat@ethernet.edu.et በኩል ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚችሉ ተነግሯል።

ሁሉም አመልካቾች የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖራቸው እንደሚገባና የምዝገባ እና የአገልግሎት ክፍያ 750 ብር በTeleBirr በኩል ብቻ መከፈል እንደሚኖርባቸው ማሳሰቢያ ተላልፏል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🥰1
ለመረጃ ያህል‼️👇👇
ከንግድ ባንክ ወይም ከአንድ ባንክ ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ ሲላክ ገንዘቡ የሚተላለፈው ሁሉም ባንኮች በጋራ ያቋቋሙት እና ሁሉንም ባንኮች በአንድ ሲስተም አስተሳስሮ በሚገኘው "ኢትስዊች" በሚባል የዲጂታል ገንዘብ ማስተላለፊያ chain (e-payment) ሲሆን ለዚህም ከማንኛውም ባንክ ወደ ሌላ ባንክ ገንዘብ ስታስተላልፉ የኮሚሽን ክፍያ ያስከፍላል።
Etswich በ 2011 ሁሉም ባንኮች በሼር ያቋቋሙት የ e-payment አገልግሎት ሰጪ ተቋም ነው።
ነገር ግን ከንግድ ባንክ ወደ ሌላ የንግድ ባንክ  አካውንት ወይም ከአንድ ባንክ ሂሳብ አካውንት ወደ ተመሳሳይ የባንክ አካውንት ገንዘብ ሲልኩ የአገልግሎት ክፍያ እና የአገልግሎት ክፍያውን 15% ቫት ይከፍላሉ። የአገልግሎት ክፍያ ቫት ከትናንት ጀምሮ ንግድ ባንክ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1
ወንዶገነት ምን ተፈጠረ
በሻሸመኔ አቅራቢያ በወንዶገነትና በማልጋ ወረዳ ትናንት መስከረም 20/2018 ዓ.ም የአካባቢው ሽማግሌዎች በባህሉ መሰረት ሴቶች ሱሪ መልበስ የለባቸውም ብለው መልዕክት አስተላልፈዋል በሚል ወጣት ወንዶች ሴቶችን እያሳደዱ ሱሪያቸውን ሲያስወልቁ እና የለበሱትን ሱሪ በአደባባይ አስፋልት ለአስፋልት እያባረሩ ሲቀዱ እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመላክታል።
በዚህ ሳቢያ የተጎዱ ሴቶችም አሉ ብለውናል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1😍1
የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት‼️
ትምህርት ሚኒስቴር የ2017 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤትን ከ300 ወደ 297 ዝቅ አድርጓል፡፡

ሚኒስቴሩ እንደገለጸው ÷ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተማሪዎች ወደቀጣይ የትምህርት ደረጃ ለመዛወር 50 በመቶና ከዚያ በላይ ማምጣት እንዳለባቸው ይደነግጋል።

በዚህ መሰረትም በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና አማካይ ውጤታቸው 49 ነጥብ 50 እስከ 49 ነጥብ 99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ወደ 50 በመቶ እንዲጠጋጋ መወሰኑን አመልክቷል፡፡

ውሳኔውን ተከትሎም 49 ነጥብ 5 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ እንዳሟሉ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ስለሆነም 49 ነጥብ 5 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስቴሩ አረጋግጧል፡፡
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1🥰1
በግሸን ሌቦች ተያዙ‼️
በግሸን ደብረከርቤ አመታዊ በዓል ላይ ከህዝቡ ስልክ እና ገንዘብ ሲሰርቁ የነበሩ ሰዎች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ታስረዋል።
አንድ ግለሰብ ስምንት ስልኮችን እንዲሁም ገንዘብ ሰርቆ በፀጥታ ኃይሎች እጅ ከፍንጅ ተይዞ በአስቸኳይ ፍርድ የእስር ትዕዛዝ ተላልፎበታል።
አዩዘሀበሻ
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
2
Update
በአማራ ክልል ምንጃር አረርቲ ማሪያም ቤተክርስቲያን በተፈጠረው አደጋ የሟቾች ቁጥር 40 መድረሱን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልፀዋል።
የጎን አጥንታቸው የተሰበረ፣አይናቸው የጠፋ...ሌላም ጉዳት ያስተናገዱ እጅግ በርካታ ናቸው።
አሳዛኝ አደጋ፣አሳዛኝ ጠባሳ😥
ለመላው የምንጃር ህዝብና ለተጎጂ ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍1
2027 ዲቪ ለመሙላት‼️
ከዚህ በኋላ የዲሺ ሎተሪ ወይም የግሪን ካርድ ሎተሪ ለመሙላት ለመመዝገቢያ 1 ዶላር የሚያስከፍል ሲሆን የዲቪ ሎተሪ የደረሰው ግለሰብ ለቪዛ አፕልኬሽን 330 ዶላር የሚከፍል ይሆናል።
ይህ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው ከመጪው October 16/2025 ጀምሮ ነው። ዲቪ ሎተሪ ለመሙላት ክፍያ ሲጠየቅ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የ2027 ዲቪ ሎተሪ በፈረንጆቹ ከጥቅምት ወር እስከ ህዳር ድረስ መሙላት ይቻላል።
ክፍያው የሚፈፀመው በ e-paymet ነው። ውጤት ማየት የሚቻለው may 2026 ነው።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
የሞባይል ባንኪንግ ላይ ያነጣጠረ አዲስ የአንድሮይድ ቫይረስ መከሰቱ ተነገረ‼️
"ክሊዮፓትራ" የሚል ስያሜ የተሰጠዉ የሞባይል ባንኪንግ ላይ ያነጣጠረ አዲስ የአንድሮይድ ቫይረስ መከሰቱን የሳይበር ደህንነት ስጋቶች ላይ የሚሰራዉ ክሌፊስ #Cleafy’s ቡደን አሳወቀ።

የዚህ ቫይረስ መከሰት በሞባይል ባንኪንግ ስጋት እድገት ዉስጥ ከፍተኛ የሚባል ለዉጦች እየተከሰቱ መሆናቸዉን ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

በክሌፊስ ቡድን አማካኝነት በነሃሴ ወር መጨረሻ የተለየዉ ይህ ቫይረስ በአውሮፓ የፋይናንስ ተቋማት ላይ ባነጣጠሩ መጠነ ሰፊ ዘመቻዎች ዉስጥ ጥቅም ላይ እንደዋለ ተገልጿል። 

"ክሊዮፓትራ" የተራቀቀ የባንክ ትሮጃን ቫይረስ የመረጃ መንታፊዎች በርቀት ሆነዉ የተደበቀ ምናባዊ ኔትዎርክ ስርዓትን በመጠቀም ለጥቃት ሰለባ የሆኑ መሳሪያዎችን መቆጣጠር የሚያስችላቸዉ መሆኑ ተነግሯል።  

ይህ አጥፊ ሶፍትዌር ከገሃዱ ዓለም የማጭበርበር ሙከራዎች ጋር ቁርኝት የፈጠረ ሲሆን ለጥቃት ኢላማ የተደረጉ አካላት መሳሪያዎቸዉን ቻርጅ ሲያደረጉ እንዲሁም ብዙም ክትትል አይደረግበትም ብለዉ በሚያስቡት ምሽት ላይ ጥቃቶች በጥንቃቄ እንደሚሰነዝሩ ታዉቋል። 

የደህንነት ባለሙያዎች ቫይረሱ ለወደፊቱ የዘርፉ ስጋቶች ማሳያ ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ያስጠነቀቁ ሲሆን ይህም የፋይናንስ ተቋማትን ላይ ያለዉ የስጋት ደረጃ ከፍ እንደሚያደርገዉ ጠቁመዋል።

የቫይረሱ መከሰት ለፋይናንሺያል ተቋማት እና ፀረ-ማጭበርበር ቡድኖች፣ ከስታቲክ ትንታኔ በላይ የሆኑ ስራዎችን እንደሚጠበቅባቸዉ ያሳየና በመጠቀሚያ መሳሪያዎች ላይ የሚከሰቱ የባህሪ ለዉጦች ላይ ክትትል ማድረግ እንዲሁም የስጋት ማሳወቂያ መፍትሄዎችን መተግበር ወሳኝ መሆኑን ተገልጿል።
======
💎📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
አዲሱ የደመወዝ ስኬል‼️
አዲሱ የመንግስት ሰራተኞች የደሞዝ ስኬል ከላይ ተያይዟል። ይህ የደመወዝ ማሻሻያ ከተያዘው መስከረም ወር ጀምሮ የሚፈፀም ይሆናል፣የመስከረም ወር ክፍያው በ back payment በጥቅምት ወር ይፈፀማል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass