G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
ፎርብስ የ2025 የቢሊየነሮች ዝርዝር ይፋ አደረገ‼️

ፎርብስ መጽሔት 39ኛውን አመታዊ የቢሊየነሮች ዝርዝር ያወጣ ሲሆን ዘንድሮ የቢሊየነሮች ብዛት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ መሆኑን ዘግቧል።

በዝርዝሩ ውስጥ 3,028 ቢሊየነሮች የተካተቱ ሲሆን ይህ ቁጥር ከአምናው በ247 ከፍ በማለት ሪከርድ ሰብሯል።

የነዚህ ቢሊየነሮች ሀብት ድምር 16.1 ትሪሊየን ዶላር የተገመተ ሲሆን ይህም ከአለማችን አጠቃላይ ሀብት ውስጥ 15% ነው።

ዝርዝሩን የሚመሩት የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ባለቤቶችና አለቆች ሲሆኑ ከአንደኛ እስከ አስረኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ወንዶች ናቸው። በተጨማሪም ከምርጥ አስሩ ውስጥ ስምንቱ አሜሪካውያን ናቸው።

የቴስላ፣ ስፔስ ኤክስ፣ ኤክስ እና ኤክስ ኤ.አይ ባለቤትና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አማካሪ የሆነው ኢላን መስክ የ342 ቢሊየን ዶላር ባለሀብት በመሆን አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከመስክ ቀጥሎ የሜታ መስራች ማርክ ዙከርበርግ በ216 ቢሊዮን ዶላር፣ የአማዞን መስራች ጄፍ ቤዞስ በ215 ቢሊየን ዶላር፣ የኦራክል ኮምፒውተር ድርጆት መስራች ላሪ ኤሊሰን በ192 ቢሊየን ዶላር እንዲሁም የሉዊ ሺቶን እና ሌሎች የቅንጦት ምርቶች ቢዝነስ ባለቤት በርናርድ አርኖልት እና ቤተሰቡ በ178 ቢሊየን ዶላር ከሁለተኛ እስከ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የ5.1 ቢሊየን ዶላር ባለሀብት በመሆን 700ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከ3,028ቱ ቢሊየነሮች ውስጥ 406ቱ ሴቶች ሲሆኑ የዋልማርት ወራሽ የሆነችው አሊስ ዋልተን በ101 ቢሊየን ዶላር ትመራለች።

የዘንድሮው ዝርዝር ውስጥ 22 አፍሪካውያን ቢሊየነሮች የሚገኙ ሲሆን ናይጄሪያዊው የ23.9 ቢሊየን ዶላር ባለቤት አኪኮ ዳንጎቴ ከአለም 83ኛ ከአፍሪካና ከጥቁሮች ደግሞ አንደኛ ሆኗል።
ጅቡቲም ውጡልኝ አለች‼️
በትናንትናው ዕለት የጂቡቲ መንግስት የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጽያዊያን ሀገሪቱን በ30ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፉን በጅቡቲ ታጁራ ከተማ የሚኖሩ የአዩዘሀበሻ ቤተሰቦች ተናግረዋል።
ከዚህ በፊት ፑንትላንድ እንዲሁም ሶማሊላንድ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማስወጣታቸው ይታወሳል።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ጡረታ‼️
የቤት ሠራተኞችን የጡረታ ተጠቃሚ የሚያደርግ የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ ደንብ በ6 ወር ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገለጸ‼️
የቤት ሠራተኞች ጡረታን ጨምሮ የማህበራዊ ዋስትና አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች ደንብ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አንድነት የኢትዮጵያ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ማህበራት ሕብረት አስታውቋል።

የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ሂሩት አበራ የቤት ሠራተኞችን ሕግ በሚመለከት በዓለም አቀፉ ኮንቬንሽን 189 በተቀመጠው ሕግ መሠረት በቀጥታ ለመተግበር አስቻይ ሁኔታ ባለመኖሩ፤ ከኢትዮጵያ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ ደንቡና የሥራ ቅጥር ውሉ እንደሚዘጋጅ ተናግረዋል፡፡

ይኸው ደንብ በረቂቅ ደረጃ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል እየተዘጋጀ እንደሚገኝም ጨምረው አስታውቀዋል።

ለአብነትም በቋሚነት የሚሰሩ ሠራተኞች በሥራ ቦታቸው ላይ የመኖር፣ ተመላላሽ የሆኑት ደግሞ ሰርተው የሚሄዱበትን አግባብ የለየና የሥራ ቅጥር ውሉን ጨምሮ የሚወጣው ደንብ መሠረታዊ የሆኑ መብቶቻቸው ላይ ያተኮረ መሆኑን የሕብረቱ ፕሬዝደንት ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የሥራ ቅጥር ውሎች መኖራቸውን የጠቀሱት ፕሬዚዳንቷ፤ ነገር ግን ውሎቹ ሕጋዊ አለመሆናቸውን አስረድተዋል።

ከዚህም በመነሳት ለቀጣሪዎችም ሆነ ለቤት ሠራተኞች የሚጠቅም ወጥ የሆነ የሥራ መቀጠሪያ ውል እንዲኖር ለማስቻል ያሰበ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከዚሁጋ ተያይዞም ውሉ መውጣቱ ብቻ ሳይሆን 'ተፈፃሚነቱስ እስከምን ድረስ ነው?' የሚለውን ጉዳይ ማህበረሰቡ በደንብ ማየት ስላለበት የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ እየተሰራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የቤት ሠራተኞች ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ዘርፈ ብዙ እንደሆኑ የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፤ የሥራ ቅጥር ውሉን ጨምሮ አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች የሕግ ማዕቀፍ ጸድቆ ተግባራዊ በሚሆንበት ወቅት የሚታዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ሁሉ ሊቀርፍ እንደሚችል አንስተዋል።

አክለውም "ውሉ ለቤት ሠራተኝነት ሥራ እውቅና የሚሰጥ በመሆኑ የሕክምና አገልግሎት፣ ሰርተው ሲደክማቸው በጡረታ የሚካተቱበት አግባብን ጨምሮ ማህበራዊ ዋስትናቸውን ሊያረጋግጡ የሚችሉበትን መንገድ ይፈጥራል" ብለዋል።

በመሆኑም በዚህ 6 ወር ጊዜ ውስጥ የሥራ ቅጥር ውሉና አጠቃላይ የቤት ሠራተኞች ደንብ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
አሀዱ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👌2
ቅጣት‼️
የጥምቀትን በዓልን ምክንያት በማድረግ በታቦተ ህግ ላይ የተሳለቁ ግለሰቦች 1 ዓመት ከ4 ወር እንዲቀጡ የወላይታ ዞን አረካ ወረዳ ፍርድ ቤት ወስኗል‼️

የጥምቀት እና ከተራ በዓልን ምክንያት አድርገው በታቦተ ህግ ላይ የስላቅ ትዕይንት በቲክቶክ የማኅበራዊ ሚዱያ አጋርተው እምነትም ከእምነት ለማጋጨት ሙከራ ያደረጉ

በወላይታ ዞን አረካ ወረዳ የሚገኙ ግለሰቦች ላይ የአረካ ወረዳ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት 1 ዓመት ከአራት ወራት በእስር እንዲቀጡ ወስኗል።
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
ከጋብቻ በፊት የነበረ የግል ቤት በትዳር ዉስጥ ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ ቢደረግለትም የጋራ ንብረት ሊሆን አይገባም፡፡ (የፌደሬሽን ምክር ቤት መስከረም 28-2017 ዓ.ም)‼️

ቀደም ሲል ከጋብቻ በፊት የግል የነበረ ቤት በትዳር ዉስጥ መሰረታዊ በሚባል ደረጃ እድሳት ከተደረገለት ወይም ከፍተኛ ወጪ ወጥቶ ማሻሻያ ከተደረገለት ቤቱ የባልና ሚስት የጋራ ይሆናል በማለት በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔ ተሰጥቶ ነበር፡፡ ይህ የሰበር ሰሚ ችሎቱ ዉሳኔ ሕገ-መንግስቱን ይቃረናል በሚል የሕገ-መንግስት ትርጉም ለፌደሬሽን ምክር ቤት ቀርቦት የነበር ሲሆን  የፌዴሬሽን ምክር ቤቱ መስከረም 28-2017 ዓ.ም  በሰጠዉ ዉሳኔ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሰጠዉን ዉሳኔ በመሻር ተፈጻሚነት የለዉም ብሏል፡፡ፌደሬሽን ምክር ቤት ዉሳኔ ከጋብቻ በፊት የግል የነበር ቤት በጋብቻ ዉስጥ ማሻሻያ እና ማስፋፊያ  መደረጉ ቤቱን የጋራ ንብረት አያደርገዉም፡፡ ቤቱን ለማሻሻል እና ለማስፋፋት የወጣ ወጪ ተጣርቶ ወጪዉ በድርሻ እንዲወስዱ ከሚደረግ በስተቀር ቤቱ የጋራ አይሆንም፡፡
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🥰2
Update‼️
አብዛኞቹ በጥይት ተመተዋል:-የተጎጂ ቤተሰቦች‼️
ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ-ጎጃም መስመር ጎሃፅዮን አቅራቢያ አንድ መኪና ሙሉ ተሳፋሪዎች ላይ የጥይት ሩምታ መከፈቱን ዘግበን ነበር።
አሁን ላይ የተጎጂ ቤተሰቦች ለአዩዘሀበሻ እንደተናገሩት "ከሁለት የወንድሞቼ ልጆች ውስጥ አንዷ ተገላለች ያሉ ሲሆን አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች በጥይት እንደተመቱ ደውለው ነግረውናል" ብለዋል።
ታጣቂዎቹ አግተው የወሰዷቸው አሉ? አግተው የወሰዱ አይመስለንም ያሉ ሲሆን፣የሞቱትን ጭኖ ለመውሰድ መኪና አጥተን እየተጉላላን ነው ብለዋል። አብዛኛው ተሳፋሪ ግን ቁስለኛ ሆነዋል"ሲሉ የተጎጂ ቤተሰቦች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።
የሚያልፉ መኪኖች ቁስለኞችን በመጫን ትብብር እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
😢3
ትራዎሬ‼️
ቡርኪና ፋሶ ከአሜሪካ ታስገባ የነበረው ልባሽ ጨርቅ/ቦንዳ ልብስ/ ከዚህ ወዲያ እንዳይቀጥል  በይፋ አገደች።
የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራዎሬ በጉዳዩ ላይ “አፍሪካ አህጉር እንጅ የቆሻሻ ገንዳ  አይደለችም!” ብሏል።
አሁን በቡርኪናፋሶ ተማሪዎች፣ ዳኞች፣ ፖሊሶች፣ ወታደሮች የሚለብሱት ልብስ በሀገሪቱ የተመረቱ ናቸው።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
👇👇👇👇👇
@GT12192123

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ

👇👇👇👇👇👇

#share
#share

🙏🙏🙏🙏🙏

🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝
JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝
👏3
የግድያ ሙከራ‼️
#አፍሪካ ጀግና መሪ ቢፈጠርም መስዕዋት ሁኖ ለማለፍ እንጅ ለመስራት አይታደልም። ትራዎሬ ስልጣን በያዘ ሁለት ዓመት ጊዜ እንኳ ከ 18 በላይ የግ ድያ ሙከራ ተደርጎበታል።

በባለፈው ሀሙስ ማታ ብቻ ትራዎሬ ላይ ግድያ ለመፈጸም ሲዘጋጁ የተገኙ 113 በላይ ዜጎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከኋላ ሴራውን ሸራቢዎች ምዕራባውያን ቢሆኑም ድርጊቱን ፈጻሚዎቹ የገዛ ዜጎቹ ናቸው።ፈረንሳይ የመሆን እድሏም ከፍ ያለ ነው።በአንድ ወቅት ትራዎሬ ከፈረንሳዮ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮኒ ጋር ያደረገው ንግግር ኃያላኑን ያስደነገጠ ነበር።ነገሩ እንዲህ ነው

ኢማኑኤል :- "ፕሬዝዳንት ትራዎሬ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ለማጠንከር በሀገርህ ወታደር የማሰፍርበት ቦታ ስጠኝ" በማለት ይጠይቀዋል።

የትራዎሬ ምላሽ :- "አሜሪካ ፣ ብሪታኒያ ፣ ብራዚል ወዳጆችህ ናቸው።ታዲያ ለምን ወዳጅነትህን ለማጠንከር በነዚህ ሀገሮች ላይ የጦር ሰፈር አልኖረህም?" የሚል ነበር።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍5
አንድ ትሪሊዮን ብር እዳ‼️
"መንግስት  አንድ ትሪሊየን ብር እዳ አለበት" የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ‼️
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸሙን በተመለከተ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት፣ በአጠቃላይ ካለው የብድር ክምችት አንድ ትሪሊዮን ብር ዕዳ የመንግሥት መሆኑን አስታውቋል ።

የባንኩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደገለጹት፣ የባንኩ የብድር ክምችት 1.393 ትሪሊዮን ብር መድረሱንና ከዚህ መጠን ውስጥ 74.4 በመቶ ወይም አንድ ትሪሊዮን ብር የመንግሥት ዕዳ መሆኑን ገልጸዋል።

የባንኩ ጠቅላላ የብድርና ቦንድ ክምችት መጠን ከ1.3 ትሪሊዮን ብር በላይ የተሻገረ ሲሆን፣ ከዚህም ላይ የግል ተበዳሪዎች ድርሻ ከ300 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተጠቅሷል።

ከተገለጸው አጠቃላይ የብድር ክምችት መጠን በቦንድ የተወሰደ ብድር 66.7 በመቶ ያህሉን በመሸፈን የአብላጫውን ድርሻ ሲወስድ፣ 27.62 ቢሊዮን ብር የተጠራቀመ ወለድ መሆኑም ተገልጿል።

ባንኩ ከነበረው አጠቃላይ ብድር ለግል ዘርፉ የተሰጠው ብድር ስምንት በመቶ ብቻ ነበር። የተቀረው 92 በመቶ በመንግሥት የተወሰደ ነው። መንግሥት ከወሰደው ብድር 98 በመቶ የሚሆነው የተሰጠው በስምንት በመቶ የወለድ ምጣኔ ሲሆን፣ የተቀረው ሁለት በመቶ ብቻ በ11 እና በ12 በመቶ የወለድ ምጣኔ የተሰጠ ብድር ነው፤›› ብለዋል።

እንደሪፖርተር ዘገባ መንግሥት በወሰደው ብድር ላይ 173 ቢሊዮን ብር ወለድ መጠራቀሙንና መንግሥት ግን ብድሩን ባያቃልልም፣ ንግድ ባንክ ወለዱን መሰብሰቡ ታሳቢ ተደርጎ በየዓመቱ ግብር ሲከፍል መቆየቱ ታውቋል ።
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
🔥1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተቃውሞ‼️
ፀረ ትራምፕ ተቃውሞ በበርካታ የአሜሪካ ከተሞች ተቀሰቀሰ‼️

ከዋሽንግተን ዲሲ እስከ ኒውዮርክ ከቦስተን እስከ ቺካጎ እና ሎስ አንጀለስ ድረስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ዋና ዋና ጎዳናዎችን በማጥለቅለቅ በጥር ወር ወደ ሥልጣን በመጡት ትራምፕ ላይ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ይገኛሉ።

ሰልፈኞቹ በትራምፕ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ወደ አደባባይ የወጡት ፕሬዝዳንቱ ከማህበራዊ እስከ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በሚያራምዳቸው አጀንዳዎች ደስተኛ ባለመሆናቸው እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ትራምፕ ያደረጓቸውን የፖሊሲ ለውጦች በመፈክሮቻቸው አንድ በአንድ በመጥቀስ "ትራምፕ ሆይ እጅዎን ያንሱልን" ሲሉ ተደምጠዋል።
የሰልፈኞች ብዛት ግማሽ ሚሊዮን አካባቢ ይደርሳል ተብሏል።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2
ጌታቸው ረዳ‼️
ለህክምና ዱባይ የነበሩት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ጠዋት ወደ አዲስ አበባ መመለሳቸውን ሰምተናል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ዱባይ በነበሩበት ወቅት ከአንድ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ "አሁንም የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት እኔ ነኝ፣ዶክመንቶች ላይ የምፈርመው እኔ ነኝ ብለዋል።
አቶ ጌታቸው “የህወሀት ትጥቅ ትግል አባል አለመሆኔ ከክልሉ አመራርነት ለመገለሌ ምክንያት ነው”ያሉ ሲሆን ወደ ትግራይ ለመመለስ ለደህንነቴ ያሰጋኛል ሲሉ በቃለምልልሱ ላይ ተናግረዋል።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
የሞቱ 5 የቆሰሉ 23‼️
ትናንት ጠዋት በኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ-ጎጃም መስመር አንድ ታታሪ አውቶቡስ ሙሉ ተሳፋሪ ይዞ ከባህርዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ በነበረበት ሰዓት  ጎሃፅዮን አቅራቢያ ሲደርስ ተሳፋሪዎችን ለማገት የጥይት ሩምታ ተከፍቶባቸው እንደነበር አዩዘሀበሻ በትናንትናው ዕለት መዘገቡ ይታወሳል።
አሁን ላይ የተጎጂ ቤተሰቦች ለአዩዘሀበሻ እንደገለፁት በጥቃቱ የሞቱ ተሳፋሪዎች ቁጥር አምስት የደረሰ ሲሆን የቆሰሉት ደግሞ 23 መሆናቸውን ገልፀዋል።
ከእገታው በኋላም ከፌደራል ፖሊስ እና ከአካባቢው የፀጥታ ሀይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ ነበር ብለዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው ወራጃርሶ ወረዳ ጭለሎ ቀበሌ ወል በሚባል አካባቢ ነው ብለዋል።
ቀሪዎቹን 37 ተሳፋሪዎችን አጋቾቹ ወደ አዋሬ ጎልጄ ቀበሌ ይዞ ሄዶ የነበረ ሲሆን ከፌደራል ፖሊስ እና ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተለቀው ጎሀፂዮን መግባታቸውን ምንጮቼ ገልፀዋል።
አዩዘሀበሻ
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍3
#Burkinafaso
ትራዎሬ በቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ ጄኔራል ቻርለስ ዲጎል ስም የነበረውን የቡርኪናፋሴን ዋና ከተማ ኡጋዱጉን ዋና ጎዳና በቶማስ ሳንካራ ስም ሰይሞ ቶማስ ሳንካራ በተገደለበት ስፍራ መታሰቢያ ሙዚየም በመገንባት እኔም ብሞት ሀገሬ ሌላ ጀግና ታፈራለች እንጅ ፈጽሞ እጅ አትሰጥም ሲሉ 15 የአርበኝነት ቀናትን አስጀምረዋል።
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
👍3