G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
Philosophy ን እንደ መግቢያ ነው የማስተምራችሁ ፡ ደረቅ ንባብ ስለሆነ ግቢ ስትገቡ ለፈተና አንብቡት ። ምን አይነት የ concept ጥያቄ ስለማይወጣበት እንዲሁ ከሸመደዳችሁት ትሰሩታላችሁ። ስለዚህ የለቀቅንላችሁ pdf ላይ ኖቱን አንብቡት ፡ ሸምድዱት ፈተና ሲደርስ😊። እንደ መግቢያ ግን እንመልከተው በትንሹ።

📍Introduction

🌀 Chapter One

✏️Philosophy

📚 Philosophy ን እንዲሁ በቀላሉ define ማድረግ ወይም ብያኔ መስጠት ይከብዳል። እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ብያኔዎች አሉት። አንዱን formal የሚባለውን Definition እንመልከት።

🎈Philosophy is a process of reflecting and criticizing our most deeply held conceptions and beliefs.

ፍልስፍና ማለት ስለ አንድ ነገር ምሳሌ ስለ ተፈጥሮ፡ ስለ ማህበራዊ ትስስር ፡ ስለ ዩኒቨርስ ፡ ስለ ውበት ወዘተ ያለንን ጥልቅ የሆነ አመለካከት እና እምነት የምንገልፅበት ፡ የምናፀባርቅበት ፡ የምንገመግምበት ፡ የምንተችበት ሒደት ፍልስፍና ይባላል።

📍 Types of Philosophy

👩‍🏫 Epistemology
🌹 Aesthetics
🤔 Metaphysics
🤝 Ethics
🚸 Logic

እያንዳንዳቸውን እንደ መግቢያ ያክል እንመልከት። ዋናው ትምህርታችን ሎጂክ ነው።

👩‍🏫 Epistemology

is a branch of Philosophy that deals with the nature, scope, meaning and possibility of knowledge.

ዕውቀት ምንድን ነው? አንድ ሰው አወቀ የሚባለው ምን ሲሆን? የዕውቀት ምንጩ ምንድን? ዕውቀት ከሌሎች የሚለየው በምንድን ነው? እውነት ምንድን ነው? አንድ ነገር ዕውነት መሆኑን እንዴት ነው የምናውቀው? በ እምነት እና በምክንያታዊነት መካከል ያለው ዝምድ እና ልዩነት ምንድን ነው? እነዚህን እና የመሳሰሉትን የሚያጠና የፍልስፍና ክፍል Epistemology ተብሎ ይጠራል።

🌹 Aesthetics

is a branch of Philosophy that deals with beauty, art, enjoyment, perception, sense of taste and sentiment.

ጥበብ ምንድን ነው? የጥበብ ሀገሯ ወዴት ነው? ውበት ምንድን ነው? የውበት መለኪያ ምንድን ነው? የሚዳሰስ ነው? በ ውበት, በጥበብ እና በዕውነት መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው? ውበት ምንጩ ምንድን ነው? በተፈጥሮ ወይስ በሰው ሰራሽ? እነዚህን ና የመሳሰሉትን የሚያጠና የፍልስፍና ክፍል Aesthetics ተብሎ ይጠራል።

🤔 Metaphysics

is a branch of Philosophy that deals with the ultimate nature of reality or existence.

የአንድ ነገር መገኘት ወይም መፈጠር ምን ማለት? የመጨረሻው ትልቁ ዕውነት ምንድን ነው? የሰው ልጆች ነገሮችን የሚያደርጉት በራሳቸው ነፃ ፍቃድ ነው ወይም በ supernatural power ቀድሞ ተወስኖላቸው ነው? ፈጣሪ አለ🤭? ካለ መኖሩንስ እንዴት ማረጋገጥ የምንችለው? የሰው ልጅ ምንድን ነው😬? የሚያስብ ጭንቅላት ያለው🤔? የሚንቀሳቀስ የተዋቀረ አካል ያለው🤥? ጊዜ ምንድን ነው😾? ህይወት ማለት ምን ማለት ነው? እነዚህን እና የመሳሰሉትን የሚጠና Metaphysics ይባላል። ወይ metaphysics🤭🤭

🤝 Ethics
Civics ላይ ተምራችሁታል።

🙌 Logic
ይህን የፍልስፍና ክፍል ነው ፍሬሽማን ላይ የምትማሩት።

ነገር ግን ስለ ሎጂክ ከ ማየታችን በፊት statement እና proposition ምን እንደሆነ እንመልከት።

🌀 Statement - is a declarative sentence that has truth value.

🌀 Statement - is a sentence that is either true or false.

Statement ማለት እውነት ወይም ሀሰት የሆነ ዐነገር ነው። ወይም

እውነት ነው ወይም ሀሰት ነው ብለን የምንፈርጀው ዐነገር statement ይባላል።

ምሳሌ ፡

👉 Mekelle is the capital city of Oromia Region.

👉 2+2 = 5.

👉 Barack Obama is the first black American president.

👉 All planets revolve around the sun.

የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ዐ.ነገሮች ውሸት(false)

የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ዐነገሮች እውነት(true) ናቸው።

ስለዚህ በአጠቃላይ አራቱም ዐ.ነገሮች statement ናቸው ማለት ነው።

🌀 Proposition - is an information content of statements.

Proposition ማለት ደግሞ statement ቱን ይዘት የሚገልፅን መረጃ ወይም የ statement ቱ ትርጓሜ ማለት ነው።

Logic የተገነባው ከ statement or proposition ነው።

ብዙውን ጊዜ ሎጂሽያኖች statement እና proposition በአንድ አይነት መንገድ(interchangeably) ይጠቀሙበታል። ነገር ግን statement እና proposition አንድ አይነት ናቸው ማለት አይደለም።

ብዙውን ጊዜ true/false ላይ ፈተና ስለሚወጣ ይቺን ሀሳብ ያዟት👇👇👇👇

"in the strict sense of the terms , statement and proposition do not have exactly the same meaning."

Now let us proceed to the further study of Logic.( አሁን ሎጂክን እንመልከት)


📕 CHAPTER TWO`

📑 Basic Concepts of Logic

Definition of Logic🤔

ሰዎች ብዙውን ጊዜ ይህ ነገር logical ነው ፡ ይህ ነገር logical አይደለም እያሉ በተለምዶ ይናገራሉ። ግን ሰዎች በተለምዶ logical ነው ወይም logical አይደለም የሚሉት ነገር በትክክል ሎጂክ ን ይገልፀው ይሆን🤔?

🤔 What is Logic

🎯 Logic(ስነ-አመክንዮ) - is the science or philosophy that deals with and evaluates Argument.

🎤 Logic(ስነ-አመክንዮ) ማለት ስለ Argument የሚያጠና እና Argument ን የሚገመግም የ ሳይንስ ወይም የፍልስፍና አይነት ነው። ታዲያ Argument ምንድን ነው🤔?

Dictionary ላይ ብታዩት Argument ማለት ክርክር ማለት ነው። እናንተም Argumentative passage እያላችሁ ተምራችሗል። logic የሚያጠናው argument ግን ይለያል። እስኪ እንየው!

👉 Argument (አመክንዮ)

👨‍💼 Argument - is a group of statements, some of which are intended to provide support or evidence to conclude about something.

👌 Argument (አመክንዮ) - ማለት የሆነ ማስረጃን መሰረት በማድረግ ወይም የሆነ ማስረጃን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት Argument ይባላል። ስለዚህ ሁለት ነገሮች አሉን ማለት ነው።

👉 1ኛ) ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የተጠቀምነው ማስረጃ(evidence)::

👉 2ኛ) ማስረጃውን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው ድምዳሜ( conclusion)::

👐 ታዲያ ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የምንጠቀመው ወይም የተጠቀምነው ማስረጃ premises ተብሎ ይጠራል።

👐 ማስረጃውን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው ድምዳሜ Conclusion ተብሎ ይጠራል። so,

🎈 Premises - is a group of statements that set forth the reason(evidence). Or

🎈 Premises - is a group of statements that are claimed to provide logical support or evidence to the conclusion.

🎈 Conclusion - is a statement which is claimed to follow the alleged evidence.

👆 ፈተና ላይ ስለሚወጡ ያዟቸው።

😻 ስለዚህ

😎 Argument = Premises + Conclusion.

እስቲ ምሳሌዎችን እንመልከት፡

🔷 Example 1

➡️All Ethiopians are Africans.
➡️ Solomon is an Ethiopian
➡️ Thus, Solomon is an African.

👆 ሁሉም ኢትዮጵያውያን አፍሪካዊ ናቸው። ሰለሞን ኢትዮጵያዊ ነው። ስለዚህ ሰለሞን አፍሪካዊ ነው።

🥺 አያችሁ አይደል!!

ሰለሞን አፍሪካዊ ነው ብለን ድምዳሜ(conclusion) ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አፍሪካዊ ናቸው እና ሰለሞን ኢትዮጵያዊ ነው የሚሉት ናቸው።

🙌 ስለዚህ ከላይ ያየነው ምሳሌ argument ነው። ምክንያቱም ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት ማለትም ሰለሞን አፍሪካዊ ነው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት ማስረጃዎችን ተጠቅመናል።

ስለዚህ ከላይ ያየነው ምሳሌ argument ከሆነ የግድ premises እና conclusion አለው ማለት ነው ምክንያቱም argument የሁለቱ ድምር ውጤት ስለሆነ። ስለዚህ የትኛው ነው premises? የትኛው ነው conclusion?

👉 Premises ማለት ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የምንጠቀመው ማስረጃ ነው ።

ስለዚህ ሰለሞን አፍሪካዊ ነው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት የተጠቀምነው ማስረጃ ፡

👉 All Ethiopians are Africans.
👉 Solomon is an Ethiopian.

ስለዚህ ሁለቱ👆 premises ናቸው።

Conclusion ማለት ደግሞ ማስረጃዎችን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት ነው። ስለዚህ

👉 Solomon is an African የሚለው conclusion ነው።

🔷 Example 2

➡️ Three is prime number.
➡️ Five is prime number.
➡️ Seven is prime number.
➡️ Therefore, all odd numbers between two and eight are prime numbers.

በ 2 እና 8 መካከል ያሉ ሁሉም odd ቁጥሮች prime number ናቸው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው 3 , 5 እና 7 prime number ናቸው የሚለው ነው። ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት ማስረጃ ስለተጠቀምን argument ነው ማለት ነው። argument ከሆነ ደግሞ የግድ premises እና conclusion አለው ማለት ነው። የትኛው ነው premises? የትኛው ነው conclusion ?

🔶 Premises ማለት ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የምንጠቀመው ማስረጃ ነው። ስለዚህ በ 2 እና በ 8 መካከል የሚገኙ ሁሉም odd ቁጥሮች prime number ናቸው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት የተጠቀምነው ማስረጃ፡

👉 3 is prime number.
👉 5 is prime number.
👉 7 is prime number.

እነዚህ👆 premises ናቸው።

👐 Conclusion ማለት ደግሞ ማስረጃዎችን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው ድምዳሜ ነው። ስለዚህ

👉 All odd numbers between 2 and 8 are Prime numbers. የሚለው conclusion ነው።

🔷 Example 3

➡️ It has rained for the past 5 consecutive days.
➡️ As a result, It will rain today.

ዛሬ ዝናብ ይዘንባል ብለን ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ባለፋት ተከታታይ 5 ቀናት ዝናብ መዝነቡ ነው። ስለዚህ argument ነው ማለት ነው። ታዲያ የትኛው ነው premises? የትኛው ነው conclusion?

Premises ማለት ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ነው። ስለዚህ ዛሬ ዝናብ ይዘንባል ብለን ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ላለፋት ተከታታይ 5 ቀናት መዝነቡ ነው። ስለዚህ

👉 It has rained for the past 5 days.(Premises)

👉 It will rain today. (conclusion)

🔶 ስለዚህ logic ማለት ስለ argument የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ማለት ነው። በሌላ አባባል በ premises እና conclusion መካከል ያለውን ዝምድና ወይም ግንኙነት የሚያጠና እና የሚገመግም የፍልስፍና ዘርፍ ነው። ስለዚህ ከዚህ ምን እንረዳለን??

Logic ማለት ነባራው ዕውነታ(General truth) ማለት አይደለም። ለምሳሌ ፡

ፕላኔቶች በፀሀይ ዙሪያ ይዞራሉ።ይኸ ነባራዊ ዕውነታ ግን logic አይደለም።

አስተውሉ logic ማለት ነባራዊ ዕውነታ ወይም General truth አይደለም።

Logic ማለት ስለ argument የሚያጠና ነው ።
ማለትም ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት በምንጠቀመው ማስረጃ እና ማስረጃውን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር በምንሰጠው ድምዳሜ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠና እና የሚገመግም የ ፍልስፍና ዘርፍ ነው።

ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር በምንሰጠው ድምዳሜ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠና እና የሚገመግም የፍልስፍና ዘርፍ ነው።

👉 እስቲ እንመልከት logic ነባራዊ ዕውነታ አለመሆኑን።

🔷Example

➡️ All human beings are immortal.
➡️ Samuel is a human being.
➡️ Therefore, Samuel is immortal.

የሰው ልጅ ሟች አይደለም። ሳሙኤል የሰው ልጅ ነው። ስለዚህ ሳሙኤል ሟች አይደለም።

😜 አያችሁ አይደል ሳሙኤል ሟች አይደለም ብለን ድምዳሜ ለመስጠት ማስረጃ አቅርበናል። ስለዚህ logic ነው።

🤷‍♂ ግን ነባራዊ ዕውነታው የሰው ልጅ ሟች ነው። የ ሰው ልጅ ሟች አይደለም ብለን ያቀረነብነው ማስረጃ ከ ነባራዊ ዕውነታው ጋር ቢጣረስም logic ከመሆን አላገደውም ምክንያቱም logic ነባራዊ ዕውነት ሳይሆን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ እና ድምዳሜውን ለመስጠት ስለተጠቀምንበት ማስረጃ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠና ነው። ስለዚህ

🎈 Argument - is the inferential claim between premises and conclusion.

🎈 Argument - is not the factual claim between premises and conclusion.

አደራችሁን እነዚህን👆 ሁለት ሀሳቦች ያዟቸው። ፈተና ላይ ይወጣሉ።

Argument ወይም logic ማለት በ ድምዳሜው(conclusion) እና በ ማስረጃዎቹ(premises) መካከል ያለው ግንኙነት የምክንያታዊነት(inferential claim) ግንኙነት ነው እንጂ የ ነባራዊ ዕውነታ(factual claim) ግንኙነት አይደለም። ለዛ ነው

➡️ Human being is immortal.
➡️ Samuel is human being.
➡️ Therefore, Samuel is immortal.

👆👆 ይህ ሀሳብ logic ነው ያልነው።

ሌላው የምነግራችሁ መሰረታዊ ሀሳብ፡

Argument= premises + conclusion.

Argument የ premises እና conclusion ድምር ነው።

Premises አንድ እና ከ አንድ በላይ ዐ.ነገር(statement) ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን conclusion ሁልጊዜ አንድ ዐ.ነገር(statement) ብቻ ነው::

🎈 Premises can have one or more than one statements.

But

🎈 Conclusion always have only one statement.

👆👆ፈተና ላይ ስለሚወጣ ያዙት


Argument ማለት የ premises እና የ conclusion ድምር ውጤት ነው ብለናል። ታዲያ በ argument ውስጥ የሚገኙትን premises እና conclusion እንዴት ነው ማወቅ የምንችለው? የትኛው ነው premise? የትኛው ነው conclusion? እነዚህን እና ሌሎችን በቀጣይ እናያለን።

©A+ Tutorial Class.
አብዛኞቻችሁ ሰርታቹታል👏
በርቱ አነብቡ! ተከታተሉን!

በመቀጠል የLogic ጥያቄ ይለቀቃል!
አንዳንድ ትምህርቱን በቻናሉ ላይ ልታገኙ ያልቻላችሁ ተማሪዎች @ucan_scorebot ላይ አናግሩን!
🙌 ሻሎም የ A+ tutorial class ቤተሰቦች። ዛሬ በፕሮግራማችን መሰረት የሎጂክ ትምህርት ከሰአት እንማራለን😊
Hey there!

Eventhough based on the
Schedule Today is the question & answer competition day, we bypassed it to next week because we haven't finished chapter one's of each subject yet.

ዛሬ የPsychology course
ይለቀቃል፣ ቻፕተር oneን እንጨርሳለን፣ ማታ ከunit1 ጥያቄ
በphoto ይለቀቃል።

©A+ tutorial class
Geography Short Notes Clear Explanation Easy to Understand!👇

Preferable for study👍
Genet Chapter I logic 45279.docx
55.7 KB