አገርን ለመበታተን አቅደው በመከላከያ ሠራዊት ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ያደረጉ አሸባሪዎችና ዋነኛ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
#Ethiopia : ከአገር መከላከያ ሠራዊቱን በማስከዳት ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩና በጦርነቱ ከሠራዊቱ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ጄኔራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ መኮንኖች፣ መስመራዊ መኮንኖችና የግል ጥበቃዎቻቸው ላይ እርምጃ መወሰዱንም የመከላከያ ሠራዊት ሃይል ስምሪት መምሪያ ሃላፊ ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ ገልጸዋል።
ብርጋዴል ጄኔራሉ ጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል የፍተሻ ተግባሩን አጠናክሮ መቀጠሉንም ተገልጿል።
ብርጋዴል ጄኔራል ተስፋዬ እንደገለፁት የቀድምው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሰባት የጁንታው ሲቪል አመራሮች እንዲሁም ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ አመራሮችም በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በዚሁ መሰረት እርምጃ የተወሰደባቸው፡-
1ኛ- ሜጀር ጄኔራል ኢብራሂም አብዱልጀሊል፡- ቀደም ሲል የመከላከያ ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረና አሁን የጁንታው ሎጂስቲክ ሃላፊ የነበረ
2ኛ- ብርጋዴል ጄኔራል ገብረኪዳን ገብረማርያም፡- የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ሃላፊ የነበረና በጡረታ ከተሰናበተ በኋላ ጁንታውን የተቀላቀለ
3ኛ- አስር ከፍተኛ መኮንኖች
4ኛ - ሁለት መስመራዊ መኮንኖች
5ኛ- አንድ የክልሉ ረዳት ኮሚሽነር የነበረና ከፖሊስ ከድቶ ወደ ጁንታው የተቀላቀለ ናቸው።
በተጨማሪም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ገልፀዋል።
እነዚህም
1ኛ- አቶ አባይ ወልዱ፡- የቀድሞ የክልሉ ፕሬዚዳንት የነበረ
2ኛ- ዶክተር አብርሃም ተከስተ- የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበረ
3ኛ- ዶክተር ረዳኢ በርሄ፡- የክልሉ ኦዲተር ሃላፊ የነበረ
4ኛ ዶክተር ሙሉጌታ ይርጋ፡- የክልሉ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሃላፊ የነበረ
5ኛ- አቶ ዕቁባይ በርሄ- የሃይማኖት ጉዳይ ክትትል ሃላፊ የነበረ
6ኛ- አቶ ጌታቸው ተፈሪ፡- የክልሉ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤትና የሠላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረ
7ኛ- ወይዘሮ ኪሮስ ሃጎስ፡- የክልሉ ማህበራዊ ጉዳይ ሃላፊ የነበረች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ሁለት ከመከላከያ ከድተው ጁንታውን የተቀላቀሉ ከፍተኛ መኮንኖች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን እነሱም ኮሎኔል ገብረእግዚአብሄር አምባዬና ኮሎኔል ትርፏ አሰፋ መሆናቸውን ብርጋዴል ጄኔራሉ ለኢዜአ ገልፀዋል።

ሰበር ዜና ‼️
የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ሌሎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ዋነኛ የጁንታው አመራሮች አዲስ አበባ ገቡ
#Ethiopia : የቀድሞውን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩትን ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ አገር ለመበታተን ሲሰሩ ቁጥጥር ስር የዋሉ የህወሓት ጁንታ አመራሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስና የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ጥምር ሃይል በአገር መከላከያ ሠራዊት ላይ ጥቃት በማድረስ አገር ለመበታተን ሲሰሩ የነበሩ የአሸባሪው ህወሓት ቡድን አባላትን ለሕግ የማቅረብ ተልዕኮ እንደቀጠለ ነው።
በትናንትናው ዕለትም የቀድሞውን የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት አባይ ወልዱና የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ዶክተር አብርሃም ተከስተን ጨምሮ ዘጠኝ የጁንታው አመራሮች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አሁን አዲስ አበባ ገብተዋል።

“እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል” - አቶ ስብሃት ነጋ
አቶ ስብሃት “አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችንን ነው በማስፈጸም ላይ ያላችሁት” ማለታቸውን ሌ/ጄኔራል ባጫ ገለጹ!
የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ ስብሃት ነጋ በመከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር መዋላቸው መገለጹ ይታወሳል፡፡ የመከላከያ ሚኒስቴር ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴር ጄነራል ተስፋየ አያሌውን ከቀናት በፊት በሰጡት መግለጫ አቶ ስብሃት ነጋ እና ሌሎች የሕወሓት አመራሮች መያዛቸውን በገለጹበት ጊዜ ግለሰቦቹ የተያዙት በሰርጥ ውስጥ ተደብቀው ከነበረበት መሆኑን አንስተዋል፡፡
አቶ ስብሃት በመከላከያ ሰራዊትና በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተለቀቀው ተንቀሳቃሽ ምስልና ፎቶ ሲስቁ ታይተዋል፡፡በርካቶችም አቶ ስብሃት ምን አሉ በሚል ሲነጋገሩ ነበር፡፡ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን በራያ ግንባር በኩል ሲመሩ የነበሩት ሌፍተናንት ጄኔራል ባጫ ደበሌ እንደገለጹት አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ስብሃት በተያዙበት ሰዓት ለከፍተኛ የመከላከያ መኮንኖች ፣ “እኛ እኮ ከሞትን ቆይተናል“ የሚል አስተያየት እንደሰጡ ሌ/ጄኔራል ባጫ ደበሌ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
አቶ ስብሃት ከተያዙ በኋላም ልክ እንደተገመተው ፣ አንደኛው ጄኔራል ሲያናግሯቸው "ህገ መንግስቱ ጥሩ ነው፤ ተወያዩበት“ እያሉ ሲያወሩ እንደነበር ገልፀዋል። ሌ/ጄኔራል ባጫ ተጫዋች ያሉት የምዕራብ ዕዝ ሌላ ጄኔራል አቶ ስብሃትን “ስለ ሕገ መንግስቱ ተወውና አንተ እስኪ ምን ይሰማሃል“ ብሎ እንደጠየቋቸው ተናግረዋል፡፡ አቶ ስብሃት ሲመልሱ “እኔ የሚሰማኝ እኛ ከሞትን እኮ ቆይተናል“ የሚል ነው፡፡
“መቸ ነው የሞታችሁት“ የሚል ጥያቄ እንደተነሳላቸው ያስታወቁት ሌ/ጄነራል ባጫ “እኛ የሞትነውማ ኢህአዴግ የሚባለው የጠፋ ጊዜ ነው ፤ አሁን የምታደርጉት ምን እንደሆነ ልንገርህ? አሁን እያደረጋችሁ ያላችሁት የቀብር ሥነ ስነስርዓታችን እየፈጸማችሁ ነው“ ሲሉ መመለሳቸውን አንስተዋል፡፡
ምንጭ :- አል አይን
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot

Telegram
ETHIO-MEREJA®
News & Media Channel®
Addisababa, Ethiopia🇪🇹
ውድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ከዚህ የቴሌግራም ቻናል ውጪ ሌላ መረጃ የምናቀርብበት ምንም አይነት የዩቲዩብ፣ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆች እንደሌለን ለማሳወቅ እንወዳለን፣ ስለሆነም በተመሳሳይ ስም በተከፈቱ ገፆች እንዳይሸወዱ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
👉 @ethio_merejabot

በመተከል ዞን ዘጠኝ ሰዎች ተገደሉ‼️
በዛሬው እለት ጥር 8/2013 በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኤኮንቲ እና በቁጂ ቀበሌ ዘጠኝ ንፁሀን ዜጎች መገደላቸውን የአዲስ ማለዳ ታማኝ ምንጮች ተናገሩ።ማንም ሰው መሳሪያ ይዞ እንዳይንቀሳቀስ እና የሰአት ገደብ በተጣለበት መተከል ዞን ዛሬም ግድያ ተፈፅሟል ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።የተገደሉትም ዜጎች መሳሪያ መያዝ ክልክል መሆኑን ተከትሎ ራሳቸውን መከላከል በማይችሉበት ሁኔታ ወደ እርሻ ቦታቸው በማቅናት ሳሉ መገደላቸውን ነው የአዲስ ማለዳ ምንጭ የተናገሩት።
@Esat_tv1

Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ኢትዮጵያ ውስጥ በአበባ እርሻ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የ2 ቢሊዮን ፓውንድ ድጋፍ መዘጋጀቱን የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ገለጸ።
በዩናትድ ኪንግደም የኢትዮጵያን የአበባ ምርት የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጭ እድሎችን ለማስተዋወቅ በ’ቨርቹዋል’ የታገዘ የኢኮኖሚ ውይይት ተደርጓል። ውይይቱ የተካሄደው በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት ነው። መድረኩ በሀገሪቱ የሚገኙ የአበባ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን እድል ተገንዝበው መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈስሱ የሚያበረታታ መሆኑን በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ተናግረዋል ፡፡
አምባሳደሩ ኢትዮጵያ ለውጭ ኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን ገልጸዋል። ወደ ዩናይትድ ኪንግደም እየተላከ ያለው የአበባ ምርት መጠን ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መሆኑንም አመላክተዋል። አዳዲስ የኢንቨስትመንትና የንግድ እድሎችን በማስፋትና የውጪ ገበያውን ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአበባ ምርትን ለዓለም ገበያ በማቅረብ ከአፍሪካ ሁለተኛ እንደሆነች የግብርና ሚንስትር ዴኤታ ወንዳለ ሀብታሙ ገልጸዋል። ለዘርፉ ምቹ ሥነ ምህዳር፣ ለም መሬት፣ የመስኖ አማራጭና አዳዲስ የቀረጥ ነጻ ማበረታቻ መኖሩንም አስረድተዋል፡፡ የአውሮፓ ባለሃብቶች የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ሚኒስትር ዴኤታው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ (አብመድ)

❤1
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ኢትዮጵያ በጠቅላላ አገራዊ ሀብት ከአፍሪካ 6ኛ ሆነች!
10 በ2020 በጠቅላላ አገራዊ ሀብት ቀዳሚ የሆኑ የአፍሪካ አገራት ይፋ ሆኗል!
የአፍሪካ አገራት በ2020 ካስመዘገቡት ጠቅላላ አገራዊ ሀብት ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ግብጽ ስትሆን በኹለተኝነት ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ደግሞ ናይጄሪያ ናት። ኢትዮጵያ በቅደም ተከተል በደቡብ አፍሪካ፣ አልጄሪያ ሞሮኮ ተቀድማ በስድስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።ጠቅላላ ሀብቷ 272.017ቢሊዮን ዶላር ሆኖ ተመዝግቧል። (ምንጭ : አዲስ ማለዳ)

ኢዜማ ለምርጫ ማስፈፀሚያ 100 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልገው አስታወቀ፡፡
ፓርቲው በቀጣይ ለሚካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚያስችለውን የምርጫ ማስፈፀሚያ የሚሆን 100 ሚለዮን ብር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል፡፡ በዚህም የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እንዳዘጋጀ አስታውቆ በቀጣይ የካቲት 21 ቀን በግሎባል ሆቴል መርሃ ግብሩን ለማካሄድ ዝግጅት ማፀናቀቁን የኢዜማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዘላለም ወርቅ አገኘው ተናግረዋል፡፡
በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር ላይ የተዘጋጀውን ከ 10 ሺ እስከ 50 ሺ ብር የሚደርስ ትኬት በመግዛትም ደጋፊዎቹ ፓርቲውን እንዲያግዙ ጥሪ ቀርቧል፡፡ እስካሁን ድረስ ድረስ ፓርቲው በ406 በሚሆኑ ወረዳዎች እጩዎችን መምረጡን በዚሁ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡
በአጠቃላይም ፓርቲው የሚደርሱ 228 ቢሮዎችን መክፈቱን እንዲሁም በ10 ክልሎችና በ2 ቱ ከተመሰ አስተዳደሮች 435 ወረዳዎች ላይ እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ የፓርቲው የግብአት አሰባሳቢ ኮሚቴ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡(ethiofm)

መቀመጫውን እንግሊዝ ያደረገው የዓለም የጉዞና ጉብኝት ድርጅት ኢትዮጵያ ከኮቪድ 19 ስርጭት አኳያ የጉዞና የቱሪዝም ደህንነት ያለባት ነች በሚል የደህንነት ማረጋገጫ መስጠቱን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ገለጸ።
ኢትዮጵያ ለቱሪስቶች ደህንነት ምቹ ሆና የተመረጠችው የኮቪድ-19 መከላከያ ፕሮቶኮል ቀርጻ ወደ ስራ ማስገባቷ ከግምት ውስጥ ገብቶ እንደሆነም ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
አገሪቱ የተሰጣት ማረጋገጫ ቱሪስቶች የደህንነት ስጋት ሳይገባቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እንደሚያስችልና በአፍሪካ ይህ የደህንነት ማረጋገጫ የተሰጣቸው አገሮች 14 ብቻ መሆናቸውንም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገለጸው። የማረጋገጫው መገኘትም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
ኢትዮጵያ ለቱሪስቶች ደህንነት ምቹ ሆና የተመረጠችው የኮቪድ-19 መከላከያ ፕሮቶኮል ቀርጻ ወደ ስራ ማስገባቷ ከግምት ውስጥ ገብቶ እንደሆነም ሚኒስቴሩ አመልክቷል።
አገሪቱ የተሰጣት ማረጋገጫ ቱሪስቶች የደህንነት ስጋት ሳይገባቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እንደሚያስችልና በአፍሪካ ይህ የደህንነት ማረጋገጫ የተሰጣቸው አገሮች 14 ብቻ መሆናቸውንም ነው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የገለጸው። የማረጋገጫው መገኘትም በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
⭕️ባሉበት ቦታ ሆነው ሀገር ውስጥ ውስን እና ዘመናዊ እቃዎችን እኛ ጋር ማግኘትይችላሉ(ጫማዎች፣ልብሶች፣የእጅጌጣጌጦች፣ኤሌክትሮኒክሶች እናቀርባለን::
⭕️አድራሻ አዲስ አበባ 22 ከአክሱም ሆቴል ዝቅ ብሎ' ጎላጉል ባቡር መሻገርያ ጋር ትጋት ህንጻ 1ኛ ፎቅ ሱ.ቁ M-08::
⭕️ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትገኙ በፖስታ፤በመኪና አንልካለን።
⭕️ከታች ያለውን የ ቻናላችን link በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇join us/ይጫኑት👇👇
https://t.me/joinchat/SUhOPCUUscc7yHtK
📞0919998383 | 0964341513
📩@businesslidu | @businesslidu2

“የሱዳንና የግብፅ አካሄድ ከአሁን በፊት የመጣንበትን ሂደት ፉርሽ የሚያደርግ ነው” ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
የግድቡ ግንባታ በሚቀጥለው ክረምት 2ኛ ዙር ውሃ ለመያዝ በታቀደው መሰረት እየተከናወነ እንደሚገኝም አንስተዋል። ሚኒስትሩ የሕዳሴ ግድቡን የግንባታ ሂደት እና ተያያዥ ጉዳዮች በተመለከተ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሦስትዮሽ ድርድሩን በተመለከተ “የሱዳንና የግብፅ አካሄድ ከአሁን በፊት የመጣንበትን ፉርሽ የሚያደርግ ነው” ብለዋል፡፡ “ሁለቱም ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶች አላቸው” ያሉት ሚኒስትሩ “እኛ ታማኝ ሆነን እየተደራደርን ነው” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ባለፉት 7 የሕብረቱ ድርድሮች ኢትዮጵያ የምትጠየቅበት የተለየ ነገር እንደሌለም ነው ሚኒስትሩ ያነሱት፡፡ እንደ ዶ/ር ስለሺ ገለጻ ፣ በኢትዮጵያ በኩል “መጀመሪያ ስለሙሌቱ ተስማምተን እንቀጥል” የሚል ሀሳብ ቢቀርብም ፣ ግብፅ እና ሱዳን “ሙሉ ስምምነት ነው የምንፈልገው” በሚል አልተቀበሉትም፡፡
በድርድሩ ወጥ አቋም እንደሌላቸው የሚታሙት ሁለቱ ሀገራት “ስም በማጥፋት ተጽዕኖ ለማድረግ” እንደሚሞክሩም የውሃ ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የተናገሩ ሲሆን ይህ ድርጊታቸው “ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚታገለው ነው” ብለዋል፡፡የሚኒስትሩ ገለጻ እንደሚያሳየው የግድቡ ግንባታ አፈጻጸም 78 ነጥብ 3 በመቶ የደረሰ ሲሆን የሲቪል ስራዎች አፈጻጸም ደግሞ 91 በመቶ ደርሷል። የግድቡ ግንባታ ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ከነበረበት አፈጻጸም የ4.05 በመቶ ጭማሪ እንዳሳየ ሚኒስትሩ የተናገሩ ሲሆን ክረምቱ እስኪገባ በቀጣይ ወራት የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ለማሳካት እንደሚሰራም ጠቁመዋል። (አልአይን)

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አገራቸው ከአፍሪካ ህብረት ጋር ያላትን አጋርነትና ግንኙነት ለማጠናከር ቃል ገቡ።
ስልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ የመጀመሪያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸውን በተመለከተ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር ነው ይህንን ያሳወቁት።
"የኔ አስተዳደር አሜሪካ በአለም ላይ ያለንን አጋርነት ለማጠናከር እንዲሁም እንደ የአፍሪካ ህብረት ካሉ ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት እንደገና ለማጠናከር እንሰራለን" በማለት በ34ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ዋዜማ ተናግረዋል። (bbc)
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
ስልጣን ከተቆጣጠሩ በኋላ የመጀመሪያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያቸውን በተመለከተ ባደረጉት የመጀመሪያ ንግግር ነው ይህንን ያሳወቁት።
"የኔ አስተዳደር አሜሪካ በአለም ላይ ያለንን አጋርነት ለማጠናከር እንዲሁም እንደ የአፍሪካ ህብረት ካሉ ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት እንደገና ለማጠናከር እንሰራለን" በማለት በ34ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ዋዜማ ተናግረዋል። (bbc)
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ ጥር 29 ቀን 2013 ዓ.ም ወደ ላልይበላ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር ይደረጉ የነበሩ በረራዎች የተስተጓጎሉ ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሰው በረራውን የሚቀጥል መሆኑንም ገልጿል ።
በረራዎቹ ለመቀጠላቸው ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስሪያ ቤት መረጃ እንደደረሰው በጥሪ ማእከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
በረራዎቹ ለመቀጠላቸው ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት መስሪያ ቤት መረጃ እንደደረሰው በጥሪ ማእከሉ በኩል ለደንበኞቹ የሚያሳውቅ መሆኑንም ገልጿል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ የሕወሃት መወገድ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ቀንድ ሀገራት መካከል የተዘራውን የብሄር ክፍፍል መርዝ እንደሚነቅል ዛሬ ለፕሮጀክት ስንዲኬት በጻፉት መጣጥፍ ገልጠዋል፡፡
ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በትግራይ ያለውን ስጋት እንደሚገነዘቡ የጠቀሱት ዐቢይ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ በትግራይ የሰላማዊ ሰዎችን ሰቆቃ መቅረፍ ቀዳሚው ትኩረታቸው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሕወሃት ያወደማቸው የኮምንኬሽን መስመሮች ዕርዳታ አቅርቦቱን አስተጓጉለዋል፤ በዚህ ረገድ የዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
ዐለማቀፉ ኅብረተሰብ በትግራይ ያለውን ስጋት እንደሚገነዘቡ የጠቀሱት ዐቢይ፣ በትግራይ ተወላጆች ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን እና የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ በትግራይ የሰላማዊ ሰዎችን ሰቆቃ መቅረፍ ቀዳሚው ትኩረታቸው እንደሆነም ጠቁመዋል፡፡ ሕወሃት ያወደማቸው የኮምንኬሽን መስመሮች ዕርዳታ አቅርቦቱን አስተጓጉለዋል፤ በዚህ ረገድ የዐለማቀፉ ኅብረተሰብ ድጋፍ ያስፈልገናል ብለዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
በቀን 1.5 ሚሊየን ሊትር የምግብ ዘይት የማምረት አቅም ያለው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ነገ ይመረቃል።
የሃገሪቱን የምግብ ዘይት አቅርቦት 60 በመቶ የመሸፈን አቅም እንዳለው የተነገረለት ፊቤላ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከምግብ ዘይት ምርት በተጨማሪ የሰሊጥ ማቀነባበሪያ፣ ሳሙና እና የእንስሳት መኖ ያመርታልም ነው የተባለው።
በባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የተገነባው ፋብሪካው 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጭ ተደርጎበታል። ለ3 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል። በግብዓት እጥረት ምክንያት ለሙከራ ምርቱ ድፍድፍ ከውጭ የሚያስገባው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ግብዓቱን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ምርቱን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለገበያ ያቀርባል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
የሃገሪቱን የምግብ ዘይት አቅርቦት 60 በመቶ የመሸፈን አቅም እንዳለው የተነገረለት ፊቤላ ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ከምግብ ዘይት ምርት በተጨማሪ የሰሊጥ ማቀነባበሪያ፣ ሳሙና እና የእንስሳት መኖ ያመርታልም ነው የተባለው።
በባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የተገነባው ፋብሪካው 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጭ ተደርጎበታል። ለ3 ሺህ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሏል። በግብዓት እጥረት ምክንያት ለሙከራ ምርቱ ድፍድፍ ከውጭ የሚያስገባው ፊቤላ የዘይት ፋብሪካ ግብዓቱን በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን እየተሠራ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ምርቱን ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለገበያ ያቀርባል።
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የዲሞክቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ ገብተዋል!
የዲሞክራቲክ ሪፓሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሲኬዲ ትናንት ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ፕሬዝደንት ቺሲኬዲ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ይቀበላሉ፡፡ የሕዳሴ ግድቡ ድርድርም በእርሳቸው መሪነት የሚቀጥል ይሆናል፡፡ (አልአይን)
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
የዲሞክራቲክ ሪፓሊክ ኮንጎ ፕሬዝደንት ፌሊክስ ቺሲኬዲ ትናንት ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት ላይ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ፕሬዝደንት ቺሲኬዲ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበርነትን ከደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ ይቀበላሉ፡፡ የሕዳሴ ግድቡ ድርድርም በእርሳቸው መሪነት የሚቀጥል ይሆናል፡፡ (አልአይን)
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
በዛሬው እለት ባህርዳር፣ ወላይታ ሶዶ፣ ወልዲያ፣ ደባርቅ እና ሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ።
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መድኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 5,117 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 5,310 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ወልዲያ ዩንቨርስቲ በመደበኛው፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2785 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።