G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
በፈተና_ጊዜ_የሚፈጠርን_ጭንቀት_ወይም_ቴንሽንን_ልንቆጣጠር_የምንችልባቸው_ዘዴዎች!.docx
19.3 KB
በፈተና ጊዜ የሚፈጠርን ጭንቀት ወይም ቴንሽንን ልንቆጣጠር የምንችልባቸው ዘዴዎች!

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
“እኛ ጁንታ አይደለንም፤ በኃላፊነት ነው የምንሰራው፤” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ(ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ትግራይ ክልል በተካሄደ የህግ ማስከበር ሂደት ንጹሓን እንዳይጎዱ ያላሰለሠ ጥረት ሲደረግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ እናም የሃገር መከላከያ ሰራዊቱ በሰራው ህግ የማስከበር ሥራ ወቅት አንድም ሰው ላይ ችግር አልፈጠረም ነው ያሉት፡፡
ይህም መከላከያ ሠራዊቱ በቂ እና ጠንካራ ብቃት ያለው መሆኑን እንደሚያሳይ ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

አየር ሀይሉ ዒላማዎችን ለይቶ በእያንዳንዱ ዒላማ እየፈረመ፣ ኃላፊነት እየወሰደ እንደሚወሰን ተናግረዋል፡፡ ጁንታው ከታጠቀው ሮኬት ቁጥር በላይ መከላከያ ሀይሉ ቢኖረውም ህግ ወደ ማስከበሩ ሂደት ሲገባ አንድም ሮኬት ወደ ትግራይ ክልል አለመተኮሱን አረጋግጠዋል፡፡ “እኛ ጁንታ አይደለንም፤ በኃላፊነት ነው የምንሰራው፤” ሲሉ መቀሌ ከተማን ጭምር ስንቆጣጠር ንጹሓን ሳይጎዱ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ፡፡

SHARE | ሼር
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━
Forwarded from Finance Today
የቀድሞው የሠሜን ዕዝ አዛዥ ሳይመረዙ እንዳልቀሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ!!

በሠሜን ዕዝ ላይ ጥቃቱ ከመፈጸሙ በፊት የዕዙ አዛዥ ሳይመረዙ እንዳልቀረ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስተሩ እንዳሉት፤ የሠሜን ዕዝ አዛዥ የነበሩት ጄነራል ድሪባ ግጭቱ ከመፈጠሩ ከሁለት ሳምንት በፊት "ስብሰባ ከእነሱ ጋር ውሎ፣ ምሳ ከበላ በኋላ ታሞ እራሱን ስቶ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ገብቷል" ብለዋል።

ጨምረውም ከጄነራሉ ጋር የነበሩ ሰዎች "አቅምሰውት ነው" የሚል መረጃ እንዳመጡና እንዲህ ያለው ጉዳይ በህክምና እስኪጣራ ድረስ እንዲቆይ "ብለን አፈንነው" ካሉ በኋላ፤ ጄነራል ድሪባ ባጋጠማቸው ችግር ምክንያት አስካሁን አገግመው ወደሥራቸው እንዳልተመለሱ ገልጸዋል።

ይህንንም ተከትሎ ጄነራሉን በመተካት የሠሜን ዕዝን የሚመራ ጄነራል ለመመደብ መገደዳቸውንና የህወሓት አመራሮች አዲሱን ተሿሚ አንቀበልም ማለታቸውን በመግለጽ "ለካ እሱን በማኮላሸትና የሚመጣውን እምቢ የማለት ፍላጎት ነበረ" ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህም በኋላ "የሠሜን ዕዝ አዛዥ ጄነራል ድሪባ ታመሙ፣ አዲስ የተመደበውን ጀነራል አንቀበልም አሉ ከዚያም ጥቃት ፈጽመው የዕዙን ምክትል አዛዥ ጀነራል አደምን አፈኑ" ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት ከምክር ቤቱ አባላት ስለወቅታዊ ጉዳዮች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ላይ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
“ወደ ሱዳን ከተሰደዱ ወጣቶች መካከል ማይካድራ ላይ በተካሄደው ጭፍጨፋ ላይ የተሳተፉ ይገኙበታል የሚል ጥርጣሬ አለን!!

አምባሳደር ሬድዋን ይህን ያስታወቁት የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ከሬውተርስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው።

በትግራይ ክልል ከተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ እስካሁን ከ40 እስከ 43 ሺህ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ድንበር ተሻግረው ሱዳን መግባታቸውን አምባሳደሩ ተናግረዋል።

አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ለስደት የበቁት በተለይ ወደ 700 ሰዎች ከተጨፈጨፉበት የማይካድራው ክስተት ጋር ተያይዞ መሆኑንም ገልጸዋል።

በግጭቶች ወቅት አብዛኛውን ጊዜ ለስደት የሚዳረጉት ሴቶች፣ ሕፃናት እና አረጋውያን ናቸው ያሉት አምባሳደር ሬድዋን፣ ከማይካድራው ክስተት ጋር በተያያዘ ግን የሴቶች እና የሕፃናት ቁጥር አነስተኛ መሆኑን፣ የወጣቶች ቁጥር በተቃራኒው እጅግ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

በማይካድራው ጭፍጨፋ ከሕወሓት ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ በተጨማሪ መደበኛ ያልሆነ አደረጃጀት ውስጥ የነበሩ ወጣቶች የተሳተፉበት መሆኑን በዓለም አቀፍ እና በሀገር ውስጥ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት መረጋገጡን ገልጸዋል።

“ማይካድራ ለሱዳን ቅርብ በመሆኗ ወደ ሱዳን ከገቡት ስደተኞች መካከል በዚህ ድርጊት ላይ የተሳተፉ ወጣቶች ይገኙበታል የሚል ጥርጣሬ አለን ብለዋል” አምባሳደሩ።

ስለዚህ የእነዚህን ስደተኞች ማንነት እና ምንነት በመለየት ሥራ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሱዳን ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from About education
#ለ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት‼️

- የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ህዳር 24 እና 25

-የዋቻሞ ዩንቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከህዳር 21 እስከ ህዳር 23/13 ድረስ እንዲገቡ

-የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎችን ከ
ህዳር 28 -29 እንዲገቡ

-የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ህደር 24 ና 25 ሪፖርት እንዲታደርጉ ተብሏችኋል።ህዳር 26 በሁሉም ካምፓሶች Orientation ይሰጣል።
ህዳር 28 ክላስ ይጀመራል።

- የዲላ ዩኒቨርስቲ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በግቢ ደረጃ የተማሪዎችን የመግቢያ ቀን በተመለከተ የተወሰነ ነገር የለም:: ዛሬ ወይም ነገ የሚወሰነውን ውሳኔ ቀድመን የምናሳውቅ ይሆናል።

-ለኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርስቲ ተመራቂ ተማሪዎች
የምዝገባ ቀን ህዳር 25 እና 26፣2013 ሲሆን ትምህርት የሚጀመረው ህዳር 28፣2013

@NEAEA_nea

for your comments 👇👇

@ministry_of_educationbot
"ዶክተር ደብረጽዮን ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል"መባሉን አስተባበሉ።

የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል «ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል» ተብሎ የተነገረዉ ዘገባ «ሐሰት ነው» በማለት መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ደብረጽዮን «አሁንም በመቀሌ ከተማ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር እየተዋጋን ነው።» ብለዋል። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ባለፈው ቅዳሜ የመቀሌ ከተማን መቆጣጠሩን አስታውቋል።

በወቅቱ ደብረጽዮን የመቀሌ ከተማን ለቀው መውጣታቸውን ለሮይተርስ በላኩት አጭር የጽሁፍ መልዕክት አረጋግጠዋል። የሕወሓቱ መሪ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ወደ ደቡብ ሱዳን ሸሽተዋል የሚሉ ዘገባዎች መውጣታቸውን ተከትሎ በሰጡት መልስ« ከትግራይ ክልል አልወጣሁም» ሲሉ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ ቃል አቃባይ ቢለኔ ስዩም በበኩላቸው «የፌዴራል መንግሥት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በማረጋጋት ስራ ላይ ተጠምዷል፤ ተበታትኖ ላለ ወንጀለኛ ንግግር መልስ መስጠት ጉዳያችን አይደለም » ሲሉ ዶክተር ደብረጽዮን «በመቀሌ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ውግያ ቀጥለናል» ብለው መናገራቸውን ያጣጣሉበትን ሃሳብ ለሮይተርስ ነግረዋል።
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot
በትግራይ ክልል የባንክ እና ቴሌኮም አገልግሎቶች ወደ ቀድሞ አገልግሎታቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አሳሰበ።

ኮሚሽኑ የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በሰብአዊ መብቶች የሚመሩ መሆን አለባቸውም ብሏል።

ቀደም ሲል በኢሰመኮ የቀረቡ፣ በተለይም በሲቪል ሰዎች ላይ ማንኛውም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ ጥንቃቄ እንዲደረግ አጽንዖት የሚሰጡት ምክረ ሃሳቦችንና ጥሪዎችን በማስታወስ፣ በቀጣይ የሚደረጉ የመልሶ ማቋቋምና መልሶ ግንባታ ተግባራት በፌዴራል መንግሥቱ ሰብአዊ መብቶችን የማክበርና የመጠበቅ ግዴታ የሚመራ እንዲሆን አሳስቧል።

የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙና ተገቢው ሰብአዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን የተቋረጡ የቴሌኮሙኒኬሽን፣ ውሃና ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ መሰል መሰረታዊ አገልግሎቶች እንዲሁም የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ አካላት አገልግሎት ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ ማሳሰቡን ኮሚሽኑ ለኢትዮ ኤፍ ም በላከው መግለጫ ገልጿል።

እንዲሁም በግጭቱ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ሰዎች ወደ መደበኛ መኖሪያቸው እንዲመለሱ እና የተጠፋፉ ቤተሰቦች እንዲገናኙ የሚያስችል አስፈላጊ የሆነው የሎጂስቲክስና የሰብአዊ እርዳታ መሰረተ ልማት እንዲደራጅም ጠይቋል።

ተጠያቂነትን ለማረጋገጥና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የሰብአዊ መብቶች ጥሰትና ያስከተለውን ሰብአዊ ቀውስ የሚመመረምር ገለልተኛና ግልጽ የሆነ አሰራር ከወዲሁ እንዲተገበር፣ ተዓማኒና አካታች የሆኑ የእርቅና የፍትሕ ሂደቶች በጊዜ ሊደራጁ ይገባልም ብሏል።

በተጨማሪም ኢሰመኮ በትግራይ ተወላጆች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረገ መድሎዎና መገለል ስለመድረሱ የሚቀርቡለት ቅሬታዎች በከፍተኛ ደረጃ እያሳሰበውና እየተከታተለው መሆኑን ገልጿል።
(ኢትዮ ኤፍ ኤም)
---------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot
ከጠቅላይ ሚኒስተር ጽሕፈት ቤት የወጣ ማስተካከያ
____-___________________-_--
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፓርላማ ባደረጉት ንግግር ወቅት ከዓመታት በፊት አባይ የተባለ ከህወሓት ጋር ግንኙነት ያለው የመገናኛ ብዙሀን ተቋም መኖሩን ጠቅሰዋል። የተጠቀሰው ተቋም በዩቲዩብ ሥራውን በመከወን ላይ ከሚገኘው እና በቅርቡ የቴሌቪዥን ስርጭት ከሚጀምረው አባይ ሚዲያ ጋር አንድነት የለውም። ሁለቱ ተቋማት የተለያዩ እና ግንኙነት የሌላቸው መሆናቸውን እናሳውቃለን።

During Prime Minister Abiy Ahmed’s parliamentary address, he had mentioned a media entity named Abay as created by and affiliated with TPLF several years back. Please note that this is not to be confused with Abbay Media which is a new digital media currently operating on YouTube and soon to begin TV broadcast. These are to separate and unrelated media entities.

(PMOEthiopia)
--------------------------------------------------
ክቡራን ቤተሰቦች ሀሳብ አስተያየታችሁን የዜና የመረጃ ጥቆማችሁን ከሰር ባለው ሊንክ አድርሱኝ:: አመሰግናለሁ
አቤል ብርሀኑ (የወይኗ ልጅ)
👉@abel21bot
Channel name was changed to «ወቅታዊ ሹክታዎች👂🦻👂»
ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ባለፉት አራት ወራት ወስጥ ከ624 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪብሄራዊ ምክርቤት ፅፈት ቤት አስታወቀ።

የግድብ የመጀመርያ ውሃ ሙሊት በመጠናቀቁ የህዝቡን ተነሳሽነትም እደጨመረ ተገልጿል።


የፅፈት ቤቱ ህዝብ ግንኙነት እና የሚዲያ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሀይሉ አብርሀም እደገለፁት ይህ ብር የተሰበሰበው ከሐምሌ 2012 እስከ ጥቅምት ወር መሰብሰቡን ገልፀዋል።
ዳይሬክተሩ በ2012 በጀት አመት 747 ሚሊወን ብር መሰብሰቡን አስታውሰው
በተጨማሪም 155 ሚሊወን ብር ደግሞ በስጦታና በቦንድ ግዥ እንደተሰበሰበ ገለፁ።



ፅፈት ቤቱም ሚዲያን በመጠቀም ህዝቡን እንዳነሳሳና ገልህ ሚና እንደተወጣ አንስተው መቀጠል እንዳለበትም ገለፁ።
Forwarded from About education
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በጭሮ ከተማ የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ማዕከል ከፈተ።
===============================
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በጭሮ ከተማ ፖሊ-ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ  በMBA እና Developmental Economics የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማር ስራውን የጀመረ ሲሆን በመክፈቻው ፕሮገራም ላይ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ የም/ሐረርጌ ዞን አስተዳደር ተወካይ፣ የዞኑ የቴክኒክና ሙያ ኤጄንሲ ኃላፊ፣ የዩኒቨርሲቲው መካከለኛ ሃላፊዎች እና መምህራን መገኘት ችለዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የአካ/ጉ/ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም ባደረጉት ንግግር የድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ማዕከሉ መከፈት ታሳቢ ያደረገው በመደበኛ ትምህርት መማር ለማይችሉ ተማሪዎች እድሉን በመጠቀም እራሳቸውንና የማህበረሰባቸውን ችግር ፈቺ ፍላጎት ጥናት መሰረት ያደረገ መሆኑን ገልጸው ዩኒቨርሲቲው የማህበረሰቡን ፍላጎት ማዕከል ያደረገ ፕሮገራሞችን ለማሳደግ አበክሮ እንሚደራ ገልጸዋል ፡፡

@NEAEA_nea
Forwarded from About education
ለወለጋ ዩኒቨርስቲ የተመራቂ ተማሪዎች ጥሪ
===============================

ሁሉም ተመራቂ ተማሪዎች ታህሳስ 3 እና 4, 2013 ዓ.ም የተማሪ መታወቂያችሁን በመያዝ በየካምፓሶቻችሁ በመገኘት እንድትመዘገቡና ሰኞ ታህሳስ5, 2013ዓ.ም ትምህርት እንድትጀምሩ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ ያደርጋል፡፡

ማሳሰቢያ❗️
1. ሁሉም ተማሪ ሁለት የሚታጠብ የፊት መሸፈኛ ማስክ እና
2. ለዲጂታል መታወቂያ 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ መያዝ ይጠበቅባቹሃል።


@NEAEA_nea
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
በአማራ ክልል ክልል አቀፍ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከታህሳስ 12 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅም አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በፈተናው ከ415 ሺህ በላይ ተማሪዎች ይሳተፋሉ፡፡
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━
ሽሬ ጊዜያዊ ከንቲባና ምክትል ከንቲባ ተሾመላት‼️

በሽሬ ከተማ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ከንቲባ በመሆን የተመረጡት መምህር ሐጎስ በርሄ ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።“ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን በከተማዋ ሰላም እንዲሰፍን፣ ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲሳለጡና ልማት እንዲከናወን እሰራለሁ” ብለዋል።የጊዜያዊ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሆነው የተመረጡት ኢንጂነር ጀሚል ሙሐመድ በበኩላቸው ሕዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት በብቃት ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

በከተማው ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋሙ ለሕዝቡ መረጋጋት እንደሚያመጣ ጠቁመው፤ ሰላም ለማረጋገጥ ሂደትም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።በከተማው የአቅም ግንባታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው የተመረጡት መምህርት ንግሥቲ ፋንታሁንም ህዝቡን በቅንነትና ታማኝነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።የከተማው ነዋሪዎች ከጎናቸው በመቆም ድጋፍና እገዛ እንዲያደርጉላቸውም አመራሮቹ ጠይቀው፤ ቀደም ሲል በህወሃት ዘመን የነበረው በመተዋወቅ፣ በዝምድናና በኔትወርክ መስራት እንደማይደገም አረጋግጠዋል ተብሏል።የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው የተሾሙት ዶክተር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ህዝቡን በማወያየት ላይ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
ሰበር ዜና‼️

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ::

በህግ ከሚፈለጉት የህወሓት አባላት መካከል ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ እንደሰጡ ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
#EXAM_TIPS

♦️Pre-exam tips:-

Stop studying when the exam lefts few days rather keep working on examples and questions&when u found some hard ones look back at the sections and capture some informations!

A day before the exam stay calm&sleep well to help out a good mood on exam day!

If you ain't interested of studying much hours listen carefully while the teacher teaches and capture precised and main notes!

Chewing the same flavored gum both at time of studying and exam can help you remember what you read!

Don't eat much food before the exam, it puts in stress!
And even taking exams in empty stomach help you concentrate!

Try not to be panic, it is not the end of the world, but just an exam to evaluate your knowledge and ability!

♦️On exam tips:-
Make your full concentration on the exam till the end!

Don't feel dizzy if the questions are hard or you don’t know them, you can change nothing, just keep working to your capacity.

Don't spend much time on a question, simply jump it & keep doing on the others, it worthes you at last!

Whenever there are alternatives try eliminating choices which you are sure can't be answers, as a paveway to increase your chance of getting the correct answer!

Try checking your answers if you finish before time,it's the best way to retrack unexpected errors you made!

If you are almost out of time then keep filling the answers ordinarily as you can get some correct ones!

♦️After exam tips:-
If you are heading to next exam and you did have a break never ever cross check or take corrections of your former exam that it will put you in a bad mood for the next exam when you figured out you did some unexpected mistakes!

REMEMBER you can't change anything after you returned the exam so look forward the upcoming ones!

🌺 GOOD LUCK 😊

#share
@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ:- (1)

-አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ/ም ተመራቂ፣ የሕክምና (Medicine) 4ኛ እና 5ኛ ዓመት እንዲሁም የሕግ 4ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ ከኅዳር 24 - 27 እንደሆነ ገልጿል። መደበኛ ትምህርት ኅዳር 28 ይጀምራልም ብሏል።
የዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ:-

- የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች #ብቻ የመግቢያ ቀን ከታህሳስ 1 እና2 መሆኑን ገልጾልናል። ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑንም አስታውቋል።

- የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ቅድመ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች #ብቻ ህዳር 29 እና 30 በሁሉም ግቢዎች በአካል በመገኘት ሪፖርት እንዲያደርጉ አስታውቋል።

- የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ድግሪ ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች #ብቻ ምዝገባ ህዳር 30 እና ታህሳስ 1 ብቻ መሆኑን ገልጿል። ታህሳስ 2 ትምህርት እንደሚጀምርም አስታውቋል።

- የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የዕጩ ተመራቂ የመደበኛ ተማሪዎች #ብቻ ታህሳስ 5 እና 6 በትምህርት ክፍላቸው ቀርበው ሪፓርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።
-የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመራቂ ተማሪዎቹን የመግቢያ ቀን ታህሳስ 01-02/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል።

- የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ በመደበኛው መርኃግብር እጩ ተመራቂ ተማሪዎቹን ከታህሳስ 5- 6 ድረስ በዩኒቨርስቲው በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ አድርጓል።

- የደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ የተመራቂ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 3 -4 መሆኑን አስታውቋል። ተማሪዎችም በአካል በመገኘት ሪፓርት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

- የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተመራቂ ተማሪዎች፣ የሦስተኛ ዓመት የጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች፣ ለክረምት የጤና ሳይንስ ተመራቂ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ታህሳስ 3 እና 4 መሆኑን አስታውቋል።

- የሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎች መመዝገቢያ ቀን ህዳር 29 - ታህሳስ 1 ሆኗል። ታህሳስ 2 ለተማሪዎች ስለ ኮቪድ 19 ስልጠና ከተሰጠ በኋላ ታህሳስ 5 ትምህርት የሚጀመር ይሆናል።

- የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ምዝገባ ታህሳስ 3 እና 4 እንደሆነ አስታውቋል። ተማሪዎች ሲመጡም የሚታጠብ የፊት መሸፈኛ ማስክ እና ሌሎች ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚያግዙ ነገሮችን እንዲሁም ለዲጂታል መታወቂያ 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ (በሶፍት ኮፒ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።

- የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹ ህዳር 26 ና 27 ግቢ በመገኘት በአካል ሪፖርት እንዲያደርጉ አስታውቋል። ህዳር 28 ለተማሪዎች ስለ ኮሮና ቫይረስ ግንዛቤ ማስጨበጫ(ኦረንቴሸን) ከተሰጠ በኋላ ህዳር 29 ትምህርት ይጀመራል ብሏል።

- የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ምዝገባ ከህዳር 28 -29 መሆኑን አስታውቋል። ታህሳስ 1 ትምህርት የሚጀመር መሆኑንም ገልጿል።

ETHIOMEREJA - MEDIA CHANNEL
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ:- (2)

-የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች (2 ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ) ዳግም ቅበላ ህዳር 25 እና 26 (አርብ እና ቅዳሜ) ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆን ተወስኗል። ስለዚህ ከላይ በተገለፁት ቀናት ወደ ዩኒቨርሲቲ እንድትገቡ ተብሏል። ትምህርት ህዳር 28/2013 ይጀምራል።

- የጅማ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ተመራቂ ተማሪዎች ምዝገችሁ ህዳር 28 ፣29 እና 30/2013 ዓ/ም ነው። በዚህ ምዝገባ ቀናት የሁሉም ዓመት የትያትር፣ መዚቃ እና ቪዡዋል አርት፣ ነባር PGDT እንዲሁም የ3ኛ ዓመት የባዮሜዲካል እና የ4ኛ ዓመት የማቴሪያል ሳይንስ እና የኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባችሁብ እንድትፈፅሙ ተብሏል። የነባር እና አዲስ ድህረ ምርቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ከላይ በተጠቀሱት ቀናት ምዝገባችሁን እንድትፈፅሙ ተብሏል።

- የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ብቻ መግቢያ ቀን ህዳር 26 እስከ ህዳር 28 ነው።

- የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ሐሙስ እና አርብ ማለትም 24 እና 25/03/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል።

- የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች ከህዳር 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት እንደሚጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

- የመቱ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎችን
ህዳር 28 -29 የጠራ ሲሆን ትምህርት የሚጀምርበት ቀንም ታህሳስ አንድ መሆኑን አስታውቋል።

- የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች መግቢያ ህዳር 25 እና 26/03/2013 ዓ.ም መሆኑን አስታውቋል። ህዳር 28 ትምህርት እንደሚጀመርም ገልጿል።

-የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎች እና ለጤና ሳይንስ ተማሪዎች (2 ኛ ዓመት እና ከዛ በላይ የሆናችሁ) ምዝገባ ህዳር 25 እና 26 (አርብ እና ቅዳሜ) ቀን 2013 ዓ/ም መሆኑ ተገልጿል። ጥሪው የጤና ሳይንስ 1ኛ አመት ተማሪዎችን አይመለከትም ተብሏል።

[የሌሎች ዩኒቨርስቲዎች እንደወጡ እናሳውቃለን]

ETHIOMEREJA - MEDIA CHANNEL
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━━━⊰
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
"‹‹ሕወሓት የዘራውን እያጨደ ነው››
ከጊዜ ኋላ ሲራመድ የነበረውና ከስህተቱ ለመማር ያልቻለው ሕወሓት በመጨረሻም የዘራውን መረራ ፍሬ እየሰበሰበ ነው" የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ዑመር፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በአልጀዚራ ላይ ባሰፈሩት ሀተታ እንደ ሕወሓት ያሉ ፓርቲዎች የመጨረሻ እጣ ፈንታም ከዚህ እንደማያልፍ ነው የጠቀሱት፡፡

-‹‹በኢትዮጵያ ያለው ግጭት እና የሕወሓት ከመጠን ያለፈ ብሔርተኝነት›› በሚል ርዕስ የወጣው የሙስጠፌ ጽሑፍ፤ ከሕወሓት አፈጣጠር ጀምሮ የነበሩ ብልሽቶችን ዳሷል፡፡
ሕወሓት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ በጋብቻ፣ በንግድ፣ በሃይማኖትና በባሕል እጅግ የተሳሰረ የመሆኑን እውነታ በመካድ የማይታረቅ ልዩነት እንዳላቸው አድርጎ ሲሰብክ ኖሯል ሲሉ ነው የከሰሱት፡፡

-በዚህም አጥፊና ከፋፋይ የሆነውን ‹‹የእኛ እና እነሱ›› ትርክትን ፈጥሯል ይላሉ፡፡
ሀተታው ሲቀጥል የትግራይ ሕዝብ በጠላት እንደተከበበ አድርጎ በመስበክ በሚያስተዳድራቸው የመገናኛ ብዙኃን በኩልም ተከታታይ የጦርነት ዘጋቢ ፊልሞችን ሲያሳይ ስለመክረሙ አስታውሷል፡፡

-ሕወሓት ራሱን የብሔር፣ ብሔረሰቦች ሰላም ብቸኛ ጠባቂ አድርጎ ሲያስፈራራ መኖሩንም ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ያነሱት፡፡ሕወሓት ለዓመታት በበላይነት ይዞት የነበረውን የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን በ2010 ካጣ በኋላ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የተጀመሩ አገራዊ ማሻሻያዎችን ለመቀልበስ የሚችለውን ሁሉ አድርጓል ሲልም ጽሑፉ ይነበባል፡፡

-በመላ አገሪቱ ግጭቶችን በተለያዩ መንግዶች ሲደግፍ እንደነበር በመክሰስ፤ በአገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ኢትዮጵያ ሕግ ወደማስከበሩ ዘመቻ መግባቷንም ያስታውሳል፡፡(አሐዱ ቴሌቪዥን)
@ethio_mereja
🎲 እስካሁን ድረስ ለተመራቂ ተማሪዎች መግቢያ ቀን ያሳወቁ ዩኒቨርስቲዎች‼️

*ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 21-23
* ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 24 - 25
*አምቦ ዩኒቨርሲቲ ህደር 24 እና 25
*ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 23
*መቱ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 28 እና 29
*ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 እና 26
*ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 እና 26
* ኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 ና 26
* ዲላ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 3 እና 4
* ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ታህሳስ 3 እና 4
* ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 25 እና 26
* AASTU ህዳር 26 ና 27
* ጅማ የዩኒቨርስቲ ህዳር 28 -30
* ሐረማያ የዩኒቨርስቲ ህዳር 29-ታህሳስ 01
* አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከህዳር 24-27
* Woldia University ህዳር 30 ና ታህሳስ 1
* ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ህዳር 29 እና 30
* መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተህሳስ 5 ና 6
* ጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ህዳር 26 እስከ 28
* አሶሳ ዩኒቨርስቲ ታህሳስ 03 ና 04
* Mettu University ህደር 28-30
* ሰላሌ ዩንቨርስቲ ህዳር 23


↘️ የሌሎችንም እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል::
@Timhrtministers
@Timhrtministers