G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
‎"እውነት ህግ ካለ ርሸና የፈጸሙና ያስፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ ይገባል " - ነዋሪዎች

ከ13 ቀናት በፊት ‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ፦
° ተመስገን ጌታቸው
° ይታገሱ አሰግደው
° ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ወጣቶች በትራንስፖርት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው መገደላቸው ይታወቃል።

ቃላቸውን ለቲክባህ የሰጡ የአከባቢው ኗሪዎች፤ "ሶስት ወጣቶች ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው እጃቸው የፊጢኝ ታስሮ በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽነው አስክሬናቸው በትውልድ አካባቢያቸው መገኘቱ እውነት ነው " ብለዋል።

የነዚህ ወጣቶች በፀጥታ ኃይሎች መገደልና ከግድያው በኋላ የሟቾቹ አስከሬን እንዳይነሳ ተብሎ በጅብ እንዲበላ መሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ፣ ሀዘንና ስጋት መፍጠሩን ተናግረዋል።

" አስክሬናቸው ከሌሊቱ 11 ሰዓት አከባቢ በትውልድ ቀያቸው ተጥሎ ማንም እንዳያነሳና እንዳይቀብራቸው ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ በኋላ አስክሬናቸው ለጅብ ተጋልጦ እንዲቆይ ሆኗል፤ ከሶስቱ የአንዱ ቤተሰቦቹ አንስተው ቀብረዋል " ሲሉ አብራርተዋል።

‎ነዋሪው " ‎'ፋኖ ናቸው' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ነው የሰማነው። ይህ ‎በየትኛውም መመዘኛ ትክክል አይደለም፤ ጥፋትና ወንጀል ፈጽመው ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ ይገባ ነበር። እውነትም ህግ ካለ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን የረሸኑ በህግ ሊጠየቁ ይገባል " ብለዋል።

ነዋሪዎች የተጎጂ ቤተሰቦች እየሆነ ያለውን ነገር ወጥተው ለመናገርና መረጃ ለመስጠት ይፈራሉም ተብሏል።
@Gtutorialclass
2
ድርቅ‼️
በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ከባድ የድርቅ አደጋ ምክንያት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት እያለቁ መሆናቸውን ከየአካባቢው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
በትግራይ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች፣ በአማራ ክልል ዋግምራ ዞን፣ በሰሜን ጎንደር ጠለምትና የበየዳ ቆላማ አካባቢዎች የክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የቁም እንስሳት እልቂት ይበልጥ እየከፋ መጥቷል።
በተለይም በሰሜን ጎንደር ጠለምት ቀጠና ከአስራ አንድ ሺህ (11,000) በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች እንዲሁም የበግና ፍየሎች ማለቃቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በአብዛኞቹ አካባቢዎች በዚህ ክረምት የተዘራና የበቀለ እህል ጨርሶ አለመኖሩን የአዩዘሀበሻ የመረጃ ምንጮቻች ገልጸዋል።
የድርቁ ስፋትና የሚያሳድረው ተፅዕኖ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከፍተኛ እየሆነ የመጣ ሲሆን፣ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።
👉ምስሉ ጠለምት ከሚገኙ የአዩዘሀበሻ ቤተሰቦች የተላከ ነው።
👉ሼር በማድረግ የሰብዓዊነት ግዴችሁን ተወጡ
(አዩዘሀበሻ)
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@Gtutorialclass
😢2🤔1
ምፅዋ በካርጎ አውሮፕላኖች ተጨናንቋል‼️
ሱዳን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ እያራገፈች ነው‼️
ጀነራል አል_ቡርሃን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ አውሮፕላን ማረፊያ በብዛት  እያራገፈ እንሚገኝ በሳተላይት ምስል ተረጋግጧል ።
ከሱዳን ተነስተው በምፅዋዋ አውሮፕላን ማረፊያ ያረፉ በርካታ የጭነት አውሮፕላኖች ከባባድ መሳሪያዎችን፣ ተወንጫፊ ሚሳይሎችንና ጥይት እያራገፉ መሆናቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳይተዋል።
ከሱዳን በተጨማሪ ከቤላሩስ እንዲሁም ከኢራን የመጡ የጭነት አውሮፕላኖች ከሁለት ቀን በፊት ምፅዋ እንዳረፉ ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል።
(አዩዘሀበሻ)
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@GTUTORIALCLASS
2
የፖለቲካ እስረኞችን ከማይካድራ ጭፍጨፋ ፍርደኞች ጋር በይቅርታ አንድ ላይ ለመፍታት መታቀዱ ተቃውሞ አስነሳ‼️
በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በማረሚያ ቤቶች ተይዘው የሚገኙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከመንግስት የቀረበላቸውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም በማለት ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
መንግስት የፖለቲካ ታሳሪዎቹን ከስድስት ዓመታት በፊት በማይካድራ ከተፈፀመው ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ "በሰብአዊ ፍጡር ላይ የሚፈፀም ወንጀል ተከሰሱ እና ከተፈረደባቸው አካላት ጋር በአንድ ላይ አደባልቆ በይቅርታ ለመፍታት ማቀዱ ታሳሪዎቹን አስቆጥቷል።
የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት የፖለቲካ እስረኞቹ ይህንን ውሳኔ "እጅግ ዘግናኝ የሆነ ግድያና ጭፍጨፋ ፈጽመው ፍርድ ካገኙ ግለሰቦች ጋር እኩል በማሰለፍ በሕዝብ ዘንድ በተመሳሳይ እይታ እንዲታዩና የወንጀሉ ተካፋይ ተደርገው እንዲሳሉ ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ነው" ሲሉ አውግዘዉታል።
ታሳሪዎቹ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህንን የይቅርታ ሀሳብ አዘጋጅቶ ለመንግስት ማቅረቡን በመግለጽ የኮሚሽኑ እርምጃ እጅግ እንዳዘናቸውና ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ተናግረዋል።
መንግስት በሚመጣው አዲስ ዓመት ከ1,300 በላይ ሰዎችን በይቅርታ ለማስፈታት አቅዶ የይቅርታ ደብዳቤ እያስፈረመ ይገኛል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በርካቶች የቀረበላቸውን አነጋጋሪ የይቅርታ ሰነድ ቢፈርሙም 30 የሚሆኑ ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞች ግን "አልፈርምም" በማለት አቋም ይዘዋል።
የቀረበው የይቅርታ ሰነድ አወዛጋቢ ቃል የሚከተለውን ያካትታል፦ «በአማራ ክልል ፅንፈኛው ቡድን በሚያደርገው ትግል ላይ መሳተፌ ስህተት መሆኑን በማመን መንግስትንና ሕዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ።

@gtutorialclass
😢1
በ148 ቀበሌዎች ዝናብ የለም‼️

በትግራይ ክልል በድርቅና በወታደራዊ ምልመላ ምክንያት ህዝቡ ለእንግልት መዳረጉ ተነግሯል።

​የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል በሚገኙ 148 ቀበሌዎች ላይ አንዲት ጠብታ ዝናብ እንኳ አልዘነበም ብሏል።

በ​ድርቁ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት እያለቁ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ይፈልጋቸዋል ተብሏል።እርዳታ እንደምንም ቢገባም "ለታጣቂ ይሰጣል" የሚል ስጋት በረጅዎች ዘንድ መኖሩ ተጠቁሟል።

​ ህወሓት ወጣቶችን በማፈስ ወደ ጦርነት እያሰማራ ይገኛል መባሉን ተከትሎ፣ የትግራይ ህዝብ በአንድ በኩል በረሃብና በድርቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በጦርነትና የልጆቹን ህይወት በማጣት እጥፍ ድርብ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑ ዘገባው አመልክቷል።
አዩ
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@GTutorialclass
🤯1
ውጤት ዛሬ ይለቀቃል‼️
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር በላከልን መረጃ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል የሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ከሰዓት በኋላ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቅሷል።

በዓመቱ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 62 በመቶ የሚሆኑት በኦንላይን ፈተናውን ወስደዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን አጠቃላይ 563 ሺህ 501 ተማሪዎች በ607 የፈተና ማዕከላት ውስጥ የተፈተኑ ሲሆን ፈተናው በ6 ዙሮች ተሰጥቷል።

ከዘንድሮ ጠቅላላ ተፈታኞች መካከል 306 ሺህ 456 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ 257 ሺህ 45 ደግሞ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ነበሩ፡፡

ውጤቱን በተመለከትም ትምህርት ሚኒስቴር በ9 ሰዓት መግለጫ ይሰጣል፡፡
የውጤት ማሳያ ሊንክ በዚሁ ቻናል ይቀርባል፣join now.
Via:- Shegerfm
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
#የ12ኛ ክፍል ውጤት‼️

ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው።

ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው።
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
አዩዘሀበሻ
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
1
565 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ሲሆን ከእዚህ ውስጥ 98 ትምህርት ቤቶች በአማራ ክልል የሚገኙ ናቸው።
[አዩዘሀበሻ]
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና ዋና መረጃዎች‼️

📊 የማለፊያ ውጤት
• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።
• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ነው።
• 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

🏫 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች
• አምና — 62
• ዘንድሮ — 88
➡️ በዚህ ዓመት 26 ትምህርት ቤቶች ጨምረዋል።

💻 በፈተና አሰጣጥ ዘዴ
• በኦንላይን የተፈተኑ — 18.37% አልፈዋል።
• በወረቀት የተፈተኑ — 4.2% አልፈዋል።

🏆 የክልሎች የማለፊያ ምጣኔ
🥇 አዲስ አበባ — 32.4%
🥈 ሀረሪ — 22.76%
🥉 አማራ — 15%
• ድሬዳዋ — 11.92%
• ትግራይ — 11.2%
• ጉምዝ — 10.53%
• ደቡብ — 9.2%
• ሶማሌ — 9%
• ሲዳማ — 6.95%
• ጉምዝ — 6.1%
• ደቡብ ኢትዮጵያ — 4.2%
• 3.74% — የክልሉ ስም አልተጠቀሰም።

🎯 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ
• 591/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ወንድ — ኦዳ ትምህርት ቤት
• 583/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ሴት — አገው ምድር ትምህርት ቤት
• 576.25/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ወንድ — ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
• 569/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ሴት

📌 በአጠቃላይ፦ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ምጣኔ 12.8% ሲሆን፣ አዲስ አበባ 32.4% በማስመዝገብ ከፍተኛውን የክልል ደረጃ ይዟል። በተጨማሪም 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ከ62 ወደ 88 ከፍ ብለዋል።
" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።
[አዩዘሀበሻ]
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
1
ውጤት መቼ ይታያል

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።
የውጤት ማሳያ ሊንኮችን በዚሁ ቻናል የምናጋራ ይሆናል፣join now.
#አዩዘሀበሻ
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
1