G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የተቀማጭ ገንዘብ ወለድ‼️
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አዲስ ባወጣው መመሪያ ቁጥር NBE/INT/13/2026 መሠረት፣ ባንኮች የሚሰጡት የቁጠባ እና የብድር ወለድ ተመን ከዚህ በኋላ በገበያ ፍላጎት እና አቅርቦት ላይ ተመስርቶ በየባንኮቹ እንዲወሰን አዝዟል።


📌 ዋና ዋና ነጥቦች፦
የቁጠባ ወለድ ተመን (Saving Rate): ከዚህ ቀደም ብሄራዊ ባንክ ያስቀምጠው የነበረው ዝቅተኛ የቁጠባ ወለድ ተመን ቀርቶ፣ እያንዳንዱ ባንክ እንደ ፍላጎቱ የራሱን የቁጠባ ወለድ ተመን ይወስናል።

የጊዜ ገደብ ተቀማጭ (Time Deposit): ባንኮች ለጊዜ ገደብ ተቀማጭ የሚከፍሉትን የወለድ መጠን ራሳቸው በነፃነት ይወስናሉ።

የዳይሬክተሮች ቦርድ ኃላፊነት: የእያንዳንዱ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የወለድ መጠኑን በጽሁፍ የመወሰን እና ግልጽ የሆነ አሰራር የመዘርጋት ኃላፊነት ተጥሎበታል።

አድልዎ መከልከሉ: ባንኮች ለተመሳሳይ የቁጠባ ዘርፍ ደንበኞች እኩል የሆነ የወለድ ተመን መተግበር አለባቸው፤ አድልዎ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው።

💡 ይህ ምን ማለት ነው?
ባንኮች ደንበኞችን ለመሳብ የተሻለ የወለድ መጠን በማቅረብ እርስ በርሳቸው እንዲወዳደሩ በር ይከፍታል። ይህም የሀገሪቱን የፋይናንስ መረጋጋት እና የኢኮኖሚ እድገት ለማፋጠን የታለመ መሆኑ ተገልጿል።

​መመሪያው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሁሉም ባንኮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል።
#አዩዘሀበሻ
​=========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
😍4
ከባዱ ወደ ጨረቃ መውጣቱ ሳይሆን መመለሱ ነው‼️
አራቱ የናሳ ተመራማሪዎች የ13 ደቂቃ ከህዋ ወደመሬት የመመለስ (Reentry) ስህተት ፍርሃት፤ መሞት ወይም በህይወት የመገኘት ታሪክ ሊፈፀም:- ጥቂት ሰዓት ብቻ ቀርቷል
=======================================
ዛሬ እኤአ ኤፕሪል 10፣ 7:53 ምሽት ET ወይም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከሌሊቱ 9 ሰአት፣ በፓሲፊክ ውቅያኖስ ላይ  የሆነ ቦታ፣ አራት ሰዎች ከዚህ በፊት ማንም ሰው በሕይወት ባልተረፈበት ፍጥነት  አንድ ነገር ሊያደርጉ ተዘጋጅተዋል። ከ ዛሬ ዘጠኝ ቀን በፊት 4 የናሳ ተመራማሪዎችን ይዛ ወደ ህዋ የመጠቀችው አርጤምስ ሁለት የተባለችው መንኩራኩር ለዘጠኝ ቀን በመሬትና በጨረቃ መካከል ስትዞር ቆይታ ዛሬ ወደምድር ሊመለሱ ተዘጋጅተዋል። የመንኮራኩሩ አብዛኛው አካል በህዋ ላይ ቀርቶ ወደምድር መመለሻ  ኦሪዮን የሚባለው መንኮራኩር የመሬት ከባቢ አየር የላይኛው ጫፍ ሲገባ፣ ፍጥነቱ  በሰዓት 38,000 ኪሎሜትር በሰአት እየተምዘገዘገ ወደ መሬት  ፍጥነት እየተጓዘ ይመጣል።
እንደገና አንብቡት።
38,000 ኪሎሜትር በሰዓት።
ለምሳሌ፣ የመደበኛ አየር መንገድ አውሮፕላን በሰዓት 900 ኪሎሜትር ይበርራል። የወታደር ስናይፐር ጥይት በሰዓት 3,500 ኪሎሜትር ያህል ይጓዛል። ኦሪዮን ግን በMach 32 ፍጥነት ይንቀሳቀሳል፣ ከጥይት 11 እጥፍ ይፈጥናል ማለት ነው። ይህ በታሪክ ውስጥ በሰው ተሸካሚ መንኮራኩር የሚደረግ ፈጣን ወደ መሬት ለመመለስ የሚደረግ ጉዞ ይሆናል ማለት ነው።
መንኮራኩሩ ውስጥ አራት ሰዎች በመቀመጫቸው ተጠግተው  በre cycling የተመረተ  አየር እየተነፈሱ፣ ልባቸው በፍርሃት እተመታ፣ ፊዚክስ ሕይወታቸውን ወይም ሞታቸውን ሊወስን እየተጠባበቁ ነው።

🔥 የእሳት ግድግዳ (The Wall of Fire)
ኦሪዮን ከአየር ጋር ሲገጥም፣ ከፊቱ ያለው አየር ለመንቀሳቀስ ጊዜ የለውም። ወዲያውኑ ይጨመቃል። የተጨመቀ አየር ይሞቃል። በ38,000 ኪሎሜትር ፍጥነት ደግሞ እጅግ ከፍ ያለ ሙቀት ይፈጠራል። በመንኮራኩሩ ውስጥ ያለ ሁሉ እስከ 5,000°C ሙቀት ድረስ ይግላል አለያም ሊቀልጥ ይችላል ማለት ነው። ። ይህ ከእሳተገሞራ  ሁለት እጥፍ የሚሞቅ ሙቀት ነው። ብረትን ሊያተን የሚችል፣ መንኮራኩሩን እና ውስጥ ያሉትን ሰዎች ወደ አመድነት ሊያስቀይር የሚችል ሙቀት ነው።
ታዲያ ኦሪዮንን ከዚህ እሳት የሚከላከለው 16.5 ጫማ ዲያሜትር ያለው AVCOAT የተባለ ቁሳቁስ ነው። ይህ የሙቀት መከላከያ በቀስ በቀስ ይቃጠላል፣ ይሰነጠቃል፣ እና እየተበላሸ ሙቀቱን ከመንኮራኩሩ ይወስዳል ወይም ያስወግዳል። እሳቱን አያቆምም—ለሰዎቹ ሕይወት እራሱን ይሰዋል።

⚠️ ይህም ሙከራ  የተሳካ የሆነው  አንድ ጊዜ ቢሆንም  የተሳሳተ የሙቀት መከላከያ ነበር ። በፈረንጆቹ 2022 በArtemis I ጊዜ፣ ኦሪዮን ያለ ሰው ከጨረቃ ሲመለስ፣ የሙቀት መከላከያው በ100 በላይ ቦታዎች ተሰነጠቀ እና ተበታተነ።
ምክንያቱ የተጠመዱ ጋዞች ነበሩ። በመመለስ ሙቀት ጊዜ ግፊት ተፈጠረ፣ እና ክፍሎቹ ተበታተኑ።
Artemis I ላይ ሰው ስለሌለ ችግር አልነበረም።
Artemis II ግን አራት ሰዎች አሉ።
NASA መፍትሄ አልቀየረም—የመመለስ አንግልን ቀየረ። ሙሉ አዲስ መከላከያ አልሰራም።

አሁን የ⏱️ 13 ደቂቃ ዝምታ ተቃርቧል
የመመለስ ሂደቱ ከ13 ደቂቃ ይሆናል።በዚህ ጉዞ ላይ በሙቀቱ ምክንያት በሚፈጠር ከፍተኛ የፕላዝማ ነፀብራቅ መገናኛ ሬድዎችና የሲግና ዘዴዎች ከመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ጋር ይቋረጣል
ያኔ NASA ምንም አይሰማም መልዕክት አይደርሰው ታድያ ፍርሃት ጭንቀት ሰአት ይሆናል ። ሰዎቹ አይነጋገሩም።
አራት ሰዎች በእሳት ውስጥ በሙሉ ዝምታ ይወርዳሉ።
🌊 ማረፊያቸው ውቅያኖስ ላይ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል
መንኮራኩሩ በፓሲፊክ ውቅያኖስ 100 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ያርፋል ተብሎ ይጠበቃል ።
ለዚህም ሂደት 11 ፓራሹቶች በትክክል መከፈት አለባቸው ምክንያቱም
ፍጥነቱን ከ38,000 ኪሎሜትር በሰአት ወደ 27 ኪሎሜትር በሰአት ዝቅ እንዲል ያደርገዋል።
አንድ ፓራሹት እንኳ ቢሳሳት ውጤቱ ከባድ ይሆናል።
👨‍🚀 አሁን ያሉበት ስሜት
አራቱ አባላት ዛሬ የመጨረሻ ቀናቸውን በስፔስ አሳልፈዋል። ምግብ ተዘጋጅቷል፣ ስርዓቶች ተፈትሸዋል። አሁን የ13 ቷን ደቂቃዎች የሰቀቀን ጉዞ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
የፊዚክስ ምስጢር ህይወት ወይ ሞት
እሳት እና ሕይወት ፍት ለፊት  ተገናኝተዋል።
የ13 ደቂቃ ረጅም ጊዜ
7:53 PM — መግቢያ
የ13 ደቂቃ — ዝምታ
ከዚያ — እሳት
ከዚያ — ፓራሹቶች
ከዚያ — ፓስፊክ ውቅያኖስ
Girum Tekle
@Gtutorialclass
2
የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ!።

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ድረስ ይሰጣል

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 የትምህርት ዘመን የሚካሄዱ ፈተናዎች የሚሰጡባቸውን ቀናት ይፋ አደረገ።

በዚህም መሰረት የሪሚዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ 20፣ የቅደመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 12 እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

በተመሳሳይ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከሐምሌ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሰጥ፤ የመሰረታዊ የንብባና የስሌት ክህሎት ምዘና ፈተና ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሰጣል፡፡የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር )÷ እስከ ተጠቀሱት ጊዜያት ድረስ ተፈታኞች አስፈላጊውን የይዘትና የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲደርጉ አስገንዝበዋል።ወላጆች፣ መምህራንና በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር ተፈታኞቻቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል  ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
2
ወደ ካናዳ ምዝገባ አልተጀመረም‼️
ለካናዳ የስራ ስምሪት ምንም አይነት ይፋዊ ምዝገባ አለመጀመሩን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንዳስታወቀው የሰው ሰራሽ አስተውሎትን ወይም AI/Deepfake በመጠቀም የተፈበረኩና አሳሳች ምስሎችንና በቪዲዮዎችን በማሰራጨት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወደ ካናዳ "ምዝገባ ጀምሯል" የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመልቀቅ ማህበረሰቡን በማደናገር የሚገኙ አካላት መኖራቸውን አስታውቋል።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል እና ከካናዳ ኤምባሲ ጋር በመተባበር ዜጎችን አሰልጥኖ ወደ ካናዳ ለመላክ የሚያስችል ስምምነት ሚያዝያ 1 ቀን 2018 ዓ.ም መፈራረሙ ይታወሳል።ይህንኑ ተከትሎ፣ አንዳንድ ሕገ-ወጥ አካላት  የፈጠራ ወሬዎች በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ የሚገኙ ሲሆን በሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI/Deepfake) በመጠቀም የተፈበረኩና አሳሳች ምስሎችንና በቪዲዮ በማሰራጨት  "ምዝገባ ተጀምሯል" የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎችን በመልቀቅ ማህበረሰቡን ማደናገር ላይ ይገኛሉ።

በግል ስልክ ቁጥሮች ደውሉ በማለት ዜጎችን ለኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ መጋበዝ ላይ ሲሆኑ እነዚህ ማስታወቂያዎች ሙሉ በሙሉ የማጭበርበር ተግባራት መሆናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማስጠንቀቁን አዩዘሀበሻ ሰምቷል፡፡በአሁኑ ወቅት ለካናዳ የሥራ ስምሪት ምንም አይነት ይፋዊ ምዝገባ አልተጀመረም፡፡

በግል ስልክ ቁጥሮች የሚደረጉ ጥሪዎችም ሆኑ የሚላኩ አጫጭር መልዕክቶች ሚኒስቴሩን መስሪያ ቤቱን እንደማይወክሉ ያስታወቀው ቢሮው የምዝገባ ጥሪ የሚደረገው በብሔራዊ ቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች፤ የሚኒስቴሩን ይፋዊ የማረጋገጫ ምልክት ባላቸው ማህበራዊ ትስስር ገጾች ብቻ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስቧል፡፡
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ
@Gtutorialclass
2
ከመጪው ሰኔ 24/2018 ዓ/ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተፈታኞች የተዘጋጀ የመፈተኛ ክፍል መግቢያ ካርድ (Admission Card) በፈተና አስተዳደር ሲስተም (https://exam.eaes.et/) ከ03/09/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለክልል ትምህርት ቢሮ፣ ለዞን ትምህርት መምሪያዎች እና ለትምህርት ቤት ተወካዮች መለቀቁን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል 📢📝

አገልግሎት መ/ቤቱ ፦

1. እያንዳንዱ ተፈታኝ ተማሪ በአድሚሽን ካርዱ ጀርባ ላይ የትምህርት  ቤቱን ወይም የወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ማህተም የተደረገበትን አድሚሽን ካርድ ከትምህርት ቤቱ ወስዶ በእጁ መያዝ መያዝ እንዳለበት አሳስቧል 🎓

2. በምዝገባ ወቅት በተፈታኙ ወይም በመዝጋቢው የተከሰተ የትምህርት መስክ ፣ የጾታ ፣ የፎቶ እና መሰል ማስተካከያዎች ካሉ ከግንቦት 30/2018 ዓ.ም በግድግዳ ለትምህርት ቤቱ ማሳወቅና ሂደቱን ጠብቆ መስተካከሉንም ከትምህርት ቤቱ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጿል 🔄📅

3. እያንዳንዱ ተፈታኝ አድሚሽን ካርዱን ወደ መፈተኛ ማዕከል ሆነ መፈተኛ ክፍል ለመግባት የሚጠቀምበት በመሆኑ በአግባቡና በጥንቃቄ እንዲይዝ አሳስቧል ⚠️🛡️

4. ተፈታኞች ፈተና ላይ ከአድሚሽን ካርድ በተጨማሪ የፋይዳ መታወቂያ መያዝ እንደሚጠበቅባቸው ገልጿል 🆔📋
1
ውጤትዎን ይመልከቱ! 📄

ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም ከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት 

ውጤትዎን ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et

ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ። 📝🔍
2
1
#በአማራ ክልል የ2018 #የትምህርት ዘመን #የ8ኛ ክፍል #ክልላዊ ፈተና #ውጤት ይፋ ሆነ።
በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል #አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ከሰኔ 3-5/2018ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት  ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 173699 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135003(77.72%)ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

ተማሪዎችም ውጤታቸውን   በሁለት  አማራጮች ማየት የሚችሉ ሲሆን:-
🔴 በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ  የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት
3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

🔴 በተጨማሪም  @emacs_ministry_result_qmt_bot  በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን መጀመሪያ
     1) start የሚለውን ይጫኑ!
      2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ
      3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ
       4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት  ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ
🔴 በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ
1)  ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ
2)  በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና  የተማሪውን  የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት
3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን
4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ
5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን  ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን  ማቅረብ ይችላሉ።

🔵ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡

2018ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል።
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
2
የመሬት መንቀጥቀጥ‼️
በዛሬዉ እለት በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር።

በዛሬዉ እለት ምሽት 2 ሰዓት ከ 11 ደቂቃ ላይ በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.6 የተለካ መሆኑን ቮልካኖ ዲስከቨሪ የተሰኘዉ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተገሞራ ፍንዳታዎችን የሚከታተል ተቋም በገጹ አሳዉቋል።

የመሬት መንቀጥቀጡ በአዲስአበባም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ተሰምቷል።
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@Gtutorialclass
3
የኤሌክትሪክ ኃይል አዲስ ኃይል ማስገቢያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ በሙሉ ተነሳ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስገቢያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች ይጠየቅ የነበረውን ከ3 እስከ 9 በመቶ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ።

ቀደም ሲል የዱቤ ክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ወለድ ይጣል ነበር።

አሁን ወለዱ መነሳቱ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ዜጎች የምስራች መሆኑንና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተጀመረው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር በሁለት ሳምንታት ብቻ 19,231 አዳዲስ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል።

ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 664,505 አዳዲስ ደንበኞችን ያገናኘ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም. ደግሞ 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ለማገናኘት አቅዷል።

ኢንጅነር ጌቱ እንደገለጹት፣ አገልግሎቱ በ70 ዓመታት ታሪኩ 5.88 ሚሊዮን ደንበኞችን ማገናኘት ችሏል፤ አሁን ግን በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ደንበኞችን የማገናኘት አቅም ላይ ደርሷል።

ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም

@Gtutorialclass
2
ተጨማሪ መረጃ‼️
ዛሬ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ በራያ አላማጣ ወረዳ በመረዋ ንዑስ ወረዳ የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በአራት ዙር መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀውልናል።
እንደ የአካባቢው ምንጮች ገለጻ፣ ጥቃቱ:-
📌በመረዋ 2ኛ ደረጃ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
▪️📌በችግኝ ጣቢያው አካባቢ በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
📌ከቤተ-ክርስቲያን አለፍ ብሎ ባለው ዋርካ (ዳዕሮ) ዛፍ ስር በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ
📌ሚይ ሓርማዝ በሚገኙ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተፈፀመው።
ጥቃቱ በአራት ዙር የተፈፀመ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ታጣቂዎች ተሰውተዋል።
የተጎዱ ታጣቂዎች ደግሞ ወደ አላማጣ ለህክምና ተወስደዋል። መረዋ አካባቢ በሚገኝ በአንድ የቤተክርስቲያን ዋሻ ውስጥ የህክምና አገልግሎት መስጫ አዘጋጅተው ነበር ተብሏል።
Please
Strive for👉🕊🕊🕊🕊🕊
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
@Gtutorialclass
@Gtutorialclass
1👏1
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል።

በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፓሊሲ ላይ "የሙያና ቴክኖሎጅ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜያቸው ጋር የተመጣጠነ ሆኖ እንዲሰጥ ይደረጋል" በሚል አቅጣጫ መቀመጡን ያመለክታል።

በዚህ መሰረት በየደረጃው የሥራና ተግባር ትምህርት ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ተቀናጅቶ እንዲሁም 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ በሚያስችል መልኩ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ በሁለተኛው ዙር እንዲተገበሩ ለተለዩት 11 የሙያ አይነቶች ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ ትምህርቶች እንዲሁም ለ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችና የመምህር መምሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህን ተጨማሪ የሙያ አይነቶች ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ለማስጀመር :-

• የክልሉ/የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት እና እቅዱን ለማከናወን በጀት በመያዝ የሙያ አይነቶችን በትምህርት ቤት እና በተማሪዎች ደረጃ በማስመረጥ፣

• የየሙያ አይነቱ መምህራንን በመቅጠር፣
• የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓት በሂደት በማሟላት፣
• መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠን እና የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን ትምህርቱን ለማስጀመር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል።

@Gtutorialclass
2
‎"እውነት ህግ ካለ ርሸና የፈጸሙና ያስፈፀሙ አካላት ሊጠየቁ ይገባል " - ነዋሪዎች

ከ13 ቀናት በፊት ‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ፦
° ተመስገን ጌታቸው
° ይታገሱ አሰግደው
° ግዛው ግርማዬ የተባሉ ሶስት ወጣቶች በትራንስፖርት እየተጓዙ በነበረበት ወቅት ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው መገደላቸው ይታወቃል።

ቃላቸውን ለቲክባህ የሰጡ የአከባቢው ኗሪዎች፤ "ሶስት ወጣቶች ከመኪና እንዲወርዱ ተደርገው እጃቸው የፊጢኝ ታስሮ በአሰቃቂ ሁኔታ ተረሽነው አስክሬናቸው በትውልድ አካባቢያቸው መገኘቱ እውነት ነው " ብለዋል።

የነዚህ ወጣቶች በፀጥታ ኃይሎች መገደልና ከግድያው በኋላ የሟቾቹ አስከሬን እንዳይነሳ ተብሎ በጅብ እንዲበላ መሆኑ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቁጣ፣ ሀዘንና ስጋት መፍጠሩን ተናግረዋል።

" አስክሬናቸው ከሌሊቱ 11 ሰዓት አከባቢ በትውልድ ቀያቸው ተጥሎ ማንም እንዳያነሳና እንዳይቀብራቸው ማስጠንቀቂያ ከተሰጠ በኋላ አስክሬናቸው ለጅብ ተጋልጦ እንዲቆይ ሆኗል፤ ከሶስቱ የአንዱ ቤተሰቦቹ አንስተው ቀብረዋል " ሲሉ አብራርተዋል።

‎ነዋሪው " ‎'ፋኖ ናቸው' ተብለው ከመኪና እንዲወርዱ ከተደረጉ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ነው የሰማነው። ይህ ‎በየትኛውም መመዘኛ ትክክል አይደለም፤ ጥፋትና ወንጀል ፈጽመው ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ ይገባ ነበር። እውነትም ህግ ካለ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን የረሸኑ በህግ ሊጠየቁ ይገባል " ብለዋል።

ነዋሪዎች የተጎጂ ቤተሰቦች እየሆነ ያለውን ነገር ወጥተው ለመናገርና መረጃ ለመስጠት ይፈራሉም ተብሏል።
@Gtutorialclass
2
ድርቅ‼️
በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰተው ከባድ የድርቅ አደጋ ምክንያት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቤት እንስሳት እያለቁ መሆናቸውን ከየአካባቢው የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።
በትግራይ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች፣ በአማራ ክልል ዋግምራ ዞን፣ በሰሜን ጎንደር ጠለምትና የበየዳ ቆላማ አካባቢዎች የክረምት ዝናብ ባለመዝነቡ ምክንያት የቁም እንስሳት እልቂት ይበልጥ እየከፋ መጥቷል።
በተለይም በሰሜን ጎንደር ጠለምት ቀጠና ከአስራ አንድ ሺህ (11,000) በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች እንዲሁም የበግና ፍየሎች ማለቃቸው ታውቋል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በአብዛኞቹ አካባቢዎች በዚህ ክረምት የተዘራና የበቀለ እህል ጨርሶ አለመኖሩን የአዩዘሀበሻ የመረጃ ምንጮቻች ገልጸዋል።
የድርቁ ስፋትና የሚያሳድረው ተፅዕኖ በሰሜን ኢትዮጵያ አካባቢዎች ከፍተኛ እየሆነ የመጣ ሲሆን፣ ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን የደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ።
👉ምስሉ ጠለምት ከሚገኙ የአዩዘሀበሻ ቤተሰቦች የተላከ ነው።
👉ሼር በማድረግ የሰብዓዊነት ግዴችሁን ተወጡ
(አዩዘሀበሻ)
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@Gtutorialclass
😢2🤔1
ምፅዋ በካርጎ አውሮፕላኖች ተጨናንቋል‼️
ሱዳን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ እያራገፈች ነው‼️
ጀነራል አል_ቡርሃን ከባባድ መሣሪያዎችን በኤርትራ ምፅዋ አውሮፕላን ማረፊያ በብዛት  እያራገፈ እንሚገኝ በሳተላይት ምስል ተረጋግጧል ።
ከሱዳን ተነስተው በምፅዋዋ አውሮፕላን ማረፊያ ያረፉ በርካታ የጭነት አውሮፕላኖች ከባባድ መሳሪያዎችን፣ ተወንጫፊ ሚሳይሎችንና ጥይት እያራገፉ መሆናቸውን የሳተላይት ምስሎች አሳይተዋል።
ከሱዳን በተጨማሪ ከቤላሩስ እንዲሁም ከኢራን የመጡ የጭነት አውሮፕላኖች ከሁለት ቀን በፊት ምፅዋ እንዳረፉ ከሳታላይት ምስሎች ለማየት ተችሏል።
(አዩዘሀበሻ)
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@GTUTORIALCLASS
2
የፖለቲካ እስረኞችን ከማይካድራ ጭፍጨፋ ፍርደኞች ጋር በይቅርታ አንድ ላይ ለመፍታት መታቀዱ ተቃውሞ አስነሳ‼️
በአማራ ክልል ከተቀሰቀሰው ግጭት ጋር በተያያዘ በማረሚያ ቤቶች ተይዘው የሚገኙ በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ከመንግስት የቀረበላቸውን የይቅርታ ሰነድ አንፈርምም በማለት ጠንካራ ተቃውሞ ማቅረባቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
መንግስት የፖለቲካ ታሳሪዎቹን ከስድስት ዓመታት በፊት በማይካድራ ከተፈፀመው ዘግናኝ የጅምላ ጭፍጨፋ ጋር በተያያዘ "በሰብአዊ ፍጡር ላይ የሚፈፀም ወንጀል ተከሰሱ እና ከተፈረደባቸው አካላት ጋር በአንድ ላይ አደባልቆ በይቅርታ ለመፍታት ማቀዱ ታሳሪዎቹን አስቆጥቷል።
የመረጃ ምንጮች እንደገለጹት የፖለቲካ እስረኞቹ ይህንን ውሳኔ "እጅግ ዘግናኝ የሆነ ግድያና ጭፍጨፋ ፈጽመው ፍርድ ካገኙ ግለሰቦች ጋር እኩል በማሰለፍ በሕዝብ ዘንድ በተመሳሳይ እይታ እንዲታዩና የወንጀሉ ተካፋይ ተደርገው እንዲሳሉ ሆን ተብሎ የተሸረበ ሴራ ነው" ሲሉ አውግዘዉታል።
ታሳሪዎቹ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ይህንን የይቅርታ ሀሳብ አዘጋጅቶ ለመንግስት ማቅረቡን በመግለጽ የኮሚሽኑ እርምጃ እጅግ እንዳዘናቸውና ተስፋ እንዳስቆረጣቸው ተናግረዋል።
መንግስት በሚመጣው አዲስ ዓመት ከ1,300 በላይ ሰዎችን በይቅርታ ለማስፈታት አቅዶ የይቅርታ ደብዳቤ እያስፈረመ ይገኛል። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የነበሩት አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በርካቶች የቀረበላቸውን አነጋጋሪ የይቅርታ ሰነድ ቢፈርሙም 30 የሚሆኑ ታዋቂ የፖለቲካ እስረኞች ግን "አልፈርምም" በማለት አቋም ይዘዋል።
የቀረበው የይቅርታ ሰነድ አወዛጋቢ ቃል የሚከተለውን ያካትታል፦ «በአማራ ክልል ፅንፈኛው ቡድን በሚያደርገው ትግል ላይ መሳተፌ ስህተት መሆኑን በማመን መንግስትንና ሕዝብን ይቅርታ እጠይቃለሁ።

@gtutorialclass
😢1
በ148 ቀበሌዎች ዝናብ የለም‼️

በትግራይ ክልል በድርቅና በወታደራዊ ምልመላ ምክንያት ህዝቡ ለእንግልት መዳረጉ ተነግሯል።

​የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል በሚገኙ 148 ቀበሌዎች ላይ አንዲት ጠብታ ዝናብ እንኳ አልዘነበም ብሏል።

በ​ድርቁ በሺዎች የሚቆጠሩ እንስሳት እያለቁ ሲሆን፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወገኖች ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ይፈልጋቸዋል ተብሏል።እርዳታ እንደምንም ቢገባም "ለታጣቂ ይሰጣል" የሚል ስጋት በረጅዎች ዘንድ መኖሩ ተጠቁሟል።

​ ህወሓት ወጣቶችን በማፈስ ወደ ጦርነት እያሰማራ ይገኛል መባሉን ተከትሎ፣ የትግራይ ህዝብ በአንድ በኩል በረሃብና በድርቅ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በጦርነትና የልጆቹን ህይወት በማጣት እጥፍ ድርብ ስቃይ እየደረሰበት መሆኑ ዘገባው አመልክቷል።
አዩ
=====================
💎👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ
ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
@GTutorialclass
🤯1