G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ልዩነት

1. ነዳጅ (Crude Oil/Petroleum) ምንድነው?

ነዳጅ (ድፍድፍ ዘይት) ከጥንት የባሕር ውስጥ ሕይወት ቅሪት የተገኘ ፈሳሽ የቅሪተ አካል ነዳጅ ነው። ከማጣራት በኋላ ለተለያዩ ነገሮች ይውላል። ዋና ዋናዎቹ፡-

*ቤንዚን (Gasoline): ለመኪናዎች
*ናፍጣ (Diesel): ለትላልቅ ተሽከርካሪዎች እና ጄኔሬተሮች
*ኬሮሲን እና የአውሮፕላን ነዳጅ
ፕላስቲኮችና አስፋልት ለመሥራት ግብዓት ነው።

2. የተፈጥሮ ጋዝ (Natural Gas) ምንድነው?

በአብዛኛው ሚቴን (Methane) ከተባለ ጋዝ የሚሰራ ሲሆን፣ እንደ ነዳጅ ሁሉ ከጥንታዊ ሕይወት ቅሪት የተፈጠረ ነው።

ለኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች
ለቤቶች ማብሰያ እና ማሞቂያ
ለኢንዱስትሪዎች እና እንደ የተሽከርካሪ ነዳጅ (CNG)፣ለማዳበሪያ (Fertilizer) ማምረቻ ወሳኝ ግብዓት ነው።

🇪🇹 ኢትዮጵያ ይፋ ያደረገችው የትኛውን ነው?

የሀገራችን የኃይል ስትራቴጂ ትልቁ ትኩረት በሶማሌ ክልል ኦጋዴን ተፋሰስ የሚገኘው የተፈጥሮ ጋዝ ላይ ነው።

ኢትዮጵያ በቅርቡ ወደ ምርት እያስገባች ያለችው ዋነኛው የተፈጥሮ ሃብት: የተፈጥሮ ጋዝ ነው!
የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) ፕሮጀክት፡ በቅርቡ በካሉብ አካባቢ የተፈጥሮ ጋዝን ለሀገር ውስጥ ፍጆታና ለኢንዱስትሪ የሚሆን ፈሳሽ ጋዝ (LNG) የሚያመነጨው ፕሮጀክት የመጀመሪያ ምዕራፍ ተመርቆ ሁለተኛው ተጀምሯል።

ይህ የተፈጥሮ ጋዝ የማዳበሪያ ፋብሪካዎችን ለመገንባት እንደ ወሳኝ ግብዓት ያገለግላል። ይህም ሀገሪቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር አውጥታ ከውጭ የምታስገባውን ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ ማምረት እንድትችል ትልቅ በር ይከፍታል።.

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
የኤርትራ አመራሮች‼️
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ዛሬ ጠንከር ያለ መግለጫ አውጥቷል፡፡
ከሰሞኑ horn review "ኢትዮጵያ ለኤርትራ የሰጠችውን የሀገርነት እውቅና ማንሳት አለባት፣ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት እውቅና ለማንሳት አለምአቀፍ ህጎች እንዳሉ እንዲሁም የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማቅረብ" ረዘም ያለ ፅሁፍ ማሰራጨቱን ተከትሎ የኤርትራ አመራሮችን ክፉኛ ያበሳጨ ይመስላል፡፡
ይህን ተከትሎ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስቴር አቶ የማነ ገብረመስቀል "ነጻነታችንን ከኢትዮጵያ በስጦታ አልተረከብንም ኢትዮጵያን አሸንፈን ያገኘነው ነው ብለዋል፡፡ የኤርትራ ሉዓላዊነት እውቀና መሰጠት የነበረበት በ1940 ቢሆንም አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት በቀጠናው የነበራቸው ፍላጎት ሌላ በመሆኑ ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እንደተባለው የምታደርግ ከሆነ እኛም ከ1952 እስከ 1993 እ.ኤ.አ ኢትዮጵያ ለወሰደችብን ሀብትና ንብረት በቢሊየን ዶላር የሚቆጠር ካሳ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡ለዚህም የኢራቅ እና ኩዌትን ታሪክ አጣቅሰዋል፡፡
በፅሁፉ የኢትዮጵያ ሰራዊትን ሲዋጉ በተለይ በመንደፈራ፣በምፅዋና በአሰብ እንዴት እንዳሸነፉና ከኢትዮጵያ በኩል ምን ያህል ሰራዊት እንደተበተነ፣እንደቆሰለ፣እንደሞተ እና እንደተማረከ በቁጥር ለማስቀመጥ ሞክረዋል።
በተያያዘ ዜና ከሰሞኑ የኤርትራ ወታደራዊ አመራሮች ከኢትዮጵያ ጋር በተዋጉባቸው በእያንዳንዱ ግንባር በመሄድ የጦርነቱን ሂደትና አሰላለፍ ምን ይመስል እንደነበር ለሰራዊታቸው አመራሮች እና መኮንኖች የጦርነት ትንታኔ ሲሰጡ ታይተዋል።
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
3
ለወንዶች የወሊድ ፈቃድ‼️
በደቡብ አፍሪካ አባቶች ከእናቶች እኩል የወሊድ እረፍት ተፈቀደላቸው

"ለደቡብ አፍሪካ የወደፊት አባቶች ፈር ቀዳጅ እርምጃ ነው"

#Ethiopia | የደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ሁሉም ወላጆች እኩል የወሊድ እረፍት እንዲኖራቸው ወሰኗል።

ውሳኔው ትልቅ ውሳኔና ለፆታ እኩልነትና የቤተሰብ መብት ግዙፍ አሸናፊነት ተደርጎ ተወስዷል።

በቀደመው ሕግ እናቶች የአራት ወር የወሊድ ፈቃድ ያላቸው ሲሆን፤ አባቶች ደግሞ 10 ቀናት ብቻ ይሰጣቸው ነበር።

የአገሪቱ ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት ባሳለፈው ውሳኔ፣ ሕጉን ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ያለው ሲሆን፤ ለአባቶች አድሎአዊ ነው ብሏል። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ወላጆች እንደፈቀዱ የሚጠቀሙበት እኩል የወሊድ እረፍት እንዲያገኙ በይኗል።
'ሲንግል ዳድስ ኔትወርክ' የተባለ ድርጅት መስራች የሆኑት ሴትምቢሶ ፓኪቲ፤ "ይህ ለእኩልነት፣ ለቤተሰብ ደኅንነትና ለደቡብ አፍሪካ የወደፊት አባቶች ፈር ቀዳጅ እርምጃ ነው" ብለዋል።

እ.ኤ.አ በ2023 የአገሪቱ የታችኛው ፍርድ ቤት፣ የአገሪቱ ሁለት ሕጎች የተወሰኑ ክፍሎች ፍትኃዊነት የጎደላቸው መሆናቸውን እንዳገኘና የበርካታ የቤተሰብ መብቶችን የሚጥሱ ናቸው ብሏል።

ከፍተኛ ፍርድ ቤት የወሊድ ፈቃድና የሥራ አጥ ጥቅማ ጥቅሞችን ማግኘትን በተመለከተ ለወላጆች ፍትኃዊ አለመሆኑን ወስኗል።

ጉዳዩ በብቸኝነት በሴቶች ላይ የሚጣለውን ማኅበረሰባዊ ጫና ፍትኃዊ ለማድረግ በወጠኑ በሁለት ጥንዶች፣ በፆታ እኩልነት ኮሚሽንና በሌሎችም ወደ ፍርድ ቤት የቀረበ ሲሆን፤ የወላጅነት ኃላፊነት የጋራ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።
ቢቢሲ
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
😁43
ፈተናው መቼ ይሰጣል
የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያው ዙር ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጡሹኔ በቀን መስከረም 26/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ሰርኩላር፥ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተናው ጥቅምት 03/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይገልጻል።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1
ሰበርኢትዮጵያ ደብዳቤ ላከች‼️
👉ኢትዮጵያ ኤርትራ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።
በባለፈው በሰኔ ወር ከተላከው ደብዳቤ በተጨማሪ ኢትዮጵያ በውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤርትራን በማስጠንቀቅ October 2/2025 የአቤቱታ ደብዳቤ አስገብታለች።
ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የተላከው ደብዳቤ “የኤርትራ መንግስት ህወሃትን ጨምሮ ሌሎች በክልል የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎችን እየደገፈች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እየተዳፈረች መሆኑንና ኢትዮጵያም ይህን በሉዓላዊነቷ ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማስቆም ህጋዊ፣ሞራላዊ እና ተፈጥሯዊ መብቷን ትጠብቃለች” ማለቱን ከሆርን ሪቪው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር የተገለለችበት መንገድ ህጋዊ ባለመሆኑ ኢትዮጵያ የወደብ ባለቤት ለመሆን ያነሳችውን ጥያቄ አሁንም አቋሟን እንደማትቀይር አቋሟን በግልፅ ለተባበሩት መንግሥት ድርጅት አሳውቃለች።

===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🥰1
የሪሜዲያል መግቢያ ነጥብ‼️
ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎችን በተፈጥሮ እና ማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት መስኮች ከ49.5% በታች ያስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን እናሳውቃለን።
1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 33% ከመቶ እና ከዚያ የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ተቋማት (ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥቡን ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
በዚህ መሠረት የተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ለወንድ 216/600፣ ለሴት 204/600፣ታዳጊ ክልል እና አርብቶ አደር ሁለቱም ፆታ 198/600፣ለአይነ ስውራን 165/600 ሆኗል ።
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍1
🚨 አስደንጋጭ ዜና‼️
ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ለመዝረፍ የሞከሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ በሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በተከሰተው አስከፊ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሰለባ ለሆኑ ዜጎች ከተሰበሰበው የድጋፍ ገንዘብ ላይ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ለመዝረፍ የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አስታወቀ።

* አደጋው በደረሰባቸው ወገኖች ህይወትና ችግር ለመበልጸግ ያሰቡት ተጠርጣሪዎች፣ ለተጎጂዎች የተሰበሰበውን 60,276,383 ብር ከጎፋ ዞን አደጋ ስጋት አካውንት ለመውሰድ ሞክረዋል።

* ገንዘቡን ለመዝረፍም ቀደም ሲል ቮይድ በተደረገ የቼክ ቁጥር (42221123) አስመስለው በማሳተም ሙከራ አድርገዋል።

* የወንጀል ሙከራው የተጋለጠው ከአዲስ አበባ ንግድ ባንክ ሸገር ቅርንጫፍ ለጎፋ ዞን አስተዳደር በተደረገ ፈጣን ጥቆማ ምክንያት ነው።

* በጥቆማው መሠረትም ከአዲስ አበባና ከክልል ፖሊስ ጋር በመተባበር፣ ገንዘቡ ሳይወጣ ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ችለዋል።

የዞኑ መንግሥት ኮሙኒኬሽን፣ ሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የለገሰውን ድጋፍ 'ወደ ኪሴ ገብቶ ካልበለጸግኩ' በሚል አስተሳሰብ የተጠመዱ አካላት ያሰቡት "አስነዋሪና ስብዕና የጎደለው ተግባር" አለመሳካቱን ገልጿል።
Via አሐዱ
===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
4
ደብዳቤው‼️
#ኢትዮጵያ #ኤርትራ እና #ህወሓት"ጦርነት ሊከፍቱብኝ በቅንጅት እየሰሩ ነው" ስትል ከሰሰች፤ በወልዲያ በተፈጸመው ጥቃት ተሳትፈዋል አለች‼️
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኤርትራ መንግሥትና ህወሓት “ፅምዶ” በተሰኘ አዲስ ጥምረት “ኢትዮጵያን ለመውጋት” እየሰሩ ነው ሲል ከሰሰ።  በተጨማሪም በቅርቡ በአማራ ክልል ወልዲያ ከተማን ለመያዝ በፋኖ ሀይሎች በተፈጸመ ጥቃት ውስጥ ሁለቱ ተዋናዮች ተሳትፈዋል ሲልም ገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዎን ጤሞቲዎስ (ዶ/ር) የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ ለሆኑት አንቶኒዮ ጉተሬዝ መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም. በጻፉት ደብዳቤ፤ “በኤርትራ መንግሥትና በህወሓት አንጃ መካከል ያለው ቅንጅት ባለፉት ጥቂት ወራት ይበልጥ ግልጽ ሆኗል” ብለዋል።

ሚኒስትሩ በደብዳቤው ቅንጅቱ “በኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ለመክፈት በንቃት እየተዘጋጀ ነው” ሲሉ ገልጸው፤ ሁለቱንም ተዋናዮች “የግጭቱን አድማስ ለማስፋት እንደ ፋኖ ያሉ ታጣቂ ቡድኖችን በገንዘብ በመደገፍ፣ በማሰባሰብ እና በመምራት” ከሰዋል።

===================
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
3
የዩኒቨርሲቲ ምደባ‼️
የዩኒቨርስቲ ምደባ እየተጠባበቃችሁ ላላችሁ ተማሪዎች በሙሉ፤
የዩኒቨርስቲ ምደባችሁን በእነዚህ ሊንኮች ማየት ትችላላችሁ👇👇
Website: https://student.ethernet.edu.et
Telegram bot: @moestudentbot
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
3
ደመወዝ‼️
አዲሱ የፖሊስ አባላት የደመወዝ ስኬል ከላይ ተያይዟል።

==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍4
ባንኮቹ ምን ገጠማቸው‼️
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ ከትናንት በስተያ ማክሰኞ መስከረም 27/2018 ዓ.ም የመርሳ ቅርንጫፍ የሆኑት አቢሲንያ ፤አዋሽ፤ዳሽን፤አማራ፤ሂጂራ፤ቡና እና ዘምዘም ባንኮች ከቀኑ 10:00 ሰዓት ላይ በተመሳሳይ ሰዓት በታጣቂዎች ዝርፊያ መፈፀሙን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልጸዋል።
ዳሽን ባንክ ላይ ብቻ ከ5 ሚልዮን ብር በላይ ሳይወሰድ እንዳልቀረ የገለፁልን ሲሆን ከሌሎች ባንኮች አጠቃላይ ምን ያህል ብር እንደተወሰደ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ለ67 ሚሊዮን የስራ እድል‼️
በሕዝብ ቁጥር መጨመር ምክንያት ኢትዮጵያ ለ67 ሚሊዮን አዳዲስ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ማዘጋጀት አለባት ተባለ‼️
በኢትዮጵያ እየጨመረ በመጣዉ የህዝብ ቁጥር ምክንያት በመጪዎቹ ዓመታት ለ67 ሚሊዮን የሚሆኑ አዳዲስ ሠራተኞች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ግዴታ እንደሚኖርባት አዲሱ የአለም ባንክ መረጃ አመላከተ።

ይህም በአፍሪካ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ከናይጄሪያ እና ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቀጥሎ ኢትዮጵያን በሦስተኛ ደረጃ እንድትቀመጥ የሚያደርግ ከፍተኛ ፈተና ነው።

የዓለም ባንክ በሰጠው መረጃ መሠረት፣ በኢትዮጵያ በተለይም እኤአ እስከ 2050 ዓ.ም. ድረስ በ15-64 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው የሥራ ዕድሜ ህዝብ ቁጥር ዕድገት እጅግ ፈጣን ከመሆኑ የተነሳ ይህን ያህል ተጨማሪ የሥራ ዕድል መፍጠርን ይጠይቃል።

ተቋሙ የዚህን ፈተና መክበድ ምክንያት ሲያብራራ “የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው አጥጋቢ አለመሆን እና ፈጣን የህዝብ ቁጥር መጨመር” መሆኑን አክሏል።

ኢትዮጵያ ከናይጄሪያ፣ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ከታንዛኒያ እና ከዩጋንዳ ጋር በመሆን በአፍሪካ ከሰሃራ በታች ከሚጠበቀው አጠቃላይ የሥራ ዕድል ፈተና ግማሽ ያህሉን የሚሸፍኑ አምስቱ ሀገራት ውስጥ አንዷ ነች።

የአለም ባንክ ሪፖርት እንዳመለከተው፣ አፍሪካ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ለእያደገው ህዝቧ የሚፈለገውን ያህል ቋሚ ደሞዝ የሚያስገኝ ሥራ ለመፍጠር እየተቸገረች ነው። ይህም ወደ ከፍተኛ የችሎታ በታች መሥራት፣ ያለፍላጎት በግል ሥራ መተዳደር እና መደበኛ ባልሆነ የሥራ ዘርፍ መመደብ ምክንያት ሆኗል ሲል አስታውቋል።
Via Capital
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
አዲሱ ደመወዝ መክፈል ተጀምሯል‼️
ከመስከረም ወር ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ትናንት ጀምሮ ክፍያ መፈፀም የተጀመረ ሲሆን በርካታ ዩኒቨርስቲዎች መክፈል መጀመራቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።
እስከ መስከረም 30 ጭማሪው ደመወዝ እንዲከፍል አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ክፍያው እንዳይዘገይ አንዳንድ ተቋማት ጭማሪውን ከካዝናቸው ከፍለው ተመላሽ  (Refund) እንደሚደረግላቸው አቅጣጫ ተቀምጧል። ገንዘብ የሌላቸው አንዳንድ የክልል ተቋማት እና ከተማ አስተዳደሮች "ከዚህ ቀን እስከ እዚህ ቀን ባለው ውስጥ እንከፍላለን" በሚል ለሰራተኞቻቸው እያሳወቁ መሆኑን ገልፀውልናል።
==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ውሃ ይቋረጣል‼️
"የውሃ አገልግሎት ይቋረጣል" - ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን ‼️
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውሃ እና ፍሳሽ ባለሥልጣን የለገዳዲ ግድብ የጥሬ ውሃ ማስተላለፊያ ቫልቭ ቅየራ ስራ ከጥቅምት 2/2018 ዓም እስከ ጥቅምት 16/2018 ዓም ድረስ የሚከናወን መሆኑን ገልጿል።

የጥገና ስራው እስከሚጠናቀቅም በአንዳንድ የከተማዋ አካባቢዎች የውሃ አገልግሎት በከፊል እና ሙሉ በሙሉ የሚቋረጥ ይሆናል ብሏል።

የውሃ አገልግሎት በከፊል የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች :-

- በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2፣ 3፣ 5፣ 8፣ 9፣ 10 እና 13

- በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 11፣ 13 እና14

- በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ 2፣ 3፣ 7፣ 8፣ 10 እና 11

ስራው እስከሚጠናቀቅ የውሃ አገልግሎት በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ ስለሚቋረጥ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ሲል ባለሥልጣኑ አሳስቧል::
#==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
ብድር ለወሰዳችሁ ማስጠንቀቂያ‼️
#ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ኢትዮ ቴሌኮም አጋርነት በቴሌብር ማይክሮ ክሬዲት (እንደራስ) አገልግሎት በመጠቀም ብድር ወስደው የብድር ዕዳዎን በወቅቱ ስላልከፈሉ ያለብዎትን የብድር ዕዳ በአስቸኳይ እንዲከፍሉ በፍ/ብሔር ሕግ ቁጥር 1772 መሰረት የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል።
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🥰2
አምቡላንስን ለኮንትሮባንድ‼️
በምስራቅ ሸዋ ዞን መተሐራ ከተማ በአምቡላንስ ተሽከርካሪ ታማሚ የጫነ በማስመሰል በፍጥነት ሳይረን እያስጮህ የፍተሻ ኬላ ለማለፍ የሞከረ የአንቡላስ አሽከርካሪ በውስጡ 1.3 ሚሊዮን ብር  የሚገመት የኮትሮባንድ እቃ ጭኖ ሲጓዝ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል።
#==========≠============
💎⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass