G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
#Burkinafaso
ትራዎሬ በቅኝ ገዥዋ ፈረንሳይ ጄኔራል ቻርለስ ዲጎል ስም የነበረውን የቡርኪናፋሴን ዋና ከተማ ኡጋዱጉን ዋና ጎዳና በቶማስ ሳንካራ ስም ሰይሞ ቶማስ ሳንካራ በተገደለበት ስፍራ መታሰቢያ ሙዚየም በመገንባት እኔም ብሞት ሀገሬ ሌላ ጀግና ታፈራለች እንጅ ፈጽሞ እጅ አትሰጥም ሲሉ 15 የአርበኝነት ቀናትን አስጀምረዋል።
====================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
👍3
📚Anthropology Course

📖What is Anthropology?


📍It is a Subject that enables human beings to deal with themes such as culture, kinship(ዝምድና፣ጠንካራ ትስስር), marriage, cultural relativism, ethnocentrism, humanity(ሰውነት), human origins, cosmologies, race, ethnicity, ethnic relations, ethnic boundaries....

ለመግቢያ ያክል Anthropology ካላይ በዘረዘርናቸው ነገሮች ላይ ትኩረት ያደርጋል ካልን፣ አሁን የModuleኡን Content ደግሞ እንየው፦ በአጠቃላይ Anthropology Freshman Course 7 Chapter አለው!

ነገር ግን Generally Focus የሚያደርገው በሚከተሉት ላይ ነው፦

📍Scope of Anthropology
📍Branches of Anthropology
📍Unique features of Anthropology and
📍 Research methods in Anthropology


📖Unit One

🗒Introducing Anthropology and its Subject Matter


በዚህ Chapter ስር ስለ Anthropology ምንነት በሰፊው እናያለን፣ ትርጉሙን፣ ስፋቱን (ምን ምን እንደሚያጠቃል/Scope)፣ የAnthropologyን Subfeildኦች፣ መሰረታዊ የሆኑትን የAnthropology መርሆች እናያለን።

🔖Concepts in Anthropology

📍The term anthropology is a compound of two Greek Words
'anthropos' and
'logos'.


"Anthropos" ማለት 'Human being/Man kind) ሲሆን

"Logos" ማለት ደግሞ እንደምታውቁት "Study/Sceince/" ማለት ነው።

So, In General 'Anthropology means
The study or science of humankind or humanity.'


ስለዚህ በቀላሉ Anthropology ምንድነው ከተባለ ስለ ሰውነት (humanity) የሚያጠና ሳይንስ ነው ብለን መመለስ እንችላለን።

Definitionኡን በጣም Precise አድርገን (አጥብበን) ደግሞ ካየነው፦

📌Anthropology is the study of people---their origins, their development, and contemporary variations, wherever and whenever they have been found.

አያቹአ ስለ ሰው ልጅ መፈጠር🐣፣ ስለ እድገቱ🐥፣ ከዚያ ደግሞ የሰው ልጆች ልዩነት (በዘር፣ በቋንቋ..) እነዚህን እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች ይዳስሳል።

📌የAnthropology Scope ሰፊ ነው።👇👇
It is the study of humans as a group, from its first appearance on earth to its present stage of development.

አያቹ ይህን👆 ሁሉ ነገር ነው በውስጥ ያጠቃለለው [የሰው ልጅ ከተፈጠረበት አንስቶ እስካሁን ያለውን ያጠናል]


🔖The Historical Development of Anthropology

Anthropology did not arise as a science until the 1850s. Anthropology እንደ Science of Humanity መቆጠር የጀመረው በተለምዶ ምዕራባውያን "The West" ብለን በምንጠራቸው፣ Specifically ደግሞ France🇫🇷, Great Britain🇦🇺, USA🇺🇸 and Germany🇩🇪!

Historically Speaking, We can say that Anthropology is European discipline.

📖Generally speaking, anthropology as an academic discipline was born during the 19th century, out of the intellectual atmosphere of Enlightenment, which is the eighteenth century social philosophical movement.

ስለዚህ Anthropology 19th Century ውስጥ ሲወለድ መሠረቱ "Enlightment" እና "Darwin Theory of Evolution" ነበሩ።

📌Ethnography  is a branch of anthropology and the systematic study of individual cultures.
Ethnography ማለት የአንድን ግለሰብ🧔/ማህበረሰብ👨‍👨‍👧‍👧 ባህል ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ማጥናት ማለት ነው። ለምሳሌ፣ የሀገራችንን ባህል ማጥናት የፈለገ Anthropologist👨‍💼 መጥቶ በእኛ መካካል እየኖረ፣ ከእኛ ጋር እየበላ እየጠጣ..ባህላችንን ሲያጠና Enthnographic research ይባላል።

📌Ethnology is the comparative study of two or more cultures.
ይህ ደግሞ የተለያዩ ማህበረሰብን ባህል እያነፃፀራችሁ ስታጠኑ ምናምን Ethnology ይባላል።

📚Sub-fields of anthropology

There are four major sub-fields:

📍Physical/Biological Anthropology
📍Archeology
📍Linguistic Anthropology 📍Socio-Cultural Anthropology

1⃣Physical/Biological Anthropology

This branch Seek to understand how humans adapt to different environments, what causes disease and early death, and how humans evolved from other animals.

አንብባችሁታላ☝️ They are also interested in how biology and culture work together to shape our lives.

It has two broad Areas of investigation:

📌Human evolution is the study of the gradual processes of simple forms into more differentiated structures in hominid.

ይህም ብዙ sub branch አለው፣ ነገር ግን Major የሆኑት 2 አሉ።
1. Paleoanthropology is the study of human evolution through the fossil and archaeological records.
🔖ቀድሞ Record ተደርገው የተቀመጡትን መረጃዎች በመጠቀመ ስለ ሰው ልጅ Evolution ስናጠና ማለት ነው።

2. Primatology is the study of the behavior, biology, evolution, and taxonomy of nonhuman [gorillas, Chimpanzees] primates.

📌Human Genetics It focuses to examine the genetic materials of an organism such as DNA and RNA.
ይህ የሚያጠናው የሰው ልጅ የፊቱ መልክ፣ ቁመናው፣ በአጠቃላይ genetic ነገሩ ምናምን እንዴትና ለምን እንደዚያ እንደ ሆነ ነው።

2⃣Archaeological Anthropology

🔖Studies the ways of lives of past peoples by excavating and analysing the material culture/physical
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :
👍4🙏2
1.3 Unique/Basic Features of Anthropology

📌What Makes Anthropology Unique?

Anthropologyን ከሌሎች ተመሳሳይ Subjectኦች የሚለየው ነገር ምንድነው ካልን፣ የሚከተሉት ዋነኞቹ ናቸው፦
📌Its Scope
📌Its Approach
📌Its Focus
📌Its Method of Study.

1. Its Scope: Anthropology has broad Scope. It is the broad study of human kind, around the world and throughout time.

ከዚህ በፊት እንዳየነው Anthropology የሚያጠነጥነው (ይሄ word..😂) ብዙ ነገሮች ላይ ነው። ይህም ከሌሎች disciplineኦች ልዩ ያደርጓል።

2. Its Approach: In its approach anthropology is holistic, relativistic, and focused one.

📍Holistic: Holism means that an anthropologist looks at the entire context of a society when analysing any specific feature.
ለምሳሌ: አንድ Anthropologist👨‍💼 ስለ ኢትዮጵያ የቡና ስረዓት ማወቅ ከፈለገ የሀገሪቱን ባህል፣ ሃይማኖት፣ ታሪክ👑 በስፋት ማጥናት ይኖርበታል። ይህ ነው Holism የሚያስብለው።
📍Relativistic: Anthropology አንድን እምነት፣ ባህል...ሲያብራራ በራሱ Context ውስጥ ሆኖ ነው፣ ማለት ይህ ባህል መጥፎ ነው🙅‍♂ ወይም ጥሩ ነው💁‍♂ በሎ Judge አያረግም።
📍Focused: Anthropological studies give attention to how people perceive themselves and understand their world. ይሄኛውን አይነት Perspective Anthropologistኦች "Emic Perspective" ብለው ይጠሩታል።

3. Its Method of Study: Anthropology is highly dependent on qualitative research (quantitative ካለ እንዳትሸወዱ😎) to understand the meaning behind any human activity.

📖Misconceptions about anthropology

እስኪ የተለያዩ ሰዎች ስለ Anthropology ያላቸውን የተሳሳተ መረዳት እንመልከት፣

📌Anthropology is limited to the study of "primitive"👴 societies.
ነገር ግን ይህ ትክክል አይደለም! Anthropology ስለ ጥንት/ስለ ቀደሙት ሰዎች/ነገሮች ብቻ ሳይሆን በአሁን ዘመን ስላሉትም👱‍♂ የሚያጠና ነው!

📌Anthropologists only study the rural people and rural areas.
ነገር ግን ስለ urban Peoples እና ስለ urban areasም ያጠናል [Urban Anthropology].

📌Anthropology is the study/analysis of fossil evidences of the proto-humans like that of Lucy/Dinkeneshe.
ስለ እነዚህም ያጠናል ነገር ግን anthropology ስለ human Evolution ብቻ ነው የሚያጠናው ካልን ስህተት ነው።

እነዚህና የመሳሰሉት ማብራርያቸው ስለ anthropology የተሳሳቱ ናቸው! ድንገት ፈተና ላይ ከመጡ miss ልታረጓቸው አይገባም!👌

በቀጣይ Chapter 2 እንገባለን!🤗

ጥያቄ የሆነባችሁ ካለ


All Rights Reserved!


━━━━━━━━━━━━
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
━━━━━━━━━━━━
👍2🙏1
"ስፖርት መስራት እጀምራለሁ፣ አንድ መፅሀፍ በሳምንት አነባለው፣ በጠዋት እነሳለው፣ ራሴን አሻሽላለው" ብለህ ካሰብክ ቆየህ ፤ ግን መቼ ነው ወደ ተግባር የምትገባው? ሁልጊዜ ሰኞ ሲመጣ ወይ ወሩ ሲያልቅ፣ ወይ አመቱ ሲፈፀም ማቀድ አልሰለቸህም?
ወዳጄ ምግብ የበላ እንጂ ለመብላት ያሰበ አይጠግብም እኮ! መድሀኒቱን የዋጠ እንጂ ስለ መድሀኒቱ አብዝቶ ያወቀ አይድንም እኮ! ማወቅ ማሰብ ማቀድ አሪፍ ቢሆንም ተግባር ከሌለው ግን በዜሮ ነው ሚባዛው!
❗️ስለዚህ አንዱን ዕቅድ አሁኑኑ ጀምረው
መልካም ምሽት❤️

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
5
በኬንያ ጉንዳኖችን ደብቀው ከሃገር ሊያስወጡ የነበሩ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ከሃገር ሊወጡ የነበሩት ጉንዳኖች በአፍሪካ የሚገኙት ትላልቆቹ ጉንዳኖች እንደሆኑ ሲገለፅ እያንዳንዳቸው እስከ 220 ዶላር በእንግሊዝ ሻጮች በኩል እንደሚሸጡም ተገልጿል።

ግለሰቦቹ ጉንዳኖቹን በሲሪንጅ እና ትናንሽ ቱቦዎች ይዘው ሊወጡ የሞከሩ ሲሆን በእያንዳንዱ ቱቦ ውስጥ ሁለት ወይም ሶስት ጉንዳኖች እንደነበሩ እና ውስጡ ያለው ነገር እንዳይታወቅ በጥጥ ሸፍነውት እንደነበር አገልግሎቱ ገልጿል።

የጉንዳኖቹ መዳረሻ አውሮፓ ወይም እስያ እንደነበር ሲገለፅ የተያዙት ግለሰቦች ሁለቱ ቤልጂየማውያን፣ አንድ ቬትናማዊ እና ኬንያዊ መሆናቸው ተዘግቧል።

የዱር እንስሳት አገልግሎቱ ጉንዳኖቹ ከተወሰዱ በኋላ ልዩ መኖሪያ ወደ ተባለው ፎርሚካሪየምስ እንደሚኖሩ እና ቡድናቸውን ሲገነቡ ለመመልከት እንደሚፈልጓቸው ገልጿል።

ከኬንያ ሊወጡ ነበር የተባሉት ጉንዳኖች ሜሶር ሴፋሎቲስ ተብለው የሚታወቁ ሲሆን ወንዱ እስከ 20 ሚሊ ሜትር ሴቷ ደግሞ እስከ 25 ሚሊ ሜትር እንደምታድግ ተነግሯል።
BBC
===================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2🥰1😁1
በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ናይጄሪያዊያንን ያስለቀሰው የ500ሚሊየን ዶላር ማጭበርበር‼️
በሐምሌ ወር 2024 ላይ ናይጄሪያ ውስጥ የበርካታ ናይጄሪያዊያንን ሕልማቸውን እውን የሚያደርግ አንድ ድርጅት ብቅ አለ። 1000 ዶላር ኢንቨስት ያደረጉ ሰዎች በአንድ ወር ውስጥ ሌላ አንድ ሺህ ዶላር መሥራት ጀመሩ። ጭራሽ በሥራቸው ተጨማሪ ሰዎችን ማስገባት የቻሉ ሰዎች በየወሩ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ዶላር አካውንታቸው ላይ መጠራቀም ጀመረ። ገንዘባቸውን ማውጣት የፈለጉ ሰዎችም ለአካውንት ማረጋገጫ ከ100 እስከ 200 ዶላር ብቻ እየከፈሉ ትርፋቸውን ማውጣት ቻሉ። በእርግጥ በየወሩ ገንዘቡ እጥፍ እየኾነ ከመሄዱ አንፃር ገንዘቡን ለማውጣት የሚጣደፍ ብዙም ሰው አልነበረም። ገንዘብ ለማውጣት የቻሉ ሰዎች ግን ለወዳጅ ዘመድ እየደወሉ በዚህ እድል ተጠቀሙበት ይኸው እኔ አግኝቼበታለሁ፥ አውጥቻለሁ እያሉ የአካውንታቸውን ስክሪንሾት ማሰራጨት ያዙ። ባገኙት ድንገተኛ ገንዘብ ደስተኛ የኾኑ ሰዎች ዶላርና አካውንታቸውን እያሳዩ ቲክቶኩን ዳንስ በዳንስ አደረጉት።
በርካታ ናይጄሪያዊያን፣ የተወሰኑ ኬንያዊውን እና ሌሎችም FOMO(Fear of missing out) ውስጥ ገቡ። የቻለ ቁጠባውን፣ ያልቻለ እየተበደረ፣ አንዳንዱም ንብረቱን እየሸጠ የCBEX exchange አባል መሆን ጀመረ። በእርግጥም እንደተባለው የበርካቶች አካውንት
እያደገ ነው። ወደ 300 ሺህ የሚገመቱ ናይጄሪያዊያን ሕይወታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚቀየር አምነው እየተሳተፉበት ነው።
በApril 9, 2025 ገንዘባቸውን ለማውጣት ጥያቄ ያቀረቡ በርካታ ሰዎች ለማውጣት እንደተቸገሩ ወሬው በሶሻል ሚዲያ መዛመት ጀመረ። CBEX exchange የአካውንት ጠለፋ እንዳጋጠመውና በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልፆ ገንዘብ ለማውጣት የሚፈልጉ ተጠቃሚዎች አካውንታቸው የራሳቸው መኾኑን ለማረጋገጫ 100 ዶላር እየከፈሉ የወጪ ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ ገለፀ። በጠለፋ ዜናው የተደናገጡ ደንበኞች የተጠየቁትን ከመቶ እስከ ሁለት መቶ ዶላር ገንዘብ እያስገቡ ያላቸውን በሺዎች የሚቆጠር ዶላር ወጪ ለማድረግ ጥያቄ ማቅረባቸውን ቀጠሉ። ነገር ግን አካውንታቸው ቁጥር ብቻ ነበር። መጀመሪያ በኢንቨስትመንት ቀጥሎ ደግሞ በአካውንት ማረጋገጫ ስም ያስገቡት ዶላር የማይጨበጥ ጉም ኾነ። ከApril 14,2025 ጀምሮ የCBEX ዌብሳይት ጭራሽ ምላሽ መስጠት አቆመ። የሶሻል ሚዲያ አካውንቶቻቸውም ከጥቅም ውጭ ኾኑ። በአጠቃላይ ወደ 500 ሚሊየን ዶላር የሚገመት ገንዘብ የፖንዚ ስኪም ሰለባ ሆኖ ተጠናቀቀ።
እያንዳንዱ ተጠቃሚዎች ገቢ የሚያደርጉት ገንዘብ በTron Network በኩል 'እየታጠበ' ይሸሽ እንደነበረ ታወቀ።
መጭበርበራቸው የተገለጠላቸው ሰዎች ናይጄሪያ ውስጥ ወደሚገኙት ሶስቱ የድርጅቱ ቢሮዎች በብስጭት ቢተሙም የተወሰኑ ወንበርና ጠረጴዛ ከመሰባበርና ከጥቂት ኮምፒዩተሮች በስተቀር ለማግኘት የቻሉት ነገር አልነበረም።
ነገሩ ወደ ኋላ ሲጠነጠን CBEX የChina Beijing Equity Exchange የሚባለውን የቻይና ተቋምን ስም አስመስሎ ነው የጀመረው። ለዚህም እንዲያግዘው ካናዳ ውስጥ የተመዘገበ የክሪፕቶ ኤክስቼንጅ መኾኑን የሚያሳይ የተጭበረበረ ሰነድ አዘጋጅቶ የነበረ ሲኾን ናይጄሪያ ውስጥም ሶስት ቢሮዎችን ከፍቶ እየሠራ ነበር። እነዚህ ነገሮች ሰዎች በአቋራጭ ገንዘብ ለማግኘት ካላቸው ጉጉት ጋር ተደማምረው ይህ ሁሉ ሰው የማጭበርበሩ ሰለባ እንዲሆን እንዳደረገ ተነግሯል።
ሊቢያ ተሰድጄ ያመጣሁትን 1500 ዶላር ተነጠቅኩ ካለች ሴት ጀምሮ ቤታቸውን ሸጠው እስከከሰሩ ሰዎች ናይጄሪያዊያን ኡኡታ ላይ ናቸው። ዳሩ "ጅብ ከሄደ ውሻ ጮኸ" ከመኾን የሚዘል አይመስልም።
የዚን ያህል የተጋነነ ባይኾንም የፖንዚ ስኪም ዜና ለኢትዮጵያውያን አዲስ አይደለም። ፖንዚ ስኪም በባህርይው የማይለመድና ዘወትር መልኩን እየቀየረ የሚመጣ በመኾኑ ለጥንቃቄ እንዲሆን አጋራሁት።

Bottom line:
🚫 ገንዘባችሁን በአጭር ጊዜ ውስጥ እጥፍ አደርጋለሁ የሚል አካል ሲመጣ ደግማችሁ ማሰብ ሳያስፈልጋችሁ እምቢ በሉ። ገንዘብ እጥፍ ማድረግ የሚችል ሰው የራሱን ወይም የዘመዶቹን ገንዘብ እጥፍ ያደርጋል እንጂ እድሉን ለማያውቀው ሰው አሳልፎ አይሰጥም።
🚫 ገንዘብ ልታገኙበት የምታስቡት ነገር ገንዘቡ በትክክል እንዴት እንደሚመጣ በግልፅ ማወቅ አለባችሁ። የማይታወቅ ነገር ካለው probably it is a scam.
🚫 Crypto, Forex, Stock... የመሳሰሉት የትሬዲንግ ዓይነቶች ራሳቸውን የቻሉ በቂ እውቀት የሚያስፈልጋቸው እንደየሁኔታው high risk-high reward የኾኑ የቢዝነስ ዘርፎች ናቸው። ያለበቂ ዝግጅትና እውቀት የገባ ሰው ለፖንዚ ስኪምም ሆነ እንደ አንበጣ ለሚፈለፈሉ የስካም ዓይነቶች ተጋላጭ ይኾናል። እድል ቀንቶት የቱንም ያህል ገንዘብ ቢያገኝም በአንዲት ቅፅበት መልሶ ያጣዋል። It is that much dangerous!
እናም ወደ ክሪፕቶ፣ ፎሬክስ ወደመሳሰሉት ዘርፎች ለመሳተፍ ፍላጎት ያላችሁ ሰዎች ምንም ዓይነት አጓጊ እድል ቢቀርብላችሁ ገንዘብ ኢንቨስት ከማድረጋችሁ በፊት ጊዜ ወስዳችሁ ተማሩ።
#አዩዘሀበሻ
===================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
👍1
የ12ኛ ክፍል ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው‼️

🗣 ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንደሚሰጥ ጠቁመው " ይሄ አራተኛው ነው በአዲሱ የፈተና አሰጣጥ ፈተና የሚሰጥበት " ብለዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከትምህርት ቤቶች ወጥቶ ተማሪዎችን ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አስገብቶ ፈተና እንዲሰጥ እያደረገ መሆኑ አስታውቀው ትምህርት ሚኒስትሩ ስለዘንድሮው የ2017 ዓ/ም ፈተና 150 ሺህ ተማሪዎች ፈተናቸውን በኦንላይ እንዲወስዱ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፥ " እንደ ከዚህ ቀደሙ አድካሚ በሆነ ከቦታ ቦታ ልጆችን እያዘዋወሩ ከመሄድ ባለፈው ዓመት 29 ሺህ ተማሪ ነበር ኦንላይን ፈተና የሰጠነው ዘንድሮ ደግሞ 150 ሺህ ተማሪ ኦንላይን ፈተና ለመስጠት እየተዘጋጀን ነው " ያሉ ሲሆን ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን ቆርጠው ባይናገሩም ፈተናው ከአንድ ወር / ከአንድ ወር ተኩል በኃላ እንዲሰጥ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
===================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
የመውጫ ፈተና‼️
በሰኔ 2017 የሚሰጠውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ዳግም ለመፈተን እየተጠባበቃችሁ ያላችሁ አመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ሚያዝያ 14 /2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 05/2017 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመመዝገቢያ ቅፅ https://exam.ethernet.edu.et ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

ፈተናውን ለመውሰድ የብሔራዊ (ፋይዳ) መታወቂያ መያዝ ግዴታ ሲሆን፤ የአገልግሎት ክፍያ (500 ብር) በቴሌብር በኩል ብቻ የሚፈፀም መሆኑ ተገልጿል፡፡
===================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍3
ራሺያ ለቡርኪናፋሶ‼️
የቡርኪናፋሶ መሪ በሆነው ኢብራሂም ትራኣሬ ላይ ከቀናት በፊት ለ19ኛ ጊዜ የተቀነባበረ የግድያ ሙከራ መደረጉን ተከትሎ ትራኦሬ ለራሺያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አስቸኳይ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲደረግለት መጠየቁን እና ራሺያም የጦር መሳሪያ በአስቸኳይ ወደ ቡርኪናፋሶ ለመላክ ቁርጠኛ መሆኗን የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
የግድያ ሙከራው በፈረንሳይ የሚደገፍ በመሆኑ እና በሀገሪቱ የታጠቁ ቡድኖች ከፍተኛ ስጋት መፍጠራቸውን ተከትሎ ራሺያ ለቡርኪናፋሶ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንደምታደርግ ይጠበቃል።
ራሺያ እና ቡርኪናፋሶ በባለፈው ጥቅምት ወር በወታደራዊ ጉዳዮች በትብብር ለመስራት መስማማታቸው የሚታወስ ነው።
ትራኦሬ "ሀገሬ እና ህዝቤ ነፃ እስከሚወጣ ድረስ እዋጋቸዋለሁ" ብለዋል(አዩዘሀበሻ)።
===================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍31
#Factcheck‼️
ይሄ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ ተመልክተናል።
ይሄ መንገድ የተቆፈረው በአማራ ክልል ውስጥ ሳይሆን Umzinyathi በሚባል በደቡብ አፍሪካ አንዲት ከተማ ውስጥ ሲሆን እነዚህ ሰዎች መንገድ ለመቆፈር የተገደዱት ውሃ እና መብራት አልገባልንም በሚል ነበር።
ምስሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተነሳነው ከአምስት አመት በፊት November 24 2020 ላይ ነው።
የአማራ ክልል በመንገድ እጦት የሚሰቃይ ክልል እንደሆነ ይታወቃል። መንገድ የደም ስር እንደመሆኑ መጠን ያለውን መንገድ መጠበቅ እና ተጨማሪ መንገዶችን መስራት ለዚህም ተባባሪ መሆን ለአማራ ህዝብ ከሚቆረቆር ግለሰብም ይሁን ቡድን የሚጠበቅ ነው።
በዚሁ አጋጣሚ አጠራጣሪ ምስሎችን ሲያገኙ Tineye የሚባል ድረገፅ ላይ በማስገባት ምስሉ መቼ እና የት እንደተሳ ማረጋገጥ ትችላላችሁ።
አዩዘሀበሻ
===================
ትኩስ ያልተሰሙ መረጃዎችን ለማግኘት
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍7
የቡርኪናፋሶ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ አፍሪካውያን ለምን እርስበርስ ለመዋደድ እንደሚቸገሩ ሀሳባቸውን በቅርቡ አካፍለዋል።

🗣️🗣️ "አፍሪካን ስንመለከት ፈጣሪ ከባረካቸው እጅግ ሰላማዊ አህጉራት አንዷ ነች። አሁን ላይ በመካከላችን የምናያቸው ግጭቶች በዋናነት አውሮፓውያን አንዱ ሀገር ከሌላ ሀገር እንዳይዋደድ፣አብሮ እንዳይሰራ እና እንዳያድግ የመለያየት ዘር ስለዘሩ ነው።

እራሳችንን መጠየቅ አለብን፡ ለምንድነው አውሮፓውያን በአፍሪካውያን ዘንድ እንደምናየው እርስበርስ ሲጠላለፉ የማናየው? እነሱ እኛን ሆን ብለው እርስ በርሳችን እንድንጋጭ ስላደረጉን ነው። እነሱ አንድ ሆነው ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እንድንጠላ አስተምረውናል።

በአውሮፓ ውስጥ እንዲህ ዓይነቱን ክፍፍል ማየት ብርቅ ነው። ይህንን ተገንዝበን ጥላቻን ማቆም እና የተሻለች አፍሪካን ለመገንባት በጋራ መስራት አለብን" የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል(አዩዘሀበሻ)።
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍6🔥1
ራሺያ ሰራዊት ላከች‼️
ራሺያ በፑቲን ቀጥተኛ ትዕዛዝ የቡርኪናፋሶውን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ትራዎሬን ለመደገፍ  በከፍተኛ የስልጠና ብቃት ያጠናቀቁ ልዩ ኮማንዶዎችን ወደ ቡርኪናፋሶ መላኳን ከሀገሪቱ የዜና ምንጮች ለመረዳት ተችሏል።
ራሺያ ለቡርኪናፋሶ ልዩ ወታደሮችን ለመላክ ያስገደዳት በፈረንሳይ እና በሌሎች ሀገራት የተመራ ልዩ ገዳይ ቡድን ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ ተደጋጋሚ የግድያ ሙከራ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው።
ወደ ቡርኪናፋሶ ያቀኑት የራሺያ ወታደሮች የቡርኪናፋሶን ዋና አየር ማረፊያ እንደሚቆጣጠሩ ተጠቁሟል።
ከራሺያ በተጨማሪ ሰሜን ኮሪያ እና ቻይና ኢብራሂም ትራኦሬ ላይ አንዳች ነገር ቢፈጠር ዝም ብለን አናይም ማለታቸውን Burkina 24 አስነብቧል።
የራሺያው ፕሬዚደንት ፑቲን "እኛ እያለን ኢብራሂም ትራኦሬ  ላይ ምንም አይነት አደጋ አይደርስበትም ፣ አሜሪካ እና ፈረንሳይ የአንድ ነፃ አገር ፕሬዘዳንትን ይዘው የማሰር መብት የላቸውም ያሉ ሲሆን ሩሲያ ከቡርኪናፋሶ ምንም ነገር አትሰርቅም፣ ሀብት ብዝበዛ የማድረግ ፍላጎት የላትም ፍህታዊ  ንግድ እንዲኖር  እንፈልጋለን" ብለዋል።
እኛ ሀገራችን ላይ ሆነን ወደ  ቡርኪናፋሶ አገር ሳንገባ ቡርኪናፋሶ ያላትን ማእድን በራሷ አገር አምርታ በንግድ ስምምነታችን መሰረት  ወደ እኛ አገር መሸጥ ነው"ብለዋል።
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👏5
Crows anting behavior‼️
የአሞራ እና የጉንዳን ግንኙነት‼️
Crow የሚባለው አሞራ የህመም ስሜት ሲሰማው የጉንዳን መንጋ አጠገብ ይሄድና ክንፉን ይዘረጋል ጉንዳኖች ጠላት መጣ ብለው ጥቃት ይፈጽሙበታል።

ይሄን የሚያደርግበት በቂ ምክንያት አለው።ጉንዳን ሲነክሰው ሰውነቱ ውስጥ ፎርሚክ አሲድ ይገባል ይሄ ንጥረ ነገር ደግሞ በሽታን በተፈጥሮ መንገድ ይከላከልለታል፣ክንፎቹን ከባክቴሪያ እና ከሌሎች ተባዮች ያስለቅቅለታል።
ፎርሚክ አሲዱ አሞራው በሰውነቱ ውስጥ ያሉ እንደ ባክቴሪያ፣ፈንገስ፣ ትላትል፣.......ያስወግድበታል።
ተፈጥሮ ለሁሉም ፍጥረት ተመርምሮ የማያልቅ ጥበብ ሰጥቷል።
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍5
የትራኦሬ ጠባቂ‼️
የቡርኪናፋሶው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ትራኦሬ ጠባቂ እንዲህ ይላል…
“ኢብራሂም ትራኦሬ ለአምላኩ ተንበርክኮ በሚጸልይበት ወቅት እንድመታው አምስት ሚሊዮን ዶላር አቀረቡልኝ። ከዚህም በላይ ለእኔና ለቤተሰቤ የዚያን ሀገር ዜግነት እንደሚሰጡን ቃል ገቡልኝ። ይህን ጥያቄ እንዴት እንደምቀበል ሳስብ ተገረምኩ። ለእነርሱ ገንዘብ ከሰው ልጅ ክብር በላይ ነው ማለት ነው።”

“ራሴን ጠየቅሁ… አምስት ሚሊዮን ዶላር የጥፋተኝነት ስሜቴን እስከ ዘላለም ድረስ ሊሸፍንልኝ ይችላል? ይህ ገንዘብ በባዕድ ሀገር ንጉሥ ያደርገኛል ወይስ በወንዶችና በሴቶች ልጆቻቸው የሚሳለቁበት ሞኝ? በከተማቸው እንደ ውሻ ከመኖር በገዛ ምድሬ እንደ አንበሳ መኖር እመርጣለሁ!”
#አዩዘሀበሻ
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍41🥰1
ሰላም ውድ የዚህ ቻናል ቤተሰቦች እንዴት አመሻችሁ በያላችሁበት ሰላማችሁ ይብዛ እያልኩኝ መልካም ምኞቴን ጽጌልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው ::

እነሆ ዲቪ 2025 ሊወጣ ነው እና እንዲታይላችሁ የምትፈልጉ በዚህ አናግሩኝ ማለካም አዳር 🙏🙏

👇👇👇👇👇
@GT12192123

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ

👇👇👇👇👇👇

@GT12192123

#share
#share

🙏🙏🙏🙏🙏

🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝
JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝🔝
🙏3👍1