G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
351 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ መሪዎች ሰው መሆናቸውን እጠራጠራለሁ አሉ‼️

👉🏿 ከ50 ዓመታት የአህጉሪቷ የነጻነት ጉዞ በኋላ፣ ለህዝባችው አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ካላሟላችው ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?


👉🏿በወርቅ፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ፣ በዩራኒየም፣ በብረት፣ በማዕድን፣ በብር፣ በማግኒዥየም፣ በነሐስ፣ በጋዝ የተፈጥሮ ሃብቶቻችው ላይ ተቀምጣችው፣ ህዝባችው በረሃብ፣ በትምህርት አለመዳረስ፣ በጤና አገልግሎት እጦት፣ ቢሞት፣ ሰው ነን ብላችው ታምናላችው?

👉🏿በስልጣን ላይ ቆይታችው፣የራሳችሁን  ዜጎች ለመግደል ከውጭ የጦር መሣሪያዎችን ስታስገቡ፣ ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?

👉🏿የገዛ ዜጎቻችሁን እንደውሻ ስታንገላቱና ስትገድሉ፣ ማን ዜጎቻችሁን እንዲያከብር  ትጠብቃላችው?

👉🏿በራሳችው  አገር ላይ ቀማኛና ሌባ በመሆናችው ፣ የሃገራችሁን  ሀብቶች ሁሉ በመስረቅ፣ አብዛኞቹ ዜጋዎቻችው በስደትና በድህነት ውስጥ እንዲያልፉ ስታረጉ፣ የሰው ልጆ ነን ብላችው ታስባላችው?
ትራምፕ ይሄን የተናገሩት ሰሞኑን በዋሽንግተን ዋይት ሀውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መሆኑን ተመልክቻለሁ።
[አዩዘሀበሻ]
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍82
የፋይዳ መታወቂያ ግዴታ ሆኗል‼️
በአካል ኢትዮጵያ ውስጥ የማይገኙ ዜጎችና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንደ ዩናይት ዶት ኢቲ ያሉ አማራጮችን ተጠቅመው ፋይዳን ሳይዙ የባንክ አገልግሎት ማግኘት እንደማይችሉ ተገልጿል።

በቅርቡ በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንደ ቅደመ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ብሔራዊ ባንክ አቅጣጫ ማስቀመጡን ያስታወሰው መረጃው ይህው አሰራርም በውጭ የሚኖሩ ዜጎችን እንዲያካትት መደረጉን ነው የተናገረው።

ፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን መያዝ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የውጪ ሀገር ዜጎችንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚያጠቃልል መሆኑ ጭምር የተገለፀ ሲሆን መመሪያው በብሔራዊ ባንክ መውጣቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ መሥሪያ ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🤣2🥰1
ሰው ጨክኗል‼️
በአዲስ አበባ ከተማ ከ3ሚሊየን ብር በላይ የሚያውጣ የተበላሸ በርበሬ ተወገደ‼️
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ግምታዊ ዋጋው ከ3ሚሊየ ብር የሚያወጣ 100 ኩንታል ለምግብነት የማይውል የተበላሸ በርበሬ ማስወገዱን የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የምግብ እና መድኃኒት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስታወቀ።
በአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በ8864 ነጻ ስልክ ጥሪ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ሞቢል አካባቢ የበርበሬ ወፍጮ ቤት የተበላሸ በርበሬ እየፈጨ ለህብረተሰቡ እያከፋፈለ ይገኛል በሚል በተሰጠ ጥቆማ ነው የበርበሬ ምርቱ የተገኘው።

በዚህም  የቅርንጫፉ ባለሙያዎች በቦታው በመገኘት የተበላሸ እና ንጽህና በጎደለው አቀማመጥ  መሆኑን ባለሙያዎቹ  በማረጋገጣቸው እና በናሙና ምርመራ ለጤና ጎጂ ሆኖ በመገኝቱ መወገዱን ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🤯4🔥1😱1
በፍቺ ለተጠናቀቁ ትዳሮች ሞቅ ያለ ድግስ የሚደገስባት ሞሪታንያ‼️
👉የተፋቱ ሴቶች የበለጠ ለትዳር ይፈለጋሉ
በፍቺ ለተጠናቀቁ ትዳሮች ሞቅ ያለ ድግስ የሚደገስባት ሞሪታንያ
ሰሜን አፍሪካዊቷ ሞሪታንያ ከሌሎች ሀገራት ለየት ያለ ባህል ያላት ሀገር ነች፡፡ ከነዚህ መካከልም ትዳራቸውን በፍቺ ላጠናቀቁ ሴቶች ሞቅ ያለ ድግስ መደገስ አንዱ ነው፡፡
አምስት ሚሊዮን ገደማ ህዝብ ያላት ሞሪታንያ ከፍተኛ ፍቺ ከሚፈጸምባቸው ሀገራት መካከልም አንዷ ናት፡፡
በዚች ሀገር ባህል መሰረት አግብተው የፈቱ ሴቶች ገና ካላገቡት ይልቅ በወንዶች ተፈላጊ ሲሆኑ ይህም ያገቡት የተረጋጋ ትዳር ለመምራት ይጠቅማሉ፣ ችግር የመፍታት ልምድ አላቸው እንዲሁም ቤትን በጥበብ የመምራት ልምድ እንዳላቸው ይታሰባል፡፡
ይህን ተከትሎም አግብታ የፈታች ሴትን በድግስ እና በደስታ የመቀበል ባህሉ እያደገ መምጣቱ ተገልጿል፡፡
ያገቡ ሴቶች የበለጠ ተፈላጊ መሆናቸው ደግሞ ፍቺ እንዲበዛ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡
እንዲሁም አንዲት ሴት ትዳሯን በመፍታቷ እንዳይከፋት በሚል ሴቷን በድግስ መቀበል ተለምዷል፡፡
ትዳሯን ለፈታች ሴት በሚዘጋጀው ድግስ ላይ ከምግብ እና መጠጥ ባለፈ የሴቷን ውበት እና ስነ ልቦናዋን ከፍ የሚያደርጉ የስነ ጽሁፍ ዝግጅቶችም ይቀርቡበታል ሲል ቲአርቲ ዘግቧል፡፡
በተለይም የቀድሞ ባል እሷን በመፍታቱ እንዲጸጸት እና ዳግም ወደ እርቅ እንዲመጡ የሚያደርጉ ይዘቶችም ይቀርቡበታልም ተብሏል፡፡
እንዲሁም ይህ ሞቅ ያለ ድግስ ትዳሯን የፈታችው ሴት በቀጣይ ባል የሚሆናትን ወንድ ለመተዋወቅም እንደ ጥሩ እድል ተደርጎም ይወሰዳል፡፡
በጓደኞቿ እና የቅርብ ቤተሰቦቿ የሚዘጋጀው ይህ ድግስ ህይወት እንደሚቀጥል፣ በቀጣይ የተሻለ እድል ሊገጥማት እንደሚችል ማሳያ ተደርጎም ይቆጠራል፡፡
ይሁንና ዝግጅቱ በትዳር መካከል የሚወለዱ ልጆችን ሊጎዳ ይችላል፣ የኢኮኖሚ ድቀት እና ሌሎች ማህበራዊ ጉዳቶችን ያደርሳል በሚል ከስነ ማህበረሰብ ጥናት ባለሙያዎች ትችት ገጥሞታል፡፡
ሀገሪቱ ሴቶች በትዳር ውስጥ ምቾት ካልተሰማቸው በሰርግ ወቅት የወጣ ወጪን እና ለጥሎሽ የወጡ ወጪዎችን በመክፈል ወደ ቤተሰቦቿ ቤት እንድትመለስ የሚፈቅድ ህግንም ትከተላለች፡፡
የነዳጅ እና ብረት ማዕድን ሀብታም እንደሆነች የምትገለጸው ሞሪታንያ አብዛኛው ህዝቧ በግብርና ዘርፍ እና በድህነት ውስጥ የሚኖር ነው፡
#አል አይን
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
👍2🥰1
ፓስፖርት‼️
አዲሱ ፖስፖርት ዛሬ ይፋ ተደረገ‼️
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ዘርጋሁት ባለው የኢ-ፓስፖርት ሲስተም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የሚስጥራዊ ህትመትና ቴክኖሎጂ ልምድ አለው ከተባለው የጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ኢትዮጵያ አ.ማ አማካይነት ዘመኑ በደረሰበት የሚስጥራዊ ህትመት የታተመ አዲስ ፖስፖርት ዛሬ የካቲ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም ይፋ እያደረገ ነው፡፡
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍4
Update‼️
አሊባባ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ ከነገ ጀምሮ መቀበል ሊጀም መሆኑን አሳወቀ‼️
አለም አቀፉ ግዙፍ የኤሌክትሮኒክስ ግብይት ተቋም አሊባባ፣ ከሰኞ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በብር ክፍያ መቀበል እንደሚጀመር አሳዉቋል።
ይህ እርምጃ ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ በቀላሉና በአገር ውስጥ ገንዘባቸው እንዲገበያዩ ያስችላቸዋል።
አሊባባ ይህን ውሳኔ የወሰነው ለአፍሪካ ተጠቃሚዎች ይበልጥ ተደራሽ ለመሆንና በዓለም አቀፍ የክሬዲት ካርዶችና የውጭ ምንዛሬ ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ በማሰብ ነው ተብሏል። ይህ እርምጃ በአለም አቀፍ የክፍያ ስርዓት ምክንያት ለአፍሪካውያን ትልቅ እንቅፋት የነበረውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ መሆኑም ተሰምቷል።

ይህም ማለት አሁን ኢትዮጵያውያን በአሊ ኤክስፕረስ ላይ የተለያዩ እቃዎችን ሲገዙ በብር ገንዘባቸው ክፍያ መፈጸም ይችላሉ። አሊባባ ይህን ለማሳካት በኢትዮጵያ ካሉ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ትብብር መፍጠሩን አስታውቋል።
====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍1👏1
ሰላም ነው አይደል
"ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ"
💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢

ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ
ከወንዙ በወድያኛው ዳር
ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።
ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ።
በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።

ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?"
አለው።

ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?"
በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም
የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም
የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።

ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው
መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም።
ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ
ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው
ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡
ስለዚህ የሰዎችን የህይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ህይወት አምጥተን ለመትግበር
ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን።
መልካም ቀን
👍6👏1
"ደሃ ስትሆን ሰላምታህ ጭምር ልመና ይመስላቸዋል"እንደሚባለው..👇
አንድ የዋይት ሀውስ ሪፖርተር  " ለመሆኑ ሱፍ ታውቃለህ እንዴ? እንዴት አሜሪካ ፕሬዚዳንት ፊት፣ በዚህ በትልቅ መድረክ ላይ ሱፍ ሳትለብስ መጣህ? ሲል ይጠይቃል።
ዘለንስኪ:- "ሱፍ ጦርነቱ ካለቀ በኋላ እለብሳለሁ፣ለጦርነት ሱፍ ምን ይሰራል" ብሏል።
ትራምፕ:- ዘለንስኪን በሚቀበሉበት ወቅት"ዛሬ ጥሩ ለብሷል"ሲሉ ተሳልቀውበታል።
"ደሃ ስትሆን አሜሪካ ጋር ሉዓላዊነት የሚባል ነገር አይሰራም"።
Take a lesson from this.

====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍1🥰1
በአፍሪካ ከፍተኛ የግብረ ሰዶማውያን ቁጥር የሚገኙባቸው 10 ሀገራት‼️
1.ደቡብ አፍሪካ/especially in cape town/
2.ኬንያ
3.ሲሸልስ
4.አንጎላ
5.ሞዛምቢክ
6. ናሚቢያ
7.ቦትስዋና
8.ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ
9.ኬፕ ቨርዴ
10.ሌሴቶ ናቸው።

====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👏2👍1
ከ1884-1885 ሰባት ዋና ዋና የአውሮፓ ሀገራት በንግድ ሰበብ አፍሪካን ለመቀራመት በጀርመን በርሊን/Berlin conference/ ድብቅ ውሳኔ አሳለፉ፣ማን ማንን መውረር እንዳለበት ተስማሙ።
ብዙ የአፍሪካ ሀገራት የአውሮፓውያንን ቅኝ ግዛት ተጎነጩ። የብዙ የአፍሪካ ሀገራት ባህላቸው፣ ወጋቸው፣ሀይማኖታቸው፣ ነፃነታቸው፣ታሪካቸው ጠፋ፣ተበረዘ። ቋንቋቸው ተቀየረ፣በቅኝ ግዛት ማቀቁ፣የባሪያ ንግድ ሰለባ ሆኑ፣ብዙዎች የውቅያኖስ ሲሳይ ሆኑ፣በሀገራቸው ባይተዋር ሆኑ፣እንደሰው ሳይሆን እንደ እንስሳት ተቆጠሩ፣ንብረታቸውንና ማዕዳናቸውን እራሳቸው ጭነው እራሳቸው ውቅያኖስ አቋርጠው ለአውሮፓውያን አስረከቡ።
በወቅቱ ኢትዮጵያን ለመውረር እና ቅኝ ግዛት ለመግዛት የተመደበችው ጣሊያን ግን ድል አልቀናትም፣በኢትዮጵያ ጀግኖችና ብልሃተኛ መሪዎች እና አባቶች አድዋ ላይ ተደባይቶ ተመለሰ።
የአድዋ ድል በወቅቱ በጨለማ ውስጥ ለሚገኙት የአፍሪካ ሀገራት የጨለማ ውስጥ ችቦ ለኮሰ፣የነፃነት ተምሳሌት ሆነ፣የጥቁር ህዝቦች ኩራት ሆነ፣ኢትዮጵያም በቅኝ ግዛት ሳትገዛ፣ቋንቋዋ፣ባህሏ፣የአመጋገብ ስርዓቷ፣ሀይማኖቷ...ሳይበረዝና ሳይጠፋ በኩራት የአፍሪካ ተምሳሌት ሆነች።
አድዋ ፍቀህ የማጥለው፣ልትበርዘው የማትችለው የኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆን ነፃነትን ለሚሹ ፍጡራን ሁሉ ተምሳሌት ነው።
"ከላይ ያስቀመጥኩት ምስል አፄ ምኒልክ መጋቢት 23 ቀን 1888 ለፈረንሳዩ ጓዳቸው የፃፉት የድል ደብዳቤ ነው።
ክብር ለጀግኖች አባቶቻችን❗️
እንኳን አደረሳችሁ

====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🔥2👍1
እንኳን ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

#Ethiopia   #ኢትዮጵያ   #Adwa  #share #GTutorialclass
🙏2
ናይጀሪያ በጾም ሰዓት ምግብ ተመግበዋል በሚል 25 ሰዎችን አሰረች‼️
የናይጀሪያዋ ኮኖ ግዛት በረመዳን የጾር ላይ ምግብ ሲመገቡ አግኝቻቸዋለሁ ያለቻቸውን 20 ሰዎች ስራለች፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አምስት ሰዎች ደግሞ ምግብ ሲሸጡ ነበር በሚል የጣሰሩ ሲሆን ሁሉም ታሳሪዎች በሸሪዓ ህግ እንደሚዳኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በዚች ግዛት በእስልምና የጾም ወር ወቅት በአደባባይ ምግብ መመገብ ክልክል ነው፡፡

የግዛቲቱ ፖሊስ ያልተገባ የጸጉር አቆራረጥ፣ የተገላለጠ እና ሰውነትን የሚያሳይ አለባበስ የሚከተሉ ሰዎችን እንደሚያስር አስጠንቅቋል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት በነበረው ተመሳሳይ የጾም ወቅት ፖሊስ የማይጾሙ ሰዎችን አስሮ የነበረ ሲሆን ታሳሪዎቹ እንደሚጾሙ ቃል መግባታቸውን ተከትሎ ከእስር ተለቀው ነበርም ተብሏል፡፡

====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👍2