G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
"አብዛሀኞች ሴቶች ቆንጆ ከሆኑ ፡ ሀና ሴት ከሆነች ስለዚህ ሀና ቆንጆ ናት" ተመልከቱ እዚጋ🥺

አብዛሀኞቹ ሴቶች ቆንጆ ናቸው ፡ ሀና ሴት ናት። ታዲያ ሀና ከአብዛሀኞቹ ሴቶች ውስጥ የመሆን ዕድሏ ከፍተኛ ነው ፡ ስለዚህ ሀና ቆንጆ የመሆን ዕድሏ ከፍተኛ ነው። ማለትም ድምዳሜ ዕውነት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ስለዚህ Inductive argument ነው። so,

እንዴት ነው ሀና ከ አብዛሀኞቹ ሴቶች (most women are beautiful) የመሆን ዕድሏ ከፍተኛ የሆነው🤔? Probability ተምራችሗል ኣ።

🌷Argument I- Deductive
🌷Argument II- Inductive

እስቲ ለጫላ ሞቅ ያለ ጭብጨባ አጨብጭቡለት👏👏

😊ልዩነቱ በደምብ እንዲገባችሁ ብዬ ነው ነው እንጂ Deductive argument ን ባለፈው ተምረናል። ዛሬ የምንማረው Inductive argument ን ነው።

👩‍💻 እሺ አሁን ደግሞ የምንማረው አንድ argument Inductive argument መሆኑን ለማወቅ የሚረዱን መለያ ዘዴዎችን ነው። ሶስት መለያ ዘዴዎች አሉ።

1) The actual strength of the inferential claim between the premises and the conclusion.

2) Indicator words.

3) character or form of argument.

ሶስቱንም ዘዴዎች በደምብ እንመልከታቸው😊

1) The actual strength of the inferential claim between the premises and the conclusion.

ይህ ዘዴ ቅድም የነገርኳችሁ ነው። ማለትም ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው ብለን በአምሮኣችን assume እናደርጋለን። ስለዚህ ማስረጃዎቹ እውነት ናቸው። ታዲያ ማስረጃዎቹ እውነት ሁነው ፡ ድምዳሜው ውሸት የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ ከሆነ(improbable) ወይም ዕውነት የመሆን ዕድሉ ከፍተኛ ከሆነ Inductive argument ይባላል።

2) 🌹Indicator words

አንድ argument Inductive መሆኑን ለማወቅ ከምንጠቀምባቸው ዘዴዎች አንዱ indicator words ን መጠቀም ነው።

🎈Inductive argument ማለት ማስረጃዎቹ ለ ድምዳሜው በአብዛሀኛው(80% 90%) ዋስትና የሚሆኑበት ሒደት ነው። ታዲያ ማስረጃዎቹ ለድምዳሜው በአብዛሀኛው ዋስትና መሆናቸውን ለማመልከት ጠቋሚ ቃላትን እንጠቀማለን። እነዚህ ጠቋሚ ቃላት Inductive indicator words ይባላሉ። ታዲያ እነዚህ ጠቋሚ ቃላት ምን ምን ናቸው🤔?

🔥Inductive indicator words👇

📍Probably(probable)
📍Improbably(improbable)
📍Plausibly(plausible)
📍Implausibly(implausible
📍Likely
📍Unlikely
📍Reasonable to conclude

ስለዚህ እነዚህን👆ጠቋሚ ቃላት ድምዳሜው(conclusion) ላይ የሚጠቀም argument Inductive argument ይባላል። እስቲ ምሳሌዎችን እንመልከት☺️

🔷Example 1

The Vast majority of film actors are charismatic.
Teddy Afro is a film actor.
Therefore, probably Teddy Afro is charismatic.

🔷Example 2

It has rained for the past five consecutive days. Therefore, it is likely to rain today.

👆ስለዚህ Example 1 እና Example 2 Inductive argument ናቸው ማለት ነው። ምክንያቱም probably እና likely የሚባሉ Inductive indicator words ስለተጠቀሙ።


👐🙌👐 ክቡራት እና ክቡራን ተከታታዮቻችን ከመሸጋገሪያ ወሬ በሗላ ተመልሰን እንመጣለን ፡ አብራችሁን ሁኑ።

"ወሬ ወሬ አይ ወሬ ኸረ ወሬ..😁 እስቲ አንድ ወሬ ላውራችሁ ፈታ በሉልኝ ውዶቼ::"

"የመጀመሪያ አመት የግቢ ተማሪ እያለሁ Dynamics የሚባል ኮርስ ወስጃለሁ። እናንተም General Physics ላይ ትወስዱታላችሁ። እና ምን ተፈጠረ መሰላችሁ👶። highschool እና pre ላይ ስንማር normal force ማለት ዕቃዎችን ደግፎ የሚይዝ upward force ነው እየተባልን ነው የተማርነው። እና Dynamics ኮርስ ላይ ስንማር ግን መምህሩ downward force ነው አለ። ከዛ አንድ የክላሳችን ተማሪ ምን አለ መሰላችሁ "ቲቸር normal force እኮ downward ሆነ ማለት እኔን ወደ ላይ ደግፎ የሚይዘኝ force ስለማይኖር ተገልብጬ በጭንቅላቴ ነው የምራመደው ማለት ነው ፡ ስለዚህ ይህን ኮርስ አልማርም ብሎ ክላሱን አቋርጦ ወጣ😂

😎ውድ የ A+ tutorial class ቤተሰቦች ከመሸጋገሪያ ወሬ ተመልሰናል። የትምህርት ጊዜ☺️፡ ዳይ ወደ ትምህርት።


3) 🌹Character or form of argument.

አንድ argument Inductive መሆኑን ከምናውቅባቸው ዘዴዎች አንዱ form of argument ነው። form of argument ማለት ደግሞ argument ቱ የሚመሰረትበት ወይም የሚቀርብበት መንገድ ነው።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት Form of argument በሙሉ Inductive argument ናቸው ናቸው።👇

🎈 A) Prediction.

🎈 B) Inductive Generalization.

🎈 C) Casual inference.

🎈 D) Argument based on sign.

🎈 E) Argument from authority.

🎈 F) Argument from Analogy.

እስቲ እያንዳንዳቸውን እንመልከት።

📍Prediction

Prediction - is an argument that predicts what will happen in the future based up on what has happened in the past or in the present.

🗣Prediction ማለት ከአሁን በፊት(past) የነበረን ማስረጃ ወይም አሁን(present) ላይ ያለን ማስረጃ መሰረት በማድረግ ስለ ወደፊቱ መተንበይ ማለት ነው።

😴ለምሳሌ፡ ዛሬን ጨምሮ ለ 3 ተከታታይ ቀናት ዝናብ ቢዘንብ።ይህን እንደ ማስረጃ ተጠቅመን ነገም ዝናብ ይዘንባል ብለን ብንተነብይ prediction ነው ማለት ነው። so,

" It has rained for three consecutive days.As a result, it will rain tomorrow."

📍Inductive Generalization

Inductive Generalization - is an argument that procedes from the knowledge of a selected sample to some claim about the whole group or population.

☹️ በቅድሚያ ሁለት ነገሮችን እንረዳ።

🎯 population- ማለት አንድ የሆነ ስብስብ ወይም ቡድን ማለት ነው።

🎯Sample - ማለት ደግሞ ከስብስቡ ወይም ከቡድኑ መካከል ለ ናሙና የተመረጡ አካላት።

ለምሳሌ: በአንድ ክላስ ውስጥ 40 ተማሪ ቢኖር። ከ 40 ው ተማሪ የ 10 ተማሪ ውጤት randomly ተመርጦ ቢታይ።

40 ው ተማሪ population ይባላል። 10 ሮቹ ተማሪዎች ደግሞ sample ይባላሉ።

🤔ታዲያ Inductive Generalization ማለት ከ ቡድኑ ወይም ከስብስቡ መካከል ለናሙና የተመረጡ አካላትን
እንደማስረጃ በመጠቀም ስለ ቡድኑ ድምዳሜ መስጠት ማለት ነው።

ለምሳሌ፡ በአንድ ክላስ ውስጥ 40 ተማሪ ቢኖር እና ከ 40 ው ተማሪ የ 10 ሩ ተማሪ ውጤት randomly select ተደርጎ ቢታይ ና የ 10 ሩም ተማሪ ውጤት ከፍተኛ ቢሆን፡ የ 10ሩን ተማሪዎች ውጤት እንደ ማስረጃ ተጠቅመን የዚህ ክላስ(40) ተማሪዎች ውጤት ከፍተኛ ነው ወይም ጎበዝ ናቸው። ብለን ድምዳሜ ብንሰጥ Inductive Generalization ይባላል።

ሌላ ምሳሌ፡

ምርጫ እየደረሰ ነው😩። የአፍሪካ ተስፋዋ ምርጫ ሳይሆን አብዮት እና አመፅ ነው😂

😂 Etv አንዳንድ የ አዲስ አበባ ነዋሪዎችን(ለምሳሌ 2000ነዋሪዎችን) በ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማንን ትመርጣላችሁ ብሎ ቃለ መጠይቅ ቢያደርግ እና ከ 2000 ነዋሪዎቹ 1500 ዎቹ ኢዜማ ን እንመርጣለን ቢሉ። ይህን እንደ ማስረጃ በመጠቀም አብዛሀኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ኢዜማን ነው የሚመርጠው ተብሎ ድምዳሜ ቢሰጥ argument ቱ Inductive Generalization ነው ማለት ነው።

📍 Casual inference

Casual inference - is an argument that procedes from the knowledge of a cause to the knowledge of effect or from the knowledge of effect to the knowledge of cause.

Casual inference ማለት ምክንያትን እና ውጤትን መሰረት በማድረግ የሚመሰረት ነው።

🎯አንድ መንስኤ ቢኖር እና የዛ መንስኤ ውጤቱ እንደዚህ ነው ብለን ብንደመድም cause to effect ይባላል።

ለምሳሌ ፡ ውሀ ፍሪጅ ውስጥ ብታስቀምጡ እና ወደ በረዶነት ቢቀየረር(cause) ፡ ከዛ ውሀው በረዶ ሁኗል ወይም freez አድርጓል (effect) ብላችሁ ድምዳሜ ብትሰጡ።

🎯 አንድ ውጤት ቢኖር እና ለ ውጤቱ መንስኤው ይህ ነው ብለን ድምዳሜ ብንሰጥ effect to cause ይባላል።

ለምሳሌ፡ አንድ ተማሪ ፈተና ቢውድቅ(effect) ፡ የወደቀው እኮ ጠንክሮ ስላላጠና ነው(cause) ብለን ድምዳሜ ብንሰጥ።

📍Argument based on sign.

is an argument procedes from the knowledge of a sign to claim about a thing or situation that the sign symbolizes.

Argument based on sign ማለት የምናያቸውን እና የምናስተውላቸውን ምልክቶች እንደ ማስረጃ በመጠቀም ምልክቱ ስለሚወክለው ነገር ድምዳሜ መስጠት ማለት ነው።

ለምሳሌ፡ 😳አያድርገው እና ቤታችሁ ተዘርፎ ፡ ጧት ከእንቅልፋችሁ ስትነሱ የፊት ለፊት እና የሗላው መስኮት ብርግድ ብሎ፡

የፊት ለፊት መስኮቱ ላይ የእግር ዱካ(ለምሳሌ ጭቃ ነገር) ብታዩ፡ መስኮቱ የተሰበረበት መስበሪያ ሽቦ ነገር ብታዩ፡ እነዚህን ምልክቶች እንደ ማስረጃ ተጠቅማችሁ ፡ ሌቦቹ የገቡት በፊት ለፊት ባለው መስኮት ነው ብላችሁ ድምዳሜ ብትሰጡ argument based on sign ይባላል። so,

"Although both the front and rear doors were found open after the burglary, there were pry marks around the lock on the front door and deposits of mud near the threshold. Therefore, it follows that the thief entered through the front door."

📍Argument from authority.

is an argument that concludes something is true because a presumed expert or witness has said that it is.

Argument from authority ማለት በአንድ ሙያ ላይ የተሰማራ እና የተካነ ሰው በሙያው ዙሪያ ስላላ ነገር ሀሳብ ቢሰጥ ፡ የባለሙያውን ሀሳብ እንደ ማስረጃ በመጠቀም የባለሙያው ሀሳብ ትክክል ነው ብሎ ሌላ ሰው ድምዳሜ መስጠት ማለት ነው። ስለዚህ ሁለት ሰዎች አሉ ማለት ነው😊። እነርሱም

ሰው 1: በአንድ ነገር ላይ ባለሙያ የሆነ ሰው(ለምሳሌ ፡ ዶክተር ÷ ቄስ ÷ ሳይንቲስት÷ ኤኮኖሚስት ወዘተ) እና በሙያ ዙሪያ ስላለ ነገር ሀሳብ የሰጠ።

ሰው 2: የ ሰው 1 ን ወይም የባለሙያውን ሀሳብ እንደ ማስረጃ በመጠቀም የባለሙያው ሀሳብ ትክክል ብሎ ድምዳሜ የሚሰጠው።

ምሳሌዎችን እንመልከት፡

"James Dobson, founder of focus on the family, says that Men has divine obligation to lead their families and women has divine obligation to submit to their husband's order. Given Dobson's apparent ability to receive message from God, we must conclude that his statement is true."

👆ይኸን argument ተመልከቱ። ሁለት ሰው አሉ።

ሰው 1: James Dobson የሀይማኖት መሪ ነው። ካለው የሀይማኖት ዕውቀት አንፃር ሴቶች ለ ባሎቻቸው ይገዙ ፡ ባሎችም ቤተሰባቸውን በአግባቡ የመምራት ሀላፊነት አለባቸው ብሎ ሀሳብ የሰጠ።

ሰው 2: James Dobson የሀይሜኖት መሪ ስለሆነ ከፈጣሪ መልዕክት ስለሚላክለት ፡ የሱ ሀሳብ ትክክል ነው ብሎ ድምዳሜ የሰጠ።

😁ስለዚህ በአንድ ሙያ ላይ የተሰማራ ሰው በሙያው ዙሪያ ስላላ ነገር ሀሳብ ቢሰጥ እና የባለሙያውን ሀሳብ እንደማስረጃ በመጠቀም ሀሳቡ ትክክል ነው ብሎ ሌላ ሰው ድምዳሜ ሲሰጥ argument from authority ይባላል።

📍Argument from Analogy.

is an argument that depends on analogy or similarity between two things or state of affairs.

Argument from Analogy ማለት ሁለት አካላት በሆኑ ነገሮች ቢመሳሰሉ እና ይህን መመሳሰላቸውን እንደ ማስረጃ በመጠቀም በሌላም ነገር ይመሳሰላሉ ብሎ ድምዳሜ መስጠት ማለት ነው። ለምሳሌ፡

👩‍🏫 Mekdes is beautiful, tall and clever.
👩‍💼Sara is beautiful and tall.
Therefore, Sara is clever.

አሁን ተመልከቱ መቅደስ እና ሳራ ሁለቱም ቆንጆ ናቸው፡ ረዝም ናቸው። እና ደግሞ መቅደስ ጎበዝ ናት። በቁንጅ ና በቁመት ይመሳሰላሉ። ይህን መመሳሰል እንደ ማስረጃ በመጠቀም በጉብዝናም ይመሳሰሉ ብሎ ድምዳሜ መስጠት ማለትም እንደ መቅደስ ሳራም ጎበዝ ናት ብሎ ድምዳሜ መስጠት።

ሌላ ምሳሌ፡
➡️Facebook is a social media and has many users.
➡️Telegram is a social media and has many users.
➡️ Facebook gets 500 Millon dollars per year.
➡️ Therefore, Telegram also gets 500 million dollars per year.

አያችሁ ኣ😂
ፌስ ቡክ እና ቴሌግራም ሁለቱም ማህበራዊ ሚድያ ናቸው ፡ ብዙ ተጠቃሚ አላቸው። እና ደግሞ ፌስ ቡክ በአመት 500 ሚሊዬን ዶላር ያገኛል። ሁለቱም ማህበራዊ ሚዲያ በመሆናቸው እና ብዙ ተጠቃሚ በመኖራቸው ይመሳሰላሉ። ይህን መመሳሰል እንደ ማስረጃ በመጠቀም ቴሌግራምም 500 ሚሊየን ዶላር ያገኛል ብሎ ድምዳሜ መስጠት።

©A+ tutorial class
🙌 ሰላም ሰላም ቤተሰቦቻችን እንዴት ናችሁ። በትናንቱ የሎጂክ ትምህርት ላይ argument based on sign, argument from authority እና argument from analogy አልተካተቱም ነበር። ዛሬ edit አድርጌ አካትቻቸዋለሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

Deductive እና Inductive argument ላይ ያልገባችሁን ማንኛውንም ጥያቄ በ @Inquiry_receving_bot ላይ መጠየቅ ትችላላችሁ።

በተረፈ ብዙ ጥያቄ ስለሚወጣበት ትኩረት ሰጥታችሁ አንብቡት።

😎ቡሗላ ላይ የ psychology worksheet ይለቀቃል። እሁድ psychology ፈተና ከ 30% ይኖራችሗል። ከ 1 እስከ 5 ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ይሸለማሉ።

©A+ tutorial class
ለተወሰኑ ደቂቃዎች ስለዘገየን በጣም ይቅርታ።

የተሰጠው ሰአት 45 ደቂቃ።

ሙሉ ስማችሁን በመፃፍ መልሳችሁን በ @Ucan_scorebot ላይ መላክ ትችላላችሁ።
AnswerForThe Worksheet.pdf
26.4 KB
Quiz bot ለምትፈልጉ👇
ተወዳጆች ሆይ ሰላማችሁ ይብዛ በያላችሁበት🙌

ዛሬ የ psychology worksheet መልስ ይለቀቃል።

📍ከ 30% የ psychology ፈተና የምትፈተኑት ነገ እሁድ 11:00 ሰአት ላይ ነው።

📚 ፈተናው የሚሰጠው በሁለት አይነት መንገድ ነው።

🎈1ኛው) በ quiz bot
🎈 2ኛው) በ pdf

ስለዚህ ከሁለት አንዱ በተመቻችሁ መንገድ መስራት ተችላላችሁ።

መልካም ዕድል😊

ለጥያቄ ለአስተያት @Ucan_scorebot ን ይጠቀሙ።
Psycho2 WoRksheet.pdf
23.4 KB
Psychology Test
[Prep. By A+ Tutorial Class]
Unit 1 And Unit 2

1. The selectivity of perception implies that our feild of experience is divided into
A. Attention
B. Focus and margin
C. Absolute and difference threshold
D. It is undivisible

2. The first-born children get more attention from parents, from the factors of attention this could imply that:
A. Repetition
B. Movement
C. Expectancy
D. Novelty

3. Items which are close together in space or time tend to be perceived as belonging together or forming an organized group. This imlies which law of perceptual Organization
A. Similarity
B. Closure
C. Proximity
D. Continuation

4. _____the degree of difference between the image of an object that are focused on the two retinas.
A. Difference Threshold
B. Retinal Disparity
C. Relative Threshold
D. Retinal increase

5. Which of the following couldn't be one of the Goals of Psychology
A. Perception
B. Description
C. Prediction
D. Explanation

6.___________refers to modifying the behaviour from undesireable one to desirable one.
A. Description
B. Shifting
C. Control
D. Prediction

7. Which of the following research method allows researchers to study the cause and effect relationship between variables.
A. Experimental research
B. Correlational research
C. Descriptive research
D. Predictive research

8. The binocular cue for depth perception based on signals from muscles that turn the eyes to focus on near or approaching object is called:
A. Convergence
B. Retinal disparity
C. Shape constancy
D. Interposition

9. In an experiment, Naol is going to investigate how alcohol affects aggression. The number of alcoholic drinks the subject has is called:
A. Dependent variable
B. Independent variable
C. Controlled variable
D. Experimental variable

10. What are formed whenever a marked difference occurs in the brightness or color of the background?
A. Organization
B. Brightness constancy
C. Difference threshold
D. Contour

11. Sigmund Freud was the Founder of School of thought called Psychodynamics.
A. True
B. False

12. Gestalt psychologists argued that the mind is not made up of combinations of elements, rather They held that "the whole is greater than the sum of its parts"
A. True
B. False

13. Motion parallax is the tendency to perceive ourselves as passing objects faster when they are closer to us than when they are farther away.
A. False
B. True

14. List at least three monocular cues?

15. What helps you in general to separate the figure from the general around in your visual perception?

Your Answer on👇👇
@Ucan_scorebot

©A+ Tutorial Class
ብዙዎቻችሁ ፈተናውን ሰርታቹታል፣
እኛም ልፋታችን በከንቱ እንዳልሆነ
አረጋግጣቹልናል👏👏👏

ውጤታችሁ በቅደም ተከተል👇

[30/30]😯😯
🥇Muba Abdu
🥈Meklit Fiseha
🥉Bery Tadese
4. Miita J
5. Deribewu Shimelis
6. B A
7. ...who knows@
8. Abubeker Mohammed
9. M/A @MelkemariamAyana
10. Ashenafi Alemu

[28/30]😮😮
11. the villager(@I_dont_mind1)
12. Tigist Bersoma
13. ØÑ€ ĐAY
14. Rehima Ahmed
15. Sirag Ahmed
16. K.I King (@Kakuwak)
17. Wubalem Tagele
18. Kubra
19. Keron Abdulkadir
20. Yoseph Zewdu
21. Abel Misganaw
22. Samiha Shemsu
23. Asefa Negash
24. Awoke Melesse
25. G/mariam (@gebirr)
26. Teka geze
27. Husen Ahmed
28. Tigist Fiseha
29. Leul @Leulmak...

ስማችሁ ያልተጠቀሰ በጣም ብዙ ናችሁ! ሁላችሁም ጎበዞች በርቱ❤️ ከ1-5 የወጡት የሞባይል ካርድ ተሸላሚዎች ናቸው!

የፈተናው መልስ እንደሚከተለው ነው👇
#ANSWER

1. B
2. D
3. C
4. B
5. A
6. C
7. A
8. A
9. B
10. D
11. B
12. A
13. B
14. Accomodation
Motion parallax
Pictorial cue and so on.
15. Contour
Organization
SUMMARY OF DEDUCTIVE AND INDUCTIVE ARGUMENT.

👉 Deductive argument - The conclusion is claimed to follow necessarily from the premises. So, it impossible for the premises be true and the conclusion false.

👉 Inductive argument - The conclusion is claimed to follow probably from the premises. So, it is improbable for the premises be true and the conclusion false.

👉 Deductive argument - involves necessary reasoning.

👉 Inductive argument - involves probabilistic reasoning.

👉 Deductive argument - the conclusion is not supposed to contain more information than the premises.

👉 Inductive argument - the conclusion contains more information than the premises.

👉 Deductive argument - does not always proceed from General to Particular.

👉 Inductive argument - does not always proceed from Particular to General.

👉 Argument based on pure Mathematics is Deductive argument.

👉 Argument based on statistical mathematics(statistics) is Inductive argument.

🙌👆 እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ንፅፅሮች ያዟቸው። true/false ላይ ወይም ደግሞ ምርጫ ላይ ሊያወጡት ይችላሉ።

📍 The methods that used to determine whether an argument is Deductive or Inductive are:

👉 The actual strength of the inferential link between the premises and the conclusion.

👉 Special indicator words.

👉 Character or form of argument.

🥺 ሁሉም ግቢዎች ሊባል በሚቻል መልኩ ከዚህ part ላይ ፈተና እንዴት አድርገው ያወጣሉ መሰላችሁ፡ ፈተናው ላይ የሚያወጧቸው argument ቶች በ form of argument መልክ ነው። ለምሳሌ፡

🌀 Which one of the following is deductive argument?

A) The rainfall in Ethiopia has been more than 15 inches every year for the past thirty years. Therefore, the rainfall next year will be more than 15 inches.

B) Alemu is bachelor. Thus, Alemu doesn't get married.

C) Biology is a branch of natural since and has contributed a lot and studies about living things.
Physics is a branch of natural science and has contributed a lot. Therefore, Physics studies about living things.

D) More than seven hundred students scored 600 and above in last year Entrance Exam. It follows that, all students who took last year Entrance Exam are clever.

😊ተመልከቱ ይህን ጥያቄ ። መልሱ የቱ ይመስላችሗል? እስቲ እንየው።

Choice A - prediction ነው።
Choice B - argument from definition ነው።
Choice C - argument from analogy ነው።
Choice D - Inductive generalization ነው።

ስለዚህ መልሱ B ነው።

ስለ form of argument ካሁን በፊት ኖት ለቀናል ፡ተምረንዋል። ስለዚህ አሁን ማብራራት አያስፈልግም። ሌላ ጥያቄ፡

📍 Which of the following is Inductive argument?

A) Some animals are mammals. No mammals are Americans. Thus, some animals are not Americans.

B) Eyerus is 50 kg. It follows that Eyerus weighs 500N on earth.

C) If I study hard, I will join pass Entrance Exam. If I pass Entrance Exam, I will join a university. Hence, We may conclude that If I study hard, I will join a university.

D) Lester Brown, universally respected author of the yearly state of the world report has said that the destruction of tropical rainforests is one of the ten most serious worldwide problems. Thus, it must be the case that this is indeed a very serious problem.

🥺ተመልከቱ ይህን ጥያቄ። እስቲ እንስራው፡

Choice A- Categorical syllogism ነው።
Choice B- argument based on mathematics ነው።
Choice C- hypothetical syllogism ነው።
Choice D- argument from Authority ነው።

ስለዚህ መልሱ D ነው።

😎 ስለዚህ ሁሉንም form of argument ፅንሰ ሀሳቡን በአግባቡ ተረዱት። ከተረዳችሁት የፈለገው argument ቢሰጣችሁ አይከብዳችሁም።

🙌 ሌላ ደግሞ ፈተናውን በምን አይነት መልክ ትፈተኑታላችሁ መሰላችሁ።

Argument ቱ ይሰጣችሁና types of argument እና form of argument ፃፍ ትባባላላችሁ።
ምሳሌ፡

📌 write the types of argument and form of argument of the following arguments?

1) "Triangle A and Triangle B are congruent with each other and Triangle A is isosceles triangles. Therefore, Triangle B is isosceles triangle."

Types of argument________
Form of argument ____

2) " Although it is now sunshine, the road is too muddy and the flood impedes viechles. It follows that, heavy rain was rained a moment ago."

Types of argument________
Form of argument________

እስቲ መልሱን እናንተ ስሩት።

በቀጣይ Evaluating of Arguments አይተን chapter 2 እንጨርሳለን።

©A+ tutorial class.


Principles of Classical Conditioning

The basic Principles የሚባሉት👇👇

A. Stimulus generalization and stimulus discrimination

Stimulus generalization Is a process in which, after a stimulus has been conditioned to produce a particular response, stimuli that are similar to the original stimulus begin to produce the same response.
ይሄ ማለት ውሻው የእራት ደውል ሲደወል ሮጦ ከመጣ፣ የስልክ፣ የበር.. ደውል ሲሰማ ሮጦ የሚመጣበት ሂደት ነው

Stimulus discrimination is the process of distinguishing two similar stimuli; the ability to differentiate between stimuli.
ይሄ ማለት ውሻው ደዉሉን ለይቶ ካወቀና ለእራቱ ደውል ብቻ response ካረገ ነው

B. Extinction and spontaneous recovery

Extinction is when the US (food) does not follow the CS (the bell's tone🛎), and then when the CR (salivation) begins to decrease and eventually causes extiniction.
ሁሌ ምግብ ሳታመጡለት ደዉል እየደወላችሁ ብቻ ውሻውን ምታገረጡት ከሆነ😁 የውሻው response እየቀነሰ ይመጣል።

Spontaneous recovery is when after rest period, an extinguished CR (salivation) spontaneously recovers, but if the the bell (CS) persists alone, the CR becomes extnict again.
ይሄ ያው የExtniction ተቃራኒ ነው፣ ምግቡን ከደዉሉ ጋር ማምጣት ስትጀምሩ የውሻው የተለመደ ምላሽ እያገገመ ይመጣል።

Classical Conditioning theory ይህን ይመስላል፣ በቀጣይ Operant Conditioning እናያለን።

የዛሬው በዚህ አበቃ😊 ደከማቹ አ!
በደንብ ግልፅ እንዲሆንላችሁ ደጋግማችሁ አንብቡት😇

Good bye🙌

All Rights reserved!
©A+ tutorial Class
8. Massed and distributed learning👉 በአንድ ጊዜ ለብዙ ሰዓት ከምንማረው ነገር ይልቅ በመሃል ዕረፍት እየወሰድን የምንምረው ተመረጭ ነው፣ እናንተም ስታጠኑ እንደዚያ አድርጉ😊

3.3 Theories of Learning and their Applications

1⃣Behavioural Theory of Learning
🔖Classical Conditioning Theory
🔖Operant Conditioning Theory
2⃣Social Learning Theory
3⃣Cognitive Learning Theory

በዝርዝር እንያቸው እስኪ ጠንከር ስለሚሉ እራሳችሁን አበርቱ፣ ደጋግማችሁ አንብቡ!😊

1⃣Behavioral theory of learning
🌷Believes that learning occurs as a result of stimulus-response associations. ይህ Theory የሚያምነው Learning የሚፈጠረው ከተፈጠረው ክስተት እና እኛ ከምንሰጠው ምላሽ የተነሳ ነው ብሎ ነው።
There are two major behavioral theories of learning.

Classical Conditioning Theory

🌷Focuses on the learning of making involuntary emotional or physiological responses to stimuli that normally elicit no response.
ይህ Theory ትኩረት ያደረገው ያለውዴታህ ለአንድ Stimuli ስለምትሰጠው ምላሽ ላይ ነው።

ለምሳሌ ከጅብ ጋር ፊትለፊት ተገናኝተህ አስበው ምን እንደሚፈጠር ላብ በላብ ሆነ🥵፤ የልብ ምትህ ጨምሮ🩺 ምናምን፣ ይህ አሁን involuntary ነው።

🌷Classical conditioning involves what are known as conditioned reflexes.
An example of this is a "knee-jerk" reflexes.
ከጉልበት ሎሚ( ክቧ ነገር😃) በታች ሲመታ የሚሰማው ንዝረት ነው knee-jerk የሚባለው።
እና ይሄኛው አይነት Reflex በአይምሮ አይደለም Controlled የሆነው በSpinal Cord ነው።

🌷Another example of a reflex is the production of saliva in a response to food when you are hungry.
ለምሳሌ Pavlov የተባለው ሰውዬ ይሄንን Classical Conditioning theory discover ሲያረግ የወሰደውን ምሳሌ እንመልከት👇👇

ውሻ እንደምታቁት ለምግብ Respond የሚያደርገው በምራቅ (Salivation) ነው። ፈልጎዳቸው ሳይሆን በቃ ልማዱ ስለሆነ salivate ያረጋሉ። እናም ደግሞ ደውል ሲደወል Salivate እንዲያረጉ አስለመዳቸው...እና ከዛ Pavlov ምን አረገ ደጋግሞ ደውል እየደወለ, ምግብ🍲 ባቀረበላቸው ቁጥር ውሾቹ ምራቃቸውን እያዝረከረኩ ሮጠው ይመጣሉ😎..በቃ ምግብ ኖረም አልኖረም ደውሉ ሲደወል ምግብ ያለ መስሏቸው ሮጠው ይመጣሉ።

So, Pavlov ከዚህ Conclude ያደረገው Classical Conditioning is Learning to associate automatic behaviour (feeling) with a stimulus. ልክ ውሾቹ ደውሉን ከምግቡ ጋር associate እንዳረጉት🤷‍♂

Basics of Classical Condition

📍Neutral stimulus: This is the stimulus that does not naturally cause the subject to respond in a certain way. ከላይ በምሳሌ እንዳየነው ደውል🛎 በራሱ (Naturally) ውሻ ሮጦ እንዲመጣ አያረግም።

📍Unconditioned stimulus (UCS): This is a stimulus that naturally (no learning involved) causes a particular response. እንደምታውቁት ውሻ በተፈጥሮው ስጋ ሲያይ ሮጦ ይመጣል (response ይሰጣል)

📍Unconditioned response (UCR): is a response that is natural and needs no training. ውሻው አሁን ስጋ ሲያይ ሳይወድ በግዱ Salivate ያረጋል፣ ይሄ ተፈጥሮአዊ ነው። እኔ ምለው የስጋ emoji የለምንዴ🤔😁

📍Conditioned stimulus (CS): is a neutral stimulus that does not normally elicit an automatic response; only after pairing it repeatedly with the UCS, does the CS come to provide a conditioned response. ይሄ የሚወክለው ደውሉን ነው (The bell🛎)..ውሻው naturally ለደውሉ ምንም response አይሰጥም! ግን Pavlov እንዳደረገው ሁሌ ደውሉን ከምግቡ (UCS) ጋር እያቀረበ..ከዚያ ውሻው ልማድ ሆኖበት ደዉሉ ሲደወለ Salivate ማድረገ (response መስጠት) ጀመረ።

ግን እየገባቹ ነዋ🙌🙌 እንቀጥል!

📍Conditioned Response: is the learned response that occurs when the CS is presented alone, without the UCS. ያው ይሄ ከላይ ላየነው Conditioned Stimuli የሚሰጠው response ነው፣ ማለትም ውሻው🐕 ምግቡ ሳይኖር ደዉሉን ብቻ ሰምቶ ሮጦ ሲመጣ ማለት ነው🤷‍♂

እነዚህን👆 በአይምሮአችሁ ያዟቸው

Hence, the theory of classical conditioning represents a process in which a neutral stimulus, by pairing with a natural stimulus, acquires all the characteristics of natural stimulus.
ይሄ ማለት ገብቷቿላ ማለትም Unconditioned stimulusን (ስጋውን) ከConditioned stimulus (ደዉሉ) ጋር associate በማድረግ ውሻው ልክ ለስጋው response ይሰጥ እንደነበረው ለ ደዉሉም response እንዲሰጥ ማስቻል ማለት ነው።👍

It is also sometimes called substitution learning because it involves substituting a neutral stimulus(The bell) in place of natural stimulus (The food).

እስኪ አሁን የPavlovን Experiment በሶስት Step እንይ

📌Before Conditioning
[ማለትም ውሻው ሳይለማመድ]
Food [Unconditioned stimulus, US] Produces Salivation [Unconditioned Response, UR]
However, the bell [Neutral stimulus] does not.

📌During Conditioning
[ውሻው በልምምድ ላያ እያለ]
The neutral stimulus (The bell's tone🛎) and the US (food) are paired, resulting in salivation(UR).

📌After Conditioning
[ከልምምዱ በኃላ]
The neutral stimulus (now conditioned stimulus, CS) elicits(provides) Conditioned Response, CR)

ግራ ገባቹንዴ? በጣም ግልፅ እንዲሆንላችሁ እስኪ ከታች የላኩትን Photo እዩት😊 እና ደግሞ ደጋግማችሁ አንብቡ
📚CHAPTER 3

📖Learning And Theories of Learning

በዚህ ቻፕተር የምናያቸው👇👇
🔖Definition, Characteristics and Principles of Learning

🔖Factors Influencing Learning

🔖Theories of Learning and their Applications

እነዚህን ትማራላችሁ ይሄ Chapter ብዙም አይከብድም! ብዙም እራሳችሁን ሳታጨናንቁ አንብቡ🕺🕺💃😎

🌱There are many definitions of learning. But, Psychologists in general define Learning as relatively permanent behavioural modifications which take place as a result of experience.

ያው Learning ማለት መማር ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ!😊 ነገር ግን መማር ማለትስ ምን ማለት ነው! የተለያየ ትርጉም ሊኖረው ቢችልም ግን ብዙዎቹ እንዲህ ያብራሩታል👉 "ከልምድ ወይም ከልምምድ የሚመጣ ቋሚ የሆነ የባህሪ ለውጥ ማለት ነው።"

🌱ልብ በሉ👆 This definition of learning stresses on three important elements of learning:

📌Learning is a behavioural change. የባህሪ ለውጥ ነው (ጥሩም የሆነ መጥፎ ባህሪ ሊሆን ይችላል)

📌This behavioural change should take place as a result of practice and experience. ሰው በአካል ሲያድግ፣ ወይ ደግሞ ሲያመው Or ሲደክመው የባህሪ ለውጥ ሊታይበት ይችላል ነገር ግን Learning ከልምምድ የሚመጣ ነው።

📌This change in behavior is relatively permanent. የባህሪ ለውጡ ደግሞ በአንዴው ታይቶ የሚጠፋ ሳይሆን For a long time የሚቆይ ነው።

Characteristics of learning

ያው እነዚህ የLearning ባህሪያት ናቸው፣ Yoakman and Simpson የተባሉ ሰዎች ናችው 9ኙን የLearning Characteristics describe ያደረጉት👇👇 እና ፈተና ላይ ስለማይቀሩ ልትይዟቸው ይገባል😊

1. Learning is continuous modification of behavior throughout life.
📍ቀጣይነት ያለው በህይወት ውስጥ ያለ የባህሪ ለውጥ/መሻሻል ነው

2. Learning is pervasive, it reaches into all aspects of human life.
📍የህይወታችንን አካል የሆኑ ነገሮች ውስጥ ሁሉ ዘልቆ ይገባል ለዚህ ነው pervasive የተባለው

3. Learning involves the whole person, socially, emotionally & intellectually.
📍የሰውን ውስጣዊ፣ ስሜታዊ እንዲሁም ማህበራዊ ነገሮች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው

4. Learning is often a change in the organization of experiences.

5. Learning is responsive to incentives.
📍Learning ለሚያበረታታ ወይም ለሚገፋፋ ነገር መልስ የሚሰጥ ነው።

6. Learning is an active process.

7. Learning is purposeful

8. Learning depends on maturation, motivation and practice.

9. Learning is multifaceted
📍multifacated ማለት Having many different parts ማለት ነው።

Principles of learning

What does it take for learning to take place effectively? መማር ተፅእኖ እንዲፈጥር ማለትም ጠቃሚ እንዲሆን ምን ምን ያስፈልጋል?

📌 Individuals learn best when they are physically, mentally, and emotionally #ready to learn.

📌 Students learn best and retain information longer when they have #meaningful_practice and #exercise.

📌Learning is strengthened when accompanied by a #pleasant or #satisfying_feeling
Learningን በጥሩ ስሜት ካልያዝነው ጠንክሮ ሊቀጥል አይችልም።

📌 Things learned first create a strong impression in the mind that is difficult to erase. Things most recently learned are best remembered.
መጀመሪያ ላይ የተማርናቸውን እንዲሁም በቅርቡ የተማርናቸውን ነገሮች ለመርሳት ከባድ ነው

📌The principle of intensity implies that a student will learn more from the real thing than from a substitute.
ሰዎች ከተመሳሰለው ነገር በላይ ከእውነታ ብዙ ነገር ይረዳሉ።

📌Individuals must have some abilities and skills that may help them to learn.

📌Things freely learned are best learned - the greater the freedom enjoyed by individuals, the higher the intellectual and moral advancement.
በነፃነት የምንማራቸው ነገሮች በመጨናነቅ ከምንማረው በላይ አሪፍና የተሻለ ነው። ስለዚህ ስትማሩ ፈታ እያላችሁ💃 የምን መጨናነቅ ነው☺️

Factors Influencing Learning

1. Motivation👉በውስጣችን ያለው ተነሳሽነት ከፍተኛ ሲሆን, ተማሪው ለትምህርቱ በጣም የጓጓ ይሆናል።

2. Maturation👉The learner's motivation matters for the effective learning. ለምሳሌ ህፃን ልጅ እንዲማር መጀመርያ መብሰል/ማደግ አለበት።

3. Health condition of the learner👉 The learner should be in a good health status to learn. የተለያዩ ህመሞች ካሉብን የመማር ሁኔታችን ደካማ ሊሆን ይችላል።

4. Psychological wellbeing of the learner👉 ፍርሀት፣ ጭንቀት🤕፣ የብቸኝነት ስሜት🤦‍♀ ምናምን የሚሰማን ከሆነ Learning ላይ አሉታዊ ተፅኖ ይኖረዋል፤ ይልቁኑ Self respect, self confidence ምናምን ይኑራችሁ☺️

5. Good working conditions👉absence or presence of fresh air, light, comfortable surroundings...እና የመሳሰሉት ነገሮች Matter ያረጋሉ፣ እናንት ግን ዶርማችሁን ፅድት አርጋችሁ፣ ስታጠኑም ደግሞ አሪፍ አየር ያለበት ቦታ ምናምን ምረጡ።

6. Background experiences👉 ከዚህ በፊት ያላችሁ ልምምድ በLearning ላይ Matter ያረጋል

7. Length of the working period👉 Learning periods should neither be too short nor too long. እንደምታውቁት ለረጅም ጊዜ መማር ያደክማል ደግሞም ይሰለቻል፣ ለአጭር ጊዜም ከሆነ ደግሞ በበቂ መማር ያለብንን አንማርም
Philosophy ን እንደ መግቢያ ነው የማስተምራችሁ ፡ ደረቅ ንባብ ስለሆነ ግቢ ስትገቡ ለፈተና አንብቡት ። ምን አይነት የ concept ጥያቄ ስለማይወጣበት እንዲሁ ከሸመደዳችሁት ትሰሩታላችሁ። ስለዚህ የለቀቅንላችሁ pdf ላይ ኖቱን አንብቡት ፡ ሸምድዱት ፈተና ሲደርስ😊። እንደ መግቢያ ግን እንመልከተው በትንሹ።

📍Introduction

🌀 Chapter One

✏️Philosophy

📚 Philosophy ን እንዲሁ በቀላሉ define ማድረግ ወይም ብያኔ መስጠት ይከብዳል። እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ብያኔዎች አሉት። አንዱን formal የሚባለውን Definition እንመልከት።

🎈Philosophy is a process of reflecting and criticizing our most deeply held conceptions and beliefs.

ፍልስፍና ማለት ስለ አንድ ነገር ምሳሌ ስለ ተፈጥሮ፡ ስለ ማህበራዊ ትስስር ፡ ስለ ዩኒቨርስ ፡ ስለ ውበት ወዘተ ያለንን ጥልቅ የሆነ አመለካከት እና እምነት የምንገልፅበት ፡ የምናፀባርቅበት ፡ የምንገመግምበት ፡ የምንተችበት ሒደት ፍልስፍና ይባላል።

📍 Types of Philosophy

👩‍🏫 Epistemology
🌹 Aesthetics
🤔 Metaphysics
🤝 Ethics
🚸 Logic

እያንዳንዳቸውን እንደ መግቢያ ያክል እንመልከት። ዋናው ትምህርታችን ሎጂክ ነው።

👩‍🏫 Epistemology

is a branch of Philosophy that deals with the nature, scope, meaning and possibility of knowledge.

ዕውቀት ምንድን ነው? አንድ ሰው አወቀ የሚባለው ምን ሲሆን? የዕውቀት ምንጩ ምንድን? ዕውቀት ከሌሎች የሚለየው በምንድን ነው? እውነት ምንድን ነው? አንድ ነገር ዕውነት መሆኑን እንዴት ነው የምናውቀው? በ እምነት እና በምክንያታዊነት መካከል ያለው ዝምድ እና ልዩነት ምንድን ነው? እነዚህን እና የመሳሰሉትን የሚያጠና የፍልስፍና ክፍል Epistemology ተብሎ ይጠራል።

🌹 Aesthetics

is a branch of Philosophy that deals with beauty, art, enjoyment, perception, sense of taste and sentiment.

ጥበብ ምንድን ነው? የጥበብ ሀገሯ ወዴት ነው? ውበት ምንድን ነው? የውበት መለኪያ ምንድን ነው? የሚዳሰስ ነው? በ ውበት, በጥበብ እና በዕውነት መካከል ያለው ዝምድና ምንድን ነው? ውበት ምንጩ ምንድን ነው? በተፈጥሮ ወይስ በሰው ሰራሽ? እነዚህን ና የመሳሰሉትን የሚያጠና የፍልስፍና ክፍል Aesthetics ተብሎ ይጠራል።

🤔 Metaphysics

is a branch of Philosophy that deals with the ultimate nature of reality or existence.

የአንድ ነገር መገኘት ወይም መፈጠር ምን ማለት? የመጨረሻው ትልቁ ዕውነት ምንድን ነው? የሰው ልጆች ነገሮችን የሚያደርጉት በራሳቸው ነፃ ፍቃድ ነው ወይም በ supernatural power ቀድሞ ተወስኖላቸው ነው? ፈጣሪ አለ🤭? ካለ መኖሩንስ እንዴት ማረጋገጥ የምንችለው? የሰው ልጅ ምንድን ነው😬? የሚያስብ ጭንቅላት ያለው🤔? የሚንቀሳቀስ የተዋቀረ አካል ያለው🤥? ጊዜ ምንድን ነው😾? ህይወት ማለት ምን ማለት ነው? እነዚህን እና የመሳሰሉትን የሚጠና Metaphysics ይባላል። ወይ metaphysics🤭🤭

🤝 Ethics
Civics ላይ ተምራችሁታል።

🙌 Logic
ይህን የፍልስፍና ክፍል ነው ፍሬሽማን ላይ የምትማሩት።

ነገር ግን ስለ ሎጂክ ከ ማየታችን በፊት statement እና proposition ምን እንደሆነ እንመልከት።

🌀 Statement - is a declarative sentence that has truth value.

🌀 Statement - is a sentence that is either true or false.

Statement ማለት እውነት ወይም ሀሰት የሆነ ዐነገር ነው። ወይም

እውነት ነው ወይም ሀሰት ነው ብለን የምንፈርጀው ዐነገር statement ይባላል።

ምሳሌ ፡

👉 Mekelle is the capital city of Oromia Region.

👉 2+2 = 5.

👉 Barack Obama is the first black American president.

👉 All planets revolve around the sun.

የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ ዐ.ነገሮች ውሸት(false)

የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ዐነገሮች እውነት(true) ናቸው።

ስለዚህ በአጠቃላይ አራቱም ዐ.ነገሮች statement ናቸው ማለት ነው።

🌀 Proposition - is an information content of statements.

Proposition ማለት ደግሞ statement ቱን ይዘት የሚገልፅን መረጃ ወይም የ statement ቱ ትርጓሜ ማለት ነው።

Logic የተገነባው ከ statement or proposition ነው።

ብዙውን ጊዜ ሎጂሽያኖች statement እና proposition በአንድ አይነት መንገድ(interchangeably) ይጠቀሙበታል። ነገር ግን statement እና proposition አንድ አይነት ናቸው ማለት አይደለም።

ብዙውን ጊዜ true/false ላይ ፈተና ስለሚወጣ ይቺን ሀሳብ ያዟት👇👇👇👇

"in the strict sense of the terms , statement and proposition do not have exactly the same meaning."

Now let us proceed to the further study of Logic.( አሁን ሎጂክን እንመልከት)


📕 CHAPTER TWO`

📑 Basic Concepts of Logic

Definition of Logic🤔

ሰዎች ብዙውን ጊዜ ይህ ነገር logical ነው ፡ ይህ ነገር logical አይደለም እያሉ በተለምዶ ይናገራሉ። ግን ሰዎች በተለምዶ logical ነው ወይም logical አይደለም የሚሉት ነገር በትክክል ሎጂክ ን ይገልፀው ይሆን🤔?

🤔 What is Logic

🎯 Logic(ስነ-አመክንዮ) - is the science or philosophy that deals with and evaluates Argument.

🎤 Logic(ስነ-አመክንዮ) ማለት ስለ Argument የሚያጠና እና Argument ን የሚገመግም የ ሳይንስ ወይም የፍልስፍና አይነት ነው። ታዲያ Argument ምንድን ነው🤔?

Dictionary ላይ ብታዩት Argument ማለት ክርክር ማለት ነው። እናንተም Argumentative passage እያላችሁ ተምራችሗል። logic የሚያጠናው argument ግን ይለያል። እስኪ እንየው!

👉 Argument (አመክንዮ)

👨‍💼 Argument - is a group of statements, some of which are intended to provide support or evidence to conclude about something.

👌 Argument (አመክንዮ) - ማለት የሆነ ማስረጃን መሰረት በማድረግ ወይም የሆነ ማስረጃን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት Argument ይባላል። ስለዚህ ሁለት ነገሮች አሉን ማለት ነው።

👉 1ኛ) ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የተጠቀምነው ማስረጃ(evidence)::

👉 2ኛ) ማስረጃውን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው ድምዳሜ( conclusion)::

👐 ታዲያ ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የምንጠቀመው ወይም የተጠቀምነው ማስረጃ premises ተብሎ ይጠራል።

👐 ማስረጃውን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው ድምዳሜ Conclusion ተብሎ ይጠራል። so,

🎈 Premises - is a group of statements that set forth the reason(evidence). Or

🎈 Premises - is a group of statements that are claimed to provide logical support or evidence to the conclusion.

🎈 Conclusion - is a statement which is claimed to follow the alleged evidence.

👆 ፈተና ላይ ስለሚወጡ ያዟቸው።

😻 ስለዚህ

😎 Argument = Premises + Conclusion.

እስቲ ምሳሌዎችን እንመልከት፡

🔷 Example 1

➡️All Ethiopians are Africans.
➡️ Solomon is an Ethiopian
➡️ Thus, Solomon is an African.

👆 ሁሉም ኢትዮጵያውያን አፍሪካዊ ናቸው። ሰለሞን ኢትዮጵያዊ ነው። ስለዚህ ሰለሞን አፍሪካዊ ነው።

🥺 አያችሁ አይደል!!

ሰለሞን አፍሪካዊ ነው ብለን ድምዳሜ(conclusion) ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን አፍሪካዊ ናቸው እና ሰለሞን ኢትዮጵያዊ ነው የሚሉት ናቸው።

🙌 ስለዚህ ከላይ ያየነው ምሳሌ argument ነው። ምክንያቱም ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት ማለትም ሰለሞን አፍሪካዊ ነው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት ማስረጃዎችን ተጠቅመናል።

ስለዚህ ከላይ ያየነው ምሳሌ argument ከሆነ የግድ premises እና conclusion አለው ማለት ነው ምክንያቱም argument የሁለቱ ድምር ውጤት ስለሆነ። ስለዚህ የትኛው ነው premises? የትኛው ነው conclusion?

👉 Premises ማለት ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የምንጠቀመው ማስረጃ ነው ።

ስለዚህ ሰለሞን አፍሪካዊ ነው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት የተጠቀምነው ማስረጃ ፡

👉 All Ethiopians are Africans.
👉 Solomon is an Ethiopian.

ስለዚህ ሁለቱ👆 premises ናቸው።

Conclusion ማለት ደግሞ ማስረጃዎችን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ መስጠት ነው። ስለዚህ

👉 Solomon is an African የሚለው conclusion ነው።

🔷 Example 2

➡️ Three is prime number.
➡️ Five is prime number.
➡️ Seven is prime number.
➡️ Therefore, all odd numbers between two and eight are prime numbers.

በ 2 እና 8 መካከል ያሉ ሁሉም odd ቁጥሮች prime number ናቸው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው 3 , 5 እና 7 prime number ናቸው የሚለው ነው። ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት ማስረጃ ስለተጠቀምን argument ነው ማለት ነው። argument ከሆነ ደግሞ የግድ premises እና conclusion አለው ማለት ነው። የትኛው ነው premises? የትኛው ነው conclusion ?

🔶 Premises ማለት ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት የምንጠቀመው ማስረጃ ነው። ስለዚህ በ 2 እና በ 8 መካከል የሚገኙ ሁሉም odd ቁጥሮች prime number ናቸው ብለን ድምዳሜ ለመስጠት የተጠቀምነው ማስረጃ፡

👉 3 is prime number.
👉 5 is prime number.
👉 7 is prime number.

እነዚህ👆 premises ናቸው።

👐 Conclusion ማለት ደግሞ ማስረጃዎችን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር የምንሰጠው ድምዳሜ ነው። ስለዚህ

👉 All odd numbers between 2 and 8 are Prime numbers. የሚለው conclusion ነው።

🔷 Example 3

➡️ It has rained for the past 5 consecutive days.
➡️ As a result, It will rain today.

ዛሬ ዝናብ ይዘንባል ብለን ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ባለፋት ተከታታይ 5 ቀናት ዝናብ መዝነቡ ነው። ስለዚህ argument ነው ማለት ነው። ታዲያ የትኛው ነው premises? የትኛው ነው conclusion?

Premises ማለት ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ነው። ስለዚህ ዛሬ ዝናብ ይዘንባል ብለን ድምዳሜ ለመስጠት እንደ ማስረጃ የተጠቀምነው ላለፋት ተከታታይ 5 ቀናት መዝነቡ ነው። ስለዚህ

👉 It has rained for the past 5 days.(Premises)

👉 It will rain today. (conclusion)

🔶 ስለዚህ logic ማለት ስለ argument የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ማለት ነው። በሌላ አባባል በ premises እና conclusion መካከል ያለውን ዝምድና ወይም ግንኙነት የሚያጠና እና የሚገመግም የፍልስፍና ዘርፍ ነው። ስለዚህ ከዚህ ምን እንረዳለን??

Logic ማለት ነባራው ዕውነታ(General truth) ማለት አይደለም። ለምሳሌ ፡

ፕላኔቶች በፀሀይ ዙሪያ ይዞራሉ።ይኸ ነባራዊ ዕውነታ ግን logic አይደለም።

አስተውሉ logic ማለት ነባራዊ ዕውነታ ወይም General truth አይደለም።

Logic ማለት ስለ argument የሚያጠና ነው ።
ማለትም ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ ለመስጠት በምንጠቀመው ማስረጃ እና ማስረጃውን ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር በምንሰጠው ድምዳሜ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠና እና የሚገመግም የ ፍልስፍና ዘርፍ ነው።

ተጠቅመን ስለ አንድ ነገር በምንሰጠው ድምዳሜ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠና እና የሚገመግም የፍልስፍና ዘርፍ ነው።

👉 እስቲ እንመልከት logic ነባራዊ ዕውነታ አለመሆኑን።

🔷Example

➡️ All human beings are immortal.
➡️ Samuel is a human being.
➡️ Therefore, Samuel is immortal.

የሰው ልጅ ሟች አይደለም። ሳሙኤል የሰው ልጅ ነው። ስለዚህ ሳሙኤል ሟች አይደለም።

😜 አያችሁ አይደል ሳሙኤል ሟች አይደለም ብለን ድምዳሜ ለመስጠት ማስረጃ አቅርበናል። ስለዚህ logic ነው።

🤷‍♂ ግን ነባራዊ ዕውነታው የሰው ልጅ ሟች ነው። የ ሰው ልጅ ሟች አይደለም ብለን ያቀረነብነው ማስረጃ ከ ነባራዊ ዕውነታው ጋር ቢጣረስም logic ከመሆን አላገደውም ምክንያቱም logic ነባራዊ ዕውነት ሳይሆን ስለ አንድ ነገር ድምዳሜ እና ድምዳሜውን ለመስጠት ስለተጠቀምንበት ማስረጃ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠና ነው። ስለዚህ

🎈 Argument - is the inferential claim between premises and conclusion.

🎈 Argument - is not the factual claim between premises and conclusion.

አደራችሁን እነዚህን👆 ሁለት ሀሳቦች ያዟቸው። ፈተና ላይ ይወጣሉ።

Argument ወይም logic ማለት በ ድምዳሜው(conclusion) እና በ ማስረጃዎቹ(premises) መካከል ያለው ግንኙነት የምክንያታዊነት(inferential claim) ግንኙነት ነው እንጂ የ ነባራዊ ዕውነታ(factual claim) ግንኙነት አይደለም። ለዛ ነው

➡️ Human being is immortal.
➡️ Samuel is human being.
➡️ Therefore, Samuel is immortal.

👆👆 ይህ ሀሳብ logic ነው ያልነው።

ሌላው የምነግራችሁ መሰረታዊ ሀሳብ፡

Argument= premises + conclusion.

Argument የ premises እና conclusion ድምር ነው።

Premises አንድ እና ከ አንድ በላይ ዐ.ነገር(statement) ሊኖረው ይችላል። ነገር ግን conclusion ሁልጊዜ አንድ ዐ.ነገር(statement) ብቻ ነው::

🎈 Premises can have one or more than one statements.

But

🎈 Conclusion always have only one statement.

👆👆ፈተና ላይ ስለሚወጣ ያዙት


Argument ማለት የ premises እና የ conclusion ድምር ውጤት ነው ብለናል። ታዲያ በ argument ውስጥ የሚገኙትን premises እና conclusion እንዴት ነው ማወቅ የምንችለው? የትኛው ነው premise? የትኛው ነው conclusion? እነዚህን እና ሌሎችን በቀጣይ እናያለን።

©A+ Tutorial Class.