G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
⚙️ ልብህን የሚሰብረው ከሰዎች ብዙ መጠበቅ ነው፤ ስለዚህ ከሰዎች ብዙ አጠብቅ። እህቴ የሚከፋሽ ሌሎች የሚያደርጉልሽን ጠብቀሽ ስላላገኘሽ ነው።

🤔 ከሰው መጠበቁን አቁመን ደስታችንን ከፈጣሪና ከራሳችን ልብ ውስጥ ማግኘት ነው ያለብን፤ ያኔ አንዱን ቀን ደስ ብሎን ሌላኛውን ቀን አይከፋንም ምክንያቱም ደስታችን ሌሎች ላይ ጥገኛ አይደለም።

@🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
2
🔥Addictive students

የግቢ ተማሪዎችና የሱሳምነት ፈተና

ማንኛውም ተማሪ ቢሆን ግቢ ወይም ዩንቨርሲቲ ሲገባ የመጀመሪያ   ትኩረቱ ትምህርትና ትምህርት ብቻ በመሆኑ ምንም አይነት እንቅፋት ቢያጋጥመው ከአላማው እንደማያሰናክለው እርግጠኛ በመሆን ወደ ዩንቨርሲቲ ይቀላቀላል ።  ይህን እንጂ ብዙውን ተጨባጭ በምናይበት ጊዜ ነገሩ እንዲህ ቀለል የሚል አይመስልም ፥ ምክንያቱ ደግሞ ባላሰብነው መንገድ እንቅፋቶች ስለሚያሰናክሉን ነው።
ከትምህርት ገበታችን የሚያሰናክሉን ብዙ ነገሮች ቢኖሩም እኔ ግን ለዛሬ ስለ ሱስ ለመፃፍ ከጀልኩ ።
ካልተሳሳትኩ 99%u ተማሪ ወንድም ይሁን ሴት ከቤተሰቡ አደራ ተቀብሎ ብሎም ተመርቆ ወደ ዩንቨርሲቲ ሲላክ ከማንኛውም ዓይነት ሱስ ነፃ እንደሆነ አስባለሁ፤ ስለ ቀሪዋ1%ት  ምንም ማለት አልፈልግም ምክንያቴ ደግሞ ከቤተሰባቸው በላይ ልመክራቸው ስለማልችል ነው


እናም እነዚህ ብዙሃኑ ተማሪዎች ግቢ ሲገቡ ከሚሸነፉባቸው ነገሮች ውስጥ በሱስ መጠመድ ግንባር ቀደሙ ነው ማለት እችላለሁ።
ስለ ሱሱ ሳይሆን ማውራት የምፈልገው ስለ መንስኤው ነው
ለሱሳምነት አሳልፈው ከሚሰጡን ምክንያቶች መካከል ትልቁና ዋናው እኔም ሁሌ የምላቹህ አስተሳሰባችን ነው ፤ የእውነት ዩንቨርሲቲ  መግባት ማንነታችንን ሊገዛን አይገባም
የብዙ ፍሬሾች ችግር ግቢ ሲገቡ የዘመኑን እርድና መምረጣቸው ነው ፤ ስለ ዘመኑ አራዳነት ባለፈው ጽሁፌ ነግሬያቹህ ነበር ካልረሳችሁት
አራዳ ነኝ ብለህ ወይም ብለሽ ባላሰብከው መንገድ እንዳትሰናከል ፡ እንዳትሰናከዪ..

እናም እስከቻላችሁት ድረስ የዘንድሮ አዲስ ገቢ ተማሪዎች (ፍሬሾች) ክፉ ደጉን እስከምትለዩ ድረስ ብትረጋጉና ሙሉ ለሙሉ ትምህርታቹህ ላይ ብቻ ብታተኩሩ ከሱስ አደጋ ለመዳን ሰበብ ሊሆናቹህ ይችላል ባይ ነኝ።

ሌላው መንስኤ ደግሞ 👇👇
ጓደኛ ነው
ለግቢ ቆይታችን እጅግ በጣም ወሳኙ ነገር ጓደኛ ነው
የሀገሬ ሰው እንዲህ ይላል " ጓደኛህን ንገረኝና ማንነትህን እነግርሃለሁ " (አቦ ምን አይነት ድንቅ ንግግር ነው )

ማንኛውም ሰው ወደደም ጠላ በጓደኛው ተፅእኖ ስር ይወድቃል እናም ግቢ ስትገቡ አደራችሁን ከኢቦላ በላይ የምትቀርቡት ጓደኛ ያስፈራቹህ
ሰዎች ስንባል social animaሎች በመሆናችን በየትኛውም የህይወታችን ክፍል ውስጥ ተገንጥለን መኖር አንችልም ፤  ግቢ ደግሞ ካለ ጓደኛ በጣም ከባድ ነው ፡ ለምን መሰላቹልህ ከቤተሰብ በመራቃቹህ ብዙ ክፍተት ሊፈጠርባቹህ ይችላል በተለይ ሴቶች  ስለዚህ ስለ ምትጎዳኙት ተማሪ ጠንቅቃቹህ ማወቅ አለባቹህ ።

ሌላው ደግሞ ከግቢ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን  ከመጎብኘት መጠንቀቅ ያስፈልጋል

በተለይ አንዳንድ ግቢዎች አከባቢ ያሉ መጠጥ ቤቶችና ጫት ማላመጫዎች ብሎም ምናምን ማጨሻ ቤቶች ሆን ተብለው ተማሪውን ከትምህርት ገበታው ለማሰናከል የተዘጋጁ ይመስላሉ ።

እንደው አደራ ብዬ የምላቹህ እንደዚህ አይነት ቦታዎች ላይ ድርሽ እንዳትል ፥ ብዙ ወንድም እህቶች የሚሸወዱት እንደቀልድ በመልከስከስ ነው።
በቃ የጓደኛዬን ሙድ አላበላሽም ምናምን ብለው በርጫ ቤት ይከሰታሉ ፡ ለተወሰኑ ቀናት አይቅሙም ፣ አያጨሱም ምናምን ፤ ከሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ግን ከነባሮቹ በርጮሎጂስቶች ብሰው ቁጭ ይላሉ። ( በማይቀለድ ነገር አትቀልዱ)

ሌላ ሳልነግራቹህ የማላልፈው ኦቨር የሚሏትን ጨብሲ ነው

ብዙ ሳላወራ በጥቂቱ ኦቨር ማለት ወደ ከተማ ወጣ ብሎ መጠጥ ቤት ሂዶ  መስከር ማለት ፤ ጣጣው በስካር ብቻ ቢያቆም ትንሽ ይሻል ነበር ችግሩ ግን ብዙ ነው
በትንሹ እንኳ የlocal( የከተማው ጎረምሶች) ጡንቻ መመዘኛ ይሆናሉ፣ ስልክ ይነጠቃሉ ፣ ግቢ ይበጠብጣሉ ፣ ዶርም ይበጠብጣሉ ( ሻታ ይበረግዳሉ)...... አያልቅም

እባካቹህ የቤተሰቦቻችሁን አደራ አትብሉ ፥ እድሜያችሁንም በከንቱ ሱስ አትግደሉ

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🔥2
#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ትምህርት ዘመን አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 24 እና 25/2016 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2015 ዓ.ም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ በተመሳሳይ ህዳር 24 እና 25/ 2016 ዓ.ም መሆኑም ተገልጿል።

የአንደኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር መማር ማስተማር ሒደት ህዳር 26/2016 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል፡፡

በተለየያ ምክንያት የአንደኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ሳትጨርሱ ዊዝድሮ ያደረጋችሁ እንዲሁም በውጤት ምክንያት የመልሶ ቅበላ ሞልታቹ ትምህርት ያቋረጣቹ ተማሪዎች ህዳር 27/2016 ዓ.ም ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ እንዲሁም የለሊት አልባሳት (አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ) እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች የ2016 ዓ.ም ምዝገባ ታህሳስ 04 እና 05/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➢ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➢ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➢ ስድስት 3×4 ፎቶግራፍ፣
➢ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ፣
➢ የስፖርት ትጥቅ።

የሶሻል ሳይንስ ተማሪዎች በቦቆጂ ካምፓስ ፤ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በአሰላ ከተማ ዋናው ግቢ ሪፖርት እንድታደርጉ ተብላል፡፡

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
🎯 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን።

         ❇️Worksheet

🔰Worsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡  ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ።

    ❇️የአጠናን መንገድ(ስልት)

🔰እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?

🎯 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።

🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።

ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔

🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷‍♀️

ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ

🎯 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።

🎯  መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።

🎯 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።

🗣 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።

     ❇️የጊዜ አጠቃቀም

🔰ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።

      ❇️ አለመሰልቸት

🔰ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።

   ❇️ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።

🔰ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።

    ❇️Google

🔰ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video  ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘

          😊 The End

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
👨‍🎓🧑‍🎓የተማሪዎች አይነት (types of learners)

📮ይህ ፅሁፍ ሁሉም የትምህርት ብቃት እንዳለው ነገር ግን የትምህርቱ ዘዴ እና አቀባበላችን እንደሚለያይ
ያሳያል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ አይነት ተማሪዎችን እና የሚቀላቸውን የመማር ዘዴ ማጣጣም ያስፈልጋል።
የራሳችሁ የመማር ምርጫ ከየት እንደሆነ መመርመርም አትርሱ።

🧑‍🎓1— የእይታ ተማሪዎች (Visual learners)

እነዚህ የተማሪ አይነቶች የሚገባቸው መማር በእይታ ሲሆን ነው። ያዩት ነገር እንዲሁ በቃል ከሚነገራቸው
ይልቅ አይረሳቸውም። እነዚህ ተማሪዎች በተግባር ማየት ካልቻሉ በሃሳባቸው እየሳሉ ቢያነቡ በቀላሉ ማስታወስ ይችላሉ።

🧑‍🎓2— የተግባር ተማሪዎች (Kineshetic learners)

እነዚህ በበኩላቸው ራሳቸው በተግባር የሞከሩት ነገር ቶሎ ይገባቸዋል፣ አይረሱትም። ሰው ሲያደርግ ከማየት
በላይ ራሳቸው በማድረግ ይማራሉ። ለነዚህ ወደ ተግባር እየቀየሩ መሞከር ይመከራል።

🧑‍🎓3– የመስማት ተማሪዎች (auditory learners)

እነዚህ አንድን ነገር ከሰሙት በቂያቸው ነው። ብዙ ከማጥናት በላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲያዳምጡ ይመከራሉ። የሰሙትን ነገር ይረዳሉ።

🧑‍🎓4– የጭንቀት ተማሪዎች (Stress learners)

ያስጨነቃቸው ነገር አይረሳቸውም። ተጨናንቀው ግዴታ አውቄ መግባት አለብኝ ካሉ ማን እንደነሱ። ትኩረት
መስጠት እና መጣር ይመከራሉ።

🧑‍🎓5— የመዝናናት ተማሪዎች (Ease learners)

ዘና ፈታ ብለው ያነበቡት እና የተማሩት አይረሳቸውም። እነዚህ ሳይጨናነቁ፣ አእምሯቸውን ዘና አድርገው እና ጥሩ ስሜት ውስጥ ሆነው ቢያነቡ በጣም ውጤታማ ይሆናሉ።

🧑‍🎓6– የፅሁፍ ተማሪዎች (Scrubble learners)

ለየት ባለ መልኩ ትምህርት ወደ አእምሯቸው የሚገባው ሲፅፉት ነው። እንዳልረሳው ብለው ቢፅፋም
ስለማይረሱት ደግመው ላያዩት ይችላሉ። እነዚህ ሲያጠኑ ደጋግመው እንዲፅፉ እና ከጥናት በሗላም ራሳቸውን የሚፈትኑት ያጠኑትን በወረቀት ላይ ደግመው
ለመፃፍ በመሞከር እንዲሆን ይመከራል።

🧑‍🎓7— የእምነት ተማሪዎች (trust learners)

አነዚህ ከሚያምኑት ወይም ከሚያከብሩት አለያም ከባለስልጣን የተሰጠን ትምህርት በጭራሽ አይረሱም። ትምህርቱ ሳይሆን መምህሩ ነው ለነሱ ወሳኙ። ይሄን
ከሆን የተማርነውን ከምናምነው ሰው እንደተነገረ አድርገን እያሰብን ድጋግሞ ከማጥናት የተሻለ ምክር አይኖርም።

🧑‍🎓8— በማስተማር የሚማሩ (teach learners)

እነዚህ አንድን ነገር ካስተማሩት አለቀ—ተመጠጠ ማለት ይቀላል። እና ሁሌም ተማሪ ስለማይገኝ የተወሰነ አንብበው ቀሪውን– ቆም ብሎ፣ ተማሪዎች
እንዳሉ ራስን አሳምኖ፣ ጮክ ብሎ በማስተማር ማጥናት ይመከራል።

🧑‍🎓9— ተመሳሳዩን በመስራት የሚማሩ (copy learners)

ለየት ባለ ሁኔታ ያዩትን ወይንም የተማሩትን ነገር አስመስለው ሲሰሩት አይረሱትም። ያየነውን ነገር ደግመን ሁሉንም ቅደም ተከተል ሳንረሳ አስመስሎ
ለመስራት በመሞከር እንዲያጠኑ ይመከራል።

⭐️#ማጠቃለያ፦ አንድ አይነት ዘዴ በመጠቀም የሁሉንም ተማሪዎች የመማር ምርጫ እና ብቃት ማሟላት አይቻልም።
ከኢትዮጵያ መምህራን መድረክ - partially edited

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
Logic chapter 1.pdf
249.3 KB
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
💊 Pharmacy | ፋርማሲ

🦠ፋርማሲ ከ other health ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአድሱ የትምህርት ስርአት freshman course ጨምሮ የ5 አመት ትምህርት ነው ።
ፋርማሲ ስትገቡ የምትማሯቸው ኮርሶች mostly chemistry ነክ around [ 60%] ,biological around [25%] እና ሌሎችም አሉ ።ስለዚህ chemistry የሚወድና አንባቢ ተማሪ በብቃት ይወጣዋል።

🔬ፋርማሲ ስትማሩ የሚያስደስቱ ነገሮች ፦

🔺የመድሃኒት ቅመማ በላብላቶሪ ትሰራላችሁ ፤ ከባህላዊ ህክምናና ከእፅዋት እንዴት መድሃኒት ማግኘት እንደምትችሉ  ታውቃላችሁ  ፤ በላብላቶሪ ውስጥ lotion, cream, gel, shampoo, sanitaizer....የመሳሰሉትን ኮስሞቲክስ ታመርታላችሁ ፤መድሃኒትን አይጥ ላይ በመውጋት ትመራመራላችሁ ወዘተ....

💊በፋርማሲ ስትመረቁ ምን ትሰራላችሁ? ገቢውስ እንዴት ነው ? 🤔

1️⃣, clinical pharmacy የሚባለው hospital ውስጥ ተቀጥራችሁ

2️⃣, 🧪pharmaceutical company የመድሃኒት ፋብሪካና በተወሰነ መልኩ የኮስሞቲክስ ፋብሪካ ጋር

3️⃣, የመድሃኒትና የምግብ ቁጥጥር ማለትም ወደ ሀገር የሚገቡና የሚወጡትን መፈተሽ

4️⃣, በግላችሁ community pharmacy በመክፈት በተለይ ቤተሰቦቻችሁ በገንዘብ የሚያግዟችሁ ከሆነ በጣም አዋጭ ነው።

5️⃣, 💉የማንኛውንም የህክምና መድሃኒትና ቁሳቁስ በ pharmacist ቁጥጥር ስር ነው የሚገዛው (የሚቀርበው) ስለዚህ እዛ ላይም የናንተ ሙያ አለ።

6️⃣, የ fingerprint,forensics, food toxicity,drug toxicity,.....የመሳሰሉትን የወንጀል ምርመራ ላይ መስራት ይቻላል ።

7️⃣, እኛ ሀገር ብዙም ባይኖር የመድሃኒት ጥናትና ምርምር ላይም ትሰራላች

⭕️ስለ ገቢው፦ እውነቱን ለመናገር በፋርማሲ ትምህርት  ከተመረቃችሁ በኋላ ስለ ገንዘብ አያሳስባችሁም ። እያጋነንኩ አይደለም ከቻላችሁበት በጣም ባለሀብ ትሆናላችሁ ። ስለ ፋርማሲ ብትጠይቁ ቀድመው የሚነግሯችሁ businesses ነውና እሱ አያሳስባችሁ ።

📌ስራ ላላገኝ እችላለሁ? እንደማንኛውም የጤና ተማሪ ከhospital,ጤና ጣቢያ ትሰራላችሁ plus ሌላ አማራጭ በግል ትሰራላችሁ ወይም ከላይ ከ ተራ  ቁጥር 2-7 ያሉት አማራጮች አሉላችሁ ።

📺ትምህርቱ ከባድ ወይስ ቀላል? pharmacy ከ medicine በመቀጠል የሚመደብ ስለሆነ ከበድ ይላል ነገር ግን chemistry,biology and labolatory ነክ ትምህርቶ ለሚሰራና ለሚያነብ ተማሪ በቀላሉ ማለፍ ይችላል ። እንደዬ ዩንቨርስቲው ቀለል ባለ መልኩ የሚያስተምሩም አሉ ። ስለዚህ ጠንከር ያለ ተማሪ ቢሆን የተሻለ ውጤት ያመጣል።

🔘በአጠቃላይ ፋርማሲ ከሌሎች የጤና ዘርፎች ለየት የሚያደርገው ብዙ የስራ መስኮች ያሉትና ጥሩ የሚባል ክፍያ የሚገኝበት መሆኑ ነው።

🚖ስለ ፊልድ መረጣ በተመለከተ እንደ medicine ገና የመጀመሪያ ሴሜስተር ኮርስ እንደጨረሳችሁ ነው ። ሌሎች other health ግን 1ኛ አመት ከጨረሳችሁ በኋላ ነው።

⭐️ለRemedial እና ለ12 ተማሪዎች   ቻናል👇
@GTUTORIALCLASS
🙌ይቀላቀሉ

📌 Join and share 👇👇👇

           📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1