G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
#ሰበር_ዜና‼️

ኢትዮ-ኤርትራ፡

ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ግዛት ለማስወጣት ተስማማች!

ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ያስገባቻቸውን ወታደሮቿን ለማስወጣት ከስምምነት መደረሱን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ፣ አርብ ጠዋት ባወጣው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሐሙስ ዕለት አሥመራ የገቡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ባደረጉት ውይይት ኤርትራ ሠራዊቷን ከኢትዮጵያ ድንበር ለማስወጣት ተስማማታለች።

ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የድንበር አካባቢዎቹን ተረክቦ ጥበቃውን ወዲያውኑ እንደሚጀምር ሁለቱ መሪዎች ከስምምነት ደርሰዋል።

ዝርዝር መረጃውን እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት በተመለከተ በዩትዩብ ገፃችን ይዘን እንመለሳለን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
#ትኩረት!!

የጭላሎ ጋለማ ደን እሳት እየነደደ ነው።

በአርሲ ብሔራዊ ተራሮች ፓርክ በጭላሎ ጋለማ ደን ላይ የእሳት አደጋ በድጋሜ ተከስቷል።

በጭላሎ ተራራ ላይ የተከሰተዉን እሳት ለመቆጣጥር ከፍተኛ ጥረት ቢደረግም እሳቱ ከአቅም በላይ መሆኑን የአረሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓረክ አስታውቋል፡፡

ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ በአካባቢዉ የተገኙት የህብረተሰብ ክፍሎች የተከሰተዉን እሳት ለማጥፋት ያደረጉት ጥረት ከአቅማችዉ በላይ በመሆኑን ተናረዋል፡፡

ፓርኩ ከሚያካልላቸው ዘጠን ወረዳዎች ውስጥ በዘጠኙ (9) ወረዳዎች ዉስጥ የእሳት አደጋዉ የተከሰተ መሆኑን የአርሲ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አሳውቋል።

እሳቱ በፍጥነት እየተጓዘ እና አብዛኛዎቹን የተራራዉን ክፍል እያካለለ እንደሚገኝ ተገልጿል።

ፓርኩ እሳቱ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ በመሆኑ ለክልሉ አሳውቋል ፤ አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚፈልግ ጥሪ ማቅረቡን ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ምዝገባ በቀጣይ ሳምንት እንደሚጀመር የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች የኦንላይ ምዝገባ ከመጋቢት 20 እስከ ሚያዝያ 15/2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

ምዝገባው የዞንና ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያዎች በሚያወጡት ፕሮግራም መሰረት እንደሚፈፀም ከቢሮው የፈተና ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በአማራ ክልል በ2013 የትምህርት ዘመን በመደበኛ እና በግል ከ165 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና ይቀመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አስፈታኝ ትምህርት ቤቶችም 370 ሲሆኑ የፈተና ጣቢያዎች ደግሞ 357 ናቸው፡፡

የ2013 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦንላይን እንደሚሰጥ ከዚህ ቀደም ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
የአክሱም ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ከጥቃት ተረፉ!

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት አካባቢ የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ፡፡ ድንገቴ ጥቃቱ በተደረገበት በቅርብ ርቀት ላይ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ውስጥ የነበሩት ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ የሚጓዙ ተማሪዎች ከጥቃቱ ተርፈዋል፡፡

የአዲስ ዘይቤ ሪፖርተር በአካባቢው ከነበሩ የዓይን እማኞች እንደተረዳው፡- ከአዲግራት አቅጣጫ በመምጣት ላይ በነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ላይ የሕወሓት ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተዋል፡፡ በታጣቂዎቹ ጥቃት ወታደሮቹን ጨምሮ በአካባቢው በነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካከል በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ዓድዋ በማምራት ላይ የነበሩ ሲቪል ተጓዦችም ይገኙበታል፡፡ 8 የአካባቢው ገበሬዎችን ጨምሮ የ17 ሰዎች ህይወትም አልፏል፡፡ እንደ ዓይን እማኞች ምስክርነት በጥቃቱ 25 የሚጠጉ ወታደሮች፣ ገበሬዎችና ሲቪሎች ሞተዋል፡፡

ቤቶችም ተቃጥለዋል፡፡ በተሽከርካሪዎቹ ውስጥ የነበሩ ሴቶችም ታፍነው ተወስደዋል፡፡ ወደ አክሱም ዩንቨርሲቲ በመጓዝ ላይ የነበሩት ተማሪዎችም ተኩስና ግርግሩን በመሸሽ ወደመጡበት መመለሳቸውን ሰምተናል፡፡

ምንጭ : አዲስዘይቤ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#FAKE NEWS
ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ትምህርት ይቋረጣል‼️

ስድስተኛውን ሀገራዊ ምርጫ አስመልክቶ ትምህርት ይቋረጣል ፤ ዩንቨርሲቲዎች ይዘጋሉ በሚል የሚናፈሰው መረጃ ትክክለኛ አለመሆኑንና ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚባክን የትምህርት ጊዜ እንደማይኖር ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ስለሆነም ተማሪዎች ባልተረጋገጠ መረጃ ግራ አትጋቡ ፤ አዲስ ነገር ሲደርሰን የምናሳውቃቹህ ይሆናል!

#SHARE
ለተጨማሪ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉን👇👇
@Timhrtministers
@Timhrtministers
የጉራፈርዳ ጥቃት ...

በማነታቸው ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እየተፈፀመባቸው መሆኑን በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ተናግሩ።

ጥቃት የተፈፀመው አብዛኛው በሚባል ደረጃ በአማራ ተወላጆች ላይ ሲሆን በተፈፀመው ጥቃት የሰው ህይወት መጥፋቱን፣ ሃብት እና ንብረት መውደሙን ተጠቂዎች አሳውቀዋል።

ችግሩ በመንግስት ይፈታል/የንፁሃን ጥቃት ያስቀማል እየተባለ ቢጠበቅም ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ እና እየከፋ መምጣቱን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች ጥቃት እየተፈፀመብን ያለው "ውጡ" በሚል ነው ብለዋል።

ከተፈፀመው ጥቃት የተረፉ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እና ከቄያቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ።

የተፈናቀሉት ወገኖች በብርድ እና በፀሃይ እየተሰቃዩ ነው።

ህፃናት ፣ እናቶች ፣ ነፍሰ ጡሮች ተፈናቅለው ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የጥቃቱ ሰለባዎች በቀጣይ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፀመ መንግስት ጥበቃ እንዲያደርግላቸው የጠየቁ ሲሆን እራሳቸውን ተደራጅተው ከጥቃት እንዲጠብቁም አስተዳደራዊ መዋቅር ይፈጠረልን ሲሉ መጠየቃቸውን የአ/ብ/ኮ ዘግቧል።

ከጉራፈርዳው ጥቃት ጋር በተያያዘ መልዕክት ያስቀመጡ የጉራፈርዳ ቢፍቱ ቲክቫህ አባላት ከሰሞኑ በገለቲ ቀበሌ በተፈፀመ ጥቃት 10 ሰዎች መገደላቸውን ፣ በርካቶችም መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

ወረዳው አሁንም መረጋጋት አይታይበትም ያሉ ሲሆን ነዋሪው በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ መሆኑና መንግስት ታጥቀው ንፁሃንን በሚገድሉት ላይ እርምጃ እንዲወስድ ሲሉ ጠይቀዋል።

የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ በእጅግ ስልካቸው ለማግኘት የነዋሪዎችን ደህንነት ፣ ስለደረሰውን ጉዳት ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ስልክ ብንመታላቸውም ስልካቸውን አልተነሳም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከጉራፈርዳ ወረዳ ጋር በተያያዘ ...

ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ የተገኘው ከደቡብ ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ወሰኑ ወዳጆ ይፋዊ የማህበራዊ ገፅ ሲሆን የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳደር በወረዳው ያለው ችግር ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ይገልፃል።

ወረዳው ከጥቅምት ወር ከአንድ ቀበሌ የጀመረው የፀጥታ ችግር ከቀን ወደ ቀን ወደሌላ ቀበሌ እያካለለ የ "ሽፍታ" ቁጥርም እየጨመረ በመምጣቱ ወረዳው ከአቅም በላይ መሆኑን ከዚህ በፊት 24/6/2013 ዓ/ም በደብዳቤ የፀጥታ ኃይል እንዲመደብለት ፣ በቂ ትጥቅ እንዲላክለት ይህም በወቅቱ ካልቀረበ ያለው ችግር ከወረዳው ከአቅም በላይ መሆኑን አሳውቆ እንደነበር አስታውሷል።

ከዞኑ የተጠየቀበት ቀን ጀምሮም ከክልል ጋር በመነጋገር የተጠየቀው ጥያቄ ባለመሟላቱ አሁንም ከ3 ቀበሌ ወደ 6 ቀበሌ የፀጥታ ችግሩ መስፋፋቱን አመልክቷል።

በአጭር ጊዜ ወረዳው ፦
- መከላከያ ሰራዊት እንዲመደብለት
- ለሚሊሻ ወባላት ትጥቅ እንዲመቻችለት
- ከፖሊስ አባላት ጀምሮ የጥይት ፍሬ የሌላቸው መሆኑና
- በወረዳው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማውጣቱ ምንም የጥሬ ገንዘብ ስለሌለው ምላሽ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተጠየቁት ጥያቄዎች ምላሽ ካላገኙ / ካልተመቻቸ በአሁን ሰዓት የፀጥታው ሁኔታ ወረዳው መቆጣጠር የማይችልበት እና ከአቅም በላይ መሆኑን እንዲታወቅ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ መርሃ ግብር በደብረ ማርቆስ እና ጎንደር መካሄድ ጀምሯል!

የአማራ ብልጽግና ፖርቲ የምርጫ ቅስቀሳ በምሥራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ እና ጎንደር ዞኖች መካሄድ ጀምሯል።

በደብረ ማርቆስ በተጀመረው የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር፣ የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ሀላፊ አቶ አብርሃም አልኸኝና ሌሎችም የክልሉና የዞኑ የስራ ሀላፊወች ተገኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር በድጋፍ ሰልፉ ላይ እንደገለፁት ብልፅግና የኢትዮጽያን እንድነት የሚፈታተኑ ሀይሎች በፅናት በመታገል ያሸንፋቸዋል ብለዋል።

ፅንፈኛ ብሄርተኝነት የወለዳቸው ችግሮችን ለመቅረፍም ብልፅግና ፓርቲ የአማራ ህዝብ እሴቶች የሆኑትን ወንድማማችነትንና አብሮነትን በማቀንቀን የተደገሱልንን ፈተናዎች ለመሻገር በትጋት እንደሚሰራም ገልፀዋል።

የአማራ ብልፅግና ፓርቲ በተፈተኑ አመራሮች የተደራጀ በስሜት ሳይሆን በስሌት የሚራመድ ፓርቲ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ የልማት ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ ህዝቡ በምርጫው ድምፁን ለብልፅግና እንዲሰጥም ጠይቀዋል።

ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅም ሁሉም አካል ለሰላም ዘብ እንዲቆምም ጥሪ አቅርበዋል።

በተያያዘ ዜና የአማራ ብልጽግና ፓርቲ በጎንደር የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሀግብር እያካሄደ ነው።

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ በአራቱ የጎንደር ዞኖች ማለትም በማእከላዊ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን ጎንደር ዞኖችን ጨምሮ የጎንደር ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉበት የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃግብር በጎንደር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመርኃግብሩ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራል፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የምርጫ ቅስቀሳ መርኃግብሩ አካል የሆነው የፓርቲው የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት "አምፖል" የያዘ ቢልቦርድ በይፋ ተመርቋል።

#via Ebc

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from .D Typing
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዛሬ/ነገ ይፋ ይሆናል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ዕርማት መጠናቀቁን የትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አሳውቀዋል።

ተፈታኞች ውጤታችሁን ዛሬ/ነገ በ8181 ተጠባበቁ ተብሏል።

ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን ፥ "ፈተናው በሰላም መጠናቀቁ እና ኢንተርኔት አለመቋረጡ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል ፈተና ስኬት ሲሆን፣ በ2 ሳምንት ዕርማቱ መጠናቀቁ ደግሞ ተጨማሪ ስኬት ያደርገዋል" ብለዋል በትዊተር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
Forwarded from Deleted Account
😳😳ግቢ ላይ ያሉ ችግሮች 😳
♨️♨️ Part 1♨️♨️

⭕️ተማሪዎች ግቢ ላይ መጥፎ የተባሉ ነገሮች ይገጥማቸዋል። ከነሱ ዉስጥ አንድንዱን ልንገራችሁ.......

የዉ ብዙን ግዜ የምቸገሩት ሴቶች ስለሆኑ ይህን እንደምክር አቅርበናል። ሴቶች ላይ ከሚደርሱት ጥቃቶች ዉስጥ መደፈር የምል ነገር አለ። ብዙን ግዜ ዩኒቨርስቲዎች ከከተማ ዉጭ ናቸው። so ሴቶች ለማያትም ሆነ ለመጎብኘት ብቻቸውን ወደ ጫከ መሄድ የለባቸውም። እንኳን ሁለት ሆኖው እራሱ መሄድ የለባቸውም።

የምን ሴቶች ብቻ ወንዶች እራሱ ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ። ለምን ብትሉኝ ሌቦች በብዛት ከ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ስልክ ና pc(ላፕቶፕ) በማስፈራራት መውሰድ ለምደዋል።

👉በተለይ ወደ ጫከ አከባቢ 3'ና ከዛ በላይ ሆናችሁ መንቀሳቀስ አላባችሁ....

ሌለዉ ደግሞ በፈቃደኝነት ስተት በመስራት የማይመለስ ፀፀት ዉስጥ የምትገቡባት ነው። ወንዶች ዩኒቨርስቲ ስትገቡ አፋቸውን ከፍተዉ😂 እጃቸውን ዘርግተው ይቀበላቸዋል። እሄን ሚለዉ senior(ነበር) ተማሪዎች #fresh_set ተማሪዎች ግቢ ስገቡ ሁሉም ወንድ ተማሪዎች አንሰፍስፈው ጓደኛ በሚል ስም ሴቶችን ያዘናጋሉ።

🔹አገባብ 👇👇👇

☝️1)መጀመሪያ ልክ ግቢ ስትገቢ ያይሻል። ሻንጣሽ ትልቅ ስለሆነ ይመጣና ነይ ላግዚሽ ይላል....ከዛን ይሸከሚና አስከ #Dorm(setoch_gibi) ድረስ ያወራሻል...ከዛን ስ.ቁ ስጪኝ.....ነገሩ አለቀ

✌️2)ምዝገባ ላይ ተሯሩጦ ያስመዘገብሻል....እሱም በዚሁ.... ይቀጥላል

🤚 ተዉት ይሄን.... ለምን? የሴቶች ስልክ መቀበል (ስ.ቁ ማግኘት) በጣም ቀላል ነዉ.....ከዛ ቡሃላ ምን ይፈጠራል መሰለሽ.......አንድ ቀን #Over እንዉጣ ይልሻል። አንድ ቀን አብረሺዉ ካደርሽ ቡሃላ ምክንያት በመፍጠር ከንቺ ይርቃል ሌላ ይጠብሳል። በቃ ይሄው ነዉ።

🗣በተለይ ከገጠር አከባቢ የምመጡ ሴቶች ከተሸወዱ በጣም አስከፊ ነገር ላይ ይወድቃሉ። ማርገዝ የሚባል ነገር አለ ፍቅር ያሳየሽ መስሎ አታሎ...... ህይወትሽን ያጨልማል።

ከ ገጠር የሚመጡ ሴቶች በጣም ደስ ይላሉ ለምን ብትሉኝ አላማቸው አንድ ብቻ ነዉ። ፍቅረኛ አያቁ በትዳር ያምናሉ።
የከተማ ልጆች ደግሞ ሲታስጠሉ😂😂 ሁሉም አይደለም።

☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️ምክንያት አለኝ ግቢ ስትገቡ ሴት ልጅ ሰክራ በየ አስፓልቱ ስትወድቅ ምን ይባላል 🙈🙈 ይሄን የሚያደርጉት.... አወቅን ባይ የከተማ ልጆች ናቸው።

👷‍♀ሴቶች አደራ ሚላቹ የወንድ መጫወቻ እንደትሆኑ።

👷 አንተም ብሆን ተጠንቀቅ

👥ሁሉም ወንዶች አንድ አይደሉም። አንዳንድ ግዜ ሴቶች ይበልጣሉ... ቤተሰብ ጋር እያለች ሙሉ ጉርድ(ቀምስ) የምትለብስ ከሆነ ግቢ ስትገባ #mini_skrt ፣ ሱሪ የምትለብስ ከሆነ.... ተዉት አሁን መናገር ያሳፍራል።😁😁

🙆‍♂🙆‍♂ከ አስተማሪዎች ደግሞ ብዙ ችግር ይገጥማቸዋል። በተለይ ሴቶች...... ወንዶች እራሱ.....🤷‍♂🤷‍♂
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን ከግማሽ በላይ ተማሪዎች ከ350 በላይ ማምጣታቸው ተገለፀ።
-------------

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዲላሞ ኦተሪ(ዶ/ር) የ2012ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በተመዝጋቢ፣ በተፈታኝም እንዲሁም በውጤትም ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል።

ፈተናውን ከወሰዱ አጠቃላይ ተፈታኞች ውስጥ 55.7 ፐርሰንቱ ከ 350 በላይ አምጥተዋል።

በመግለጫው የፈተና ውጤት ከባለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በዚህም ከ 600 በላይ ያመጡ ተማሪዎች 702 መሆናቸው ተገልጿል።

የዓመቱ ከፍተኛ ውጤትም 669 ሆኖ መመዝገቡን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል ።

ተማሪዎችም ውጤታቸውን በፈተናዎች ኤጀንሲ ድረገፅ እንዲሁም በአጭር የፁሁፍ መልዕክት 8181 የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ከነገ ጀምሮ ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።

ወደ ዪኒቨርሲቲ መግቢያ ጊዜን እና ማለፊያ ነጥብን በተመለከተ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየተሰራ መሆኑም ዳይሬክተሩ በመግለጫው አስታውቀዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
የ12ኛ ክፍል ፈተና ይፋ ሆነ❗️

የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል። ውጤት ለማየት http://result.neaea.gov.et የሚለውን ክሊክ በማድረግ ይግቡ።

መልካም ውጤት ተመኝንላችሁ!

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
🥰1
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
ትምህርት ሚኒስተር የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤት ቅሬታ አቤቱታዎችን ከ ሚያዚያ 05 በኀላ አይቀበልም‼️

የ2012ዓ,ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤት የቅሬታ አቤቱታዎችን ት/ሚ የሚያስተናግደው የጊዜ ሠሌዳ ከመጋቢት 28/2013ዓ,ም እስከ ሚያዚያ 05/2013 ዓ,ም ድረስ በፈተና ኤጀንሲው ድህረ ገፅ በመሆኑ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች በድህረ ገፅ በሚወጣው ቅፅ መሠረት ቅሬታችሁን ማቅረብ እንደሚቻል ት/ሚ አስተውቋል፡፡

በትምህርት ሚንስቴር ዌብሳይት ላይ የሚገኘው የቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ👇

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSd2taZnPEhGPldTwTIx87tnYfEhYPkCWHnm3eRWjRhnD-FtTg/viewform

ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች ከ27 ጀምሮ ቅሬታ እንዲያቀርቡ ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር በጎሳ ግጭት 18 ሰዎች ተገደሉ በተፈናቃዮች ካምፕ የሚገኙ ቤቶች እና በአካባቢው የሚገኝ አንድ የህክምና ማዕከል መቃጠላቸውም ተገልጿል!

ዝርዝር መረጃውን ያንቡ👇

https://www.facebook.com/108129258039908/posts/116272407225593/?app=fbl
የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ድንበር ለቆ እየወጣ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ!

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች መግለጫ በሰጠው ምላሽ፣ የኤርትራ ወታደሮች ከኢትዮጵያ ግዛት በመውጣት ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።

የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ከቀናት በፊት በጋራ ባወጡት መግለጫ ላይ በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ከገለፁ በኋላ የኤርትራ ወታደሮች በፍጥነት እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ እንዲወጡ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው “ባለፈው ሳምንት እንደተገለጸው በሕወሓት ቀስቃሽነት ድንበር አቋርጠው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች አሁን ለቀው መውጣት የጀመሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ኃይልም ድንበሩን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል” ብሏል። (አዲስዘይቤ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአፋር ክልል በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ!

በአፋር ክልል ሀሩቃ በተባለ ቦታ ባለፈው አርብ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መቁሰላቸውን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ጥቃቱን ፈጸሙ የተባሉት የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በዚያኑ ዕለት ምሽት ገዋኔ በተባለ ቦታ በከፈቱት ተኩስ ሁለት የክልሉ መንግስት ሰራተኞች መገደላቸውንም ኮሚሽኑ ገልጿል። የሶማሌ ክልል ጥቃቱ የተፈጸመው “በክልሉ ልዩ ኃይል አባላት ነው” የሚለውን ውንጀላ አስተባብሏል።

የአፋር ክልል የፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ አቶ አህመድ ሁመድ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ዛሬ እንደተናገሩት፤ ወደ ክልላቸው ዘልቆ የገባው የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል፣ በሀሩቃ ቀበሌ ጥቃቱን የፈጸመው ከሁለት ቀን በፊት፤ መጋቢት 25፤ ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ ነው። የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ወደ ቀበሌዋ ገብተው ተኩስ መክፈታቸውን የሚገልጹት ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነሩ፣ በጥቃቱም “ከ30 በላይ ንጹሃን ዜጎች ተረሽነዋል” ብለዋል። (Ethiopia Insider)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
በጋምቤላ ክልል በሰዎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ የቆየው አዞ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተገደለ

በጋምቤላ ክልል ባሮ ወንዝ ለበርካት ጊዜያት የሰው ልጅ ህይወት ላይ አደጋ የደቀነው ግዙፍ አዞ ተገድሏል።ሰዎችን በመተናኮል ለህልፈት እና ለአካል ጉዳት የዳረገው ይህ አዞ እንዲገደል ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማውጣት ሶስት ጊዜ ለመግደል ሙከራ ቢደረግም ሳይሳካ መቅረቱን በጋምቤላ ከተማ የብልፅግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ድንገቱ ረፓሽ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ሰዎችን በመብላት ከፍተኛ ጉዳት ሲያደርስ የቆየው ይህ አዞ መሃል ከተማ ላይ ሳይቀር ጉዳት ሲያደርስ ቆይቷል።የፀጥታ አካላቱ በወሰዱበት እርምጃ ተገድሏል።

አዞ ከተገደላ በኋላ ሆዱ ሲቀደድ የሰው ልጅ እግር፣ሶስት ነጠላ ጫማ መገኘቱን አቶ ድንገቱ ረፓሽ ከብስራት ሬድዮ ዘጋቢ ስምኦን ደረጄ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (π)
#12ኛ ማለፊያ ነጥብ የሚነገረዉ የተማሪዎች ቅሬታ መልስ ካገኘ ቡሃላ ነው። ስለዚህ ማለፍያ ነጥቡ እስከ ሚያዝያ 5 ድረስ ይቆያል።

በጣም ብዙ ተማሪዎች በአካል ና በ Online ቅሬታ እያቀረቡ ይገኛሉ። የነዚህ ተማሪዎች ቅሬታ ምላሽ ካገኘ በኃላ ነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን ማወቅ የሚቻለው።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
Forwarded from Finance Today
መልካም ዜና ፌስቡክን ለሚያዘወትሩ ተከታታዮቻችን!!!

የመገኛ አድማሳችንን ከማስፋት አንፃር እና ከቴሌግራም ፌስቡክን መጠቀም ይቀለኛል ለሚሉ ቤተሰቦቻችን እነሆ የምስራች ብለናል! ቻናላችን ፔጅ ሆኖም ብቅ ብሏል።

በዚህ አዲሱ የፌስቡክ ገፅ የተለያዩ አነቃቂ እና አስተማሪ የሆኑ ነገሮችን አጋራቹሀለው በዚህ ሊንክ አዲሱን የፌስቡክ ገፄን ላይክ በማድረግ ቤተሰብ ሁኑ። አመሰግናለሁ

ከዚህ እንደሚከተለው የተቀመጠችውን ማስፈንጠሪያ በመጫን የፌስቡክ ገፃችንን ማግኘት ይችላሉ👇

https://www.facebook.com/108129258039908/posts/108130731373094/?substory_index=0&app=fbl