G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል ፈተና የካቲት 29 ይሰጣል።

የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና የካቲት 29 ቀን እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከየካቲት 22 እስከ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የዲጂታል መታወቂያ ይሰራጫልም ብሏል።

የፈተናው ገለጻ የካቲት 26 ቀን ተካሂዶ ፈተናው ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንደሚሰጥም ሚኒስቴሩ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቀጥታ (ኦንላይን) ይሰጣል ተብሎ የነበረው ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥም የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
G-Tutorialclass pinned «የ12ኛ ክፍል ፈተና በወረቀት ይሰጣል። ትምህርት ሚኒስቴር በኦንላይን ሊሰጥ የነበረውን የ2012 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እንደሚሰጥ ዛሬ አስታውቋል። በኦንላይን ለመስጠት የታሰበው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በኮቪድ-19 ምክኒያት መፈተኛ ታብሌቶች በግዜ ወደ ሀገር ውስጥ መግባት ባለመቻላቸው ነው በወረቀት ለመስጠት የታሰበው ብሏል ሚኒስቴሩ። ከየካቲት 21 እስከ…»
ባለቤቱንና ልጁን የገደለው ግለሰብ የሞት ውሳኔ ተላለፈበት።

በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ "አለም ገበያ ከተማ" ልዩ ስሙ ጤና ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት የገዛ ባለቤቱንና የ4 ዓመት ልጁን በቤት ውስጥ እያሉ ቤት ላይ ቤንዝል አርከርክፎ ያቃጠለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

በስልጤ ዞን በሳንኩራ ወረዳ አለም ገበያ ከተማ ልዩ ስሙ ጤና ተብሎ በሚጠራው አከባቢ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ከሌሊቱ 9፡00 ሰዓት የገዛ ባለቤቱንና የ4 ዓመት ልጁን በቤት ውስጥ እያሉ ቤት ላይ ቤንዝል አርከርክፎ ያቃጠለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ እንደተላለፈበት የስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የስልጤ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋ/ኢ/ር ካሚል ሀምድ ስለወንጀል ድርጊቱ እንዳስታወቀው ተከሳሽ ይልማ ዱባለ የተባለው ግለሰብ ሟች ሀዲሪያ ሲራጅ የተባለችውን ባለቤቱን 12 ዓመት አረብ አገር ለፍታ ያመጣችውን ሀብት በስሜ አዙሪ በማለት የተጀመረው ጭቅጭቅ ውሎ እያደረ ሌላ አጀንዳ እያስከተለ በባልና ሚስት ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እየከረረ ሲሄድ በስሜ ማዞር ያልፈለግሽው ንብረትሽን በጎን ሌላ ፍቅረኛ ስላለሽ ነው በማለት በመሀላቸው ያለውን ግንኙነት ወደ አደገኛ ደረጃ እንዲሸገር አድርገል፡፡ 
ተከሳሽ የገዛ ባለቤቱንና የልጁን የሚገልበትን ምቹ ሁኔታ አመቻችቶ የካቲት 13 ቀን 2012 ዓ/ም ቤንዝል ገዝቶ ወደ ቤት ሲመጣ ሟች ቤንዝሉን ለምን ገዛህው ብላ ስትጠይቀው ገዝቸው ሳይሆን ሞቴር ያለው ጓደኛ አስቀምጥልኝ ብሎኝ ነው ይላታል።
ቀኑ መሽቶ የ5 ወር ነፍሰ ጡር የሆነችው ባለቤቱ ሀገር አማን ነው ብላ የ4 ዓመት ህፃኑዋን በጉያዋ ታቅፋ በተናችበት በውድቅት ሌሊት ባሏ በቡና መውቀጫ ዘነዘና የተለያየ የሰውነት ክፍሏን ደጋግሞ በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ቤቱን ዘግቶ በህይወት የነበረችው የ4 ዓመት ህፃን በቤቱ እያለች በቤንዝል አርከፍክፎ ቤቱን እንዲቃጠል አድርጎ የእናትና የልጅ ህይወት እንዲያልፍ ካደረገ በኋላ ወደ ኦሮሚያ ክልል አጋሮ ከተማ ለጥቂት ወራት ተሰውሮ መኖር ይጀምራል፡፡  
የስልጤ ዞን ፖሊስ ተከሳሽ ይልማ ዱባለን ከተደበቀበት ኦሮሚያ ክልል አጋሮ ከተማ አድኖ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን ከዓቃቤ ህግ ጋር በመሆን ለስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀርባል የክስ መዘዝገቡ የቀረበለት የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዳዩን በጥንቃቄ መመልከት ይጀምራል፡፡ 
የቀረበለት የክስ መዝገብ የተመለከተው ፍ/ቤት ግራና ቀኙን ተመልክቶ ተከሳሽን እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ መከላከል ባለመቻሉ ለተፈፀመው ወንጀል ተከሳሽን ይመጥናል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል በማለት የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል መረጃውን ያገኘነው ከስልጤ ዞን ፖሊስ መምሪያ ነው፡፡
(ፌዴራል ፖሊስ)
የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ‘የመደመር መንገድ’ መፅሃፍ ገበያ ላይ ዋለ‼️

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ‘የመደመር መንገድ’ የተሰኘው መጽሐፍ ገበያ ላይ ዋለ። መጽሐፉ፥ የለውጡን ፈለግ እና መደመር ያለፈበትን መንገድ እንደሚዳስስ ተነግሯል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Entrance Exam Time Table
@Timhrtministers
@Timhrtministers
Forwarded from Deleted Account
ሰበር ዜና......እባክህ/ክሽ ካነበቡት በሁዋላ Shere አርጉት
😳😳😳😳😳😳😳😳😳😳
😯😯😯😯😯😯😯😯😯😯
😞😞😞😞😞😞😞😞😞😞
ያልሰማ ካለ plz ለህይወትህ ስትል ስማ
ትናንት በናሽናል ጂኦግራፊ ዋይልድ ቻናል ላይ
የተላለፈው ዜና አስደንጋጭ ነበር😟
, ማለትም ሳይንቲስቶች እንደገለፁት ከሆነ በጣም
አደገኛ እባብ 🐍ተገኝቷል ሳይንቲስቶቹ እንደተናገሩት
እባቡ ምግብ በበላ ቁጥር 0.5ሴ.ሜ ያድጋል
ምግቡን ደግሞ የሚበላው ቢበዛ በ 30 ሰከንድ
ውስጥ ነው ታዲያ ይህን እባብ በምንም አይነት
ሰው ሰራሽ መሳሪያ መግደል አለመቻሉ ነው ነገሩን
አስፈሪ ያደረገው ሊሞት የሚችለው እራሱን
በራሱ ከነከሰ ብቻ ነው ነገር ግን ሳይንቲስቶች
ሌላ የሚገድለውን ነገር እየፈለጉ ነው ይህ እባብ
በሰዉ ልጆች ታሪክ ከተመዘገቡ ገዳይ በጣም
አደገኛና መርዛማ ከሆኑ እባቦች ሁሉ ዋናው ነው😳
ታዲያ ይህ እባብ አንድ ቦታ ብቻ ነው የሚገኘው
እሱም








ኖኪያ 3310 የስልክ ቀፎ ላይ የጌም ምርጫ
ውስጥ snake xenzia. ላይ ነው ፡፡
በትእግስትና በጥሞና ስላነበባችሁት
አመሰግናለዉ 😂😂


እወዳቹሀለው መልካም አዳር 😍😍

ሼር አርጎ ማስደንገጥ እንዳረሱ 😂😂
@ethiofunnypp 🦋
ሁሌም ፈታ ለማለት join በሉ😍😍😘😘😘❤️❤️❤️
Forwarded from Ýøñä
Forwarded from Free Education Ethiopia ︎ (BÊŽÂ)
የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦

↘️የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

↘️በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

↘️አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።

↘️ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።

↘️የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

        @Free_Education_Ethiopia
Stay safe
የሰው ማገትና ግድያ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦች እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጡ!

በተከሰሱበት የሰው ማገትና ግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው የተገኙ ሁለት ግለሰቦች እስከ እድሜ ልክ ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን አስተባባሪ አቶ አበበ ማስሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ግለሰቦቹ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በፈጸሙት የሰው ማገት ወንጀል ተከሰዋል።

ተከሳሾች በተጠቀሰው እለት በመተማ ወረዳ ጉባይ ጀጀቢት ቀበሌ ልዩ ቦታው ኩሊት መገንጠያ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ከሽንፋ ወደ ገንዳ ውሃ ሲጓዝ የነበረ ሲኖ ትራክ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ በማስቆም አሽከርካሪውንና ረዳቱን አግተው ወስደዋል።

እገታውን ከፈጸሙ በኋላ የታጋች ቤተሰቦችን በማስገደድ 150 ሺህ ብር ተቀብለው ታጋቾችን መልቀቃቸውን ተናግረዋል።

ግለሰቦቹ ታጋቾችን ወደ ጫካ በወሰዷቸው ወቅት ባደረሱባቸው ከባድ ድብደባና እንግልት አሽከርካሪው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

ተጨማሪ የምስል መረጃዎችን ለማግኘት #የዩትዩብ ገፃችንን #subscribe ያርጉ👇
https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg

@ethio_mereja_news
@etho_mereja_news
ሳሚያ ሱሉሁ ሐሳን ቃለ መሃላ ፈጽመው የታንዛኒያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆኑ!

ታንዛኒያን ለቀጣዮቹ 5 ዓመታት ይመራሉ ተብሏል

ሳሚያ እስከ ጆን ማጉፉሊ ህልፈተ ህይወት ድረስ በምክትል ፕሬዝዳንትነት ማገልገላቸው የሚታወስ ነው

ከደቂቃዎች በፊት ቃለ መሀላቸውን የፈጸሙት ፕሬዘዳንት ሳሚያ ታንዛኒያን ለቀጣዮቹ 5 ዓመታት ይመራሉ ተብሏል፡፡

ይህም ላለፉት 7 ዓመታት በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሲያገለግሉ የነበሩትን የ61 ዓመቷን አዛውንት ታንዛኒያን በፕሬዝዳንትነት ለመምራት የቻሉ የመጀመሪያዋ ሴት ያደርጋቸዋል፡፡

እንደ ጎርጎሮሲያን ዘመን አቆጣጠር በ1960 በዛንዚባር ራስ ገዝ አስተዳደር የተወለዱት ሳሚያ ከ2015 ጀምሮ የማጉፉሊ ካቢኔ አባል ሆነው አገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በህዝብ አስተዳደር 2ኛ ዲግሪ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውም ሲሆን ከባለፈው ዓመት ጀምሮ የታንዛኒያ ፓርላማ አባል እንደነበሩ የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል።

ባለትዳር እና የ4 ልጆች እናትም ናቸው ሳሚያ፡፡

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከህዝብ እይታ የመሰወራቸው ጉዳይ ሲያነጋግር የነበሩት ፕሬዝዳንት ጆን ፖምቤ ማጉፉሊ ትናንት የማረፋቸው ዜና ተሰምቷል።

በፕሬዝዳንቱ ሞት ምክንያትም ታንዛኒያ 14 ብሔራዊ የሀዘን ቀናትን አውጃለች።

ጎረቤቷ ኬንያም የስድስት ቀናት ብሔራዊ የሀዘን ቀን ማወጇን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል። የኬንያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ዛሬ ከታንዛኒያ አቻው ጋር ሊያደርግ የነበረውን የወዳጅነት ጨዋታ ለማጉፉሊ ክብር ሲባል መሰረዙንም የሃገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

እንደ ታንዛኒያ ህገ መንግስት አንቀጽ 37 (2) ከሆነ የአገሪቱ ፕሬዘዳንት በሞት አልያም በሌላ በማንኛውም ምክንያት በስልጣን ላይ ሆኖ አገሪቱን መምራት ካልቻለ ምክትል ፕሬዘዳንቱ እንዲመሩ ይፈቅዳል።

@ethio_mereja_news
#ሰበር_መረጃ‼️

መንግስት ከሕገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ጋር ለሚተባበሩ አካላት የመጨረሻ ማሳሰቢያ ሰጠ❗️

የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫውም መንግሥቱን እና ሌሎች የሀገሪቱን መሠረታዊ ሕጎች በመጣስ በሕወሓት ውስጥ የበላይነቱን የያዘው ቡድን፣ የሀገር አለኝታ እና ኩራት በሆነው የመከላከያ ሠራዊት ላይ የኃይል ጥቃት መሰንዘሩን አስታውሷል።

ከዚህ ጥቃትም አስቀድሞ፣ የጥቃቱ ጠንሳሽ የሆነው ቡድን፣ የሀገርን ሰላም እና የሕዝቦችን አንድነት አደጋ ላይ የሚጥሉ የተለያዩ ሕገ ወጥ ተግባራትን ሲፈጽም ነበር ብሏል ፅህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ፡፡

ይህ ሕገ ወጥ የሕወሓት ቡድን በቀጥታና በተዘዋዋሪ በፈጸማቸው የጥፋት ተግባራት የሰላም መደፍረስ፣ የዜጎች ሞት እና መፈናቀል እንዲሁም አካባቢያዊ መናጋት ተፈጥሮ ቆይቷል፡፡

የፌዴራል መንግሥት ችግሩን በሰላማዊ መንግድ ለመፍታት ያሳየውን ትዕግሥት እንደ ድክመት በመቁጠር ሕገ ወጡ የሕወሓት ቡድን ሀገርን የመድፈር ወንጀል ፈጽሟልም ብሏል፡፡

በተለይም በመከላከያ ሠራዊት ላይ የተፈጸመው ሰፊ ጥቃት ሊታለፍ የማይችል እና የሀገርን ህልውና የሚፈታተን ትልቅ ወንጀል መሆኑን ያነሳው መግለጫው፥ ይህ ሁኔታ መንግሥት ተገቢ ሕግ የማስከበር እርምጃ እንዲወስድ የሚያስገድድ ቅርብና ግልጽ አደጋ የደቀነ እንደነበርም አውስቷል፡፡

እንዲህ ያለ ነገር ሲፈጠር መንግሥት የሀገርን ሉዓላዊነትና የሕዝብን ደኅንነት ለመጠበቅ ሲል ተገቢውን ሕግ የማስከበር እርምጃ የመውሰድ የሞራል እና የሕግ ግዴታ እንዳለበት እሙን ነውም ብሏል መግለጫው።

ይህን ግዴታውን ለመወጣት የፌደራል መንግሥት በሕወሓት ሕገ ወጥ ቡድን ላይ የሀገሪቱ ሕግ የሚያዘውን እርምጃ መውሰዱንም አስታውሷል፡፡

በዚህ እርምጃም ከሀገር አልፎ ለቀጠናው ሥጋት ሆኖ የቆየው የሕወሓት ሕገ ወጦች ቡድን ከፍተኛ ወታደራዊ አቅም እና ዝግጁነት መደምሰሱንም ጠቅሷል።

የዚህ ቡድን ቁልፍ አመራር የሆኑት ግለሰቦች ከፊሎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው ለሕግ የቀረቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ አቅማቸው እና ኃይላቸው እጅጉን ተዳክሞ፣ ከሕግ በመሸሽ የሚባዝኑ የፍትሕ ተሳዳጆች መሆናቸውንም አንስቷል።

በክልሉ በሕገ መንግሥታዊ አግባብ እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ የፌደራል መንግሥትም አጥፊው ቡድን በቀሰቀሰው ግጭት የደረሰውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት መልሶ ለመገንባት እና ለማቋቋም እየሠራ እንደሚገኝም አስረድቷል።

ይህ የመልሶ ግንባታና የማቋቋም ሥራ የሁሉንም ርብርብ እና እገዛ የሚጠይቅ ነው ያለው መንግስት፥ ለዚህም መላው ኢትዮጵያውያን፣ እንዲሁም የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡንም አስታውሷል።

የደረሰውን ሰብአዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ለመቀነስ እና ክልሉን በተሻለ የአስተዳደር እና የልማት ቁመና ላይ ለማድረስ የማይተካ ሚና ካላቸው ተዋንያን ዋነኛዎቹ የክልሉ ተወላጅ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ናቸውም ነው ያለው።

ከእነዚህ ዜጎች አንዳንዶቹ በሕወሓት ፕሮፖጋንዳም ሆነ በሕገ ወጡ ቡድን አስገዳጅነት ነፍጥ አንግበው በውጊያ ሜዳ ላይ እስከመሰለፍ መድረሳቸውንም ገልጿል፡፡

ነገር ግን እነዚህ የክልሉ ተወላጆች ዋነኛው የጥፋቱ ጠንሳሽ እና ባለቤት አለመሆናቸውን መንግሥት ይገነዘባል ያለው መግለጫው፥ ከዝርፊያው እና ከምዝበራው ተካፋይ ያልነበሩ፣ ሀገራቸውን የሚወዱ የክልሉ ተወላጆች በአጥፊው ቡድን ጎትጓችነት እና ቅስቀሳ ከመንግሥት ጋር ተቃርነው፣ መሣሪያ ታጥቀው የተሰለፉ ቢሆንም እንኳን መንግሥት ነገሩን በሆደ ሰፊነት ማየት እንደሚገባው ያምናልም ብሏል።

በመሆኑም የሀገር አንድነትን ለማጠናከር እና አጥፊው ቡድን ያፈረሳቸውን የጋራ እሴቶችን፣ አብሮነትን እና መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት የተለያዩ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን መንግሥት እንደሚያምንም ጠቅሷል፡፡

በመሆኑም፣ በሕገ ወጥ ጥቃቱ እና ተያያዥ በሆኑ የወንጀል ተግባራት ጉልህ ተሳትፎ አላቸው ተብለው ከተጠረጠሩ እና በዚህ መነሻ የፍርድ ቤት መያዣ ከወጣባቸው ከፍተኛ የሕወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች በስተቀር ሌሎች ዜጎች ያለ ሥጋት ወደ ቀደመው ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ፤ ይህንንም እውን ለማድረግ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደ ቀያቸው እና መኖሪያቸው በመመለስ ማኅበረሰቡን እንዲቀላቀሉም ጥሪውም አቅርቧል።

በዚህ መንገድ ከአጥፊው ቡድን ተለይተው ወደሰላማዊ ኑሯቸው የሚመለሱ የክልሉ ተወላጅ ዜጎች፣ የትኛውም የሕግ ተጠያቂነት ሳይኖርባቸው፣ ከአጥፊ ተግባራት ተቆጥበው፣ ወደ ሥራቸው እና ኑሯቸው በሰላም መሠማራት እንደሚችሉም ነው አንስቷል።

እነዚህን ዜጎች በመልካም ሁኔታ በመቀበል እንዲተባበሩ እና የተቻላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ለሚመለከታቸው የጸጥታ፣ የአስተዳደር እና የሕግ አስከባሪ ተቋማት አስፈላጊው መመሪያ መሰጠቱንም ነው የገለጸው።

የጥፋት ቡድኑ አካል ሆነው በተፈጸመው ወንጀል ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ፣ የፍርድ ቤት መያዣም የወጣባቸው ከፍተኛ የሕወሓት ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ አመራሮች፣ በሰላም እጃቸውን ለሕግ አስከባሪ ተቋማት እንዲሰጡም መንግሥት ጥሪ አቅርቧል።

እነዚህ አመራሮች እስከዛሬ ከደረሰው ሀገራዊ ጥፋት እና ጉዳት በመማር፣ ለፍትሕ ራሳቸውን በማቅረብ፣ ተጨማሪ ሀገራዊ ኪሣራ እንዳይደርስ እና በከንቱ የዜጎች ደም እንዳይፈስ የበኩላቸውን በጎ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም ነው መንግሥት ጥሪ ያቀረበው።

ይህንን የሚያደርጉ ከፍተኛ የሕወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ራሳቸውን ከከፋ ቅጣት፣ ወገናቸውን ከመጎሳቆል ይታደጉታል ሲልም ነው ጥሪው ያቀረበው፡፡

ይህንን የመጨረሻ ጥሪ ተጠቅመው ራሳቸውን ለፍትሕ በማያቀርቡ የሕወሓት ከፍተኛ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ ግን ሕግ በሚፈቅደው ሁሉም ዓይነት መንገድ፣ ሕግ ለማስከበር ሲባል፣ አስፈላጊው ሁሉ የሚፈጸም ይሆኗል ብሏል መንግስት፡፡

ተጨማሪ የምስል መረጃዎችን ለማግኘት #የዩትዩብ ገፃችንን #subscribe ያርጉ👇
https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Finance Today
የዓለም አገራት ህዝቦች የደስተኝነት ደረጃ ፤ የኢትዮጵያ ስንተኛ ?

በተመድ በሚደገፈው በዓመታዊ የዓለም አገራት ሕዝቦችን ደስተኝነት በሚለካው ጥናት ፤ ከ149 አገራት ሕዝቦችን የደስተኝነት ደረጃ #ኢትዮጵያ 133ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ከዓለም አገራት በተለያዩ መለኪያዎች ደስተኛ ሕዝብ ያላት ቀዳሚዋ አገር ፊንላንድ ስትሆን ዴንማርክ ሁለተኛ ፣ ስዊትዘርላንድ ሦስተኛ ፣ አይስላንድ አራተኛ እና ኔዘርላንድስ አምስተኛ በመሆን ተከትለዋታል።

ከአንደኛ እስከ አስረኛ ደረጃ ከያዙት አገራት ውስጥ አውሮፓዊ አገር ያልሆነችው ኒውዚላንድ ብቻ ናት።

ይህ ውጤት የተገኘው ጋሉፕ በተባለው የመረጃ ተንታኝ አማካይነት ደስተኛነታቸውን ለማወቅ ከ149 የዓለም አገራት በተሰበሰበ መረጃ መሠረት ነው።

ይህ የሰዎች የደስተኝነት ሁኔታ የተለካው የሚያገኙት ማኅበራዊ ድጋፍ፣ ግለሰባዊ ነጻነት፣ ጠቅላላ አገራዊ ምርት (ጂዲፒ) እና በአገራቱ ውስጥ ባለው የሙስና መጠንን ጨምሮ ሌሎችንም መመዘኛዎች በመመልከት ነው።

በዚህ ዓመቱ ጥናት ከዓለም አገራት ውስጥ ደስተኛ ያልሆኑ ሕዝቦች ይኖሩባቸዋል የተባሉት አፍጋኒስታን፣ ሌሶቶ፣ ሩዋንዳ እና ዚምባብዌ ናቸው።

የጥናቱ አዘጋጆች እንዳሉት ዓለምን ባጠቃት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሰበብ አንድ ሦስተኛ በሚሆኑ አገራት ውስጥ "አሉታዊ የሆኑ ስሜቶች በተደጋጋሚ የመከሰታቸው ሁኔታ ከፍተኛ ነበር" ብለዋል።

የእስያ አገራት ባለፈው ዓመት ከነበራቸው ደረጃ መሻሻልን ሲያሳዩ ቻይና ቀደም ባለው ዓመት ከነበራት የ94ኛ ደረጃ ወደ 84ኛ ከፍ ብላለች።

Via BBC
Forwarded from Finance Today
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ.pdf
95.5 KB
#UPDATE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛዉን አጠቃላይ ምርጫ ለመታዘብ ለሲቪል ማህበራት እውቅና የመስጠት ስራውን እንዳጠናቀቀ ዛሬ አሳውቋል።

በምርጫው 134,109 የአገር ውስጥ ታዛቢዎች ይሰማራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

- በሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሰሩ 8 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የቀረቡ 61,851 ሴት ታዛቢዎች (46%) ሲሆኑ፣

- በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን ስር የታቀፉ 7 ማህበራትን ያካተተ 244 ታዛቢዎች እና

- በሀገር ዉስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ሂደትን ለመታዘብ በተመረጠ 1 የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የቀረቡ 100 ታዛቢዎች እና በስሩ 37 ያህል ሲቪል ማህበራትን ያቀፈ የሲቪል ማህበረሰብ ኔትወርክ ይገኙበታል።
Forwarded from Finance Today
ሰበር መረጃ‼️ አሁን የደረሰን ዜና/ረብሻ ተነሳ/21 ሸኔዎች ተደመሰሱ/ከ1900 በላይ ሰዎች ተያዙ/ግብፅ በአባይ ጉዳይ ተወያየች

linkun በመጫን ዝርዝር መረጃው ያድምጡ👇

https://youtu.be/O8JLwypIWxg
Forwarded from Finance Today
በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀሙ ዘር ተኮር ጥቃቶች በአጥፊዎች ላይ ርምጃ በመውሰድ እንዲቆሙ አብን ጠየቀ‼️

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ባወጣው መግለጫ በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬና አጎራባች አካባቢዎች የጥላቻ ኃይሎች በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት በሕዝብ ላይ መክፈታቸውን እንዳረጋገጠ አስታውቋል። በዚህም ምክንያት ሕይወት መጥፋቱን፣ አካል መጉደሉንና ንብረት መውደሙን አመላክቷል።

“ጥቃቱ የተከፈተውና እየተፈፀመ ያለው በመሀል የአማራ አካባቢዎች ሲሆን ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ የነበሩ ጥቃቶች ቀጣይ ክፍል ሆኖ በተለይ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ የትህነግን አሸባሪ ኃይል ለመመከት፣ ሕዝቡን፣ ክልሉንና ሀገሩን ለመከላከል ወደ ክልሉ ምዕራባዊና ደቡባዊ ግዛቶች መንቀሳቀሱን ተከትሎ መሆኑ ብዙ ነገር ይገልጣል” ብሏል ፓርቲው።

ፓርቲው ቀደም ብሎ መረጃው በደረሰው ወቅት ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት በማሳሰብ አጥፊዎቹ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት አፋጣኝ እርምጃ ተወስዶ የሕዝብ ሰላም እንዲረጋገጥ ጠይቆ እንደነበርም ባወጣው መግለጫ አስገንዝቧል።

ተጨማሪ የምስል መረጃዎችን ለማግኘት #የዩትዩብ ገፃችንን #subscribe ያርጉ👇
https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from G-Tutorialclass (Gebre Tesfu)
👋ሰላም Gebre ይህ ከታች የላክንልዎ የእርሶ መለያ ቁጥር ነው ይህን ለ 25 ሰዎች በመላክ እና Start እንዲሉ በመጋበዝ የ 500 ብር የሞባይል ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/AwashBankRefferalBot?start=r05511284830

💞 መልካም እድል 💞
💎Awash Bank💎
Forwarded from Natnael Mekonnen
#Ethiopia : በሸዋሮቢት የተከሰተው ተኩስና ጥቃት ከከተማው ፖሊስ ቁጥጥርና አቅም በላይ መሆኑን አሁን በስልክ ያገኘውት የፖሊስ አባል አሳውቆኛል:: ያለን አማራጭ የቀብሌ 05 ህዝብን ከቦታው ማስወጣት ነው ይህንንም እያደረግን ነው በማለት የፖሊስ አባሉ ገልጾልኛል::
​​◦◉◉◎አይዞሽ ኢትዮጵያዬ◦◉◉◎

አንች ትልቅ ሀገር
በአባቶቸ አጥንት
በአባቶቸ ደም ፀንተሽ የቆየሽው
፡፡
ምን? አድርገሽ ይሆን
በአጥፊዎች ሰበዝ የምትታመሽው።
በምን ?ሀጢአትሽ ነው

ወልደሽ ባሳደግሽ የምትነከሽው።

የበረከት ምድር: የታሪክ ማህደር
ኤትዮጵያ ሀገሬ።
ስልጣን አገኝ ብለው

በእንባ ያራጬሽ
በደም ያጨቀዩሽ ገለውሻል ዛሬ።


አይዞሽ እናታለም ፡
አይታለፍ የለም ይሄም ጊዜ ያልፋል ።
ከችግርሽ በላይ

ባርኮ የፈጠረሽ ፈጣሪ ይገዝፋል።

አይዞሽ ኢትዮጵያየ

ሳቅሽን ያጠፋው
ለቅሶሽን ያበዛው
መከራሸ ቢያመኝም።

ይሁን ቻል አድርጊው
ከመከራው በፊት ትንሳኤ አይገኝም።

01/03/13
Samuel Adane
@Sam2127
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው

➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @Daniel_bewketu
@Daniel_bewketu
➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟
Forwarded from Finance Today
ዛሬ ጠዋት ከብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች ጋር በነበረን ስብሰባ ወቅት፣ሠራዊታችን የሠላም ጠባቂ እና የሀገራችንን ሉዓላዊነት የሚያስከብር በመሆኑ የሚሰማኝን ኩራት ገልጫለሁ!

ስነ ምግባርን እና ሙያተኝነትን የማጠናከር እና በየትኛውም የሕግ ማስከበር ሥራ የመከላከያ ሠራዊታችንን እሴቶች የማይወክል ተግባር የሚፈጽሙትን ተጠያቂ ማድረግ፣ በአግባቡ ኃላፊነታቸውን የሚወጡትን መሸለም እንደሚገባ አሳስቤያለሁ።

የተጠያቂነት እና የስነ ምግባር ክፍተቶች በተገቢው ስርዓት ርምጃ የሚወሰድባቸው ይሆናል።

©ጠ/ይ ሚ/ር አብይ አህመድ

ተጨማሪ የምስል መረጃዎችን ለማግኘት #የዩትዩብ ገፃችንን #subscribe ያርጉ👇
https://www.youtube.com/channel/UCHaghmzBorbg1g2Bb_cO5Vg

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news