G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የዩኒቨርሲቲዎችን ትክክለኛ ገፅ ብቻ በመከተል ከሀሰተኛ የዩኒቨርሲቲ ጥሪዎች እራሳችሁን ጠብቁ ፦

👉 ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/DDUniv/

👉 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Hawassa.University/

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Addis-Ababa-University-496255483792611/

👉 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/TheUniversityofGondar/

👉 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/bduethiopia/?ref=page_internal&mt_nav=0

👉 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/?_se_imp=0ueaW0ZojpEObV9zR

👉 ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/HRMUNIV/

👉 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/JimmaUniv/

👉 አርሲ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=357578986410375&id=100064748293256

👉 ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፦https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

👉 ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WachemoUniversity2008/

👉 ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/265529850297666/posts/1845133279003974/?app=fbl

👉 መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/141864125910414/posts/4794315817331865/?app=fbl

👉 ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education-website/Wollega-University-Corporate-Communications-2319182621440303/

👉 አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/234983083247967/posts/5141798579233035/?app=fbl

👉 ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/2181225212102194/posts/3109977289226977/?app=fbl

👉 ቦረና ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/BoranaUniversityBRU/

👉 ቀብሪድሃር ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education/Kebri-Dehar-University-306587496533329/

👉 ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/pages/category/Education/Jinka-University-178538809733160/

👉 ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/547073878695780/posts/5065885566814566/?app=fbl

👉 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/1879460055640998/posts/3057857987801193/?app=fbl

👉 ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WoldiaUniversity/

👉 ወሎ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/WolloUniversity111/

👉 ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/1301588393256101/posts/5145148712233364/?app=fbl

👉 ኦዳቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/OBUEthiopia/

👉 አምቦ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/AmboUniversityofficial/

👉 ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Mizan-Tepi-University-MTU-362390684253048/

👉 ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/614590095253065/posts/5432186613493365/?app=fbl

👉 ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/979926502053136/posts/5129611493751262/?app=fbl

👉 ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/336146983089022/posts/5029908297046177/?app=fbl

👉 ኮተቤ ፦ https://www.facebook.com/792405150779154/posts/5397052686981021/?app=fbl

👉 ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/100064618752509/posts/386404006856888/?app=fbl

👉 መቱ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://www.facebook.com/330316734055129/posts/1468350973585027/?app=fbl

👉 መቅደላአምባ ዩኒቨርሲቲ ፦ https://m.facebook.com/Mekdela.Amba.University/

ተጨማሪ ጥያቄዎች ካላችሁ ከታች በአስተያየት መስጫው አስቀምጡ።
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass

@NEAEA_nea
1
📚 ደብረ ታቦር ዪኒቨርስቲ ለደረሳችሁ አጠር ያለች ማብራሪያ❗️

🤞ደብረታቦር ከተማ ከአዲስ አበባአበባ 600 km የደቡብ ጎንደር የምትገኝ አነስ ያለች ከተማ ስትሆን አቅራቢያው የሚገኙከተማዎች ጎንደር እና ባህርዳር ናቸው አካባቢው ትንሽ ብርድ አለበት ወፍራም ልብስ ይዛችሁ ሂዱ።

👉ግቢያችን ናቹራልም ሶሻልም department የሚሰጥ ሲሆን
የሶሻልም እና የናቹራሉ ግቢ አንድ ነው።
ግቢው፡
👉Technology (ENGINEERING , Computer science, IT)
👉HEALTH (medicine , phamra, medical lab...)
👉SOCIAL(law, Accounting, management... )
👉COMPTITIONAL ( physics, chemistry, history, maths...)
👉Agriculture

👉የወንዶች ዶርም ለ4 ሲሆን የሴቶች ጋር አንዳንዴ ለ6
የሚመደቡበት case አለ ያኔ locker share ማረግ ሊኖርባቸሁ ይችላል ። Almost ሁሉም block ላይ Ds tv አለ ።
የቤት ኪራይ universityው አካባቢ ከ400- 600 ይገኛል
ኮንደሚኒየም ከፈለጋችሁ ደሞ 800 ማገኝት ይቻላል።

👉ኑሮ የcafe ምግብ average የሚባል አይነት ሲሆን Non cafe
መሆን ለምትፈልጉ የግቢ ውስጥ ላውንጆች እና የውጪ ምግቢ
ቤቶች መጠቀም ይቻላል ዋጋቸው ተለዋዋጭ ነው።

🤞እንኳን ወደ ደብረታቦር university በሰላም መጣችሁ🙏

ሌላ እንዲተዋወቃችሁ የምትፈልጉት ግቢ ካለ ኮሜንት ስጡን። እንዲሁም senior ተማሪዎች ስለግቢያችሁ አዲስ
ለሚገቡ ተማሪዎች በዚህ አይነት ማብራርያ ፅፋችሁ
ብትልኩልን በደስታ እናደርሳለን🙏

Yab Reckless 🙏

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
🗣🗣 ዩኒቨርሲቲ እና ተግዳሮቶቹ

🔰 ክፍል 1

@GTutorialclass ቻናል አዘጋጅነት የቀረበ።

መነሻ ሀሳብ ኢትዮ ዩኒቨርሲቲ።


🤗 ዩኒቨርሲቲ ላወቀበት ተማሪ እጅግ በጣም ብዙ መልካም የሆኑ ገፀ በረከቶች አሉት፡፡

እነዚህን መልካም ገፀ በረከቶች ስትገቡ ታጣጥሙታላችሁ🤓። እኛ ግን የምንፈልገው እናንተ ተግዳሮቱቹን አውቃችሁ ፡ ራሳችሁን እንድትታደጉ ነው።



😥ተማሪዎች ግቢ ላይ መጥፎ የተባሉ ነገሮች ይገጥማቸዋል።

እስኪ የተወሰኑትን እንመልከት

1ኛ) 🥺 ብዙን ግዜ ዩኒቨርስቲዎች ከከተማ ዉጭ በተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ራቅ ብለው ነው የሚገነቡት። ከከተማ ውጭ ስለሆኑ fresh air የተትረፈረፈበት ፡ ራስን ለማዝናናት ና ለመመሰጥ እንድሁም ለማንበብ ምቹ የሆኑ ጫካዎች ና የተፈጥሮ መስህቦች አሉ።ስለዚህ ተማሪዎች ለመዝናናት ፡ ለማንበብ እንድሁም walk ለማድረግ ወደ ጫካዎች ና ሰው ወደማይበዛበት ቦታዎች ሊሄዱ ይችላሉ። በዚህ ምክንያት ፡

📌 ሴቶች የመደፈር አደጋ ያጋጥማቸዋል።

📌 ወንዶች ደግሞ የ መሰረቅ አደጋ ያጋጥማቸዋል ምክንያቱም ሌቦች( የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወይም የአካባቢው ሰው ሊሆን ይችላል) ከ ግቢ ተማሪዎች ስልክ ፡ ብር ና ላፕቶፕ በማስፈራራት መውሰድ ለምደዋል። ስለዚህ ፡

ከላይ የጠቀስናቸው ቦታዎች ላይ ስትሔዱ ተሰባስባችሁ መሔድ ወይም ደግሞ አለመሔድ🙅‍♂🤷‍♀

2ኛ) ይኸ ደግሞ በሴቶች ላይ የሚስተዋል ሲሆን በፈቃደኝነት ስህተት በመስራት የማይመለስ ፀፀት ዉስጥ የምትገቡበት ነው።
ገና ወደ ግቢ ስትገቡ ፡ ለግቢው አዲስ ናችሁ ፡ ለአካባቢው ና ለማህበረሱ አድስ ናችሁ ፡ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ና ግቢ ውስጥ ስለሚሰሩ ነገሮች አድስ ናቸው። ስለዚህ ነባር(senior) ተማሪዎች ይኸን ደካማ ጎናችሁን( አዲስነታችሁን) ተጠቅመው የህይወት መስመራችሁን ያስቷችሗል☹️

ምን መሰላችሁ ሴቶችዬ 🤔

ገና ዩኒቨርስቲ ስትገቡ ነባር ወንዶች ተማሪዎች አፋቸውን ከፍተዉ😂 እጃቸውን ዘርግተው ይቀበሏችሗል። ምክንያቱም የመጀመሪያ አመት ሴት ተማሪዎች ተማሪዎች ወደ ግቢ ስትገቡ ነባር(senior) ወንድ ተማሪዎች ሴት ይፈልጋሉ።

ስለዚህ ምን ያደርጋሉ መሰላችሁ

😎 መጀመሪያ ልክ ግቢ ስትገቢ ያይሻል። ሻንጣሽ ትልቅ ስለሆነ ይመጣና ላግዚሽ ይላል....ከዛን ይሸከምና እስከ ተመደብሽበት ዶርም #Dorm(setoch_gibi) ድረስ ያወራሻል...ከዛን ግቢውን እንዳላምድሽ ስ.ቁ ስጪኝ ይልሻል። አንቺም ለሁሉም ነገር አድስ ስለሆንሽ ስ,ቁ ትሰጭዋለሽ.....ነገሩ አለቀ🥺

😴ከዛ ምዝገባ ላይ ተሯሩጦ ያስመዘገብሻል....እሱም በዚሁ.... ይቀጥላል።

🤗ከዛ ግቢውን ያስጎበሽኛል ፡ ከተማውን ያሳይሻል ፡ ላውንች( Lounge) ይጋብዝሻል።

😴.....ከዛ ቡሃላ ምን ይፈጠራል መሰለሽ.......አንድ ቀን #Over እንዉጣ ይልሻል ፡ ከዛም🥃🍷🥂🍻 ትጠጣላችሁ። ከዛም በመጠጥ ሀይል አብረሺዉ ታድሪያለሽ። ካደርሽ ቡሃላ ምክንያት በመፍጠር ካንቺ ይርቃል ሌላ ይጠብሳል። በቃ ይሄው ነዉ🤢🤨☹️

☹️ ማርገዝ የምባል ነገር አለ ፍቅር ያሳየሽ መስሎ አታሎ...... ህይወትሽን ያጨልማል።

ከ ገጠር የሚመጡ ሴቶች በጣም ደስ ይላሉ ለምን ብትሉኝ አላማቸው አንድ ብቻ ነዉ። ፍቅረኛ አያቁ በትዳር ያምናሉ።
የከተማ ልጆች ደግሞ ስታስጠሉ😂😂 ሁሉንም አይደለም።

🥺 ስለዚህ ሴቶችዬ ጠንካራ ፡ ፅኑ ፡ አላማችሁን የምታስቀድሙ መሆን አለባችሁ💃💃

3ኛ) Over🕺💃🕺💃🕺

የዩኒቨርሲቲ ተማሪ over ካልወጣ oxygen እንዳጠረው የሚታሰብበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

እንደ ሰደድ እሳት የ ግቢ ተማሪዎችን ህይወት እያበላሸ ያለው over ነው። over ከጥቅሙ ጉዳቶች ያመዝናሉ ምክንያቱም ፡

📌#over በወንዶች ተማሪዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ።

የግቢ ተማሪዎች over ወጥተው ይጠጣሉ ። ከዛም ሞቅ ይላቸዋል ፡ ከዛም በ ደረቅ ሌሊት ከ አካባቢው ወጣቶች ጋ ይጣላሉ ፡ ከዛም በጩቤ ይወጋሉ አልያም በጠርሙስ ይመታሉ ። ከዛም በሌሊት 6 ወይም 7 ሰአት ወደ ሆስፒታል😏። ከ አካል ጉዳት እስከ ህይወት መጥፋት የሚያስከትል ችግር በ #over ምክንያት። እንደታደል ሁኖ ካልተጣላችሁ ፡ በ ደረቅ ሌሊት 8 ሰአት ምናምን ወደ ግቢ ዘበኛ ለምናችሁ ትገባላችሁ። ከመጥን በላይ ቀላቅላችሁ ስለምትጠጡ በየ ሽንት ቤቱ ሻታ🤮🤮🤮

👷‍♂ ወንዶችየ ተጠንቀቁ ነፃነት አገኘን ብላችሁ ነፃነታችሁን እንዳታጡ🤨

📌 #over በሴቶች ተማሪዎች ላይ ያለው ተፅዕኖ ።

በተለይ የ ከተማ ሴቶች shameless ናቸው☹️። ሲጠጡ ራሱ😴😴

ሴቶች #over ይወጣሉ ፡በ ወንዶች ጋባዥነት ይጠጣሉ🥂🍻🍷 ፡፡ ከዛ ይሰክራሉ ። ከዛ ደግሞ አልጋ ይዘው ለማደር ብር ላይኖርቸው ይችላል። ስለዚህ ጎዳና ላይ ማደር ስለማትፈልጊ ፡ ከአንዱ ጋር ታድሪያሽ🙁። ከዛ ያልተፈለገ ዕርግዝና ሊከሰት ይችላል። ከዛ በሗላ የሚመጣውን ጣጣ አስቡት😱😱


ሴት ልጅ ሰክራ በየ አስፓልቱ ስትወድቅ ምን ይባላል 🙈🙈 ይሄን የሚያደርጉት.... አወቅን ባይ የከተማ ልጆች ናቸው።

👷‍♀ሴቶችዬ ተጠንቀቁ። ነፃነት አገኘን ብላችሁ ነፃነታችሁን እንዳታጡ።

😈 ክፍል ሁለት ይቀጥላል😈


🗣🗣🗣 ማሳሰቢያ

👆👆 ከላይ የዘረዘርናቸው የግቢ ተግዳሮችን ለመፃፍ እና ለ እናንተ ለማጋራት ያሰብንበት ዋና ምክንያት ግቢ እንደዚህ አይነት ነገር ስለሚኖር ካሁን አውቃችሁት ፡ እንድትጠነቀቁ ነው እንጅ ስለ ግቢ መጥፎ ነገር መናገር ፈልገን ወይም እንድትሳቀቁ ፈልገን አይደለም።

🕺 ራሳችሁን በአግባቡ መምራት ከቻላችሁ ግን ግቢ ላይ ምርጥዬ ህይወት ይኖራችሗል።

ለ አስተያየት እና ጥያቄ👇👇

On comment

Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
👍1
🗣 ምክር ለፍሬሽ ሴት ተማሪዋች

❗️ ጉዋደኛ ምረጡ.... አብረን እንጨፍር, አትጨናነቂ ምናምን የሚል ሁላ የወደደሽ or ያፈቀረሽ አይደለም

❤️ ለወንድ ልጅ ያለሽ ቀረቤታ በልኩ ይሁን! ወንዶች ብዙ ጊዜ ፍሬሽ ተማሪዎች ላይ practice ማድረግ ይወዳሉ ቢወድሽም ባይወድሽም የሆነ ያህል step ይሄዱና ወይ ላሽ ይልሻል😏😏😏 የዛኔ አንቺ በእልህ😭😢 ብዙ ነገር ውስጥ ልገቢ ትችያለሽ ስለዚ ጠንቀቅ በይ🤔🤔🤔🤔

❤️ even ላይብረሪ ውስጥ እንኩዋን በሰፊው ሴቶች ሲሸወዱ ይስተዋላል
ወንዶች አንድ ሴቶችን የማጥመጃ ስፍራ
(ላይብረሪ) በመባል ይታወቃል😳😳😳😜😜😜😜😜😜
ወረቀት ከዚም ከዛም ሚወረውረው.... መቼም በዛ ቅፅበት ወዶኝ ነው አትዪኝም😝😜


❤️grade በምንም አይነት ምክንያት እዲበላሽብሽ ክፍተት አትፍጠሪ: mostly ሴቶች ላይ ያ ችግር በስፋት ይታያል በዛ time የወንድ አስተማሪ መጫወቻ ትሆኛለሽ....

❤️ Don't forget y'r target ኢሄ ለ ወንዶችም ድረስ ነው🙏🙏🙏

❤️እኔ ነኝ ያልኩዋቹ 1ኛ አመትን ወጥራቹ ስሩ፣ ዞሮ ከተማ ማየቱን ትታቹ...
የከተማውን ጉብኝት ለ ቱሪስቶች ትታቹ ማለት ነው።

❤️ለሙድ ብላቹ የትኛውም አይነት ሱስ ውስጥ አትግቡ ለመጣቹበት አላማ ብቻ ኑሩ please ቁም ነገሩ ጋወን መልበስ ብቻ እንዳይሆን...
ግቢው በ2:00 ስላስመረቀ ብቻ በዛ ግሬድ ተመርቆ መውጣት ትርፉ ድካም ብቻ ነው...

❤️በጣም ስለምወዳቹ ነው ከተጨቃጨኩ ቻሉት ለናንተው ነው

🎯 Forwarded from wa
🎯 Presented by Gebre

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
👍1
በዚህ አመት ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ባላችሁበት ሰላማችሁ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ይሁን🙌

ወደግቢመግባትለው ዝግጅት እና ሽርጉድ እንዴት ነው🕺🕺🕺🕺💃💃💃

የ በሶ ፡ ዳቦ ቆሎ ፡ ኩኪስ ፡ የለውዝ ቅቤ እና ሌሎችም የማቆያ ምግቦች ዝግጅት ተጧጡፏል አሉ።😋😋😋🙈🙈🙈

📚 የመጀመሪያውን ሴሚስተር አሪፍ ውጤት ለመስራትስ ምን ያህል ዝግጅት አድርጋችሗል

😋 4 ነጥብ ማምጣት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ 1000% እርግጠኛ ሁኜ የምነግራችሁ በብልጠት ካነበባችሁ 4 ነጥብ የማታመጡበት ምንም ምክንያት የለም።

📚 ግቢ ላይ ፈተና በተጋነነ መልኩ አያከብዱባችሁም። ስለዚህ በብልጠት ፅንሰ ሀሳቡን እየተረዳችሁት ካነበባችሁ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ። ውጤታችሁን ዝቅ የሚያደርጉባችሁ በ assignment ሊሆን ይችላል።

📚 ስለዚህ assignment ስትሰሩ አሪፍ ፅሁፍ ያለው ተማሪ ነው መፃፍ ያለበት። cover page ጁን አሪፍ አድርጋችሁ አሳምሩት ። በቃ የግቢ መምህሮች አሳይመንቱ አሸብርቆ ደምቆ ሲያዩት ማርክ ያሸክሟችሗል።

📚 ተወዳጆች ሆይ ስለዚህ ዝቅተኛ 3.5 እንዲሁም ከፍተኛ 4 ከእናንተ እጠብቃለሁ።

📚 እየውላችሁ ስሙኝማ ፡ ኸሯ አንተው ምን ሁነሀል ፍላጎትህን መኖር ትፈልጋለህ ፡ ኸረግ አንቺው ክህሎትሽን ማበልፀግ ትፈልጊያለሽ የልጅነታችሁን ህልም መማር ትፈልጋላችሁ 12 አመት የተማርከው የምትፈልገውን ዲፓርትመንት ለመማር ነው አይደል የወገንሽን ስቃይ ለማስታገስ ከ ለጋ እድሜሽ ጀምሮ ዶክተር መሆን ነው ኣ የምትፈልጊውበፍትህ እጦት የጎበጠውን ህዝብ ቀና ለማድረግ ካለሽ ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ዳኛ መሆን ነው ኣ የምትፈልጊው ሀገርህን ለማተራመስ( ማለቴ ለመምራት😤) ፓለቲካል ሳይንስ ነው ኣ ማጥናት የምትፈልገው ሀገርህ በቴክሎጂው ዘርፍ ከፍተኛ እምርታ እንዲታስመዘግብ ኢንጂነሪንግ ነው ኣ መማር የምትፈልገው ኤኮናሚስት ማናጀር ሳይካትሪስትወዘተ መሆን ትፈልጋላችሁ

📚 ስለዚህ የነዚህ ህልማችሁ እና ፍላጎታችሁ መንገድ ጠራጊ የመጀመሪያው ሴሚስተር ነው። ዳይ ወደ ስራ‼️

በ ስነ - ልቦና ስ ዝግጁ ናችሁ

አዎ በስነ ልቦና ዝግጁ መሆን አለባችሁ።🥺🥺 ምክንያቱም

1ኛ) ከቤተሰብ ቁጥጥር እና ተፅዕኖ ውጭ ናችሁ። ራሳችሁን የምትመሩት ና የምታስተዳድሩት ራሳችሁ ብቻ ናችሁ። ስለዚህ ይኸን ነፃነት እንዴት በአግባቡ እንጠቀምበት🤔? ቅድሚያ ትኩረት መስጠት ያለባችሁ ለ ትምህርታችሁ ና ለአላማችሁ ነው።

2ኛ) የጓደኛ ተፅዕኖ( peer influence) ጓደኛን ለመምሰል ብሎ ፡ ለመቀላቀል ተብሎ ፡ ወደ አልባሌ ሱስ መግባት


ከቤተሰብ ቁጥጥር ውጭ ነን ፡ ነፃነት አገኘን ብላችሁ

📌 የማታነቡ ከሆነ
📌 ትምህርታችሁን በአግባቡ የማትከታተሉ ከሆነ
📌Over( ጭፈራ ቤት) መውጣት የምታበዙ ከሆነ
📌 ቺክ የምታሳድዱ ከሆነ ወይም ወንድ የምታሳድጂ ከሆንሽ 🙈
📌 አልባሌ ሱስ ውስጥ የምትዘፈቁ ከሆነ
📌 እና ሌሎችም መጥፎ ወይም ትምህርታችሁን የሚያስተጓጉሉ ነገሮች የምታደርጉ ከሆነ

ጊዜያችሁን አባክናችሁ☹️ ፡ ቤተሰብን ላልተገባ ወጪ ና ኪሳራ ዳርጋችሁ😣 ፡ በመጀመሪያው ሴሚስተር ሻንጣችሁን ጠቅልላችሁ ወደ መጣችሁበት ትመለሳላችሁ🙅‍♂🤷‍♀

ግቢ ላይ እየቀለድኩ እያሾፍኩ እማራለሁ ማለት ዘበት ነው ምክንያቱም ኩረጃ በፍፁም የማይታሰብ ነው። ስለዚህ ግቢ ገብታችሁ

📌 ለማንበብ
📌 ጊዜያችሁን በአግባቡ ለመጠቀም
📌 ራሳችሁን በአግባቡ ለመምራት
📌 አላማችሁን ለማሳካት
📌 የሚደርስባችሁን ጫና ለመቋቋም

ራሳችሁን በ ስነ ልቦና በደንብ ማዘጋጀት ይጠበቅባችሗል።

ይኸን ስንል ግቢ ገብታችሁ አትዝናኑ ማለት አይደለም። ኸረ ፈታ በሉ please enjoy ። ግን ትምህርታችሁን በማይጋፋ መልኩ ፡ እናንተን ለመጥፎ ሱስ በማይዳርግ መልኩ። ኸረ ፈታ በሉ ብዙ መዝናኛ ሞልቷል።

ሌላኛው አንገብጋቢ ጉዳይ ደግም የምትፈልጉትን department ማግኘት ነው።

😌 Department ስትመርጡ

📌 የእናንተን ፍላጉት ፡ የእናንተን skill (ክህሎት) ፡ ዝንባሌ ፡ አቅም መሰረት ያደረገ መሆን አለበት።

📌 በቤተሰብ ተፅዕኖ ፡ በጓደኛ ተፅዕኖ ወዘተ መሆን የለበትም።

እዚጋ ብዙዎች ጋ የሚስተዋለው ነገር ብዙ ብር ክፍያ አገኛለሁ ብሎ በማሰብ ፡ ቶሎ ስራ አገኛለሁ ብሎ በማሰብ አንዳንድ ተማሪዎች ያለ ዝንባሌያቸው ዲፓርትመንት ሲመርጡ ይስተዋላሉ። ስለዚህ

📌 ፍላጎታችሁን ፡ የትምህርት ክህሎታችሁን ፡ ጫናዎችን የመቋቋም ዝግጁነታችሁን ና አቅማችሁን መሰረት አድርጋችሁ ብትሞሉ አሪፍ ነው።

የምፈልገውን Department እንዴት ማግኘት እችላለሁ?

📚 ጥሩ ውጤት ከሰራችሁ የምትፈልጉት ዲፓርትመንት መግባት ትችላላችሁ።

ጥሩ ውጤት እንዴት እንስራ?

1ኛ) ግቢ ገብታችሁ የምትወስዱት የመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤት እጅግ በጣም በጣም በጣም ጠቃሚ ነው። 50% ከመጀመሪያው ሴሚስተር ውጤታችሁ ነው የሚወሰደው ዲፓርትመንት ስትመርጡ። የመጀመሪያውን ሴሚስተር ቅጥቅጥ አርጋችሁ ማንበብ ነው።

እንደመታደል ሁኖ የመጀመሪያ ሴሚስተር የምትወስዷቸው ኮርሶች የተወሰኑት 11 እና 12 የተማራችሗቸው ናቸው። ስለዚህ ያላችሁን አጋዥ መፅሀፍ ፡ PDFs እና የተለያዩ ማቴሪያሎችን እንዳትጥሏቸው፡ ወደ ግቢ ይዛችሁት ሒዱ።

2ኛ) COC exam ነው። የመጀመሪያውን ሴሚስተር ከጨረሳችሁ በሗላ COC exam ትፈተናላችሁ። 30% ከ coc exam ውጤታችሁ ነው የሚወሰደው ዲፓርትመንት ስትመርጡ።

እንደመታደል ሁኖ coc exam የምትፈተኑት 11 ና 12 ኛ የተማራችሗቸውን ነው። ስለዚህ 11 ና 12 የተማራችሁባቸውን ማቴሪያሎች ወደ ግቢ ይዛችሁ መሔድ ነው።

3ኛ) Entrance exam ነው። 20% ከ Entrance ውጤታችሁ ነው የሚወሰደው ዲፓርትመንት ስትመርጡ።

ስለዚህ የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጤት እና COC ን በደምብ መስራት አለባችሁ አዲስ የተቀየረ ነገር ከሌለ።

🙌 ተውዳጆች ሆይ መልካም የትምህርት ዘመን።🎯 Forwarded from wa
🎯 Presented by Gebre

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
Staffing Class (1).pdf
243.6 KB
Read
It's For management students
👍1
G-Tutorialclass pinned «በዚህ አመት ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ባላችሁበት ሰላማችሁ እንደ ምድር አሸዋ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ይሁን🙌። ወደግቢመግባትለው ዝግጅት እና ሽርጉድ እንዴት ነው🕺🕺🕺🕺💃💃💃። የ በሶ ፡ ዳቦ ቆሎ ፡ ኩኪስ ፡ የለውዝ ቅቤ እና ሌሎችም የማቆያ ምግቦች ዝግጅት ተጧጡፏል አሉ።😋😋😋🙈🙈🙈 📚 የመጀመሪያውን ሴሚስተር አሪፍ ውጤት ለመስራትስ ምን ያህል ዝግጅት አድርጋችሗል 😋»
25 ሰወችን በፙጋዝ ብቻ 1000 ብሮን ይቀበሉ💵💵👇👇⤵️

👇👇👇💵👇👇👇

እንኳን ወደ ኢትዮ ቴሌኮም / የቴሌብር አገልግሎት በሰላም መጡ‼️

💬 ይህ በ ኢትዮ ቴሌኮም አዘጋጅነት የቴሌብር አገልግሎት አጠቃቀም ባህል ለማበረታታት የቀረበ የ 1000 ብር የገንዘብ ስጦታ ና የ2GB የሞባይል ጥቅል ስጦታ ነው‼️

የሽልማቱ አሸናፊ ለመሆን ይህን ሊንክ በመጫን ቡቱን በመቀላቀል መመሪያውን ይከተሉ 👇👇
https://t.me/EthTelebirr_bot?start=r05511284830

ተሸላሚዎችን ሊንኩን በመጫን በቴሌግራም ገፃችን ይመልከቱ👇👇
https://t.me/joinchat/1QQbOvBFC504OGFk

ይህ የእርስዎ መጋበዣ መልዕክት ነው #SHARE ወይም #FORWARD በማድረግ ውድድሩን ይቀላቀሉ🔻

መልካም እድል 🚀
It's real,so
share and get your 💰💵💵
#ዒድ_ሙባረክ

እንኳን ለ 1443ኛው ለዒድ አል-ፊጥር በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!

ተቀበለላሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኻል አዕማል!

🌺ʝσιи🌺
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
📚 የታላቅ መልዕክት ለፍሬዎች....!


ግቢ በየትኛውም ሰዓት ብትደርሱ ስለሚያስተናግዷቹህ በጭራሽ ቤርጎ እንዳትከራዩ ፤ በተለይ ከሩቅ ቦታ የምትመጡ ተማሪዎች ግቢው ስለሚረ'ዳቹህ ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እንዳትዳረጉ ፤ ስርቆትም ሊኖር ስለሚችል ለብቻቹህ ከሆናቹህ ቤርጎ ባትከራዩ ፒስ ነው(በተለይ ሴቶች)

ከብዙ ወከባዎች ለመትረፍ ከፈለጋቹህ አንድ ቀን ቀደም ብላቹህ ግቢ ግቡ ማለት ግቢው በ29 ከጠራ እናንተ በ28 ግቡ ያስገቧቹሃል ፤ ቀደም ብሎ የሚመጣን ተማሪ አናስተናግድም የሚሉት ሳክስ ነው ፤ቀደም ብላቹህ ከመሄዳቹህ በፊት ግን ነባር ተማሪዎችን ለማንኛውም አናግሩ ።


ሻንጣ እንዳይቀያየርባቹህ የናንተን ሻንጣ የምትለዩበት መለያ ምልክት ይኑራቹህ ፤ ብዙ ሻንጣ ሊኖር ስለሚችል በስህተት እንዳይቀያየር (ለክፉም ለደጉ ግን ስልክ ቁጥር የሆነ ቦታ ላይ አስፍሩበት በወረቀትም ቢሆን....!)

ግቢ በር ላይ ጥብቅ ፍተሻ ስለሚኖር ባለፈው የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ይዛቹህ እንዳትመጡ ፤በስህተት ካመጣቹህ በር ላይ ይቀሟቹሃል ።
የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ቅርብ ቦታ አስቀምጡ ማለት ሻንጣ ውስጥ አታርጉት ፤ በር ላይ ቅድሚያ ስለምትጠየቁ ሁሉንም ዶክመንቶች በእጃቹህ ለመያዝ ሞክሩ ።

ወንዶች ፀጉራችሁን ከልክ በላይ አታሳድጉ ቀለምም አትቀቡ ፤ የመጀመሪያ ቀናቶች ላይ ፀጉር ምናምን ሊባል ስለሚችል በተቻላቹህ ያህል እይታ ውስጥ የሚያስገባ የፀጉር style አይኑራቹህ(ምቺ ያስመታቹሃል....!)

ሴቶች አለባበስ ላይ ወጥ አትርገጡ ፤
አንዳንዶቻቹህ ለትምሮ የምትሄዱ እስከማትመስሉ ድረስ ትራቆታላቹህ ፥ የምር አይነፋም ይብራብሽ እርድናም አይደለም ( ለነገሩ ግቢ በር ላይም አይፈቱሽም ጥበቃዎች...!)

ግቢ ስትገቡ ፀባያቹህ የቱንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆን ትዕግስተኛ መሆን አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው። ከማንም ጋር ብትጣሉ ካለምንም ማስተዛዘኛ የመባረር እድላቹህ ይሰፋል ።

የጥላቻና የዘረኝነት ንግግሮችንም ይሁን አመለካከቶችን በፈጠራቹህ ጌታ ይሁንባቹህ እንዳትጠቀሙ ፤ የማንንም ስብዕና የሚነካ ንግግር በስህተት እንኳ እንዳትናገሩ ።

ግቢ ውስጥ ማንንም እንዳትንቁ ፤ እኔንም ጨምሮ ፤ ከየትኛውም ከተማ ልትመጡ ትችላላቹህ ግቢ ውስጥ እስካላቹህ ድረስ ግን እኩል ናቹህ ማለትም አትበላለጡም።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
📌የጥሪ ማስታወቂያ

በ2014 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ #በኦንላይን ከግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ጊዜ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ስለምዝገባ ሂደቱ ዝርዝር መረጃዎች በተቋሙ ድረ-ገጽ https://hu.edu.et እና በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ገጾች የሚገለጹ መሆኑ ተገልጿል፡፡


ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲሄዱ ሊይዟቸው የሚገቡ፦

• የ12ኛ እና የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት
ዋናውና ኮፒው
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ዋናውና ኮፒው
• ጉርድ ፎቶግራፍ (4)
• የሌሊት አልባሳት
• የስፖርት ትጥቅ

ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ግንቦት 10 እና 11/2014 ዓ.ም እንድታመለክቱ ተብሏል፡፡

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
   
📌 join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
የጥሪ ማስታወቂያ‼️
#OdabultumUniversity

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ሲሆን ምዝገባ የሚካሄደው ግንቦት 10 እና 11 ይሆናል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ጊዜ፡-

🗝የ8ኛ ክፍል ሰርትፊኬት ኦርጅናልና ኮፒ
🗝የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ኦርጅናልና ኮፒ

🗝ከ9-12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪብት ኦርጅናልና ኮፒ

🗝አራት ፓስፖርት ሳይዝ ጉርድ ፎቶ ግራፍ እንዲሁም

🗝 አንሶላ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የትራስ ጨርቅ እና ብርድ ልብስ በመያዝ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ ሐረርጌ ዞን ጭሮ ከተማ በሚገኘዉ ዋናዉ ካምፓስ በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ www.obu.edu.et ወይም https://t.me/OBURegistrar ይጎብኙ

የኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

 📌 join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
+ መጫር !


📚 አንድ ተማሪ ግቢ ውስጥ ሊጫር የሚችለው በዲሲፕሊን ወይም በትምሮ ነው።( የግል ጉዳዮችን አይመለከትም like ህመም)

በዲሲፕሊን የሚጫረው የግቢውን ህግና ደንብ ጥሶ ሲገኙ ነው ቀጥታ የሚያስጭሩ የህግ ጥሰቶች አሉ ፥ በተለያየ የቅጣት እርከን እስከ መጫር የሚያደርሱም ጥፋቶች ይኖራሉ።

በሁሉም ግቢዎች ግን
እርስ በርስ መጣላት
ስለታማ መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት
አደንዛዥ እጽ መጠቀም
ግቢ ውስጥ እንትን ማድረግ
የዘረኝነት ቅስቀሳ ላይ በየትኛውም መልኩ መሳተፍ
መምህራን ጋር መጣላት
የግቢ ንብረት መስረቅ
ፆታዊ ትንኮሳ በሴት የቢሮ ሰራተኞች ማድረስ( ለከፋንም ጨምሮ ) ወዘተ በቀጥታ ሊያስጭሩ የሚችሉ ነገሮች ናቸው።

📚 አብዛኛው ተማሪ በትምሮ ምክንያት ይጫራል የሚገርመው ግን ትምህርት በጣም ከብዶ ሳይሆን በራሳችን ቸልተኝነት መሆኑ ነው።

በመጀመሪያው ሴሚስተር 1.5 ማምጣት አቅጦት የሚጫር ተማሪ ምን ይባላል

በሁለተኛው ሴሚስተር 1.75 ማምጣት ይኖርብናል ላለ መጫር

Please ግን ስለ ጭረት እያሰባቹህ አትማሩ coz የስካትን በር ይዘጋባቹሃልና

ከዛ በኋላ ግን SGPA ( semister GPA) የግድ 2 እና ከዛ በላይ ማምጣት አለብን በwarning ምናምን የሚመዘገቡ ተማሪዎች አሉ ግን please እዛ ደረጃ ድረስ ዝቅ ባንል ጥሩ ነው በቃ በእቅድ እንማር ከዛ እቅዳችንን ማሳካት ላይ እንፍጨርጨር ።

📚 ስታቅዱ ደግሞ በልካቹህ ይሁን በጣም ዝቅ አታድርጉትም የሆነ ኮርስ ለምሳሌ B አመጣለሁ ብለህ ካሰብክ B ለማምጣት ታገል ነገር ግን ያንኑ ኮርስ A ለማምጣት ብታቅድና ብትቸክል A ማምጣት ቢያቅትህ እንኳ B ታመጣለህ ፤ በዛው ልክ ደግሞ በD እፋታዋለሁ ብለህ የምታቅድ ከሆነ እመነኝ F ይፈላልሃል coz D ለማምጣት ማንበብ አያስፈልግም ብለህ ፈታ ማለት ስለምታበዛ ❗️

📚 በነገራችን ላይ አምና የሆነ ሴሚስተር ላይ አንድ ጮማ ራስ አስተማሪ ጋር ተጣልተን D ለማምጣት ብዙ ቸክለናል ፡ F ያመጣው peoplm አሸን ነበር እናም grade አትናቁ ልላቹህ ፈልጌ ነው።አንዳንዴ F ለራሱ በጣም ውድ ትሆናለች ። የምሬን ነው F አርግልን ብለው አስተማሪውን ሲለምኑ አይቻለሁ ።



እንዴ ከF በላይ ደግሞ ምን አለ

Incomplete መባልም አለ ።



📚 እናም ወዳጆቼ ግቢ ውስጥ እስካላቹህ ድረስ በሁሉም ኮርስ በሁሉም አስተማሪ ላትረኩ ወይም እቅዳቹህ ላይሳካ ይችላል ቢሆንም ግን ሰፋ አድርጋቹህ በማቀድና በመቸከል ከጭረት ኬላ ነፃ መሆን ትችላላቹህ እረ እንደውም ምርጥ ውጤት ሊኖራቹህ ይችላል።

★እጫራለሁ ካልክ ፥ ትጫራለህ ★
ዶ/ር አመዲን ሙሃመድ የቀድሞው የግቢያችን ዲን ፍሬሽ እያለን ኦረንቴሽን ላይ የተናገሩት ።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass