G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
በ video በ ቅርቡ

📚 Communicative English Skill I.

📚 Unit One - Study Skills.

📚 Grammar Focus - Present Perfect Tense.

📚 Targeted Group - First year University Students.

☑️Present Perfect Tense

🔰Affirmative form
I/we/they/you + have + V3.
He/She/It + has + V3

🎴Negative form
I/we/they/you+haven't+V3.
He/She/It + hasn't + V3.

🎁Question form
Have + I/we/they/you +V3?
Has + he/she/it + V3?

🍄Usage

🌹1⃣) to describe an event that happened in the past and are still true now because you can see the result.

📚 ከአሁን በፊት የተከናወነ አንድ ድርጊት ነበር፡ ታድያ ይኸ ከአሁን በፊት ተከናውኖ የነበረው ድርጊት ውጤቱ አሁን ላይ የሚይታይ ወይም ያለ ከሆነ ፡ ከአሁን በፊት ተከናውኖ የነበረው ድርጊት በ present perfect ይገለፃል።

📚 ማለትም ድርጊቱ ከአሁን በፊት(past) ነው ተከናውኖ ያለቀው ነገርግን የ ድርጊቱ ውጤት አሁን(present) ላይ የሚታይ ከሆነ ይኸን ድርጊት በ present perfect እንገልፀዋለን ማለት ነው።

🎯 Example 1

📚 ትናንት 11:00 አካባቢ ከዛፍ ላይ ወደክ በመውደቅህ ምክንያት ታመህ ወይም ተሰብረህ ዛሬ አልጋ ላይ ተኛህ። ስለዚህ ትናንት ከዛፍ ላይ መውደቅህ ከአሁን በፊት የተከናወነ ድርጊት ነው፡ በመውደቅህ ምክንያት ዛሬ ታመህ አልጋ ላይ መተኛትህ የትናንቱ ድርጊት ውጤት ነው። ዛሬ ታድያ ጓደኞችህ ምን ሁነህ ነው ብለው ቢጠይቁህ፡ ከዛፍ ላይ ወድቄ ነው ብለህ ነው ምትመልስላቸው። so,

🚼I have fallen from a tree.

📚 ታዲያ ብዙዎቻችን ድርጊቱ ማለትም ከዛፍ ላይ መውደቁ ትናንት ተከናውኖ ያለቀ ድርጊት ነው፡ ለምን በ simple past አይገለፅም የሚል ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን። አሪፍ ጥያቄ ነው ነገርግን ማስተዋል ያለብን ነገር በትናንትናው ድርጊት ምክንያት ውጤቱ ማለትም ዛሬ ላይ ታሞ መተኛቱ ነው present perfect እንድንጠቀም ያደረገን። ነገር ግን ትናንት በመውደቁ ምክንያት ዛሬ ላይ ካልታመመ ጤነኛ ከሆነ፡ የትናንቱ ድርጊት አሁን ላይ የሚታይ ውጤት ስለለው በ simple past ይገለፃል። ልዩነቱ፡

🔘I have fallen from a tree.( አሁን ላይ ታምሜአለሁ ወይም ተሰብሬአለሁ ወይም የደረሰብኝ ጉዳት አለ ማለት ነው።)

🔘I fell from a tree.( አሁን ላይ የደረሰብኝ ጉዳት የለም እንደማለት ነው።)

🎯 Example 2

📚 ለምሳሌ ልጁ(the boy) መኪናውን አፅድቶ ጨርሷል። እና አሁን መኪናው ፅድት ብሎ አዲስ መስሏል። ተመልከቱ ልጁ መኪናውን አፅድቶ ጨርሷል ማለትም ከአሁን በፊት የተከናወነ ድርጊት ነው። ነገር ግን ውጤቱ ማለትም መኪናው ፅድት ብሎ አዲስ መምሰሉ አሁን ላይ የሚስተዋል የሚታይ ነው። ስለዚህ

🍄 The boy has cleaned the car. It looks new again.

🌹2⃣) to describe an event that happened a few minutes ago.

📚 ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት የተከናወነን ድርጊት ለመግለፅ። ማለትም ከ 10 ደቂቃ በፊት፡ ከ 15 ደቂቃ በፊት፡ ከ 20 ደቂቃ በፊት፡ ከ 5 ደቂቃ በፊት ወዘተ የተከናወኑ ድርጊቶችን ለመግለፅ present perfectን እንጠቀማለን ።

🎯 Example

📚 የ Arsenal ና chelsea ን ጨዋታ DSTV ቤት ሔደህ አየህ፡ ጨዋታው በ Arsenal አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ጨዋታው አልቆ ከ 20 ደቂቃ በሗላ ጓደኛህ ማን አሸነፈ ብሎ ቢጠይቅህ፡ ድርጊቱ ከትንሽ ደቂቃ(ከ 20 ደቂቃ) በፊት የተከናወነ ስለሆነ በ prsent perfect ትገልፀዋለህ።

🔘Arsenal has won the match.
ነገር ግን ጨዋታው ካለቀ ከ አንድ ቀን ምናምን በሗላ ማን አሸነፈ ብሎ ቢጠይቅህ በ present perfect ሳይሆን በ simple past ነው የምትገልፀው።so,

🔘Arsenal won the match.

🌹3⃣) to describe an event that started in the past and is still happening now.

📚 ካሁን በፊት ሲከናወን የነበረ አሁንም በመከናወን ላይ ያለ ድርጊትን ለመግለፅ present perfect ን እንጠቀማለን።

📚 እዚጋ ታድያ ድርጊቱ ከአሁን በፊት ለምን ያክል ጊዜ ተከናውኖ እንደነበር ለመግለፅ 'For' ን ስንጠቀም ፡ ከአሁን በፊት ሲከናወን የነበረው ድርጊት ከመቼ
ጊዜ ጀምሮ እንደተከናወነ ለመግለፅ ደግሞ 'Since' ን እጠቀማለን።

📚 እንዲሁም ካሁን በፊት(past) ሲከናወን የነበረ አሁንም በመከናወን ላይ ያለ ድርጊት መሆኑን ለማመልከት So far , till now , up to now የመሳሰሉትን መጠቀም እንችላለን። ትርጉማቸውም 'እስካሁን' ማለት ነው።

🎯 Example

📚 Million የ computer science መምህር ነው። computer science ን ከ 2006 ጀምሮ ለ 8 አመት አስተምሯል አሁንም በማስተማር ላይ ይገኛል። ስለዚህ😎

🔘Million has taught computer science for 6 years.(ለ 6 አመት አስተምሯል፡ አሁንም እያስተማረ ነው።)

🔘 Million has taught Computer Science since 2006.( ከ 2006 ዐ.ም ጀምሮ እስካሁን እያስተማረ መሆኑን።)

📚 እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር million ከ 2006 ጀምሮ ለ 8 አመት አስተምሮ አሁን ላይ ግን ሌላ ስራ ይዞ ይኸን ትምህርት የማያስተምር ከሆነ በ present perfect ሳይሆን በ simple past ነው የምንገልፀው።

🔘Million taught Computer Science for 6 years.(ለ 6 አመት አስተምሮ ነበር አሁን ላይ ግን እያስተማረ አይደለም።)

🍄 Million ከ 2006 ጀምሮ እስካሁን computer science እያስተማረ መሆኑን ለመግለፅ ደግሞ👇

Million has taught computer science so far.(million እስካሁን CS እያስተማረ ነው) በ so far ቦታ till now ወይም up to now ን መጠቀም እንችላለን።

@Aconcise
📚 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላላን ።

📚@GTutorialclass
@GTutorialclass ተፃፈ።


📚 ማንበብ + መረጃ 👀

ግቢ የቱንም ያህል ብታነብ ፡ ላይብረሪ ውስጥ ብትውል ብታድር ፡ ሺህ መፅሀፎችን ብታነቢ መረጃ ከሌለሽ ልፋትሽ ከንቱ ነው ፡ በለፋህበት ልክ አትሰራም መረጃ ከሌለህ😥። መረጃው ምን አይነት ይሆን🤔?

📌 ለምሳሌ አንዳንድ ፈጣን ተማሪዎች በነሱ ዲፓርትመንት ውስጥ ያሉ ነባር ተማሪዎችን ( senior ) ይጠይቃሉ።

🤔 ለምሳሌ ነባር ተማሪዎች ያንን ኮርስ በሚወስዱበት ጊዜ ምን ምን መፅሀፍ ይጠቀሙ እንደነበር ፡ መምህራኖች ጥያቄ የሚያወጡበት መፅሀፍ ምን እንደነበር ይጠይቃሉ ፡ ከዛም መፅሀፋን ይቀበላሉ😉። ስለዚህ እናንተ ተፍ ተፍ ማለት ፡ የ ክላሳችሁን መጠየቅ ፡ ምን መፅሀፍ እንደተቀበሉ ምን መፅሀፍ እንዳላቸው ፡ መጠየቅ😁

📌 ሌላኛው ደግሞ መምህሩ ክላስ ውስጥ በሚያስተምርበት ሰአት ፡ ይኸን part በደምብ አንብቡ ፡ ይሄን ያዙ ምናምን እያለ ፈተና የሚወጣበትን part ሊጠቁም ይችላል። ክላስ ካልገባህ ወይ ደግሞ ክላስ ውስጥ የምንታቀላፊ ከሆነ ፡ ተበላሽ😂። ስለዚህ ክላስ የገቡ ተማሪዎችን መምህሩ ምን ምን እንዳለ መጠየቅ😉

📌 ሌላኛው ደግሞ Affirmative action 😳😂። ምን መሰላችሁ ፡ ለምሳሌ mid exam የሚወጣው chapter 1&2 ከሆነ ፡ መምህሩ 2 ቱን chapter አስተምሮ እንደጨረሰ ፡ ፈተናው 3 ወይም 4 ቀን ሲቀረው ለ ሴት ተማሪዎች ብቻ የሚሆን ለፈተናው የሚጠቅም መምህሩ tutorial ይሰጣቸዋል። ፈተና የሚወጣበትን part ያስተምራቸዋል ፡ ከ ፈተናው ጋ ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ይሰራላቸዋል። ኸረ እንደውም አንዳንድ ጊዜ ፈተና ላይ የሚወጣውንም ጥያቄ ይሰራላቸዋል🙈። ስለዚህ የ ክላሳችሁን ሴት ተማሪዎች እንዳትፋቷቸው😁። በ tutorial class መምህሩ ያፃፋቸውን ኖት ፡ ያሰራቸውን ጥያቄ በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ አንብቡ☺️
አሁን ደግሞ

😌 በ ግቢ ቆይታየ ከ መረጃ ጋ በተያያዘ ያጋጠመኝ አንድ ሁለት ገጠመኝ ላጫውታችሁ😅

🦸‍♂ " Mass and Heat transfer " የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና እኔ አንዳንድ ጊዜ ከነሸጠኝ ክላስ አልገባም🤷‍♂። ከዛ ክላስ ባልገባሁበት ሰአት ፡ መምህሩ አስተምሮ ፡ በ Cartesian and cylindrical የሚሰራ proof ነበር። በ Cartesian የሚሰራውን መምህሩ proof አደረገላቸው። በ cylindrical የሚሰራውን ደግሞ እናንተ proof አድርጉ አላቸው ። " አደራ አደራ እንዳትረሱት " አላቸው😒። እኔ በወቅቱ ክላስ ስላልገባሁ መረጃው አልነበረኝም😢። ይኸን የሰሙ ተማሪዎች ላይብረሪ ገብተው proof ፋን ሽምድድ።

ከዛ mid exam ስንፈተን በ cylindrical proof አድርጉ ያላቸውን 8 mark ይዞ መጣ😞
እኔ መረጃው ስላልነበረኝ ከ 8ቱ 0 አመጣሁ🤨። ከዛ ይኸን ኮርስ 77.5 (B+) አመጣሁ ከ 100%። ግን መረጃው ቢኖረኝ ወይም ክላስ ባልቀጣ proof ፋን እሰራው ነበር ።

77.5 + 8 = 85.5( A )

🥺 አያችሁ አይደል በዚች የመረጃ ክፍተት A የማመጣውን ኮርስ B+ አመጣሁ😡


🗣 ከመረጃ ጋር በተያያዘ ሌላ ገጠመኝ

🦸‍♂ "Probability and Statistics" የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና በወቅቱ መምህሩ ፈተና የሚያወጣበት ፡ አሳይመንት የሚያወጣበት መፅሀፍ ነበር። እና እኔ ደግሞ በወቅቱ መረጃው አልነበረኝም መምህሩ ያን መፅሀፍ እንደሚጠቀም። ከዛ መምህሩ የሰጠንን handout ለ ፈተና አንብቤ ገባሁ። ግን መምህሩ ጥያቄውን ከዛ መፅሀፍ ስለነበር ያወጣው 5/10 አገኘሁ😏። ያንን መፅሀፍ ያነበቡ ልጆች ግን ደፈኑት😁። ከዛ ከፈተና በሗላ ስጠይቃቸው "እንትን" የሚባል አሪፍ መፅሀፍ አለ ከዛ ነው ያወጣው አሉኝ ። ከዛ ተቀበልኳቸው🕺💃። ከዛ ለ mid exam ያንን መፅሀፍ ቅጥቅጥ አድርጌ አነበብኩ ፡ ሰራሁት☺️። ከዛ አሳይመንትም እንደዚሁ ከ መፅሀፉ ቁጥር እንኳን ሳይቀር አመጣው ፡ ከዛ እኛም ድፍን☺️። ምን ቀረ🤔? Final exam😴። ለ final exam አሁንም ያንን መፅሀፍ ቅጥቅጥ አድርጌ አነበብኩ ፡ ከዛ 'A' አመጣሁ🕺💃

🥺 አያችሁ አይደል ያንን መፅሀፍ ባልቀበል ወይም ደግሞ መረጃው ባይኖረኝ ፡ handout ቱን ብቻ ነበር የማነበው ፡ A አላመጣም ነበር።

‼️ በ ነገራችን ላይ Chemical Engineering, Electrical and Computer engineering, civil engineering ምናምን የምትገቡ ልጆች " probability and statistics" ኮርስ ትወስዳላችሁ ። የ ግቢ መምህሮች አሁን ያልኳችሁን መፅሀፍ ፈተና ለማውጣት ፡የ አሳይመንት ጥያቄ ለማውጣት ፡ handout ለማዘጋጀት ይጠቀሙበታል። ስለዚህ " probability and statistics" ኮርስ በምትወስዱበት ጊዜ ፡ በውስጥ መስመር አናግሩኝ እሰጣችሗለሁ።

🗣 የመጨረሻ ገጠመኝ ፡ አላብዛባችሁ😊

🦸‍♂ " Applied Electrochemistry" የሚባል ኮርስ ወስደናል። እና መምህሩ አሳይመንት አስቀድሞ ነበር የሰጠን። በቅፅል ስም " Smith " እያልን የምንጠራው ልጅ አለ ፡ መፅሀፍ በመጎርጎር 1ኛ ነው👌። አመናችሁም አላመናችሁም መምህሮች የሚጠቀሙበትን እያንዳንዱን መፅሀፍ ያገኘዋል ። እንደውም ከመምህሮች በላይ መፅሀፍ የሚያውቅ ይመስለኛል😁። በዚሁ አጋጣሚ ለ Smith ያለኝን አድናቆት እና ምስጋና መግለፅ እወዳለሁ🙏። ብቻ ምን አለፋችሁ መምህሩ አሳይመንቱን ያወጣበትን መፅሀፍ አገኘው🙈። ከዛ መፅሀፋን ስናየው መምህሩ note የሚያወጣውም ከዛው መፅሀፍ ነው ፡ መረጃ ይልሀል ይኸ ነው😜። እኛም አሳይመንቱን ድፍን😉። ከዛ ለ mid exam ፈተና ያንን መፅሀፍ አንብበን ገባን። ከክላሱ ዝቅተኛ ውጤት የመጣው 24 ከ 30። መረጃ ይሉሻል ይኸ ነው😉

😊 በዚሁ አጋጣሚ Chemistry ነክ የምትማሩ ልጆች ለምሳሌ Medicine, pharmacy, biomedical engineering, medical laboratory, Chemical engineering, biology, Chemistry.... የምትገቡ ልጆች Applied organic Chemistry, Analytical chemistry, inorganic chemistry, Applied Electrochemistry....ስለምትማሩ እንዲሁም የ natural science ተማሪዎች freshman course ላይ General Chemistry ስለምትማሩ አሁን የነገርኳችሁን መፅሀፍ ተጠቀሙ ። አሪፍ የሆኑ የ concept ኖቶችን ታገኛላችሁ ፡ አሪፍ አሪፍ ጥያቄዎችን ታገኛላችሁ። በቃ Chemistry እንዲገባችሁ ከፈለጋችሁ መፅሀፋን ተጠቀሙበት።

የመፅሀፉ ስም 👇
" University of Meinosota"

የመፅሀፋ መገኛ 👇
Library ( natural library)

🙋‍♂ ሀሳቤን ስጠቀልለው ፡ ግቢ ላይ ማንበብ ብቻውን አይጠቅምም። መረጃ አነፍናፊ መሆን አለባችሁ። ስለ ፈተናው አወጣጥ ፡ ፈተናው ምን part ላይ አንደሚያተኩር ፡ ፈተናው ምን መፅሀፍ ላይ ሊወጣ እንደሚችል ምናምን መረጃዎች ሾልከው ይወጣሉ ። ስለዚህ ከንባብ በተጨማሪ መረጃ ላይም አደራ ትኩረት አድርጉ ።

📌 Join and share 👇👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
📖 How to become A straight A student

📝 The unconventional strategies Real college students use to score high while studying less

Author : Carl New port

በ Concise English Channel
(@Aconcise) ብቻ የሚቀርብ ።

ክፍል አንድ

" Go big or Go home , seriously Work Hard when You work and You will have plenty of time to play Hard "

📚 ወደ ተመደብኩበት ግቢ በገባሁበት የመጀመርያ አመት እንዴት ለፈተና ማንበብ ፣ አሳይመንቶችን መስራትና ግዜን በአግባቡ መጠቀም እንዳለብኝ ምንም ፍንጩ አልነበረኝም ። ልክ እንደ አብዛኛው ተማሪ ማጥናት ማለት የመምህራንን Note እስከቻልነው ድረስ ደግሞ ደጋግሞ ማንበብ ብቻ የሚል እምነት ነበረኝ ነገር ግን College እንደ High school አልነበረም ።

📚 ግዜ በገፋ ቁጥር የተሻለ መንገድ እንዳለና እሱን ለመፈለግ ውሳኔ ላይ መድረስ እንዳለብኝ ተሰማኝ ። በዙርያዬ ያሉት ሌሎች ተማሪዎች በተመሳሳይ ሁኔታው ውስጥ ቢሆኑም አንዳቸውም ለምን ብለው ጠይቀው እንደማያቁ እና ሁኔታውን ለመለወጥ ፍላጎት እንደሌላቸው ተረዳው ።

📚 ለረጅም ሰአታት አድካሚና አታካች የአጠናን መንገድን ተከትሎ በማንበብ መካከለኛ ውጤትን ማምጣት ልፋቴን እንደማይመጥን ስረዳ እንቅልፌንና በግቢ ውስጥ ያለኝን ማህበራዊ ህይወቴን በማይጎዳ መልኩ በውጤት ልዩ ሆኜ መውጣት እንዳለብኝ ከውሳኔ ላይ ደረስከኝ ። ለአብዛኞቻችን ረጅም ሰዓታትን እንቅልፋችንን እያጣን ካላጠናን ውጤታማ መሆን አንችልም የሚለውን የተሳሳተ እምነት በመስበር ኮከብ ሆኜ ለመውጣት ወሰንኩኝ።

📚 ለአብዛኛው ተማሪ የማይሆን መስሎ አይቻልም ብሎ የሚያስበውን በተፈጥሮዬ ቀና ነበርኩኝና በቀን ለአጭር ሰዓታት በማንበብ እንቅልፌንና ማህበራዊ ህይወቴን ሳልጎዳ ውጤታማ የምሆንበትን መንገድ ለመከተል በመወሰን የነበረኝን የአጠናን መንገድ እና የተሳሳተ እምነት በመጣል ውጤታማውን መንገድ ፍለጋ ሙከራ ጀመርኩኝ ።

📝 ይቀጥላል

🎯 Join And Share .

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 1.pdf
632.5 KB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter one short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 2.pdf
999.2 KB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter two short note

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 3.pdf
1.8 MB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter three short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
👍1
@Aconcise Logic short note 4.pdf
1 MB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter four short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
@Aconcise Logic short note 5.pdf
1.3 MB
📚 Logic and Critical thinking.

📚 Chapter five short note.

📚 እጥር ምጥን ያሉ በብስለት የተዘጋጀ ነው። ፅንሰ ሀሳቡን ለመረዳት አመቺ ነው። ንባብ ለጀመራችሁ ፍሬሽማኖች።

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
#Advert

ስለ 📚 @GTutorialclass ሰምታችሁ ይሆን🤔</span>

🥇ዛሬ ላይ በጣም ብዙ የTelegram ቻናሎች ማስታወቂያቸው ስለሚዘዋወር ፣ አይታችሁት ከሆነ ዝም ያላችሁት እንዳትሸወዱ።

🏆እኛ የመጣነው በምክኒያት ነው።🏆

🗂በየትኛውም የትምህርት ደረጃ ላይ ብትሆኑ ፡ ምንም ሊያስጨንቃችሁ አይገባም
🤌ምክንያቱም፡
እኛ
@GTutorialclass አለንላችሁ።

🪴ከ9ኛ ክፍል እስከ University ድረስ በሁሉም የትምህርት አይነቶች Handout በጠየቃችሁን የትምህርት ደረጃዎች ግልጽ እና ውብ አድርገን እናዘጋጃለን።

📚ምናልባት ሰፋ ያለ ይዘት ያለው መጽሃፍ አንብባችሁ ይሆናል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ሃሳባችሁን ጠቅለል አድርጎ የሚይዝ MindMap ያስፈልጋችሃል።
ለእሱ ደግሞ እኛ አለን፡
🔖MindMap እጥር ምጥን አድርገን በአንድ Page ላይ ብቻ ሙሉ ሃሳቡን ቁጭ አድርገን እፎይ እናስብላለን።

📖ቀን በቀን ደግሞ Tutorials ይኖረናል። አጭር ግልጽ እና ውብ በሆነ አቀራረብ ውድ ውዱን ሁሌም ለእናንተ አለን እያልን አንድ እርምጃ ከፍ ከፍ እያልን ስኬት ላይ እናደርሳለን

📒ምናልባት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ከብዷችሁ ከሆነ መብትሄው እኛ ጋር አለ።
📁የAdvanced Worldwide English በአማርኛ እያዋዛን ስለምናቀርብ ምንም ሊያሳስባችሁ አይገባም።
📒English Entrance examination ከመነሻው እስከ መድረሻው በአማርኛ ግልጽ እና ልዩ በሆነ መንገድ በማቅረብ ላይ ነን።

📘Cambridge university World book በየቀኑ የሚያወጣቸውን የEnglish Vocabulary ከማርኛ ትርጉም ጋር ቀን በቀን....

🔐በሌላ በኩል ደግሞ🔐
📌 ከተለመደው የመጽሃፍ ይዘቶች ለየት ባለ መልኩ ምርጥ Advanced የተባሉትን መጽሃፎች እኛ ጋር ታገኛላችሁ።

❤️ይቀላቀሉን......
💕ትርፋችሁ እልፍ ነው፡ ምክንያቱም የሚሰራው ሁሉም ነገር ስለ ፍቅር ስለሆነ....
❤️ለሚወዱት የሚሰጥ ልዩ፡ ስጦታ፡ የደከሙለትን ፡ መስዋዕት ከፍሎ ያገኙትን ያለገደብ ማካፈል ነው።

💡💡💡💡💡💡💡💡
💡📚@GTutorialclass
:
@GTutorialclass💡
💡💡💡💡💡💡💡💡
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
💕ለእናንተ እኛ አለን 💕
🎈ትርፋችን የእናንተ ደስታ ነው🎈
🤌🤌🤌🤌🤌🤌🤌🤌🤌
💡📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :
@GTutorialclass💡
👍1
BDU Statistics and probability Mid Exam.pdf
6.3 MB
📚 Bahirdar University.

📚 2014 Statstics and Probability Mid Exam.

📚 Targeted group - 2nd year Engineering students.

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
💭 የካንፓስ የመጀመርያ አመት ቆይታ ......በትንሹ

📚 ፍሬሽማን መሆን እንደእናንተ ስብዕና ይወሰናል ። የተለያየ ሰው የተለያየ experience ነው ያለው ። ግን ብዙዎች ጋር የሚኖረውን የፍሬሾች የጋራ ኑሮ ቆንፅለን ለማየት እንጥራለን ...!


💡 ናፍቆት .....!

📚 አንዳንድ ከቤታቸው ሱቅ ለመላክ ካልሆነ ወጥተው የማያቁ ልጆች ድንገት ከቤተሰብ ሲርቁ ምናምን አይችሉም ይነፋረቃሉ ...ከሰው ጋር የማይግባቡ ዝጋታም ልጆች ስላሉ እነሱም ... ለብቸኝነት ሲጋለጡ ሊከብዳቸው ይችላል ። አንድ ነገር እወቁ ከምትወዷቸው ሰዎች መለየት ይሄ የመጀመርያቹ ሊሆን ይችላል ግን ብርቅ አይደለም ...አቅፎ የሚያስተዛዝን ፤ ህመምን የሚጋራ ደስታን የሚካፈል ጓደኛ ቤተሰብ ወዳጅ መለየት በጣም ከባድ ነገር ነው ። ግን ቻሉት በህይወታችሁ ነፍ ግዜ ከምትወዷቸው የህይወት አጋጣሚ ይለያቹሃል ። ካንፓስም የምታገኟቸው ልጆች ከአመታት ውብ የጓደኝነት ቆይታ በኃላ ትለያያላችሁ ። ናፍቆት ያለ ነው ግን መቻል ነው ። በካንፓስ ጥሩ ጓደኛ ያዙ ...እስክትለምዱት ነው ። ከዛ ይለቃቹሃል ።


💡 ምግብ ....!

📚 እንደ እናትህ ውይ ልጄ ተነስ ቁርስ ብላ ና ትተኛለህ አቡኪያዬ ...ምናምን የለም በጠዋት ተነስተህ ሰልፍ ካልወጣህ ሲሞረሙር ይውላል ካፌ ሊያልቅም ይችላል ....ሻይ በዳቦ ለመብላት ይሄ ያክል ሰልፍ ልትልም ትችላለህ ግን በመክሰስ ሰዓት 12 ስለሆነ ራት የሚገረሰው ችከላ ካደርክ ይሞረሙራል...ዳቦ ራሱ ስንት ጣዕሙ ..ከረሃብ ይሻላል ። ሩዝ ፤ ፍርፍር ...ስላለ አትቸጋገር ....ግን ጥሩ ነገር መብላት የለመደ ሰው....ወይኔ ግቢው ጥሩ ባልቴት የሌለው ይመስል ..ጥቅል ጎመን ብለው ቀጭን ሾርባ ጎመን ጣል ጣል ያለበት ሊያቀርቡ ይችላሉ ...ታዲያ አሪፍ ነገር የለመደ አይችልም 500 ብር አከባቢ ይገጨውና ውጪ ይበላል .... ምግቡ እንደ ካንፓሱ ነው በተለይ በቅርቡ የተከፈቱ አርሲ ፤ ቦንጋ ምናምን ምንም አይልም ባህርዳርም አሪፍ ነው ። ሃሮማያማ በሳምንት አራቴ ነው ስጋ የምትግጡት ...ብቻ ብዙ ልጆች የጣፈጠ ነገር ለምደው እነደ ነገሩ የሚሰራው ምግብ አይጥማቸውም ።



💡 ጓደኛ መረጣ ...!

"ጓደኛ መረጣ ላይ መጠንቀቅ አለባችሁ ። በጣም መጥፎ ሰዎችም ጥሩ ልጆችም ይኖራሉ ። ከሱሰኛ ፤ ጨባሽ ፤ ዘረኛ ..ራቁ..በቢሊዮን ማይል ራቁ ...ከእናንተ ጋር የሚሄድ ሰው ፈልጋችሁ ከዶርም ውስጥ አንድ የልብ ጓደኛ በቂ ነው ። ታዲያ ምንም መጥፍ ባህሪይ ቢኖርባቸው ከዶርም ልጅ አትጣሉ ...ትቸገራላችሁ ተንከባክባችሁ ....ተከባብራችሁ በፍቅር አርጉት ...ጓደኛ ምርጫችሁን ተጠንቀቁ ዝም ብሎ ሲያነብ የሚውል የሚተሽንም ሰው አትጠጉ በቃ አራዳ ሆናችሁ ማንበብ ሲኖርበት የሚያነብ ፈታ ግድ ሲል የሚፍታታ ነገሮች የሚገቡ ምርጥዬ ሰው ፈልጉ ።


💡 ሱስ....

📚 በዙ ሰዎች ካንፓስ በጓደኛ ምክንያት ያልሆነ ነገር ውስጥ ይገባሉ ይሄ መሆን የለበትም ...ምንም ቢሆን ሱስ አለም እንዳትገቡ ...ያለባችሁ ችግር ይበቃል ... አንዳንዴ ግዜ ሊተርፋችሁ የምትሰሩት ታጡም ይሆናል ...ሱስ ከምትገቡ አንዷን/ዱን ጠብሳቹሁ ተጃጃሉ እሱ ይሻላል ... ጭራሽ ሱሰ ውስጥ ራሳችሁን እንዳታገኙ በርቱ ....!




💡 መወዛገብ ......!

📚 ከጠበቃችሁ በጣም የተለየ ነገር ሊገጥማችሁ ይችላል ....ያኔ ውዝግብግብ የተለመደ ነው ።ተሳስታችሁ የሰው ዶርም ከች ትሉም ይሆናል ።ብዙ ግዜ ልጆች እስኪለምዱ ድረስ እንዳይጠፋባቸው አንዴ ባዮት መንገድ ብቻ ነው የሚጓዙት ....ሌላ አጭር መንገድ ቢኖርም አይሄዱም በረጅመ ይሄዳሉ የፍሬሽ ነገር የተለመደ ነው ። በቃ በየስርቻው ሲዋሰቡ ፤ ትምህርት ብሎ መጥቶ አባቱን በሬ አሽጦ ፤ እናቱን ፆም አሳድሮ እሱ ጫት ቤት ፤ ቅምቀማ ስታዮት (2 or 3 ተማሪ እንዳይመስሏቹሁ ወደ ግማሽ የሚጠጋው ተማሪ .)...በቃ ላይብረሪው ውስጥ 3 ሰው ብቻ ስታዮ ....ትደነግጣላችሁ ወይኔ ካንፓስ ልትሉም ትችላላችሁ ...!ለምግብ ሰልፍ ስታዮ ..ዋይፋይ ሰዎች ለሊት ሙሉ ሲጠቀሙ ስታዮ....በቃ ትወዛገባላችሁ ...ትምህርት ቤት ያላችሁ መሆኑ ትዝ የሚላችሁ ...የፈተና ሰሞን ነው ላይብረሪ 3 የነበረው ሰው መቀመጫ አጥቶ አንድ ወንበር ለሁለት ተቀምጦ ስታዮ ...ዶርም አዳር ሲቸከል ስታዮ ይገባቹሃል ።



💡 የአስተማመር አይነት ....!.

📚 እንደ Highschol 40 ደቂቃ ሳይሆን 3 ሰዓት ሙሉ አንድ ሳብጀክት ትዳረቃላችሁ .....እሱም ደህና መመህር ካጋጠማችሁ ነው የሚገባችሁ ። በቃሉ እየተጀነነ ሲያወራ የሚውል.... ኖት የሚቸከችክ ...ደብተር ሁላ የሚያርም አለ ። የለመዳችሁት አይነት ...የመማር ማስተማር ሂደት ሲቀየር አትደናገጡ እንደ አየሩ መሆን ነው ። እስከትለምዱት ነው ።



💡 ወሲብ.......!


📚 ወሲብ ከባድ ነገር ነው ። እንኳን እንዲሁ ተለቃችሁ ወትሮም ....የporno ቪዲዮ ይታየዋል ለጉድ በቃ ። ሱሰኞች ካጋጠማችሁማ ዶርም ላይ ...በቃ ላይብረሪ ሁላ ወሲብ ይፈፀማል ......በጣም አስጠሊ ነገር ነው ። ይሄ አይወራ እዛው እዮት .....


💡 ሙድ መያዝ .....❗️

📚 ፍሬሾች ገና ከመግባታችሁ ...የሲኒየሪዎች ነቆራ አይጣል በቃ ምንም ስለማታውቁ ...የማይሆ ነገር ሊነግራቹሁ ይችላል የመመዝገቢ ቦታ ጠይቃችሁ ሽንት ቤት ሊሊሉካችሁ ይችላሉ ። ግን አይደብራችሁ እናንተም በተራቹሁ አየር ስለምትይዙ ....ፈታ በሉበት እስክትለምዱ አየር አታብዙ አትኳትኑ ልጎብኝ እያላችሁ አታካሉ ወሬ ሰብስቡ መጀመርያ ። የመጀመርያ ምግብ ካፌ ማሰታወሻ ፎቶ አንሱት ።

📚 ሁሉንም አውርተን አንጨርሰውም ....በቃ የቀረ ካለ ግቢ ታዮታላችሁ ፥ ብዙ አትጨናነቁ እኛም አለን አዳዲስ ነገር እንነግራቹሃለን ። አይዞን ..! ከዘካንፓስ ጋር ትወጡታላችሁ ...!

© Source - 📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass.

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
"በጦርነትና በግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በዚህ ዓመት ይፈተናሉ" - ትምህርት ሚኒስቴር

🔰 በጦርነት እና በግጭት ውስጥ ሆነው ተፈትነዋል ተብለው የተለዩ እና የ12ኛ ክፍል የማለፊያ ውጤት ያላመጡ ተማሪዎች በዚህ ዓመት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደ መደበኛ ተማሪ ሆነው መፈተን እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ምንጭ፦ EBC ዜና

━━━━━━━━━━━━
📚 JOIN :
@GTutorialclass
JOIN :
@GTutorialclass
━━━━━━━━━━━━
# የዩኒቨርሲቲ ምደባ

የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ፤ ከተያዘው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ የ2013 ዓ.ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች የዩኒቨርሲቲ ምደባቸውን ማወቅ ይችላሉ ሲል አሳውቋል።

©Tikivah Ethiopia.

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
እሚገርም ታሪክ ነዉ
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚማሩ የ 3ኛ አመት የሳይኮሎጂ ተመራቂ ጓደኛሞች ነገ Final ፈተና እያላቸዉ ማታ ሲጨፍሩ አመሹ ፡፡ እናም ወደ ተከራዩበት ቤት ሲመለሱ ለማጥናት ጊዜ ስላልነበራቸዉ ወዲያዉ ተኝተዉ ጠዋት በመነሳት ወደ መፈተኛ ክፍሉ ይሯሯጣሉ ፡፡

በዚህ ጊዜ ሳያጠና መፈተኑ የጨነቀዉ አንድ ተማሪ አሪፍ ሀሳብ ያቀርባል ፡፡
"ለምን ግን ሳናጠና ከምንፈተን ፥ አስተማሪያችንን ትናንት ማታ ወደ ግቢ ላይብረሪ ስንመጣ የምንመጣበት ታክሲ ጎማ ፈንድቶ እሱ እስኪስተካከል ጠበቅን ከዛም ደግሞ በመንገድ ላይ አንዱ ጓደኛችን ታሞ እሱን ሆስፒታል ወሰድን ግቢ እንደገባንም ስለደከመን ሳናጠና አደርን አንለዉም " የሚል ሃሳብ አቀረበ ፡፡ በዚህ ጊዜ ሁለቱም በሀሳቡ በደስታ ተስማምተዉ ለአስተማሪዉ ሊነግሩት ወደ ቢሮዉ በፍጥነት አመሩ ፡፡ የሳይኮሎጂዉ ፕሮፌሰርም ባጋጠማቸዉ ነገር እጅግ በጣም አዝኖ ለነሱ ብቻ ሌላ ፈተና አዉጥቶ በነጋታዉ ሊፈትናቸዉ ተስማሙ ፡፡

3ቱ ጓደኞችም በብልጠታቸዉ እጅግ በጣም ተደስተዉ ቀጥታ ወደ ኬኔዴ ላይብረሪ ገብተዉ ማጥናት ጀመሩ ፡፡ በዛን ቀን ደግሞም ማታዉን ጨምረዉ ወጥረዉ ሲያጠኑ ካማሹ በኅላ በነጋታዉ ለፈተና ቀረቡ ፡፡ አስተማሪዉም ሌላ አንድ ፈታኝ አስተማሪ ጨምሮ 3ቱን ተመራቂ ተማሪዎች ሰፊ ክፍል ካስገባቸዉ በኀላ አራርቆ አስቀምጦ የፈተና ወረቀ ሰጣቸዉ ፡፡

3ቱም ጎደኞች ያለፈዉ ቀን እጅግ በጣም አጥንተዉ ስለነበር በተጨማሪ ትናንት ከተፈተኑት ጓደኞቻቸዉ ስለ ፈተዉ ብዙ መረጃ ይዘዉ ገብተዉ ስለነበር ፈተናዉን እንደሚሰቅሉት ያላንዳች ጥርጣሬና በሙሉ መተማመን ነበር የገቡት ፡፡

የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩም የፈተና ወረቀቱን ሰጣቸዉና በሉ ስሩ ተማሪዋቼ አለ ፡፡ 3ቱም ተማሪዋች ፈተናቸዉን ገልብጠዉ ስማቸዉንና ID ቁጥራቸዉን ከፃፉ በኀላ ጥያቄዉን ማንበብ ጀመሩ ፡፡ ጥያቄዋቹ እንዲህ የሚሉ ነበሩ ?
1. የፈነዳዉ የታክሲ ጎማ የትኛዉ ነበር ?
ሀ.የፊት ቀኝ ለ.የፊት ግራ
ሐ. የኀላ ቀኝ መ.የኀላ ግራ
2.ጎማዉ የፈነዳዉ የት አካባቢና ስንት ሰአት ነዉ?_______
3. ጎማዉ የተቀየረዉ የት ጎሚስታ ቤት ነዉ?
____
4.የታመመዉን ጓደኛችሁን የት ሆስፒታል ወሰዳችሁት?
___

መልካም ፈተና ! መልካም ቅዳሜ
ይህን ፈ
ተና ከደፈናችሁ Final exam ለመፈተን ብቁ ናችሁ !
😂

😊 ስለወደድኩት አጋራሗችሁ

📌 Join and share 👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
🤩2👍1
ስለ 12ኛ ክፍል ተጨማሪ መረጃ
።።።።።።።።።።።።።።።።
1. አማራ ክልልን በተመለከተ በጦርነት አካባቢ የነበሩ ማለት የክልሉን ሁሉንም ዞኖች ማለት ነው። መጀመሪያ ቅሬታ እና ክርክሩ የተነሳው ከአማራ ክልል ብቻ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም በክርክራችን መሰረት በልዩ ሁኔታ ውሳኔው ሁሉንም የክልሉን ተማሪዎች እንዲያካትት የተደረገው ለአማራ ክልል ብቻ ነው። ይህ ማለት ወደ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጡት ሁሉም የክልላችን ተማሪዎች በመደመበኛ ተማሪነት ፈተናውን በድጋሜ ይወስዳሉ ማለት ነው።

2. ተጨማሪ የተወሰነላቸው 4339 ተማሪዎች ደግሞ 50 ፐርሰንት እና ከዛ በላይ ካመጡ ከክልላችን ሁሉም ዞኖች መካከል ተማሪዎች በውጤታቸው ቅደም ተከተል የሚመረጡ ይሆናል።

3. ይህ በዚህ እንዳለ ሌሎች 50 ፐርሰንት እና በላይ ውጤት አምጥተው ወደ ዩኒቨርስቲዎች መግባት ያልቻሉት ደግሞ በክልላችን መምህራን ኮሌጆቾ በመደበኛው የዲግሪ ኘሮግራም የመምህርነት ስልጠና እንዲጀምሩ ሰፋ ያለ ቁጥር ለመቀበል ዝግጅት እያደረግን ነው።

4. በዚህ ሁሉ ጥረት ውስጥ ወደ ዩኒቨርስቲዎችም ሆነ ወደ መምህራን ኮሌጆቾ መግባት ያልቻሉት ተማሪዎቻችን በቂ ዝግጅት አድርገው መፈተን እንዲችሉ የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል የፈተና ጊዜ እንዲራዘምልን ለትምህርት ሚኒስቴር ባቀረብነው ጥያቄ መሠረት ከመስከረም 2015 ዓም በፊት ፈተናው እንደማይሰጥ በትናንትናው ዕለት ተወስኗል።

ስለሆነም የተከበራችሁ የክልላችን ተማሪዎች የ2014 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከመስከረም 20 ቀን 2015 ዓም ጀምሮ ባሉት ጊዚያት ሊሰጥ እንደሚችል አውቃችሁ ተገቢውን ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን በቢሮው በኩል አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑን እናረጋግጥላችኋለን።
Via amhara education bureau

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
  👉 📚 @GTutorialclass
On comment


   ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
እንኳን በደህና አደረሳችሁ
😂🙆‍♂😂🙆‍♂😂🙆‍♂😂🙆‍♂


😢የዓመቱ ምርጥ ለቅሶ


😂😂😂😂ምደባዬ?

© Comment

📌 Join and Share 👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
መልካም ዕድል

የ 2013 12ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ምደባ ይፋ ተደርግዋል ተብሏል ።



ለሁላችሁም መልካም እድል 🙏🙏🙏

ዩኒቨርሲቲ ምደባው ለማየት👇👇👇

Telegram bot👇👇👇
@moestudentbot

Google link👇👇👇👇
https://result.ethernet.edu.et

📌 Join and share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass