G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
አጋጣሚዬን ላካፍላችሁ ብላናለች አንዲት እህታችን። ፍሬዎች ስሙ😂

......( ለሴቶች ብቻ ....! )


"📚Fresh ተመሪ ሆኜ የገጠመኝ ነገር ነበርና ላጋራቹ ፈልጌ ነው ። ለሴቶች ብቻ ነው ወንዶችን አይመለከትም (አንተ አይመለከትህም ተባልክ ኣ ተቀይስ በቃ ...!


📚 ይሀውላቹ ሴቶችዬ ልክ ግቢ ገብቼ ሳምንት ምናምን ከቆየው በኋላ ነበር ብዙ ወንዶች ስልክ ቁጥሬን ከየት እንደሚያገኙ ባላውቅም ይደውሉልኛል ስተገቡ ታዩታላቹ በተለይ ቆንጆ ከሆንሽ አያድርስ ነው ። ያም ይሄም በፍቅርሽ የወደቀ ነው የሚያስመስለው እኔ ብዙም ቶሎ ሰውን የምቀርብ አይነት ሰው አይደለሁም ተናዳጅ ነኝ እናም ለሚደውሉልኝ ብዙም ጥሩ መልስ ስለማልሰጣቸው ይሰደቡኛል ደሞ የሚገርመው ከሚደውሉልኝ ወንዶች አብዛኞቹ GC ተማሪዎች ናቸዉ ። Gcwoch ብዙም እንደሌላው ተማሪ አይጨናነቁም እና አብዛኛው የእነሱ ስራ ሴቶችን ማሳደድ ነው በተለይ fireshochን እነሱንም ተጠንቀቁ እና አንድ በጣም የሚያስቸግረኝ GC ተማሪ ነበር ። በጣም ብዙ ጊዜ እንገናኝ ሲለኝ እምቢ አልኩት ከዛ አንድ ቀን ከጓደኞቼ መሀል ጎትቶኝ ሰደበኝ ፤ በጣም በሚደብሩ ቃላቶች እውነት ምን እንደነካኝ አላውቅም በጥፊ ብዬው ስመለስ ነው እራሴን ያወኩት ። ደነገጥኩኝ ግን በጣም ተናድጄ ነበር ከየት እንደመጡ እንኳን ያላወቋቸው ተማሪዎች ከሁዋላ ሲጮኹ እና ሲያሾፉብኝ ሰምቼ ምንም አላልኩም ዝም ብዬ መንገዴን ቀጠልኩ ። ከዛ ቀን በኋላ ብዙ ወንዶች እየተጠቋቀሙ ያቺ እንትናን የመታችው እያሉ ያሾፉብኛል ነገ አንዱ ጠብ ሲያረግሽ እናያለን ይሉኛል ። ምንም ቢሉ ግድ አይሰጠኝም ነበር ጎበዝ ተማሪ ነበርኩ እና ፍቅር ምናምን ነገር ብዙም አይደለዉም ግን first semister ሊያልቅ አከባቢ የሆነ ልጅ ተዋወኩ ከልጁ ጋ በጣም ተቀራረብን በጓደኛዬ አማካኝነት ነበር የተዋወቅነው በቃ ምን ልበላቹ በየቀኑ እንደዋወላለን ወደድኩት ፤ ሁሉ ነገሩ ደስ ይላል በማጠናበት ሰአት space እየመጣ ትመለሺያለሽ እያለ ይዞኝ ይወጣ ነበር በቃ ማጥናት አልቻልኩም ከዛ አንድ ቀን እወድሻለሁ አበረን እንሁን ምናምን አለኝ ። አቤት...! ያኔ የነበረው ደስታዬ ምንም ማሰብ አልፈለኩም አብረን ሆነን ትምህርትም ተረሳ ማንበብ ሙሉ በሙሉ ባልተውም እንደ ድሮ አልነበረም ገና ፍቅር ከመጀመራችን break ደረሰ በየቀኑ ነበረ ምንደዋወለው...!


📚 ውጤት ተለቆ ሳየው በጣም ነበር የደነገጥኩት 3.07 ነበር ያመጣሁት አልጠበኩም ነበር እራሴን ማስተካከል አለብኝ ብዬ ባስብም ጊቢ ስሄድ ግን አልቻልኩም በቃ ሲጠራኝ እሄዳለሁ በቃ የሆነ ጊዜ አብረን ማጥናት ጀመርን ግን አልሆነም እሱ GC ነበርና ብዙም አያነብም ግን እንደ ድሮ አይደውልልኝም እኔ ነበረኩ ምደውልለት በቃ በጣም ጨንቆኝ ማለቀስ ነበር ስራዬ ወይ ከትምህርቴ አለሆንኩ ይባስ ብሎ አንድ ቀን "በቃ ላንቺ ያለኝ ስሜት ቀንሶዋል" አለኝ ያኔ ይሄን ቃል ከአፉ ስሰማ መሬት ተከፍታ ብትውጠኝ ደስታዬ ነበር ። በጣም የሚያስጠላ ጊዜ ነበር ምንም እራሴን መሆን አልቻልኩም አስከ ዛሬ ድረስ እንደምንም ጓደኛዬ አየተቆጣችኝ አያፅናናችኝ ማንበብ ጀመርኩ ፤ግን በቃ ብቻ ከባድ ነው final ተፈትነን ወደየቤታችን ገባን እስከ ዛሬም አንድ ቀን ተሳስቶ እንኳን ደውሎልኝ አያውቅም ፈጠሪ ይመስገን ye second semster ወጤታ ምንም አይልም ነበረ 3.42 ነበረ ያመጣሁት ግን እሄ ሁሉ ነገር ባይኖር አሪፍ ወጤት ይኖረኝ ነበር ።

💬 እባካችሁ ሴቶች ጊቢ ስትሄዱ የሄዳቹበትን አላማ አትርሱ ሁሉም በጊዜው ይደርሳል ለማለት እወዳለሁ።"

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
😁1
Logic 1-6.pptx
427.7 KB
📚 Logic and Critical Thinking.

📚 Chapter 1 - 6.

📚 ንባብ የጀመራችሁ ልጆች እንዴ ማጠቀሻ መጠቀም የሚያስችል ፋይል ነው።

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
History Grade 11 Unit 7.pdf
1019.5 KB
📚 History Grade 11.

📚 Chapter 7.

📚 Targeted Group - Entrance Candidates.

📚 ይዘቶቹ ለማንበብ ምቹ በሆነ ሁኔታ የቀረበ ፋይል ነው።

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
CHEMISTRY GRADE 11 UNIT 3 SUMMARY.pdf
878.9 KB
📚 Chemistry Grade 11.

📚 Chapter three.

📚 Targeted Group - Entrance Candidates.

📚 ለማንበብ በጣም ምቹ ነው🥰

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
📚 Chemistry Grade 11.

📚 Chapter three.

📚 Short note


© Source - D Marv tutorial.

📌 join and share👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
📢 ንብረቶቻችን የት እናስቀምጣለን


ማንኛውም ፍሬሽ ተማሪ ግቢ ሲገባ የመጀመሪያ መስተንግዶው የሚሆነው የዶርም ሰርቪስ ማግኘት ይሆናል። ምክንያቱም ብዙ እቃዎችን ስለሚጠገረርና የጉዞ ድካምም ስለሚሰማው በዛ ሁኔታ መመዝገብ ስለማይችል ነው።
ወደ ግቢ የምትገቡት የentrance result originalun ምናምን በማሳየት ስለሆነ ብዙም አያስስባቹህ ።


የያዝናቸውን ጓዞች በሙሉ የምናስቀምጠው ዶርማችን ውስጥ ሲሆን ለንብረቶቻችን safety በተወሰነ መልኩ ይረዳን ዘንድ locker ይሰጠናል ፥ ይሁን እንጂ ብዙዎቹ ግቢዎች ላይ የሎከር እጥረት ስላለ ቅድሚያ ዶርም ለሚገቡ ተማሪዎች ብቻ ተደራሽ ሊሆን ይችላል 😔
አንዳንድ ብሎኮች ላይ ደግሞ ትርፍ ሎከር ይኖር ይሆናል ግን በጣም rare ነው፤ጭራሽ ሎከር የማይኖርባቸው ዶርሞችም ሊኖሩ ይችላል ታድያ በዚህን ጊዜ ለንብረቶቻችን ሃላፍትና የምንወስደው የዶርሙ አባላት በመተማመን ይሆናል ማለት ነው ።

ሎከር ኖረም አልኖረ ከዶርሜቶቻቹህ ጋር እስከምትላመዱ ድረስ አንዳንድ ነገሮች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቹሃል ጥንቃቄው ብዙ አይነት ነው ዋናው ግን አለመዝረክረክ ነው ።

Mostly ፍሬሾች የሚዘረፉት በዶርም አባላቶቻቸው ትብብር ወይም ቸልተኝነት or ደግሞ ቀጥታ ከዶርም አባላቶቻቸው ባንዱ ተማሪ ነው።

ብዙ አይነት ተማሪ ሊኖር ስለሚችል በጣም አትዝረክረኩ 👊


PC ምናምን ያላቹህ ልጆች የመጀመሪያውን ሴሚስተር ወደ ግቢ PC ይዛቹህ ባትሄዱ የተሻለ ነው ምክንያቱም ልትበሉ ትችላላቹህ ፤ ደግሞስ የሀገራችሁን ታሪክ ለመማር PC ምን አስጠገረራቹህ ? በርግጥ ኮፒ ምናምን ከማድረግ ሊታደጋቹህ ይችላል ቢሆንም ግን የመጀመሪያዋን ሴሚስተር መታገስ አቅቷቹህ ለቀሪዎቹ አመታት የሚያገለግላችሁን PC ....🏃‍♂️🏃‍♀️

በጣም የሚያስጥላው ደግሞ PCwn እንደ ጨቅላ ልጅ ተሸክሞ መዞሩ coz ዶርም ብናስቀምጠው ጅብ ሊበላው ስለሚችል 😕
በተለይ ፍሬሽ ከሆናቹህ ለተወሰኑ ቀናት ሽንት ቤትና ሻወር ቤት ሁላ ተሸክማቹህ መሄድ ሊጠበቅባቹህ ይችላል 😄።አያ ጅቦ አለህ ?እያላቹህ 😂😂

አንዳንድ የእጅ አመል ያለባቸው senior ተማሪዎች የፍሬሾችን ንብረት እስከ ሻንጣው ተሸክመው እንደሚወስዱም ሰምተናል በሶ እንኳ አይቀራቸውም አሉ 😁😁😁😁

እንደ አጠቃላይ averagun በምናይበት ጊዜ በአንድ ዶርም ውስጥ 4፣6፣ 8 እና 12 ተማሪ ይመደባል ።

ሎከር ብዙዎቹ ግቢዎች ላይ የሚገኝ ቢሆንም ተደራሽነቱ ግን እምብዛም አይደለም ፤ የተወሰኑ በጣም ጥቂት ግቢዎች ላይ አንድ ሎከር ለአንድ ሰው ይዳረሳል most of our campuses ላይ ግን የሎከር እጥረት ስለሚኖር ቀድመው የሚገቡ ተማሪዎች ብቻ እድለኛ ይሆናሉ ። አንድ ሎከር ለሁለት የሚጠቀሙ ብዙ ተማሪዎችም አሉ ዋናው love. ብቻ ነው ።

ሎከሮቹ ሁለት አይነት ናቸው የብረትና የእንጨት
🔒የእንጨት ሎከሮች ብዙም safe አይድሉም የሆነ partachew crack ስለሚኖረው ብሎም ጀርባ ላይኖራቸው ስለሚችል .....
🔒የላሜራ(ብረት) ሎከሮች በጣም አሪፍ ናቸው ቢሆንም ግን ለንብረታችን ሙሉ ዋስትና ሊሰጡን አይችሉም ፤ ለንብረታችን ሙሉ ዋስትና ከፈለግን ከዶርሜቶቻችን ጋር መደመር አማራጭ የሌለው ግዴታ ነው ።


🔒አንዳንድ ግቢዎች ላይ ደግሞ የማይንቀሳቀስ ሎከር አለ ማለትም ከግድግዳው ጋር አብሮ የተሰራ ማለት ነው ያው ይሄም ጥሩ ሊሆን ይችላል ግን በሩ አከባቢ ከእድሜ ብዛት የተነሳ ችግር ይኖርበታል ።

ዶርሜቶች ጋር pis ከሆናቹህ ሎከር ላያስፈልጋቹህ ይችላል ምክንያቱም ዋናው ......... ነውና

©Keleme 2013

📌 Join and Share 👇👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
🤔 ከሃያ አመት በላይ የስራ ልምድ ያለው።(For Anesthesia Dept ) ባጭሩ በደርግ ዘመን የተማረ ማለት ነው😂::

📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
History Grade 12.pdf
1.2 MB
HISTORY Textbook for Grade 12

Brought to you by:
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
Physics Grade-12.pdf
89 MB
Physics Text Book for Grade 12

Brought to you by
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
Tutorial class for all student✍️✍️
𝐴𝑙𝑙 𝑡ℎ𝑖𝑛𝑔𝑠 𝑖𝑠 𝑝𝑜𝑠𝑖𝑏𝑙 𝑤𝑖𝑡ℎ 𝑟𝑒𝑎𝑑𝑖𝑛𝑔
https://t.me/GTutorialclass
Guys please 🙏 🙏 share this channel to your friends
Workbook Biology Grade 11&12 1-1(1).docx
126.7 KB
Biology Work Book for Grade 12

ከ2004-2011 ድረስ ያሉትን የማትሪክ ጥያቄዎች በክፍል እና በምእራፍ ከፋፍሎ የተቀመጠ

👌🏾ለማጥናት ይመቻል

Brought to you by
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
WORK BOOK-PHYSICS-GRADE-11&12.pdf
1.3 MB
Physics Work Book for Grade 12

Work Book ማለት ከ2007-2011 ድረስ ያሉትን የማትሪክ ጥያቄዎች በክፍል እና በምእራፍ ከፋፍሎ የተቀመጠ

👌🏾ለማጥናት ይመቻል

Brought to you by
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass
pdfsat-practice-test-1.pdf
5.1 MB
Physics Work Book for Grade 12

Work Book ማለት ከ2007-2011 ድረስ ያሉትን የማትሪክ ጥያቄዎች በክፍል እና በምእራፍ ከፋፍሎ የተቀመጠ

👌🏾ለማጥናት ይመቻል

Brought to you by
📚 JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass