G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ ከፈተና እርማት እና ቅሬታዎች ጋር በተያያዘ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በመግለጫቸው የፈተናው እርማት ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ በጥንቃቄ የተከናወነ ቢሆንም በሁለተኛው ዙር ፈተና እርማት ላይ የቴክኒክ ችግር ማጋጠሙን እና እርማት መደረጉን ገልፀዋል፡፡

የእርማት ችግሩ የተፈጠረው በ 559 ባልበለጡ ተማሪዎች ላይ እንደሆነ እና ዳግም ምልከታ ተደርጎ መሰተካከል እንደተደረገም ጨምረው ገልፀዋል፡፡የፈተና እርማት ችግር ማጋጠሙ የተገኘውም የፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ምርመራ እንደሆነም ተናግረዋል፡

ቅሬታዎችን በተመለከተም ተማሪዎች ሳይጉላሉ ባሉበት ቦታ ሆነው ቅሬታቸውን ለመፍታት የ ሚያስችል ስርዕት ተዘርግቶ መሰራቱን ገልፀዋል፡፡

በስርዓቱም ከ 20ሺህ በላይ ተማሪዎች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ መሰጠቱንም ነው የተናገሩት፡፡
በተደጋጋሚ የሚነሱ የፆታ እና የስም ስህተቶች በትምህርት ቤቶች አካባቢ የተፈጠረ ክፍተት እንጂ የፈተናዎች አገልግሎት ክፍተት አለመሆኑን ም/ዋ/ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

በዘንድሮው አመት የተፈታኝ ተማሪዎች መብዛት እና በአገራችን ውስጥ ካሉት 47 ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ውስጥ አሁን 43 ቱ ከፍተኛ የት/ት ተቋማት ብቻ የሚቀበሉ ስለሆነ ይህም የዩኒቨርስቲ ቅበላ አቅም አነስተኛ እንዲሆን በማድረጉ መግቢያ ነጥቡን ከፍ እንዳደረገውም ተገልጿል፡፡

በዚህም ምክኒያት በዘንድሮው አመት ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 25 ፐርሰንት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንደሚገቡ ተነግሯል፡፡


📚 JOIN :@GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
#Update

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 25 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ ካሉት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 43ቱ ብቻ ተማሪዎች የሚቀበሉ መሆኑ የዩኒቨርስቲዎችን የቅበላ አቅም ዝቅ ማድረጉ ተነስቷል።

በተጨማሪም ዘንድሮ የተፈታኝ ተማሪዎች ብዛት የጨመረ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ነጥብ ከፍ እንዲል እንዳደረገው ተገልጿል፡፡

በሁለት ዙር የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 598 ሺህ 679 ተማሪዎች የተፈተኑ ሲሆን 287 ሺህ 223 ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወሳል።



📚 JOIN : @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
ትምህርት ሚኒስቴር ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጠ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከ " 12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ውጤት እና ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ " ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍል ከ12ኛ ክፍል የፈተና ውጤት እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ጋር ተያይዞ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የ12ኛ ክፍል ፈተና በ2 ዙር እንዲሰጥ መደረጉንና በመጀመሪያው ዙር የስነ-ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት ከፈተናው ቀን ቀድሞ በመውጣቱና የውጤት ግሽበት በመምጣቱ እንዲሰረዝ መደረጉን ተናግረዋል።

በመጀመሪያ ዙር ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታው በመጀመሪያው ዙር ፈተና ከወሠዱት 544ሺ 682 ተማሪዎች ውስጥ 44 ከመቶዎቹ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን አብራርተዋል።

በሁለተኛው ዙር ከተፈተኑት 53ሺ 997 ተማሪዎች ውስጥ 28 ከመቶዎቹ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር 554 ሺ 682 ተፈታኞች ውስጥ ደግሞ 25 ከመቶዎቹ ይመደባሉ ብለዋል።

የ10 ክፍል የማትሪክ ፈተና በመቅረቱ ምክንያት በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎች በዘንድሮው አመት የ12ኛ ክፍል ፈተናን ወስደዋል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው አራት ዩኒቨርሲቲዎቻችን መቀበል በማይችሉበት ሁኔታ ከአምናው የተሻለ ቁጥር ያለው ተማሪ ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉን አብራርተዋል።

በትግራይ ያሉ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች መመደባቸውና ዘንድሮም ይመደቡ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉ 48ሺ ተማሪ የቅበላ አቅም አጥተናል ብለዋል።

ነገር ግን ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመነጋገር በ43 የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 152 ሺ 14 ተማሪዎች እንዲመደቡ መደረጉና ይህም ከአምናው የቅበላ አቅም ጋር ሲነፃፀር ከፍ ያለ መሆኑን አብራርተዋል።

ፀጥታ ችግር ያጋጠማቸው አከባቢዎች በተመለከተ የተለየ መቁረጫ ነጥብv ለመወሰን የሚያስገድድ የውጤት ትንተና ስላልተገኘ በበመደበኛው የመቁረጫ ነጥብ ተስተናግደዋል ብለዋል።

በባለፈው አመት በ47 ዩኒቨርሲቲዎች 147 ሺህ ተማሪዎች ምደባ የተደረገ ሲሆን ዘንድሮ በ43 ዩኒቨርሲቲዎች 152ሺ 014 ተማሪዎች እንዲመደቡ ተደርጓል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

====================
∞ ነኝ።😊👍
======================

ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !

📚 JOIN: @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
✏️ እንቀልድ እስቲ በዮኒቨርስቲዎቻችን ፥


💬 በተማሪዎች ጥያቄ የቀጠለ፦

📚 የት ዮኒቨርስቲዎች ከደረሳችሁ ምን ይዛቹሁ መሄድ አለባችሁ ፦ (ለቀልድ)


📍 ክፍል ሁለት ፦



💡 አዲስ አበባ

💬 ግቢ ስትገቡ እና ስትወጡ 4ኪሎ በሩን ያጣበበ ስራ አጥ ስትሾፉ ተስፋ መቁረጣቹሁ ስለማይቀር ተስፋችሁን መስፌያ ክር በርከት አርጋቹሁ ያዙ ።

======================


💡አንቦ

💬 የሃጫሉን ዘፈን አላስጫናችሁም ብቻ የቴዲ አፍሮ ዘፈን ስልኮት ውስጥ እንዳይኖር ኧረ አንቦዎች ፍቅር ናቸው ። ረብሽ እስከሌለ ብትነኳቸውም አይነኳችሁም ትላለህ ።

======================


💡ባህርዳር

💬 የካፌ ምግብ ምንም አይነፋም ሻይ ቅጠል መያዝ አትርሱ ዳቦዎቸው አሪፍ ስለሆነ በሻይ ታጣጥሙታላቹሁ (ፔርሙስም ብትይዙ አይከፋም)

======================


💡ASTU

💬 ለሚጠብቋቹሁ ተንከሲሲስ እና ወዝጋ መምህራኖች ልምምድ ከሰፈራቹ ንክ ጋር መግባባት ልመዱ ።

======================


💡 ወላይታ ሶዶ

💬 ፍራፍሬ ብቻ ስለሆነ ሀገሩ ፤ ስፓርት ብትጀምሩ ለመወጣር አትለፉም ። የብር 3 ገዝታቹሁ 4 ይመረቃል ።
======================

💡ሀዋሳ

💬 አሳ የልብ ጓደኛዎ ሊሆን ስለሆነ ስለ ዓሳ ባህሪያት ማጥናት ጀምሩ ። ዓሳኛ ብትለማመዱ ጥሩ ነው ።

======================


💡 ደብረብርሃን

💬 ብርዱ አጥንት ይቆረጥማል ፤ ከቻላችሁ በሱፍ መልክ የምትለብሱት ብርድልብስ አሰፉ ፤ አያሳስብ ደሞ በተፈጥሮ ፍሪጅ የቀዘቀዘ በሶ ነው የምትጠጡት ።

======================

💡ወልዲያ

💬 በረብሻ አትታማም እናም በኃላ ለመሮጥ ከምትቸገሩ አሁኑኑ በቤቶት ዱብ ዱብ ይበሉ ።

ዞግ ነበርኩ ከተመቻችሁ እንቀጥላለን ..!

😘 ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !


📚 JOIN : @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
✏️ እንቀልድ እስቲ በዮኒቨርስቲዎቻችን ፥

💬 በተማሪዎች ጥያቄ የቀጠለ፦

📚 የት ዮኒቨርስቲዎች ከደረሳችሁ ምን ይዛቹሁ መሄድ አለባችሁ ፦ (ለቀልድ)


📍 ክፍል ሶስት ፦



💡ደብረ ታቦር

💬 ለሹሩባ ያሎት አስተሳሰብ እንዴት ነው አፄ ቴድሮስ ማድነቅ ግድ ወላ ከቻላችሁ ሹሩባ መሰራት አትርሱ ።
======================


💡ወለጋ

💬 የሃጫሉን ዘፈን አላስጫናችሁም ብቻ የቴዲ አፍሮ ዘፈን ስልኮት ውስጥ እንዳይኖር ኧረ ፍቅር ናቸው ። ረብሽ እስከሌለ ብትነኳቸውም አይነኳችሁም ትላለህ ።

======================


💡ሰላሌ

💬 የፈረስ ጉግስ አይችሉም ወይኔ ተበሉ አሁኑኑ ፈረስ ጋር ያሎትን ግንኙነት አስተካክሉ ሰላሌዎች በፈረስ ቀልድ አያውቁም (ፋንዲያም ማታውቁ ካላችሁ እወቁ )

======================


💡ደባርቅ(ዴንማርክ)

💬 ዴንማርክ ስኮላር እንዳላገኙ ቁጠሩት ፤ ታዲያ ሀገሬ ሀገሬ የሚል ዘፈን አትርሱ ።

======================


💡መቀሌ

💬 ገላዎትን በአመት 3ቴ ስለሚታጠቡ የሰውነቶን መከርፋት ተለማመዱ ፤ ውሃ በስለትም ውድ ነው ። =====================

💡ወልቂጤ

💬 የስራ ሞራላቸውን ስታዩ እናንተም ስለሚነሽጣቹሁ ፤ ንግድ ለመጀመር የሚሆን ጨላ መያዝ አትርሱ ።
======================


💡 አርሲ

💬 ገነት ልትገቡ ስለሆነ በሩ ላይ ሀጢያታችሁን መናዘዝ አትርሱ ።(የምሬ ኮ ነው..)

======================

💡ወሎ

💬 የቆንጆ ሀገር ስለምትሄዱ በቃ ትምህርቶን መርሳቶት ነው ፤ ፀረ መስተፋቅር ማሰራታችሁ እንዳትረሱ ።



g ነበርኩ ከተመቻችሁ እንቀጥላለን ..!


=====================
ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN : @GTutorialclass
=================
የዩኒቨርስቲ ምደባ ሊደረግ ነው ምደባውን በፍጥነት የሚያሳውቃችሁን ቻናል ልጠቁማችሁ 👇👇👇 @GTutorialclass
📚 የ2013 ዓ.ም Entrance ተፈታኞች ተማሪዎች የፍሬሽነት ዘመን ያስዋበ ቻናል ልጠቁማችሁ ። JOIN : @GTutorialclass

📚 ብዙዎች ጂኒየስ ሆነዋል ፤ በርካታ በካንፓስ ሰቃይ ተማሪዎችን አፍርተናል በፍሬሽነት ዘመኖት A+ ወዳጅዎት እንዲሆን ከፈለጉ ይቀላቀሉን በእርግጠኝነት ያተርፉብናል ።

ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN :@GTutorialclass
📚 JOIN :@GTutorialclass
======================
Geography Grade-12 Unit 3 -5(2012 E.C).pdf
1.1 MB
📚 Grade 12 Geography.

📚 Unit 3 - 5 elegant notes.

📚 ለማንበብ ምቹ የሆኑ ኖቶችን የያዘ ፋይል ነው Entrance ተፈታኞች።

📚 Addis Ababa Education Bureau - ©prepared by Teshome Kefyalew.

📌 Join and share 👇👇👇

@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
Physics G-12 UNIT 5- Powerpoint.pdf
1.7 MB
📚 Grade 12 Physics .

📚 Unit 5 elegant notes.

📚 ለመረዳት ም ሆነ ለማንበብ እጅግ በጣም ምቹ ኖቶችን🥰 የያዘ ፋይል ነው Entrance ተፈታኞች።

📚 Addis Ababa Education Bureau.

📌 Join and share 👇👇👇


@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
♦️Notes on States of Matter

Parameters of Gases
The characteristics of gases are described in terms of following four parameters

Mass
Volume
Pressure
Temperature

1. Mass (m):
The mass of the gas is related to the number of moles as

n = w/M
Where n = number of moles
w = mass of gas in grams
M = molecular mass of the gas

2. Volume (V):
Since gases occupy the entire space available to them, therefore the gas volume means the volume of the container in which the gas is enclosed.

Units of Volume: Volume is generally expressed in litre (L), cm3 & dm3

1m3 = 103 litre = 103 dm3 = 106 cm3.

3. Pressure:
Pressure of the gas is due to its collisions with walls of its container i.e. the force exerted by the gas per unit area on the walls of the container is equal to its pressure.
Pressure is exerted by a gas due to kinetic energy of its molecules.

As temperature increases, the kinetic energy of molecules increases, which results in increase in pressure of the gas. So, pressure of any gas is directly proportional to its temperature.

Units of Pressure:

The pressure of a gas is expressed in atm, Pa, Nm–2, bar and lb/In2 (psi).

760 mm = 1 atm = 10132.5 KP­a = 101325 Pa = 101325 Nm–2

760 mm of Hg = 1.01325 bar = 1013.25 milli bar = 14.7 lb/2n2 (psi)

3. Temperature (T):
Temperature is defined as the degree of hotness. The SI unit of temperature is Kelvin. oC and oF are the two other units used for measuring temperature. On the Celsius scale water freezes at 0°C and boils at 100°C where as in the Kelvin scale water freezes at 273 K and boils at 373 K.

K = oC + 273.5
F = (9/5) oC + 32


📌 ከ6-12 PDF & Worksheet@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
📌ለፍሬሽ ማን PDF & Worksheet @GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
📌ለመወያየት @GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclassrs

@Tmhrt_Minister
Stay safe!
45 የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ዌብሳይቶች
Webs


1 AA SCI. & TECH UNIVERSITY
http://www.aastu.edu.et/
2 Adama science & technology University
http://www.astu.edu.et/
3 Addis Ababa University
http://www.aau.edu.et/
4 Adigrat University
http://www.adu.edu.et/
5 Ambo University
http://www.ambou.academia.edu/
6 Arba Minch University
http://www.amu.edu.et/
7Arsi University
https://www.arsiun.edu.et/
8 ASOSSA UNIVERSITY
http://www.asu.edu.et/
9 Axum University
http://www.aku.edu.et/
10 Bahir Dar University
http://www.bdu.edu.et/
11 BONGA UNIVERSITY
http://www.bongau.edu.et/
12 BULE HORRA UNIVERSITY
http://www.bhu.edu.et/
13 DEBARK UNIVERSITY
http://www.dku.edu.et
14 Debrebirhan University
http://www.dbu.edu.et/
15 Debremarkos University
http://www.dmu.edu.et/
16 DEBRETABOR UNIVERSITY
http://www.dtu.edu.et/
17 DEMBI DOLO UNIVERSITY
http://www.dedu.edu.et
18 Dilla University
http://www.du.edu.et/
19 Dire Dawa University
http://www.ddu.edu.et/
20 Gambella University
http://www.gmu.edu.et
21 Gondar University
http://www.uog.edu.et/en/
22 Haramaya University
http://www.haramaya.edu.et/
23 Hawassa University
http://www.hu.edu.et/hu/
24 INJIBARA UNIVERSITY
http://www.inu.edu.et/
25 Jigjiga University
https://www.jju.edu.et/
26 Jimma University
https://www.ju.edu.et/
27 JINKA UNIVERSITY
http://www.jnu.et/
28 KEBRI DEHAR UNIVERSITY
http://www.kdu.edu.et/
29 Kotebe Metropolitan University
http://www.kmu.edu.et/
30 Meda Welabu University
http://www.mwu.edu.et/
31 Mekelle University
http://www.mu.edu.et/
32 MEKIDELA AMBA UNIVERSITY
http://www.mau.education/
33 METU UNIVERSITY
http://www.meu.edu.et/
34 Mizan-Tepi University
http://www.mtu.edu.et/
35 Oda Bultum
http://www.odabultum.edu.et
36 RAYA UNIVERSITY
http://www.rayu.org/
37 Selale University
http://www.seu.edu.et
38 Semera University
https://www.su.edu.et/
39 WACHAMO UNIVERSITY
http://www.wachemouniversity.academia.edu/
40 Welketie UNIVERSITY
http://www.wku.edu.et
41 WERABE UNIVERSITY
http://www.edu.et/
42 Wolayita Sodo University
http://www.wsu.edu.et/
43 Woldiya University
http://www.fh2web.academia.edu/
44 Wollega University
http://www.wuni.academia.edu/
45 Wollo University
http://www.wollo.academia.edu/


@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass

2013/14 EUEE exam solution
👇👇👇


Freshman maths tutor on YouTube 👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCLPTQfMXS6we7aTT4g9MwCw@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
#AASTU #ASTU

#ADDIS_ABABA_SCIENCE
& TECHNOLOGY

💢Engineering departments
🍮 Architecture
🍮Civil Engineering
🍮 Chemical Engineering
🍮Mechanical Engineering
🍮 Electrcal & Compter eng
🍮Electromechanical Eng
🍮Software Engineering
🍮 Environmental Eng.
🍮Mining Engineering

💢Applied Science departments

🍝Biotechnology
🍝Industrial Chemistry
🍝 Food Science & Applied nutrition
🍝 Geology


#ADAMA_SCIENCE &
TECHNOLOGYY

💢Engineering departments.

🚩Architecture
🚩Civil eng.
🚩 Chemical eng.
🚩Mechanical eng.
🚩Electronics power & control eng.
🚩Electronics & Communicaton eng.
🚩Computer science eng.
🚩Water source eng.
🚩 Material Science & eng.
🚩 Software engineering


💢Applied Science departments

🔅Applied biology
🔅Applied physics
🔅Applied geology
🔅Applied mathematics



Maqaan barattoota ulaagaa guutanii karaa marsaariitii armaan gadii ibsama.
www.aastu.edu.et, www.astu.edu.et


For all 2014 freshman students
join our telegram channel
On our channel you get:
👉 2014 EUEE university info.
👉 fresh man first semester handouts
👉 first semester mid and final exams
👉 first semester short notes
👉 COC exams for medicine, other health, software eng., law, and etc
👇👇
@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass

@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass

To get freshman and grade 12 EUEE Solution video tutor subscribe our YouTube channel👇👇
" .. የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው ይራዘምልን " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ጠየቀ።

ቢሮው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን ገልጿል።

በተጨማሪ በትምህርት አመራሩና በትምህርት ማህበረሰቡ ዘንድ በርካታ ጥያቄዎች እየተነሱ በመሆኑ ቢሮው የተማሪዎች ውጤት በአግባቡ ተፈትሾላቸው ተገቢው መተማመን እስኪፈጠር ድረስ የተማሪዎች መግቢያ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል።

ቢሮው ይህን ጥያቄ ያቀረበው ለትምህርት ሚኒስቴር በፃፈው ደብዳቤ ነው።

ለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ለ መሰናዶ ተማሪዎች
👉Entrance exam 👉COCexams
👉 PDFs 👉 Guide books 👉 Short notes
👉 worksheets
👉Mid exams 👉Final exams
👉Assignments 👉Lecturer's power points

እንዲሁም በአንድ ወር ውስጥ እንግሊዘኛ አቀላጥፈው መናገር ከፈለጉ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ👇👇
@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass
Freshman maths tutor on YouTube 👇👇👇
https://youtube.com/channel/UCLPTQfMXS6we7aTT4g9MwCw
🔴ለአዲስ ገቢ ዩንቨስርቲ ተማሪዎች በሙሉ⤵️

በጥሞና ይነበብ

↪️ዩኒቭርሲቲ ትንሿ ኢትዮጵያ እንደ መሆኗ ከሁሉም ብሄር የመጡ ተማሪዎች ስላሉ ከሁሉም ተማሪዎች ጋር በመቻቻል ማሳለፍ።

↪️ብሄርን መሰረት ያደረገ ማንኛውንም ስድብ ከመሳደብ ተቆጠቡ በዚህ ጉዳይ ላይ ማንኛውም ዩኒቨርሲቲ የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ መሆኑን እንገልፃለን።

↪️የክፍል አስተማሪዎች ላይ ቅረታ ቢኖራችሁ በተቻላችሁ መጠን በትህትና አናግሯቸው ወይም የኮሌጃችሁን አላፊ ያነጋገራቸው ግን በፍፁም ከመከራከር እና እላፊ ከማውራት ተቆጠቡ።

↪️እንደ ዩኒቨርሲቲው ቢለያይም በተመራቂ ተማሪዎች የሚከበሩ በአላት ሊኖሩ ይችላሉ ስለሆነም አዲስ ገቢ ተማሪዎች በዚህ ቀናት ከቻላችሁ ከዶርም አለመዉጣት ከወጣችሁ ግን በሚያጋጥማችሁ ነገር ከተማሪዎች ጋር ከመጣላት ይቆጠቡ።

↪️በምትኖሩበት ዶርም ወይም ብሎክ ላይ የተማሪዎችን ሰላም አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ካጋጠማችሁ ለብሎክ ተቆጣጣሪ ወይም ለተማሪዎች ህብረት ተወካዮች አሳውቁ።

↪️ፈተና ሲደርስ ብዙ ተማሪዎች ፈተና ተስርቆ ወጣ የሚል የውሸት ፕሮፖጋንዳ ስለምያሰራጩ እንደነዚህ አይነት አሉባልታ ከመስማት ተቆጠቡ።

↪️በፍፁም መታወቅያ ካርድ ሳትይዙ ከዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ እንዳትወጡ።

↪️በፍፁም ከየትኛውም የዩኒቨርስቲው ሰራተኞች ጋር ከመጣላት ተቆጠቡ።

↪️ከዩኒቨርስቲው ረጅስትራር ወይም ከተማሪዎች ህብረት ዉጪ የሚለጠፍ ማስታወቂያ ተቀብሎ ከማስተላለፍ ተጠንቀቁ።

↪️በተቻላችሁ መጠን የራሳችሁን ንብረት በጥንቃቄ ጠብቁ።

↪️የዩኒቨርስቲውን ሰላም ለማወክ ከሚንቀሳቀሱ ተማሪዎች በፍፁም አትተባበሩ ከቻላችሁ ለዩኒቨርስቲው ፀጥታ አስከባሪ አሳውቁ ካልሆነ ለተማሪዎች ህብረት ተወካዮች አሳውቁ።

↪️የሕይወታቹ ሙሉ መስመር በእጃቹ ላይ ናት እና ግዜያችሁን ከመቼውም በላይ በአግባቡ ተጠቀሙ።

🔴ማሳሰቢያ🔴
በዩኒቨርስቲው ግቢ ውስጥ የሚነሳው ከዩኒቨርስቲው እዉቅና ያላገኙ ማንኛውም ሰልፍ ወይም ርብሻ ከተማሪዎች ህይወት ማለፍ እና መቁሰል ብሎም የማስተማር ሂደትን ከመስተጓጉል ያለፈ ጥቅም አለመኖሩን ተገንዝባችሁ እነዚህ ድርጊቶች ላይ ከመሳተፍ ይቆጠቡ ጥያቅያቹን በሰላማዊ መንገድ እንድትጠይቁ እናሳስባለን።


😘 ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !


JOIN :@GTutorialclass
📚JOIN :@GTutorialclass
👍1
🄳🄾🅁🄼 🄻🄸🄵🄴 
የዶርም ህይወት በጥቂቱ

📚 ግቢ ውስጥ ከምንም በላይ ደስ የሚልና የማይረሱ ብዙ ክስተቶችን የምናሳልፈው በዶርም ህይወታችን ውስጥ ሲሆን በቆይታችንም እጅግ በጣም ብዙ አይነት ትምህርቶችን እንማራለን ።(የቀለም ትምህርት አላልኩም)

📚በብዙ ግቢዎች ያለውን የሎከር እጥረት በተወሰነ መልኩ ልጥቀስላችሁ እናም በሎከር እጥረት ምክንያት አንድ ሎከር ለሁለትና ከዛም በላይ በመጠቀም ደስ የሚል መተሳሰብ እንዳለም ትንሽ አቋድሼያቹህ ነበር ባንፃሩ ደግሞ የዶርም ጭቅጭቅም በብዙ ነገራቶች ይፈጥራል ገና ከጅምሩ በሎከርና በአልጋ ምርጫ የሚጨቃጨቅ ተማሪም አይጠፋም ።

📚 ሎከር ላይ ያለው ንትርክ ቀድሞ የያዘው ተማሪ ለሁለት ወይም ከዛ በላይ አልደበልም በማለት ሲሆን የአልጋው ግን ብዙ ጊዜ ከታች ያሉትን አልጋዎች ፍልጋ የሚፈጠር ሹኩቻ ነው ። ከላይ ያሉት አልጋዎች የመብራት ብርሃን ስለሚያስቸግርና አንዳንድ ተማሪዎችም ከላይ መሆንን ስለሚፈሩ or ስለማይመቻቸው ይመስለኛል ( ሎከር ላይ ያለው ነገር በስምምነት ይፈታል ከቻላቹህ ለመቅደም ሞክሩ ከተቀደማቹህ ደግሞ አምባጓሮ ሳትፈጥሩ በpeace...)



📚 ዶርም ውስጥ በምትኖሩበት ጊዜ ከተለያዩ ተማሪዎች ጋር ስለምትኖሩ ፀባያችሁን በጣም መግራት ይጠበቅባቹሃል ። በአንድ ዶርም ውስጥ 8 ተማሪ ቢኖር ከስምንቱም ተማሪ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ፀባይ ላይኖረን ይችላል። ያንተ ፀባይ የቱንም ያህል አሪፍ ቢሆን ምንም ደስተኛ የማይሆን የዶርም አባል ሊኖር ይችላል ካዲያ ከኛ ሚጠበቀው እንደዛ አይነት ተማሪዎችን ለማስደሰት መፍጨርጨር አልያም በንዴት እነሱን ፊት መንሳት ሳይሆን ባለንበት ጥሩ ፀባይ ለመፅናት መሞከር ነው ።

📚 አስባችሁታል? እንግዲህ ስምንት ተማሪ ጋር ሆኖ ስምንት አይነት ፀባይ መቻል እንዴት እንደሚከብደ ? ★ዋናው love ነው ★ ብላቹህ የምታምኑ ከሆነ ግን ለሀያ ምናምን መኖርም አይከብዳችሁም

ዶርም ላይ
# በጣም ሀይማኖተኛ
# በጣም ነጭናጫ
# በጣም ሱሳም
# ከፊል ዘረኛ
# በጣም ዝርክርክ
# በጣም ተጠራጣሪ
# መቼም የማያወራ(ልጉም )
# ለሰከንድ ዝም ማለት የማይችል (BBC)
እና ሌሎችንም የመሳሰሉትን አይነት ተማሪዎች ያጋጥሙሃል/ሻል የናንተም የሆነ type of ፀባይ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው ። እናም ከላይ የተዘረዘሩትንና ሌሎችንም አይነት ፀባይ ያላቸውን ተማሪዎች እንደ አመጣጣቸው ማስተናገድ ይኖርባቹሃል ማለት ነው።



📚ፍሬሽ ላይ ዶርማችን ውስጥ ብዙ አይነት ፀባይ ያላቸው ተማሪዎች ጋር ነበር የደረሰኝ ከሁሉም ግን የማይረሳኝ እርስ በርስ የነበረን መተሳሰብና መቻቻል መቼም መቼም አይረሳኝም ።አንዳንዴ ደግሞ ደባሪ ነገሮችንም ልታስተናግዱ ችችላላቹህ ለምሳሌ አንዱ የዶርም አባል ቅዳሜን አክባሪ ከሆነ ጨብሶ በመምጣት ቁም ስቅላችሁን ያሳያቹሃል ( ቅዳሜ የመጠጥ ቀን ናት ብለው ስለሚያስቡ ነው)
እናም የጨበሰው ወይም የጨበሰችው ተማሪ ዶርም ውስጥ በብዙ አይነት መልኩ አዛ ያደርጓቹሃል ፦

😂 ሻታ በርግደው የዶርሙን ንፅህና በማስዋብ(ማስመለስ)

😂 በተኛችሁበት ብርድ ልብስ በመግፈፍ

😂 ከአልጋ ለማስወረድ በመታገል

😂 ሳትፈልጉ በስካር ቅላፄ ዘፈን መጋበዝ

😂 ሌሎችንም like this 👆 የመሳሰሉትን የስካር አመሎችን ሊያሳዩ ስለሚችሉ በታቻላቹህ አቅም ስካራቸው እስኪለቃቸው በትዕግስት በመቻል እንዴትም ጊዜዋን ማሳለፍ ይጠበቅባቹሃል
ከትዕግስታቹህ በኋላ ቀጣዩ እርምጃ የእናንተ ይሆናል ማለትም ለዶርም ተቆጣጣሪዎች (ለፕሮክተሮች) በማመልከት ችግሩን መቅረፍ ይቻላል ። ፕሮክተር ጋር ከመሄዳቹህ በፊት ግን መጀመሪያ በፍቅር ለመፍታት ሞክሩ coz አብሯቹህ ከሚኖር ሰው ጋር መኗቀር በጣም ያስጠላል ፡ይጎዳልም

📚 ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ወንዶችን ብቻ የሚመለከቱ አይደሉም ከወንዶቹ ባልተናነሰ መልኩ የሴቶችም በሽታ ነው ።

📚 ሌላው ከዶርም ህይወት ደስ የሚለው የዶርም ላይ ወሬዎች ናቸው

ዶርም ውስጥ
📢 አሳዛኝ ታሪኮችን መስማት
📢 በማይጠቅሙ topicoch ሌቱን ሙሉ መከራከር
📢 ዶርም ውስጥ የሚኖር ብሽሽቅ (postively)
📢 የዶርም ጨዋታዎች
📢 ትምሮን በግሩፕ መፍለጥ
📢 ፕሮጀክቶችንና assignmentochn አብሮ መወረክ
📢 ከቱሃን ጋር መሯሯጥ
📢 መቻቻል
📢 በሶ መቋደስ (ኢትዮጲያዊነት መልካምነት J..)
📢 ስለ ተቃራኒ ፆታ ማቡካት
📢 የሰው ስጋ ቁርጥምጥም አርጎ መብላት (በተለይ ቺኮች አካባቢ 😂)
📢 ስልክ እየደወሉ በሰው ሙድ መይዝ ( ፍሬሽ ላይ ስንቱን እንዳስለፈለፍኩት አልረሳውም)

📚 ግን ከጠቀስኳቸው negative የሚመስሉትን ነገሮች ፈልጋቹህ ሳይሆን ሳታስተውሉ የምትፈፅሟቸው በመሆናቸው ብዙም ለመጠንቀቅ አትሞክሩ 😂


📚ሌላው ደስ የማይለው ወንዶች ዶርም አካባቢ ያሉ ጥፊዎች 😪

😷😷😷😷😷😷😷😷😷😷

💬 የጫማ ሽታ በራስችን ዝርክርክነት የሚመጣ ትልቅ በሽታ ሲሆን ችግሩን ከተከሰተ በኋላም ቢሆን በቀላል መቅረፍ ይቻላል ሆኖም ግን እንደዚህ አይነት ችግር ያለባቸው ተማሪዎችን ለመናገር ትንሽ ሼም ይቆነጥጣል coz ሳይኮ ምናምን እንዳይጎዱ ....
ስለዚህ ወንድሞቼ እባካቹህ ሰው እስኪነግራቸህ ሳጠብቁ daily ካልሲዎቻችሁን check አርጉ ። ምናልባት ዶርም ውስጥ የጫማ ጥፊ የሚያስቸግራቹህ ከሆነ የካልሲውን ባለቤት ሳይኮ በማይጎዳ መልኩ ለብቻው በማናገር የራሳችሁንም ሆነ የዶርማችሁን ጤና መጠበቅ ይኖርባቹሃል
አይ ይቺ አለም😭😭😭😭😔😔

እንቀጥላለን!


ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
@GTutorialclass📚 JOIN :@GTutorialclass

=================
የትምህርት ሚኒስቴር ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን
እንዲያስተካክሉ የሰጠው የጊዜ ገደብ ትናንት ተጠናቋል።

የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃጻጸም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13/2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ መጋቢት 08/2014 ዓ.ም ማሳወቁ አይዘነጋም።

ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ መግለጹ ይታወሳል።

በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ላይ በርካታ ቅሬታዎች በተለይ ከአማራ ክልል መነሳታቸው ይታወቃል።

ሚኒስቴሩ በቅሬታዎቹ ላይም ሆነ በዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከያው ላይ ያለው አዲስ ነገር የለም።
======================
∞ ነኝ።😊👍
======================

ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN : @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
=================
Physics G-12 UNIT 5- Powerpoint.pdf
1.7 MB
📚 Grade 12 Physics .

📚 Unit 5 elegant notes.

💡 ለመረዳት ም ሆነ ለማንበብ እጅግ በጣም ምቹ ኖቶችን🥰 የያዘ ፋይል ነው Entrance ተፈታኞች።
======================
∞ ነኝ።😊👍
======================

ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN : @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
=================
Geography Grade-12 Unit 3 -5(2012 E.C).pdf
1.1 MB
💡 Grade 12 Geography.

📚 Unit 3 - 5 elegant notes.

📚 ለማንበብ ምቹ የሆኑ ኖቶችን የያዘ ፋይል ነው Entrance ተፈታኞች።
======================
∞ ነኝ።😊👍
======================

ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN : @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
=================
የማመልከቻ ቀኑ የተራዘመ ማስታወቂያ

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን መረጃዎች እንድትመለከቱ እንጠይቃለን

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

©ትምህርት ሚኒስቴር

ውብ የካንፓስ ቆይታ ከዘ ካንፓስ ጋር !
======================
📚 JOIN : @GTutorialclass
📚 JOIN : @GTutorialclass
=================
📌 የዩኒቨርሲቲ ምንጫ ማስተካከያ ጊዜው እስከ መጋቤት 19 መራዘሙን ትምህርት ሚኒስትር ገለፀ።

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ ባስመዘገባችሁት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችላችሁ ታማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳችሁ ይታወቃል። ስለሆነም ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን አውቃችሁ የሚከተሉትን መረጃዎች እንድትመለከቱ እንጠይቃለን

1ኛ. የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ http://Portal.neaea.gov.et ገብታችሁ እንድታስተካክሉ እየገለጽን ከምደባ በኋላ የሚቀርብ ምንም አይነት የምደባ ለውጥ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

2ኛ. በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላችሁ የምታመለክቱ ተማሪዎች መረጃችሁን እስከ መጋቢት 19/2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንድትልኩ እያሳሰብን በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን።

©ትምህርት ሚኒስቴር

📌 Join and Share 👇👇👇

🎯JOIN :@GTutorialclass
JOIN :@GTutorialclass