G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
Woldia University‼️
የጥሪ ማስታወቂያ!

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ ዓመትና አራተኛ ዓመት የፔዳጎጅካል ሳይንስ መደበኛ ተማሪዎች ጥሪ አስተላልፏል።

በመሆኑም ከላይ በማስታወቂያው በተገለፀው ቀን በአካል ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

@GTutorialclass
AppliedOne.pdf
2.9 MB
📚 ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰኞ ለምትፈተኑ ፍሬሽማን ተማሪዎች።

📚 Applied Mathematics One.

📚 Freshman second semeseter course.

📚 Faculty of Technology የተመደባችሁ ልጆች የምትወስዱት ኮርስ ነው።

📚 ይኸን መፅሀፍ ካሁኑ Download አድርጋችሁ ያዙት። የፈተና ስሞን ላይብረሪ ራሱ በ ሰልፍ አታገኙትም😱

@GTutorialclass
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለተኛ ዙር የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት እየታረመ ነው።

በሁለተኛው ዙር ከ58 ሺህ በላይ ተማሪዎች በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ፈተናውን ወስደዋል።

ብሔራዊ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከመጀመሪያ ዙር ተፈታኞች ጋር አብሮ እንደሚገለጽ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ተናግረዋል።

@GTutorialclass
ጥንቃቄ‼️ #Grade12+1

የዩኒቨርሲቲ ምርጫችሁን ልክ መሆኑ ና portal ላይ መግባቱን ቼክ አድርጉ🙏

http://result.neaea.gov.et/Home/Choice

በተለይ የፊልድ ምርጫችሁን ቼክ አድርጉ። አምና ብዙ ልጆች ሳይፈልጉ #teaching ገብቷል።

© Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!

@GTutorialclass
' #12ኛ_ክፍል '

የ 12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እንደተባለው ከሆነ ከ መክሰኞ እስከ አርብ ድረስ ይለቀቃል።

ስለዚህ በርካታ ተማሪዎች ጥያቄ ጀምሯል። መልሶችን በተቻለው መጠን ከታች👇

1ኛ- ከ Natural ወደ Social መቀየር ይቻላል። ነገር ግን ከ Social ወደ Natural አይቻልም።

መቼ ነው ለምለው ደግሞ ውጤታችሁ ከመጣ ቡሃለ ምደባ ሳይደረግ በፊት ነው። መቀየር የምትፈልጉ ጊዜው ስደርስ ኢትዮ ዩኒቨርስቲ ቻናል ያሳውቃቹሃል።

2ኛ ውጤታችሁ ከመጣ ቡሃላ ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ማስተካከል ትችላላችሁ። ነገር ግን ዘንድሮ ጊዜ የለንም ብለው ልከለክሉ ይችላሉ።

3ኛ- የተሰረቁ ፈተናዎች አሉ ተብለው ነበር። እነሱን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር ብቻ ነው የሚያውቀው።

4ኛ - ASTU ,AASTU እና Phaulos መወዳደር የሚትፈልጉ ተማሪዎች ከዚህ በፊት የነበረውን ፈተና እያያችሁ ተዘጋጁ።

ፈተናው ውጤት መጥቶ ማለፊያው ከታወቀ ቡሃላ ግቢዎች ማስታወቂያ ያወጣሉ።

Point:- የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ማገዝ የምትፈልጉ Senior ተማራዎች ተዘጋጁ🙏

12ኞች ደግሞ ይሄን መልዕክት ሼር በማድረግ ለተማሪዎች እንድደርስ አድርጉ🙏

ጥያቄ ና አስተያየት ለመስጠት
 @Entrance_Exambot

ለተጨማሪ መረጃ ይሄን የቴሌግራም ቻናል JOIN ማድረግ ትችላላችሁ👇👇

https://t.me/+D-0GtJwnikQxZDE0
https://t.me/+D-0GtJwnikQxZDE0
https://t.me/+D-0GtJwnikQxZDE0
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
ቅሬታ‼️ #12ኛክፍል

የ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩንቨርስቲ ምርጫቸው ወረቀት ላይ የሞሉት እና Portal ላይ የገባላቸው አይመሳሰልም በማለት አብዛኛው ተፈታኞች ቅሬታ አቅርበዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ለተማሪዎች አሁንም የተወሰነ የማስተካኪያ ቀን እንዲሰጠን እንፈልጋለን ሲሉ በአስተያየት መስጫው እና በቦታችን በኩል አድርሰውናል።

ይህ ስህተት በየአመቱ የሚከሰት ስለሆነ ተማሪዎች ውጤት ይፋ ሆኖ ምደባ ሳይደረግ በፊት ትምህርት ቤታችሁ በመሄድ ማስተካኪያ እንድትጠይቁ እንላለን።

ትምህርት ሚኒስቴር እና የሚመለከተው አካል ለተማሪዎች መፍትሔ እንዲሰጥልን በአክብሮት እንጠይቃለን።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
👍1
የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

የካቲት 16 ወቀን 2014 (ኢዜአ)በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ተራዝሞ የቆየው የ2013 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዝናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በመጀመሪያ ዙር የተሰጠው የ12ኛ ክፍል የስነዜጋና ስነምግባር ትምህርት የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑንም ኤጀንሲው ገልጿል።

ተማሪዎችም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

የፈተና እርማቱ ደህንነታቸው አስተማማኝ በሆኑና ከንክኪ ነጻ በሆኑ የማረሚያ ማሽኖች አስፈላጊው የደህንነት ጥበቃ በፌደራል ፖሊስና በሴኩሪቲ ካሜራዎች ታግዞ በጥንቃቄ መከናወኑንም ነው የገለጸው።

ከዚህ በተጨማሪም የፈተናዎች ውጤት በትምህርት ዓይነት፣በትምህርት ቤትና በተማሪ ደረጃ ሰፊ የውጤት ትንተና በማካሄድ የእያንዳንዱ የትምህርት ዓይነት ውጤት ተገምግሟል ብሏል ኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ።

በዚሁ መሰረት በመጀመሪያው ዙር (ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም) በተሰጠው የስነዜጋና ስነምግባር ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ስለታየበት የፈተና ውጤቱ ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ መወዳደሪያነት እንዳያገለግል መወሰኑንም ጠቅሷል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለበትም ተገልጿል።

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል ሲልም አስረድቷል ኤጀንሲው።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት እንደሚገለጽ ጠቁሟል።

ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et
2) በትምህርት ሚኒስቴር ድረገፅ፡- result.ethernet.edu.et
3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot - በዚህ ማስፈንጠሪያ በመግባትና Exam Result የሚለውን በመጫን በመልዕክት መጻፊያው ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት እና የ ምልክት በመጫን መላክና ውጤታቸው ማየት ይችላሉ።

4) በ9444 የ ኤስ ኤም ኤስ (9444 SMS) ፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

በውጤት ላይ ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች result.neaea.gov.et በመግባት እና Compliant የሚለውን በመጫን ቅሬታቸውን በፎርሙ ላይ በመሙላት ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 02/2014 ዓ.ም ለወንድ 293 ሺህ 865 ሴት 250 ሺህ 703 ድምር 544 ሺህ 568 ተማሪዎች ተሰጥቷል።

ከፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ በመጀመሪያው ዙር ሳይፈተኑ ለቀሩ ለወንድ 27 ሺህ 979 ሴት 26 ሺህ 456 ድምር 54 ሺህ 435 ተማሪዎች ደግሞ ከጥር 24-27/2014 ዓ.ም በሁለተኛው ዙር ፈተና እንዲወስዱ ተደርጓል።

በአጠቃላይ በሁለቱም ዙር ከተመዘገቡት 617 ሺህ 991 ተማሪዎች ውስጥ ወንድ 321 ሺህ 844 ሴት 277 ሺህ 159 ድምር 599 ሺህ 003 (96.9%) ተማሪዎች ፈተናውን መውሰድ ችለዋል።
@GTutorialclass
@GTutorialclass
🥰1
#AASTU
#ማስታወቂያ

በ2013 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስደው ወደ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ መልዕክት ተላልፏል።

ሁለቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ የተማሪዎች ቅበላን የሚያከናውኑት በሀገር አቀፍ ደረጃ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚያስገባው ውጤት ከተወሰነ በኃላ ነው፡፡

ይህንን ሂደት ተከትሎም ሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመመዝገቢያ እና ለፈተና ብቁ የሚያደርገውን ውጤት የሚወስኑ ሲሆን ምዝገባውም በኦንላይን ብቻ የሚከወን ይሆናል፡፡

በመሆኑም አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በሚወጣው መስፈርት መሰረት ለመግባትና ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች ቀጣይ ሂደቶችን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ይገለፃል ተብሏል።


@GTutorialclass
Let’s be the positive influence in our world!
Stay Safe
ቅሬታን በተመለከተ አምና ቅሬታ አቅርበው ምላሽ ከተሰጣቸው ጥቂት ተማሪዎች ውስጥ በቅርብ የማውቀውን ተማሪ የሆነ ነገር በልልኝ ብዬው ነበር.....


፨የሌሎች የግቢ ተማሪዎችንም መልዕክት አስደምጣቹሃለው👍

Credit : #atc_news

@GTutorialclass
Let’s be the positive influence in our world!
Stay Safe
@GTutorialclass
የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡት እነማን ናቸው?

° ተማሪ አላዛር ተካ (ወ)
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ሚኒሊክ I ሳይንስ ሼር ካምፓስ (አዲስ አበባ)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 659
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 563

(🎯 ሒሳብ 100/100 ፤ 🎯 ፊዚክስ 100/100)
-------------------------------

° ተማሪ ተመስገን ገብረወልድ (ወ)
ሊቃ ትምህርት ቤት (ዎላይታ)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 651
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 555

(🎯 ሒሳብ 100/100 )
-------------------------------

° ናታኒም በላይ (ሴ)
ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርሲቲ ሚኒሊክ I ሳይንስ ሼር ካምፓስ (አዲስ አበባ)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 651
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 554
-------------------------------

° ተማሪ ሙሴ ፊሊጶስ (ወ)
ሊቃ ትምህርት ቤት (ዎላይታ)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 647
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 551
-------------------------------

° ተማሪ ኮኬት ተስፋዬ (ወ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 643
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 548

(🎯 ፊዚክስ 100/100 )
-------------------------------

° ተማሪ አብዱላዚዝ ዜኑ (ወ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 644
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 547
-------------------------------

° ተማሪ ሲፈን ፊጣ (ሴ)
የኦሮሚያ ልማት ማህበር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት (ODA)

አጠቃላይ ውጤት ከ7 መቶ ፦ 639
አጠቃላይ ውጤት ከ6 መቶ ፦ 542

(🎯 ሒሳብ 100/100 )

NB፦
- በ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና የሲቪክ ፈተና ውጤት ለዩኒቨርሲቲ መግቢያ እንደማያገለግል መገለፁ ይታወቃል።
- መረጃው ከተላኩልን መልዕክቶች የተሰበሰበ መሆኑና የጸና መረጃ አለመሆኑ ከግምት ውስጥ ይቀመጥ።

Via -tikvahethmagazine


@GTutorialclass 
Let’s be the positive influence in our world!
Stay Safe
@GTutorialclass
‼️Announcement ‼️‼️‼️‼️

የstream እንዲሁም የሀገር ምርጫ ማስተካከያ ለጊዜው የተዘጋ መሆኑን ልንገልፅ እንወዳለን። ስለዚህም ት/ቤት መሄድ አይጠበቅባችሁም። አዲስ መረጃ ስናገኝ እኛው የምንለቅላቹ ይሆናል።

@GTutorialclass
Let’s be the positive influence in our world!
Stay Safe
@GTutorialclass
K
ትዝብት ‼️ #Grade_12

ትምህርት ሚኒስቴር በአዲሱ ካሪኩሉም ላይ የ 10ኛ ክፍል ማትሪክ እንዲቀር ማድረጉ ይታወሳል። በ ዘንድሮ 2013/14 የ 12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች የ10ኛ ክፍል ማትሪክ ፈተና ተፈትኖ ውጤቱ ሳይታይ ሁሉም ተማሪ ማለፉ ይታወሳል።

የዛኔ የነበረው ደስታ ሁላችንም እናውቃለን። አሁን ግን ያ ደስታ ተገልብጦ ሌላ ችግር በተማሪዎች ላይ ፈጥሯል። ተማሪው የዛኔ ባያልፍ ኖሮ የራሱን ህይወት፣ጊዜ እና ጉልበት ተጠቅሞ የሚፈልገውን ማድረግ ይችል ነበር።

ባጭሩ ለማለት የፈለግነው ከ 50% በታች ያመጡ ተማሪዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መማር አይችሉም የተባለው በጣም ያሳዝናል። በርግጥ ኮሌጆችም የመያዝ አቅማቸው ውስንነት አለው። ቢሆንም ግን ይሄ ሁሉ ትውልድ......????

ይህ ጉዳይ ተጠንቶ ይህ ማለፊያ ነጥብ ዝቅ ቢልና ለተማሪዎች ተስፋ ቢደረግ እንላለን። ይህ ማይቻል ከሆነም ትምህርት ሚኒስቴር ሌላ አማራጭ ለተማሪዎቹ ቢፈልግ የተሻለ ይሆናል።

በመጨረሻም ተማሪዎች ወደ ሌላ የቢዝነስ አለምም እይታቸውን ቢያሰፉ ይመክራል FEE። ከ 300 በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ

@GTutorialclass
Let’s be the positive influence in our world!
Stay Safe
1
ትምህርት ሚኒስቴር የኦንላይን መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎት ማስጀመሩን ገለጸ።

ትምህርት ሚኒስቴር የኦንላይን መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎት ሚኒስቴሩ ካዘጋጃቸው እና ለተማሪዎች ይጠቅማሉ ካላቸው ከተለያዩ የውጭ ምንጮች በማካተት ይዤ ቀርቢያለው ብሏል።

ሥርዓቱ መደበኛና አጋዥ መጽሃፍት፣ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ያካተተ ሲሆን አገልግሎቱ ለተማሪዎች ግብዓቶችን በክፍል፣ በትምህርት አይነት፣ በምዕራፍ ለመምረጥ በሚያስችል መልኩ ለአጠቃቀም ቀላል ሆኖ መቅረቡ ተገልጿል።

በተጨማሪም የአካል ጉዳተኞችን እና ወደ ትምህርት ቤት መምጣት የማይችሉ ተማሪዎችን ችግር እንዲያቃልል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን ልዪ ተሰጥኦ ያላችውን ተማሪዎች የትምህርት ስርዓቱን ሳይገደቡ መከታተል ያስችላልም ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የመማር ማስተማር ግብዓቶችን በክፍል፣ በትምህርት አይነት እና በምዕራፍ ተከፋፍሎ ወደ ሲስተሙ የመጫን ስራ ተሰርቷል። በቀጣይም ለመጀመሪያ ደረጃ እና የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች የዚሁ አግልግሎት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ይሰራልም ተብሏል።

ተማሪዎችም የኦንላይን መማሪያ ስርዓትን እና ዲጂታል ላይብራሪ አገልግሎትን ለማግኘት የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም እንደሚችሉ ተገልጿል
https://elearn.moe.gov.et

@GTutorialclass
Stay Safe!
🔰 የ ዩኒቨርስቲ ምርጫ እንዴት እንሙላ

ADDIS ABABA UNIVERSTIY የምመደበው ምን ባረግ ነው400/700 አምጥታችሁ AAU የምትመደቡበት እድል?

📊ውጤታችሁን ካያችሁ በኋላ የ ዩኒቨርስቲ ምርጫ አሞላላችሁን ከ አመጣችሁት ነጥብ ጋር በማነፃፀር ማስተካከል ለምትፈልጉ

📃 የቀሰም ቤተሰብ በ ዉስጥ መስመር የላከው መልዕክት

💡ቻLu አሁን ጊቢ ለሚመርጡ በጣም ጠቃሚ ምክር ነው። ከባለፈው አመት experienceኤ ያገኘሁትን ነው የማካፍላቸው።

📚ጊቢ በውጤት ብቻ የምትሞሉ ካላችሁ ትበላላችሁ (በተለይ የአዲስ አበባ ተማሪዎች)። ጊቢ ከመሙላታችሁ በፊት check ማድረግ ያለባችሁ ነገሮች አሉ። አለበለዚያ ግን እንደኛ 560-590 ቤት ሆናችሁ እንኳን ከ1-5 ራሱ ላይደርሳችሁ ይችላል።

💡መጀመርያና ዋናው check የምታደርጉት ነገር የትምህርት ቤታችሁን competitiveness ነው። ትምህርት ቤታችሁ በከተማው (በሀገሪቱ) ያለውን አጠቃላይ ታዋቂነት ወይም ደረጃ እና በትምህርት ቤታችሁ ምን ያህል ተማሪዎች ከናንተ በላይ ውጤት አመጡ የሚለውን ቼክ ማድረግ አለባችሁ። ይህን ለማድረግ የተለያዩ የቴሌግራም ቦቶችን መጠቀም አለባችሁ። ለምሳሌ ትምህርት ቤታችሁ የከተማው በጣም ታዋቂ ከሆነና ከናንተ በላይም የተወሰኑ ተማሪዎች በውጤት rank የሚበልጧችሁ ከሆነ፤ እመኑኝ የማትፈልጉት ቦታ የመድረስ እድላችሁ በጣም ከፍተኛ ነው።

📚ሁለተኛው ደግሞ የዩኒቨርሲቲዎችን generation ማወቅ ነው። ከ1-3 1st generation ሞልታችሁ፤ ለሰላሙ ብላችሁ ደግሞ 2nd generation በመሃል ብትቀላቅሉ፤ እዛ ጊቢ የመድረስ እድላችሁ ከ90% በላይ ነው። አይ የመጀመርያ ምርጫዬ 1st generation አይደለም የመጀመርያ ምርጫዬ 2nd generation ነው ብላችሁ ከ1-3 ብትሞሏቸው ግን በቀላሉ ታገኟችኋላችሁ።

💡ሶስተኛው ደግሞ የምትፈልጓቸው ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ አመራረጥ ነው። ከላይ ያልኳችሁን ሁለቱን በማመዛዘን ዩኒቨርሲቲዎችን ከመረጣችሁ በኋላ፤ የነሱን የአመራረጥ rankንም ማየት ይኖርባችኋል። ለምሳሌ.... ከታዋቂ high school (ታዋቂ high school የምለው እሱ በጣም ምርጫችሁን influence ስለሚያደርግ ነው... በራሴ experience መሰረት ስላየሁት) school rank ቢያንስ 50 ሰዎች ቢበልጧችሁና እና ከ1-6 1st generation ብትሞሉ፤ የምትፈልጉትን ዩኒቨርሲቲ 1ኛ ላይ ማስቀመጥ የለባችሁም። Machineኡ የሚሰራው comprehensively ሁሉንም አይነት ምክንያቶችን ባማከለ መንገድ ስለሆነ እና ከመላው ሀገሪቱ ተማሪዎች እንዲሁም ከምትፈልጉት ዩኒቨርሲቲ የመቀበል አቅም ጋር ስለሚያስተያይ..... ማስተዋል ይኖርባችኋል። ስለዚህ ከላይ በፃፍኩት ውስጥ የምትጠቃለሉ ተማሪዎች፤ አንደኛ ምርጫችሁን ቢያንስ 3 or 4ኛ ላይ ብታደርጉት more የመድረስ እድል ይኖራችኋል።

📚ይህንን ሁሉ በቀላል ምሳሌ ለማስረዳት..... የፈለገ ውጤት ብታመጡ (ለምሳሌ 500 አናቱ ላይ) እና ከተማራችሁበት school በrank ከ1-10 ውስጥ ብትሆኑ፤ ከ1-3 ምርጫችሁ በእርግጠኝነት ይደርሳችኋል። ለዛ ነው ብዙ ተማሪዎች "እከሌ እኮ ከኔ በታች አምጥቶ/ታ አንደኛ ምርጫው/ዋ ደረሰው/ሳት" ሲሉ የሚደመጡት። ነገር ግን 570/80 አምጥታችሁ፣ በschool rank ከ10-20 ወይም ከ20 በላይ ወይም እንደየትምህርት ቤታችሁ የተማሪ ብዛ ከ50 በላይ ብትሆኑ፤ እንኳን 1ኛ ምርጫችሁ ይቅርና ከ1-3 እንኳን ላይደርሳችሁ ይችላል። ስለዚህ በኋላ ከመፀፀት፣ ምርጫችሁ ላይ smartly በደንብብብብብ እንድታስተውሉና እንድታስቡበት ከልቤ እመክራችኋለሁ። ይሄን ምክርና example የሰጠሁት ጥሩ ውጤት ላላቸው ተማሪዎች ቢሆንም፤ ሌሎቹም ተማሪዎች 3ቱን conditionኦችን ከራሳችሁ ውጤት ጋር በማስተያየት በቀላሉ ማሰብ ትችላላችሁ። 400 ቤት ሆኜ አዲስ አበባ አይደርሰኝም ማለት በድሮው የትምህርት system እንጂ ባሁኑ ዘመን አይሰራም 😊። እንደውም more chance አላችሁ እመኑኝ።

ይቅናችሁ ❤️😊

Via-qessemaccadamy
@GTutorialclass
Let’s be the positive influence in our world!
Stay Safe
👍1