G-Tutorialclass
813 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
በውጭ ሀገራት እየኖሩ የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከኢንተር ፖል ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል ይሰራል-የፌደራል ፖሊስ‼️

በውጭ ሀገራት እየኖሩ ከጁንታው ጋር ተባባሪ በመሆናቸው የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ምክትል…

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በአማራ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው‼️

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

ክልል አቀፍ ፈተናው በ5 ሽህ 162 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ከትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

የፈተና ቁሳቁሶች ተሟልተው ክልል አቀፍ ፈተናው እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ገልፀዋል፡፡

ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የፀጥታ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

በመደበኛ፣ የማታ እና የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ415 ሽህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ መገለጹን አብመድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
#Ethiopia : የመተከል ጉዳይ የውጪ ሀይለኝኛ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም:: ትናት በዶሊ ቀበሌ ቁጥራቸው 300 የሚሆኑ የተደራጁ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ በወሰዱት ጥቃት የመከላክያ ሰራዊት አባልን ጨምሮ ስድስት ሰው መሞቱ ታውቋል:: የቲክቫህ አባላት መረጃን ከስፍርው እንዳደረሱት መከላክያ ገብቶ እርምጃ ባይወስድ የተደራጁት ታጣቂዎች ብዙ ሰው ይገሉ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል::
በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ 100 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ!

#Ethiopia : በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት አካባቢ ለውጥን በማይፈልጉ አማጺያን የበርካታ ሰዎች ሞት እና ንብረት መውደሙን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ ኮሎኔል አያሌው በየነ ተናግረዋል።

ቀጠናውን በበላይነት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጥፊዎች ላይ በወሰደው እርምጃም 42 ጸረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮሎኔል አያሌው ገልጸዋል። 7 የሚደርሱ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።

ምንጭ:- የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ
የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን እንዳረጋገጠ ገለጸ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባካሄደው የጥናትና ቁጥጥር ስራ እንዳረጋገጠ ገለጸ።

በመተከል ዞን እየደረሰ ባለው የዜጎች ጭፍጨፋ፣ የንብረት ውድመትና ከቤት መፈናቀል የክልሉ መንግስትና የጸጥታ መዋቅር ድርጊቱን መከላከልና ማስቆም ለምን እንዳልቻሉ ለመመርመርና ለማጥናት ተሞክሯል ብሏል ተቋሙ።

ጉዳዩን የሚመረምር የጥናትና ቁጥጥር ቡድን ወደ አካባቢው በመላክ ባደረገው ጥናትም በዞኑ ማንዱራ፣ ዳንጉር፣ ጉባ፣ ደባጤ፣ ቡለንና ወንበራ ወረዳዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ የተካሄደ መሆኑን እንዳረጋገጠ አመልክቷል።

“እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ163 በላይ ዜጎች ህይወት ያለፈ መሆኑን እንዲሁም ከ31 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ለመረዳት ተችሏል” ብሏል በመግለጫው።

በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት የክልሉ መንግስት አስተዳደር አካላት፣ የፓርቲ አመራሮችና የጸጥታ መዋቅር አካላት እንደተሳተፉም ጠቁሟል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት የነበራቸው ድጋፍና ክትትል ዝቅተኛ እንደነበር ገልጾ፤ “”ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረው የኮማንድ ፖስት ከችግሩ ክብደትና ስፋት አንጻር የሰራው የጸጥታ ማስከበር ስራና በአጥፊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ደካማ እንደነበር የተቋሙ የጥናትና የቁጥጥር ቡድኑ ለይቷል” ብሏል።
በመሆኑም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለ የመንግስት መዋቅር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ቀዳሚ ተግባርና ሃላፊነቱን ተገንዝቦ የዜጎችን ንብረትና ደህንነት በአግባቡ እንዲጠብቅና ዳግም ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደርስ አሳስቧል።

ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመተከል ዞን ከህብረተሰቡ ተወካዮችና ከአመራሮች ጋር ተወያይተው ያስቀመጧቸው አቅጣጫዎች በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆኑ ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል።

በተጨማሪም በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የነበሩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድና ለህዝቡም ይፋ እንዲሆን መጠየቁን ተቋሙ ለብስራት በላከው መግላጫ አስታውቋል።

የፌዴራል የጸጥታ መዋቅር አካላት ህጉ በሚፈቅደው መንገድ ከሁሉም ክልሎች የተቀናጀ የጸጥታ ሃይል በማዋቀር በክልሉ ተሰማርቶ የዜጎችን ህይወትና ንብረት ሊታደግ በሚችልበት ቁመና ላይ እንዲገኝ መንግስት ከውሳኔ ላይ እንዲደርስ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።
Forwarded from About education
እንኳን ደስ አላችሁ! የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆናል፡፡

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን የተሻለ ውጤትም የተመዘገበ በመሆኑ ተማሪዎች ፣ ወላጆች በአጠቃላይ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡

የፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች በዛሬዉ እለት የተሰራጨ ሲሆን ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ውጤታችሁን በየትምህርት ቤቶቻችሁ መመልከት እንደምትችሉ ይጠበቃል፡፡

@NEAEA_nea
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

>>>ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።<<<<
Forwarded from Deleted Account
[Forwarded from ዣንዣድ]
አስቸካይ ማስተንቀቂያ 😲😲

በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

የፊታችን መጋቢት 29 የሚካሄደው የህዝብ ቆጠራ ምክንያት በማድገግ የተለያዩ ሀይማኖቶች የኦርቶዶርስን እምነት ሊያጠፉ ይፈልጋሉ !!!
እናም ቆጠራ በሚካሄድበት ጊዜ
😟😟 አስተውሉ 😟😟
በክርስቲያን እምነት ውስጥ ከ 35.000 በላይ የሚሆኑ እምነቶች አሉ እናም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ በማለት እምነታችን እንዳይጠፋ እንጠብቅ።
አስብት እስቲ አሁን የመንግስት ሰራተኖች እረፍታቸው በሰንበት (እሁድ) ነው እረፍታቸው ግን የሀይማኖታችን ቁጥር ካነሰ ይቀየራል በነፃነት መስቀልንም ሆነ ጥምቀትን በጋራ ማክበራችንም ሊቆም ይችላል ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምንም ነች እናም
አናስብ ሀይማኖታችን እንዳይጠፍ ጥር 11 የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ በአልም ሊቀር ይችላል እባካችሁ ሀይማኖታችንን እንጠብቅ
ቢያንስ አንድ ኦርቶዶስ ለጋደኞቹ 10 ሰው ቢልክ ሀይማኖቱን ይጠብቃል
ድንግል ማርያም እናቴ አንቺ ጠብቂን በእግዚአብሔር ስም እለምናችሁለሁ ሁላችሁም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ናችሁ ቢያንስ ለ10 ሰወች ከተቻለ በጣም ለምትችሉት አድርጉ የሁላችንም ግዴታ ነው በዚ ምክንያት እኛን ለመበታተን ጠላት አድብቶ ይሰራል እኛ ዛሬም ነገም እስክንሞት ድረስ ኦርቶዶክሶች ነን ስለዚ ሸር ለሁሉም ይድረስ ፡፡
Forwarded from . ?
👋ሰላም Just ይህ ከታች የላክንልዎ የእርሶ መለያ ቁጥር ነው ይህን ለ 25 ሰዎች በመላክ እና Start እንዲሉ በመጋበዝ የ 500 ብር የሞባይል ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/AwashBankRefferalBot?start=r04361188530

💞 መልካም እድል 💞
💎Awash Bank💎
የ12ኛ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል !

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል።

በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ገልፀዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።

በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!
#Ethiopia : ከስር በምስል የምትመለከቱት ኮረኔል የማነ ገብረሚካኤል የማይካድራዉን ጭፍጨፋ መሪ ተዋናይ ነዉ ሲባል የተወነጀለዉ መከላኪያ እርምጃ ተወስዶበታል ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም እጅ ስጡ ተብለው እጅ አንሰጥም በማለት እርምጃ የተወሰደባቸው የህወሃት ጁንታ ወንበዴዎች መካከል

1. ኮሎኔል የማነህ ገ/ሚካኤል
2. ኮማንደር ተስፋዬ ገብረ መድህን
3. ኮሎኔል ዮሀንስ ካላዕዩ
4. ኮሎኔል የአለም ገ/መድህን
5. ኮሎኔል ቢንያም ገ/መድህን
6. ኮሎኔል እንባዮ
7. ኮሎኔል ይርጋው ስዩም
8. ኮረኔል ማዕሾ
9. ኮሎኔል ሀዲሽ
10. ሌ/ኮ ብርሀኔ
11. ኮሎኔል አፅብሀ
12. ኮሎኔል ገ/እግዛብሔር
13. ሁለት የዞን አመራሮች ማንነታቸውን ለመለየት አስቸጋሪ የሆኑና አራት ኮሌኔሎች መድፍ አስተኳሽ የነበሩ ይገኙበታል::

በተጨማሪም በቤተክርስቲያን ፂማቸውን አሳድገው የአባቶችን ልብስ ለብሰው ከተያዙት የህወሃት ባለስልጣናት መካከል::

1. ዶር አለም ብርሀኔ
2. ኮሎኔል መብርሀቱ ገ/መድህን
3. ኮሎኔል ሀዲሽ ሀጎስ
4. ኮሎኔል ህሉፍ ገ/መድህን
5. የሜጄር ጀረናል አታክልቲ በርሄ ሚስት ታጋይ ወ/ሮ አበባ እና ሌ/ኮ ተክለህይውት አስፋ የመቀሌ ዩንቨርስቲው ሙሁር ተብየውና በየፌስቡኩ ፕሮፓጋንዳ ሲናገር የነበረው ገብረዐምላክ ነብዩ በቁጥጥር ስር ውለዋል:: ከዚህ በተጨማሪ የቢሮ ሰራተኞች የነበሩ በጣም ብዙ የህወሃት አባሎች በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል::
Forwarded from ETHIO-MEREJAÂŽ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አቶ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር የዋሉት ተደብቀው ከነበሩበት ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ በሆነ ሰርጥ ውስጥ ነው።

አቶ ስብሃትን የህወሓት ቡድን አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀዋቸው የነበር ሲሆን የመከላከያ ሰራዊት እና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻ እና አሰሳ፣ ከተደበቁበት በማውጣት በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጻል። ሀገር መከላከያ ሰራዊት በቁጥጥር ስር የዋሉ አመራሮችን ለመከላከል በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረ የታጠቂ ሀይልን መደምሰሱን ገልጿል። (ebc)
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
Forwarded from ETHIO-MEREJAÂŽ
በሕንድ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 10 አዲስ የተወለዱ ህጻናት ሞቱ

በሕንድ ሀብታም በሆነችው ማሃራሽትራ ግዛት በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ አስር አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናት ዛሬ ቅዳሜ ዕለት ሞተዋል፡፡ ብሃንዳራ በተሰኘው ሆስፒታል በደረሰው አደጋ ገባ እንደተወለዱ በማቆያ ውስጥ ከነበሩ 17 ህጻናት አስሩ ሲሞቱ ሰባቱን ማትረፍ ተችሏል፡፡ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ እና ሌሎች ባለሥልጣናት ሀዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኤኤፍፒ እንደዘገበው የእሳት አደጋው መንስኤ እንዲጣራ የግዛቱ አስተዳደር ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
ከ50 በላይ መንገደኞችን የጫነ የኢንዶኔዢያ የመንገደኞች አውሮፕላን (Sriwijaya Air Boeing 737) ጠፋ።

አውሮፕላኑ የተነሳው ከጃካርታ ሲሆን እስካሁን የደረሰበት አልታወቀም።

የኢንዶኔዢያ ትራንስፖርት ሚኒስትር ከጃካርታ ከተነሳ በኃላ በደቂቃዎች ውስጥ ደብዛው የጠፋውን አውሮፕላን የመፈለጉ ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።
በቢንሻንጉልጉሙዝ በደባጤ ወረዳ የ 130 ንጹሀን ሂወት አልፎል ጥቃቱም ብሄር ተኮር ነው ሲል ኢሳት ዘግቧታል
👋ሰላም Gebre ይህ ከታች የላክንልዎ የእርሶ መለያ ቁጥር ነው ይህን ለ 25 ሰዎች በመላክ እና Start እንዲሉ በመጋበዝ የ 500 ብር የሞባይል ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/AwashBankRefferalBot?start=r05511284830

💞 መልካም እድል 💞
💎Awash Bank💎
ይሄንን መልካም እድል ጆይን በማድረግና ሼር በማድረግ ይጠቀሙ ጓደኛዎንም ይጥቀሙ መልካም እድል ይሁንሎ👂🤳‼️
የኢትዮጲያ መስማት የተሳናቸው ማህበር የ45 ዓመት ጥያቄው እንደተመለሰለት አስታወቀ።

መስማት የተሳናቸው ዜጎች አሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ገብተው የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና መውሰድ ሊጀምሩ ነው፡፡

የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ከጥር 16 ጀምሮ የሚሰጥ መሆኑን ኤትዮ ኤፍ ኤም ከኢትዮጲያ መስማት የተሳናቸው ማህበር ሰምቷል፡፡

ይህንን ጥያቄ ማህበሩ ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት 45 ዓመታት ሲጠይቀው የነበረው መሆኑን የማህበሩ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት ዓለማየሁ ገልፀዋል።

ኢትዮጲያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የአካል ጉዳተኞችን መብት ኮንቬንሽን ከፈረሙ ሀገራት መካከል እንደመገኘቷ አካል ጉዳተኞች ያለአንዳች አድሎ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ተጠቃሚዎች ይሆኑ ዘንድ ዋስትና የመስጠት ግዴታ ተጥሎባታል፡፡

በመሆኑም መስማት የተሳናቸው ዜጎች አሰፈላጊውን ስልጠና በመውሰድ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማግኘት እንዲችሉ የአሰራር ማንዋል ሲዘጋጅ መቆየቱን የኢትዮጲያ መስማት የተሳናቸው ማህበር ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ትዕግስት ዓለማየሁ ለኤትዩ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

መስማት የተሳናቸው ዜጎች የማሽከርከር መብታቸው ተረጋግጦ የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ቀጣይና ዘላቂ እንዲሆን የራሳቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ ማድረግ እና ማሽከርከር አይችሉም በሚል የተሳሳተ አመለካከትና ግንዛቤ የሚፈጥረውን የስራ አጥነት ችግር በመቅረፍ ወደ አምራች ዜጋ መቀየር የጥረታችን ዋና አላማ ነው ብለዋል ወ/ሮ ትዕግስት፡፡

ስራ አስኪያጇ አክለውም በሀገራችን የህግ ማእቀፎችን በማሻሻል መስማት የተሳናቸው ዜጎች ባላቸው እውቀትና ችሎታ በማንኛውም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተሳታፊነታቸውን ለማረጋገጥ እየተሰራ ይገኛል፡፡

በዚህ መሰረት የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አዋጅ 1074/2010 መሰረት በማድረግ መስማት የተሳናቸው ሰዎች አሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት ገብተው የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና በመውሰድ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማግኘት እንዲችሉ የአሰራር ማንዋል ተዘጋጅቷል፡፡

ማህበሩ ከትራንስፖርት ሚኒስትር ፣ ከጤና ሚኒስትር ከትራፈክ ፖሊስ ፅ/ቤት እና ከሰራተኛና ማህበራዊ ጎዳይ ጋር በመሆን እየሰራ መሆኑን አንስተው ከዚህ በፊት በጤናው ዘርፍ ምርመራ ሲደረግ በጆሮ አካባቢ ችግር ካለ የይለፍ ወረቀት አይሰጥም ነበር።

አሁን ግን ጤና ሚኒስትር ይህንን ለጤና ተቋማት በሙሉ ማሰረጃ እንዲሰጥልን እንዲሁም ደግሞ የትራፊክ ፖሊስ ፅ/ቤት ይህ መረጃ እንዲኖረው ለማድረግ ጊዜ ቢወስድብንም ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ስልጠናው ይጀመራል ተብሏል፡፡

(Ethio fm)
ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ ለማሳወቅ ጎረቤት ሀገራትን እየዞረች ነው

የሱዳን የተለያዩ ባለስልጣናት ሳዑዲን ጨምሮ ወደ ተለያዩ ሀገራት ጉዳዩን ለማሳወቅ አቅንተዋል። የሱዳን ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤትና የሚኒስትሮች የጋራ ምክር ቤት ሀገሪቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የድንበር ውዝግብ በተመለከተ ወደ ጎረቤት ሀገራት ጉብኝት እንዲደረግ መወሰኑን አስታወቀ፡፡

የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ወደ ካይሮ፣ አስመራ፣ ጁባና ሳዑዲ አረቢያ በመሄድ ጉዳዩን እያስረዱ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ አባል ሌፍተናንት ጄነራል ሻምሰዲን ካባሺ በደቡብ ሱዳን፣ የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ ምክትል ሊቀመንበር ሌፍተናንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወደ ኤርትራ፣ የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ አባል ሌፍተናንት ጄነራል ኢብራሂም ጃቢር ወደ ቻድ፣ መሐመድ ፋኪ ሱሌማን ወደ ሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

የሀገሪቱ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦማር ቀመረዲን፣ የስለላ ኃላፊው ጄነራል ጃማል አዲን ኦማር ፣የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ፋይሳል መሐመድ ሳሊህ እና የሉዓላዊ ሽግግር ምክር ቤቱ አባል ሌፍተናንት ጄነራል ሻምስ ኢል ዲን ካባሺ ዛሬ ወደ ካይሮ አቅንተዋል፡፡
Forwarded from ETHIO-MEREJAÂŽ
የአፄ ቴዎድሮስ የልደት በዓል በጎንደር ከተማ እየተከበረ ነው!

202ኛው የአፄቴዎድሮስ የልደት በዓል በጎንደር ከተማ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ በበዓሉ ላይ አጼ ቴዎድሮስን የሚዘክሩ ትርኢቶችም በወጣቶች ቀርበዋል፡፡ የአማራ ክልል ማርሽ ባንድም በአከባበሩ ላይ በመገኘት የማጀቢያ ጣዕመ ዜማዎችን አሰምቷል፡፡ በአከባበሩ ላይ ጎንደር ከተማን ጨምሮ ከዞኑ የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡ (አብመድ)
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot