G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
የ4 አመት ህፃን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱ ተገለፀ!

በምዕራብ ጎጃም ዞን ቡሬ ዙሪያ ወረዳ የ4 አመት ህፃን አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የወረዳው ኮሚውኒኬሽን ቢሮ ገልጿል።

ተከሳሽ ''በስካር መንፈስ ተነሳስቼ ወንጀሉን ፈፅሚያለሁ ጥፋተኛ ነኝ'' ሲል ለፍርድ ቤት ቃሉን ሰጥቷል። ታህሳስ 8 የዋለው ችሎትም ተከሳሹን በ17 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን አና አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በውጭ ቋንቋዎች ከሚጽፉ የ‘ሜይንስትሪም’ ሚዲያ ባለሙያዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ጋር ተወያዩ‼️


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታና የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ቃልአቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው ዕለት በእንግሊዝኛ፣ በአረብኛ፣ በፈረንሳይኛ እና በአገር ውስጥ ቋንቋዎች በ‘ሜይንስትሪም’ ሚዲያ እና በድረ ገጽ ከሚጽፉ ተንታኞች እና ከማህበረሰብ አንቂዎች ጋር በወቅታዊ እና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ሬድዋን በውይይቱ ወቅት ካተኮሩባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል በአገሪቱ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ፣ ከታችኞቹ የአባይ ተፋሰስ አገራት ጋር በታላቁ የኢትዮጵያ ህሳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ለበርካታ ዓመታት ሲደረግ የቆየው የሶስትዮሽ ድርድር እና አገራቱ በድርድሩ ላይ የሚከተሉት አቋም ጂኦፖለቲካዊ አንደምታ፣ በአገሪቱ እየተተገበረ ያለው ሪፎርምና በሂደቱ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ከተግዳሮቶቹ ጀርባ ያለው ድብቅ ሚስጢር ይገኙባቸዋል።
በእነዚህ ዋና ዋና ጉዳዮች ምክንያት በአገሪቱ ላይ የሚደርሰውን አሉታዊ ተጽኖ ለመመከት ከዜጎች የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በተለይ የማህበረሰብ አንቂዎች አገራዊ ፈተናዎችን ለመሻገርና አና መግባባትን ለመፍጠር ያላቸውን ከፍተኛ ሚና ተገንዝበው ከትናንሽ አጃንዳዎች እየወጡ በዋና ዋና አገራዊ አጃንዳዎች ላይ በማተኮር የማህበረሰቦችን አብሮነት ማጠናከር እና የባዕዳንን እኩይ አጃንዳዎች ማክሸፍ እንዳለባቸው በአጽንኖት ተናግረዋል።
አቶ ሬድዋን አክለውም የማህበረሰብ አንቂዎች መንግሥት ነቅቶ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ማገዝ፣ የአገር ብሄራዊ ጥቅሞች እንዲከበሩ ማድረግ እንዲሁም በህዝቦች መካከል የአብሮነትና የወንድማማችነት መንፈስ እንዲጎለብት ማስቻል አለባቸው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የትግራይ ህዝብ የጁንታውን ርዝራዦች አሳልፎ ሊሰጥ ይገባል- ዶ/ር አረጋዊ በርሄ

መንግስት የጁንታውን ርዝራዦች የትግራይ ህዝብ አሳልፎ እንዲሰጥ ያቀረበውን ጥሪ በደስታ በመቀበል ለራሱ ሰላም እና ደህንነት ሲል አሳልፎ ሊሰጥ ይገባል ሲሉ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ገለጹ፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ከዋልታ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ በሀገር ላይ ክህደት የፈጸመው ጁንታ ከምንም እና ከማንም በላይ ሲጨቁነው እና ሲዘርፈው የኖረው የትግራይን ህዝብ ነው፡፡

በትግራይ ክልል የነበሩ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ህገ መንግስቱ በሚፈቅድላቸው መንገድ በክልሉ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ ጽንፈኛው የትህነግ ቡድን አፈና ሲያደርግባቸው መቆየቱን የገለጹት ዶ/ር አረጋዊ፣ አሁን ላይ ግን ምቹ መደላድል ይፈጠራል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

የትግራይ ተወላጅ የሆኑት አቶ ዮሃንስ ሃይሉ በበኩላቸው፣ አስፈላጊ በሆነው መንገድ ሁሉ በክልሉ ከተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልጸው፣ የህወሓት ጁንታው ቡድን ላለፉት ረጂም አመታት ሲጨቁነው ከቆየው ህዝብ ውስጥ ተሸሽጎ እንዳለና ይህን ጁንታ በማጋለጥ የትግራይ ህዝብ አኩሪ ታሪክ ሊሰራ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደሩ እያከናወነ ያለው ስራ የሚደነቅ እንደሆነና በቀጣይም ጠንከር ያሉ የቤት ስራዎች የሚጠብቅ በመሆኑ እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጎን ሊቆም እንደሚገባም ጠይቀዋል፡፡መንግስት በክልሉ ያቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደርም ህበረተሰቡን በማወያየት ስራውን የጀመረ ሲሆን፣ በራስ ወዳዱ ጁንታው ቡድን የተበላሸውን የመልካም አስተዳደር ችግር ለማስተካከል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ የእሳት አደጋ ተከሰተ‼️

በወላይታ ሶዶ ከተማ መርካቶ ገበያ ዛሬ ንጋት ላይ መንስኤው ለጊዜው ባልታወቀ ምክንያት የእሳት አደጋ መከሰቱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል።

የከተማዋ እሳት አደጋ መከላከያ ቡድን እሳቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ተገልጿል።

በአካባቢው ያለው ከባድ ነፋስ እሳቱ በከፍተኛ ፍጥነት እንዲዛመት እያደረገው ስለመሆኑም የከተማዋ ነዋሪዎች ገልፀዋል ሲል ደሬቴድ ዘግቧል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በልደታ ክ/ከተማ ስልጤ መስኪድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት አለፈ ‼️

በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ በፈነዳ ቦንብ የሰው ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦንብ ጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ የሦስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በአምስት ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ኮሚሽኑ ገልጿል።

በኮሚሽኑ የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑን ገልፀው፤ የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ግልጽ ይደረጋል ነው ያሉት።

በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ መሆናቸውን አስታውሰው ያሰታወሱት ዳይሬክተሩ፤ ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@Esat_tv1
@Esat_tv1
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ለወሰደችው ሕግ የማስከበር ተግባር ሕጋዊነት እውቅና በመስጠታቸው አመሰገኑ!

የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያ ለወሰደችው ሕግ የማስከበር ተግባር ሕጋዊነት በመረዳታቸው እና እውቅና በመስጠታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመሰገኑ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ኢጋድ 38ኛ አስቸኳይ የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ በጅቡቲ ተካሂዷል። በዚህ ጉባኤም የኢጋድ አባል አገራት መሪዎች ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት መግለፃቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ገፃቸው አስታውቀዋል።
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
T.me/ethio_mereja
T.me/ethio_merejabot
⊰━━━━━━━━━━━━⊰
በውጭ ሀገራት እየኖሩ የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከኢንተር ፖል ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል ይሰራል-የፌደራል ፖሊስ‼️

በውጭ ሀገራት እየኖሩ ከጁንታው ጋር ተባባሪ በመሆናቸው የእስር ማዘዣ የወጣባቸውን ተጠርጣሪዎች ከዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት (ኢንተርፖል) ጋር በመነጋገር በቁጥጥር ስር ለማዋል እንደሚሰራ የፌደራል ፖሊስ አስታወቀ። በፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መላኩ ፋንታ ዛሬ በመቐለ ከተማ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። ምክትል…

@Esat_tv1
@Esat_tv1
በአማራ ክልል የ8ተኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እየተሰጠ ነው‼️

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከዛሬ ጀምሮ እስከ ታኅሣሥ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል፡፡

ክልል አቀፍ ፈተናው በ5 ሽህ 162 የፈተና ጣቢያዎች እንደሚሰጥ ከትምህርት ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

የፈተና ቁሳቁሶች ተሟልተው ክልል አቀፍ ፈተናው እየተሰጠ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ገልፀዋል፡፡

ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው የፀጥታ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ ተገብቷል ብለዋል፡፡

በመደበኛ፣ የማታ እና የግል ተፈታኞችን ጨምሮ ከ415 ሽህ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ መገለጹን አብመድ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

@Esat_tv1
@Esat_tv1
#Ethiopia : የመተከል ጉዳይ የውጪ ሀይለኝኛ እጅ ሳይኖርበት አይቀርም:: ትናት በዶሊ ቀበሌ ቁጥራቸው 300 የሚሆኑ የተደራጁ ታጣቂዎች ሰላማዊ ሰዎች ላይ በወሰዱት ጥቃት የመከላክያ ሰራዊት አባልን ጨምሮ ስድስት ሰው መሞቱ ታውቋል:: የቲክቫህ አባላት መረጃን ከስፍርው እንዳደረሱት መከላክያ ገብቶ እርምጃ ባይወስድ የተደራጁት ታጣቂዎች ብዙ ሰው ይገሉ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል::
በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ 100 ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ!

#Ethiopia : በቡለን ወረዳ በኩጅ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት ከንጋቱ 11:00 ሰዓት አካባቢ ለውጥን በማይፈልጉ አማጺያን የበርካታ ሰዎች ሞት እና ንብረት መውደሙን የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት አዛዥ ኮሎኔል አያሌው በየነ ተናግረዋል።

ቀጠናውን በበላይነት የሚመራው የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአጥፊዎች ላይ በወሰደው እርምጃም 42 ጸረ ሰላም ሃይሎች መደምሰሳቸውን ኮሎኔል አያሌው ገልጸዋል። 7 የሚደርሱ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል።

ምንጭ:- የዞኑ ኮሚውኒኬሽን ቢሮ
የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን እንዳረጋገጠ ገለጸ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ መካሄዱን የኢትዮጵያ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ባካሄደው የጥናትና ቁጥጥር ስራ እንዳረጋገጠ ገለጸ።

በመተከል ዞን እየደረሰ ባለው የዜጎች ጭፍጨፋ፣ የንብረት ውድመትና ከቤት መፈናቀል የክልሉ መንግስትና የጸጥታ መዋቅር ድርጊቱን መከላከልና ማስቆም ለምን እንዳልቻሉ ለመመርመርና ለማጥናት ተሞክሯል ብሏል ተቋሙ።

ጉዳዩን የሚመረምር የጥናትና ቁጥጥር ቡድን ወደ አካባቢው በመላክ ባደረገው ጥናትም በዞኑ ማንዱራ፣ ዳንጉር፣ ጉባ፣ ደባጤ፣ ቡለንና ወንበራ ወረዳዎች ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ የተካሄደ መሆኑን እንዳረጋገጠ አመልክቷል።

“እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ163 በላይ ዜጎች ህይወት ያለፈ መሆኑን እንዲሁም ከ31 ሺህ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን ለመረዳት ተችሏል” ብሏል በመግለጫው።

በተፈጸመው የወንጀል ድርጊት የክልሉ መንግስት አስተዳደር አካላት፣ የፓርቲ አመራሮችና የጸጥታ መዋቅር አካላት እንደተሳተፉም ጠቁሟል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት የነበራቸው ድጋፍና ክትትል ዝቅተኛ እንደነበር ገልጾ፤ “”ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተል የነበረው የኮማንድ ፖስት ከችግሩ ክብደትና ስፋት አንጻር የሰራው የጸጥታ ማስከበር ስራና በአጥፊዎች ላይ የወሰደው እርምጃ ደካማ እንደነበር የተቋሙ የጥናትና የቁጥጥር ቡድኑ ለይቷል” ብሏል።
በመሆኑም በየትኛውም ደረጃ ላይ ያለ የመንግስት መዋቅር የዜጎችን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅ ቀዳሚ ተግባርና ሃላፊነቱን ተገንዝቦ የዜጎችን ንብረትና ደህንነት በአግባቡ እንዲጠብቅና ዳግም ተመሳሳይ ጉዳት እንዳይደርስ አሳስቧል።

ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመተከል ዞን ከህብረተሰቡ ተወካዮችና ከአመራሮች ጋር ተወያይተው ያስቀመጧቸው አቅጣጫዎች በፍጥነት ተግባራዊ እንዲሆኑ ምክረ ሃሳብ ሰጥቷል።

በተጨማሪም በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳታፊ የነበሩ አካላት በህግ እንዲጠየቁ፣ ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድና ለህዝቡም ይፋ እንዲሆን መጠየቁን ተቋሙ ለብስራት በላከው መግላጫ አስታውቋል።

የፌዴራል የጸጥታ መዋቅር አካላት ህጉ በሚፈቅደው መንገድ ከሁሉም ክልሎች የተቀናጀ የጸጥታ ሃይል በማዋቀር በክልሉ ተሰማርቶ የዜጎችን ህይወትና ንብረት ሊታደግ በሚችልበት ቁመና ላይ እንዲገኝ መንግስት ከውሳኔ ላይ እንዲደርስ ምክረ ሃሳብ አቅርቧል።
Forwarded from About education
እንኳን ደስ አላችሁ! የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ156 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆናል፡፡

ለክልላዊ ፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከልም 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል የተዛወሩ ሲሆን የተሻለ ውጤትም የተመዘገበ በመሆኑ ተማሪዎች ፣ ወላጆች በአጠቃላይ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ ፡፡

የፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች በዛሬዉ እለት የተሰራጨ ሲሆን ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ውጤታችሁን በየትምህርት ቤቶቻችሁ መመልከት እንደምትችሉ ይጠበቃል፡፡

@NEAEA_nea
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

>>>ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።<<<<
Forwarded from Deleted Account
[Forwarded from ዣንዣድ]
አስቸካይ ማስተንቀቂያ 😲😲

በስመ አብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን

የፊታችን መጋቢት 29 የሚካሄደው የህዝብ ቆጠራ ምክንያት በማድገግ የተለያዩ ሀይማኖቶች የኦርቶዶርስን እምነት ሊያጠፉ ይፈልጋሉ !!!
እናም ቆጠራ በሚካሄድበት ጊዜ
😟😟 አስተውሉ 😟😟
በክርስቲያን እምነት ውስጥ ከ 35.000 በላይ የሚሆኑ እምነቶች አሉ እናም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ነኝ በማለት እምነታችን እንዳይጠፋ እንጠብቅ።
አስብት እስቲ አሁን የመንግስት ሰራተኖች እረፍታቸው በሰንበት (እሁድ) ነው እረፍታቸው ግን የሀይማኖታችን ቁጥር ካነሰ ይቀየራል በነፃነት መስቀልንም ሆነ ጥምቀትን በጋራ ማክበራችንም ሊቆም ይችላል ሀገራችን ኢትዮጵያ ያለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምንም ነች እናም
አናስብ ሀይማኖታችን እንዳይጠፍ ጥር 11 የሚከበረው የኢየሱስ ክርስቶስ በአልም ሊቀር ይችላል እባካችሁ ሀይማኖታችንን እንጠብቅ
ቢያንስ አንድ ኦርቶዶስ ለጋደኞቹ 10 ሰው ቢልክ ሀይማኖቱን ይጠብቃል
ድንግል ማርያም እናቴ አንቺ ጠብቂን በእግዚአብሔር ስም እለምናችሁለሁ ሁላችሁም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች ናችሁ ቢያንስ ለ10 ሰወች ከተቻለ በጣም ለምትችሉት አድርጉ የሁላችንም ግዴታ ነው በዚ ምክንያት እኛን ለመበታተን ጠላት አድብቶ ይሰራል እኛ ዛሬም ነገም እስክንሞት ድረስ ኦርቶዶክሶች ነን ስለዚ ሸር ለሁሉም ይድረስ ፡፡
Forwarded from . ?
👋ሰላም Just ይህ ከታች የላክንልዎ የእርሶ መለያ ቁጥር ነው ይህን ለ 25 ሰዎች በመላክ እና Start እንዲሉ በመጋበዝ የ 500 ብር የሞባይል ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/AwashBankRefferalBot?start=r04361188530

💞 መልካም እድል 💞
💎Awash Bank💎
የ12ኛ ፈተናን ለመውሰድ 311 ሺህ 421 ተማሪዎች ተመዝግበዋል !

በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ።

በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን ለሚደረገው የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 500 ሺ ታብሌቶች ተዘጋጅተዋል።

በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የተፈታኞች ምዝገባና ውጤት ጥንቅር ዳይሬክተር አቶ ዩሴፍ አበራ እንደገለጹት፤ የአጠቃላይ ሀገር አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ከጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም በኋላ ለመስጠት መርሐግብር ተይዟል።

በዚህ መሰረት የተማሪዎች ምዝገባ መደረጉን ገልጸው፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ብቃት መመዘኛ ፈተና ለመውሰድ እስከ አሁን 311 ሺህ 421 ተማሪዎች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል።

ምዝገባው ከትግራይ ክልል እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን በስተቀር በሁሉ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካሄዱን ገልፀዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ካጋጠመው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ ተማሪዎችን ለመመዝገብ እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

በትግራይ ክልልና በመተከል ዞን ቀደም ሲል ምዝገባ የተጀምረ ቢሆንም ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ መቋረጡን አስታውሰው፤ በእነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ተማሪዎችን ለመመዝገብ የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛልም ብለዋል።

በትግራይ ክልል 80 ያህል ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በመተከል ደግሞ እስከ 14 ትምህርት ቤቶች አሉ ተብሎ ይገመታል፣ በእነዚህ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ምዝገባ ከተደረገ ቁጥሩ ይጨምራል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቀዋል።

@Free_Education_Ethiopia
Stay Safe!