G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
ይሰውረን .....Thingዎች ....

[ለእናንተ የሚጠቅም ሆኖ ስላገኘን ከዘ
@GTutorialclass ቻናል በመውሰድ አጋራናችሁ። ሙሉዉን አንብቡት👌]

📚 ግቢ በጣም አሪፍ ነገሮች የምታሳልፉበት ነው ። በዛውም ልክ ብዙዎች ካለመረዳት ህይወታቸው የሚበላሽበት ነው ። በግቢ መጥፎ ነገሮች እና ባይደርሱብን ባንደርስባቸው የምንመኛቸው ጉዳዮች እንዳስሳለን ።


💡 ዘ... መጫር


📚 የምትጫረው ዝም ተብሎ አይደለም ህግ ካላከበርክ ነው ። በቃ ከአስተማሪ የምትጣለ ከሆነ ...በየሜዳው እንደ ውሻ ሴክስ የምታረግ ከሆነ ና ፕሮክተሮቹ ካገኙ ....ግርግር አስነሳለሁ ካልክ ...ሴት አስተማሪዎችን የምታስቸግር ከሆነ ....ሱሳሱስ ይዞ ገብቶ መጦዝ ....ወይ ከዶርም ልጆች ጋር ፒስ ከሌለህ ....ትጫራለህ ...ካንፓስ በነጥብም ላሽ ልትባይ ትችያለሽ ። ከመጫር ይሰውራቹሁ ነገር ግን የመጫር መነሻዎችን አውቃችሁ ብትጠነቀቁ መልካም ነው ።


💡 ዘ ....ማርገዝ


📚 ሴቶችዬ እንደው አላስችል ብሎ ጭን መክፈት ግድ ከሆነ ኮንዶምሼ አትርሱ...ማርገዝ በጣም አስጠሊ ነው ። የጋሽ ጣሰው ልጅ ተማሪ ቤት ሄዳ ልጅ ታቅፋ መጣች ይባልልኛል .....ህይወትሽ በሙሉ ነው ሚበላሸው እሱ ምን አለበት ሆዱ አያብጥ ፤ አይነፋ .......አበስገበርኩ ራሷ ሳታድግ ልጅ ... ወቸውጉድ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ.....አንቺ ጨለልሽ ይሄ...ካረገዛችሁ ተበላቹሁ በቃ ሉሉ( አስወርዳለሁ ) ሌላ ጣጣ ውስጥ ...ላይፍ ሃርድ ነው ። አንድ ሰሞን ደሞ ፈተና ካለፋችሁ F ራሱ የማይሰጡ ገገሙ ቲቸሮች ስላሉ ትባክናላቹሁ ። ታነቁ ታነቁ ነው የሚላችሁ ። ባካችሁ ህይወታችሁ እንዳይበላሽ ከፈለጋችሁ ...ፍቅር እንኳን ብትጀምሩ ተጠንቀቁ ...ሴቶች ሆዳቹ አበጥ ሲል ጠርጥሩ ቦርጭ እያላቹሁ ጉድ እንዳትሆኑ በኃላ ከምትታነቁ ... በመጨረሻም በመጀመርያ ጥንቃቄ ።


💡 ዘ ...ሃንግ


📚 ግቢ ሳይዘረፉ መምጣት ተኣምር ነው ። በቃ ወይ ስልክ ወይ ላፕቶት ወይ ልብስ ወይ መጀመርያ ላይ በሶ .....ብቻ የሆነ ነገር ሳትደረጉ አትመጡም ። ስልክ ግቢ ውስጥ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል መሸት ሲል ከክላስ ወይ ላይብረሪ ወደ ዶርም መንገድ ላይ ጭለማ ተገን ተደርጎ ወይም ለሽረሽር ወጥታቹ ወደ ካንፓስ ስትመለሱ ግቢ አከባባቢ ቆመው የሚጠብቁ እነ አቶ ግብዳ BODY አሉ ። ዶርምም ሱሱስ የምትጠቃቀም ሰውዬ ካለች ሲጠርባት መንጩ ሊላቹሁ ይችላል ። ልብስ አስጥታቹሁ የምትወዷትን አንድ ያለቻችሁን ማጣትም ብርቅ አይደለም ። በግርግር ግዜ ለመሸሽ ጫካ ከገባችሁ ስልካችሁ ሰታቹ ነው የምታልፎት ። ፍሬሽ የሆናቹ ሰሞን ሰው አትመኑ ፥ ወደ ጫካም ለማየት ብላችሁ አትሂዱ ......ፍሬሽ ሲገባ የአየር ሰዓት ነው ብዙ ጀዋል ይሰረቃል ready ሆነው ነው ሚጠብቋቹሁ ..በር ሳትዘጉ ደሞ እንቅልፍ እንዳይወስዳቹሁ ከፍታቹሁ እንዳትሄዱ ...ዘው ብለው ያገኙትን ይዘው ነው የሚወጡት ......ተጠንቀቁ ..!


💡 እመት ....ሱስ .....!


📚 ሱስ በካንፓስ መጠንቀቅ ያለባቹሁ ነገር ነው ። ሱሰኞች ለገንዘብ ሲሉ ፍሬሾችን ለመከተብ ይጥራሉ ። በምትወዱት ይዢቹሃለሁ ሱስ የሚባል ነገር ለFUn እያላቹሁ ለፍሬንዶች ብላቹሁ ..ለጥናት ምናምን እንዳትሞኩሩት... ራሳችሁን የሲኦል ደጃፍ ነው የምታገኙት ...ሱስ ካለብህ ስልክን ሸጠህ ጫት ትቅምበታለህ ...ከዛ መዝረፍ ትጀምራለህ ትምህርት ይረሳሃል ...ግዜ ካላቹሁ ክበብ ምናምን ተሳተፎ ከሱሰኛ በ billion miles መራቅ ነው ። ዘመናችሁን ወይኔ ካንፓስ ነው የሚያስብሏቹ ። ጠንቀቅ ነው ።


💡 ጋሽ ...ራስን ማጥፋት ...!


📚 ብዙ ቴንሽናሞች ፈተና ውጤት ሲበለሽባቸው መታነቅ ከፎቅ መፈጥፈጥ ይቀናቸዋል ። ለምን የF መኣት ...የ incomplete መኣት አይደረደርም ... ሁሉም ሲቀር ይቀራል ምንም ሁኑ በቃ ...ሞታቹሁ ሲኦል ከምትገቡ ግን ይሻላል ። በቻላችሁ ሰግጣችሁ ለውጤት ስሩ .. ነገር ግን ግሬድ ተበላሽቷል ብላቹሁ ገመድ መግዛት ...በረኪና መጠጣት የፋራ ነው የምር ። ፏንቃ ያዘኝ ብላችሁ ....ካልሞትኩ ወፍ .....ህንድ በትምህርት ጭንቅት (ቴንሽን) ምክንያት ከፎቅ በመፈጥፈጥ በአለም አንደኛ ነች ። ህንዶች ለዛ ብለው የሰሩት ያበደ ፊልም አለ ። The Three Idiots (ሶስቱ ደደቦች ..) ልታዩት የሚገባ የአሚር ከሃን ፊልም ነው ። ስለ ትምሮ ያላቹሁ አመለካከት ይቀየራል ፊልሙን ፈልጌ በቻናሉ እለቀዋለሁ ። የምር ትምህርት ሳትጀምሩ እዩት ።


💡 አጅሬ ....ፖለቲካ ...


📚 ካንፓስ የካፌ ካልሆነ በቀር ...ሰልፍ ስታዮ ...ቀነኒሳ እንዳይቀድማቹሁ አርጋቹሁ ሩጡ ። ለምን የሴት ልጅ ግርዛት ይቁም ...የሚል ሰልፍ አይሆንም አትሳተፎ ....በምን ፍጥነት ተቀይሮ አንገታችሁን እንደሚገርዝላቹ አታውቁም ....ከፓተሊካ ራቅ ነው ። ጀዋር .....ኮ ....ምን አገባኝ .... አብይ....ምንአገባኝ .....ምርጫ ምን አገባኝ ...... ሆሆ ከዚኛው ትሪሊየን ማይል ነው መራቅ ያለባቹሁ .....ይሄ ሞት ቅርብ የሆነበት ሰፈር ነው ። ወገብ አገዳችሁን ፤ ጥርሰ ፍንጭታችሁ ነው ሚሏቹሁ ....ከሞትማ ራቅ ነው ። ግቢ የሰውነት አቋማችሁን እንጂ የፓለቲካ አቋማችሁን ለራሳቹሁ ራሱ እንዳትናገሩ .....ኤርፎን ያዙ ልክ ወሬው ፓለቲካ ሲሆን ጆሮዎኣቹ የምትሰኩት ...ከፓለቲካ የጩባውን ዘፈን ነው ሚሻላችሁ ።


💡 ዘ.....መጣላት


📚 ካንፓስ በፍፁም ጫማ መለካካት የሌለብን ማስቀየም የሌለብን ሰዎች አሉ ። የመጀመርያው ከLocal ጋር ነው ማለትም ጎንደር ልጅ ሆነው ጎንደር የተመደቡ ሀገራቸው የሆነ .....በቃ ሀገሩን ስለሚያቁት አሳራችሁ ነው ሚያበሏቹሁ ከማ ጋር እንደምትሳፈጡ እወቁ ። ቢናገራቹሁም ቻል ረብሽ በተነሳ ቁጥር ደብቁኝ ከማለት ይሻላል ። ሌላው ዶርም ሜት ነው ። የዶርም ልጆች ምንም ጠባይ ቢኖራቸው አትቀያየሙ LOVE ግድ ነው ። ከተቀያየማቹሁ እቃ ሊያዘርፋችሁ ምናምን ይችላል ። ዶርም ነቆራ ካለ ለማረፍም አይመችም ....አትጣሉ በምንም። proctor ("ጠባቂዎችን) በፍቅር ያዙ ይጠቅማቹሃል .... ከአስተማሪም እንዳትጣሉ ....ለሴት ብላቹሁ ሌላ ሙዱ ውስጥም እንዳትገቡ ..20ሺ ሌሎች አሉ ኣ ምን በወጣቹሁ ትጣላላችሁ ....!መርጣችሁ ነው የምታፎነቅቁት ...አብሽር ..!
@GTutorialclass
1
ficha-29-more-relative-clauses.pdf
444.7 KB
📚 Relative Clause - Worksheet V

📚 በጣም ጠቃሚ ጥያቄዎችን የያዘ ነው። የሚጠቅማችሁን እየመረጣችሁ መስራት ነው። ፈተናችሁ ከዚህ አይዘልም በለቀኩላችሁ worsheet መሰረት ስለሆነ የሚወጣው በደንብ ስሩት።

@GTutorialclass
relative_clauses_exercise_1.pdf
66.2 KB
📚 Relative Clause - Worksheet VI

📚 በጣም ጠቃሚ ጥያቄዎችን የያዘ ነው። የሚጠቅማችሁን እየመረጣችሁ መስራት ነው። ፈተናችሁ ከዚህ አይዘልም በለቀኩላችሁ worsheet መሰረት ስለሆነ የሚወጣው በደንብ ስሩት።

@GTutorialclass
relative_clauses_exercise_2.pdf
59.7 KB
📚 Relative Clause - Worksheet VII

📚 በጣም ጠቃሚ ጥያቄዎችን የያዘ ነው። የሚጠቅማችሁን እየመረጣችሁ መስራት ነው። ፈተናችሁ ከዚህ አይዘልም በለቀኩላችሁ worsheet መሰረት ስለሆነ የሚወጣው በደንብ ስሩት።

@GTutorialclass
rc005-relative-clauses.pdf
46.6 KB
📚 Relative Clause - Worksheet VIII

📚 በጣም ጠቃሚ ጥያቄዎችን የያዘ ነው። የሚጠቅማችሁን እየመረጣችሁ መስራት ነው። ፈተናችሁ ከዚህ አይዘልም በለቀኩላችሁ worsheet መሰረት ስለሆነ የሚወጣው በደንብ ስሩት።

@GTutorialclass
defining-and-non-defining-relative-clauses.pdf
856 KB
📚 Relative Clause - Worksheet 9

📚 በጣም ጠቃሚ ጥያቄዎችን የያዘ ነው። የሚጠቅማችሁን እየመረጣችሁ መስራት ነው። ፈተናችሁ ከዚህ አይዘልም በለቀኩላችሁ worsheet መሰረት ስለሆነ የሚወጣው በደንብ ስሩት።

@GTutorialclass
relative-clauses-1.pdf
32.8 KB
📚 Relative Clause - Worksheet 10

📚 በጣም ጠቃሚ ጥያቄዎችን የያዘ ነው። የሚጠቅማችሁን እየመረጣችሁ መስራት ነው። ፈተናችሁ ከዚህ አይዘልም በለቀኩላችሁ worsheet መሰረት ስለሆነ የሚወጣው በደንብ ስሩት።

@GTutorialclass
relative_clauses_exercise_4.pdf
66.6 KB
📚 Relative Clause - Worksheet 11

📚 በጣም ጠቃሚ ጥያቄዎችን የያዘ ነው። የሚጠቅማችሁን እየመረጣችሁ መስራት ነው። ፈተናችሁ ከዚህ አይዘልም በለቀኩላችሁ worsheet መሰረት ስለሆነ የሚወጣው በደንብ ስሩት።

@GTutorialclass
AAU Civics exam(2).docx
32.8 KB
📖Civics 185 Choice Questions

📓እነዚህን ጥያቄዎች ከሰራቿቸው ሌላ መስራት አይጠበቅባችሁም👌

በተጨማሪ ደግሞ Civics Course እየከበዳችሁ ላላችሁ ተማሪዎች You tube ላይ Videoዎችን ተመልከቱ [ለምሳሌ እንደነ Crash Course ያሉት ቻናሎች አሪፍ በሆነ መንገድ ነው የሚያብራሩት። Search እያረጋችሁ እዩ👌

@GTutorialclass
Ch~6 (1).pdf
244.3 KB
📓Emerging Technology

📚Chapter 3 4 5 6

📚 Short note Final Exam ላለባቹ ይሄ በቂ ነው ።

@GTutorialclass
emerging-t-mid-final-exam.pdf
2 MB
📓Emerging Technology Mid and Final Exams

📓It contains +3 universities

@GTutorialclass
pythonlearn.pdf
2.3 MB
📓የAAU ተማሪዎች ቤተሰቦቻችን ቀጣይ ላለባችሁ Final Exam እቺን የPython Module ማንበብ እንዳትረሱ።

📖ጥያቄዎቹን ስሯአቸው፣ ፈተና ላይ ሊመጡ ስለሚችሉ።

ሌሎቻች የEngineering ተማሪዎችም ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ።

©A+ Tutorial Class
📚 በጣም ትንሽ ተማሪ ብቻ ነው መልስ የላከው🤸‍♂🤸‍♂። ገብቷችሗል ማለት ነው አብዛኞቻችሁ😊። እሱ ነው የሚያስፈልገው😉

📚 ለማንኛውም Final ፈተና በዚህ መልክ ስለሆነ የምትፈተኑት እንዴት መስራት እንዳለባችሁ ልንገራችሁ። ከ መጀመሪያው ጥያቄ እንጀምር።

#1) The man_____ you meet in the church is my brother.

🎯The man(human being, object) + whom + you(pronoun) ... ስለዚህ መልሱ Whom ነው።

#2) The Woman___ simplicity and discipline influnced me much is a greater social worker.

📚 Whose + noun .... so, whose + simplicity and discipline(noun). ስለዚህ መልሱ whose ነው።

#3) The speech____ I heard at the meeting excited me so much.

📚 ባለፈው ስንማር which ለ ነገሮች(thing) ሁኖ ነው የሚያገለግለው ተባብለናል። ይህ ዐ.ነገር የሚያወራው The Speech ስለሚለው ነው። The Speech ደግሞ thing ነው። ስለዚህ በ which ይገለፃል። ዐ.ነገሩ ምንም comma አልተጠቀመም ስለዚህ defining clause ነው። ስለዚህ that ን በ which ቦታ መጠቀም እንችላለን። ስለዚህ መልሱ which/that ነው።

#4) This is the girl___ I talked about.

📚The girl(human being, object) + whom + I(pronoun). ስለዚህ መልሱ whom ነው።

#5) The boy_____ cheated is my brother.

The boy(human being, subject) + who + cheated(verb). ስለዚህ መልሱ who ነው።

#6) The house in _ I am staying is very nice.

📚 እዚጋ ብዙዎቻችሁ መልሱ whom ነው የምትሉት በእርግጠኝነት ምክንያቱም whom + pronoun(I) በሚለው ቀመር ወይም preposition(in) + whom በሚለው ቀመር። ልክ ናችሁ ኮ ግን አንድ የረሳችሁት ነገር አለ። whom የሚያገለግለው ለ ሰው ፍጥረት(human being) ብቻ ነው። እንደውም ላስታውሳችሁ

Human being(object) + whom + pronoun. ይህን ፎርሙላ ነግሬያችሗለሁ።

ስለዚህ whom ለሰው ፍጥረት ብቻ ነው የሚያገለግለው። ነገር ግን ይህ ዐ.ነገር የሚያወራው "the house" ስለሚለው ነው። the house የሰው ፍጥረት አይደለም ግዑዝ አካል ነው😳። ስለዚህ whom ን አንጠቀምም🤸‍♂🤸‍♂። ባለፈው አንድ ፎርሙላ ነግሬያችሗለሁ

preposition + whom....(for human being).

preposition + which....(for things).

human being(subject) + who + verb.
Things(subject) + which + verb.

Humam being(object) + whom + pronoun.
Things(object) + which + pronoun.

🤸‍♂ እነዚህ ፎርሙላ ምጥጥ አድርጋችሁ ያዙ።

ለማንኛውም መልሱ which/that ነው የሚሆነው።

#7) The girl__ father died in the accident wanted to marry me.

Whose + noun.... whose + father(noun)....:possession.... ስለዚህ መልሱ whose ነው።

#8) My friend, __ I always respect, does not try to understand me.

📚 My friend(human being, object) + whom + I (pronoun) ... ስለዚህ መልሱ whom ነው።

#9) My sister, _ is a doctor in Italy, wanted to come back to Ethiopia.

📚My sister(human being, subject) + who + verb.... ስለዚህ መልሱ who ነው። ታዲያ እዚጋ that ን መጠቀም አንችልም በ who ቦታ። ለምን?? መልሱት!!

ጨርሱት...በቀጣይ ስለ Modal verbs እናያለን። Dani ነኝ🤸‍♂🤸‍♂🤸‍♂😁😁

@GTutorialclass
👍1
AAU_ANTHOLOGY_FINAL_Exam.pdf
1.3 MB
📓Anthropology_AAU Last_Year

📖ፋይናል ፈተና ላለባችሁ ተማሪዎች ይጠቅማችኋል።

@GTutorialclass
📚 Communicative English Skill II

📚 Chapter Three

📚 Grammar Focus - Modal Verbs.

🙌 ተወዳጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ። ዛሬ የምንማረው ስለ Modal Verbs ነው። ፈተና ላይ የሚያምታቱ ሊሆኑ ይችላሉ ግን የ concept ተማሪ ይሰራዋል። እኔም በቻልኩት መጠን ፅንሰ ሀሳቡን ለማስረዳት እሞክራለሁ። አብራችሁኝ ቆዩ። Dani ነኝ😊። Dani ይወዳችሗል😘😘😘😘❤️❤️

📚 በርግጥ Modal Verbs ለእናንተ አዲስ አይደሉም። ነገር ግን አንዳንድ አዳዲስ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለማንኛውም በርካታ Modal Verbs አሉ። አገልግሎታቸውን እንመልከት😊

🎯 Express Possibility

📚 Possibility ማለት ሊሆን የሚችል ክስተት(ድርጊት) ማለት ነው። ታዲያ

👉አሁን ላይ "ሊሆን የሚችል ክስተት ይኖራል"(Present Possibility).
👉 ወደ ፊት "ሊሆን የሚችል ክስተት ይኖራል"(Future Possibility).
👉 ከአሁን በፊት "ሊሆን የሚችል ክስተት" ይኖራል(Past Possibility).

😊 ታዲያ ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስት possibility ዎችን ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው Modal verbs አሉ። እነማን ይሆኑ🤔

📚 May , Might and Could are used to express present or future possibility.

📚 May/Might/Could + perfect infinitive(have + v3) are used to express past possibility.

😎 እስኪ እንመሰጥበት በትንሹ

🌹 May/Might/Could

📚 ቅድም እንደነገርኳችሁ May, Might እና Could አሁን ላይ ሊሆን ስለሚችል ክስተት(present possibility) ን እና ወደ ፊት ሊሆን ስለሚችል ክስተት(future possibility) ን ለመግለፅ ያገለግሉናል። ታዲያ ሊሆን የሚችሉ ክስተቶችን ስንገልፅ

📌 May - 50% ሊሆን የሚችል ክስተትን( perhaps 50% chance) ለመግለፅ ያገለግላል።

📌 Might - 30% ሊሆን የሚችል ክስተትን( perhaps 30% chance) ለመግለፅ ያገለግላል።

📌 Could - ከ 30% በታች ሊሆን የሚችል ክስተትን( perhaps less than 30% chance) ለመግለፅ ያገለግላል።

🙌 እንዴ አጠቃላይ ግን ሶስቱም ማለትም May, Might and Could የሚያገለግሉት present or future possibility ን ለመግለፅ ነው። ምሳሌዎችን እንመልከት😁

🌹 Example 1

📚 የ ዶርም ጓደኛህ ይህ መፅሀፍ የማን ነው? ብሎ ጠየቀህ። አንተ የማን እንደሆነ አላወክም። ግን እርግጠኛ ባትሆንም የ በረከት ሊሆን ይችላል(present possibility) ብለህ አስበሀል። So,

👨‍🏫ጓደኛህ - Whose book is this?

👨‍🏫 አንተ - I am not sure. It may be Bereket's book.(perhaps 50% it is Bereket's book.)

👨‍🏫 አንተ - I am not sure. It might be Bereket's book.(perhaps 30% it is Bereket's book.)

👨‍🏫 አንተ - I am not sure. It could be Bereket's book.(perhaps less than 30% it is Bereket's book).

👆 የሶስቱም ትርጉም - የ በረከት መፅሀፍ ሊሆን ይችላል።

👆 አያችሁ ኣ ሶስቱም present possibility ን ነው የሚገልፁት። present possibility መሆኑን እንዴት አወቅን?? ምክንያቱም መፅሀፉ የማን ነው?? ብሎ ሲጠይቅ ስለ አሁን ነው የሚያወራው። መፅሀፉ የማን ነበር? ብሎ ቢጠይቅ ደግሞ ስለ past ነበር የሚያወራው።

📚 anyways ግን ሶስቱም አሁን ላይ ሊሆን ስለሚችል ክስተት ን ነው የገለፁልን ልዩነታቸው degree of possibility ነው። ሶስቱንም መጠቀም እንችላለን።

📌 Example 2

አሁን ላይ ግቢ ነው ያላችሁት። እና ከሳምንት በሗላ ፋይናል ፈተና ትጨርሳላችሁ እንበል ለ ዕረፍት ወደ ቤተሰብ ለመሔድ አስባችሗል። ከዛ የዶርም ጓደኛሽ መቼ ነው ወደ ቤተሰብ የምትሔጂው ብላ ጠየቀችሽ። አንቺም ገና አልወሰንሽም ግን ከ 10 ቀን በሗላ የመሔዱ ሀሳቡ አለሽ። ገና አልወሰንኩም ግን ከ 10 ቀን በሗላ ልሔድ እችላለሁ(future possibility) አልሻት። ስለዚህ

👩‍🏫 ጓደኛሽ - When will you go to your family?

👩‍🏫 አንቺ - I haven't decided yet. I may go to after 10 days.(perhaps 50% I will go to after 10 days ማለት ነው)

👩‍🏫 አንቺ - I haven't decided yet. I might go to after 20 days.( perhaps 30% I will go to after 10 days.)

👩‍🏫 አንቺ - I haven't decided yet. I could go to after 10 days.( perhaps <30% I will go to after 10 days).

👆 የሶስቱም ትርጉም - ከ 10 ቀን በሗላ ልሔድ እችላለሁ ማለት ነው።

👆 አያችሁ ኣ ሶስቱም future possibility ን ነው የሚገልፁት። future possibility መሆኑን እንዴት አወቅን?? ከ 10 ቀን በሗላ(future) ሊሆን የሚችል ክስተትን ነው የሚገልፀው።

📚 anyways ግን ሶስቱም ወደ ፊት ላይ ሊሆን ስለሚችል ክስተት ን ነው የገለፁልን ልዩነታቸው degree of possibility ነው። ሶስቱንም መጠቀም እንችላለን።
🎯 Example 3

📚 ምሳሌ "ማታ ዝናብ ሊዘንብ ይችላል" ብትል

👉 It may/might/could rain during the night.(future possibility).

📚 ምሳሌ " አሞህ ሊሆን ይችላል"

👉 You may/might/could be sick.

🙌 ተወዳጆች ሆይ ታዲያ እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር አለ። እስካሁን ያየነው positive sentence ላይ ነው። Negative sentence ወይም Negative present possibility or Negative future possibility ን ለመግለፅ የምንጠቀመው እነማንን ነው😿??

😊 May not and Might Not are used to express negative present or future possibility. ግን Could not Negative possibility ን አይገልፀልንም።

☺️ ምሳሌ- "ማታ ዝናብ ላይዘንብ ይችላል" ብትል

👉 "It may not rain during the night."
👉" It might not rain during the night."
👉 It could not rain during the night." ግን አይባልም

🙌 እሺ አሁን ደግሞ ስለ past possibility እንመልከት።

🌹 May/Might/Could + Perfect infinitives.

📚 May/Might/Could + Perfect infinitives(have + v3) are used to express past possibility.

🎯 ከ አሁን በፊት(past) ሊሆን የሚችል ክስተትን ለመግለፅ May/Might/Could + perfect infinitives እንጠቀማለን።

🎯 ለምሳሌ :- የዶርም ሎከርህን ስትከፍት ደብተርህን አጣኸው። ከዛ ደብተሬን ማን ወስዶት ነው ብለህ ጠየከው ጓደኛህን። እሱም አላወኩም ምን አልባት ቢኒያም ወስዶት ሊሆን ይችላል አልከው።

🎯 ስለዚህ "ቢኒያም ደብተሩን ወስዶት ሊሆን ይችላል" ስንል ከአሁን በፊት(past) ሊከናወን የሚችል ድርጊት ነው። እንዴት😒 ምክንያቱም ደብተሩ አሁን ላይ የለም። ስለዚህ የደብተሩ መወሰድ ድርጊት የተከናወነው ከአሁን በፊት(past) ነው። ነገር ግን ቢኒያም ስለምወሰዱ 100% እርግጠኛ አይደለንም ምክንያቱም ሲወስድ ስለላየን። ነገር ግን እሱ ሊሆን ይችላል ብለን ጠረጠርን። ስለዚህ

🔆 ድርጊቱ የተከናወነው ማለትም የደብተሩ መወሰድ ከአሁን በፊት ነው(past)::

🔆 ቢኒያም ሊሆን ይችላል የወሰደው(possibility)::

😊 ስለዚህ past possibility ነው። ይህን past possibility የምንገልፀው በ May/might/could + perfect infinitives(have + v3) ነው። so,

📌 Biniam may have taken the execersise book.
📌 Biniam might have taken the execrsise book.
📌 Biniam could have taken the execersise book.

👆 ሶስቱም ይቻላል። ትርጉማቸውም "ቢኒያም ወስዶት ሊሆን ይችላል" ማለት ነው። ግን ቢኒያም ይውሰድ አይውሰድ 100% እርግጠኛ አይደለንም። ከበደ ጫላ ወይ ሌላ ወስዶት ሊሆን ይችላል።

😿 ሌላ ምሳሌ :- እህትህ ወደ አዲስ አበባ ሔዳለች። እና ግን በምን ትራንስፖርት እንደሔደች አላወክም። እና ጓደኛህ እህትህ በምን ወደ አአ ሔደች ብሎ ጠየቀህ። አንተም አላወኩም ግን በ plane ሊሆን ይችላል አልከው።

🎯 ስለዚህ "በ plane ሔዳ ሊሆን ይችላል" ስንል ከአሁን በፊት(past) ሊከናወን የሚችል ድርጊት ነው። እንዴት😒 ምክንያቱም ወደ አአ ሔዳለች ምናልባት ከ ሳምንት በፊት ምናምን ብቻ ግን መሔዷ ከአሁን በፊት የተከናወነ ድርጊት ነው። ስለዚህ ወደ አአ መሔዷ ከአሁን በፊት(past) ነው። ነገር ግን በ plane ወደ አአ ስለመሔዷ 100% እርግጠኛ አይደለህም ምክንያቱም ስላላወክ። ስለዚህ

🔆 ድርጊቱ የተከናወነው ማለትም ወደ አአ መሔዷ ከአሁን በፊት ነው(past)::

🔆 በ plane ሊሆን ይችላል የሔደችው(possibility)::

😊 ስለዚህ past possibility ነው። ይህን past possibility የምንገልፀው በ May/might/could + perfect infinitives(have + v3) ነው። so,

📌 She may have gone by plane.
📌 She might have gone by plane.
📌 She could have gone by plane.

👆 ሶስቱም ይቻላል። ትርጉማቸውም "በ plane ሔዳ ሊሆን ይችላል" ማለት ነው። ግን 100% እርግጠኛ አይደለህም። ምናልባትም በ Bus or Minibus ሔዳ ሊሆን ይችላል።

😁 እሺ በቀጣይ ደግሞ ሌሎቹን እናያለን። A+ ይለያል🤸‍♂🤸‍♂😂


@GTutorialclass
📚 Communicative English Skill II.

📚 Chapter Three

📚 Grammar Focus - Modal Verbs For Giving advice.

🙌 ተወዳጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ እንዴት ናችሁ። በባለፈው ትምህርታችን ስለ Expressing possibility ተምረናል። ዛሬ ደግሞ ስለ Modal Verbs for giving advice እንማራለን። እስኪ እንማረው😊

🎯 Giving Advice

📚 ሁላችሁም እንደምታውቁት Giving Advice ማለት ምክር መስጠት ማለት ነው። ታዲያ ምክር ስንሰጥ ምክር መስጠታችንን ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው Modal Verbs አሉ። ታዲያ ምክር ለመስጠት የምንጠቀምባቸው Modal Verbs የትኞቹ ናቸው🤔

📚 Should , Ought to and Had better are used to give advice.

🎯 ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩት Should, Ought to እና Had better የተባሉት Modal verbs ምክረ ሐሳብ ለመስጠት የሚያገለግሉ ናቸው። ምሳሌዎችን እንመልከት😎

📚 ለምሳሌ አንቺ የ እንግሊዝኛ ቋንቋን አቀላጥፈሽ መናገር ትፈልጊያለሽ። ነገር ግን መናገር አትችይም። ከዛ ጓደኛሽን "እንግሊዝኛ አቀላጥፌ መናገር እፈልጋለሁ ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለሽ ጠየቅሻት። ጓደኛሽም "በየቀኑ ማውራት ብትለማመጂ(practise) ብታደርጊ ጥሩ ነው" ብላ ሞክሯን ሰጠችሽ። ስለዚህ😎

👩‍🏫 You - I want to speak English fluently. What shall I do?

👩‍🏫 You friend - You Should practice speaking everyday.
👩‍🏫 You friend - You ought to practise speaking everyday.
👩‍🏫 Your friend - You had better practise everyday.

👆 ስለዚህ የ ጓደኛሽ ምክር ልገሳ በ should , ought to ና had better ይገለፃል ማለት ነው።

📚 ሌላ ምሳሌ አንድ ሰው በተደጋጋሚ አልኮል መጠጥ ሲጠጣ ብታየው እና "መጠጣት የለብህም ለጤናህ ጥሩ አይደለም" ብለህ ምክር ለመስጠት ብትፈልግ

🎯 You should stop drinking alcohol.
🎯 You ought to stop drinking alcohol.
🎯 You had better stop drinking alcohol.

👆 ስለዚህ የአንተ ምክረ ሐሳብ በ should, ought to እና had better ይገለፃል ማለት ነው::

🎯 Had better

📚 እሺ አሁን ደግሞ አንድ ነገር ልንገራችሁ። Should, Ought to እና Had better አገልግሎታቸው ተመሳሳይ ነው። ሁሉም ምክር ለመስጠት ነው የምንጠቀምባቸው። ነገር ግን ጠንከር ያለ ምክር ለመስጠት ስንፈልግ ደግሞ Had better ን እንጠቀማለን።

📚 Had better can be used for emphatic, stronger advice.

📚 ስለዚህ አፅንኦት ያለው ወይም ጠንካራ ምክር ለመስጠት Had better ን እንጠቀማለን። ምሳሌ

📚 የ ዶርም ጓደኛህ "አሞኛል ምን ባደርግ ይሻለኛል" ብሎ ሲጠይቅህ አንተም "ክሊኒክ ብትሔድ ጥሩ ነው" ብለህ ጠንከር ያለ ምክር መስጠት ብትፈልግ Had better ን ትጠቀማለህ ማለት ነው።

👨‍🏫 Your friend - I am sick. What shall I do?
👨‍🏫 You - You had better go to clinic.

👆 ከዚህ ዐ.ነገር ላይ should ንም ought to ንም መጠቀም እንችላለን ግን ምክራችን ጠንካራ መሆኑን ለመግለፅ ነው በተለዬ መልኩ had better ን የተጠቀምነው።

📚 እሺ እስካሁን Should , Ought to እና Had better ን በ positive statement ነበር ምሳሌ ያየነው። አሁን ደግሞ Negative statement ላይ ያላቸው ፎርም ምንድን ነው?

🎯 Should not

📚 ስለዚህ should ለ positive statement ሲሆን should not ደግሞ ለ negative statement ይሆናል። ምሳሌ

🎯 You should study hard.(positive statement).

🎯 You should not drink alcohol.(negative statement).

🎯 Ought not to

📚 ስለዚህ ought to ለ positive statement ሲሆን ought not to ደግሞ ለ negative statement ነው። አስተውሉ👇

👉 Ought not to (ነው የሚባለው)
👉 ought to not(በፍፁም አይባልም ስህተት ነው። ፈተና ላይ እንዳትሸወዱ)።

🎯 You ought to study hard.(positive statement).

🎯 You ought not to drink alcohol.(negative statement).

🎯 You ought to not ግን አይባልም። Gramatically ስህተት ነው። ፈተና ላይ ስለሚያወጡት ትኩረት ስጡት።

🎯 Had better not

📚 ስለዚህ had better ለ positive statement ሲሆን had better not ደግሞ ለ negative statement ነው። ምሳሌ

🎯 You had better study hard.(positive statement).

🎯 You had better not drink alcohol.(negative statement).

📚 የዛሬው ክላስ በዚሁ ይቋጫል። Should , Should not, Ought to, Ought not to እና Had better, Had better not ምክርን ለመስጠት የሚያገለግሉ Modal verbs ናቸው።

@GTutorialclass
📚 Communicative English Skill II.

📚 Chapter Three.

📚 Grammar Focus - Modal Verbs.

☺️ ተወዳጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ። በባለፈው ትምህርታችን ስለ expressing possibility እና giving advice ተምረናል። ዛሬ ም ስለ ሌሎች የ Modal verbs አገልግሎት እንማራለን።

🎯 Asking for Permission

📚 Permission ማለት ፈቃድ ማለት ነው። አንድ ነገር ለማድረግ ከሆነ አካል(ከባለቤቱ) ፈቃድ መጠየቅ asking for permission ይባላል። ታዲያ ፈቃድ መጠየቃችንን ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው Modal verbs አሉ። እነርሱም

🎯 Can, Could and May are used with I and We to ask for permission in the present or future.

🎯 ይህ ማለት Can/Could/May + I/we!

📚 ስለዚህ Can , Could ና May ን ተጠቀምን ፈቃድ መጠየቅ እንችላለን ማለት ነው። ታዲያ Can, Could ና May ን ተጠቅመን ፈቃድ ስንጠይቅ ከ Can , ከ Could ና ከ May ቀጥሎ የሚመጡት I ና we ናቸው። Examples

🌹 Can I use your cell phone?
🌹 Could we go to a cinema house?
🌹 May I borrow your pen?

🎯 Make a request

📚 request ማለት ሰዎች አንድ ነገር እንዲያደርጉልን ወይም ውለታ እንዲውሉልን መጠየቅ ማለት ነው። ታዲያ ያ ሰው የሆነ ውለታ እንዲውልልን ወይም የሆነ ነገር እንዲያደርግልን በምንጠይቅበት ጊዜ የምንጠቀማቸው Modal verbs አሉ። እነርሱም

🎯 Can, Could and Would ናቸው። ስለዚህ Can, Could ና Would ን ተጠቅመን ሰዎች አንድ ነገር እንዲያደርጉልን ትህትና በተሞላበት መልኩ መጠየቅ እንችላለን።

📚 ለምሳሌ ክላስ ውስጥ ስኪብርቶ አልቆብህ መምህሩን " ስኪብርቶ አውሰኝ" ብለህ ለመጠየቅ👇

🌹 Would you lend me your Pen?
🌹 Could you lend me your pen?
🌹 Can you lend me your pen?

ብለህ መጠየቅ ትችላለህ። Would > Could > Can (degree of politeness).

📚 በቀጣይ ስለ Deduction ሰፋ ያለ ትምህርት ለመማር እንሞክራለን😊። መልካም ጊዜ❗️

@GTutorialclass
© Your Sucess is guaranted with @GTutorialclass