G-Tutorialclass
811 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
356 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
ከመሸወዳችሁ በፊት ይሄን አንብቡት ❗️❗️

📚Freshman course ላይ የ A+ ሚስጥር!!

📌በ ቀለሜ የ Telegram Channel 👉@Gtutorialclass ተፅፎ የቀረበ።

Highschool ላይ ጓበዝ ተማሪ ልትሆኑ ትችላላችሁ ኧረ አንደውም Entrance result Above 500 ወይም 600 አምጣችሁ የኛ ጀግና💪🏾 ተብላችሁ ሊሆን ይችላል ግን ይሄ ዉጤት እና በፊት የነበራችሁ የ ማንበብ strategy ለ Freshman course guarantee ይሆናችኋል ማለት አይደለም ። 620 አምጥቶ Freshman course ላይ ስንት የሚዋዥቅ አለ መሰላችሁ። ይሄን በ photo አስደግፌ ማሳየት አችላለሁ ....በ አጭሩ @Gtutorialclass
✔️Campus ላይ ተቀጥቅጣችሁ ካነበባችሁ GPA 3.5 .....or 3.8 ልታመጡ ትችላላችሁ። ግን
✔️ተቀጥቅጣችሁ አንብባችሁ አራዳ ከሆናችሁ እመኑኝ 4 ታመጣላችሁ። አራዳ ሁኑ ስልህ እንዴት መሠላችሁ ... ወጣት ናችሁ ብዙ ነገሮች ይፈትኗችኋል ግን ለሁሉም የተለያየ ጊዜ ሰጣችሁ ሚቀድመውን አስቀድማችሁ 4 ሊያስመጣላችሁ የሚችሉትን መንገዶች በሚገባ እወቋቸው እና ተጠቀሟቸው እያልኩ ነው። ያኔ እንደናንተ አራዳም ጭስም የለም😎@Gtutorialclass
"በ ገለጠ ሳይሆን በተገለጠለት ነው" ሲባል አልሰማክም?.... ወንድሜ Campus ላይ በትምህርትህ ንቁ መሆን አለብህ ዝም ብለክ ስለገገምህ ምንም አታመጣም። አንችም እንደዛው ....... እና ምን አይነት መንገድ ልከተል? እያላችሁ ይሆናል በቃ እነዚህን 4 ወርቃማ ህግጋት ተከተሉ😊

1⃣ :- Universityያችሁን አጥኑ!!

እናንተ ያላችሁበት university የሚያስተምሩበት ሂደት ምንድን ነው? መምህራንስ እውቀታቸው፣ ፀባይአቸው ምን ድረስ ነው?...Universityዉ ሃርድነቱስ በ ዉጤት ድርድር አለው? ስንተኛው Generation ነው? @Gtutorialclass universityያችሁን እንደ እጅህ መዳፋችሁ ማወቅ አለባችሁ። በ ተለይ Universityዉ first Generation ከሆነ ጠጠር ይላል ልብ በሉ። እነዚህን ነገሮች ካወቃችሁ በ ደንብ ማንበብ አንዳለባችሁ ይጠቁሟችዋል።

2⃣:- ምታነቡትን ምረጡ!!

አንዳንድ ተማሪወች ያሳዝኑኛል። መቀበሪያ ሳጥን ሚያክል Reference Book ይዘው የሚያነቡትን ዋና ፍሬ ሀሳብ ሳይረዱ ዝባዝንኬውን በማንበብ Energy እና Time ይገላሉ.....አንዳንዶች ደግሞ Module በማንበብ ማይማሩትን አፈስገፈሱን ሁላ በማንበብ አዕምሮአቸውን Bussy የያደርጉታል......ወንድም ዓለም!! እንደ ጓደኞችህ ማንበብ ያለብህን አንበህ በትርፍ ስሀትህ መዝናናት አያምርህም? አንችስ ለምን በዝባዝንኬ ትዝጊያለሽ?
እርግጥ ብዙ ነገሮችን ማንበብ እውቀት ያስገኛል ግን አሁን እያወራን ያለነው Grade እንዴት እንስቀል? ነው።... ይች አባባል በደንብ ትገልጠዋለች " Don't study hard be smart " እና ምናባህ እናንብብ?🙊 እያላችሁ ይሆናል እኔ ደግሞ Handout እላችኋለሁ።😊@Gtutorialclass

📄 Handout😘 በየአንዳንዱ Course አስተማሪዎች ተመካክረው ከ Module ላይ አፈስገፈሱን አሳጥረው፣ ሚቆረጠውን Portion ቆርጠው፣ እጥር ምጥን አድርገው ለዩኒቨርስቲው የሚመጥነውን ቅመም የሆነች Note ሚያሰፍሩባት Document ናት። (ከ ዩኒቨርስቲ የኒቨርሲቲ ይለያያል..).... ሲጀመር አስተማሪወች የሚመክሩት ካለን ጊዜ አንጻር handout እንድናነብ ነው ፈተናውም ከ 90% በላይ የሚመጣው እዚሁ ላይ ነው በተለይ ሚሸመደዱ ትምህርቶች።

❗️እንደ Maths ና physics የ Calculation ትምህርቶች ግን Module አንዳንዴም Reference ያስፈልጋል።

3⃣ :- የ ሚያስተምራችሁን መምህር አጥኑት!!

በሚያስተምርበት ጊዜ በንቃት ተከታተሉ!!

ሰውየው ምንአይነት አስተማሪ ነው?
Module ላይ ያለችውን ሽምድድ አድርጎ ብቻ መጥቶ ለናንተ ይነግራችኋል? እንደዛ ከሆነ Module ላይ ግግም በሉ ምክኒያቱም ይህ ሰውየ ከ Module ሌላ ሚያውቀው ነገር የለም ስለዚህ ጥያቄወቹን አንዳለ ቃል በቃል Moduleሉ ላይ ነው ሚያወጣቸው። ወይስ ሰውየው ስለ Google ይሰብካችኋል? አንዳንዴ " Thanks to internet ልጆች Googleን ተጠቀሙ ሁሉ ነገር እኮ አለ።" ይላል? እንደዚ ከሆነ እሱ በሚያስተምርበት ዙሪያ ጥያቄዎችን ከ Google እየጓለጓላችሁ መፍለጥ አለባችሁ .... አንዳንድ Lecturers ደግሞ የሆነ መጽሐፍ አሪፍ ነው እንደ Reference ተጠቀሙ ይሏችኋል ያንመጽሀፍ አሳደህም ቢሆን አግኝተህ ጥያቄወችን ስራ።
@Gtutorialclass
❗️አስታውሱ ይሄ የሚያገለግለው Quiz እንዲሁም ለ Practice ምናምን የሚያስተምራችሁ መምህር ሚፈትናችሁ ከሆነ ነው።
.... Mid እና Final ጥያቄወችን ሚያወጧቸው በ Department የተመረጡ ፈተና ሚያወጡ ኮሚቴወች ናቸው።
🎈ለምሳሌ 28 class ቢኖር እነዚህ ሚማሩት በተለያዩ መምህራን ቢሆንም የሚወሰዱት mid And final exam ግን ተመሳሳይ ነው። @Gtutorialclass Maths ከሆነ በ ማትስ Department የተመረጡ ጥያቄ ሚያወጡ አንድ 3 ኮሚቴዎች አሉ። ስለዚህ የነሱን የጥያቄ አወጣጥ ዘዴ ማወቅ አለብን። ግን እንዴት? ህግ 4ትን ተጠቀሙ

4⃣ :- የፈተናውን Style አጥኑ!!

የሌላ University mid ና final ጥያቄወችን በመፍለጥ ግዜያችሁን በከንቱ አታባክኑ!! እደግመዋለሁ ጊዜ ማባከን ነው። ወንድሜ መጀመሪያ እስኪ የናንተን Last year Examኦችን ስራ... አምና ምን ላይ ነበረ ያተኮሩት? True falseሱን ከየት አመጡ? ዳሽ ሙላውንስ? ከፍተኛ point የሚይዘውን ዘርዝር ጥያቄውንስ? @Gtutorialclass የ courseሱ Department ዋና ትኩረት ምንድን ነው? መጀመሪያ እነዚህን እወቅ እና ያንተን ግቢ ጨርስ። ከዛ የሌላ ግቢ ብትሰራ ምንም አደለ አሪፍ ነው።

ስለዚህ Departmentቱ ለምሳሌ Psychology department ጥያቄ ሚያወጣ ምን ላይ ነው?
ከ Handout (እነሱ ካስተማሩበት)?
ከ Module? @Gtutorialclass
ከ internet?
ከ Reference book? ምን ላይ እንደሚያወጡ Last year examኦችን በማየት ማወቅ እንችላለን። ከዛ በነሱ የፈተና አወጣጥ Style ማንበብ ነው።

🍁በደንብ አንብቡ ግን አራዳም ሁኑ ና ብልጠት ስሩ!!!

🔰 በመጨረሻም....
ለሰው ልጅ ከተሰጠው ትልቁ ነገር ነፃ ፍቃድ ነው። እኔ ይሄን ያቀረብኩላችሁ እንድታውቁት እንጂ በግድ እንድተገብሩት አደለም ሚመቻችሁ መንገድ ካለ እንደ ሙዳችሁ.... ግን ይሄ ለኔ ከምጠብቀው በላይ ውጤት አምጥቶልኛል ለእናንተም እንደሚጠቅም ተስፋ አደርጋለሁ።

ጥያቄ ና አስተያየት ካላችሁ በዚህ አናግሩኝ 👉🏾@Gtutorialclass

━━━━━━━━━━━━━━━━━
🍁••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @Gtutorialclass
@Gtutorialclass
AAU Civics exam(2).docx
32.8 KB
📖Civics 185 Choice Questions

📓እነዚህን ጥያቄዎች ከሰራቿቸው ሌላ መስራት አይጠበቅባችሁም👌

በተጨማሪ ደግሞ Civics Course እየከበዳችሁ ላላችሁ ተማሪዎች You tube ላይ Videoዎችን ተመልከቱ [ለምሳሌ እንደነ Crash Course ያሉት ቻናሎች አሪፍ በሆነ መንገድ ነው የሚያብራሩት። Search እያረጋችሁ እዩ👌

@Gtutorialclass

@Gtutorialclass
Ch~6 (1).pdf
244.3 KB
📓Emerging Technology

📚Chapter 3 4 5 6

📚 Short note Final Exam ላለባቹ ይሄ በቂ ነው ።

@Gtutorialclass


@Gtutorialclass
emerging-t-mid-final-exam.pdf
2 MB
📓Emerging Technology Mid and Final Exams

📓It contains +3 universities

@Gtutorialclass


@Gtutorialclass
pythonlearn.pdf
2.3 MB
📓የAAU ተማሪዎች ቤተሰቦቻችን ቀጣይ ላለባችሁ Final Exam እቺን የPython Module ማንበብ እንዳትረሱ።

📖ጥያቄዎቹን ስሯአቸው፣ ፈተና ላይ ሊመጡ ስለሚችሉ።

ሌሎቻች የEngineering ተማሪዎችም ብታነቡት ትጠቀሙበታላችሁ።

@Gtutorialclass
👍1
4_5848080581799185122.pptx
30.1 MB
Share '4_5848080581799185122.pptx'
@Gtutorialclass
Entrepreneur unit three power point,,,,,,,
📃📃📃📃📃📃📃📃📃📃
@Gtutorialclass
📚 በጣም ትንሽ ተማሪ ብቻ ነው መልስ የላከው🤸‍♂🤸‍♂። ገብቷችሗል ማለት ነው አብዛኞቻችሁ😊። እሱ ነው የሚያስፈልገው😉

📚 ለማንኛውም Final ፈተና በዚህ መልክ ስለሆነ የምትፈተኑት እንዴት መስራት እንዳለባችሁ ልንገራችሁ። ከ መጀመሪያው ጥያቄ እንጀምር።

#1) The man_________ you meet in the church is my brother.

🎯The man(human being, object) + whom + you(pronoun) ... ስለዚህ መልሱ Whom ነው።

#2) The Woman___________ simplicity and discipline influnced me much is a greater social worker.

📚 Whose + noun .... so, whose + simplicity and discipline(noun). ስለዚህ መልሱ whose ነው።

#3) The speech________ I heard at the meeting excited me so much.

📚 ባለፈው ስንማር which ለ ነገሮች(thing) ሁኖ ነው የሚያገለግለው ተባብለናል። ይህ ዐ.ነገር የሚያወራው The Speech ስለሚለው ነው። The Speech ደግሞ thing ነው። ስለዚህ በ which ይገለፃል። ዐ.ነገሩ ምንም comma አልተጠቀመም ስለዚህ defining clause ነው። ስለዚህ that ን በ which ቦታ መጠቀም እንችላለን። ስለዚህ መልሱ which/that ነው።

#4) This is the girl_______ I talked about.

📚The girl(human being, object) + whom + I(pronoun). ስለዚህ መልሱ whom ነው።

#5) The boy_________ cheated is my brother.

The boy(human being, subject) + who + cheated(verb). ስለዚህ መልሱ who ነው።

#6) The house in _____ I am staying is very nice.

📚 እዚጋ ብዙዎቻችሁ መልሱ whom ነው የምትሉት በእርግጠኝነት ምክንያቱም whom + pronoun(I) በሚለው ቀመር ወይም preposition(in) + whom በሚለው ቀመር። ልክ ናችሁ ኮ ግን አንድ የረሳችሁት ነገር አለ። whom የሚያገለግለው ለ ሰው ፍጥረት(human being) ብቻ ነው። እንደውም ላስታውሳችሁ

Human being(object) + whom + pronoun. ይህን ፎርሙላ ነግሬያችሗለሁ።

ስለዚህ whom ለሰው ፍጥረት ብቻ ነው የሚያገለግለው። ነገር ግን ይህ ዐ.ነገር የሚያወራው "the house" ስለሚለው ነው። the house የሰው ፍጥረት አይደለም ግዑዝ አካል ነው😳። ስለዚህ whom ን አንጠቀምም🤸‍♂🤸‍♂። ባለፈው አንድ ፎርሙላ ነግሬያችሗለሁ

preposition + whom....(for human being).

preposition + which....(for things).

human being(subject) + who + verb.
Things(subject) + which + verb.

Humam being(object) + whom + pronoun.
Things(object) + which + pronoun.

🤸‍♂ እነዚህ ፎርሙላ ምጥጥ አድርጋችሁ ያዙ።

ለማንኛውም መልሱ which/that ነው የሚሆነው።

#7) The girl______ father died in the accident wanted to marry me.

Whose + noun.... whose + father(noun)....:possession.... ስለዚህ መልሱ whose ነው።

#8) My friend, ______ I always respect, does not try to understand me.

📚 My friend(human being, object) + whom + I (pronoun) ... ስለዚህ መልሱ whom ነው።

#9) My sister, _____ is a doctor in Italy, wanted to come back to Ethiopia.

📚My sister(human being, subject) + who + verb.... ስለዚህ መልሱ who ነው። ታዲያ እዚጋ that ን መጠቀም አንችልም በ who ቦታ። ለምን?? መልሱት!!

ጨርሱት...በቀጣይ ስለ Modal verbs እናያለን። Dani ነኝ🤸‍♂🤸‍♂🤸‍♂😁😁

@Gtutorialclass
AAU_ANTHOLOGY_FINAL_Exam.pdf
1.3 MB
📓Anthropology_AAU Last_Year

📖ፋይናል ፈተና ላለባችሁ ተማሪዎች ይጠቅማችኋል።

@Gtutorialclass
📃📃📃📃📃📃📃📃
📚 Communicative English Skill II

📚 Chapter Three

📚 Grammar Focus - Modal Verbs.

🙌 ተወዳጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ። ዛሬ የምንማረው ስለ Modal Verbs ነው። ፈተና ላይ የሚያምታቱ ሊሆኑ ይችላሉ ግን የ concept ተማሪ ይሰራዋል። እኔም በቻልኩት መጠን ፅንሰ ሀሳቡን ለማስረዳት እሞክራለሁ። አብራችሁኝ ቆዩ። Dani ነኝ😊። Dani ይወዳችሗል😘😘😘😘❤️❤️

📚 በርግጥ Modal Verbs ለእናንተ አዲስ አይደሉም። ነገር ግን አንዳንድ አዳዲስ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለማንኛውም በርካታ Modal Verbs አሉ። አገልግሎታቸውን እንመልከት😊

🎯 Express Possibility

📚 Possibility ማለት ሊሆን የሚችል ክስተት(ድርጊት) ማለት ነው። ታዲያ

👉አሁን ላይ "ሊሆን የሚችል ክስተት ይኖራል"(Present Possibility).
👉 ወደ ፊት "ሊሆን የሚችል ክስተት ይኖራል"(Future Possibility).
👉 ከአሁን በፊት "ሊሆን የሚችል ክስተት" ይኖራል(Past Possibility).

😊 ታዲያ ከላይ የተዘረዘሩትን ሶስት possibility ዎችን ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው Modal verbs አሉ። እነማን ይሆኑ🤔

📚 May , Might and Could are used to express present or future possibility.

📚 May/Might/Could + perfect infinitive(have + v3) are used to express past possibility.

😎 እስኪ እንመሰጥበት በትንሹ

🌹 May/Might/Could

📚 ቅድም እንደነገርኳችሁ May, Might እና Could አሁን ላይ ሊሆን ስለሚችል ክስተት(present possibility) ን እና ወደ ፊት ሊሆን ስለሚችል ክስተት(future possibility) ን ለመግለፅ ያገለግሉናል። ታዲያ ሊሆን የሚችሉ ክስተቶችን ስንገልፅ

📌 May - 50% ሊሆን የሚችል ክስተትን( perhaps 50% chance) ለመግለፅ ያገለግላል።

📌 Might - 30% ሊሆን የሚችል ክስተትን( perhaps 30% chance) ለመግለፅ ያገለግላል።

📌 Could - ከ 30% በታች ሊሆን የሚችል ክስተትን( perhaps less than 30% chance) ለመግለፅ ያገለግላል።

🙌 እንዴ አጠቃላይ ግን ሶስቱም ማለትም May, Might and Could የሚያገለግሉት present or future possibility ን ለመግለፅ ነው። ምሳሌዎችን እንመልከት😁

🌹 Example 1

📚 የ ዶርም ጓደኛህ ይህ መፅሀፍ የማን ነው? ብሎ ጠየቀህ። አንተ የማን እንደሆነ አላወክም። ግን እርግጠኛ ባትሆንም የ በረከት ሊሆን ይችላል(present possibility) ብለህ አስበሀል። So,

👨‍🏫ጓደኛህ - Whose book is this?

👨‍🏫 አንተ - I am not sure. It may be Bereket's book.(perhaps 50% it is Bereket's book.)

👨‍🏫 አንተ - I am not sure. It might be Bereket's book.(perhaps 30% it is Bereket's book.)

👨‍🏫 አንተ - I am not sure. It could be Bereket's book.(perhaps less than 30% it is Bereket's book).

👆 የሶስቱም ትርጉም - የ በረከት መፅሀፍ ሊሆን ይችላል።

👆 አያችሁ ኣ ሶስቱም present possibility ን ነው የሚገልፁት። present possibility መሆኑን እንዴት አወቅን?? ምክንያቱም መፅሀፉ የማን ነው?? ብሎ ሲጠይቅ ስለ አሁን ነው የሚያወራው። መፅሀፉ የማን ነበር? ብሎ ቢጠይቅ ደግሞ ስለ past ነበር የሚያወራው።

📚 anyways ግን ሶስቱም አሁን ላይ ሊሆን ስለሚችል ክስተት ን ነው የገለፁልን ልዩነታቸው degree of possibility ነው። ሶስቱንም መጠቀም እንችላለን።

📌 Example 2

አሁን ላይ ግቢ ነው ያላችሁት። እና ከሳምንት በሗላ ፋይናል ፈተና ትጨርሳላችሁ እንበል ለ ዕረፍት ወደ ቤተሰብ ለመሔድ አስባችሗል። ከዛ የዶርም ጓደኛሽ መቼ ነው ወደ ቤተሰብ የምትሔጂው ብላ ጠየቀችሽ። አንቺም ገና አልወሰንሽም ግን ከ 10 ቀን በሗላ የመሔዱ ሀሳቡ አለሽ። ገና አልወሰንኩም ግን ከ 10 ቀን በሗላ ልሔድ እችላለሁ(future possibility) አልሻት። ስለዚህ

👩‍🏫 ጓደኛሽ - When will you go to your family?

👩‍🏫 አንቺ - I haven't decided yet. I may go to after 10 days.(perhaps 50% I will go to after 10 days ማለት ነው)

👩‍🏫 አንቺ - I haven't decided yet. I might go to after 20 days.( perhaps 30% I will go to after 10 days.)

👩‍🏫 አንቺ - I haven't decided yet. I could go to after 10 days.( perhaps <30% I will go to after 10 days).

👆 የሶስቱም ትርጉም - ከ 10 ቀን በሗላ ልሔድ እችላለሁ ማለት ነው።

👆 አያችሁ ኣ ሶስቱም future possibility ን ነው የሚገልፁት። future possibility መሆኑን እንዴት አወቅን?? ከ 10 ቀን በሗላ(future) ሊሆን የሚችል ክስተትን ነው የሚገልፀው።

📚 anyways ግን ሶስቱም ወደ ፊት ላይ ሊሆን ስለሚችል ክስተት ን ነው የገለፁልን ልዩነታቸው degree of possibility ነው። ሶስቱንም መጠቀም እንችላለን።
🎯 Example 3

📚 ምሳሌ "ማታ ዝናብ ሊዘንብ ይችላል" ብትል

👉 It may/might/could rain during the night.(future possibility).

📚 ምሳሌ " አሞህ ሊሆን ይችላል"

👉 You may/might/could be sick.

🙌 ተወዳጆች ሆይ ታዲያ እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር አለ። እስካሁን ያየነው positive sentence ላይ ነው። Negative sentence ወይም Negative present possibility or Negative future possibility ን ለመግለፅ የምንጠቀመው እነማንን ነው😿??

😊 May not and Might Not are used to express negative present or future possibility. ግን Could not Negative possibility ን አይገልፀልንም።

☺️ ምሳሌ- "ማታ ዝናብ ላይዘንብ ይችላል" ብትል

👉 "It may not rain during the night."
👉" It might not rain during the night."
👉 It could not rain during the night." ግን አይባልም

🙌 እሺ አሁን ደግሞ ስለ past possibility እንመልከት።

🌹 May/Might/Could + Perfect infinitives.

📚 May/Might/Could + Perfect infinitives(have + v3) are used to express past possibility.

🎯 ከ አሁን በፊት(past) ሊሆን የሚችል ክስተትን ለመግለፅ May/Might/Could + perfect infinitives እንጠቀማለን።

🎯 ለምሳሌ :- የዶርም ሎከርህን ስትከፍት ደብተርህን አጣኸው። ከዛ ደብተሬን ማን ወስዶት ነው ብለህ ጠየከው ጓደኛህን። እሱም አላወኩም ምን አልባት ቢኒያም ወስዶት ሊሆን ይችላል አልከው።

🎯 ስለዚህ "ቢኒያም ደብተሩን ወስዶት ሊሆን ይችላል" ስንል ከአሁን በፊት(past) ሊከናወን የሚችል ድርጊት ነው። እንዴት😒 ምክንያቱም ደብተሩ አሁን ላይ የለም። ስለዚህ የደብተሩ መወሰድ ድርጊት የተከናወነው ከአሁን በፊት(past) ነው። ነገር ግን ቢኒያም ስለምወሰዱ 100% እርግጠኛ አይደለንም ምክንያቱም ሲወስድ ስለላየን። ነገር ግን እሱ ሊሆን ይችላል ብለን ጠረጠርን። ስለዚህ

🔆 ድርጊቱ የተከናወነው ማለትም የደብተሩ መወሰድ ከአሁን በፊት ነው(past)::

🔆 ቢኒያም ሊሆን ይችላል የወሰደው(possibility)::

😊 ስለዚህ past possibility ነው። ይህን past possibility የምንገልፀው በ May/might/could + perfect infinitives(have + v3) ነው። so,

📌 Biniam may have taken the execersise book.
📌 Biniam might have taken the execrsise book.
📌 Biniam could have taken the execersise book.

👆 ሶስቱም ይቻላል። ትርጉማቸውም "ቢኒያም ወስዶት ሊሆን ይችላል" ማለት ነው። ግን ቢኒያም ይውሰድ አይውሰድ 100% እርግጠኛ አይደለንም። ከበደ ጫላ ወይ ሌላ ወስዶት ሊሆን ይችላል።

😿 ሌላ ምሳሌ :- እህትህ ወደ አዲስ አበባ ሔዳለች። እና ግን በምን ትራንስፖርት እንደሔደች አላወክም። እና ጓደኛህ እህትህ በምን ወደ አአ ሔደች ብሎ ጠየቀህ። አንተም አላወኩም ግን በ plane ሊሆን ይችላል አልከው።

🎯 ስለዚህ "በ plane ሔዳ ሊሆን ይችላል" ስንል ከአሁን በፊት(past) ሊከናወን የሚችል ድርጊት ነው። እንዴት😒 ምክንያቱም ወደ አአ ሔዳለች ምናልባት ከ ሳምንት በፊት ምናምን ብቻ ግን መሔዷ ከአሁን በፊት የተከናወነ ድርጊት ነው። ስለዚህ ወደ አአ መሔዷ ከአሁን በፊት(past) ነው። ነገር ግን በ plane ወደ አአ ስለመሔዷ 100% እርግጠኛ አይደለህም ምክንያቱም ስላላወክ። ስለዚህ

🔆 ድርጊቱ የተከናወነው ማለትም ወደ አአ መሔዷ ከአሁን በፊት ነው(past)::

🔆 በ plane ሊሆን ይችላል የሔደችው(possibility)::

😊 ስለዚህ past possibility ነው። ይህን past possibility የምንገልፀው በ May/might/could + perfect infinitives(have + v3) ነው። so,

📌 She may have gone by plane.
📌 She might have gone by plane.
📌 She could have gone by plane.

👆 ሶስቱም ይቻላል። ትርጉማቸውም "በ plane ሔዳ ሊሆን ይችላል" ማለት ነው። ግን 100% እርግጠኛ አይደለህም። ምናልባትም በ Bus or Minibus ሔዳ ሊሆን ይችላል።

😁 እሺ በቀጣይ ደግሞ ሌሎቹን እናያለን። A+ ይለያል🤸‍♂🤸‍♂😂


@Gtutorialclass
📃📃📃📃📃📃📃📃
📚 Communicative English Skill II.

📚 Chapter Three

📚 Grammar Focus - Modal Verbs For Giving advice.

🙌 ተወዳጆች ሆይ ሰላም ለእናንተ እንዴት ናችሁ። በባለፈው ትምህርታችን ስለ Expressing possibility ተምረናል። ዛሬ ደግሞ ስለ Modal Verbs for giving advice እንማራለን። እስኪ እንማረው😊

🎯 Giving Advice

📚 ሁላችሁም እንደምታውቁት Giving Advice ማለት ምክር መስጠት ማለት ነው። ታዲያ ምክር ስንሰጥ ምክር መስጠታችንን ለመግለፅ የምንጠቀምባቸው Modal Verbs አሉ። ታዲያ ምክር ለመስጠት የምንጠቀምባቸው Modal Verbs የትኞቹ ናቸው🤔

📚 Should , Ought to and Had better are used to give advice.

🎯 ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩት Should, Ought to እና Had better የተባሉት Modal verbs ምክረ ሐሳብ ለመስጠት የሚያገለግሉ ናቸው። ምሳሌዎችን እንመልከት😎

📚 ለምሳሌ አንቺ የ እንግሊዝኛ ቋንቋን አቀላጥፈሽ መናገር ትፈልጊያለሽ። ነገር ግን መናገር አትችይም። ከዛ ጓደኛሽን "እንግሊዝኛ አቀላጥፌ መናገር እፈልጋለሁ ምን ባደርግ ይሻለኛል?" ብለሽ ጠየቅሻት። ጓደኛሽም "በየቀኑ ማውራት ብትለማመጂ(practise) ብታደርጊ ጥሩ ነው" ብላ ሞክሯን ሰጠችሽ። ስለዚህ😎

👩‍🏫 You - I want to speak English fluently. What shall I do?

👩‍🏫 You friend - You Should practice speaking everyday.
👩‍🏫 You friend - You ought to practise speaking everyday.
👩‍🏫 Your friend - You had better practise everyday.

👆 ስለዚህ የ ጓደኛሽ ምክር ልገሳ በ should , ought to ና had better ይገለፃል ማለት ነው።

📚 ሌላ ምሳሌ አንድ ሰው በተደጋጋሚ አልኮል መጠጥ ሲጠጣ ብታየው እና "መጠጣት የለብህም ለጤናህ ጥሩ አይደለም" ብለህ ምክር ለመስጠት ብትፈልግ

🎯 You should stop drinking alcohol.
🎯 You ought to stop drinking alcohol.
🎯 You had better stop drinking alcohol.

👆 ስለዚህ የአንተ ምክረ ሐሳብ በ should, ought to እና had better ይገለፃል ማለት ነው::

🎯 Had better

📚 እሺ አሁን ደግሞ አንድ ነገር ልንገራችሁ። Should, Ought to እና Had better አገልግሎታቸው ተመሳሳይ ነው። ሁሉም ምክር ለመስጠት ነው የምንጠቀምባቸው። ነገር ግን ጠንከር ያለ ምክር ለመስጠት ስንፈልግ ደግሞ Had better ን እንጠቀማለን።

📚 Had better can be used for emphatic, stronger advice.

📚 ስለዚህ አፅንኦት ያለው ወይም ጠንካራ ምክር ለመስጠት Had better ን እንጠቀማለን። ምሳሌ

📚 የ ዶርም ጓደኛህ "አሞኛል ምን ባደርግ ይሻለኛል" ብሎ ሲጠይቅህ አንተም "ክሊኒክ ብትሔድ ጥሩ ነው" ብለህ ጠንከር ያለ ምክር መስጠት ብትፈልግ Had better ን ትጠቀማለህ ማለት ነው።

👨‍🏫 Your friend - I am sick. What shall I do?
👨‍🏫 You - You had better go to clinic.

👆 ከዚህ ዐ.ነገር ላይ should ንም ought to ንም መጠቀም እንችላለን ግን ምክራችን ጠንካራ መሆኑን ለመግለፅ ነው በተለዬ መልኩ had better ን የተጠቀምነው።

📚 እሺ እስካሁን Should , Ought to እና Had better ን በ positive statement ነበር ምሳሌ ያየነው። አሁን ደግሞ Negative statement ላይ ያላቸው ፎርም ምንድን ነው?

🎯 Should not

📚 ስለዚህ should ለ positive statement ሲሆን should not ደግሞ ለ negative statement ይሆናል። ምሳሌ

🎯 You should study hard.(positive statement).

🎯 You should not drink alcohol.(negative statement).

🎯 Ought not to

📚 ስለዚህ ought to ለ positive statement ሲሆን ought not to ደግሞ ለ negative statement ነው። አስተውሉ👇

👉 Ought not to (ነው የሚባለው)
👉 ought to not(በፍፁም አይባልም ስህተት ነው። ፈተና ላይ እንዳትሸወዱ)።

🎯 You ought to study hard.(positive statement).

🎯 You ought not to drink alcohol.(negative statement).

🎯 You ought to not ግን አይባልም። Gramatically ስህተት ነው። ፈተና ላይ ስለሚያወጡት ትኩረት ስጡት።

🎯 Had better not

📚 ስለዚህ had better ለ positive statement ሲሆን had better not ደግሞ ለ negative statement ነው። ምሳሌ

🎯 You had better study hard.(positive statement).

🎯 You had better not drink alcohol.(negative statement).

📚 የዛሬው ክላስ በዚሁ ይቋጫል። Should , Should not, Ought to, Ought not to እና Had better, Had better not ምክርን ለመስጠት የሚያገለግሉ Modal verbs ናቸው።

@Gtutorialclass
📃📃📃📃📃📃
Civic የባለፈው semester ፈተና
©astu2013

Share 👇👇👇👇
Gtutorialclass

Gtutorialclass

To get more use this bot
@Gtutorialclass
📚 Introduction to Economics Final Exam.

📚 Dilla University.

📚Targeted group - Freshman.
Share 👇👇👇👇



@Gtutorialclass
@Gtutorialclass

To get more use this bot
@Gtutorialclass