G-Tutorialclass
812 subscribers
2.23K photos
29 videos
1.43K files
357 links
Impossible is possible with learning & reading.
Download Telegram
Applied math 1 video የቱ ይለቀቅላቹህ
Anonymous Poll
67%
Ch 1 vectors
33%
Ch 2 matrics & Determinants
Communicative English 2 Teachers Guide .pdf
625.8 KB
📌 Communicative English 2
Teachers Guide

👉 ከዚ በፊት " Fundamentals of English Grammar Longman "
Module ሲፃፍ እንደ Reference ጥቅም ላይ የዋለ መፅሀፍ እንደለቀቅን ይታወሳ
🎯 በቀጣይ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የ ማህበራዊ ሳይንስ(social science) ተማሪዎች የ መጀመሪያው ሴሚስተር ላይ ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ።

📚 JOIN :@GTutorialclass
          ተፅፎ በ Concise English ተዘጋጅቶ የቀረበ።

🎬 የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የምትወስዷቸው ኮርሶች👇

📌 Communicative English Skill I

📌 Economics

📌 Geography

📌 Maths(Social)

📌 Logic and Critical Thinking

📌 General Psychology

📌 Physical Fitness


🙌 አሁን ደግሞ ስለ እያንዳንዱ ኮርስ መጠነኛ የሆነ ገለፃ ወይም ጅንጀና እናድርግ።

🎯 Communicative English Skill I

ይህ ኮርስ የብዙ ተማሪዎችን ውጤት የሚያነሳ ነው እንግሊዝኛ ሞካሪ ከሆናችሁ። በዚህ ኮርስ በዋናነት የምትማሩት

🗞 Speaking skill ( ከ ክላስ presentation ታቀርባላችሁ። ማርክ አለው ፡ ስለዚህ ስታቀርቡ እንዳትፈሩ።)

🗞 Reading skill ( ልክ Entrance እንደተፈተናችሁ አይነት የ passage ጥያቄ ትፈተናላችሁ።)

🗞 Writing skill ( የስራ ማመልከቻ ደብዳቤ ( application letter) ፃፋ ልትባሉ ትችላላችሁ ፡ descriptive paragraph ፃፋ ልትባሉ ትችላላችሁ ወዘተ)

🗞 Grammar( Tense , passive and active voice , reported speech , conditional sentence, Modal Verbs etc ትማራላችሁ። mid exam, final exam እና CoC exam ላይ passive and active voice እና conditional sentence ብዙ ጥያቄ ስለሚወጡ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ ተረዱት።)

🎯 Economics

📚 ግቢ ላይ ብዙ ሰቃይ ተማሪዎች Economics ን አይሰሩትም🙇‍♂። 3.7 or 3.8 ያላቸው ልጆች Economics ን B- ምናምን ነው የሚያመጡት። ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው ግቢ ላይ የ Economics ትምህርት ፈተናዎች ወይም ጥያቄዎች conceptual ናቸው። ስለዚህ Economics ን ስታነቡ አትሸምድዱ። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ሞክሩ ፡ ተግባራዊ እውነታውን ተረዱ ማለትም Economics የዋጋ ግሽበትን ለመቀነስ ፡ የማህበረሰቡን ኑሮ ለማቅለል ያለውን ሳይንሳዊ ፋይዳ ተረዱት። 11 እና 12 የተማራችሁት የ Economics ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ስትገቡም ስለሚጠቅማችሁ የ 11 & 12 ኛ ክፍል Economics መፅሀፍ pdf ቢኖራችሁ አሪፍ ነው።Extreme Economics👌

🎯 Geography

📚 ለ Social science ተማሪ Geography አዲስ አይደለም። ግቢ ላይ የምትማሩትም የ Geography ትምህርትም አዲስ አይደለም። በዋናነት የኢትዮጵያን እና የምስራቅ አፍሪካን መልክአምድራዊ ገፅታ ነው በዚህ ኮርስ የምትማሩት ። ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል 🤷‍♂ ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ 😂 እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ 👍::

🎯 Maths (Social)

ከ መጠነኛ ለውጥ ( modification) ውጭ 11 እና 12 የተማራችሁት ነው። 📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::


🎯 Logic and Critical Thinking

ይህ ኮርስ ለእናንተ አዲስ ነው። የዚህ ትምህርት መሰረቱ ፍልስፍና እና ምክንያታዊነት ነው። ስለዚህ የእናንተ የመረዳት ችሎታ እና አገናዛቢነት በዚህ ኮርስ በእጅጉ ይፈተናል። የማስጠነቅቃችሁ ነገር ቢኖር ይህን ትምህርት ስታነቡ ገረፍ ገረፍ አድርጋችሁ ወይም ላይ ላዩን በፍፁም እንዳታነቡ። ፅንሰ ሀሳቡ ገብቷችሁ ነው ማንበብ ያለባችሁ ምክንያቱም አንድ በአንድ ካልገባችሁ ፈተናውን ለመስራት ትቸገራላችሁ። ሽምደዳ ብዙም አያዋጣችሁም እዚህ ኮርስ ላይ። ስለዚህ ለመረዳት ሞክሩ። ለዚህ ኮርስ አጋዥ የሆኑ ሁለት ምርጥ መፅሀፎችን ልንገራችሁ፡

1ኛው) Freshman Logic የሚለው መፅሀፍ ነው። ይህ መፅሀፍ በተወሰነ መልኩ በ አማርኛ እያብራራ ስለሚያስረዳ ብታነቡት ሳይንሱን በቀላሉ እና ቶሎ ትረዱታላችሁ።
የዚህ መፅሀፍ መገኛ ላይብረሪ በተለይም ሶሻል ላይብረሪ ታገኙታላችሁ።

2ኛው) Concise Introduction to Logic የሚለው ነው። ይህ መፅሀፍ የከባባድ ጥያቄዎች መፍለቂያ ነው። የግቢ መምህሮች ይህን መፅሀፍ በብዛት ይጠቀሙበታል በተለይ ጥያቄ ለማውጣት። በቃ በአጭሩ ከዚህ መፅሀፍ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ቀጥታ ፈተና ላይ ያወጡታል🤓። ስለዚህ እዚህ መፅሀፍ ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ስሯቸው። መፅሀፋ በ pdf ስላለኝ በቀጣይ በዚህ ቻናል እለቅላችሗለሁ።

🎯 General Psychology

📚ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል:: ይህ ትምህርት ለየትው የሚያረገው በደምብ መረዳትን ይጠይቃል Module ካነበባችሁ በቂ ቢሆንም Module በደምብ የማያብራራው ሀሳብ ስለሚኖር Google ማድረግ በጣም ተመራጭ ነው በይበልጥ ከ ምዕራፍ 3 ጀምሮ የ Case ጥያቄ ስለሚበዛ በደም Exercise መስራት ይጠቅማቹሀል በቀላሉ Google ላይ በ Topicu ርዕስ worksheet search ብታረጉ ከፈተናው ተመሳሳይ ጥያቄ ታገኛላቹ።
ሌላኛው አማራጭ YouTube ነው እኛ ሀገር በስፋት ባይለመድም በአጭር ግዜ Concept ለመረዳት ፍቱን ነው ሞክሩት ።
11 ምዕራፎች ሲኖሩት ቢበዛ እስከ ምዕራፍ 8 ብትማሩ ነው አታስቡ A+ የናንተ ናት 👍

🎯 Physical Fitness

📚 ይህ ኮርስ ውጤት የለውም። ማለትም A, B+ ,C ምናምን ተብሎ Grade አይሰራለትም። pass or fail ነው የምትባሉት። ኳስ ሜዳ ወጥታችሁ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ነው የምትሰሩት ፡ ስለዚህ የስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል። attendance ካልቀራችሁ እና መምህሩ የሚያሰራችሁን ስፖርት ከሰራችሁ pass ትባላላችሁ ማለትም ታልፋላችሁ።

🥺 የ ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች first semester course እነዚህ ናቸው። በቀጣይ የእነዚህን ኮርሶች መፅሀፍ በ pdf እንለቅላችሗለን።

🙌 ማስታወሻ - አንዳንድ ኮርሶች ከ ግቢ ግቢ እንደሚለያዩ ግምት ውስጥ አስገቡ በ ይዘትም ጭምር ❗️

📌 Join and share 👇👇

📚 JOIN :@GTutorialclass
          JOIN :@GTutorialclass
1
📚 Communicative English Skill II.

📚 Active and Passive Voice.

😊 ይህ የመጨረሻ ክላሳችን ነው ስለ Active and passive voice❗️

📚 ዛሬ በዋናነት የምንማረው passive and active voice በ Passage መልክ ፈተና ላይ ሲወጣ እንዴት መስራት እንደምንችል ነው። Dani ነኝ አብራችሁን ቆዩ ተወዳጆች ሆይ❗️

📚 እንግዲህ active and passive voice በ passage መልክ ፈተና ላይ ሲመጣ ፈተናውን ለመስራት ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን ማወቅ ወይም ማድረግ ይኖርብናል። እነርሱም:-

1ኛ) የ Active and passive voice ፅንሰ ሀሳብ ማወቅ። ማለትም Active voice ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ እንዲሁም passive voice ምን ማለት እንደሆነ ማወቅ። ይህን ደግሞ በባለፈው ትምህርታችን ተምረንዋል አይደል። እስኪ እናስታውሰው😊

📘 Active Voice - The Subject is the doer of the action.

📕Passive Voice - The Subject is the receiver of the action.

📚 ስለዚህ አንድ ዐ.ነገር Active voice ነው የምንለው የ ዐ.ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊት አድራጊ ከሆነ ወይም በሌላ አባባል ድርጊቱን የሚያደርግ ወይም የሚፈፅም ከሆነ ነው። እንዲሁም

📚 አንድ ዐ.ነገር Passive voice ነው የምንለው የ ዐ.ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊት ተቀባይ ከሆነ ወይም በሌላ አባባል ድርጊቱ እሱ ላይ የሚከናወን የሚፈፀም የሚደረግ ከሆነ ነው።

🙌 ስለዚህ ይህን ፅንሰ ሀሳብ በአግባቡ መረዳት አለብን። ይህን ፅንሰ ሀሳብ ካልተረዳንው ፈተናውን ለ መስራት እንቸገራለን። ምክንያቱም ፈተናው በ passage መልክ ወጣ ማለት በ passage ጁ ውስጥ ያሉት እያንዳንዱ ዐ.ነገር active voice ነው ወይስ passive voice ነው እንደ ማለት ነው ፈተናው። ስለዚህ አደራ አደራ አደራ ፅንሰ ሀሳቡን ተረዱት❗️❗️❗️

2ኛ) በ Passage መልክ የወጣ Active and passive voice ፈተናን ለመስራት ማወቅ ያለብን ሁለተኛው ነገር የ Active and passive voice ፎርምን(forms) ማወቅ ነው። Verbs ወይም ቴንሶች Active voice ላይ ያላቸው form ምንድን ነው🤔 Verbs ወይም ቴንሶች passive voice ላይ ያላቸው form ምንድን ነው🤔 ፎርሞቹን ደግሞ በባለፈው ትምህርታችን አይተንዋል አይደል። ስለዚህ መድገም አይጠበቅብንም።

👆 ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ሁለት መሰረታዊ ነገሮች ጠንቅቃችሁ ካወቃችሗቸው በ እርግጠኝነት ፈተናውን ትደፍኑታላችሁ። ሁለቱንም ደግሞ ከ አሁን በፊት በነበረው ትምህርቶቻችን ላይ በደንብ ተምረንዋል።

📚 ስለዚህ አሁን ምን እናድርግ መሰላችሁ አንድ passage እንስራ❗️ Modlue ሉ ላይ ያለውን Activity 1.9 እያብራራን እንስራው😊። አይዟችሁ አብሽሩ አትዛሉ ደግሞም አትድከሙ ውጣ ውረዱን ለመጋፈጥ ቆራጥ ሁኑ የ ፅንሰ ሀሳብ ተማሪ ሁናችሁ ቀጣዩን ትውልድ በ ዕውቀት እና በስነ ምግባር ቀርፁት ሀገራችን ያለ እኛ ማንም የላት ተወዳጆች ሆይ❗️Dani ይወዳችሗል😍። እሺ አሁን ወደ ጥያቄው እንሒድ😊


Activity 1. 9:

📚 Instruction: Write the correct active or passive forms of the verbs in brackets and list them in the
spaces provided below.

📚 Take care of the tense you use❗️ Numbers 2, 8 and 12 are
done for you as an example.

📚 My sister and I -------- (1. grow up) and went to school in Jamaica. We were educated (2.
educate) according to the British system. In 1997 we -------- (3. give) the opportunity to come to
the United States. We decided to finish high school before leaving our own country. We --------
(4.concern) that the education in this country might not be as good as the one we had there, and
we wanted to improve our English too.
My colleagues A, B, and I, ------------ (5. design) an experiment to test the impact on worker
perceptions of well-being when domesticated cats ------------- (6. allow) to freely roam various
work environments in which the subjects were normally employed. Three test environments -----
------ (7. select) for our experiments: a law office, a laboratory in which experiments ----------- (8.
perform) using laboratory rats, and an automobile assembly line. One-way mirrored glass panels￾were installed (9.install) to allow video cameras to record the activity and researchers to observe
the same and take notes. We secretly inserted observers directly into the work environment.
These observers posed as outside contractors and ------------ (10. uniform) as maintenance and
cleaning staff, coffee and water service vendors, and similar supporting personnel. The observers
------------ (11. draw) from the students who had been matriculated (12. matriculate) into the
experimental psychology courses from which this study ------------- (13. develop) as an example
of such studies generally.

🙌 በአጠቃላይ 13 ጥያቄዎች አሉ። እያንዳንዱን እያብራራን እንስራው ለየብቻ። ፈተና ላይ ስትሰሩ አሁን እኔ በምሰራበት መንገድ እንዲትሰሩ አበረታታለሁ😊❗️ እንጀምር😴

📜 Sentence 1

My sister and I -------- (1. grow up) and went to school in Jamaica.
👆 ተመልከቱ ይህን ዐ.ነገር❗️ የዚህ ዐ.ነገር ባለበቤት(Subject) ማን ነው🤔 የ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) ማለት በ ዐ.ነገሩ መጀመሪያ ላይ ያለው ማለት ነው። ስለዚህ My sister and I የሚሉት subject ናቸው። ታዲያ የ ዐ.ገሩ ባለቤት(subject) ድርጊት አድራጊ ወይም ፈፃሚ ከሆነ ዐ.ነገሩ Active voice ይባላል። ነገር ግን የ ዐ.ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊቱ የሚደረግበት ወይም የሚፈፀምበት ከሆነ ደግሞ ዐ.ነገሩ Passive voice ይባላል።

📚 ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆኑት My sister and I ድርጊት አድራጊ ናቸው ወይም ድርጊቱ በእነርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔 በዚህ ዐ.ነገር ድርጊቱ ማደግ(grow up) ነው። ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆኑት My sister and I የ ማደግን(grow up) ድርጊት አድራጊ ናቸው ወይስ የ ማደግ(growu up) ድርጊቱ በእነርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔

📚 ድርጊት አድራጊ ናቸው። ምክንያቱም የሚያድጉት(ያደጉት) እነሱ ናቸው ማለትም በቁመት በሰውነት በእድሜ በአስተሳሰብ የማደግን ድርጊት እየፈፀሙ ነው ወይም ፈፅመዋል😎። እህቴ እና እኔ አደግን ከዛ ጀማይካ ውስጥ የሚገኝ ትምህርት ቤት ገባን ነው ትርጉሙ በአማርኛ። ስለዚህ አደግን የሚለው ድርጊት ፈፃሚ መሆናቸውን ያመለክታል። ስለዚህ ዐ.ነገሩ Active voice ነው። አሁን ደግሞ ወደ ፎርሞቹ(forms) ነው የምንሔደው።

📚 grow up ለሚለው የ Active voice ፎርሙ ራሱ grow up ነው። grow up የሚለው ደግሞ simple present tense ነው። ነገር ግን ዐ.ነገሩ የሚያወራው ስላለፈ(past) ታሪክ ነው። እንዴት አወቅን ያለፈ ታሪክ መሆኑን🤔 'went' የ go past form ስለሆነ🤷‍♂። ስለዚህ simple past tense ነው የምንጠቀመው። grow up ለሚለው ደግሞ past ቱ grew up ነው። ስለዚህ😎

My sister and I grew up and went to school in Jemaica.

😊 ፈተና ላይ በ passage መልክ ሁኖ በዚህ format ልትፈተኑ ትችላላችሁ👇

My sister and I -------- (1. grow up, grew up, were grown up) and went to school in Jamaica.

😎 ስለዚህ grew up ትመርጣላችሁ ማለት ነው።

📜 Sentence 2

sentence 2 ሞጁሉ ላይ ተሰርቷል።

📜 Sentence 3

In 1997 we -------- (3. give) the opportunity to come to
the United States.

📚 ተመልከቱ ይህን ዐ.ነገር❗️ የዚህ ዐ.ነገር ባለበቤት(Subject) ማን ነው🤔 የ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) ማለት በ ዐ.ነገሩ መጀመሪያ ላይ ያለው ማለት ነው። ስለዚህ We የሚሉው subject ነው። In 1997 የሚለው ጊዜውን ለማመልከት ነው። ታዲያ የ ዐ.ገሩ ባለቤት(subject) ድርጊት አድራጊ ወይም ፈፃሚ ከሆነ ዐ.ነገሩ Active voice ይባላል። ነገር ግን የ ዐ.ነገሩ ባለቤት(subject) ድርጊቱ የሚደረግበት ወይም የሚፈፀምበት ከሆነ ደግሞ ዐ.ነገሩ Passive voice ይባላል።

📚 ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆነው we ድርጊት አድራጊ ነው ወይም ድርጊቱ በእርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔 በዚህ ዐ.ነገር ድርጊቱ መስጠት(give) ነው። ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆኑው we የ መስጠትን(give) ድርጊት አድራጊ ነው ወይስ የ መስጠት(give) ድርጊቱ በእርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔

📚 We ድርጊት ተቀባይ ነው ወይም ድርጊቱ በእርሱ ላይ ነው የተፈፀመው። ለምን🤔 እስቲ በ አማርኛ እንተርጉመው።

👉 In 1997 we_______(give) the opportunity to come to America.
👉 በ 1997ዓ.ም ወደ አሜሪካ የመምጣት እድሉ ተሰጠን።

👆 አያችሁ አይደል። 'ተሰጠን' የሚለው ቃል የመስጠት ደርጊት በእነርሱ ላይ እንደተከናወነ ያመለክታል። ምክንያቱም ተሰጠን ሲሉ የሰጣቸው አካል አለ ማለት ነው ስለዚህ ያነ ሰጪ አካል የመስጠትን ድርጊት በእነርሱ ላይ ፈፅሟል። ይህ ማለት ተፈፃሚነቱ በእነርሱ ላይ ነው ወይም የ ሰጪው አካል የመስጠት ድርጊት በ እነርሱ ላይ ተፈፅሟል ማለት ነው። ስለዚህ Sentence 3 passive voice ነው።

📚 አሁን ደግሞ ወደ ፎርሙ ነው የምንሔደው። የ give passive voice ፎርሙ ምንድን ነውይህን ለማወቅ ደግሞ ቴንሱን ማወቅ አለብን። In 1997 የሚለው ደግሞ ያለፈ ታሪክ መሆኑን ያሳያል። ስለዚህ ቴንሱ Simple past tense ነው። የ simple past ቴንስ passive voice ፎርም ምን እንደሆነ በባለፈው ትምህርታችን አይተንዋል። ለማስታወስ ያህል👇

singular subject + was + verb3.
plural subject + were + verb3.

we የሚለው plural subject ነው። ስለዚህ ከላይ ባለው ፎርም መሰረት were ን እንጠቀማለን። ከዛ verb3 እንጨምራለን። የ give verb3 ደግሞ given ነው። ስለዚህ😎

In 1997 we were given the opportunity to come to America.

📜 Sentence 4

We ___(4.concern) that the education in this country might not be as good as the one we had there, and
we wanted to improve our English too.

📚 ተመልከቱ ይህን ዐ.ነገር❗️ የዚህ ዐ.ነገር ባለበቤት(Subject) ማን ነው🤔 የ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) ማለት በ ዐ.ነገሩ መጀመሪያ ላይ ያለው ማለት ነው። ስለዚህ We የሚሉው subject ነው።

📚 ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆነው we ድርጊት አድራጊ ነው ወይም ድርጊቱ በእርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔 በዚህ ዐ.ነገር ድርጊቱ ማሰብ(concern) ነው። ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆኑው we የ ማሰብን(concern) ድርጊት አድራጊ ነው ወይስ የ ማሰብ(concern) ድርጊቱ በእርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔

📚 we ድርጊት ተቀባይ ነው ወይም ድርጊቱ በእርሱ ላይ ነው የተረገው። እንዴት🙃 እስቲ በአማርኛ እንተርጉመው።

👉 We ___(4.concern) that the education in this country might not be as good as the one we had there.
👉 እዚህ ሀገር የሚሰጠው ትምህርት በፊት ስንማርበት ከነበረው አንፃር ጥሩ ላይሆን ስለሚችል አሳስቦን ወይም አስጨንቆን (concern) ነበር። [በ አማርኛ].

👆 አያችሁ አይደል። 'አሳስቦን' ወይም 'አስጨንቆን' የሚለው ቃል የ ሀሳብ የ ጭንቀት ድርጊት በእነርሱ ላይ እንደተከናወነ ያመለክታል። ምክንያቱም አስጨንቆን ሲሉ ያስጨነቃቸው ነገር አለ ማለት ነው እርሱም የ ትምህርት አሰጣጡ ነው። ስለዚህ ያነ አስጨናቂ ወይም አሳሳቢ ነገር(የትምህርት አሰጣጡ) የማሰብን የጭንቀትን ድርጊት በእነርሱ ላይ ፈፅሟል ማለትም እንዲያስቡ እንዲጨነቁ አድርጓቸዋል። ይህ ማለት ተፈፃሚነቱ በእነርሱ ላይ ነው። ስለዚህ ድርጊት ተቀባይ ናቸው። ስለዚህ Sentence 4 passive voice ነው😸
👍1
📚 አሁን ደግሞ ወደ ፎርሙ ነው የምንሔደው። የ Concern passive voice ፎርሙ ምንድን ነውይህን ለማወቅ ደግሞ ቴንሱን ማወቅ አለብን። ቅድም እንደነገርኳችሁ ታሪኩ የሚያትተው ስላለፈ ድርጊት ስለሆነ ቴንሱ Simple past tense ነው። የ simple past ቴንስ passive voice ፎርም ምን እንደሆነ በባለፈው ትምህርታችን አይተንዋል። ለማስታወስ ያህል👇

singular subject + was + verb3.
plural subject + were + verb3.

we የሚለው plural subject ነው። ስለዚህ ከላይ ባለው ፎርም መሰረት were ን እንጠቀማለን። ከዛ verb3 እንጨምራለን። የ concern verb3 ደግሞ concerned ነው። ስለዚህ😎

We were Concerned that the education in this country...

📚 ፈተና ላይ በ passage መልክ ሁኖ በዚህ format ልትፈተኑ ትችላላችሁ👇

We _________(4.concern, concerned, were concerned) that the education in this country might not be as good as the one we had there, and
we wanted to improve our English too.

😊 ስለዚህ were concerned የሚለውን ትመርጣላችሁ ማለት ነወ።

📜 Sentence 5 and 6

My colleagues A, B, and I, ------------ (5. design) an experiment to test the impact on worker
perceptions of well-being when domesticated cats ------------- (6. allow) to freely roam various
work environments in which the subjects were normally employed.

🥺 5 እና 6 አንድ ላይ ስለሆነ በአንድ ላይ እንስራው። መጀመሪያ sentence 5 ን እንስራ።

📚 My collegues A,B and I_____
(5 design) an experiment to test... ሌላው ዝባንኬ ነው ይቅር። ዋናው ቁልፉ design የሚለው ነው።

👆 ተመልከቱ ይህን ዐ.ነገር❗️የዚህ ዐ.ነገር ባለበቤት(Subject) ማን ነው🤔 የ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) ማለት በ ዐ.ነገሩ መጀመሪያ ላይ ያለው ማለት ነው። ስለዚህ My collegues A,B and I subject ናቸው ወይም A,B and I subject ናቸው። ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆኑት A,B እና I ድርጊት አድራጊ ናቸው ወይም ድርጊቱ በእነርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔 በዚህ ዐ.ነገር ድርጊቱ መንደፍ(design) ነው።

📚 ድርጊት አድራጊ ናቸው። ምክንያቱም የተግባር ሙከራ(Exeperiment) ነደፍን ወይም design አደረግን ነው የሚለው ዐ.ነገሩ ወደ አማርኛ ሲተረጎም ስለዚህ design የማድረግን ድርጊት ፈፅመዋል። ስለዚህ ዐ.ነገሩ Active voice ነው። አሁን ደግሞ ወደ ፎርሞቹ(forms) ነው የምንሔደው።

📚 design ለሚለው የ Active voice ፎርሙ ራሱ grow up ነው። design የሚለው ደግሞ simple present tense ነው። ነገር ግን ዐ.ነገሩ የሚያወራው ስላለፈ(past) ታሪክ ነው። ስለዚህ simple past tense ነው የምንጠቀመው። design ለሚለው ደግሞ past ቱ designed ነው። ስለዚህ😎

My collegues A,B and I designed an experiment to test... ይሆናል ማለት ነው።

📚 ፈተና ላይ በ passage መልክ ሁኖ ነገር ግን በዚህ format ሊወጣ ይችላል👇

My collegues A,B and I_____________(5. design, designed, were designed) an experiment to test... ስለዚህ designed የሚለውን ትመርጣላችሁ ማለት ነው።

አሁን ደግሞ sentence 6 ን እንስራ😊

when domesticated cats ------------- (6. allow) to freely roam various
work environments in which the subjects were normally employed.

🙌 ተመልከቱ ይህን ዐ.ነገር❗️ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት Demesticated Cats የሚለው ነው። ታዲያ domesticated cats ድርጊት አድራጊ ናቸው ወይስ ድርጊት ተቀባይ

📚 ድርጊት ተቀባይ ናቸው ምክንያቱም አካባቢዎችን ማሰስ የሚችሉት(roam) ሲፈቀድላቸው(allow) ነው። ስለዚህ ፈቃጅ አካል አለ ማለት። ያነ ፈቃጅ አካል የመፍቀድን ድርጊት በእነርሱ ላይ ፈፅሟል ስለዚህ ድርጊቱ በእነርሱ ላይ ስለተፈፀመ ድርጊት ተቀባይ ናቸው። ስለዚህ sentence 6 passive voice ነው።

📚 አሁን ደግሞ ወደ ፎርሙ ነው የምንሔደው። የ allow passive voice ፎርሙ ምንድን ነውይህን ለማወቅ ደግሞ ቴንሱን ማወቅ አለብን። ታሪኩ የሚያትተው ስለ general fact ስለሆነ ቴንሱ Simple present tense ነው። የ simple present ቴንስ passive voice ፎርም ምን እንደሆነ በባለፈው ትምህርታችን አይተንዋል። ለማስታወስ ያህል👇

singular subject + is/am + verb3.
plural subject + are + verb3.

domesticated cats የሚለው plural subject ነው። ስለዚህ ከላይ ባለው ፎርም መሰረት are ን እንጠቀማለን። ከዛ verb3 እንጨምራለን። የ allow verb3 ደግሞ allowed ነው። ስለዚህ😎

When domesticated cats are allowed to freely roam various ....

📚 ስለዚህ Sentence 5 and 6 👇

My colleagues A, B, and I, designed (5. design) an experiment to test the impact on worker
perceptions of well-being when domesticated cats are allowed (6. allow) to freely roam various
work environments in which the subjects were normally employed.

😊 ፈተና ላይ በ passsage መልክ ሁኖ ግን በዚህ format ልትፈተኑ ትችላላችሁ👇

My colleagues A, B, and I, ----------- (5. design,designed, were designed) an experiment to test the impact on worker
perceptions of well-being when domesticated cats--------- (6. allow, allowed, are allowed) to freely roam various
work environments in which the subjects were normally employed.

😎 ስለዚህ Designed እና are allowed ን ትመርጣላችሁ ማለት ነው።
👍1
📜 Sentence 7 and 8

Three test environments -----
------ (7. select) for our experiments: a law office, a laboratory in which experiments ----------- (8.
perform) using laboratory rats, and an automobile assembly line.

📚 Sentence 7

Three test environments -----
------ (7. select) for our experiments:

👆 ተመልከቱ ይህን ዐ.ነገር❗️ የዚህ ዐ.ነገር ባለበቤት(Subject) ማን ነው🤔 የ ዐ.ነገር ባለቤት(subject) ማለት በ ዐ.ነገሩ መጀመሪያ ላይ ያለው ማለት ነው። ስለዚህ Three test environments የሚሉው subject ነው።

📚 ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆኑት Three test environments ድርጊት አድራጊ ናቸው ወይም ድርጊቱ በእነርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔 በዚህ ዐ.ነገር ድርጊቱ መምረጥ(select) ነው። ታዲያ የዚህ ዐ.ነገር ባለቤት የሆኑት Three test environments የ መምረጥን(select) ድርጊት አድራጊ ናቸው ወይስ የ መምረጥ(select) ድርጊቱ በእነርሱ ላይ ነው የተደረገው🤔

📚 Three test environments ድርጊት ተቀባይ ናቸው ወይም ድርጊቱ በእነርሱ ላይ ነው የተደረገው። እንዴት🙃 እስቲ በአማርኛ እንተርጉመው።

👉 Three test environments____________(7.select) for our experiment:
👉 ለምንሰራው Experiment ሶስት test ማድረጊያ አካባቢዎች ተመረጡ። [በ አማርኛ].

👆 አያችሁ አይደል። 'ተመረጡ' የሚለው ቃል የ መምረጥ ድርጊት በእነርሱ ላይ እንደተከናወነ ያመለክታል። ምክንያቱም ተመረጡ ሲሉ የመረጣቸው አካል አለ ማለት ነው። ስለዚህ ያነ መራጭ አካል የመምረጥ ድርጊት በእነርሱ ላይ ፈፅሟል ወይም በሌላ አባባል የ መራጩ አካል የመምረጥ ድርጊት በ እነርሱ ላይ ተፈፅሟል ማለት ነው ስለዚህ ተመረጡ ማለት የመምረጥ ድርጊት በእነርሱ ላይ ተፈፅሟል ማለት ነው ማለትም Three test environments ድርጊት ተቀባይ ናቸው ። ስለዚህ Sentence 7 passive voice ነው።

📚 አሁን ደግሞ ወደ ፎርሙ ነው የምንሔደው። የ select passive voice ፎርሙ ምንድን ነውይህን ለማወቅ ደግሞ ቴንሱን ማወቅ አለብን። ቅድም እንደነገርኳችሁ ታሪኩ የሚያትተው ስላለፈ ድርጊት ስለሆነ ቴንሱ Simple past tense ነው። የ simple past ቴንስ passive voice ፎርም ምን እንደሆነ በባለፈው ትምህርታችን አይተንዋል። ለማስታወስ ያህል👇

singular subject + was + verb3.
plural subject + were + verb3.

Three test environments የሚለው plural subject ነው። ስለዚህ ከላይ ባለው ፎርም መሰረት were ን እንጠቀማለን። ከዛ verb3 እንጨምራለን። የ select verb3 ደግሞ selected ነው። ስለዚህ😎

Three test environments were selected for our experiment: ይሆናል።

😎 ፈተና ላይ በ passage መልክ ሁኖ ነገር ግን በዚህ format ልትፈተኑ ትችላላችሁ👇

Three test enivironments_____________(7.select, selected, were slected, was selected) for our experiments:

😊 ስለዚህ were selected ን ትመርጣላችሁ ማለት ነው።

📚 Sentence 8

a law office, a laboratory in which experiments ----------- (8.
perform) using laboratory rats, and an automobile assembly line.

🙌 ተወዳጆች ሆይ መፃፉ አደከመኝ😢። የቀሩት 4 ጥያቄዎች ናቸው። ያው ተመሳሳይ ስለሆነ በዚሁ መንገድ መስራት ነው አይከብድም።

🙌ለዛሬ ይብቃን

📚 ትምህርቱ እንደገባችሁ እና እንዳልገባችሁ በዚህ ቦት አሳውቁኝ👇



📌 መልካም ቀን❗️


© Your Success is guranted with A+ Tutorial Class.
👍1
pre-exam-keleme-anthropology-mid-exams.pdf
886.7 KB
📚 Anthropology mid exams.

📚 From Different universities.

📌 Join and Share 👇👇👇
📚Anthropology Freshman Course

📖CHAPTER THREE

📕Human Diversity, Culture Areas and Contact in Ethiopia


📝Human Beings & Being Human: What it is to be human?

📌"Kluckhohn" correctly pointed out: "Anthropology holds up a great mirror to man and lets him look at himself in his infinite variety."
ይሄ ሰው Anthropologyን እንደዚህ ነው ያብራራው፥ ሰው ወደራሱ ዞር ብሎ እንዲመለከት በጣም ይረዷል። እናም በዚህ ምዕራፍ ስር የምናየው፦ "በአለም ላይ ያሉ ሰዎችን የሚያመሳስለው ምንድነው? በአለም ላይ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባህላት እንዴት ተፈጠሩ? የሰው ቆዳ Colour እንዴት ተለያየ?, etc.

እዚህ ስር በስፋት የምናየው:
📌What does every human culture do?
📌What things do only some cultures do?
📌Why aren't all human cultures the same?
📌How does humanity change through time?

ለእነዚህና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ የምናገኘው ሁለት መንገዶችን በመጠቀመ ነው።

📍Comparative Approach [Cultural Relativism]፦ ይል ባለፈው ያየነው ነው፣ Cultureኦችን Compare ስናደርግ አንዱ ከሌላው እንደሚበልጥ Judge ለማድረግ አይደለም።

📍Evolution፦ ይህም እንደምታውቅት allows us to the address the aforementioned fundamental questions regarding our distant origin, current stage of growth, forms of adaptation, and predict future direction of development.

🔖Human biology affects human culture; and similarly, human culture affects human biology.
ማለትም ለምሳሌ በጊዜ ሂደት የሰዎች "Brain size" እየጨመረ/ እያደገ እንደመጣ ከHuman Biology ማረጋገጥ እንችላለን። The change in human brain has brought cultural changes in terms of increased intelligence, language and even the emergence of writing.
አያቹ አ Biological Change [Brain size increase] በHuman Culture ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንዳመጣ👀

📌This is why anthropologists use the term biocultural to describe the dual nature of human evolution: both biological and cultural dimensions. Human beings are described as a biocultural animal.

📖The Biocultural Animal

By the way all other animals survive mainly through their biology and by relying on instinct rather than such cultural information except human being.

📍Humanity [ሰውነት] is the most common term we use to use refer to human beings. Humanity stands for the human species, a group of life forms with the following characteristics:

📌Bipedalism (walking on two legs)
📌Relatively small teeth for primates of our size
📌 Relatively large brains for primates of our size
📌Using modern language to communicate ideas
📌Using complex sets of ideas called culture to survive

እንግዲህ Anthropologistኦች እንደሚሉት ከሆነ ከላይ ያሉትን የሚያሟሉት ናቸው #ሰው የሚባለው።😊

📍Humanity is a general term that does not specify whether you are talking about males, females, adults, or children; it simply means our species- Homo sapiens sapiens- at large.

📓Origin of the Modern Human Species: Homo sapiens sapiens

አሁን 'Humanity' ስንል እያልን ያለነው በዚህ ዘመን ያለውን [Homo Sapiens Sapiens]👱‍♂👱‍♀ና የተወሰኑትን ያለፉትን👨‍🦳 [Homo Sapiens] የሰው ልጅን ዘር ነው።

Keep in Mind! "Homo Sapiens Sapiens" እና "Homo Sapiens" ልዩነት አላቸው፥ የመጀመሪያው Human that are anatomically modern and behaviorally modern, የሁለተኛው ግን በቀድሞ ዘመን የነበሩትን፣ ያልዘመኑትን😁 የሚወክል ነው።

Cosmologies Vs. Evolutionally and Paleo-anthropological Explanations

Modern የሆነውን Human [Homo Sapiens Sapiens] አፈጣጠር [Origin] በሁለት መንገድ ነው የምናብራራው።

1. Cosmologies and Human Origins
📌Cosmologies are conceptual frameworks that present the universe (the cosmos) as an orderly system.
ይህ ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ በሆነ መልኩ የሰውን አፈጣጠር የምናብራራበት መንገድ ነው።

እስኪ የተወሰኑትን እንይ🙌

🎈 አንድ Taoism በሚባል ባህል ውስጥ የሚያምኑት የሰው ልጅ የመጣው Yin እና Yang ከሚባሉት መንፈሳዊና ቁሳዊ ነገር ከሆኑት ነው ይላል። እና Taoists የሚያምኑት እነዚህ ነገሮች ተዋህደው ነው ይህ አለምና ሰው የተፈጠረው።😁 ከፈለጋችሁ ከGoogle ላይ በሰፊው እዩ።

🎈አንዱ የግሪክ ፈላስፋ ደግሞ የሰው ልጅ ከዉሃ ነው የመጣው፣ የሰው ልጅ እንደዚህ ሞደርን ሳይሆን በፊት Fishlike [አሳ የሚመስል] ነበር።🙈 ይህ ደግሞ ጭራሽ ያስቃል😂

🎈ሌላው ደግሞ ታዋቂውና ብዙዎች የሚያምኑበት "ይህ አለም [Cosmos] እና የሰው ልጅ የተፈጠረው በፈጣሪ ነው፣ በኤደን ገነት አዳምና ሔዋን..

Evolutionary and paleo-anthropological perspectives on human origin

ይህ ደግሞ Scientific በሆነ መንገድ የሰውን አፈጣጠር የሚያጠና ነው።
እዚህ ስር ሁላችንም የምናውቀው በCharles Darwin የተመሰረተው Evolution Theory መውሰድ እንችላለን😭

Evolution is used to describe the cumulative effects of three independent facts.

📌Replication: The fact that life forms have offspring;

📌 Variation: The fact that each offspring is slightly different from its parents, and
its siblings;

📌Selection: The fact that not all offspring survive, and those that do tend to be the ones best suited to their environment.
[ለምሳሌ Dinosaur Survive አላደረገም ነገር ግን ደግሞ የሰው ልጅ Survive አድርገው ዛሬም አለን😊]

በቀጣይ ይህን👇 አይተን Unit 3 እንጨርሳለን።
እያነበባችሁ ጠብቁን! ጥያቄዎችንም በpoll እንለቅላችኃለን።

The Kinds of Humanity: human physical variation

የሰው ልጅ በመልክ፣ በቁመት ምናምን ለምን የተለያየ ሆነ?


ሀሳብና አስተያይት👇


ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!
📚Anthropology Freshman Course

📖CHAPTER THREE

📕Human Diversity, Culture Areas and Contact in Ethiopia


📝Human Beings & Being Human: What it is to be human?

📌"Kluckhohn" correctly pointed out: "Anthropology holds up a great mirror to man and lets him look at himself in his infinite variety."
ይሄ ሰው Anthropologyን እንደዚህ ነው ያብራራው፥ ሰው ወደራሱ ዞር ብሎ እንዲመለከት በጣም ይረዷል። እናም በዚህ ምዕራፍ ስር የምናየው፦ "በአለም ላይ ያሉ ሰዎችን የሚያመሳስለው ምንድነው? በአለም ላይ የተለያዩ ቋንቋዎች እና ባህላት እንዴት ተፈጠሩ? የሰው ቆዳ Colour እንዴት ተለያየ?, etc.

እዚህ ስር በስፋት የምናየው:
📌What does every human culture do?
📌What things do only some cultures do?
📌Why aren't all human cultures the same?
📌How does humanity change through time?

ለእነዚህና ለመሳሰሉት ጥያቄዎች መልስ የምናገኘው ሁለት መንገዶችን በመጠቀመ ነው።

📍Comparative Approach [Cultural Relativism]፦ ይል ባለፈው ያየነው ነው፣ Cultureኦችን Compare ስናደርግ አንዱ ከሌላው እንደሚበልጥ Judge ለማድረግ አይደለም።

📍Evolution፦ ይህም እንደምታውቅት allows us to the address the aforementioned fundamental questions regarding our distant origin, current stage of growth, forms of adaptation, and predict future direction of development.

🔖Human biology affects human culture; and similarly, human culture affects human biology.
ማለትም ለምሳሌ በጊዜ ሂደት የሰዎች "Brain size" እየጨመረ/ እያደገ እንደመጣ ከHuman Biology ማረጋገጥ እንችላለን። The change in human brain has brought cultural changes in terms of increased intelligence, language and even the emergence of writing.
አያቹ አ Biological Change [Brain size increase] በHuman Culture ላይ እንዴት ተፅዕኖ እንዳመጣ👀

📌This is why anthropologists use the term biocultural to describe the dual nature of human evolution: both biological and cultural dimensions. Human beings are described as a biocultural animal.

📖The Biocultural Animal

By the way all other animals survive mainly through their biology and by relying on instinct rather than such cultural information except human being.

📍Humanity [ሰውነት] is the most common term we use to use refer to human beings. Humanity stands for the human species, a group of life forms with the following characteristics:

📌Bipedalism (walking on two legs)
📌Relatively small teeth for primates of our size
📌 Relatively large brains for primates of our size
📌Using modern language to communicate ideas
📌Using complex sets of ideas called culture to survive

እንግዲህ Anthropologistኦች እንደሚሉት ከሆነ ከላይ ያሉትን የሚያሟሉት ናቸው #ሰው የሚባለው።😊

📍Humanity is a general term that does not specify whether you are talking about males, females, adults, or children; it simply means our species- Homo sapiens sapiens- at large.

📓Origin of the Modern Human Species: Homo sapiens sapiens

አሁን 'Humanity' ስንል እያልን ያለነው በዚህ ዘመን ያለውን [Homo Sapiens Sapiens]👱‍♂👱‍♀ና የተወሰኑትን ያለፉትን👨‍🦳 [Homo Sapiens] የሰው ልጅን ዘር ነው።

Keep in Mind! "Homo Sapiens Sapiens" እና "Homo Sapiens" ልዩነት አላቸው፥ የመጀመሪያው Human that are anatomically modern and behaviorally modern, የሁለተኛው ግን በቀድሞ ዘመን የነበሩትን፣ ያልዘመኑትን😁 የሚወክል ነው።

Cosmologies Vs. Evolutionally and Paleo-anthropological Explanations

Modern የሆነውን Human [Homo Sapiens Sapiens] አፈጣጠር [Origin] በሁለት መንገድ ነው የምናብራራው።

1. Cosmologies and Human Origins
📌Cosmologies are conceptual frameworks that present the universe (the cosmos) as an orderly system.
ይህ ባህላዊ ወይም ሃይማኖታዊ በሆነ መልኩ የሰውን አፈጣጠር የምናብራራበት መንገድ ነው።

እስኪ የተወሰኑትን እንይ🙌

🎈 አንድ Taoism በሚባል ባህል ውስጥ የሚያምኑት የሰው ልጅ የመጣው Yin እና Yang ከሚባሉት መንፈሳዊና ቁሳዊ ነገር ከሆኑት ነው ይላል። እና Taoists የሚያምኑት እነዚህ ነገሮች ተዋህደው ነው ይህ አለምና ሰው የተፈጠረው።😁 ከፈለጋችሁ ከGoogle ላይ በሰፊው እዩ።

🎈አንዱ የግሪክ ፈላስፋ ደግሞ የሰው ልጅ ከዉሃ ነው የመጣው፣ የሰው ልጅ እንደዚህ ሞደርን ሳይሆን በፊት Fishlike [አሳ የሚመስል] ነበር።🙈 ይህ ደግሞ ጭራሽ ያስቃል😂

🎈ሌላው ደግሞ ታዋቂውና ብዙዎች የሚያምኑበት "ይህ አለም [Cosmos] እና የሰው ልጅ የተፈጠረው በፈጣሪ ነው፣ በኤደን ገነት አዳምና ሔዋን..

Evolutionary and paleo-anthropological perspectives on human origin

ይህ ደግሞ Scientific በሆነ መንገድ የሰውን አፈጣጠር የሚያጠና ነው።
እዚህ ስር ሁላችንም የምናውቀው በCharles Darwin የተመሰረተው Evolution Theory መውሰድ እንችላለን😭

Evolution is used to describe the cumulative effects of three independent facts.

📌Replication: The fact that life forms have offspring;

📌 Variation: The fact that each offspring is slightly different from its parents, and
its siblings;

📌Selection: The fact that not all offspring survive, and those that do tend to be the ones best suited to their environment.
[ለምሳሌ Dinosaur Survive አላደረገም ነገር ግን ደግሞ የሰው ልጅ Survive አድርገው ዛሬም አለን😊]

በቀጣይ ይህን👇 አይተን Unit 3 እንጨርሳለን።
እያነበባችሁ ጠብቁን! ጥያቄዎችንም በpoll እንለቅላችኃለን።

The Kinds of Humanity: human physical variation

የሰው ልጅ በመልክ፣ በቁመት ምናምን ለምን የተለያየ ሆነ?




ስኬትዎ ከA+ ጋር የተረጋገጠ ነው!
📚 Communicative English Skill II

📚 Chapter Two

📚 Speculation about the Future of Science.

📚 Grammar - Future Tenses.

🎯 እሺ በዛሬው ትምህርታችን የምናየው የ ወደፊት ድርጊቶችን(future actions) ለመግለፅ የምንጠቀማቸው የ tense አይነቶች እነማን እንደሆኑ እና አገልግሎታቸው ምን እንደሆነ እንማራለን።

🎯 ታዲያ የወደፊት ድርጊቶችን(future actions) ለመግለፅ የምንጠቀማቸው ቴንሶች እነማን ናቸው🤔 አገልግሎታቸውስ ምንድን ነው🤔ከታች የተዘረዘሩት ቴንሶች በሙሉ የወደፊት ድርጊቶችን ለመግለፅ የምንጠቀማቸው ናቸው።

👉 Present Continuous Tense.(Present Progressive Tense).
👉 Simple Present Tense.
👉 Simple Future Tense.(will and going to)
👉 Future Continuous Tense.
👉 Future Perfect Tense.
👉 Future Perfect Continuous Tense.

🙌 እነዚህ በሙሉ ከላይ የተዘረዘሩት ቴንሶች የወደፊት ድርጊትን(future action) ለመግለፅ የሚያገለግሉ ናቸው። ታዲያ ምንም እንኳን ሁሉም የወደፊት ድርጊትን ቢገልፁልንም አገልግሎታቸው የተለያየ ነው። እኛም በዋናነት አገልግሎታቸውን የምናይ ይሆናል።

🎯 ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉንም ቴንሶች አንማራቸውም። በ Communicative English Skill II ሞጁል መሰረት የምንማረው Present Continuous Tense , Simple Present Tense , Simple Future Tense(will and going to) እነዚህን ሶስቱን ብቻ ነው የምንማረው።

🎯 ካሁን በፊት ስለ ቴንስ ካለን ዕውቀት እና መረዳት አንፃር ታዲያ ብዙዎቻችን በውስጣችን አንድ ጥያቄ ሊፈጠርብን ይችላል🤔ያ ጥያቄ ምንድን ነው🤔 እንዴት Present Continuous Tense እና Simple Present Tense የወደፊት ድርጊትን(Future action) ለመግለፅ እንጠቀምባቸዋለን🤔 Simple Present Tense እና Present Continuous Tense እኮ ስለ present አይደል እንዴ የሚያወሩት እንዴት ለ future action እንጠቀማቸዋለን🤔 የሚል ጥያቄ በውስጣችሁ ሊመላለስ ይችላል😁። ይህ ጥያቄ የሚመነጨው በጣም በርካታ ተማሪዎች ቴንሶችን በአግባቡ ካለመረዳታችን የተነሳ ነው። ብዙ ተማሪዎችም ስላጋጠሙኝ ነው። እንግዲህ የ A+ ቤተሰቦች አጥንት ለመቆርጠም የተዘጋጃችሁ ሁኑ። አሁን ወደ ትምህርቱ እንሒድ።


📚 Present Continuous Tense


🔸Affirmative form

I + am + V-ing.
You/we/they + are + v-ing.
He/she/it + is + v-ing.

🔹Negative form

I + am not + v-ing.
You/we/they+ aren't + v-ing
He/she/it + isn't + v-ing.

🔵 Question form

Am + I + v-ing?
Are + you/we/they + v-ing?
Is + he/she/it + v-ing?

👆 እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት ፎርሞቹ ናቸው። ለማስታወስ ያክል ነው። በዋናነት የምንማረው አገልግሎቶቹን(usages) ነው የምንማረው። ፈተናም የምትፈተኑት አገልግሎቱን ስለሆነ።

📚 Usages

🎯 እንግዲህ ሁላችንም እንደምናውቀው Present Continuous Tense ከ 3 በላይ አገልግሎቶች አሉት። ነገር ግን በዚህ ኮርስ በዚህ ቻፕተር የምናየው አንዱን አገልግሎት ነው እርሱም የወደፊት ድርጊትን ለመግለፅ የምንጠቀምበትን አገልግሎት ነው የምንማረው። ተወዳጆች ሆይ በጣም ትኩረት ሰጥታችሁ አንብቡት❗️እሺ እንመልከተው አገልግሎቱን።

Present Continuous Tense is used to describe plans and arrangements in the future.

🎯 ከ Present Continuous Tense ጥቅሞች መካከል አንዱ ወደ ፊት(future) ሊደረጉ ሊከናወኑ እቅድ የወጣላቸውን ወይም program የተያዘላቸውን ድርጊቶች ለመግለፅ ነው።

🎯 ወደ ፊት ለማድረግ ያቀድናቸውን ድርጊቶች ለመግለፅ ማለትም
👉ቀጣይ አመት
👉 የዛሬ ወር
👉2022 ላይ
👉ነገ
👉መስከረም ላይ ወዘት ልናደርጋቸው ያቀድናቸውን ድርጊቶች ለመግለፅ፡ Present Continuous Tense ን እንጠቀማለን ማለት ነው።

😻ስለዚህ ከዚህ ምን ተረዳችሁPresent Continuous Tense ዕቅድ የወጣላቸውን ወይም በሌላ አባባል program የተያዘላቸውን የወደፊት ድርጊቶችን(planned future actions) ለመግለፅ ያገለግላል ማለት ነው። ምሳሌዎችን እንመልከት😎

🌹Example 1

🎯 ለምሳሌ ነገ ልብስ አጥባለሁ ብለህ ዕቅድ ካወጣህ ወይም program ከያዝክ ነገ ለማድረግ ዕቅድ ያወጣህለትን ወይም program የያዝክለትን ድርጊት(ልብስ ማጠብ) በ Present Continuous Tense ትገልፀዋለህ ማለት ነው። ስለዚህ

📚 I am washing my clothes tomorrow.

🎯ታድያ እዚጋ tomorrow እኮ future ን አይደል እንዴ የሚገልፀው Simple Future Tense(will) ን ነው እንጅ መጠቀም ያለብን እንዴት Present Continuous Tense ን እንጠቀማለን🤔 የሚል ጥያቄ ልናነሳ እንችላለን።

🎯 ጥሩ ጥያቄ ነው። ነገር ግን እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር ወደፊት ልናደርጋቸው ያሰብናቸውን ድርጊቶች ዕቅድ ወይም program ካወጣንላቸው እነዚህ ዕቅድ የወጣላቸው ድርጊቶች በ present continuous Tense ነው እንጂ የሚገለፁት በ Simple Future Tense አይደለም። ልዩነቱን ተመልከቱ👇

☑️ I am washing my clothes tomorrow.(ነገ ልብስ ለማጠብ አቅጃለሁ፡ ስለዚህ ማጠቤ sure ነው።)

☑️I will wash my clothes tomorrow.( ነገ ልብስ ላጥብ እችላለሁ፡ ግን ዕቅድ ስላላወጣሁለት ላላጥብም እችላለሁ።)


🌹 Example 2

🎯 ለምሳሌ ቀጣይ ሳምንት የዳንኤል ልደት ነው። ታዲያ ዳንኤል ሳምንት ልደቱን ለማክበር ዕቅድ ይዟል ዕቅድ አለው። ከወዲሁ አንዳንድ ዝግጅቶችንም እያደረገ ነው። ታዲያ ይህ ሳምንት የሚከናወነውን ድርጊት(ልደቱን ማክበር) ዕቅድ ስለተያዘለት በ Present Continuous Tense ይገለፃል ማለት ነው። ስለዚህ😎

😇 Daniel is celebrating his birth day next week.
🤔 Next week የሚለው future የሚያሳይ ነው። ለምንድን ነው simple future tense ያልተጠቀምነው🤔የሚል ጥያቄ ልታነሱ ትችላላችሁ። Present Continuous ን የተጠቀምንበት ምክንያት ልደቱን ለማክበር ዕቅድ ስለያዘ program ስላወጣ ነው። ልዩነቱን ተመልከቱ👇

Daniel is celebrating his birthday next week.(ልደቱን ለማክበር ዕቅድ ይዟል ማክበሩ sure ነው።)

Daniel will celebrate his birthday next week.( ልደቱን ለማክበር ዕቅድ አልያዘም ሊያከብርም ላያከብርም ይችላል ማለትም ማክበሩ sure አይደለም።)

🙏 Dani ለልደቱ ጠርቷችሗል😁

🌹 Example 3

ምሳሌ ቢኒያም በሚቀጥለው ወር ወደ ለንደን ይሔዳል። ለጉዞ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች visa , tickets ምናምንን አሟልቷል። ስለዚህ ተመልከቱ ለጉዙ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አሟላ ማለት በሚቀጥለው ወር ወደ ለንደን ለመሔድ program ተይዞለታል ማለት ነው። መሔዱ sure ነው። ስለዚህ😎

✈️ Biniyam is travelling to London next month.

🎯 እሺ ተወዳጆች ሆይ ፈተና ላይ በዚህ መልኩ ብትፈተኑትስ🤔

Biniyam _______(will travel, is travelling) to London next week. He has fullfilled all the requirements necessarily for the tour including visa nd ticket.

🤔 next month የሚለው future ን የሚያሳይ ስለሆነ future tense ነው መጠቀም ያለብን ልንል እንችላለን። ነገር ግን visa እና ሌሎች ነገሮችን አሟልቷል፡ ለንደን መሄዱ sure ሁኗል፡ ስለዚህ next month ለመሄድ plan ወይም program አድርጓል ፡ ስለዚህ present continuous እንጠቀማለን ማለት ነው።

🎯 እሺ የዛሬውን ክላስ በዚሁ እንጨርሳለን። ነገ ይቀጥላል።



© Your Sucess is guaranted with A+ Tutorial Class.
📚 Communicative English Skill II.

📚 Unit 2 - Speculation about the Future of Science.

📚 Grammar- Future Tenses

🙌 ተወዳጆች ሆይ እንዴት ናችሁ😘በ ትናንትናው ትምህርታችን ስለ present continuous or present progressive tense ተምረናል። ዛሬ ደግሞ ስለ simple future tense እንማራሩን። እየተከታተላችሁን እየገባችሁ ነው ግን😢ካልገባችሁ ንገሩኝ🙏። እሺ ወደ ትምህርቱ እንሒድ ፈተናም እየደረሰ ነው መሰል።


📚 Simple Future Tense


🗳Affirmative form

Subject + will + verb-1

📭Negative form

subject + will not + verb-1

📮Question form

Will + you + verb-1?

🙌 እሺ አሁን ደግሞ ወደ አገልግሎቱ(usage) ነው የምንሔደው። እንደሚታወቀው simple future tense በርካታ አገልግሎቶች ነው ያሉት። ነገር ግን ሞጁላችሁ ላይ ያሉትን ብቻ እንማራለን። Come on everybody come on💪💪💪💪💪💪💪:: እሺ እንማር😢

🎁Usage

📚 1) to talk about the future.

🎯 የ simple future tense አንዱ ጥቅም ወደ ፊት ሊከናወኑ ስለሚችሉ ወይም ሊከናወኑ ስላሉ ድርጊቶች ለማውራት ወይም ለመግለፅ simple future ን እንጠቀማለን። ነገርግን ወደፊት ሊከናወኑ ስላሉት ድርጊቶች ዕቅድ ወይም program ከታቀደላቸው ግን simple future ን ሳይሆን የምንጠቀመው፡ 'Going to' ን ወይም present continuous ን ነው የምንጠቀመው።

⚽️ ለምሳሌ ነገ ኳስ ለመጫወት ካሰብክ ማለትም ግዴታ እጫወታለሁ ብለህ program ካልያዝክ፡

🏟 I will play football tomorrow.

📚 2) to make predictions.

🎯 ወደፊት ሊከሰት ይችላል÷ ሊደረግ ይችላል ÷ ሊሆን ይችላል÷ ወይም ደግሞ ላይከሰት÷ ላይደረግ ÷ ላይሆን ይችላል ብለን ያሰብናቸውን ድርጊቶች ለመግለፅ። በአጭር ቃል ፡ ትንቢት ለመናገር simple future ን እንጠቀማለን ማለት ነው።

🎯 ታዲያ ወደፊት ይህ ነገር ይከናወናል ወይም አይከናወናም ብለን ስንተነበይ ምንም አይነት ማስረጃ ከሌለን ነው simple future ን የምንጠቀመው። ነገር ግን predict ስናደርግ የሆነ ማስረጃ ወይም ፍንጭ ተጠቅመን ከሆነ ግን Going to ን ነው የምንጠቀመው። ስለ going to በቀጣይ ክላስ እንማረዋለን።

🌹 Example 1

🌎 በ 2050 ሰዎች በባህር ውስጥ ይኖራሉ ብለን ብንተነብይ፡

👨‍👨‍👧‍👧 In the year 2050, people will live under the sea.

🌹 Example 2

የቁንጅና ውድድሩን መቅደስ ናት የምታሸንፈው ብለህ ብትነብይ፡

🌝 Mekdes will win the beauty contest.

🙌 ታዲያ እዚጋ ትንበያችንን ለማሳመር I think... will and I don't think....will የሚሉትን ቃላት መጠቀም እንችላለን። ለምሳሌ😎

In the year 2050, I think people will live under the sea.
I think Mekdes will win the beauty contest.

🎯 I don't think....will ን የምንጠቀመው negative ለሆነ ነገር ነው። ለምሳሌ

I don't think Mekdes will win the beauty contest.(መቅደስ የቁንጅና ውድድሩን የምታሸንፍ አይመስለኝም።)

🙏 ታዲያ እዚጋ ማስተዋል ያለብን ነገር👇

I don't think Mekdes will not the beauty contest. አይባልም። Double Negative መጠቀም አይቻልም።

📚3) to make promise.

🎯 እንድህ አደርጋለሁ ወይም እንድህ አላደርግም ብለን ቃል የምንገባውን ድርጊት ለመግለፅ።

🌹 Example 1

🎯 ምሳሌ ጓደኛህ ና አንተ ብቻ የምታውቁት ሚስጢር፡ ቢኖር ና አንተ ለጓደኛህ ሚስጥሩን ለማንም እንደማትናገር ቃል ለመግባት ብትፈልግ፡ simple future ን ትጠቀማለህ ማለት ነው።

🙊 I will not tell the secret to anyone.
እዚጋ ታድያ፡ will not አጥሮ ሲፃፍ won't ይሆናል። ስለዚህ

🙊I won't tell the secret to anyone. ማለት እንችላለን።

🌹 Example 2

😎 በዚህ በሁለተኛው ሴሚስተር 3.8 አመጣለሁ ብለህ ለ ፍቅረኛህ/ለፍቅረኛሽ ቃል ብትገባ/ብትገቢ በ simple future ትገልፁታላችሁ ማለት ነው።

🙏 I will score 3.8 in this semester. አቦ ውዶቼ ያድርግላችሁ😊😘

📚 5) used for decisions in that moment or used for instant decesions.

🎯 በዛው ቅፅበት ላይ ወደፊት ለማድረግ የወሰነውን ድርጊት ለመግለፅ ወይም ድንገተኛ(ቅፅበታዊ) ውሳኔን እና ድርጊትን ለመግለፅ።

🌹 Example 1

🎯 ምሳሌ ካፌ ገብተህ አስተናጋጁን sprite አምጣልኝ አልከው፡፡ sprite አልቋል አለህ። አስተናጋጁ sprite አልቋል ባለህ በዛች ቅፅበት(in that moment) sprite ከሌለ coca ልጠጣ ብለህ ወስነህ፡ በቃ እሽ coca አምጣልኝ አልከው። ስለዚህ አስተናጋጁ sprite የለም ባለህ በዛች ቅፅበት coca ለመጠጣት ወስነህ ፡ coca አምጣልኝ ወይም coca ይሁንልኝ ብለህ ለአስተናጋጁ ለመናገር simple future ን ትጠቀማለህ ማለት ነው። በ አንተ ና በአስተናጋጁ መካከል፡ የሚደረገው ቃለ ምልልስ ይኸን ይመስላል።👇👇👇👇

You: "Would you give me sprite, please!"

Waiter: " Sorry, we don't have any sprite."

You:" That is ok, I will have coca"

🌹 Example 2

🎯 ለምሳሌ የሆነ ዕቃ ግዛ ብሎ ቤተሰብ አዘዘህ። ከዛ አንተ ብሩን አጠፋኸው😂። ጭራሽ ረስተው ስትጫወት ዋልክ። ከዛ በስተመጨረሻ ወደ ቤት ለመሔድ ስታስብ ዕቃውን አለመግዛትህ ትዝ አለህ። በቃ በዛው ቅፅበት(in that moment) አይ ወደ ቤት አልሔድም ብለህ ወሰንክ🥵:: ስለዚህ ይህን ቅፅበታዊ ውሳኔህን በ simple future ትገልፀዋለህ ማለት ነው።

🚶🚶‍ I will not go home.

🙌 ለዛሬ በዚህ ይብቃን። መልካም ቀን😁። ነገ እንቀጥላለን።

© A+ Tutorial Class.

© Your Sucess is guaranted with @kegebregar
Ch~3.pdf
600 KB
📓Emerging technology
Best short note

📓Chapter 3
sign up to get a 10 US Dollar newcomer bonus! I made more than 200 US Dollars by watching the video here, so you can try it. https://usf-video.xyz/8813479182057530/
𝐬𝐞𝐰𝐨𝐜𝐡 𝐭𝐞𝐭𝐞𝐤𝐞𝐦𝐮𝐛𝐞𝐭 𝐠𝐞𝐫𝐚𝐦𝐢 𝐧𝐞𝐰 𝐚𝐲𝐭𝐨 𝐦𝐚𝐦𝐞𝐧 𝐧𝐞𝐰
Channel name was changed to «G Tutorial ይመቻል 👌👌»
Channel name was changed to «Tutorial class with 𝐆𝐞𝐛𝐫𝐞 ይመቻል 👌👌»