ሀሁ አፍሪካ👋
64 subscribers
335 photos
33 videos
10 files
1 link
ቻናላችን ለጠቃሚ መረጃ፣ አንድነት፣ፍቅር፣ለጤና፣ጠቅላላ እውቀት፣ አእምሮ ማዝናኛ፣ ለተለያዩ ሙያዎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለናንተ ለውድ ቤተሰቦቻችን የምናቀርብበት ቤታችን ቤታቹ ነው ።
ከዘር፣ከአጥንት፣ከደም የልብ ፍቅር ይበልጣል።
😊 አፍሪካዬ👋👋
Download Telegram
😂😂😂😂😂😂😂 @greatafrica
@Greatafrica...kusi😜😜😜😜
🙈🙈🙈🙈🙈❤️❤️❤️Melkam ken
@Greatafrica...kusi
👏👏👏🙏🙏🙏❤️❤️❤️
@greatafrica ...kusi
Enkuwan lenatoch ken aderesen ❤️❤️❤️❤️❤️❤️
‼️‼️ወንዶች የማያወሯቸው‼️‼️‼️ አምስት አሳሳቢ ነገሮች
በዓለም ዙሪያ በእያንዳንዱ 40 ሰከንድ አንድ ሰው ራሱን ያጠፋል። ብዙ ጊዜ ራሳቸውን የሚያጠፉት ወንዶች ሲሆኑ ምክንያቱ ደግሞ ያጋጠሟቸውን ችግሮች የማውራት ወይም እርዳታ የመጠየቅ ባህል ስለሌላቸው ነው።

ታዲያ ወንዶች በግልጽነት ሊያወሯቸው የሚገቡ ጉዳዮች ምንድናቸው?

የማህበራዊ ሚዲያ ሕይወትና እውነታው መጋጨት

ማህበራዊ ሚዲያ የአዕምሮ ጤና ላይ ከፍተኛ ጫና የማሳደር አቅም አለው።

የአሜሪካው ፔንስሎቬንያ ዩኒቨርሲቲ በሰራው አንድ ጥናት ማህበራዊ ሚዲያን አብዝተው የሚጠቀሙ ግለሰቦች ለአዕምሮ በሽታና ጭንቀት የተጋለጡ እንደሆኑ ያሳያል። ውጤቱ የተገላቢጦሽ ሊሆንም ይችላል።

ከሌላ ጊዜ ባነሰ መልኩ ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም የጀመሩ ሰዎች ይሰሟቸው የነበሩ የብቸኝነትና የድብርት ስሜቶች እንደቀነሱላቸው በጥናቱ የተሳተፉ ሰዎች ገልጸዋል። የጥናቱ ዋና አስተባባሪና የሥነ አዕምሮ ጤና ባለሙያ የሆኑት መሊሳ ሃንት እንደሚሉት ወንዶች በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚያዩዋቸውን ነገሮች ማድረግ አለመቻላቸው ከፍተኛ ጫና ያሳድርባቸዋል።

በማህበራዊ ሚዲያ የምንመለከታቸው አስደሳችና አስገራሚ የሰዎች አጋጣሚዎች አብዛኛውን ጊዜ ከእውነታው የራቁና ሰዎች መሆን አልያም ማድረግ የሚፈልጓቸውን ነገሮች የሚገልጹ ናቸው።

በሚቺጋን ዩኒቨርሲቲ የሥነ አዕምሮ ባለሙያ የሆኑት ፕሮፌሰር ኦስካር ይባራ እንደሚሉት ሰዎች ሰው እንደመሆናቸው መጠን እነሱ ያላቸውን ነገር ከሌሎች ሰዎች ጋር ማወዳደር ይወዳሉ።

'' ራሳቸው እንኳን በማያውቁት ሁኔታ ነው ማወዳደር የሚጀምሩት። ሰዎች ሲዝናኑ ሲመለከቱ እኔስ መቼ ነው የምዝናናው? ሰዎች ከሃገር ውጪ ለሥራ ሲሄዱም ተመሳሳይ ጥያቄ ይጠይቃሉ። ይህ ደግሞ ለድብርትና ጭንቀት ስሜት ተጋላጭ ያደርጋል።

ብቸኝነት‼️
ቢቢሲ 'ዌልካም ኮሌክሽን ፈንድ' ከተባለ ተቋም ጋር በመተባባር በሰራው በዓይነቱ ትልቅ የሆነ የሙከራ ጥናት መሠረት ከ16 እስከ 24 ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ብቸኝነት ይሰማቸዋል።

በአውሮፓውያኑ 2017 በተሰራ አንድ ጥናትም በተለየ መልኩ ወንዶች ከብቸኝነት መላቀቅ እንደሚከብዳቸው ተመልክቷል።

ሴቶች ጓደኝነታቸውን ለማስቀጠል የግድ መገናኘት አይጠበቅባቸውም። ስለቀኑ ውሏቸው በስልክ ማውራት ብቻ በቂ ሊሆን ይችላል። ለወንዶች ግን ለረጅም ሰዓት ስልክ ማውራትና ስለ ቀን ውሎ መወያየት የማይታሰብ ነው።

እንደውም ወንዶች ጓደኝነታቸውን ለማስቀጠል የግድ መገናኘት አለባቸው። ሰብሰብ ብለው እግር ኳስ ይመለከታሉ አልያም ወደ መጠጥ ቤት ጎራ ይላሉ። እነዚህና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን የማያደርጉ ከሆነ ግን ለብቸኝነትና ጭንቀት የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ ነው።

ብቸኝነት ከዚህ ባለፈ ለእንቅልፍ እጦትና ከፍ ሲል ደግሞ ራስን እስከማጥፋት ሊያደርስ ይችላል።

ማልቀስ👍
ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ማልቀስ ለጭንቀትና ድብርት ፍቱን መድሃኒት ነው። ነገር ግን ወንዶችና ማልቀስ ብዙ ጊዜ አይዋደዱም። በወንዶች ዘንድ ማልቀስ እንደመሸነፍና ደካማነት ተደርጎ ይቆጠራል።

እንግሊዝ ውስጥ በተሰራ አንድ ጥናት መሰረት 55 በመቶ የሚሆኑት ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 24 የሆኑ ወጣቶች ማልቀስ ወንድነትን ዝቅ ማድረግ ነው ብለው ያምናሉ።

ራስ ማጥፋት ላይ በትኩረት የሚሰራው የአውስትራሊያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ኃላፊ የሆኑት ኮልማን ኦድሪስኮል እንደሚሉት ወንዶች ከልጅነታቸው ጀምሮ ውስጣዊ ስሜታቸውን መግለጽ እንደሌለባቸውና ማልቀስ ደካማነት እንደሆነ እየተነገራቸው ነው የሚያድጉት።

''ማልቀስ በሚገባን ሰዓት ማልቀስ፤ ሁሌም ቢሆን ጭንቀትንና ድብርትን የመቀነስ ከፍተኛ አቅም አለው።'' ይላሉ ኮልማን ኦድሪስኮል።

አባወራነት‼️
እንግሊዝ ውስጥ ከሚኖሩ ወንዶች 42 በመቶ የሚሆኑት ከፍቅር ጓደኞቻቸው አልያም ከሚስቶቻቸው ከፍ ያለ ገቢ ሊኖራቸው እንደሚገባ ያምናሉ።

ወንዶች ሙሉ የቤታቸውን ወጪ መሸፈን እንዳለባቸው የሚያስቡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ጥቂት የሚባል አይደለም። በአሁኑ ሰዓት ገንዘብና ከገንዘብ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጭንቀቶች ከሚታሰበው በላይ እየተስተዋሉ ነው።

በአውሮፓውያኑ 2015 የተሰራ አንድ ጥናት እንዳመላከተው የሥራ አጥነት መጠን አንድ በመቶ በጨመረ ቁጥር ራስን የማጥፋት ቁጥር በ0.79 በመቶ ከፍ ይላል።

አካላዊ መገለጫዎች
ብዙ ጊዜ ሰዎች ሴቶች ብቻ ስለ አካላዊ ቁመናቸው የሚጨነቁ ይመስላቸዋል። ነገር ግን እውነታው ከዚህ በጣሙን ራቀ ነው።

ጆሽ እንግሊዝ ውስጥ በሚገኝ አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ በሚቀርብ የቴሌቪዥን ውድድር ላይ ሦስተኛ ሆኖ ነው ጨረሰው። አካላዊ እንቅስቃሴ አብዝቶ መስራቱና ስለ ሰውነቱ መጨነቁ አስተዋጽኦ እንደነበረው ያምናል።

"በባህር ዳርቻዎችና በተለያዩ ቦታዎች ከወገቤ በላይ እራቁቴን ሆኜ ስንቀሳቀስ ከሴቶች አልፎ ወንዶች እንዴት እንደሚመለከቱኝ አያለው። ምናለ እንዳንተ ዓይነት ሰውነት ቢኖረኝ ብለው የሚያወሩኝም አሉ። '' ብሏል።

ወንዶች ሁሌም ቢሆን ከሌሎች ወንዶች በሁሉም ነገር የተሻሉ ሆነው መገኘት ይፈልጋሉ ። አካላዊ ገጽታቸው ደግሞ ከፍተኛውን ቦታ ይይዛል
@greatafrica
@Greatafrika kusi
❤️❤️❤️❤️🙏🙏🙏
@greatafrica...kusi😍😍😍👏👏👌👌❤️❤️❤️
🙏🙏👍
ስለ # 👏ኢትዮጵያ ❤️አስገራሚ እውነታዎች
*************
(ዳንኤል ክብረት)
እውነት እውነት እልሃለሁ ብታነበው ይጠቅምሀል
ኢትዮጵያ ማለት የቃሉ ትርጉም እነዚያ አዕምሯቸውን የታወሩ ጠላቶቿ
እንደሚያወሩት የተቃጠለ ፊት ማለት ሳይሆን ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ
የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው ትርጉሙ።
ሲተነተንም ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ
ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።
ኢትዮጵያ ማለት እኔና እናንተ በምናውቃት ልክ ብቻ ያለች ሀገር አይደለችም።
ኢትዮጵያ ከምድር ሀገራት ሁሉ እጅግ ምስጢራዊና ረቂቅ ሀገር ናት። ይሄን
ስላችሁ ደግሞ በግምት ወይም በስሜት ተገፍቼ አይደለም። በብዙ ማስረጃዎች
ነው እንጅ። ይሄን ጽሁፍ ስታነብቡ ውስጣችሁ የማይቀበልላችሁ፣ የኢትዮጵያ ነገር
የማይዋጥላችሁ፣ ተራ አሉቧልታ ወይም አፈ ታሪክ የሚመስላችሁ፣ ኅሊናችሁ
ኢትዮጵያዊያን በጠባብነት በዘረኝነት ወይም በገንዘብና በክህደት የታወረ ጥቂት
ትኖራላችሁ። አልፈርድባችሁም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ማንነት አልገባችሁምና
ነው።
(((ብሉይ ኪዳን)))
1ኛ) ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው
# ኢትዮጵያዊው_ዮቶር ነው። ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ መውጣት
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው። ቴዲ አፍሮ በጥቁር ሰው አልበሙ
ላይ የዮቶርን ኢትዮጵያዊነት ለመጥቀስ ሞክሯል። የዮቶር እርስት ውብ ሀገር
ኢትዮጵያ ነች።
2ኛ) አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት # ሲጳራ ኢትዮጵያዊት ነች።ሐበሻዊት
ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች። ሙሴ ይቺን ሴት በማግባቱ ወንድሙ
አሮንና እህቱ ማርያም ያጉረመርሙበት ነበር።
3ኛ)የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው ይህ ካህን በክርስትና
አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል።
4ኛ) በሀገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሡልጣን) ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ
ነች። ይሄንን ቦታ ምዕራባዊያንና አንዳንድ የምስራቅ ሀገራት ለመውሰድ
ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ታሪክ ይዘክራል።
5ኛ) ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ ቋንቋ (ግዕዝ)
የሚገኘው ኢትዮጵያ/ቤተ ክርስትያን/ ውስጥ ነው። ይሄን ቋንቋ እኛ የቋንቋው
ባለቤቶች ብናቃልለውም ቅሉ ዓለም ግን እጅግ የሚያከብረው ትልቅና ቀዳሚ
ልሣን ነው። ይሄንን ደግሞ ራሳቸው ምዕራባዊያን ይመሰክራሉ። በዚህ ቋንቋ ብዙ
እልፍ ድርሳናትና ምስጢራት ተከትበዋል።
6ኛ) ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ # ኖኅ የተቀበረው ኢትዮጵያ/ጎንደር/
ውስጥ ነው። የሰው ልጅ ከሰማይ ከተጣሉት መላዕክት (ኔፍሊሞች) በተማረው
ምድራዊ ጥበብ ምክንያት ልቦናው ከፈጣሪው ራቀ። ለምሳሌ ኮኮብ ቆጠራ፣
በአንገት የሚታሰሩ በጆሮ የሚንጠለጠሉ በእጅና እግር ጣቶች የሚታሰሩ
ከንፈርንና ገላን የሚቀቡ ሁሉም ምድራዊ ጌጣጌቶች የመጡት ከወደቁት
መላዕክት ወይም ከኔፍሊሞች ነው። እነዚህ መላዕክት የሰውን ልጅ ከፈጣሪው
እንዲርቅ ዝሙትን፣ መዳራትን፣ ያለ አግባብ መብላትና መጠጣትን አስተማሩት።
በዚህም ምክንያት የሰው ልጅ ኅልቆ መሳፍርት ሀጢያትን በመስራቱ
እግዚአብሔር ምድርን በንፍር ውኃ መላት። ሁሉም አለቁ። ኖኅና ቤተሰቦቹ ብቻ
ቀሩ። ይህ ሰው መቃብሩ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።
7ኛ) ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን ያሳረፋት
# ኢትዮጵያ_ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ ነው
8ኛ) የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአራት ባህሪያተ ስጋ ነው።
ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ
ነው። ከዚህም በመነሳት አንዳንዶች # አዳምና_ሄዋን_ኢትዮጵያዊያን ናቸው
ይላሉ። እውነት ነው። ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች።
@Greatafrica ...kusi😜😜😜👍👍
Kusi❤️❤️❤️👍👍
Forwarded from Deleted Account
Voice 114.m4a
721.9 KB
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
ባሳለፍነው ቅዳሜ በብሔራዊ ቲያትር አዳራሽ ለመጀመሪያ ግዜ በታላቅ ድምቀት የተከፈተው የሳጥናኤል አበሳ አዲስ ቲያትር በድጋሚ የፊታችን ቅዳሜ ነሃሴ 25 ከቀኑ 7 ጀምሮ በድጋሚ ለይታ ይበቃል በርካታ የቲያትር አፍቃሪያንን ፣ የሙያው ባለቤቶችን እንዲሁም የሀገራችን ሚዲያዎችን እያስገረመ እና እያነጋገረ የሚገኝው ይህ ሽሙጣዊ ኮሜዲ ቲያትር እዳያመልጦ ይምጡና እርሶም በቲያትሩ ይደመሙ