God, I know You are the only One who can truly satisfy me. The things of this world try to convince me I need them for happiness, but I know true joy only comes from You.(እግዚአብሔር ሆይ በእውነት የምታረካኝ አንተ ብቻ እንደሆንክ አውቃለሁ። የዚህ አለም ነገሮች ለደስታ እንደምፈልጋቸው ሊያሳምኑኝ ይሞክራሉ፣ ነገር ግን እውነተኛ ደስታ ከአንተ ብቻ እንደሚመጣ አውቃለሁ።)
Channel name was changed to «#ያድናል ኢየሱስ»
ፊልጵስዩስ ሰዎች 2፥6-8፦እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ።
ትንቢተ ኢሳይያስ 53:1-5፦
1 የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
2 በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
3 የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
4 በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
5 እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

ገላትያ ሰዎች 3፡13-14፦ በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤ የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፥ የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ።
ወደ ዕብራውያን 7፡24- 27፦
24ኢየሱስ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
25ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። 26 ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢአተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ፥ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባልና፤
27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5፥12
ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።

Awooo bamigabawu enemi misikir ngn
ቲቶ 3፥5-7፦ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2፥5፦
ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

መዝሙረ ዳዊት 118
28፤ አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንህማለሁ።
አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤
ሰምተኸኛልና፥
መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
28፤ አንተ አምላኬ ነህ አመሰግንህማለሁ።
አንተ አምላኬ ነህ፥ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤
ሰምተኸኛልና፥
መድኃኒትም ሆነኸኛልና አመሰግንሃለሁ።
ሐዋርያት ሥራ 4፥12 ፦
መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።
ሐዋርያት ሥራ 2፥21፦
የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል።

እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የሉቃስ ወንጌል 2፥10-11፦
10 መልአኩም እንዲህ አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤
11 ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።
የዮሐንስ ወንጌል 1፥9-10
9 ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን ወደ ዓለም ይመጣ ነበር።
10 በዓለም ነበረ፥ ዓለሙም በእርሱ ሆነ፥ ዓለሙም አላወቀውም።
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 5 ፥1
ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።

መልካም በዓል!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!❤️
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል👋🌅
#Jesus Christ the same yesterday, and to day, and for ever(ያድናል ኢየሱስ)
ቲቶ 3፥5-7፦ እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤ያን መንፈስም፥ በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን፥ በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው።
አሜን የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን።እኛ በእግዚአብሔር የተወደድን ነን።ፍቅሩም ልጁን እስከመስጠት ነው(ዮሐንስ ወንጌል 3:16) እንደምለው።እኛ ከእንግዲህ ተራ ሰዎች አይደለንም፤ታላቁ በውስጣችን አለና።ያውም ብርሃን የሆነው።እኛም ይህንን ብርሃን በአለም ለማብራት በእግዚአብሔር የተመረጥን ውድ ልጆቹ ነን።ውድ የሆንነው፣ውድ ልጁ ለሞት አሳልፎ ስለሰጠው ነው።ስለዚህ እንደ ተራ ሰዎች አንመላለስ።ለዚህች ዓለም ብርሃን ሆነን ራሳችንን እንግለጥ።
በእርግጥ ቀድሞ ወገን አልነበረንም፣እንደበጎች ስንቅበዘበዝ ነበርን(ቃሉ እንደምለው 1 የጴጥሮስ መልዕክት 2:10) ከጨለማ ወደ ብርሃን አውጥቶ ወገኑ ያደረገን ኢየሱስ ነው።ለዚህ ነው ኢየሱስን የምናገንነው፣ደጋግመንም የምናወድሰው።የዳንነውም በሆነ ሰው አይደለም፤በሠራነውም መልካም ሥራችን አይደለም፤ኢየሱስ በሰራው ስራ ነው እንጂ።
ይህን ጌታ ወደ ውስጣችሁ አስገቡት።ደጉ ኢየሱስ ከኃጢአታችሁ ልያድን ዘንድ ይጠራችኋል።ኢየሱስን ተቀበሉት የህይወታችሁ ዋስ ነውና።"በልጁ የሚያምን አይፈረድበትም፤የማያምን ግን ባንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስላላመን አሁን ተፈርዶበታል።ዮሐንስ ወንጌል 3:18"
ደጉ ጌታ ያግኛችሁ።ሰላም ሁኑ!