ግጥም ብቻ 📘
68.6K subscribers
1.53K photos
31 videos
61 files
172 links
በየቀኑ ምርጥ ምርጥ የጥበብ ስራዎችን ለማግኘት የቻነላችን ተከታይ ስለሆኑ እናመሰግናለን።

@getem @serenity13
@wegoch @Words19
@seiloch @shiyach_bicha
@zefenbicha

@leul_mekonnen1
Download Telegram
ተለያይተን ፡ አይደል ? ተጣልተሽኝ ፡ የለ ?

ቀኑን ፡ ባላስብሽ ፡ በህልሜ ፡ ባትመጪ ፡ምን አለ ?

ትዝ ፡ እያልሽኝ ፡ ሁሌ ፡ ከአጥንቴ ፡ በቀር ፡ ስጋዬስ ፡ የታለ ?

ቀልቤስ ፡ ቢሆን ፡ የታል ? በድኑን ፡ ለእኔ ትቶ ፡ ካንቺጋ ፡ እየዋለ ፣

አላሳዝንሽም ? ትወድጅኝ ፡አልነበር ? ትንገበገቢልኝ ?

ላላገኝሽ ፡ ነገር ፡ ባንቺ ፡ እንዲህ ስሰቃይ ፡ ምናለ ፡ ብተይኝ ?

በምሰማው ፡ ደምፅ ፡ በማየው ፡ መልክ ሁሉ ፡ የምትታወሺኝ ?

በህልሜም ፡ በእውኔም ፡ ካላንቺ : የማላውቅ ፡ ሌላ ፡ ማይታየኝ ፣

አዋቂ ፡ ጋር ፡ ሄድሽ ፡ ወይ ? የኔታን ፡ አማከርሽ ፡ ያኔ ፡ እንደዛትሽብኝ ?

ተለያይተን ፡ አይደል ? ተጣልተሽኝ ፡ የለ ?
ባክሽ ፡ አትናፍቂኝ ፣

ከሰው ፡ አለያይተሽ ፡ ከፍጥረት ፡ ነጥለሽ ለብቻ ፡ አታዉይኝ ፣

አጥቼሽም ፡ ቢሆን ፡ ባክሽ ፡ ልኑርበት ፡  አትፈታተኚኝ ።

                 ዘረ ሠናይ
             @Prince_zeresenay

@getem
@getem
@paappii
(የሚያደበዝዘው..)
==============

የትናንቱን ዝናብ
ያመሰግናል ሰው ሰማይ ስላጠራ
ምን ነበር ባየልኝ
ቤቴን እንደናደው ጎርፉ ሆኖ መከራ

ምናል ሰው ደስታውን
ለልቡ ለራሱ አምቆ ቢይዘው
ያንዱ መድመቂያ ነው
የሌላኛውን ቤት የሚያደበዝዘው

@kiyorna

መነሻ: The last breath " Japanese Movie on storm"

@getem
@getem
@paappii
ጌጤ እና ሽጉጤ ቀናቸው ነው ዛሬ
ሲባባሉ ያድራሉ ሀኒ፣ ቤቢ ፍቅሬ
ጌጤም በመልኳ ላይ ሜካፗን ለቅልቃ
ችሎ ያኖራትን ሺቲዋን አውልቃ
የእራት ልብሷን ለብሳ ቀጭ ቋ እያለች
ከሽጉጤ ዕቅፍ ጠልቃ ትገባለች
.
ሽጉዬም ላመሉ ፀጉሩን አስፈርዞ
የኪራይ ሱፍ ኮቱን በእጁ ላይ ይዞ
እንደ ውጪዎቹ አበባ አንጠልጥሎ
ለአንድ ቀንም ቢሆን ድህነቱን ጥሎ
ቀፍሎ ባመጣው ኪሱን አሳብጦ
ጌጥዬን እያየ ይበላል አማርጦ
.
ተበላ ተጠጣ ፍቅራቸው ነደደ
ገና ነው እያሉ ሰዓቱ እረፈደ
በፍቅራዊ ቃና እየተገፋፉ
ለሊቱን አነጉት አልጋ ሲያነጥፉ
ለስራቸው ጥራት ለድካም ወዛቸው
ከወራት በኃላ ደሞዝ ደረሳቸው

ዘንድሮም ጠንክራቹ ስሩ💪


በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
እርዕስ ስጡት!

በለበስኩት ልብስ ተመን ስታወጪ
ከኋላዬ ሆነሽ ማይሆን ስም ስትሰጪ

በገንዘብ ተታለሽ ፍቅርን ስታጪ
በዝና ተውጠሽ ባህር ውስጥ ስትሰምጪ

ታዲያ ከአሁን ወዲህ እዚህ እንዳትመጪ
ልምከርሽ ውድዬ ምንም ሳታወጪ

ሼባውን ሸብ አርጊው እሱን እንዳታጪ
ድንገተኛ መርዶ ስትሰሚ በውጪ

የፈራሁት ደርሶ ያንን ብር ስታጪ
ቤተሰብ በድንገት ሲልሽ ከቤት ውጪ

ፍቅር አለኝ ብለሽ እዚህ እንዳትመጪ
እኔም አገኘሁሽ ቤቴን ለቀሽ ውጪ።
                  
BY፦LIONEL YOHANNES

@getem
@getem
@getem
2 ኢትዮጵያ
በኤደን ታደሰ እና በኪሩቤል አሰፋ
፪ ኢትዮጵያ
በዔደን ታደሰ እና ኪሩቤል አሰፋ
ተፅፎ እንደ ቀረበ
@ediwub & @idcfe

@getem
@getem
@getem
( ባክሽ አፈር ስሆን )


በምትወጅው ደብር በአርባራቱ ታቦት
የልቤን ውስጥ ሀዘን ልብሽ ተገንዝቦት
      ቀና ብዬ እንድኖር
የፍቅርሽን ማዛ ህይዎቴ አጣጥሞት
      ባክሽ አፈር ስሆን
ጥለሽኝ አትሂጅ ተመለሽ በኔ ሞት
ያፍቃሪ ሰው ልቡ ባሀዘን ቢደነድን
ዘላለም ከማልቀስ ከመጎዳት አይድን
ላንቺ ያነባሁትን ላንቺ የደከምኩትን
ላንቺ ያለቀስኩትን ላንቺ የሆኩትን
ሄዋኔን ለማግኘት አንቺን የምትመስል
ዳግም መሷትነት እንደምንስ ልክፈል
        ታፈቅሪኝ እያለሽ
ህይዎቴ ለመኖር ይጓጓ እንዳልነበር
      ዛሬ ግን ስትከጅኝ
መኖርም ሰለቼኝ ልቤ አዝኖ ሲሰበር

ትላንት ቀና አድርጎ የጠገነኝ ፍቅርሽ
መልሶ ሰበረኝ ዛሬ ፈርሶ ቃልሽ
ትመጭ እንድሆነ ስታልፊ እንዳገኝሽ
ንገሪኝ በኔ ሞት የቱጋር ልጠብቅሽ

By@Habtishe01

@getem
@getem
@paappii
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
.
ያሳለፍነዉ ሁሉ
አሁን ትዝታ እንጂ
ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ
ታወሪያለሽ አሉ
.
.
(እኔ ግን ልንገርሽ)
የሁለታችን ፍቅር
ምን እንደሚመስል. . .
እንዴት እንደነበር
በሶስት ምስክር
1
አሁን በቀደም ለት
የሆነ ቦታ ላይ
ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ
ፒያሳ አደባባይ
ድንገት
በቀደም ለት
በዛ ቦታ ስሄድ
ከሰባት ወር በፊት
ስቀሽ የነበረዉ
ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ
መራመድ አቃተኝ
የሚገርምሽ ነገር
ያለፈ ነዉ ያልሺዉ
ትዝታ ነዉ ያልሽዉ
ፍቅርሽና ሳቅሽ
ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ
ይሰማል ልንገርሽ
.
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ
ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ
ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ
(ይልቅ እኔን ስሚኝ)
.
ወደየትም ሳይሆን
ወዴትም ተመለሽ
የትም ሳትደርሺ
ጊዜን እንዳቆምነዉ
እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ
ደቂቃ እንዳልሄደ
አስረጂ ሊሆንሽ
ምስክር ሊሆንሽ
ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ
አደባባይ መሀል
ከቡና ጠረን ጋር
እንደወንዝ የሚፈስ
ሳቅሽን ትሰሚያለሽ
.
2
ትዝ ይልሽ እንደሆን
ካንቺ መኖሪያ ቤት
(የመጣሁኝ ጊዜ)
የመራራቅ ናፍቆት
አስክሮን ቸኩለን
ሰማያት ለመዝለቅ
ከመሬት ላይ ወድቀን
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ፍቅር ስንሰራ
ከሴት ወዝሽ ጋራ
የጡትሽ ስር ሽቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ሸሚዜ ላይ ቀርቶ
ምወደዉን ሸሚዝ
ለመልበስ እርም አልኩኝ
ለብሼዉ እንዳልሄድ
ከበደኝ ጨነቀኝ
ያንቺን ጠረን ማጠብ. . .
ነፍስ የማጥፋት ያህል
ሀጥያት መስሎ ታየኝ
(የሚገርምሽ ነገር)
እስከ ዛሬ ድረስ
በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ
የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ
በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ
.
3
ታስታዉሽ እንደሆን
የሆነ ቅዳሜ
የሆነ ዉብ ሆቴል
ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ
ይኼ እንኳን ትዝ ይላል
እና. . .
እኔና አንቺ ብቻ
የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ. . .
እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ
የሚገርምሽ ነገር
ጻፊዉን ባላዉቅም
#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር
የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ
ከዘጠኝ ወር ኋላ
አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር
ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር
(ምስክር ሊሆኑን)
ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን
ከወይንም. . . Two Ocean
እኔ የጨለጥኩት
አንቺ ያጋመስሽዉ
እኛ ያስተረፍነዉ
እስከዛሬ ድረስ
ያተረፍነዉ ማዕድ. . .
ጠርሙስና ጽዋዉ
በክብር ተቀምጧል
ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ
(ታዲያ ምን ማለት ነዉ)
.
.
.
ፒያሳ አደባባይ
የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ
ከቡና ጠረን ጋ
ከኔ መኖሪያ ቤት. . .
የምወደዉ ሸሚዝ ላይ
የሽቶ መአዛሽ
ከሴት ላቦትሽ ጋር
ደግሞም
እዚያ ዉብ ሆቴል ስር
ያስተረፍነዉ . . .
ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ
አንጀት ከሚበላ
ከቆንጆ ጥቅስ ጋር
‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’
.
ነበርን እስካሁን
በመሆን እያየሽ
ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ
ከምወደዉ ሸሚዝ
የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ
ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ
ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ
(ታዲያ ለምንድን ነዉ)
ያሳለፍነዉ ሁሉ
#አሁን_ትዝታ_እንጂ.....
#ዉስጡ_ህይወት_የለም
ብለሽ ለመንደሩ
ላገሩ ማዉራትሽ
እዉነት ለምንድን ነዉ?
.
.
.


By ኤፍሬም ስዩም

@getem
@getem
@paappii
ያልወረደ እንባ
.
ላዩኝ ሁሉ ደስተኛ  ነኝ እስቃለሁ፤
በነሱ ቤት መከፋትን  የት አዉቃለሁ፤
.
የሚገርመዉ.....

በኔ መፍካት መቅናታቸዉ፤
እኔን መሆን ምኞታቸው፤

መች ያዉቁና ማስመሰሌን፤
የዉስጥ ሀዘን ስዉር ቁስሌን፤

በዉስጤ ታጭቆ ሰላም የሚነሳኝ፤
በነጋ በጠባ ሆድ ሆዴን ሚበላኝ፤

አዉጥቼ እንዳልጥለዉ አፍኖ የያዘኝ፤
ሳቅ የሸፋፈነዉ ያልወረደ እምባ አለኝ።
.......................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@getem
@getem
።።።።።።።። መሀል።።።።።።።።።።።።

እያለቀሱ መሳቅ እየቀረቡ መራቅ
።። ላይለምድለት ሆዴ።።።።።።።።
እስቲ አትደሰት ፣ አትጨነቅ ባንዴ።
ቶሎ ሰፍ አትበል አትቸኩል ፣ አታርፍድ፣
ልቤ አትንጠልጠል ሆድህን አታልምድ።
እየቀረቡ መራቅ እያለቀሱ መሳቅ
።።። ላይለምድልህ ሆዴ።።።።።።።
እስቲ አትጨነቅ፣ አትደሰት ባንዴ፣
።።።።።።።። መሀል ሁን አንዳንዴ።።።


ገጣሚ:-papiel

@getem
@getem
@paappii
የፈሰሰ አይታፈስም
ትላንትና አይመለስም
ስኖር ያኔ ከጎናቹ
ውል ጥቅሜ ያልገባቹ
ምን ፍለጋ ምን ቀረና
ከደጃፌ ተገኛቹ?
.
በትላንቴ ሳልበገር
ወደፊቴ ገስግሻለው
የራስ ዋጋ ሚገባኝን
አሁን በደንብ አውቂያለው
እንደ ወትሮው ላልጎተት
ለአንድ እራሴ ቃል ገብቼ
ሚገባኝን ስላወኩኝ
አልፊያለው ሁሉን ትቼ
.
ባለሁበት ስላልቆምኩኝ
ተጨንቃቹ ተጠባቹ
ካመለጥኩት ትላንትና
ልትመልሱኝ ላሰባቹ
.
የጣልኩትን ዞሬም አላይ
እንኳን ቀርቶ ልመለከት
በመጣ እግር ተመለሱ
ደስተኛ ነኝ ባለሁበት

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@paappii
አግኝቼ ነበር
የህዝብ መድረክ ግጥም ማንበቢያ።
ታዲያ ግጥሙ
ወረቀት የለ ከስልክ አይቻል
በቃል ነው አሉ የሚነበበው
ምን ነክቶታል ሰው
ከግጥም መሃል አንቺን ብቻ ነው የማስታውሰው።

እና ችግሩ
ህዝብ ባለበት የተለፈፈ ህዝብ አፍ ላይ ያልቃል
አንቺ...
አደባባይ ላይ አትነበቢም እንደተራ ቃል።
ላንብብሽ እንጂ
ስውር አድርጎ እርሱ እንደሠራሽ
በቃሌ ይዤሽ ወጣሁ ካዳራሽ።

By Yadel Tizazu

@getem
@getem
@paappii
“ናልኝ” ቢሉህ ፥ ትመጣለህ
“ስጠኝ” ቢሉህ ፥ ትሰጣለህ
ቸር አይደለህ !
….
እኔስ ግን…
ምን ብዬ ልጠይቅ ?
ሕይወቴን ፣ ምን ላ’ርገው ?
እወቅልኝ እስቲ
ምንድነው ጌታዬ ፥ እኔ ምፈልገው ?

@getem
@getem
@paappii

By henock bekele
እርዕስ ስጡት!

ጦሩን አስከትሎ መጣ ገሰገሰ
ሊገዛን ባርነት ሀገሩን አሰሰ
እምዬ ሚኒሊክ ያ ቆራጡ ጀግና
ኢትዮጵያ ስትፋርስ ቆሞ መች ያይና
እቴጌ ጣይቱ ልበ ሙሉ መሪ
ለጦር ግንባር ሰጠች አይደለችም ፈሪ
ባልቻ አባ ነፍሶ የደግኖች አለቃ
ጠላት አንበርክኮ ህዝቡን የሚያነቃ
ነበሩ ሌሎችም የነፃነት ታጋይ
ለታላቋ ሰንደቅ የሆኑት ተጋዳይ
ለሶስቱ ቀለማት ደማቸውን አፍስሰው
አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን አርማ ይዘው
ጉዳይ ሳይኖራቸው ከአንድ ሀገር በቀር
አድዋን ድል አረጉ ሳይጠቅሱ ብሔር ዘር
አድዋ ነፃነት ነው ላልገባው አስረዳው
የሰላማችን ጥግ የነፃነት ጌጥ ነው
ጣይቱ ስትመራው ጦሩን ከፊት ቀድማ
ደግሞ ድል አረገች ብልጠቷን ተጠቅማ
እናማ አትልፉ
አታስቡ ይቅር ህዝቦቿን አትንኩ!
የማይፋቅ የማይሻር የደም ነው ታሪኩ ።
                
BY፦LIONEL YOHANNES

@getem
@getem
@getem
የኔታ

ሀሁ አቦጊዳ
ከፊደል ገበታ
ጭራቸውን ይዘው
ሲያስቀኙን የኔታ
ሀ ግዕዝ ሁ ካዕብ
ሂ ሳልስ ሃ ራብዕ
ብለን የቆጠርን ተቀምጠን ስራቸው
አንደበት ያስፈቱን ሊቀ ቀለም ናቸው
.
ወንጌለ ዮሀንስ ውዳሴ ማርያሙን
ቅዳሴ ሰዓታት ስርዓተ ፆሙን
ገድለ መልዓክትን ገድለ ቅዱሳናት
ህማመ ፋሲካን የስቃዩን ወራት
ሰብስበው ያሳዩን መንገደ ሥላሴን
ባህረ ሀሳብ ቀመር አቋጣጠር ጊዜን
.
በፈጣሪ ያሉ ዓለም ያልገዛቸው
የኔታ የሁሉም ባለውለታ ናቸው

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem
( እንደ ፎቶሽ...)
=============

አሳዩኝ ሰሞኑን በፎቶ ስትስቂ
ጨረቃ ስትከልይ
ጀምበር ስታስንቂ !
አሉኝ መመረጧ አቤት መታደሏ
በጨለማው ዘመን
ስትፈካ መዋሏ ....
( እውነት እውነት እውነት)
እኔም በአንክሮ አየሁ
ምስልሽን በጥልቀት

ሳቅሽ ያምራል በጣም
ወደር አቻም የለው ...
ግና
ልቤን የሚታገል አንድ ጥያቄ አለው

ኑሮሽም አለሜ ልክ እንደ ፎቶው ነው ?

By @kiyorna

@getem
@getem
@getem
አያልፉ ሚመስሉ ጨለማ ቀናቶች፤
እንቅልፍ የሚነሱ ረጃጅም ሌቶች፤

ሁሉም አለፉና....

ብርሃን ፈንጥቆ ፅልመቱ ተረታ፤
ማዘን መከፋቱም ስቃዩም ተገታ፤

በእንባ የጠቆረዉ ፊታችንም ፈካ፤
አሮጌዉ ተሸኘ በአዲስ ቀን ተተካ።

..............ተመስገን..........

By ዔደን_ታደሰ

@getem
@getem
@getem
ሳቄን ፡ ነው የቀማኝ ፡ ጥሎኝ ነው ፡ የሄደው ፣
የምበርበትን ፡ ክንፌን ነው ፡ የሰበረው ፣
ያጎረሰው ፡ እጄን ፡
ያጠባሁት ፡ ጡቴን ፡ እሱ ነው ፡ የነከሰው ፣
እምነቴን ፡ የሸጠ ፡ ቃሉን ፡ ሰባሪ ፡ ነው ፣
ያከበረው ፡ ደጄን ፡
የነገሰበትን ፡ የፍቅር ፡ አክሊሌን ፣
የተገዛለትን ፡ ቅዱሱን ፡ ገላዬን ፣
ጠብቄ ፡ ያቆየሁትን ፡ የመዉደድ ፡ ኪዳኔን ፣
እጅግ ፡ የከበረ ፡ መስታወት ፡ እምነቴን ፣
ሰብሮ ፡ ነው ፡ የሄደው ፡ አንካሳውን ፡ ልቤን ፣

እያልሽ ፡ የኔ ርግብ ፡ ስታወሪ ፡ ሰማሁ ፣
ቀድሜሽ ፡ ከሄድኩኝ ፡ እንዴት ፡ ኋላሽ ፡ ቀረሁ ?

                   ዘረ ሠናይ
              @Prince_Zeresenay

@getem
@getem
@getem
አየሽ!
ሁላችንም
"ሰው ታከተኝ" - ብለን የምንተነፍሰው
ሰው እንዲሆንልን - ለምንፈልገው ሰው።
.
.
አየሽ!
ሁላችንም - እንደዚህ ዝለናል
ሰዎች ሲሰለቹን - ሰው ይናፍቀናል።
.
.
አየሽ!
ለኔና አንቺም
ርቀቱ የሰፋው - አልግባባ ያልነው
ምናልባት ስገፋሽ - እየፈለግሁሽ ነው።
.
.
እንግዲህ እወቂው!
ማኩረፍ መቆጣቴ - ብሶ ተባብሶ
ፈጣሪ ሲረሳኝ - ሰባት ሰማይ ለብሶ
ለመቅረብ ሳስፈራ
አስታውሺኝ አደራ!
.
.
በሬን ከሌላው ቀን አጥብቄ ስዘጋ!
መግባት ባትችይ'ንኳ ስታንኳኪ ይንጋ።


____
The last Eulogy
By Henock Bekele

@getem
@getem
@paappii
አንድ ሞኝ አፍቃሪ.....
.
.
ጥርቅምቅም እዉቀቱን እያንጠፈጠፈ፤
ለሚወዳት እንስት እንዲህ ብሎ ፃፈ፤
.
አንቺ የኔ ፀሐይ....
.
ጨለማ ህይወቴን ፈንጥቀሽ ያበራሽ፤
ከልቤ ምጥገጥሚ ግጣም ኮከቤ ነሽ።
.
ከአፈር ያበጃጀሽ እግዜር እጁን ታጥቦ፤
ከሁሉም አብልጦ የሰራሽ አስዉቦ።
.
እንዲህ እንዲህ እያለ......
.
ቃላት አሰካክቶ ይገጥማል ይፅፋል፤
ዉበቷን ለመግለፅ ሲዳክር ይዉላል።

ከመቼ ጀምሮ?
.
እግዜሩም ላንድ ሰዉ ማድላትን ያወቀዉ ፤
እጁን ዉሃ ታጥቦ መፍጠር የጀመረዉ።
....................................
በዔደን ታደሰ ..@topazionnn

@getem
@getem
"እማ" እና "አባቴ" ዘይቤው ተቀይሮ
የፍቅረኛ ዲስኩር ሆኖ አርፏል ዘንድሮ
.
ትላንት ላወቃት ሞትኩልህ ላለችው
የፍቅር ቴክስቶች ለደረደረችው
ውሉ ካልተስማማት የፍቅራቸው መንገድ
ሌላውን ፍለጋ ለምትረማመድ
አምጥቶ ይችራታል የእናቱን መጠሪያ
ትላንቱ በልጦበት ካለው መጀመሪያ
ደክሟት ሳትታክት ለዚህ እንዳላበቃች
በመጪ አጅ ሁሉ ሺ ጊዜ ተተካች
.
ሴቷም ለጥሪዋ ቃል ጠፍቶ ይመስል
አንዱን ጎረምሳዋን ከአባቷ እኩል ስትስል
ሞትኩኝ አበድኩልሽ ብሎ ለጠቀሰ
ያሳደገ አባት መጠሪያው እረከሰ
አዝሎ ባያጠባ ፀንሶ ባይወልድም
የአባት መጠሪያ ላወቁት አይሰጥም
.
ግና ምን ያደርጋል ግልብጥብጥ ዘመኑ
ካሳደጉት በላይ መጪዎች ገነኑ
ጊዜው አልበቃ ብሎ ስያሜ ነጠቁ
ካጎረሰው እኩል ጎራሾች መጠቁ

ሚገባውን ለማይገባው አትስጡ

በኪሩቤል አሰፋ @Ebuh_bhr

@getem
@getem
@getem