FinTech Frontier
3.76K subscribers
1.03K photos
65 videos
1 file
1.09K links
Disclaimer: Content shared here is for educational purposes only and should not be considered financial advice.

Support team @Teamsupport2022
Download Telegram
⭕የሰው ልጅን ደህንነት መጠበቅ፡ የሠራተኛ ኃይል ማረጋገጫን (Authentication) ዘመናዊ ማድረግ

➡️አጥቂዎች (Attackers) ይበልጥ ውስብስብ የሆኑ ዘዴዎችን እየተጠቀሙ ነው፣ እነዚህም የይለፍ ቃል መርጨት (credential spraying)፣ በግትርነት የመሞከር ጥቃቶች (brute-force attacks) እና የይለፍ ቃሎችንና የአንድ ጊዜ የይለፍ ቃሎችን (OTPs) የሚሰርቅ ማልዌር (malware) ይገኙበታል።

➡️በተጨማሪም፣ ፑሽ-ቦምቢንግ (push-bombing) ወይም የMFA ድካም ጥቃቶች (MFA fatigue attacks) ተጠቃሚዎችን በሞባይል ፑሽ ማረጋገጫ ማሳሰቢያዎች በማጥለቅለቅ፣ በስህተት የማጽደቅ ዕድላቸውን ይጨምራሉ።

➡️እነዚህ ተጋላጭነቶች አደጋን መከላከል ያልቻሉ እና ድርጅቶችን ለገንዘብ፣ ለዝና እና ለሥራ ላይ ጉዳት የሚያጋልጡ የቆዩ የማረጋገጫ ዘዴዎችን በአስቸኳይ መተው አስፈላጊ መሆኑን ያመለክታሉ።
❤1
ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ የ11 ቢሊዮን ዶላር መዋዕለንዋይ ሊያፈስ ነዉ።

የጃፓኑ ሶፍትባንክ ኩባንያ በኦፕን ኤ.አይ ያለውን ኢንቨስትመንት ለመደገፍ 11 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ቦንድ ለገበያ ሊያቀርብ መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል። ኩባንያው 10 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዶላር እንዲሁም 1 ቢሊዮን የሚያወጣ ቦንድ በዩሮ ለመሸጥ እየተዘጋጀ ነው።
ከቦንድ ሽያጩ የሚገኘው ገንዘብ ሶፍትባንክ ግሩፕ በኦፕን ኤ.አይ ፈሰስ ለሚያደርገዉ መዋዕለንዋይ የሚዉል መሆኑ ተነግሯል።

የቦንድ ሽያጩ በታቀደው መጠን ከተጠናቀቀ 7 ኢለቨን (7-Eleven) የተሰኘዉ ኩባንያ በአዉሮፓዊያኑ 2021 ይዞት የቆየውን የ10.93 ቢሊዮን ዶላር የቦንድ ሽያጭ ሪከርድ የሚሰብር ይሆናል።

የተዘጋጀዉ ቦንድ በተያዘዉ መስከረም የመጨረሻ ቀናት ለሽያጭ ለማቅረብ መታቀዱም ተገልጿል።

ሶፍትባንክ እና ኦፕን ኤ.አይ ከዚህ በፊት በጃፓን በኤ.አይ የታገዙ አገልግሎቶችን ለማጠናከር ብሎም በአሜሪካዉ የኤ.አይ መሠረተ ልማት ፕሮጀክት (ስታርጌት ) ላይ በጋራ ሲሰሩ ቆይተዋል።
❤2
የሚፈልጉትን የብድር/ፋይናንስ አይነት መርጠው
ባሉበት ያመልክቱ፤ ባሉበት ይከታተሉ!
**
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድርጅቶች ለሥራቸው እና ንግዳቸው ማስፋፊያ የሚያስፈልጋቸውን ብድር/ፋይናንስ እንዲሁም ግለሰብ ደንበኞች ለቤት፣ ለመኪና፣ ለግል ጉዳይ እና ለሌሎች ጉዳዮች የሚያስፈልጋቸውን ብድር/ፋይናንስ መጠየቅ ሲፈልጉ ወደ ባንክ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት የብድር ጥያቄያቸውን ማቅረብ እና መከታተል የሚያስችላቸውን ዲጂታል ስርዓት ለመደበኛ እና ለሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች ተግባራዊ አድርጓል።

አዲሱ ዲጂታል የብድር ማመልከቻ እና መከታተያ ስርአት፡

✅ ለድርጅት ወይም ግለሰብ ደንበኞች ብድር/ፋይናንስ ባሉበት ማመልከት ያስችላል

✅ የሁሉንም የብድር/ፋይናንስ አይነቶች ተፈላጊ ሰነዶች ዝርዝር ማየት ያስችላል

✅ ለብድር/ፋይናንስ ብቁ መሆንዎን ማረጋገጥ ያስችላል

✅ የድርጅትዎን ወይም የግለሰብ ደንበኞችን የብድር/ፋይናንስ ማህደር ማደራጀት ያስችላል

✅ የብድር/ፋይናንስ ማመልከቻዎ የደረሰበትን ደረጃ ባሉበት መከታተል ያስችላል።

ቀጥሎ በተመለከቱት ማስፈንጠሪያዎች በመግባት በባንካችን ዲጂታል የብድር ማመልከቻ እና መከታተያ ፖርታል ተመዝግበው፣ ባሉበት፣ ምቾትዎ እንደተጠበቀ ብድርዎን ያመልክቱ፤ ይከታተሉ!

👉 ለድርጅትዎ ብድር/ፋይናንስ ባሉበት ማመልከት እና መከታተል የሚያስችለውን ፖርታል ለማግኘት በ https://cbewholesale.cbe.com.et ይግቡ

👉 ግለሰብ ደንበኞች ባሉበት ብድር/ፋይናንስ ማመልከት እና መከታተል የሚያስችለውን ፖርታል ለማግኘት በ https://cberetail.cbe.com.et ይግቡ።

**
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
❤1🔥1
ቲክቶከሮች ሚሊዮን ብር ከአዋሽ ባንክ ተሸለሙ

አዋሽ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የፈጠራ ክህሎት እና ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች አወዳድሮ በመሸለም የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት ባንኩ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀውን የአበባየሆሽ/ሽኖዬ የቲክቶክ ቻሌንጅ ውድድር የማጠቃለያ እና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ ባህላዊ ሬስቶራንት በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።

​በዚሁ ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ በውድድሩ የላቀ የፈጠራ ሥራ አቅርበው ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ደረጃን የያዙ ወጣቶች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዚህም መሠረት Bootina አንደኛ በመውጣት የ1 ሚሊዮን ብር ስትሸለም Iamsamson 500ሺ ብር ተሸላሚ ሆኗል፣ Maria Luna የ300 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናለች።

​በተጨማሪም ተወዳዳሪዎቹ Biniye21 የ150 ሺህ ብር፣ Fikade Unkuraa የ100 ሺህ ብር፣ እንዲሁም Edu sine እና Fiyorii እያንዳንዳቸው የ75 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት አሸናፊ በመሆን ተሸልሟል።

አዋሽ ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የፈጠራ ክህሎት እና ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በተለያዩ ዘርፎች አወዳድሮ በመሸለም የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት ባንኩ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀውን የአበባየሆሽ/ሽኖዬ የቲክቶክ ቻሌንጅ ውድድር የማጠቃለያ እና የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም በዮድ አቢሲኒያ ባህላዊ ሬስቶራንት በደመቀ ሁኔታ አካሂዷል።

​በዚሁ ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ላይ በውድድሩ የላቀ የፈጠራ ሥራ አቅርበው ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ ደረጃን የያዙ ወጣቶች የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በዚህም መሠረት Bootina አንደኛ በመውጣት የ1 ሚሊዮን ብር ስትሸለም Iamsamson 500ሺ ብር ተሸላሚ ሆኗል፣ Maria Luna የ300 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆናለች።

​በተጨማሪም ተወዳዳሪዎቹ Biniye21 የ150 ሺህ ብር፣ Fikade Unkuraa የ100 ሺህ ብር፣ እንዲሁም Edu sine እና Fiyorii እያንዳንዳቸው የ75 ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት አሸናፊ በመሆን ተሸልሟል።
❤2
gmail farmer bot

✅ ሰወች ይሄ bot  አሪፍ ስለሚከፍል በደንብ ስሩ🎁

Gmail  Farmer pro
ከበፊቱ ክፍያውን በ እጥፉ 🚨

✅በ 1 Gmail 0.16-0.25$ ከ 30ብር እስከ 50ብር እንደማለት ነው
✅10 Gmail = 2.5$ = 500Birr✅

💠ስራውም ከበፊቱ ጋር ተመሳሳይ ነው GMAIL ACCOUNT መክፈት ነው በጣም ቀላል ነው የሰራቹትንም ብር በቀላሉ መቀበል ትችላላቹ✌️

🔺ደግሞ ደስ የሚለው ነገር ብዙ ብር የምታገኙበትን አማራጭ ይዛል እና ምን ትጠብቃላችሁ ወጥራቹ ስሩ እንጂ fam🍸

ሁላችሁም አሁኑኑ ጀምሩት⬇️⬇️⬇️

👥Link:
https://t.me/GmailFProBot?start=591787031
🔥1
ዩቱብ ለይዘት ፈጣሪዎች አዳዲስ የኤ.አይ ስርዓቶች አስተዋወቀ

ዩቱብ የይዘት ፈጣሪዎች ሥራቸውን በብቃት እንዲያቀላጥፉ የሚያግዙ አዳዲስ የኤ.አይ ስርዓቶችን በዩቱብ ስቱዲዮ አስተዋውቋል። አዲሱ «አስክ ስቱዲዮ» (Ask Studio) የተባለ የጥያቄና መልስ ዘዴ ፈጣሪዎች ስለ ቻናላቸው መረጃዎችን እንዲጠይቁና የቪዲዮ ሐሳቦችን እንዲያመነጩ ያስችላቸዋል።

እንዲሁም ፕላትፎርሙ ያልተጫኑ ቪዲዮዎችን ፍጥነት፣ አወቃቀርና ታሪክ አቀራረብ በመገምገም የማሻሻያ ሐሳቦችን ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪ ከቪዲዮው ይዘት ጋር የሚስማሙ ርዕሶችንና እስከ ሦስት የሚደርሱ የሽፋን ምስሎችን (Thumbnails) በኤ.አይ ማመንጨት የሚቻል ሲሆን እነዚህም ምስሎች ለተለያዩ ተመልካቾች በማሳየት የትኛው የተሻለ ውጤት እንደሚያመጣ መፈተሽ ያስችላሉ።

ኩባንያው የትንታኔ መሣሪያዎቹንም በማሻሻል፣ የቪዲዮዎችን አፈጻጸም በቁጥር ብቻ ከማሳየት ባለፈ ለምን ውጤታማ እንደሆኑ ወይም እንዳልሆኑ ዝርዝር ማብራሪያና ምክር ይሰጣል።
የAI ቴክኖሎጂ እየጎለበተ በሄደ ቁጥር በማህበራዊ ሚዲያና በኢንተርኔት የምናያቸው ምስሎች፣ ቪዲዮዎችና ድምፆች በAI የተሰሩ መሆናቸውን መለየት ትልቅ ፈተና እየሆነ መጥቷል።

Google ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስችል SynthID የተሰኘ  Platform አስተዋውቋል።

በዚህ Platform አማካኝነት በGoogle AI የተሰሩትን ብቻ ሳይሆን በOpenAI, NVIDIA, Kakaoና በቅርቡ ደግሞ በApple AI  አማካኝነት የተፈጠሩ ይዘቶችን በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል።

ለመጠቀም
synthid.com ላይ ከገባችሁ በኋላ በGoogle አካውንታችሁ login ታደርጋላችሁ።
ከዛ ማረጋገጥ የፈለጋችሁትን ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም ድምፅ በማስገባት check ማድረግ ትችላላችሁ።
❤2
http://ChatGPT.com (solve any problem)
http://supenli.ai (Create viral content)
http://Perplexity.ai (research anything)
http://Suno.ai (compose music)
http://Canva.com (design graphics)
http://ElevenLabs.io (clone voices)
http://Grammarly.com (perfect writing)
http://heygen.com (Clone yourself)
http://RecCloud.com (summarize YouTube)
http://Runway.ml (edit videos)
http://Descript.com (edit podcasts)
http://Syllaby.io (create faceless videos)
https://skysnail.io/ (create viral thumbnails)
Don’t lose this list, it could be incredibly helpful.
የአፍሪካ ልማት ባንክ የ10 ቢሊዮን ዶላር የኤ.አይ መርሃ ግብርን አስጀመረ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ጋር በመተባበር የአፍሪካን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ ያቀደበትን "AI 10 billion" መርሃ ግብር ወደ ትግበራ ማሸጋጋሩን አስታወቀ።

ባንኩ እንዳመለከተው ይህ ፕሮጀክት በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ውስጥ በዓመት 1 ቢሊዮን ዶላር በማስተባበር እ.ኤ.አ 2035 ድረስ 25 ሚሊዮን አዳዲስ የስራ እድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው።

የባንኩ የ2025 ሪፖርት እንደሚያሳየው አካታች የኤ.አይ አጠቃቀም በተለይም በግብርና፣ ንግድ፣ አምራች፣ ፋይናንስ እና ጤና ዘርፎች ላይ በማተኮር ለአህጉሪቱ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) እስከ 1 ትሪሊዮን ዶላር ሊያበረክት ይችላል።

የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት ሰለሞን ኳይኖር እንደተናገሩት የመርሃ ግብሩ ዋና አላማ የመንግስትና የግል ዘርፍ ኢንቨስትመንቶችን በማቀናጀት የኤ.አይ ጥቅሞች ወደ ተወዳዳሪነት፣ የስራ እድል እና አካታች እድገት መቀየር ነው።

ፕሮግራሙን በ5 ሀገራት በመጀመር እስከ 2027 መጨረሻ ድረስ ወደ 20 ሀገራት ለማስፋፋትና የልማት አጋሮችን ለማሳተፍ ታቅዷል።
Invest in learning Claude properly. You will thank yourself 6 months from now.