ፍሬያማ ሀሳቦች
212 subscribers
125 photos
10 videos
17 files
21 links
Welcome to this channel
Download Telegram
እሷ አታውቅም

እወዳታለሁ እኮ እሷ አታውቅም፥ትናፍቀኛለች እሷ አታውቅም፣ሁሌ አስባታለሁ እሷ አታውቅም፣ተደብቄ እንደማያት እሷ አታውቅም።

ህይወት ጨለማ ናት ስል ብርሃን ሆና ከጎኔ አገኛታለሁ።ወንድነቴ እየፈተነኝም ቢሆን ተደብቄ ከማነባበት ፈገግ የምለው መኖሯን ሳስብ ነው።

ለካስ ሰው አለኝ።የማይጠብቀኝ የምጠብቀው፣የማያውቀኝ የማውቀው፣የማያየኝ የማየው እያልኩ እፅናናባታለሁ።

እሷ ለእኔ መብራቴ ናት በጨለማዬ ውስጥ ብርሃን የማይባት፣መሸሸጊያዬ ናት ህሊናዬ እረፍት ሲያጣ እያሰባት የሚያርፍባት ምን ዋጋ አለው እሷ አታውቅም።

✍️Giyanna
💔1
እነሱ እንዲህ ናቸው። ጥቁርና ነጭ፣ውሃና ዘይት የማይቀላቀሉ።መኖሪያቸው ለየቅል ነው፣መንገዳቸው መንታ፣ሀሳባቸው ግራና ቀኝ
ግን አንድ ነገር አለ ያዋሃዳቸው፣ባያስማማም ያገናኛቸው ልባቸው ነው።

ልዩነታቸው የሆድ እና የጀርባ ያህል፣የሰማይና የምድር ያህል ይራራቃል።ለዚህ ነው ፍቅር ብቻ በቂ ያልሆነው።

ልዩቶቻችንን አንድ በማድረግ እንኖራለን የሚለው የሀገራችን ፖለቲከኞች መፈክር ለእነሱ ፍቅር አልሰራም።

ፍቅር ብቻ በቂ አይደለም🙅‍♀

Giya

@FreamaHasaboch
@FreamaHasaboch
ቁምነገር አውርቼ ከየት ሰማሽው ሲሉኝ ካንተ ነው የምላቸው....እግዚአብሔር ከአዳም አጥንት ሄዋንን ሰራት እንደተባለው።

የእኔም ማንነት የተሰራው ባንተ ነው። አንተን ሳላውቅህ በፊት ነጭ ወረቀት ነበርኩ ....ነጭ መሆኔ ግን ካንተ ለመግባባት አላገደኝም ምክንያቱ የእውቀት መጨረሻው ትህትና መኖርያው ካንተ ዘንድ ነውና።

ለምጠይቅህ ነገር ሁሉ የምትሰጠኝ ማብራሪያ .... የማወቅ ጉጉቴን ያንረዋል። ምኞቴ አንተን መሆን ወደ መፈለግ ይመጣል።

እንዳንተ ነገርን ከስር መሰረቱ መመርመር በቻልኩ እላለሁ። እንዳንተ ወግ አፌላይ ባማረልኝ። እንዳንተ እውቀት እና ትህትና በተስማሙልኝ። ትንሽ ሳውቅ ይሄንን የማያውቅ አለ እኮ ብሎ ልቤ ከመታበይ ቢዘገይልኝ እላለሁ።

እመኛለሁ። ብቻ አንተ ህይወቴ ውስጥ ባትኖር የአሁኗ እኔ እኔን መሆኗን እጠራጠራለሁ።

ነፂ_ነኝ

#ነፃሁኑልኝ


@NetsaAleme
ሁለት ሰወችን አጥቻለው አንዱን በሞት አንዱን በሕይወት
💯1
ደሞ እንደገና


ቀረብኩት ያልኩት ሲርቅ፣የካብኩት ፍቅር ሲናድ፣ያዝኩት ያሉኩት ሲሄድ ፍቅር እጅ እጅ አለኝ።

ድንገት ግን ተሸራርፎ ለቀረው ልቤ አንድ ሰው መጣ።ስብራትሽን ካልጠገንኩ አለ፣ህመምሽን ካልታመምኩ፣ጎዶሎሽን ካልሞላሁ ሞቼ እገኛለሁ አለ።ዘራፍ አፈቀርኩሽ 😊

ጥሩነቱን ባልክድም።እኔ ግን ዳግም እራሴን ማብራራት አልፈልግም።እንደገና መጠናናት፣እንደገና ፀባዬን ከፀባዩ ለማግባባት የምጥርበት አቅም አልነበረኝም።
ደሞ እንደገና መተዋወቅ ?!ይቅርብኝ ብዬ ተውኩት።

ቢቀር አይሻልም?

✍️Giyanna

@FreamaHasaboch
@Myppoem
3
ልቤ ልብ የለውም

ማስተዋሌን የተነጠኩባትን ቀን ባውቃት አበቀላት ነበር።ብልጥ ነበርኩ እኮ ።ምን ዋጋ አለው በነበረ ቀረ።

አያቴ በፊት ላይ የረጠበ እጇን የለበሰችው ሺቲ ላይ እየጠረገች ልጄ እድሜ ያስተምርሻል ብላኝ ነበር።

እኔ ግን ሳድግ ባሰብኝ።እምቢ ለማለት ይሉንታ እያነቀኝ ከስንቱ ገደል ወረወረኝ።

አይዞሽ ባዬ ሁሉ ወዳጄ መሰለኝ።እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ድንገት ፍቅር ብርቅ ሆነብኝ።ወደድንሽ ካሉኝ ሁሉ ተወዳጀሁ፣እመኚኝ ቢሉ አመንኩ።

የአያቴም የዘመናት ምክር ውሃ በላው።እንዲህ በሰዎች ስመሰቃቀል ብታይ ምን ትለኝ ይሆን!
ምክሯ ቢከመር ዳሽንን በበለጠ።እንጃ ሲበዛ ነው መሰል አእምሮዬን ትቶ የሸሸው

ልቤ ግን ልብ ያጣው መቼ ነው?!

✍️Giyanna

@FreamaHasaboch
@Myppoem
3💯1
ፈገግ በይ ሁሌ ፈገግታሽ አይጨልም
የበረደው ነፍሴን..
ያሞቀው ጥርስሽ ነው ፀሀይ እኮ አይደለም
አንቺ የሰው ልኬት የእንስቶች አውራ
ስለደግነትሽ እንዴት ብዬ ላውራ?
ምንስ ቃል ቢሰደር የትኛውም ስንኝ
አይገልፅሽምና በጥሞና ስሚኝ
ልመርቅሽ ነውና ባላረጀ እድሜዬ
አሜን ብቻ በዪ 'ባይሆን እንደ እምዬ
የነካሽው ሁሉ እንደ ውበትሽ ይመር
በእድሜሽ ላይ እድሜሽ እንደ ኤሊ ይጨምር
በየደረሽበት ዓለም ሁሉ ያርግድ
አንቺ ያለሽበት ሀዘን ሁሉ ይታገድ
ሊጥልሽ የመጣ ተንገዳግዶ ይውደቅ
ፊትሽ በፈገግታ ዘለአለሙን ይድመቅ
አሜን በዪ ኑሪልኝ የኔ ወርቅ።😘


የጓደኝነት ጥግ❤️

✍️Giyanna
19/12/2018

@Myppoem @Myppoem

@FreamaHasaboch
❤‍🔥3
ይቅርታ አትጠይቁኝ ጥሌ ከራሴ ጋራ ነው በእናንተ
አልተናደድኩም።እንታረቅ አትበሉኝ ገና ከእራሴ ጋር አልታረኩም።

Giya

@FreamaHasaboch
🔥2
መንገድ ዳር ሸንኮራ የተከለ ገበሬ ና
ቆንጆ ሚስት ያገባ ችግሩ አንድ ነው።

አንድ የሆነችው ጸሀይ ፣ ሻማውን ታቀልጣለች፣
ሸክላውን ደሞ ታጠነክራለች።

ፍሬክ ላይ ያረፈን ነፍሳት ለመግደል እጅግ እጅግ በጣም ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

አሞራ ምን ያህል ከፍ ብሎ ቢበር ሲርበው ወደ መሬት መውረዱ አይቀርም

ፊልም እያየህ አንዱ ጓደኛ ይገባና ፊልም እያየህ ነው ይልሀል!!
አይ ቲቪው እኔን እያየኝ
❤‍🔥2
አንቱ የምለው ሰውዬ ፍቅር ያዘኝ ሲል እኮ ነው ህይወት ሚዛኗን እንደሳተች የተረዳሁት።😊

Giya

@FreamaHasaboch
@Myppoem
😁2
ማኩረፍ አለብኝ?!
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''

ሁሉም ነገር ትርጉም እንዳያጣብኝ እፈራለሁ አለችኝ በደከመ ድምፅ።

ከዚህ ቀደም የማውቃት አልመስል አለኝ።ጨዋታዋና ለፍላፊነቷን ለለመደ ሰው ይህ ዝምታና ግራ መጋባቷ ያስደነግጣል።ትክለለኛውን ነገር መናገር አለመናገሯ ጥያቄ እየፈጠረብኝም ቢሆን ምን ሆነሽ ነው? አልኳት።

ሁሉም ነገር ትርጉም እንዳያጣብኝ ፈራለሁ።

እንዴት?

ተውቂያለሽ ልጅ ሳለሁ ጭፈራና ድግስ ደስ ይለኝ ነበር።ካደኩ በኋላ ግድ አልሰጥ አለኝ።እንዲያውም ለድግስ ተብሎ የሚወጣው ያላስፈላጊ ወጪ ያናደኝ ጀመር።ከዚያ ምን አልኩ እድሜ አመጣሽ ማገናዘብ ነው ብዬ አለፍኩት።

እና ? አልኳት ዋና ነጥቧ ጋር ለመድረስ ፈልጌ

እና የሆነ ጊዜ ላይ ደሞ ፍቅር ያምረኝ ነበር።ፍቅር ስልሽ ፊልም እንደምናየው አይነት ፍቅር።አብሮ መዝናናቱ፣አንዱ አንዱን ማበርታቱ ፣ቅድሚያ መሰጣጠቱ፣መነፋፈቁ፣አብሮ መሳቅ መጫወቱ ነበር ከፍቅር የምወደው ፓርት።

አሁንስ ካልሺኝ ፍቅረኛ አለኝ ግን ያኔ አስብ የነበረው አይነት ህይወት አይደለም ያለን።እንዲያውም ካልሽኝ መጃጃል ብዬ መፈረጅ ጀምሪያለሁ።

ደሞ የሆነ ጊዜ ላይ የሰርግ ሙዚቃ ወይም መዝሙር ስሰማ ውስጤ ለሰርግ ይነሳሳል።ደስ የሚል የሰርግ ፕሮግራም እንደሚኖረኝ አምን ነበር።አሁንስ? አሁን አጠገቤ ከበሮ ቢደለቅ እንኳ ያን ስሜት ማምጣት አልችልም።

ልጅ አዝለው የሚሄዱ እናቶች ሳይ እናትነት ደስ የሚል ነገር እንዳለሁ ይሰማኛል ግን ደሞ ይሄን ስሜትም አንድ ቀን እንደማጣው አስባለሁ።

ቦታው ላይ ስደርስ ሁሉም ነገር ትርጉም እንዳያጣብኝ ፈራለሁ።

ለሰርጌ ጓጉቼ ሽር ጉድ በማለት ፈንታ በግድ እንደምትዳር ሴት ግድ አጥቼ ትርጉም አልባ የሰርግ ቀን እንዳላሳልፍ እፈራለሁ።

በፊት የምጓጓላቸው ነገሮች ላይ ግድ እያጣው መምጣቴን ፈራዋለሁ።


ሁሉም ነገር ደስ የሚለው ጓግተው ሲያገኙት ነው።🤝እንጃ ብቻ ብላ ደገፍ አለች።

ልክ እኮ ናት ግን ደሞ ገና ለገና አንድን ጥሩ ስሜት ላጣው እችል ይሆን ብሎ ማኩረፍ ምን ይሉታል
ለነገሩ እኔም ለሰዎች ችግር ግድ ማጣት ከጀመርኩ ቆየሁ እኔም ማኩረፍ አለብኝ እንዴ 🤔


✍️Giyanna

Join & Share

@FreamaHasaboch
@FreamaHasaboch
@FreamaHasaboch
2
ዮሃንስ

አፄ ዮሃንስ የሸዋ መሳፍንት እንደሚያደርጉት ራሳቸውን ከሰለሞናዊ ዘር ጋር የማቆራኘት ዝንባሌ አልነበራቸውም።
የአፄ ዮሃንስ የዘር ግንድ ከአጤ ፋሲል ጋር የተያያዘ ነው።የፋሲል (የልጅ ልጅ -አሞስተኛ ትውልድ የሆነችው )መና እስራኤል አያታቸው ናት።

የአፄ ዮሃንስ ማህተም ላይ በአረብኛ
''ንጉሰነገስት ዮሃንስ ፣ንግሰ ጽዮን ዘኢትዮጵያ ፣ዘእምነገደ እስማኤል'' ይላል።

እስማኤል አብርሃም አጋር ከተባለች ገረዱ የወለደው ልጅ ስም ነው።

የአቡነ ተክለሃይማኖት (ተክልዬ)የስጋ ዘመድ ይኩኖአምላክ ዘሩን ቆጥሮና ተርትሮ ንጉስ ሰለሞን ላይ ሲያደርስ አጤ ዮሃንስ ደግሞ ከሸዋ ተረት ጋር ለመፎካከር በሚመስል መልኩ ከዚያም በላይ ርቀው የዘር ግንዳቸውን እስማኤል አብርሃም ላይ አደረሱት። 😁


✍️Giyanna (ካነበብኩት)

@FreamaHasaboch
@Myppoem
💯2
ትዝብት ነው ትርፌ
'''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''''

ስለ እርሱ ሳስብ ከሰው ተደብቄ ከእራሴ እንደምጣላ አያውቅም።ድብብቆሹ ታዲያ በአእምሮዬ እና በልቤ መሃል የቀረ አኩኩሉ ነው።

ማንነቴን በማንነቱ ስለካው ቲሽ አንቺ የሰው ከንቱ እንዴት አርጎ ቢያይ አንቺ ላይ ጣለው ብዬ ከእራሴ እሟገታለሁ።


አንዳንዴ ደሞ ፈጣሪ እንዴት ቢወደኝ እሱን ሰጠኝ ብዬ በአምላኬና በስጦታው መሀል ደማቅ ጥያቄ ምልክት አኖራለሁ።

በውሸት ያልተሽሞነሞነ እሱነቱን እወደዋለሁ።እንደ አንዳንድ አዳሞች ጣል የሚያደርገው አቁስል ንግግር የለውም።

ሳወራው መንፈሴ ይታደሳል።ልክ ባህር ዳርቻ ሄዶ እንደመዝናናት፣ህልሙ ሁሉ እንደሞላለት አይነት፣እረፍት እንዲሰማኝ ያደርገኛል።

ሰላሜን በቅፅበት የሚቀማኝ ግን እንደሚሆንልኝ መሆን ባልችልስ የሚለው ሀሳቤ ነው።በተወደድኩት ልክ ባልወድስ?

ሂሊናዬን የሚገርፈው ባልችልስ የሚል ጅራፍ ያለማቋረጥ ይመላለስብኛል።

ሚዛኔን ላለመሳት ስል ለመፈቀር ሳታንሺ እንዴት ለማፍቀር ታንሺያለሽ ብዬ እራሴን የማፅናናበት አንድ ድምፅ ድንገት ሹክ ይለኛል።

እፎይ! እላሉ።ልክ ነኝ ለምንም አላንስም።ለብዙ ነገሮች የበላይ አርጎ እራሱን የሚስለው ማንነቴ የሚተናነሰው በእርሱ ፍቅር ሲለካ ብቻ ነው።


እሱ እንዲህ ነው እኔ ግን እንደዚህ ብዬ ብዘረዝር ትዝብት ነው ትርፉ።እንደ ገለባ ሁሉ ቀልዬ እንዳልገኝ ፈራለሁ።

ደሞ እኮ አላፍርም ልባሟን ሴት መሆንም ያምረኛል።ፈጣሪዬ ሆይ ማስተዋልን አድለኝ የምለው ለዚህ በዛብኝ የምለውን ሰው ሳስብ ነው።


መወደዴን እወደዋለሁ።መዉደዴ እንዳያንስ እስክሰጋ ድረስ።


✍️ @Giyanna19


@FreamaHasaboch
1
ጷጉሜ አንድ


እንደ ሀሳብ ለምን የደራሲያን ቀን አንለውም እ ?

መፅሐፍ ላስመረቁ ፣የካሜራ አይን ለሰለቻቸው ሳይሆኑ እንደ ነገሩ የሚሞነጫጭሩ ደራሲያን እና ገጣሚያን Happy ጷጉሜ
one🤗

Giya

@FreamaHasaboch
👍2
ደሞ ደሞ ...
አዲስ ዓመትን ተገን አርጋችሁ እንኳን አደረሳችሁ በሚል ተልካሻ ምክንያት ልታናግሩን የተዘጋጃችሁ ሰዎች ቢቀርባችሁ ጥሩ ነው።

Giya

@FreamaHasaboch
@Myppoem
1💯1
For more info. @Giyanna19

Without any payment
በደሌ ልክ የለውም ወደ ቀጣይ አመት ከነ በደሌ አታሳልፈኝ አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ🙏🙏🙏

@FreamaHasaboch
🙏1