Focus On Christ
124 subscribers
274 photos
82 videos
20 files
80 links
ቆላስይስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤
²⁹ ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ።
@Focusonch
@Focusonc
Download Telegram
ወደ መንፈስ ቅዱስ ሙላት በጣም ካልተጠጋን፣ የእግዚአብሔርን ቃል በእግዚአብሔር መንፈስ ውስጥ ሆነን ካላነበብን፣ የተረጋጋ መንፈሳዊ ህብረት ከእግዚአብሔር ጋር ከሌለን፣ ድምፁን ካልሰማን እና በውስጣችን የሚፈሰውን የመንፈስ ቅዱስ እርካታ ካላጣጣምን እና ካልተሰማን፣ በቅድስና ህይወት ለመኖር ስጋችንን ካልገደብን
ሁልጊዜ ደጅ፣ሁልጊዜ social media፣ ሁልጊዜ ከጓደኛ ጋር ጨዋታ፣ ሁልጊዜ የራስ ነገር፣ሁልጊዜ ትምህርት፣ሁልጊዜ ስራ ከሆነ ህይወታችን
የእግዚአብሔርን ፈቃድ አናውቅም።እውነተኛውን የእግዚአብሔርን ፍቅር እና የመንፈስ ቅዱስን ህልውና አናስተውልም።ምን ማድረግ እንዳለብን እንኳን ግራ ይገባናል።ጊዜው ይረዝምብናል።ምናደርገው ሁሉ ይሰለቸናል።እረፍት እናጣለን።
ከዚህ የከፋው የአግዚአብሔርን ነገር(መንፈሳዊውን ነገር) በስጋዊ አዕምሮአችን እንተረጉማለን።የእግዚአብሔርን መንግስት ጉዳይ ሌላው እንደሚለው እንላለን።
ከሌሎች የምንለይበት መለያ መስመሩ ይደበዝዛል።ከሌላው ጋር ተመሳሳይ የህይወት ምልልስ ይኖረናል።
ጊዜ መስጠት ላለብን ጊዜ እንስጥ! ማስቀደም ያለብንን እናስቀድም!
#ዛሬ #እስቲ #ይህን #ቃል #ይዛችሁ #በእግዚአብሔር #ፊት #በእንባ #ቅረቡ!!👇
ያዕቆብ 4:÷7_10
@Focusonch
የፊታችን እሁድ ከሰአት ከ 9 ጀምሮ በመሐል ከተማ ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን የጌታን ፀጋ እንካፈላለን!

@Focusonch
.    የዛሬው መልዕክቴ ልዩ ነው! ለምትወዱት ሁሉ አጋሩልኝ!

ውስጣችሁ እየፈለገ፣ ልቦናችሁ እውነትን እያወቀ፣ አንድ ያልተመለሰ ትልቅ ጥያቄ ውስጣችሁ እየጮኸ እየሰማችሁ፣ የጎደላችሁ ውስጣዊ ዕረፍት እና መረጋጋት እንዳለ እያስተዋላችሁ፣ ነገ ምን እሆን? ከሞትኩ በኃላ መጨረሻዬስ ምን ይሆን? እያላችሁ ለምትጨነቁ! ምን አልባትም ይህን ሁሉ ጩኸት አፍናችሁ ዝም ለማሰኘት እና በተለያዩ ሰዋዊ ስርአቶች ለመመለስ የምትሞክሩ እናንተ የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር እጅ ስራዎች፤ ዛሬ የፈጠራችሁ የሚወዳችሁ በእጆቹ ያበጃሁ ፈጣሪያችሁ መድሀኒትን ሊሰጣችሁ እና ሊያድናችሁ ይፈልጋል።
ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ባለማመን ሀጢያት ውስጥ ካለ ሁልጊዜም በጨለማ መንግስት ባርነት ስር ነው ያለው።የዚህ ጨለማ መንግስት ገዢው ደግሞ ጨካኝ የሆነው ሰይጣን ዲያቢሎስ ነው። ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ ካላመነ ይህ ሰይጣን እንደተፈረደበት ሁሉ ከእርሱ ጋር ቅጣትን ይቀበላል።(ቅጣቱ ምን ይሆን?🤔 አስቡት እስቲ)
ሰይጣን ደግሞ እጅግ ክፉ ነው።ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን እንዳይድኑ፣ ከእርሱ(ከሰይጣን) ጋር ፍርድን እንዲቀበሉ፣ ልባቸው እውነትን እንዳያውቅ፣ ቢያውቁ እንኳን እንዳያስተውሉ፣ ቢያስተውሉ እንኳን ጌታ ኢየሱስን ወደ ማመን እና ወደ መከተል እንዳይመጡ በማድረግ፣ እንዲያውም የሚወዳቸውን ወዳጃቸውን ጠላታቸው፣ አዳኛቸውን አጥፊያቸው፣ መንገድ የሆነውን ኢየሱስን ተራ ግለሰብ በማድረግ ሰዎችን ከህይወት ያጎላል።
ለዚህ ነው መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር:-
“ለእነርሱም የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን አሳብ አሳወረ።”
  — 2ኛ ቆሮ 4፥4      ይላል።
ስለዚህ ከዚህ እውነት ያራራቃችሁን ሰይጣን አትስሙ።ልባችሁንም በሽንገላው አታታሉ።
#በኢየሱስ #ክርስቶስ #በማመን #የዘላለምን #ህይወት #በነፃ #አግኙ
#ኢየሱስ #ክርስቶስን #በማመን #በውስጣችሁ #ያለውን #ሌላው #ሊያረካው #የማይችለውን #ጥማት #አርኩ! #እውነተኛ #ዕረፍት #በሚሰጠው #በኢየሱስ #ክርስቶስ #እመኑ!!!
( በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ማለት ምን ማለት ይሆን?)
“የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”
  — 1ኛ ዮሐንስ 5፥20
በአጭሩ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፤ የዘላለም ህይወት የሚሰጥ ብቸኛ አዳኝ እንደሆነ፤ ከእርሱ በቀር የዘላለም ህይወት የሚሰጥ ማን እንደሌለ ማመን ማለት ነው።
እናንት የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር እጅ ስራዎች ኑ ወደ እግዚአብሔር ልጅነት! ኑ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች ሁኑ!
ልባችሁን አትዝጉ! መወሰን ያቃታችሁ ወስኑ!

@Focusonch
. እንጋደል! እንድከም!
ክርስቶስን ለመስበክ እና ክርስቶሰን ለማስተማር ተጋደሉ።እውነተኛ የክርስቶስን ማንነት እና ግብሩን ለማወቅ ለመማር ተጋደሉ።
ብዙ ክርስቶስን የጋረዱ ሰዋዊ ስርአቶች፣ ከንቱ ፍልስፍናዎች፣ የስህተት ትምህርቶች ሞልተዋል። ትውልዱን አሳውረው ክርስቶስን እንዳያውቅ ለማድረግ የክፉ ሀይላት የተለያዩ መንገዶችን ተጠቅመው ትውልድን እያጠፉ ነው።
ብዙዎች የክርስቶስን መኖር ባይክዱም ስለ ክርስቶስ ግን የተሳሳተ መረዳት ነው ያላቸው።
ጌታ አንተ! አንቺ! እኔ! እውነተኛውን የክርስቶስን እንድናውቅ እና እንድናስተምር ይፈልጋል።
ከበፊቱ ይልቅ ዛሬ እንትጋ! እንጋደል! ዋጋን እንክፈል! እንድከም!
ቆላስይስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ እኛም በክርስቶስ ፍጹም የሚሆን ሰውን ሁሉ እናቀርብ ዘንድ ሰውን ሁሉ እየገሠጽን ሰውንም ሁሉ በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤
²⁹ ለዚህም ነገር ደግሞ፥ በእኔ በኃይል እንደሚሠራ እንደ አሠራሩ እየተጋደልሁ፥ እደክማለሁ።
ልክ ጳውሎስ እንዳለው! እግዚአብሔር በሚሰጠን ኃይል መጠን እውነተኛውን ክርስቶስ በማስተማር እና በመስበክ እንጋደል!

@Focusonch
ወንጌል በተለያዩ ቦታዎች ሲሰበክ የአከባቢውን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ Contextualized ሆኖ ነው። Contextualization በወንጌል ስብከት ውስጥ አስፈላጊ ነገር ቢሆንም ለቅይጣዊነት ወይም ለ Syncretism አደጋ እንዳይዳርገን ግን መጠንቀቅ አለብን።
ምክንያቱም በወንጌል ይዘት ውስጥ ከሌሎች እውነቶች ጋር፣ከሌሎች ባህሎች ጋር፣ ከሌሎች አስተሳሰቦች ጋር የማይቀላቀሉ ብቸኛ እውነቶች ስላሉ እና እነዚህ ብቸኛ እውነቶች ከተቀላቀሉ የወንጌሉን ይዘት እና እውነት ስለሚቀይሩ ነው።
ከእነዚህ ብቸኛ እውነቶች አንዱ አምልኮ ነው። ላነሳ የፈለኩትም ሀሳብ ስለዚሁ ነው። ምክንያቱም ደግሞ ይህ የመስከረም ወር በአደባባይም ይሁን በስውር የተለያዩ የአምልኮ ስርአቶች ስለሚደረጉ ነው።
በአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጲያን ጨምሮ ወንጌል ከመሰበኩ በፊት ሰዎች በተለያዩ የመናፍስት አምልኮ ውስጥ እንደሚኖሩ ግልፅ ነው።ምንም እንኳን አንድ አምላክ እንዳለ ቢያምኑም አምልኮተ ስርአታቸው ግን በእኛ ላይ የመወሰን አቅም አላቸው ብለው ለሚያምኑባቸው መናፍስት ነው። በእርግጥ አሁንም በዚህ ህይወት ውስጥ ያሉ አሉ። ምንም እንኳን የአንድ ቤተ እምነት ተከታይ እንደሆኑ ቢያውጁም በስውር ይህን አምልኮ ያካሂዳሉ።
ወንጌል ከተሰበከ እና ወንጌል ከገባ በኃላ ብዙዎች ከዚህ ነፃ ቢወጡም አንዳንዶች ግን በቅይጣዊነት( syncretism ) አደጋ ተይዘው ቀርተዋል።
ተመላኪ መናፍስቶቹም ይህ አምልኮአቸው እንዳይቋረጥ ውጩን "ለአንድ አምላክ" በሚል ሽፋን የሚደረገውን አምልኮ ይቀበላሉ። ለዚህ ምሳሌ እንዲሆን ብዙዎቻችን እንደምናውቀው አብዛኞቹ ክፉ መናፍስት በተለያዩ የቤተ እምነት በአላት ላይ ነው መስዋዕት የሚቀበሉት። ምክንያቱም አምላኪዎቹ ከሌሎች እንዳይለዩ እና አምልኮአቸው ለፈጣሪ እንዲመስል ስለ ተፈለገ ነው።
በእርግጥ ክፉ መናፍስት ቀን ለይተው በግልፅ የሚመለኩበት ጊዜ አለ።ይህንም ከባህል እና ከሌሎች ነገሮች ጋር ቀላቅለው ሰው እንዲያመልካቸው እያደረጉ ነው።
ጥናት ቢያስፈልገውም ጥቂት የማይባሉ የወንጌል አማኞች በዚህ የክፉ መናፍስት አምልኮ ላይ በቅይጣዊነት ምክንያት ይሳተፋሉ።
የእግዚአብሔር ቃል ግን አምልኮ ላይ በደንብ ጥንቃቄ እንድናደርግ ያሳስበናል።ምክንያቱም ለምናመልከው ነገር ተገዢ ስለሆንን።
ለእግዚአብሔር ብቻ አምልኮአችሁን አቅርቡ!
“ስሙ ቀናተኛ የሆነ እግዚአብሔር ቅንዓት ያለው አምላክ ነውና ለሌላ አምላክ አትስገድ።”
  — ዘጸአት 34፥14
አውቃችሁ የምታደርጉ ሀጢያታችሁ ግልጥ እንዲሆን እና ንሰሀ እንድትገቡ፤ የማታውቁ እንድትጠነቀቁ እንደ ታናሽ ወንድም🙏

ለሌሎችም አድርሱልኝ!
@Focusonch
እናንት የክርስቶስ ወንጌል ሰባኪዎች አስተማሪዎች፣ እውነተኛውን የሚያድነውን የእግዚአብሔር ፀጋ የምትሰብኩ ሰባኪዎች፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ እግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የዘላለም ህይወት በእርሱ እንደሆነ የምታውጁ፣ ሰውን ወደ ክርስቶስ የምትጠሩ የእግዚአብሔር ቃል ሰባኪዎች፤ ጌታ ይህን ቃል እንዳካፍላችሁ በውስጤ አክብዷል።

“ይህን በሙሉ ሥልጣን ተናገርና ምከር ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።”
  — ቲቶ 2፥15
በዚህ በቲቶ ምዕራፍ ሁለት ላይ ከዚህ ከፍ ባለው ቁጥር ላይ ጳውሎስ ስለ ተገለጠው የእግዚአብሔር ፀጋ እና ስለ አዲኛችን ስለ ኢየሱስ ከተናገረ በኃላ ቲቶን ይህን ቃል እየተናገረ ያበረታታዋል ያደፋፍረዋል። ይህን በሙሉ ስልጣን ተማገር ይህን በሙሉ ስልጣን አስተምር ይህ የሚያድን ህይወትን የሚሰጥ ቅንጣት ታህል እንኳን ስህተት የሌለበት የማያጠራጥር የእግዚአብሔር እውነት ነው። ስለዚህ በሙሉ ስልጣን ተናገረው ይለዋል።ምከር! ገስፅ! ይለዋል። እንዲሁም ደግሞ ማንም አይናቅህ ይላል።
ስለዚህ እናንት የቃሉ አስተማሪዎች፣ የክርስቶስ ሰባኪዎች፣ በርቱ! ይህን ቃል በሙሉ ድፍረት በሙሉ ስልጣን አስተምሩ ስበኩ። የምትሰብኩት እውነት ነው።የምትሰብኩት የዘላለም ህይወት ነው። የምትሰብኩት ቅንጣት ታህል እንኳን እንከን የሌለበትን ክርስቶስን ነው። እርሱን በሙሉ ስልጣን ስበኩ! አስተምሩ! ምከሩ! ገስፁ!
ይህን ትውልድ ነፃ የሚያወጣ ህይወትን የሚሰጥ ከክርስቶስ ውጪ ሌላ የለም!
ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ የእገዚአብሔር ልጅ ያድናል!!

@Focusonch
ፍጥረት ከብዙ ቢሊየን አመት በፊት በትልቅ ፍንዳታ ነው የተፈጠረው፤ ሰውም በዝግመተ ለውጥ ከዝንጀሮ ነው የመጣው የሚሉት የሰዎች ፍልስፍና የእውነት ይገርመኛል። በእርግጥ እምነት ብንለው ነው የሚቀለው። ምክንያቱም አምነውት እንጂ ተጨባጭ መረጃ ሆነ ማስረጃ እስከ አሁን አላገኙለትም። ይህን እነሱም አይክዱም።እንደውም ጥናት ባደረጉ ቁጥር ተስፋ ወደ መቁረጡ እያመሩ ስለሆነ። ስለዚህ ይህን የዘመኑ ፍልስፍና ክህደት ያመነጨው እምነት ብንለው ምንሳሳት አይመስለኝም።
እና የሚገርመኝን ስነግራችሁ ሳይንስ ፍጥረት ከብዙ ቢለየን አመት በፊት በሂደት ነው የተፈጠረው እንጂ ማንም የፈጠረው የለም ሲል ማንም አስልቶ ሆነ አስቦ ወደ ኃላ ጥናት አድርጎ እንዳይደርስበት( ይሄ ባዮቹንም ይጨምራል) አመቱን ማስረዘማቸው ቢያስቀኝም ሳስበው ግን ልክ ናቸው እላለሁ። ምክንያቱም ይሄ የሚታየው ፍጥረት እጅግ ትልቅ ነው። እንኳን ለመፍጠር የተፈጠረውን አጥንቶ ለመድረስ አይቻልም። ሰው እንኳን ተጠንቶ አልተጨረሰም። ፍጥረት እጅግ ጥልቅ ነው።
እናም እንዲህ ዘመኑን ያራቁት እና በአንዴ ሳይሆን በለውጥ ሂደት መጣ ያሉትን እግዚአብሔር ግን ይሁን በሚለው ቃል በልጁ አለማትን ፈጠረ። ለእርሱ ጊዜም አልፈጀበትም። ሰው ይህን ያህል ዘመን ይፈጃል ያለውን ፍጥረት እግዚአብሔር በቃሉ በስድስት ቀናት ፈጠረ። ኸረ ክብር ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሁን። እነርሱ ዘመኑን ማራቃቸው እና ክህደታቸው አያስገርምም ምክንያቱም ከተፈጥሮ በላይ የሆነው እግዚአብሔርን አልተረዱትም።
እና ፍጥረቱን ያልተረዱትን የእጁን ስራ እንኳን መረዳት ያልቻሉ ሰነፎች እንዴት ፈጣሪውን ይረዳሉ። እግዚአብሔር የለም ቢሉ ምን ይገርማል እኒህ ሰነፎች። እግዚአብሔር ግን በዙፋኑ ለዘላለም ይኖራል። ክብር ለእርሱ ይሁን።
ይሄን ትልቅ እግዚአብሔር ነው ምናመልከው።
እናም በጣም ሚገርማችሁ ተፈጥሮ ከገለጠልን የእግዚአብሔር ትልቅነት በላይ ደግሞ በኢየሱስ ክርስቶስ ያገኘነው መገለጥ ደግሞ ኸረ ሁሁሁሁ ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ!
ኸረ ጌታ ስሙ ይባረክ።
እናንት በክርስቶስ ያማናችሁ የዘላለም ህይወት ያገኛችሁ የእውነት እድለኞች ናችሁ። ጌታን አመስግኑ!

በዚሁ አጋጣሚ ከትልቅ ትህትና ጋር "ኢትዮጲያ የሰው ዘር መገኛ ናት ምትሉ" ክርስቲያኖች ግን ስርአት ያዙ የእውነት! ለምን እንዲህ ተባለ ብላችሁ መርምሩ!😂

@Focusonch
የጎደለን ሲኖር ባለን በሌላኛው እንደሰታለን። ጉደለታችን እና ያጣነው ነገር ሀዘኑን አብዝቶ፥ በጨለማ እንዳይዘፍቀን ያለንን በማሰብ እና በመቁጠር ራሳችንን እንመክራለን፤ ከዚያ ሀዘን ለመውጣት እንሞክራለን። ይሄ ብዙዎቻችን ራሳችንን የምናፅናናበት መንገድ ነው። ሰዎችም የሚመክሩን ይህን ነው።
ለምሳሌ፦ አንድ ጓደኛ ሲከዳችሁ እና ልባችሁ ሲያዝን ሌሎች ብዙ ጓደኞች እንዳሏችሁ ወይም ደግሞ ብዙ አማራጭ እንዳላችሁ በማሰብ ራሳችሁን ትመክራላችሁ። ልክ እንዲሁ በሌሎች የህይወት አቅጣጫዎችም እናደርጋለን።
ታዲያ እንዲህ አይነቱ ሰው ለምን ተስፋ ይቆርጣል? ለምን በህይወት ይዝላል? ካልን መልሱ ግልፅ ነው!
ሰው በህይወት፥ የሚዝለው፣ተስፋ የሚቆርጠው፣ ሀዘን የሚበረታበት፤ ያጣው ነገር በዝቶ ያለው ትንሽ እንደሆነ ሲያስብ ነው።
ባለው ራሱን አፅናንቶ በሌለው ልቡ እንዳይሰበር ለማድረግ ሲነሳ ያለው አንሶበት ያጣው እልፍ ይሆንበታል። ያን ጊዜ ሀዘን በርትቶበት የወዳጆቹ ማፅናናት አቅም ያጣል፤ ጨለማ ከቦት ህይወት ይከብድበታል፤ መኖሩ ትርጉም አጥቶ ሞትን ያስመኘዋል።
አንተ በክርስቶስ አምነህ የዳንክ ሰው! ምን አልባት ብዙ እንዳጣህ ተሰምቶህ ባለህ ነገር ራስህን ማፅናናት የከበደህ! የገጠመህ ምንም ይሁን፤ በምንም እዘን፤ ምንም ነገር እጣ፦
አይኖችህን ሽቅብ አንሳ፥ በሰማይ የቀረልህን በክርስቶስ ያገኘኸውን የዘላለም ህይወት ተመልከት። ሀሳብህን ሰብሰብ አርገህ ወደ ውስጥህ አድምጥ መንፈስ ቅዱስ እያወራህ ነው። ይህን ካንተ ማንም አይወስድብህም። መቼም አታጣውም። ይህ እግዚአብሔር በልጁ የሰጠህ ስጦታ ስለሆነ ከአንተ ሊነጥቅ ወይም ከልክሎ ሚያሳዝንህ አንዳች አቅም ያለው የለም። ደግሞስ ከዚህ የሚበልጥ ምን ሀብት፣ ምን ተድላ፣ ምን በረከት አለ ብለህ ነው? በእውነቱ የለም። ስለዚህ ከምታገኘው ነገር በላይ በክርስቶስ ያገኘኸው ብዙ ነው። ካጣኸው እና ከተወሰድብህ ያለህ ክርስቶስ እልፍ ነው። ስለዚህ መሰለህ እንጂ ያለህ ነው የሚበልጠው!!

ባለን የዘላለም ህይወት በድነታችን እርፍ እንበል፤ በእርሱ እንረጋጋ! ውስጣችን ባለው በመንፈስ ቅዱስ እንደሰት፤
ተስፋችንን በዚህ እናድርግ። ይህች ምድር እንደሆነች አገኘንም፤ አጣንም። በለጠግንም፤ ደኸየንም። ዝነኛ ሆንም፤ ተረሳንም። ማለፏ ግድ ነው። የማያልፈው ያገኘነው የዘላለም ህይወት በክርስቶስ ያገኘነው የዘላለም ተስፋ ነው።


በእርሱ እንመካ🙏

@Focusonch
ችግርማ አለ እኮ፤ አይካድም። የውድቀቱም ወለል ርቋል፤ ድፍረት ጥጉ የትየለሌ ነው። አመፃ እና እርኩሰቱን ሆድ ይፍጀው። አለማዊነት እና አለምን መውደድ የአደባባይ ምስጢር ሆኖ በግልፅ ይታያል፤ ንዋይን ማፍቀር፣ ዝነኝነትን መፈለግ ዋናው ትኩረት ሆኖ ሁሉም ለእርሱ ይለፋል።
ተልዕኮውማ ተረስቷል። ተከታይ ማፍራቱም ችላ ተብሎአል። መለያ ልብሱ እና ክህነቱ ተጠርገው ከቤተ መቅደሱ ወጥተዋል። ራሱ መጤ አካሎቹ ደግሞ ርዕስ ሆነው ለእነርሱ ይዘፈናል።
እንጃ ልዩነቱ አይታይም! የተለያየ መንግስት ይሁን አንድ? መስመሯ፣ ድንበሩም ደብዝዘዋል።
ታዳሚውም ድራማው የተስማማው ይመስላል፤ ዝም ይላል።
የህይወት ዘመን መመሪያ፣ የላዩን ማወቂያ፣ ከጥፋት ማምለጫ እንዲሆን የተፃፈውን መልዕክት የያዘ ያለ አይመስልም፤ መኖሩንስ ያውቅ ይሆን?
ደግሞ ትንሽ አየት ሲደረግ ያነበቡትም ያሉ ይመስላል። ግን ደግሞ በትክክል ይሁን አይሁን ግራ ያጋባል። ሚያውቁም ይመስላል። ግን ጭንቅላት ውስጥ ብቻ የቀረ ይመስላል።
ኦኦኦ አያልቅም ወንድሜ!
ችግሩን እንተወው በቃ! ማብራሪያም አያስፈልገውም ግልፅ ነው፤ መፍትሄው ግን ለትውልዱ ያስፈልጋል።

ፅድቅ ይገለጥ እና ርኩሰቱ ይሸማቀቅ!
ቅዱሱ ተገልጦ ነውር የሆነው ይዋረድ!
ዋናው ተገልጦ ቀሪው ይሰወር!

@Focusonch
Channel photo removed
በቅርቡ ነው ታክሲ ውስጥ አንድ የሬድዮ ፕሮግራም ላይ ዜና ይተላለፋል፣ እናም ከዜናዎቹ ውስጥ አንዱ ዜና አስገረመኝ፤ ነገሩ የተፈፀመው ከባህር ባዶ ፈረንጆች ዘንድ ነው። እናም ነገሩ በአጭሩ እንዲህ ነው፥ " ባልና ሚስት ብዙ ጊዜ በተደጋጋሚ ይጋጫሉ። እናም ባልየው
ሚስትን ይደበድባታል፤ ኋላ ይህ ነገር ገፍቶ ባል ሚስቱን ለመግደል ሽጉጥ ይመዛል። ከዚያም ሁልጊዜ ለመገላገል መሐል ሚገባው ልጃቻው ሊገላግል ሲሞክር ለእናቱ የተተኮሰ6ው ጥይት እርሱን አግኝቶት ይገለዋል ። እናም አባትም ራሱን ያጠፋል። ነገሩ ካለፋ በኃላ እናት ስለ ልጇ ስትመሰክር 'መቼም ልትረሳው እንደማትችል እና ልጇ ለእርሷ ያለው ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ እንደተረዳች' ተናገረች፤" ይህ እንደሰማሁት እውነተኛ ታሪክ ነው!
ነገር ግን ከታሪኩ ጌታ ያስተማረኝን ነገር የተረዳሁት የዛኑ ዕለት አንድ ሰው ጋር ካወራሁ በኃላ ነው!
ይህን ታሪክ የሰማሁ ዕለት ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ሆነን አንድ በጌታ ያልሆነ ሰው ታሪኩን ያጫውተን ጀመር፥ እና ሲያወራ ከነካኝ እና ውስጤን ካዘለለው ነገር ፥ ስለ ኢየሱስ ሲናገር " እንኳን ስለ እኔ ሀጢያት በመስቀል ላይ ዕርቃኑን የሞተልኝን እና ድነት የሚያስገኘውን እና የዘላለም ህይወት የሚሰጠውን የኢየሱስን ሞት ቀርቶ አንድ ሰው መንገድ ላይ መኪና እንዳይገጨኝ ሲከላከል መኪናው እሱን ቢገጨው እና ቢሞት መቼም አልረሳውም፤ ስለ እርሱ ሁሌም ነው የማወራው።" አለን!
እና ይህን እያመነ ታዲያ እንዴት በጌታ አይደለም ትላለህ እንዳትሉኝ፤ መወሰን ይጠይቅ የለ?
እና የኢየሱስ ስለ እኛ በእኛ ፈንታ መሞቱ እና በእርሱ ሞት ህይወት ማግኘታችን ከዚህ በላይ እውነት ነው!
ምዕራፍ የቀየርንበት፣ ሞት የተሻረበት ፣ ህይወት ያገኘንበት ነው!!
ምን ያህል ገብቶኝ ይሆን?
@Focusonch
@Focusonc
#ቤተ #ክርስቲያን #ደጅ #ወጥታለች!

"ሂዱ ተብለን ነው" ይላል ሰባኪው፤ ዛሬ አንድ ታክሲ መጠበቂያ ስፍራ ላይ ሰባኪው ሲሰብክ ነው ይህን የሚለው።
እውነቱን ነው፤ ተልኮ ነው። ትዕዛዝም ጭምር።
የምስራች ሰምቶ ታላቅ ምስጢር ተገልጦለት ዝም የሚል፣ አደባባይ የማይወጣ የለም። ከዚህም በላይ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ ያስቀመጠው የነፍሳት ሸክም እረፍት የሚሰጥ አይደለም!
ሳስብ የነበረው፥ ቤተ ክርስቲያን ደጅ ወጥታለች፣ የወንጌል እውነት በህዝቡ ላይ እየተረጨ ነው፤ ልክ እንደነ ጳውሎስ ወንጌልን ይዞ አደባባይ የሚወጣ ትውልድ ጌታ ዛሬም አለው፤ ብዬ አሰብኩ።
በእርግጥ በዚህ አገልግሎት የማይሰማሙ እና መቀለጃ ሆነናል፥ ህዝቡም አይሰማንም፥ ድምፁም የሚረብሽ ነው የሚሉ ከእኛው ወገን የሆኑ አሉ።
ከዛሬው የተሰማኝን ልንገራችሁ፥ በመጀመሪያ እንደምናስበው አይደለም፤ የሚታደሉትን ወረቀቶች ጠይቀው የሚወስዱ እና አይናቸውን ነፍገው ጆሮአቸውን ጣል የሚያደርጉ አሉ። አፋቻው ስድብ የሚያወጣ ልባቸው ደግሞ እውነታውን የሚሰማ ሰዎችም አሉ።(በእርግጥ የሚታደለውን ወረቀት የሚፀየፉ እና ድምፁንም ላለመስማማት የሚሸሹ እንዳሉ ነው።) ሁሉም ደግሞ ሊቀበለን አይችልም።
ነገር ግን፥ አደባባይ ወንጌልን ይዘው ለመመስከር የሚወጡ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል የተረዱ እና የሚያነቡ ቢሆን፣ በፀሎት የሚተጉ እና በመንፈስ ቅዱስ እለት የሚሞሉ ቢሆን፣ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የተያዙ እና ህብረት የሚያደርጉ ቢሆን፣ ጥበብ የተሞሉ እና ቃሉን እንዴት መስበክ እንዳለባቸው ከመንፈስ ቅዱስ የተማሩ ቢሆን፣ ውስጣዊ መግፍኤ ሀይላቸው( motive አቸው) ተልዕኮው እና የነፍሳት ሸክም እንዲሁም ሰዎችን መውደድ ቢሆን፤ ቤተ ክርስቲያን ደጅ በመውጣቷ ታተርፋለች፣ የሚረጨው የወንጌል እውነት ብዙ ያፈራል።
በአጠቃላይ መፍትሔው ወንጌል የሚያድነው ደግሞ የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!
@Focusonch
@Focusonc
#ጥቂት #ዘወርታ

ሀይማኖታዊው ህግጋቱን ለመፈፀም ከሚሰሩት ስራ፣ ከሚማሩት ትምህርት፣ ከሚጫወቱት ጨዋታ፣ ብቻ ከማንኛውም ስፍራ አቋርጠው ይወጣሉ። መንገድ ላይ እንኳን ቢሆኑ፥ እዛው መንገድ ላይ ህግጋት ነውና ያደርጉታል፤ አያፍሩበትም። ጥቂት ቆይታ ናት፤ የሀይማኖቱ ግን መሠረታዊ ስርአት ነው። በእስልምና ሃይማኖት ካልተሳሳትኩ፥ የ "ሰላት" ስግደት ይባላል፤ በቀን አምስት ጊዜ ሚሰገድ። ይህን ነው፥ በየትኛውም ስፍራ፣ ምንም አይነት ስራ ቢይዙ የማይዘነጉት።
እናም ዛሬ ያሰብኩት፥ በምንሰራበት ስራ ቦታ፣ በምንማርበት ት/ቤት፣ በምናሳልፍበት ቦታ ሁሉ ለጥቂት ጥሞና እና ለጥቂት ፀሎት ዘወር ብንል፤ ጌታን ብናወራው እና ፈቃዱን ብንጠይቅ፤ በሳትንበት እና ባጠፋነው ምህረት ብንጠይቅ፤ ፀጋን ያበዛልን ዘንድ ደግሞ ወደ ፀጋው ዙፋን ብንቀርብ፤ ይህች ጥቂት ዘወርታ ትባርከናለች። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቂያ፣ አቅምን መቀበያ፣ መፍትሄን ማግኛ፣ መፅናኛ፣ መታደሻ ትሆነናለች።

@Focusonch
@Focusonc