“የማይረሱትን አንርሳ”
“ዘአኮ ይኤምፅ እግዚአብሔር -እግዚአብሔር ውለታን አይርሳም” እብራ ፮፥፲
ልማዱ ቸርነት የሆነ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ለሰው ራሱ ጸጋን የሰጠ ሲሆን በሰጠው ጸጋ ደግሞ ውለታ ዋላችሁልኝ ብሎ ዋጋ ይከፍላል።በሰው መዳን ደስ የሚለው ከመሆኑ ርኅሩኅ ከመሆኑ የተነሣ እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ወርዶ መናኛን ስጦታ ለምክንያተ ድኂንነት ይፈልጋል ።ሰውን የሚምርበት ነጥብ ያህል ቀዳዳ ካገኘ ገብቶ ጸዳለ ብርሃኑን ያሳድርበታል። እግዚአብሔር ቅዱሳንን ሙሉ ሕይወታቸውን ስለ ሰጡት ለዚህ ራስን መስጠታቸው ክብር ቃል ኪዳን ይገባላቸዋል።ኃጥአንን ደግሞ ቅዱሳንን በማገልገል የእኔን ስም አክብራችኋል ብሎ ምሕረት ያድላል።ለዚህ ነው ቅዱስ ጳውሎስ “ እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመፀኛ አይደለምና።” እብራ ፮፥፲ በማለት የገለጸው።
ከዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮ በመነሣት የኦርቶዶሳዊነት አንዱና ዋናው መታወቂያ ውለታን አለመርሳት ነው።ስለዚህም እግዚአብሔርን አገልግሎ ያረጀ እንኳን ሰው ዕቃ ክብር አለው።ይኸውም ይታወቅ ዘንድ የተሰበረ ፣ጽዋ፣ የተቀደደ ጥላ፣ ወይም ሌላ ንዋየ ቅድሳት በዕቃ ቤት ይቀመጣል እንጂ ተሰብሯል፣ አርጅቷል ተብሎ አይወረወርም።ንዋያተ ቅድሳት የታጠቡበት ማይ እንኳ ጉድጓድ ተቆፍሮ ይፈሳል እንጂ በሜዳ አይደፋም። እግዚአብሔርን ያገለገሉ ዕቃዎች እንኳ የቅድስና ማዕረግ አላቸው።በቅዱስ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው እንኳን በሕግ የገቡ ዕቃዎች አመፀኛ ካህናት ያለ ሕግ ወደ መቅደስ ያስገቧቸው ማዕጠንታት በክብር እንዲቀመጡ እግዚአብሔር አዟል።“በኃጢአታቸው ሰውነታቸውን ያጠፉትን የእነዚያን ሰዎች ጥናዎች ጠፍጥፈህ ለመሠዊያ መለበጫ አድርጋቸው፤ በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋቸዋልና የተቀደሱ ናቸው፥ ለእስራኤልም ልጆች ምልክት ይሆናሉ።”ዘኁ፲፮፥፴፰ እንዲል።
እንግዲህ ምን እንላለን ?እግዚአብሔርን ያገለገሉ ዕቃዎች አርጅተው፣ተሰብረው፣ተቀደው እንኳ የማይጣሉባት ቤተ ክርስቲያንን ውስጥ ሆነን ዘመናቸውን ለክርስቶስ ሰጥተው የኖሩ አበው ሊዘነጉ ይገባልን? በፍጹም !
አሁን አሁን እያየነው ያለው ነገር ግን ይኸው ነው፤ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያገለገሉ መምህራን ሲያረጁ ለመቃብር ቤት፣ለብቸኝነት እየተዳረጉ፤ ዝና በዝና እየተተካ እየተመለከትን ነው።ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከገ ግርማ ሞገሳቸው ሳሉ ብፁዕነትዎ፣ብፁዕነትዎ የሚላቸው ስፍር ቁጥር የለውም።በአደባባይ በሽንገላም ጭምር የምንወዳቸው ፣የምናከብራቸው ብፁዕ አባታችን የሚለውስ ቢሆን? አንድ ጊዜ ቅድስት ቡራኬያቸውን ፈልጌ ብለው የሚያንዣብበውም ልክ የለውም።
በአረጁ፣በታመሙ ጊዜ ግን እንኳንስ በወረፋ ተጠርቶም የሚመጣ የለም።የወንድ መኳንንቱ የሴት ወይዘሮው ሁሉ ፍለጋቸውም አይገኝም።አሁን አንድ ጥያቄ እንጠይቅ? ሌላው ቢቀር “ቀድሞ ቡራኬዎትን ፈልጌ ነበር ማግኘት እችላለሁ?” ስንል የነበርነው ሲያረጁ ከቤት ፣ሲውሉ መቅረታችን አገልግለው ሲደክሙ ቡራኬያቸው ቀነሰን? ይልቁንም ይጨምራል እንጂ።
ይህንን ያልኩት የደጉ አባታችንን የብፁዕ አባታችንን የአቡነ ዕንባቆምን ዕረፍት ተከትየ በዚያው አረጋውያን ሊቃነ ጳጳሳትን፣ መምህራንን፣ካህናትን እንድናስብ ነው።
ብፁዕ አባታችን አቡነ እንባቆም ብዙ ቀርቤ አብሬያቸው ባልኖርም ያወቅኋቸው ግን ከስምንት ዓመታት በፊት ኢየሩሳሌምን ለመሳለም ሒጄ ሳለ ነው።ብፁዕ አባታችን ፊታቸው ብሩህ፣ገራገር፣ግርማ ሞገስ ባለው አቋማቸውና ጸጋቸው ላይ ራሳቸውን ባዶ (simple ) አድርገው ለሰው የሚያቀርቡ አባት ሆነው ነበር ያገኘኋቸው።ከመንበረ ጵጵስናቸው ጠርተውን ሲያበሉን ሲያጠጡን ውለው ሸኝተው በዚያ ታላቅ ኃላፊነትና የሰው ብዛት ውስጥ እያሉ ደግመን መምጣትና አለመምጣተችንን ቆጥረው የሚያውቁ እረኛና ለጋስ የምር አባታችን ናቸው።ብፁዕ አቡነ ዕንባቆም በሲመተ ጵጵስናቸው ታላቅ፣ በሀገረ ስብከታቸው ሩቅ ቢሆኑም ልባቸው ከጉባኤ ቤት ያልራቀ፤ ነፍሳቸው ከአብነት መምራን አትሮንስ አጠገብ የቆመች የደቀ መዛሙርት አባት ናቸው።በቅርብ ዓመታት ውስጥ ኢየሩሳሌም ደግሜ ለመሳለም ሒጄ ሳለ ብዙ እንግዶች በዝተው ሳለ በዚያ መሃል ውስጥ እኔ ብፁዕ አባታችን ልመለስ ስለሆነ ሰላም ለኪ ይድገሙልኝ ስላቸው “ለመሆኑ ደቀ መዛሙርቱ ምን ይበላሉ? እስኪ ተመልሰህ በሌላ ጊዜ ናና እኔ ራሴ ሕዝቡን ልለምን ” እያሉ እንደ እናት ከውስጠኛው ሰውነታቸው በሚደመጥ ቃል የተናገሩኝን አልረሳውም።
ነፍሰ ኄር ብፁዕ አባታችን አቡነ ዕንባቆም እየሞቱም ቤተ ክርስቲያንን ለማገልገላቸው ምልክቱ በሚያስጨንቅ ሕማም ውስጥ ሆነው እንኳ ባለፈው መስከረም 50000 ብር ለቤተ ጉባኤያችን ደቀ መዛሙርት ቀለብ ሰጥተውናል።
ቡሩኩ ጻድቅ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ጌታ የምታርፍበት ጊዜ ደርሷል ሲላቸው ከወደድከኝ ለምን የመስቀል ላይ መከራህን አልሳተፍም?እንደ ሰማዕታት ለምን በመከራ አልሞትም? ሲሉት “ በአስጨናቂ ሕማም ታርፋለህ” ብሏቸው ነበርም። ብፁዕ አባታችንንም በአቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም በምናኔ፣በደቀ መዝሙርነት፣ በመምህርነት፣በጸባቴነት አገልግለው ነበርና፣መጨረሻቸውን በአስጨናቂ ሕማም በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም በማረፋቸው ጌታ ውለታቸውን ቆጥሮ በረከተ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን እንዳሳተፋቸው በእምነት እናስተውላለን።
እንዲህ ያሉ አባቶችን በቤት ሲውሉ፣ሲያረጁ፣ ሲደክሙ፣ የማይዘነጋ ልብ ይስጠን።
ብፁዕ አባታችን ሆይ በነፍስ ባርከው በሥጋ መግበው የሚያስተምሩን ልጆችዎ እኔና ወንድሞቼ ደቀ መዛሙርት ልብ የሌለው ልባችን ቢዘነጋ እንኳ በተቀደሰች ጸሎትዎ አይርሱን።
አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
ከርእሰ ገዳማት ወአድባራት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ቤተ ጉባኤ
ጥር ፲፱-፳፲፰ ዓም

❤157😢36🙏14💔14😭11🕊10👍5
Forwarded from ፈውስ መንፈሳዊ ዘጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ መጻሕፍተ ጉባኤ ሚዲያ Fewus Menfesawi / ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ / Aba Gebrekidan Girma
YouTube
🔴 እግዚአብሔርን ማስቀደም || እጅግ ድንቅ ትምህርት በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ Aba Gebrekidan New sibket 2026
ልጄ ሆይ ባለ መድኃኒትን ስማ ሕማምህን ቸል አትበል” መ.ሲራክ ፴፰፥፩
“ሐዋርያዊ ጉባኤያችንን በመጠበቅ ከቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጋር እንሻገር”
በሚል መሪ ቃል የጣና ቅዱስ ቂርቆስ ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር ጉባኤ ቤት በአይነቱ ልዩ የሆነ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመገንባት ተነስተናል። እርሶም ለዚህ ፕሮጀክት ከታች በተቀመጡት የባንክ አማራጮች አበርክቶ በማድረግ አሻራዎትን ያሳርፉ።
#aba_gebre_kidan…

❤151🙏31👍12