Feta Daily News
14.4K subscribers
1.73K photos
75 videos
256 links
Download Telegram
ዛሬ አመት በአል ነው! በዚህ ቀን ማንም ሰው በተናገረውና በጻፈው ምክንያት ከቤቱ ተጎትቶ፣ ከቤተሰቡ ተነጥሎ ሊታሰር አይገባውም።
በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ ይፈቱ!
መንግስት ሆይ፣ በአዲሱ አመት ጉልበተኛ ሳይሆን ሆደ ሰፊ ብትሆን ያዋጣሃል። ጉልበትህን በከንቱ ያለቦታው ከማባከን ለእርድ የተዘጋጁ በዋይታ ድረስልን ለሚሉህ ንጹሃንን ለመታደግ ተጠቀምበት!
መልካም አዲስ ዓመት!

Via abebe gellaw
ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንደራደር

ሕወሃት በአፍሪቃ ህብረት መሪነት የሚደረግ ድርድርን እንደሚቀበልና በአቸኳይ ጦርነት ቆሞ ወደ ድርድር ለመግባት መዘጋጀቱን አስታወቀ።

ሕወሃት ቀደም ሲል የአፍሪቃ ሕብረትን አደራዳሪነት ገለልተኛ ስላልሆነ አልቀበልም ማለቱ ይታወሳል።

ሕወሃት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ግጭት ቆሞ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ዘላቂ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ለመደራደር መዘጋጀቱንና ለዚህም ፃድቃን ገብረተንሳይና ጌታቸው ረዳን ተደራዳሪ አድርጎ መሰየሙን አስታውቋል።
በድርድሩ አለማቀፉ ማኅበረሰብ በታዛቢነትና ድጋፍ በማድረግ እንዲሳተፍ እንደሚፈልግም ሕወሃት አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ላይ እስካሁን ምላሽ አልሰጠም።
በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ሰላምና እርቅ እመኛለሁ- ፖፕ ፍራሲስ

የዓለም ካቶሊክ ቤተ-ክርስትያን ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በአዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያውያን ያላቸው ምኞት ገለጹ፡፡
አዲስ ዓመት ለሚያከብሩ ውድ የኢትዮጵያ ህዝቦች ልዩ ሰላምታዬን አቀርባለሁ ያሉት ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ “ለእያንዳንዱ ቤተሰብና ለመላው የሀገሪቱ ህዝቦች ሰላምና እርቅ እመኛለሁ” ብለዋል፡፡
“ለኢትዮጵያ እጸልያለሁም” ብለዋል ሊቃነ ጳጳስ ፍራንሲስ በትዊተር ገጻቸው ባጋሩት ጽሁፍ፡፡
ኢትዮጵያዊቷ በጀርመን በባሏ ተገደለች
አሳዛኝ መረጃ ከጀመርን አገር ተሰምቷል፣ በጀርመን Treuchtlingen ከተማ Weissenburg-Gunzenhausen አውራጃ ውስጥ በሚገኝ የጥገኝነት ማእከል መኖሪያ ህንጻ ውስጥ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ሞታ መገኘቷ ተሰምቷል፡፡ የጀርመን ፖሊስ እንደዘገበው የ35 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ የሆነው ግለሰብ ፣ ሚስቱን በሳምንቱ መጨረሻ እሁድ በጀርመን አቆጣጣር ከቀኑ 4ስአት እንዲሁም በኢትዮጵያውያን የዘመን መለወጫ ቀን ግድያ ፈጽሞ ራሱ ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ሚስቴን ገድያለው ብሎ ለፖሊስ እጁን መስጠቱ ተመልክቷል፡፡
ፖሊስም ወደ መኖሪያ አፓርታማው አምርቶ ቤት ውስጥ ሲገባ ገዳይ እጁን የሰጠባት ሴት አስክሬን ቤት ውስጥ አግኝቷልለለ ፣ ፖሊስም ከግዳይ ጀርባ ያለውን ጉዳይ ለማወቅ ለምን እንደገደላት እያጣራሁ ነው ያለ ሲሆን፣ ነገር ግን እነዚህ ሁለት ጥንዶች ከትላንትና በፊት በለቀቁት ቪዲዮ ባሏ ለሚስቱ በጊታራ ሙዚቃ እየተጫወተላት ፍቅር በፍቅር ሆነው ታይቷል ተብሏል. የጀርመን የአካባቢው ፖሊስ እሁድ አመሻሽ ላይ እንዳስታወቀው ሰውዬው ከሰአት በኋላ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመምጣት በአቅራቢያው ባለ አፓርታማ ውስጥ አንዲት ሴት እንደገደለ የተናገረ ሲሆን ባለሥልጣናቱ እሁድ ዕለት የሞተችዋን ሴት በተባለው ቦታ በመሄድ አግኝተዋል።
የእውነታው ዳራ እስካሁን ግልጽ አይደለም.የሚለው ፖሊስ ባልነና ሚስት እንደሆኑ ቢጠረጠርም በትክክል የሁለቱ ግንኙነት ጠርቶ እስካሁን አለመታወቁን ተናግሯል። ተጠርጣሪው ወደ ችሎት እንዲቀርብ እና ክስ እንዲመሰረትበት እየተሰራ ሲሆን፣ የግድያ ወንጀል ምርመራ ለማድረግ እና የሞቱን መስኤ በማስረጃ ለማስደገፍ የአስክሬን ምርመራ ታዞ ውጤት እየተጠበቀ መሆኑ ተነግሯል።
የአፍሪካ መሪዎች በአውቶብስ ወደ ቀብር ሥነ ሥርዓቱ እንዲጓዙ መደረጉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አነጋጋሪ ሆኗል።

ዛሬ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ በሚፈጸመው ቀብር ላይ በለንደን ከተማ ከተገኙ አፍሪካውያን መሪዎች መካከል የደቡብ አፍሪካው ሲሪል ራማፎሳ፣ የኬንያው ዊልያም ሩቶ፣ የጋናው ናና አኩፎ አዶ፣ የታንዛኒያዋ ሱሉሁ ሳሚያ ሐሰን እና የሴኔጋሉ ማኪ ሳል ይገኙበታል።

በተጨማሪም የኮመንዌልዝ ሊቀ መንበር የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ እና በቅርቡ ኮመንዌልዝን የተቀላቀለችው ጋቦን መሮ አሊ ቦንጎም የቀብር ሥነ ሥርዓቱን ለመታደም ለንደን ገብተዋል።

በለንደን የተገኙት የተለያዩ አገራት መሪዎች ቁጥር ብዙ ስለሆነ በተለያየ መኪና መሄድ ስላልቻሉ በአንድ አውቶብስ እንዲሄዱ የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት አመራር ሰጥቷል።

ለቀብር ሥነ ሥርዓቱ በለንደን ከተገኙ የአገራት እና የመንግሥታት መሪዎች መካከል የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንደሚገኙት በለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግን ‘ዘ ቢስት’ በሚባለው የግል ሊሞዚናቸው ነው ሥነ ሥርዓቱን የታደሙት።

የአፍሪካ መሪዎች በአውቶብስ ወደ ቀብር ሥነ ሥርዓቱ እንዲጓዙ መደረጉ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አነጋጋሪ ሆኗል።
Via - BBC
ፋኖ አሸናፊ ዓለሙ በለጎ ላይ ምሽግ ሰብረው መሰዋቱን ሰምተናል:: አሸናፊ ከዚህ በፊት በተለያዩ የውጊያ ግንባሮች ከፈታ ዴይሊ ጋር ባደረገው ቆይታ የምታስታውሱት ነው:: ለቤተሰቦቹ እንዲሁም ለትግል አጋሮቹ መፅናናትን እንመኛለን
ይህንን ማየት ያማል 😥
እናንተ ደጋግ ልጆች ለእናታችን ሼር አድርጉላቸው

🙏🙏🙏

እማማ በቀጨኔ መድሃኒአለም አካባቢ የሚኖሩ ሲሆን

እማማ የሚበሉት ሲያጡ ሲርባቸው
መሶቡን ውጩ አስቀምጠው ለመሸጥ ተገደዋል::

እንዲህ ተብለው ሲጠየቁ :-

👇👇👇

እማማ ለምን መሶቡን መሸጥ ፈለጉ?

አዬ...ልጄ የሚበላው ይገኝ እንጂ በሳህንስ አልበላውም?

እኔ ጦሜን እያደርኩ እቤት ተቀምጦ ምን ይሰራልኛል?

* ያለችንን እንተባበር እናታችን ቀና ይበሉ

ንግድ ባንክ ቁጥር

* 1000500791555
* Habtam Sajaw Gobe

Via Gursha
🤔
ዩክሬን እሳት ታቀፈች‼️
የዘለንስኪ ቢሮ በሩሲያ ሚሳኤል ተመቷል። ዘሌንስኪ ይኑርበት አይኑርበት እየተጣራ ነው። ቢሮው በሩሲያ ሚሳኤል ነዷል። ጉዳቱ ከባድ ነው። ከኬቭ ተጨማሪ እሳት ያልዘነበበት የዩክሬን ከተማ የለም። ትናንት ሩሲያ ዩክሬንን ወደ ጨለማ እንመልሳታለን ብለው ዝተው ነበር።.......
ዩክሬን ላይ ፓለቲከኞች ተቃውሟቸውን በዘለነስኪ ለይ እያሰሙ ነው። ይህ ሁሉ መአት የወረደብን ከክሬሚያ ጥቃት በኋላ የእሱ ጸብ ጫሪ ድንፋታ ነው እያሉ ነው። ሚካኤል ፌሩ " Foolish person but Dangerous Fooll " ያሉት ዘለንስኪ በእርግጥ አደገኛ ተላላኪ ጅል ይመስላል።
የሩሲያ ጥቃት ዘግናኝ በሆነ ሁኔታ ቀጥሏል። ዩክሬን በእሳትና በአመድ ተውጣለች። የስታሊን በትር ማለት ለየትኛውም የጠላት ነገር ምህረት አለማድረግ ማለት ነው። ይኽን በትር ሩሲያ ለማንሳት ገና የፍርድ ቀን ስብሰባ ለይ ነች።
ፈረንሳይ ፓሪስ በተቃውሞ ተናጠ ....
በፎቶ ላይ የሚታየው የፓሪስ ሕዝብ በ EU እና ኔቶ ላይ አደባባይ ሞልቶ የሚያካሄደውን ሰልፍ ነው። የነዳጅ ፣ የምግብ ቀውስ ገጥሞናል። ፈረንሳይ ከኔቶ ትውጣ እያሉ ነው። ቤቱ የቀረ የለም።
ለመቶ አመታት ከተዋጓት እንግሊዝ ጋር በአንድ ኔቶ ከመሰባሰብ ይልቅ አገራቸው ፈረንሳየሰ ከሩሲያ ጋር ተሰልፋ እንግሊዝን ብትዋጋ የፈረንሳውያን ፍላጎት መሆኑን የብዙ ተንታኞች እምነት ነው።