𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
11K subscribers
23.3K photos
1.86K videos
295 files
7.46K links
✅|| 𝐘𝐀𝐀𝐃𝐀 ykn komii yoo qabaattan nuuf barreessaa.

✅|| ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት ይፃፉልን

✅|| write to us if you have any comments or complaints.

👀 @Fastmereja_Bot 👀
Download Telegram
ቢዝነስ፡ #ኦሮሚያ ባንክ 2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

ኦሮሚያ ባንክ አ.ማ. በ2015 በጀት ዓመት 2 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ትርፍ ማግኘቱ ገለጸ። ባንኩ ለአዲስ ስታንዳርድ በላከው አመታዊ አፈጻጸም ሪፖርት ከተያዘዉ አመታዊ የገቢ ዕቅድ 4% በመብለጥ 8.3 ቢሊዮን ብር አመታዊ ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ትርፍ በ63% እድገት ማስመዝገቡን በመጥቀስ ዕድገቱም በባንኩ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን ባንኩ ገልጿል።

የውጭ ምንዛሪ ግኝትን በተመለከተም 371 ሚሊዮን ዶላር ማግኘቱን ያስታወቀው ባንኩ ካለፈው ዓመት የ33% ዕድገት የተመዘገበበት ነው ብሏል። የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ከቀዳሚው ዓመት በ24% በማደግ 54.3 ቢሊዮን ብር ደርሷል ነው ያለው፡፡

የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ብር 66 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ካለፈው ዓመት 27% ዕድገት ማስመዝገቡን ለአዲስ ስታንዳርድ ከተላከው ሪፖርት መረዳት ተችሏል።

https://addisstandard.com/Amharic/?p=2737
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የ #ጨፌ #ኦሮሚያ ሲኖዶስ #መንበረ_ጴጥሮስ ዛሬ በኢፋ መቋቋሙን ኢትዮ ፎረም ዘግበዋል። 👏👏👏
.
.
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/Fastsinfo99

👍         📝          📌       👉
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᾃʳ
ጥልቅ ትንታኔ፡ “#በመንግስት_የጸጥታ_ኃይሎች ጭምር" በአሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸመው እገታ፣ ዝርፊያና ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፤ በስድስት ወር ውስጥ ከ50 በላይ አሽከርካሪዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል

ከቅርብ አመታት ወዲህ በታጣቂዎች የሚፈጸም የአሽከርካሪዎች እገታ፣ ከመቶ ሺዎች እስከ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ማስከፍል፣ ድብደባ፣ ግድያ እና የንብረት ውድመት ዜና መስማት የተለመደ እየሆነ መጥቷል። በአሁኑ ወቅትም እነዚህ ድርጊቶች በ #ኦሮሚያ፣ #አማራ እና #አፋር ክልሎች ተባብሰው የቀጠሉ በመሆኑ አስጊ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ከሶስት ሳምንታት በፊት በአማራ ክልል ጎብጎብ ከተማ ሰሊጥ የጫነ አንድ ከባድ ጭነት ተሽከርካሪ መንገድ ዳር ሙሉ ለሙሉ መቃጠሉን ለ12 ዓመታት በአሽከርካሪነት ያገለገለው ቴዎድሮስ ጥላሁን ገልጿል። “በየቦታው እንዲ አይነት ትዕይንት ማየት የተለመደ ሆኗል” ሲልም ገልጿል ብሏል።

በ #አማራ ክልል ኬላ ላይ የታጠቁ አካላት “ተሽከርካሪዎችን በማስቆም ለባለንብረቱ በመደወል እስከ 300 ሺህ ብር መቀበል ጀምረዋል” ሲል ገልጿል።

የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማህበር ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ዘውዱ አሽከርካሪዎች ላይ “ሽፍቶች እና የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ዘረፋ፣ እገታና የንብረት ውድመትን ጭምሮ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱባቸው ነው” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

የማህበር የስራ አመራር ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ አዲስ አለማየሁ በበኩላቸው በ #ኦሮሚያ ክልል #መተሃራ አካባቢ በታጣቂዎች የታገቱ በርካታ አሽከርካሪዎችን ተደራድረው ማስለቀቃቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

በዚህ አሳሳቢ ጉዳይ ላይ ያዘጋጀነውን ሙሉ ትንታኔ ለማንበብ ሊንኩን ይከተሉ፡ https://wp.me/pfjhHd-10L
ዜና፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ “የፋኖ ታጣቂዎች” በፈጸሙት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎሽ መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በ #ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ደራ ወረዳ፤ “በ #ፋኖ ታጣቂዎች” ትላንት የካቲት 28/ 2016 ዓ/ም በሶስት ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መሞቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

ጥቃቱ ትላንት ጠዋት ከ11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ ጂሩ ዳዳ፣ ወሬን ጋብሮ እና ማንቀታ ዋሪዮ በሚባሉ ቀበሌዎች መፈጸሙን ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት።  በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ሽታዬ ዱባለ የምትባል የ 11 አመት ህጻን በጥይት ተመታ መገደሏን የገለጸው ነዋሪው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

ጂሩ ደዳ በሚባለው ቀበሌ ”ከሃይማኖት ተቋማት ውጭ፤ የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ ከ400 በላይ ከብቶች ተወስደዋል። በርካታ መሰረተ ለማቶች ላይም ውድመት ደርሷል” ሲል ተናግሯል። 

https://wp.me/pfjhHd-117
ዜና፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ “የፋኖ ታጣቂዎች” በፈጸሙት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎሽ መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

በ #ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ደራ ወረዳ፤ “በ #ፋኖ ታጣቂዎች” ትላንት የካቲት 28/ 2016 ዓ/ም በሶስት ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መሞቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

ጥቃቱ ትላንት ጠዋት ከ11፡ 00 ሰዓት ጀምሮ ጂሩ ዳዳ፣ ወሬን ጋብሮ እና ማንቀታ ዋሪዮ በሚባሉ ቀበሌዎች መፈጸሙን ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት። በጥቃቱ ከተገደሉት መካከል ሽታዬ ዱባለ የምትባል የ 11 አመት ህጻን በጥይት ተመታ መገደሏን የገለጸው ነዋሪው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

ጂሩ ደዳ በሚባለው ቀበሌ ”ከሃይማኖት ተቋማት ውጭ፤ የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ ከ400 በላይ ከብቶች ተወስደዋል። በርካታ መሰረተ ለማቶች ላይም ውድመት ደርሷል” ሲል ተናግሯል።

https://wp.me/pfjhHd-117
የ #ኦሮሚያ ሕብረት ሾል ባንክ 'ማስተር ካርድ'ና  'ኮሚኒቲ ፓስ' አገልግሎቶችን አስጀመረ

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ለውጭ ሀገር ተጓዦች የቅድመ ክፍያ ኮፕ ባንክ ማስተር ካርድ አገልግሎትና የግብርና ምርት እና ግብይት ሂደትን የሚያሳልጠውን ፋርም ፓስ ሥራ ላይ አውሏል።

ባንኩ እንዳለው የቅድመ ክፍያ ኮፕ ባንክ ማስተር ካርድ አገልግሎት፣ ወደ ውጭ ሀገር የሚሄዱ ሰዎች በሚሄዱበት ሀገር የሚያስፈልጋችውን የውጭገንዘብ በካርድ ይዘው ለመጓዝ የሚያስችል ሲሆን የጥሬ ገንዘብ ሸከማን የሚያስቀርና እንደ ሀገር ያለውን የውጭ ምንዛሪ ችግር በመቅረፍ ረገድ አስተዋጽኦ ያለው ነው።

በተጨማሪም በኮሚኒቲ ፓስ የቀረበው የግብርና አመራረትን አሳልጦ፣ የግብርና ምርት ንግድን የሚያዘምነው ሲስተም ፋርም ፓስ ደግሞ ጥሬ ገንዘብን በማንቀሳቀስ የሚከናወነውን ማኑዋል አሠራር በማስቀረት፣ በኅብረት ሥራ ማህበራት በኩል መረጃ በማቀናጀት፣ ለአርሶ አደሮች የምርት ግብዓት ገበያ፣ የግብርና ምርትና የፋይናንስ አገልግሎትን በዲጂታል ስልት ማስተሳሰር ሲሆን ፣ የገጠሩን ማህበረሰብ ለፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ እንዲሁም ዲጂታል ሽግግርን በማላመድ ሂደት ወሳኝ ሚና ያለው ነው በማለት ባንኩ ጨምሮ ገልጿል።

================
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

📌 t.me/Fastsinfo99

    🌴  🌴  🌴
#ኦሮሚያ #ኖኖ

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ።

የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው።

ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች  ናቸው " ብለዋል።

ኃላፊው " ሰርገኞቹ ቤት ውስጥ እያሉ በር ዘግተውባቸው ቦምብ ወረወሩባቸው። ቤት ውስጥ ከነበሩት አንድም በሕይወት የወጣ የለም። እዚያው ተቃጥለው አልቀዋል "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ታጣቂዎቹ ሰርግ ቤቱ ላይ ከአንድ በላይ ቦምብ ወርውረው ሙሽሮቹን እና አብረዋቸው የነበሩ ሰዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስት ኃላፊን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል ፥ በሰርግ ቤት ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የሟቾች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

በጥቃቱ ሙሽሪት እና ሙሽራውን ጨምሮ የሰርጉ ታዳሚዎች የሆኑ ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪው ተናግረዋል።

የወረዳው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ፥ " በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር መለየት አልተቻለም " ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል።
በ #ኦሮሚያ ክልል እየተካሄደ ያለው ግጭት እንዲቋጭ የሰሜን ሸዋ ዞን ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ አቀረበ

በኦሮሚያ ክልል በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እና በፌዴራል መንግስት መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና ሰላም እንዲሰፍን በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች ነሐሴ 19 ቀን 2016 በሰሜን ሻዋ ዞን በሱሉልታ እና ጭንጮ ከተሞች ባካሄዱት ሰልፎች ጠየቁ።

ሰልፎቹ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄ፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ ሽማግሌዎች፣ ልጆች እና ሴቶች ጨምሮ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች አንድ ላይ በመሰባሰብ ተካሄደዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ሰልፎቹን አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ ባወጣው መግለጫ “ገዢው ፓርቲ የተወሰኑ ሰዎችን በማነሳሳት የሰሜን ሸዋ ህዝብ የሰላም ጥሪ እያቀረበ ነው በማለት ላይ ነው” ብሏል።

ያንብቡ፦ https://wp.me/pfjhHd-1mK
🚨 #ስልጤ_ዞን ....

በስልጤ ዞን በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ከ#900 በላይ ቤቶች በውሃ መዋጣቸውና ከ #6ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ

በ #ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ ክልል በስልጤ ዞን ስልጢ እና ምስራቅ ስልጢ ወረዳዎች ከ6 ቀበሌዎች በላይ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ከ900 በላይ ቤቶች መዋጣቸውና ከ6ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ።

የስልጤ ዞን ኮሚኒኬሽን ሃላፊ አቶ ሳሊ ሃሰን በአደጋው ምክንያት ከ1200 ሄክታር በላይ የበቆሎ፣ ስንዴ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ቡና ምርት ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ መሆኑን ለኢቢሲ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በፊት በዞኑ ከፍተኛ ስፍራዎች ከባድ ዝናብ በሚጥልበት ወቅት የሚፈጠረው ጎርፍ ማረቆ ወረዳን አቋርጦ በ #ኦሮሚያ ክልል በመቂ አልፎ ዝዋይ ሀይቅ ይቀላቀል የነበረ ቢሆንም ከዓመታት በፊት ለመስኖ በሚል በማረቆ ወረዳ የተሰራው የመስኖ ግድብ በከፍተኛ ደለል በመሞላቱ ምክንያት ውሃው መውራጃ ሲያጣ በአካበቢው የጎርፍ አደጋ እያስከተለ መሆኑ ተጠቁሟል።

ከሁለት ሳምንት በፊት ነሐሴ 9/2016 ዓ.ም በስልጤ ዞን በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ 1650 ሰዎች መፈናቀላቸውን እንዲሁም በእንስሳት እና ሰብሎች ላይ ውድመት ማጋጠሙን መዘገባችን ይታወሳል።
 ____

 đŸ“Œt.me/Fastmereja5

  📌t.me/Fastsinfo99

   đŸŒ´   🌴   🌴
🚨🇺🇸 🇪🇹የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማሲንጋን ጨምሮ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ሚኒስትር ስፔራ፣ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ምክትል ረዳት ፀሀፊ ፋሬል እና ሌሎችም የተካተቱበት ልዑክ ከሀገር መከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ጋር መክረዋል።

በወቅቱም ኢንጂነር አይሻ ፤ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ላላት የረዥም ጊዜ ወታደራዊ ግንኙነት ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እንደገለጹና ይህንኑ ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ኢትዮጵያ ፍላጎት እንዳለት መናገራቸውን ሀገር መከላከያ ሰራዊት ገልጿል።

የአሜሪካ ኤምባሲ እንዳለው ከሆነ ደግሞ በምክክሩ ላይ #በአማራ እና #ኦሮሚያ ያለው ግጭት ጉዳይ ተነስቷል።

ሌላው የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞብላይዝ በማድረግ ወደ ማህበረሰቡ መልሶ ለመቀላቀልና ለማቋቋም ስለሚደረገው ስራ (DDR) ውይይት ተደርጓል።

በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር በማጠናከር ላይም ትኩርት ያደረገ ምክክር መደረጉን ከኤምባሲው የተገኘ መረጃ ያሳያል።

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!💎
 ____

   📌t.me/Fastsinfo99

   📌t.me/Fastmereja5

    đŸŒ´  đŸŒ´   🌴
ዜና፡ በ #ሞያሌ የ14 አመት ታዳጊ ላይ የተፈጸመው ግድያ ቁጣ አስነሳ፤ በመንግስት ጽ/ ቤቶች ላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ

በ #ኦሮሚያ ክልል #ቦረና ዞና በሞያሌ ከተማ ሸዋ ባር ቀበሌ የ14 አመት ታዳጊ “በፖሊስ አባላት” መገደሉ በነዋሪዎች ዘንድ ቁጣ ቀስቅሷል። ታዳጊው የተገደለው ባለፈው አርብ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም "በፖሊስ ኃይሎች" በተተኮሰ ጥይት መሆኑ ተገጿል።

ግድያውን ተከትሎ የከተማው ህዝብ ባለፈው ቅዳሜ ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን ፖሊስ ሰልፈኞቹን ለመበተን ተኩስ ከፍቶ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሞያሌ ከተማ ኮሚኒኬሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ፤ በታዳጊው ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ሰልፍ መካሄዱን ጠቅሶ "ጽ/ ቤቶችን ሰብሮ በመግባት የማውደም እና በእሳት የማቃጠል" ተግባር መፈጸሙን ገልጿል። ይህም ትክክል አለመሆኑንና የሰልፉን አላማ የምይወክል ነው ብሏል።

ያንብቡ፡ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6488
🚨በ #ምስራቅ_ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ሁለት ወጣቶች “በሚሊሻዎች” መገደላቸውን የቤተሰብ አባላት ተናገሩ

በ #ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኩርፋ ጨሌ ወረዳ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ/ም ከማያ ከተማ ሞተር ሳይክል ገዝተው ወደ ጉራዋ ወረዳ በመመለስ ላይ የነበሩ ሁለት ወጣቶች “በጸጥታ ኃይሎች” በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

ግድያው የተፈጸመባቸው ወጣቶች ከዲሬ ሹኢቤ እና ጃፋር አብዱራዛቅ የተባሉ የጉራዋ ወረዳ ላፍቶ ቀበሌ ነዋሪ እንደሆኑ ቤተሰቦቹ ገልጸዋል።

“ሚሊሻዎቹ በጥይት ካቆሰሏቸው በኋላ እዚያው ተተዋቸው እንደሄዱ” የተናገሩት የቤተሰቡ አባሉ፤ “በኋላም የአካባቢው ማህበረሰብ አምቡላንስ ጠርቶ ወደ ጉራዋ ሆስፒታል ቢወስዳቸውም ሊተርፉ አልቻሉም” ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ አስረድተዋል።

ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6510
ዜና፡ በ #ሰሜን ሸዋ ዞን በፍርድ ቤት ዳኞች ላይ በተፈጸመ ድብደባ እና ማስፈራሪያ የፍርድ ቤት አገልግሎት ተቋረጠ

በ #ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ያያ ጉለሌ ወረዳ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በፍርድ ቤት ዳኞች ላይ በተፈጸመ ድብደባ እና ዛቻ ምክንያት የወረዳው ፍርድ ቤት አገልግሎት መስጠት ማቆሙን የፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ገለፁ።

ድብደባ እና ዛቻው የደረሰባቸው ጄኔኑስ ነጋሳ የተባሉ ዳኛ “ስድስት ሰዎች ሆነው መሬት ላይ ጥለውኝ የቻሉትን ያህል መላ ሰውነቴን ራጋገጡን። በብረት ቀበቶ ፊቴን ሲገርፉኝም ነበር። ትንፋሽ ሲያጥረኝ አንስተው ወደ ክፍል መለሱኝ” ሲሉ ወደ ወታደራዊ ካምፕ ተወድሰው የደረሰባቸውን ጥቃት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የ #ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በያያ ጉለሌ የፍርድ ቤት ዳኛ በሆኑት ጄኔኑስ ነጋሳ ላይ የተፈጸመውን ድብደባ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጾ ከተፈጸመው ድርጊት ጋር በተያያዘ ምርመራ እንዲደረግ ለዞኑ መመሪያ ተላልፎ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ይመልከቱ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6558
ዜና ትንታኔ፡ ታስረዋል የተባሉ የ #ከረዩ_አባገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ያሉበት ቦታ አለመታወቁ ስጋት መፍጠሩን ቤተሰቦችና ነዋሪዎች ገለጹ

በ #ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ፈንታሌ ወረዳ ታህሳስ 28/ 2017 ዓ/ም “በጸጥታ ኃይሎት” ታስረዋል የተባሉ 20 የሚሆኑ የከረዩ አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ያሉበት ቦታ አለመታወቁ እንዳሳሰባቸው ቤተሰቦች እና ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ጉዳዩን በቅርበት እንደሚያውቅ የገለጸ አንደ የፈንታሌ ወረዳ ነዋሪ፤ አባ ገዳዎቹ እና የሀገር ሽማግሌዎቹ የታሰሩበት ምክንያት “ለምን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት [መንግስት ሻኔ ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን] አባላትን ለማስገባት ፍቃደኛ አልሆኑም” በሚል መሆኑን ተናግሯል።

የቱለማ አባ ገዳ እና የኦሮሚያ አባ ገዳዎች ህብረት ምክትል ሰብሳቢ የሆኑት ጎበና ሆላ በበኩላቸው አባ ገዳዎቹ እና የሀገር ሽማግሌዎቹ "በየትኛው አካል እንደታሰሩና ወዴት እንደተወሰዱ አለመታወቁን" ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

ተጫማሪ ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6595
20 የ #ከረዩ አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከሶስት ሳምንት እስር በኋላ ተለቀቁ

በ #ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ “በጸጥታ ኃይሎች” የታሰሩ 20 የከረዩ አባ ገዳዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ከ21 ቀናት እስር በኋላ ተፈትተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቀላቀላቸውን ቤተሰቦቻቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

አባ ገዳዎቹና የሀገር ሽማግሌዎቹ ላለፉት 21 ቀናት "አዋሽ አርባ አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ሰራዊት ካምፕ" ታስረው መቆየታቸውን ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል።

“በአዋሽ አርባ በቆርቆሮ በተሰራ ቤት እና መከላከያ ሰራዊት መኖሪያ ቦታ ውስጥ ነበሩ። እዚያም ያናገራቸውን ሆነ ለምን እንደታሰሩ የነገራቸው ሰው እንደሌለ ነግረውናል” ሲሉ የቤተሰብ አባል የታሰሩባቸው ነዋሪ ገልጸዋል።

ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=6639
𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
190. ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ ፈረንጄ 191. ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል 192. አቶ መለሰ አለሙ ህርቦሮ 193. አቶ እርስቱ ይርዳው 194. አቶ ሞገስ ባልቻ ገ/መድህን 195. ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ 196. አም/ር ሬድዋን ሁሴን ራህመቶ 197. ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ 198. አቶ አንተነህ ፍቃዱ ወ/ሰንበት 199. አቶ ኡስማን ሱሩር ሲራጅ 200. አቶ ስንታየሁ ወ/ሚካኤል 201. ወ/ሮ እፀገነት መንግስቱ 202.…
45 የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አባላት
========
#ኦሮሚያ_ክልል

1. ዶር ዐቢይ አህመድ
2. ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
3. ኦቦ አወሉ አብዲ
4. ኦቦ ፍቃዱ ተሰማ
5. አዴ አዳነች አቤቤ
6. አዴ ጫልቱ ሳኒ
7. ኦቦ ሳዳት ነሻ
8. ኦቦ ከፍያለው ተፈራ
9. ዶር ተሾመ አዱኛ
10. ዶር እዮብ ተካልኝ

#አማራ_ክልል

11. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
12. አቶ መላኩ አለበል
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
14. አቶ አረጋ ከበደ
15. አቶ ይርጋ ሲሳይ
16. ዶክተር አብዱ ሁሴን
17. አቶ ጃንጥራር አባይ
18. ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ

#ሶማሌ_ክልል

19. አቶ አደም ፋራህ
20. አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
21. አቶ አህመድ ሺዴ
22. ወ/ሮ ሃሊማ ዋሽራፍ

#ትግራይ_ክልል

23. ዶክተር አብርሃም በላይ
24. አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር

#ሀረሪ_ክልል

25. አቶ ኦርዲን በድሪ
26. ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም

#አፋር_ክልል

27. ሀጂ አወል አርባ
28. መሀመድ ሁሴን አሊሳ
29. መሀመድ አህመድ አሊ

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ_ክልል

30. ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
31. አቶ ፍቅሬ አማን

#ሲዳማ_ክልል

32. አቶ ደስታ ሌዳሞ
33. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
34. ዶ/ር ፍፁም አሰፋ

#ጋምቤላ_ክልል

35. ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ
36. ዶ/ር ካትሏክ ሩን ናቸው።

#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ_ክልል

37. አቶ አሻድሊ ሀሰን
38. አቶ ጌታሁን አብዲሳ

#ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል

39. አቶ እንዳሻው ጣሰው
40. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
41. ዶ/ር ዴላሞ ዶቶሬ

#ደቡብ_ኢትዮጵያ_ክልል

42. አቶ ጥላሁን ከበደ
43. ወ/ሮ ⁠ሸዊት ሻንካ
44. ዶ/ር ተስፋዬ ቤልጅጌ
45. ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ
🚨 #ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን ጉደያ ቢላ ወረዳ ኢፋ ቢያ ቀበሌ ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2017ዓ/ም በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ26 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።

በተጨማሪም 42 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የምስራቅ ወለጋ ዞን የትራፊክ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ኢንስፔክተር አስናቀ መስፊን ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ገልጸዋል።

ታታ የተሰኘው የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪው የመገልበጥ አደጋው የደረሰበት ከሻምቡ ከተማ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንስፔክተር አስናቀ በአደጋውም የ26 ተሳፋሪዎች ህይወት ማለፉን እና ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችልም አክለው ገልጸዋል።

- #AS

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ!💎
 ____

   📌t.me/Fastsinfo99

   📌t.me/Fastmereja5

    đŸŒ´  đŸŒ´   🌴
🚨በ #ኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን “የ #ፋኖ ታጣቂዎች” በፈጸሙት ጥቃት ከ20 በላይ ነዋሪዎች ተገደሉ

በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ቱሉ ሞቲ ቀበሌ ባሳለፍነው ሳምንት አርብ መጋቢት 19 ቀን 2017 ዓ/ም “የ #ፋኖ ታጣቂዎች” ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ከ20 በላይ ነዋሪዎች መገደላቸውን እና ሌሎች ሶስት ታፍነው መወሰዳቸውን የአካባቢው ኃላፊዎች እና ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የአቤ ዶንጎሮ ወረዳ ነዋሪ፤ "የፋኖ ታጣቂዎች ባለፈው አርብ ወደ ቀበሌው በመምጣት ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ መክፈታቸውንና የተኩስ ድምጽ ሰምተው ወደ ቤት በመሸሽ ላይ የነበሩ ሰዎችን በጥይት ማጥቃታቸውን" ተናግረዋል።

የአቤ ዶንጎሮ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አያና ዋቄ፤ “ፋኖ” በሚል ስም ራሳቸውን ያደራጁት ታጣቂዎች መከላከያ ሠራዊት መውጣቱን ተከትሎ ጥቃት ማድረሳቸውን ለ #አዲስስታንዳርድ አረጋግጠዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ፦ https://addisstandard.com/Amharic/?p=7416
በኮሌራ፣ በወባ እና በኩፍኝ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን #የኢትዮጵያ የጤና ክላስተር ሪፖርት አመላከተ

ከጥር እስከ ሚያዚያ ድረስ በዋናነት #በአማራ እና #ጋምቤላ ክልሎች በ32 ወረዳዎች እና በአምስት የስደተኞች ካምፕ ውስጥ በተከሰተ የኮሌራ በሽታ 4,056 ሰዎች የተያዙ ሲሆን ከነዚህም መካከል የ42 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተለይ በአማራ ክልል 89.9 በመቶ የሚሆነው በሽታ የተከሰተው በአራት ወረዳዎች ነው።

በወባ በሽታ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ የጨመረ ሲሆን 1.97 ሚሊዮን ሰዎች በበሽታው ተይዘው የ77 ሰዎች ህይወት አልፏል። በሚያዚያ ወር ብቻ በ1,147 ወረዳዎች ወስጥ የወባ በሽታ ተከስቷል። በጋምቤላ ክልል በበሽታው የተያዙ ሰዎች መጠን ከፍተኛ ሲሆን ከ100,000 ሰዎች ውስጥ 462 የሚሆኑት በወባ በሽታ መያዛቸውን ተመላክቷል።

የኩፍኝ በሽታም የቀጠለ ሲሆን 3,908 ሰዎች በበሽታው ተይዘው 22 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። #አማራ፣ #ኦሮሚያ እና #ትግራይ ክልሎችን ጨምሮ በስምንት ክልሎች በአሁኑ ወቅት በሽታው ይገኛል። በሚያዚያ ወር መጨረሻ በኦሮሚያ ደደር ወረዳ 96 አዳስ የተያዙ ሰዎችም መገኘታቸው በሪፖርቱ ተመላክቷል።

https://reliefweb.int/report/ethiopia/ethiopia-health-cluster-bulletin-april-2025