Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ወደ ✨ Fanos Library ✨ በሰላም መጡ!
❔ በዚህ ቻናል ምን ያገኛሉ?
📚 የመጽሐፍ ዳሰሳዎች (Book Reviews)
💡 ከመጽሐፍት የተወሰዱ ቁምነገሮች
📖 የነፃ PDF መጽሐፍት
📰 አነቃቂ የሆኑ ጥቅሶች
🎧 የመጽሐፍት ትረካዎች
✍️ የደራሲያን ታሪክ እና የሥነ-ጽሑፍ ወጎች
ለአእምሮ እርካታ እና ለእውቀት ማደግ ትክክለኛው ቦታ!
📒 @FanosLibrary
ለአእምሮ እርካታ እና ለእውቀት ማደግ ትክክለኛው ቦታ!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ብዙዎቻችን ቀኑን ሙሉ በስራ ስንጠመድ እንውላለን፣ ነገር ግን የረባ ውጤት አናመጣም። መሰላል ላይ በፍጥነት መውጣትህ ዋጋ ያለው፣ መሰላሉ ትክክለኛው ግድግዳ ላይ ከተደገፈ ብቻ ነው።
"መጨረሻውን አስበህ ጀምር (Begin with the end in mind)" ማለት ማንኛውንም ስራ፣ ውሳኔ ወይም የህይወት ጉዞ ከመጀመርህ በፊት መድረስ የምትፈልግበትን የመጨረሻ ግብ በግልፅ ማወቅ ማለት ነው። መድረሻውን የማያውቅ መንገደኛ የሚሄድበት መንገድ ሁሉ ትክክል ይመስለዋል።
ዛሬ፣ ከቤትህ ከመውጣትህ ወይም ስራ ከመጀመርህ በፊት፣ "የዚህ ቀን ዋና ግቤ ምንድን ነው?" ብለህ በወረቀት ፃፍ። ቀጥሎ የምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ወደዚያ ግብ የሚወስዱህ መሆናቸውን አረጋግጥ።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ትዝ ይልሻል
ከሴት ልጅ ምን ትወዳለህ ብለሽ በጠየቅሽኝ ጊዜ ምን እንዳልኩሽ
አይንሽን ትኩር በዬ ለሰከንድ አየሁሽ ብዙ አታፍጥጥብኝ አታሽኮርምመኝ አልሽኝ ልብ የሚያሞቅ ፈገግታ እያሳየሽኝ ።
ይልቅ ከሴት ምን ትወዳለህ?? ብለሽ ድጋሚ ጠየቅሽኝ ። እኔ ምን አልኩሽ ''ንፁህ ነፍስ ''
''ንፁህ ነፍስ''? አልገባኝም አብራራልኝ አልሽኝ።
ንፁህ ነፍስ ንፅት ያልሽ ነሽ አእምሮሽ እና ልብሽ ንፁህ ነው ታውቂያለሽ አንቺ ውስጥ ያለው ፈገግታ ማስመሰል የለውም አንቺ ጋር ያለው ንግግር ክፋት የለውም አንቺ ጋር ያለው ኩርፊያ የምር ነው ። አንቺ በዚህ ምድር ላይ እንዳሉት በአፋቸው እየተናገሩ በልባቸው ክፋት የሚያስቡ የይስሙላ ፈገግታ ፈገግ የሚሉ ለጥቅም ሰውን የሚያቀርቡ ማስመሰል እና ጥቅም በሞላበት ይቺ ምድር ላይ የተገኘሽ ሀሴት የምትሞይ ንፁህ ነፍስ ነሽ ''' አልኩሽ።
``
በደንብ አልገባሽም እንዲገባሽም አልፈልግም ምክንያት ስለ አለም ክፋት ከዚህ በላይ ማወቅ የለብሽም ሁሌ ፈገግ ላረግሽ ለዘላለም ካንቺ ጋር ልቆይ በእናቴ ምያለሁ እወድሻለሁ።

“ዛሬ ለምን ከፋሽ? ከፍቅረኛሽ ጋር ተጣልተሻል እንዴ?” ብሎ ጠየቃት።
እሷም በንዴት መለሰች፦ “እሺህ ጊዜ ፍቅረኛ እንደሌለኝ ነግሬሃለሁ”
እሱም እሳቀ፦“እና ለማን ነው በስልክሽ እንዲህ ተመስጠሽ የምትጽፊው?”
ልጅቷም ዓይን አይኑን እያየች፦“ለአንድ ደደብ ሰውዬ ነው የምጽፈው?” ብላ መሰለችለት።
ጠያቂው ወንድ በመገረም፦“ምን ማለትሽ ነው?”
ልጅቷ፦“እንደምወደው አያውቅም። ፍንጭ ለመስጠት ብዙ ሞከርኩ ግን ሊገባው አልቻለም። ለዚህ ነው ደደብ እንደሆነ የደመደምኩት!።”
ጠያቂው፦“እንዳንቺ አይነት ሴት እምቢ የሚል ወንድ ጤነኛ አይመስለኝም።”
ልጅቷም ተስፋ በመቁረጥ ውስጥ ሆና፦ “ደደብ ነው ባክህ” ትለዋለች።
ጠያቂው ወንድም የልጅቷን ስልክ ተቀብሎ፦ “በዚህ አጋጣሚ እዚህ ብትሆን ኖሮ ምንኛ ደስ ባለኝ። ምንአልባት ትረዳኝ ነበር።” የሚል ቴክስት ጻፈና “ለተፈቃሪው ሰው ነው” ከተመቸሽ ላኪለት አላት። ልጅቷም ስልኩን ተቀብላ ከአይኑ እይታ እስከምትሰወር እርቃ ሄደች።
ትንሽ ቆይቶ የጠያቂው ወንድ ስልክ ላይ ሚሴጅ ገበና አነበበው፦ “ምን አለ እዚህ ብትኖር..” አልጨረሰውም ይልቅ ለራሱ እንዲህ አለ፦ “ምን አይነት ደደብ ነች መልዕክቱን ለእሱ ልካለሁ ብላ ለእኔ እኮ ነው የላከችው።

"ዋጋህን ለማረጋገጥ በማይገባህ ቦታ ጊዜህን አታባክን!"
በአንድ ወቅት ሰዎች ማን ፈጣን እንደሆነ በተግባር ማረጋገጥ ፈለጉና ውሾችን እና ቀበሮዎችን ከአቦሸማኔ ጋር እንዲወዳደሩ አደረጉ።
ተመልካቾች ውድድሩን በጉጉት እየጠበቁ እንዳለ ድንገት የማስጀመሪያው ሽጉጥ ተተኮስ። ውሾቹና ቀበሮዋቹ የመጨርሻዋን ክር ለመበጠስ ሲፈተለኩ አቦሸማኔው ግን ካለበት ቦታ ጭራሽ አልተነቃነቀም ነበር።
በዚህ ጊዜ ተመልካቾቹ አቦሸማኔው በሩጫው ሊቀደም እንደሚችል በማሰብ የሩጫውን አስተባባሪ በብስጭት ምን እንደተፈጠረ ጠየቁት?
➽ እሱም እንዲህ አላቸው....."አንዳንድ ጊዜ ምርጥ እንደሆንክ ለማሳየት ከከፍታህ በታች ዝቅ ብለህ መብረር የለብህም፤ አንተ በጣም ጠንካራ መሆንህን ሌሎች እንዲገነዘቡልህ ስትል የግድ ወደ ሌሎች ሰዎች ደረጃ መውረድ አይጠበቅብህም። ይልቁንስ በደንብ አስበህ ጉልበትህን አቅምህንና ብርታትህን ለሚገባው ነገር ብቻ በትክክለኛው ሰዓትና ቦታ መጠቀም ይኖርብሃል። እናም ወዳጆቼ አቦሸማኔው ውድድሩ ያላስፈለገው፣ ውሾቹን ንቋቸው አይደለም ይልቁንስ ፈጣን እና ጠንካራ መሆኑን ለታዳሚዎቹ ከማረጋገጡ ይልቅ ጉልበቱን፣ ፈጥነቱን እና ቅልጥፍናውን በአደን ጊዜ ሊጠቀምበት ወሰነ እንጂ።" በማለት አስረዳቸው።
✅ እናም አንተ ራስህ ተመንህን ለማወቅ ከሌሎች ጋር ከመፎካከር ይልቅ የህይወት ግብህን ለማሳካት ታትር!

አዋቂ ሰው አውቃለሁ ብሎ ስለሚያስብ ፈፅሞ ለመማር ዝግጁ አይደለም። "በዕውቀቱ ወይም ዕውቀቴ ብሎ በሚጠራው ነገር እጅግ ይኩራራል። ዕውቀቱ ግን ለእኔነቱ እና ለትምክህቱ ማዳበሪያ እንጂ ምንም አይደለም"።
ሶቅራጦስ እንኳን "አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ፤ምንም አለማወቄን" ብሎ ተናግሮ ነበር። ምንም የማናውቅ ስንሆን የመጠየቅ፤ የመመርመርና፤ የመፈተሽ ፍላጎት ይኖረናል። ስለዚህ ሁልጊዜ አውቃለው ከማለት ተቆጥበን አናውቅም ማለትን ብንለምድ አለማወቃችን ብዙ ነገሮችን እንድናውቅ ያደርገናል።
📚 ርዕስ፦ህያውነት
✍️ፀሀፊ፦ኦሾ
📒 @FanosLibrary
ሶቅራጦስ እንኳን "አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ፤ምንም አለማወቄን" ብሎ ተናግሮ ነበር። ምንም የማናውቅ ስንሆን የመጠየቅ፤ የመመርመርና፤ የመፈተሽ ፍላጎት ይኖረናል። ስለዚህ ሁልጊዜ አውቃለው ከማለት ተቆጥበን አናውቅም ማለትን ብንለምድ አለማወቃችን ብዙ ነገሮችን እንድናውቅ ያደርገናል።
✍️ፀሀፊ፦ኦሾ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሕማማት - @FanosLibrary.pdf
125.2 MB
ብብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ጥራቱ ተሻሽሎ
አዲስ የተሰራ ለማንበብ ምቹ የሆነ PDF File።
📚 ርዕስ ፦ ሕማማት
✍️ ደራሲ ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
📒 @FanosLibrary
አዲስ የተሰራ ለማንበብ ምቹ የሆነ PDF File።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
[ ፍቅር ትግል ለሆነባችሁ ]
እያሳለፋችሁ ያላችሁት ነገር ቀላል ላይሆን ይችላል። አለም በፀጥታ ተኝቶ እናንተ ግን ጣራ ላይ አፍጣችሁ በአይምሮዋችሁ ውስጥ ያለውን ማዕበል ፀጥ ለማሰኘት እየታገላችሁ ይሆናል።
ሁላችንም በአንድ ወቅት እዛ ቦታ ላይ ነበርን። ትራሳችን በእንባ ርሶ ያድር ነበር፤ ልባችን መልስ ፍለጋ ይቃትት ነበር፤ ሰላምን ፍለጋ ያልቧጠጥነው ቋጥኝ አልነበረም .... የሆነ ነገር መጥቶ ሁሉንም ነገር ያስቆመው ዘንድ ብዙ ታግለናል።
ቀን በሰዎች መሀል "ደህና" እንደሆንን ለማስመሰል ብዙ ታግለናል። ቤተሰብ እና የስራ ባልደረቦቻችንን በፈገግታ ሸውደናቸዋል፤ እንዴት ናችሁ ስንባል "ደህና ነኝ" ብለን ዋሽተናል፤ በማያስቀውም ቀልድ አብረን ገልፍጠናል ...... ውስጣችን እየተፈረካከሰ ከላይ "ጠንካራ" ለመምሰል ብዙ ብዙ ሆነናል።
ያፈቀሩትን ማጣት ውስጥ ..... የማያገኙትን ማፍቀር ውስጥ .... ያለው ህመም የትም የለም። የምናጣው አብሮነታቸውን፣ አጠገባችን መቀመጣቸውን ወይም ዞር ስንል ማየታችንን ብቻ አይደለም። ያላየናቸው፣ ድምፃቸውን ያልሰማን፣ ፅሁፋቸውን ያላነበብን .... እለት ያለው ህመም ይከፋል።
ምናልባት የፅሁፍ መልዕክት ለመላክ ስልካችንን አንስተን ያለፈውንም እንዳልመለሱልን ማየቱ፤ የሚወዱት እና የሚያዘወትሩት ቦታ ሄደን እንደሌሉ ማየቱ፤ በጣም ይወዱት የነበረን ሙዚቃ ስንሰማው የሚፈጠርብን ስሜት ..... ሊሆን ይችላል። አለም እየዞረች ቢሆንም እኛ ግን ያንን የምንወደውን ሰው ያጣንበት ቅፅበት ላይ ቆመናል።
ድብርት እና ሀዘን፣ ጭንቀት እና እንባ በቅፅበት ልዩነት ሲፈራረቁብን .... አሁን ደህና ሆነን በደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ ለእብደት ፍፁም የቀረብን ሲመስለን ... የረሳነው የመሰለን ሁሉ ተራ በተራ ወደ ህሊናችን ሲመጣ ....
ሁሉም ነገር አድካሚ በሆነበት መሽቶ መንጋቱ ሲያበሳጨን፣ የሰራናቸው ስህተቶች በህሊናችን ሲመላለሱ፣ ፀፀት መጫወቻ ሲያደርገን ....
ደካማ የሆንን ... የተሸነፍን ... ያበቃልን ሊመስለን ይችላል። ግን አይደለም። እዚህ መድረሳችን፣ አሁንም መተንፈሳችን፣ ዛሬም ቆመን መሄዳችን፣ ይሄንን መፃፍ እና ማንበባችን .... በራሱ ትልቅ ጥንካሬ ነው። ፅናት ነው።
ሁሉም ነገር የራሱ ምክንያት አለው። ህይወት በፈተና ስትቀጠቅጠን እየቀጣችን አይደለም። ለነገ እየሰራችን ነው። ዘር መሬትን ፈንቅሎ ወጥቶ ፀሀይን ተገን አድርጎ ከማበቡ በፊት አፈር ውስጥ በድቅድቅ ጨለማ ይቀበራል። እኛም እንደዛ ዘር ነን። ይሄ ጨለማው ጊዜ የታሪካችን መቋጫው አይደለም። የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ እንጂ።
እጅ አትስጡ፤ አያልፍም ያላችሁት ሁሉ ዛሬ የለም። ማልቀስ ሲሰማችሁ ስቅስቅ ብላችሁ አልቅሱ። መጮኽ ሲያሰኛችሁ ትራሳችሁ ላይ ተደፍታችሁ ኡኡኡኡኡ በሉ። ስትናደዱ በሚቀላችሁ መንገድ ንዴታችሁን አውጡት። ሰው ሲያስጠላችሁ በራችሁን ዘግታችሁ ብቻችሁን ተቀመጡ።
መዳን ቀላል አይደለም። መዳን አስቀያሚ፣ አድካሚ፣ ግራ አጋቢ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያሳልፍ በዝግመት የሚመጣ ሂደት ነው። ዋናው ነገር መንገዱን መጀመራችሁ ነው። ዋናው ነገር የሆነ አንድ ሰው እንደሚረዳችሁ ማሰቡ ነው። ዋናው ነገር በዚህ ትግል ውስጥ ብቻችሁን አለመሆናችሁን ማወቅ ነው።
ሁሉም ጥሩ ይሆናል .... ሳቃችንም ይመለሳል !!
~
~
ለአንዱ ፆታ የተፃፈው ለሌላኛውም ይሰራል 🤞

አንዲት ትንሽ ቢንቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ከበረረች በኋላ ስትመለስ፣"እንዴት ነበር የመጀመሪያ በረራዉ?"ሲል አባቷ ይጠይቃታል።
ትንሿ ቢንቢም እንዲህ ስትል መለሰች፦ "'በጣም አሪፍፍፍ..... ነበር፤ ሁሉም ሰዎች እያጨበጨቡልኝ ነበር።"
ወዳጄ፥ ወደ ከፍታ በተጠጋህ ቁጥር የሚያጨበጭብ ይበዛል ፤ግን የሚያጨበጭበዉ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም፤ እንደ ቢንቢዋ በእጆቹ መሀል ሊጨፈልቅህ የሚፈልግም ይሆናልና ተጠንቀቅ!!!!!