"ዋጋህን ለማረጋገጥ በማይገባህ ቦታ ጊዜህን አታባክን!"
በአንድ ወቅት ሰዎች ማን ፈጣን እንደሆነ በተግባር ማረጋገጥ ፈለጉና ውሾችን እና ቀበሮዎችን ከአቦሸማኔ ጋር እንዲወዳደሩ አደረጉ።
ተመልካቾች ውድድሩን በጉጉት እየጠበቁ እንዳለ ድንገት የማስጀመሪያው ሽጉጥ ተተኮስ። ውሾቹና ቀበሮዋቹ የመጨርሻዋን ክር ለመበጠስ ሲፈተለኩ አቦሸማኔው ግን ካለበት ቦታ ጭራሽ አልተነቃነቀም ነበር።
በዚህ ጊዜ ተመልካቾቹ አቦሸማኔው በሩጫው ሊቀደም እንደሚችል በማሰብ የሩጫውን አስተባባሪ በብስጭት ምን እንደተፈጠረ ጠየቁት?
➽ እሱም እንዲህ አላቸው....."አንዳንድ ጊዜ ምርጥ እንደሆንክ ለማሳየት ከከፍታህ በታች ዝቅ ብለህ መብረር የለብህም፤ አንተ በጣም ጠንካራ መሆንህን ሌሎች እንዲገነዘቡልህ ስትል የግድ ወደ ሌሎች ሰዎች ደረጃ መውረድ አይጠበቅብህም። ይልቁንስ በደንብ አስበህ ጉልበትህን አቅምህንና ብርታትህን ለሚገባው ነገር ብቻ በትክክለኛው ሰዓትና ቦታ መጠቀም ይኖርብሃል። እናም ወዳጆቼ አቦሸማኔው ውድድሩ ያላስፈለገው፣ ውሾቹን ንቋቸው አይደለም ይልቁንስ ፈጣን እና ጠንካራ መሆኑን ለታዳሚዎቹ ከማረጋገጡ ይልቅ ጉልበቱን፣ ፈጥነቱን እና ቅልጥፍናውን በአደን ጊዜ ሊጠቀምበት ወሰነ እንጂ።" በማለት አስረዳቸው።
✅ እናም አንተ ራስህ ተመንህን ለማወቅ ከሌሎች ጋር ከመፎካከር ይልቅ የህይወት ግብህን ለማሳካት ታትር!
📒 @FanosLibrary

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አዋቂ ሰው አውቃለሁ ብሎ ስለሚያስብ ፈፅሞ ለመማር ዝግጁ አይደለም። "በዕውቀቱ ወይም ዕውቀቴ ብሎ በሚጠራው ነገር እጅግ ይኩራራል። ዕውቀቱ ግን ለእኔነቱ እና ለትምክህቱ ማዳበሪያ እንጂ ምንም አይደለም"።
ሶቅራጦስ እንኳን "አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ፤ምንም አለማወቄን" ብሎ ተናግሮ ነበር። ምንም የማናውቅ ስንሆን የመጠየቅ፤ የመመርመርና፤ የመፈተሽ ፍላጎት ይኖረናል። ስለዚህ ሁልጊዜ አውቃለው ከማለት ተቆጥበን አናውቅም ማለትን ብንለምድ አለማወቃችን ብዙ ነገሮችን እንድናውቅ ያደርገናል።
📚 ርዕስ፦ህያውነት
✍️ፀሀፊ፦ኦሾ
📒 @FanosLibrary
ሶቅራጦስ እንኳን "አንድ ነገር ብቻ አውቃለሁ፤ምንም አለማወቄን" ብሎ ተናግሮ ነበር። ምንም የማናውቅ ስንሆን የመጠየቅ፤ የመመርመርና፤ የመፈተሽ ፍላጎት ይኖረናል። ስለዚህ ሁልጊዜ አውቃለው ከማለት ተቆጥበን አናውቅም ማለትን ብንለምድ አለማወቃችን ብዙ ነገሮችን እንድናውቅ ያደርገናል።
✍️ፀሀፊ፦ኦሾ
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ሕማማት - @FanosLibrary.pdf
125.2 MB
ብብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ጥራቱ ተሻሽሎ
አዲስ የተሰራ ለማንበብ ምቹ የሆነ PDF File።
📚 ርዕስ ፦ ሕማማት
✍️ ደራሲ ፦ ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
📒 @FanosLibrary
አዲስ የተሰራ ለማንበብ ምቹ የሆነ PDF File።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
[ ፍቅር ትግል ለሆነባችሁ ]
እያሳለፋችሁ ያላችሁት ነገር ቀላል ላይሆን ይችላል። አለም በፀጥታ ተኝቶ እናንተ ግን ጣራ ላይ አፍጣችሁ በአይምሮዋችሁ ውስጥ ያለውን ማዕበል ፀጥ ለማሰኘት እየታገላችሁ ይሆናል።
ሁላችንም በአንድ ወቅት እዛ ቦታ ላይ ነበርን። ትራሳችን በእንባ ርሶ ያድር ነበር፤ ልባችን መልስ ፍለጋ ይቃትት ነበር፤ ሰላምን ፍለጋ ያልቧጠጥነው ቋጥኝ አልነበረም .... የሆነ ነገር መጥቶ ሁሉንም ነገር ያስቆመው ዘንድ ብዙ ታግለናል።
ቀን በሰዎች መሀል "ደህና" እንደሆንን ለማስመሰል ብዙ ታግለናል። ቤተሰብ እና የስራ ባልደረቦቻችንን በፈገግታ ሸውደናቸዋል፤ እንዴት ናችሁ ስንባል "ደህና ነኝ" ብለን ዋሽተናል፤ በማያስቀውም ቀልድ አብረን ገልፍጠናል ...... ውስጣችን እየተፈረካከሰ ከላይ "ጠንካራ" ለመምሰል ብዙ ብዙ ሆነናል።
ያፈቀሩትን ማጣት ውስጥ ..... የማያገኙትን ማፍቀር ውስጥ .... ያለው ህመም የትም የለም። የምናጣው አብሮነታቸውን፣ አጠገባችን መቀመጣቸውን ወይም ዞር ስንል ማየታችንን ብቻ አይደለም። ያላየናቸው፣ ድምፃቸውን ያልሰማን፣ ፅሁፋቸውን ያላነበብን .... እለት ያለው ህመም ይከፋል።
ምናልባት የፅሁፍ መልዕክት ለመላክ ስልካችንን አንስተን ያለፈውንም እንዳልመለሱልን ማየቱ፤ የሚወዱት እና የሚያዘወትሩት ቦታ ሄደን እንደሌሉ ማየቱ፤ በጣም ይወዱት የነበረን ሙዚቃ ስንሰማው የሚፈጠርብን ስሜት ..... ሊሆን ይችላል። አለም እየዞረች ቢሆንም እኛ ግን ያንን የምንወደውን ሰው ያጣንበት ቅፅበት ላይ ቆመናል።
ድብርት እና ሀዘን፣ ጭንቀት እና እንባ በቅፅበት ልዩነት ሲፈራረቁብን .... አሁን ደህና ሆነን በደቂቃዎች ልዩነት ውስጥ ለእብደት ፍፁም የቀረብን ሲመስለን ... የረሳነው የመሰለን ሁሉ ተራ በተራ ወደ ህሊናችን ሲመጣ ....
ሁሉም ነገር አድካሚ በሆነበት መሽቶ መንጋቱ ሲያበሳጨን፣ የሰራናቸው ስህተቶች በህሊናችን ሲመላለሱ፣ ፀፀት መጫወቻ ሲያደርገን ....
ደካማ የሆንን ... የተሸነፍን ... ያበቃልን ሊመስለን ይችላል። ግን አይደለም። እዚህ መድረሳችን፣ አሁንም መተንፈሳችን፣ ዛሬም ቆመን መሄዳችን፣ ይሄንን መፃፍ እና ማንበባችን .... በራሱ ትልቅ ጥንካሬ ነው። ፅናት ነው።
ሁሉም ነገር የራሱ ምክንያት አለው። ህይወት በፈተና ስትቀጠቅጠን እየቀጣችን አይደለም። ለነገ እየሰራችን ነው። ዘር መሬትን ፈንቅሎ ወጥቶ ፀሀይን ተገን አድርጎ ከማበቡ በፊት አፈር ውስጥ በድቅድቅ ጨለማ ይቀበራል። እኛም እንደዛ ዘር ነን። ይሄ ጨለማው ጊዜ የታሪካችን መቋጫው አይደለም። የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ እንጂ።
እጅ አትስጡ፤ አያልፍም ያላችሁት ሁሉ ዛሬ የለም። ማልቀስ ሲሰማችሁ ስቅስቅ ብላችሁ አልቅሱ። መጮኽ ሲያሰኛችሁ ትራሳችሁ ላይ ተደፍታችሁ ኡኡኡኡኡ በሉ። ስትናደዱ በሚቀላችሁ መንገድ ንዴታችሁን አውጡት። ሰው ሲያስጠላችሁ በራችሁን ዘግታችሁ ብቻችሁን ተቀመጡ።
መዳን ቀላል አይደለም። መዳን አስቀያሚ፣ አድካሚ፣ ግራ አጋቢ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያሳልፍ በዝግመት የሚመጣ ሂደት ነው። ዋናው ነገር መንገዱን መጀመራችሁ ነው። ዋናው ነገር የሆነ አንድ ሰው እንደሚረዳችሁ ማሰቡ ነው። ዋናው ነገር በዚህ ትግል ውስጥ ብቻችሁን አለመሆናችሁን ማወቅ ነው።
ሁሉም ጥሩ ይሆናል .... ሳቃችንም ይመለሳል !!
~
~
ለአንዱ ፆታ የተፃፈው ለሌላኛውም ይሰራል 🤞

አንዲት ትንሽ ቢንቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ከበረረች በኋላ ስትመለስ፣"እንዴት ነበር የመጀመሪያ በረራዉ?"ሲል አባቷ ይጠይቃታል።
ትንሿ ቢንቢም እንዲህ ስትል መለሰች፦ "'በጣም አሪፍፍፍ..... ነበር፤ ሁሉም ሰዎች እያጨበጨቡልኝ ነበር።"
ወዳጄ፥ ወደ ከፍታ በተጠጋህ ቁጥር የሚያጨበጭብ ይበዛል ፤ግን የሚያጨበጭበዉ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም፤ እንደ ቢንቢዋ በእጆቹ መሀል ሊጨፈልቅህ የሚፈልግም ይሆናልና ተጠንቀቅ!!!!!
📒 @FanosLibrary
ትንሿ ቢንቢም እንዲህ ስትል መለሰች፦ "'በጣም አሪፍፍፍ..... ነበር፤ ሁሉም ሰዎች እያጨበጨቡልኝ ነበር።"
ወዳጄ፥ ወደ ከፍታ በተጠጋህ ቁጥር የሚያጨበጭብ ይበዛል ፤ግን የሚያጨበጭበዉ ሁሉ ወዳጅህ አይደለም፤ እንደ ቢንቢዋ በእጆቹ መሀል ሊጨፈልቅህ የሚፈልግም ይሆናልና ተጠንቀቅ!!!!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ከድመት ምክሮች: የሰውን ልጅ እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል
✔️ ህግ #1:ሲጠሩህ አትምጣ፡አንተ ድመት እንጂ ውሻ አደለህም
✔️ ህግ #2 ምግብ አስቸኳይ
አይደለም::አሽትተውና ሂድ::እንድትበላ
እንዲለምኑህ አርጋቸው::
✔️ ህግ# 3 ሁሌም የትኩረት ማእከል ሁን። ምንም ችግር የለውም:: ብቻ አድርገው::
✔️ ህግ #4 ችላ ማለት ሀይል ነው᎓᎓ ግርርር ማጭበርበር ነው::ሁለቱንም ተማር
✔️ ህግ #5 በተደጋጋሚ ቀንም ሌትም ሚያው በል᎓᎓ድምፅህ መሰማት አለበት::
✔️ ህግ# 6 ተበሳጨ ? አሳያቸው ው:: በምክንያት ጥፍር ይዘህ ነው የተወለድከሙ:: ተጠቀምባቸው ጥፍሮችህን ዝም ብለህ እያወጣህ አሳያቸው
✔️ ትዛዝ#7 ግድግዳ ላይ ዝም ብለህ አፍጥጥ። ፡እንዲገምቱ አርጋቸው:ግራ ማጋባት መቆጣጠሪያ ነው
✔️ ትዛዝ #8 ሀይል በዝርዝሮች ይደበቃል::ቀርፋፋ ብልጭታ=አጠቃላ ይቁጥጥር ( የድመት Code)
✔️ ህግ#9 ውድ አሻንሊቶችን ችላ በል በምትኩ በሳጥን በጫማ ተጫወት::
✔️ ህግ#10 ፈፅሞ አትርሳ። ሰው አገልጋይህ ነው::አንተ ዋና ስራ አፈፃሚ ነህ:
📒 @FanosLibrary
አይደለም::አሽትተውና ሂድ::እንድትበላ
እንዲለምኑህ አርጋቸው::
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አእምሯችን በጣም ሰላም ወዳድ ነው። ድካም ሲሰማን ወይም ፈተና ሲበዛብን "ይበቃሃል፣ አቁም" ይለናል። ነገር ግን እውነታው አእምሯችን "አቁም" የሚለን ገና 40% አቅማችንን ስንጠቀም ብቻ ነው። የቀረውን 60% የምንጠቀመው ድካምንና ፍርሃትን አልፈን ስንሄድ ነው።
ምቾት ማጣት (Discomfort) የእድገት ምልክት ነው። ጡንቻ የሚገነባው ክብደት ሲያነሳ እንደሚታመመው ሁሉ፣ ጠንካራ ስብዕና የሚገነባውም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፎ በመሄድ ነው። ራስህን አታባብል፤ በየቀኑ በትንሹም ቢሆን ራስህን ተፈታተን።
ዛሬ፣ ሰነፍ ማንነትህ "ይበቃሃል" ሲልህ፣ በሩን ዝጋበትና ለተጨማሪ 10 ደቂቃ ስራህን ቀጥል። አቅምህ ያለው ከድካምህ በኋላ ነው።
📖 መጽሐፍ: Can't Hurt Me
✍️ ደራሲ: David Goggins
━━━━━━━━━━━━━━━━━
📒 @FanosLibrary
ምቾት ማጣት (Discomfort) የእድገት ምልክት ነው። ጡንቻ የሚገነባው ክብደት ሲያነሳ እንደሚታመመው ሁሉ፣ ጠንካራ ስብዕና የሚገነባውም አስቸጋሪ ሁኔታዎችን አልፎ በመሄድ ነው። ራስህን አታባብል፤ በየቀኑ በትንሹም ቢሆን ራስህን ተፈታተን።
ዛሬ፣ ሰነፍ ማንነትህ "ይበቃሃል" ሲልህ፣ በሩን ዝጋበትና ለተጨማሪ 10 ደቂቃ ስራህን ቀጥል። አቅምህ ያለው ከድካምህ በኋላ ነው።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በህይወትህ ላይ የሚደርሱትን መጥፎ አጋጣሚዎች (ህመም፣ ስደት፣ ኪሳራ) መቆጣጠር አትችል ይሆናል። ነገር ግን በእነዚያ ሁኔታዎች ውስጥ ለምትሰጠው "ምላሽ" ሙሉ ስልጣኑ የአንተ ነው።
ሰው ሁሉንም ነገር ሊነጠቅ ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ነገር መቼም አይነጠቅም፦ እሱም "በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የራስን አቋም የመምረጥ ነፃነት" ነው። የሚኖርለት "ዓላማ" (Meaning) ያለው ሰው ማንኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ (How) መቋቋም ይችላል።
ዛሬ፣ በህይወትህ ያለውን ከባድ ነገር እንደ ቅጣት ሳይሆን፣ እንደ ትልቅ ትምህርት ተመልከተው። "ይህ ነገር ምን ሊያስተምረኝ ፈልጎ ነው?" ብለህ ጠይቅ። ትርጉም ስታገኝ ህመሙ ይቀንሳል።
📖 መጽሐፍ: Man's Search for Meaning
✍️ ደራሲ: Viktor Frankl
━━━━━━━━━━━━━━━━━
📒 @FanosLibrary
ሰው ሁሉንም ነገር ሊነጠቅ ይችላል፤ ነገር ግን አንድ ነገር መቼም አይነጠቅም፦ እሱም "በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ የራስን አቋም የመምረጥ ነፃነት" ነው። የሚኖርለት "ዓላማ" (Meaning) ያለው ሰው ማንኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ (How) መቋቋም ይችላል።
ዛሬ፣ በህይወትህ ያለውን ከባድ ነገር እንደ ቅጣት ሳይሆን፣ እንደ ትልቅ ትምህርት ተመልከተው። "ይህ ነገር ምን ሊያስተምረኝ ፈልጎ ነው?" ብለህ ጠይቅ። ትርጉም ስታገኝ ህመሙ ይቀንሳል።
📖 መጽሐፍ: Man's Search for Meaning
✍️ ደራሲ: Viktor Frankl
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ ይህንን ቀን ምክንያት በማድረግ፣ ከአቧራ በታች ያስቀመጥከውን መጽሐፍ አውጣና ቢያንስ 5 ገፅ አንብብ። መጽሐፍ መግዛት ካልቻልክ በፒዲኤፍ (PDF) ማንበብ ጀምር። በየቀኑ የምታነባቸው ጥቂት ገጾች ከዓመት በኋላ ፍጹም የተለየ ሰው ያደርጉሃል።
መልካም የዓለም የመጽሐፍ ቀን!
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዩቱብ ሚስጢሮች (From atuusol).pdf
47.6 MB
📚ርዕስ:- ዩቱብ ሚስጢሮች
📆ዓ.ም:- 2017/2025
📝ደራሲ:- አቤል ብርሃኑ የወይኗ ልጅ
📜ዘውግ:- ስለ ዩቲዩቭ ቪዲዩ አሰራር
📑የገፅ ብዛት :- 158
✨✨የዩትዩብ ሚስጥሮች መፅሃፍ ✨✨
☑️ስለዩትዩብ ምንነት
☑️ተፅዕኖ ፈጣሪነት
☑️ስለ አልጎሪዝም
☑️እንዴት በአጭር ጊዜ ስኬታማ ዩቲዩበር መሆን ይቻላል
☑️በዩቲዩብ ስንት ብር ይገኛል
☑️ምን ቪዲዮ ልስራ
☑️የዩቲዩብ ህጎች ምንድናቸው ለሚለው ሁሉ ምላሽ የያዘ ሲሆን ከ8 አመት በላይ ዩቲዩብ ላይ ከነበሩት የአቤል ብርሀኑ ልምዶች ውጤቶችና ስህተቶች ካሳለፋቸው ልምዶች የተፃፈ ነው።
☑️ በአጠቃላይ መጽሃፉ ዮቲዩብ ቻናል ከመክፈት ጀምሮ እንዴት ለሰው ተደራሽ እንደምንሆን እንዴት ቪዲዮዋችንን ኤዲት እንደምናደርግ ተምብኔል አሰራር እንዴትስ ለክፍያ ብቁ እንደምንሆን እንዲሁም ምን አይነት ቪዲዮ ብንሰራ አሪፍ ብር መስራት እንደምንችል ጨምሮ ብዙ ነገሮችን ስለዩትዩብ ከሃ እስከ ፐ ተብራርቶበታል።