የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በ4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ እረፍት ምክንያት መላው የሚንስትር መ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች የተሰማንን ጥልቅ ሃዘን እንገልጻለን።
በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ስራ ዛሬ ማለዳ ተጀመረ፡፡
በዛሬው ዕለት ጠዋት በነበረው በረራ በአጠቃላይ 434 ሴቶች ከነዚህም መካከል 117 ህፃናት ተመላሾች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል፡፡
ከሳዑዲ ተመላሽ ዜጎችን ለመመለስ መንግስት በሚያደርገው ጥረት ከ7 እስከ 11 ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ከ100 ሺህ በላይ ዜጎችን ለመመለስ እቅድ መያዙ ይታወቃል፡፡
የዚሁ ዕቅድ አካል የሆነው የመጀመሪያው ዙር ተመላሾች ዛሬ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል፡፡
ተመላሾቹን ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ዴኤታዎች፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የፌዴራል የሴክተር ተቋማት የወጣቶችን ጉዳይ በዕቅዶቻቸውና በልማት ፕሮግራሞቻቸው ውስጥ በማካተት በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባ ተጠቆመ::
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣቶች ጉዳይ በማካተት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከፌደራል ሴክተር ተቋማት ጋር ምክክር አካሂደዋል፡፡
አቶ ሰለሞን አሰፋ በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚኒስትር አማካሪ የወጣቶች ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሙና አህመድን በመወከል ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር ወጣቶች ያለባቸውን ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮቻቸውን በጋራ ጥረት በመፍታት ወጣቶች ሀገራችን በጠንካራ መሰረት ላይ እንድትቆም ማድረግ የሚችሉ የነገ ተስፋዎች ከመሆናቸው አንፃር መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸው ተጠብቆላቸው በልማቱ ውስጥ በስፋት እንዲሳተፉ ለማድረግ መንግስታትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት የወጣቶችን ጉዳይ በዕቅዶቻቸውና በልማት ፕሮግራሞቻቸው ውስጥ በማካተት በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡
አክለውም የወጣቶች ኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተፈጠሩትን የስራ ዕድሎች በማየት ጠንካራ ጎን፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና የተወሰዱ መፍትሄዎች ላይ ውይይት በማድረግ በቀጣይ በሚኖረን መድረክ የወጣቶች ማህበራዊ ተጠቃሚነት በስፋት በማየት በፌደራል ደረጃ እንደ ተቋም ፎረም የሚቋቋምና ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ እንደሚኖር አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የግብርና ሚኒስቴር በስራዕድል ፈጠራ ዙሪያ ባለፉት ወራት የተሰሩ ስራዎቻቸውን ካቀረቡ በኃላ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም በሰነድ አቅራቢዎች እና የሚንስትር መ/ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ለቀረቡት አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶ የምክክር መርሃግብር ተጠናቋል፡፡

የሴቶች፣የህጻናት፣የወጣቶች፣ የአረጋዊን እና የአካል ጉዳተኞችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ እና አጋር አካላት ጋር ተቀናጅቶ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
https://www.facebook.com/100069070785075/posts/301422328836791/?sfnsn=mo

በቅርብ የፍቅር አጋር አማካኝነት ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃታቶችና የሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ ወጪዎችን የሚዳስስ ጥናት ውጤት ግምገማ ተካሄድ፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤እና ዩ ኤን ዉመን፤ በጋራ በመሆን በቅርብ የፍቅር ግንኙነት ባላቸው አካላት አማካኝነት በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት የሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ ወጪዎች የሚዳስስ ጥናት (Economic Costs of Intimate Partner Violence)ሲሆን በዛሬው ዕለት የጥናቱ ግምገማ ተካሂዷል፡፡
አዉደ ጥናት ግምገማው ላይ ክብርት ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታን በመወከል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ስለሺ ታደሰ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እንደገለፁት ይህ ጥናት በቅርብ የፍቅር ግንኙነት ባላቸው አካላት አማካኝነት በሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት የሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ ወጪዎች ላይ የተሰራ አገራዊ ጥናት ለሴቶች፣ ለቤተሰብ፣ ለመንግስት እና ለሰፊው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ አጉልቶ ያሳያል። ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የዩኤን ውመን ኢትዮጵያ ተወካይ ሚስ አና ሙታቫቲ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት የጥናቱ ግኝቶች በፖሊሲ አውጪዎች፣ በልማት አጋሮች እና በህብረተሰቡ በአጠቃላይ በሴቶች እና ልጃገረዶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን እና የሚያስከትላቸው ኢኮኖሚያዊ ወጪዎችን እንዲሁም የሚደርሱ ማህበራዊ ወጪዎችን በተመለከተ ግንዛቤን ለማሳደግ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
የጥናቱ ወቴት ናሽናል ዩኒቨርሲቲ ኦፍ አይርላንድ (National University of Ireland)እና ፍሮንቴር ኮንሰልት (Fronteir Consult)አማካኝነት ቀርቦ ተሳታፊዎች በቡድን በመሆን በመወያየት ግብዓት ሰተውበታል ::

ሰብዓዊነትና የሚዲያ ተቋማት ሚና ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡
ሰብዓዊነት እና የሚዲያ ተቋማት ሚና በሚል የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ከሚዲያ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡
የዉይይት መድረኩን በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕከት የከፈቱት የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ፀሃፊ እንደተናገሩት የሰብዓዊ ተቋማት የሚዲያ ተቋማትን ሰባቱ አለም አቀፍ የቀይ መስቀል መሠረታዊ መርሆች፣ በተለይም ሶስቱ ማለትም፣ አለማዳላት፣ ገለልተኝነትና ነፃነት፣ ሌሎች አንፃራዊ ባህሪዎቻችንና መገለጫዎቻችን በመሆናቸው ከሚዲያ አካላት ጋር አጋርነቱን ማጠናከር የዚህ አስፈላጊ በመሆኑ ይህ የምክክር መድረክ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባሰተላለፉት መልዕክት ሚዲያ በመንግስትና በህዝብ መካከል ድልድይ ሆኖ ገንቢ ሚና የሚጫወት መሆን ይጠበቀበታል በዚህም በሃረ መንግስት ግንባታው ሂደት ውጤታማነት ትልቅ አስተዋዕፆ ይኖራቸዋልና የሚዲያ ነፃነትን ከሃላፊነትና ከተጠያቂነትጋር አጣምረን ልንመለከት ይገባል ብለዋል፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርና አጋሮቹ እንደሁም መገናኛ ብዙሃን ቅድሚያ ለሰብዓዊነት በመስጠት የሚያከናውኗቸው ሰብዓዊነት ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑና ሚናቸውንም በሚገባ መወጣት እንዲችሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጀመረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ እንደሚቀጥልና አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
በተመሰሳይ የጤና ሚኒሰቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው፥ ሰብዓዊ ምላሽ በሚፈልጉ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ሚዲያ ያለው ሚና ትልቅ በመሆኑ ሁላችንም የሚዲያ አከላላትን አቅም ለማጎልበት ተባብረን መስራት ይገባናል ብለዋል፡፡