ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
236K subscribers
290 photos
1 video
16 files
231 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
#ቋሚ ነገር የለም

እራሳችሁን ብዙ አታስጨንቁ፣ ያሰብኩት ሁሉ ለምን አልሆነም ብላችሁ ከራሳችሁ ጋር አትጣሉ፣ ከአቅማችሁ በላይ እየታገላችሁ ራሳችሁን አታድክሙ። ሁሉም ነገር በጊዜ እንደሚቀየር አስተውሉ። ተጨነቃችሁ ተጠበባችሁ፣ አወጣችሁ አወረዳችሁ፣ እራሳችሁን ጎዳችሁ አልጎዳችሁ በስተመጨረሻ ነገሮች ሁሉ መቀየራቸው አይቀርም። ስንት ዋጋ የከፈላችሁለት፣ ደጋግማችሁ በይቅርባይነት የጠገናችሁት፣ ለረጅም ጊዜ የተንከባከባችሁት የፍቅር ህይወታችሁ የኋላኋላ እንቅልፍ ሲያሳጣችሁ፣ ከልክ በላይ ሲያስጨንቃችሁና ለከፋ ችግርም ሲያጋልጣችሁ ዝም ብላችሁ አትመልከቱ። የትኛውም ሀሳብ ስልጣን ሰጥታችሁት እንጂ በእናንተ ላይ ምንም አይነት ስልጣን የለውም፣ ሊኖረውም አይችልም። ቅዱስ መፅሐፍ ይህን ይላል፦ "ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንዳች ክንድ የሚጨምር ማነው?" ስለተጨነቅን የሚስተካከል ነገር ቢኖር መልካም ነበር ነገር ግን የለም፤ ስለተዋከብንና ስለተጣደፍን በፍጥነት የሚሳካ ነገር ቢኖረን ጥሩ ነበር ነገር ግን የለም። ሁሉም በሰዓቱ ይቀየራል፣ ሁሉም በጊዜ በእጃችን ይገባል። የእኛ ድርሻ በተቻለ አቅም ነፃ ሆኖ መኖር ነው።

አዎ! ምንም
ቋሚ ነገር የለም፣ አንዳች ዘላለም እንደነበር የሚኖር ነገር የለም። ጥቂት የማይባል ሰው ለአንዲት ነፍሱ ብሎ እራሱ የከፋ አደጋ ውስጥ ይጥላል፣ የማያውቀውን ዓለም ናፍቆ ለሞት እራሱን ያጋልጣል፣ የነገሮችን መቀየር መታስ አቅቶት የገዛ ዓለሙን በጨለማ ይሞላል። ዛሬ ላይሆን ይችላል፣ አሁን የታሰበው ነገር ላይሳካ ይችላል፣ በዚህ ሰዓት የተፈለገው ለውጥ ላይመጣ ይችላል ነገር ግን አሁን አልሆነም ማለት ነገም አይሆንም ማለት አይደለም። እስካልቸኮላችሁ ድረስ አይናችሁ እያየ ብዙ ነገር ሲቀየር ትመለከታላችሁ። ለከፋው የህገወጥ ስደት፣ ማንነትን ለሚገድለው መጥፎ ሱስ፣ አንገት ለሚያስደፋው የበታችነትና ፍረሃት እራሳችሁን አሳልፋችሁ አትስጡ። ነፍስን ሸጦ የሚኖር ህይወት የለም። አስቡት ምናልባትም እናንተ ዛሬ እራሳችሁን የሰዋችሁለት ህይወት ውስጥ እናንተ አትኖሩም ይሆናል። እራስን ከማጣት የከፋ ወድቀት የትም የለም። ሰው ሆኖ ሰውነትን መርሳት፣ የተከበሩ ሆኖ እንደ ርካሽ መናኛ መታየት፣ ብርቱ ሆኖ እነተልፈሰፈሱ መኖር የምርም ቅስም ሰባሪና ተስፋ አስቆራጭ ነው። ነገር ግን ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ያቀረቀረው አንገት ነገ ቀና ይላል፣ ዛሬ የተሰበረ ልብ ነገ ይጠቀናል።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንም የሚቀየር ነገር የለም ብለህ ቶሎ ተስፋ አትቁረጥ። ታጋሽ ሰው በረዶ ውሃ ሲሆን ያያል። በነገሮች ጊዜያዊነት የሚያምን ሰውም ከክፉው ቀን ማግስት መልካሙን ቀን ለማየት ይበቃል። ፅኑ ልብ የማይሻገረው የህይወት ፈተና የለም፣ በአምላኩ ስራ የሚያምን ሰው በየትኛውም ውድቅ አይሰበርም። ማግኘትና ማጣት፣ ማትረፍና መክሰር፣ መውደቅና መነሳት የህይወት ተቃራኒ ገፆች ናቸው። ለረጅም ጊዜ ሲያተርፍ የኖረ ነጋዴ የሆነ ጊዜ ሊከስር ይችላል፣ እንዲሁ ደጋግሞ ሲከስር የነበረ ነጋዴም አንድ ቀን ከኪሳራው በላይ የሚያተርፍበት ቀን ይመጣለታል። ለብዙዎች ሀብታም መሆን ከባድ አይደለም፣ ሀብታም ሆኖ መቆየት ግን እጅግ ፈታኝ ነው። ምክንያቱም ምንም
ቋሚ ነገር የለም። ምን እንዴትና መቼ መቀየር እንደሚችል አይታወቅም። በጊዜያዊ ስሜት አትረበሽ፣ በወቅታዊ ደረጃህ አትከፋ፣ አሁን ስለሆነብህ የከፋ ነገር ከልክ በላይ አትጨነቅ። ምንም ቋሚ ነገር በሌለበት ዓለም የእኔ ህይወት አይቀየርም ብለህ በፍፁም በራስህና በፈጣሪህ ተስፋ እንዳትቆርጥ።

#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄