ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
242K subscribers
288 photos
1 video
16 files
237 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ወደቀልቧ እስክትመለስ እና መኝታ ቤቷ ውስጥ ያልጋበዘቻችው ሰዎች እንደገቡ ለመገንዘብ ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባት ….

‹‹እንዴት ብትደፍረኝ ነው ግን ሰተት ብለህ መኝታ ቤቴ ድረስ  ሚስትህን ይዘህ የገባኸው……?.›

ኤርሚያስ ግራ ተጋባ … ተርበተበተ……‹‹ይቅርታ..ማለት ሚስቴ አይደለችም…. አላውቃትም..ይቅርታ ማለቴ አውቃታለሁ ግን ይሄውልሽ እሷ….››
አቋረጠችው ‹‹…ውጣልኝ …ውጡልኝ..››ጭንቅላቷን በእጆቾ ይዛ ጩኸቷን ለቀቀችው….

‹‹እሺ እንወጣለን..አንቺ ብቻ ተረጋጊ… እንወጣለን…ይሄው እየወጣን ነው…››የሚያደርገው ጠፍቶት ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበራፉ ፊቱን አዞረ…

ኬድሮን‹‹አባትሽን ላገናኝሽ ነው የመጣሁት››አለቻት

ከተቀመጠችበት ወንበር ንቅንቅ ሳትልል
ከትከት ብላ ሳቀች..የምፀት ሳቅ…..የእብደት ሳቀ..የንዴት ሳቅ

‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ከሞተው አባቴ ጋር ምታገናኚኝ….…?ነው ወይስ ከበድኑ ነው ልታገኛኚኝ ያሰብሺው…..አመሰግናለሁ በድኑ በእጄ ስለሆነ አትልፊ  ….››

‹‹አይ እዲያናግርሽ ማድረግ እችላለሁ››

‹‹እንዲያናግረሽ አልሽ…..ኤርሚያስ ምን በድዬሀልው..…?››አለችው ወደእሱ ዞራ

እየተርበተበተ‹‹..ሰላም አንቺ ምን በወጣሽ.. አረ ምንም አልበደልሺኝም  …ለምን እንደዛ ልትይ ቻልሽ…?››

‹‹እንዴ ያንተ ሳያንስ ሌላ ሰው ይዘህ መጥተህ እድታሾፍብኝ ታደርጋለህ……?በሀዘኔ እንዴት ታላግጣላችሁ….…?በቁስሌ እንዴት ጨው ትነሰንሳላችሁ…?ይሄ ምን አይነት ጭካኔ ነው …?…››

‹‹አረ በፍፅም እንደዛ አይደለም….አንቺን ለመርዳት እንጂ ሌላ ምንም አላማ የለንም››

‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው ከአባቴ የምታገናኘኝ……?.››

‹‹እሱን አንዴት እንደሆነ አላውቅም ..ግን ታደርገዋለች ››አለ አንዴ ኬድሮንን አንዴ ሰላምን በማፈራረቅ እያየ
ልታስረዳት ሞከረች‹‹እመኚኝ  የሙት መንፈስ ማናገር እና ከሚወዶቸው ሰዎች  ጋር የማገናኘት ችሎታ አለኝ…መቼስ ስለዚህ ጉዳይ ሰምተሸ አታውቂም  ለማለት አቸገራለው….››

‹‹ሰምቼማ አውቃለው..በመጽሀፍ ቅዱስ ላይም አንብቤያው..ግን ..››>

‹‹ምንም ግን የለም…››ብላ ንስሯን እንዲመጣ በአዕምሮዬ መልዕክት አስተላለፍችለት ….. ክንፉን እየማታ መጣና  አልፎን ፈሪጁ ላይ ጉብ  ሲል  ሰላም  በድንጋጤ ተንደርድራ ልትሰፍርበት ስትል ቦታ ቀየረና አመለጣት….

‹‹አባቴን ..አግዙኝ…. አባቴን አንዳይነካብኝ››

‹‹አይዞሽ የእኔ ንስር ነው ..ምንም አያደርግም…››

‹‹እርግጠኛ ነሽ ……?አባቴን አይነካውም…?››አለች… በእሷ ግምት የኬድሮን ንስር  የአባቷን በድን አካል ለመዘንጠል ይዳዳል ብላ ነው

‹‹እንዴ ንስር የሞተ ነገር እንደማይነካ አታውቂም…››

‹‹አላውቅም››አለች

‹‹እኔም አላውቅም ››በማለት ድጋፍ ሰጣት  ኤልያስ

ማብራሪያዬን በኩራት ቀጠልኩ ‹‹ንስር ኩሩ ነው…እራሱ አባሮ… እራሱ ታግሎ …እራሱ ገድሎ ካልሆነ ነክች አያደርግም…ለማንኛውም አሁን ተዘጋጂ ቁጭ በይ ››….ቁጭ አለች…
‹‹ይሄሁልሽ አሁን ንስሬ ያግዘኝና ከአባትሽ መንፈስ ጋር አገናኝሻለሁ...ማለት የእኔን አንደበት ተጠቅመው አባትሽ ቀጥታ ያናግሩሻል..በእኔ አንደበት በራሳቸው ድምፅ››

‹‹እሺ››

‹‹ኤርምያስ አንተ ደግሞ ካለህበት እንዳትነቃነቅ..ምንም የሚረብሽ ነገር ካለ ትኩረቴን ስለሚበታን መሀል ላይ ግንኙነቱ ሊቋረጥ ይችላል››

‹‹አረ በፍጽም ይሄው ንቅንቅ አልልም..ትንፋሼ እራሱ አይሰማም››አለና በተቀመጠበት ጭብጥብጥ አለ

ሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኑን ሳታረጋግጥ አዕምሮዋን ከንሰሯ ጋር አገናኘቸው..ለደቂቃዎች ተመሰጠች …ይሄን ነገር ከዚህ በፊት አድርጋው አታውቅም ‹‹..ግን ማድረግ አያቅተኝም›ስትል በራሷ ተማመነች….አዎ ንስሯ የአባቷን ነፍስ ካለችበት እንድትመጠ እየጋበዘ  ነው..ወይ ብዙም አላስቸገራትም ….ቀጥታ አባትዬው በኬድሮን አንደበት ልጃቸውን ማናገር ጀመሩ……

‹‹ልጄ ሰላሜ…››

ባለማመን መለሰች‹‹ወይ አባዬ..››ተንደርድራ ሬሳውን እያየች
‹‹እዛ ለምን ትፍልጊኛለሽ….…?አይ ልጄ ስጋዬ ውስጥ አይደለሁም.. …ግን ደግሞ ወደዘላለም ማረፊያዬም መሄድ አልቻልኩም..ከሁለቱም ሳልሆን በአየር ላይ ተንጠልጥዬ አለሁልሽ፡፡

‹‹ምነው አባዬ……? እኔ ልሰቃይልህ…..እኔ በአየር ላይ ለዘላለም ተንጠልጥዬ ልቅር››

‹‹አይ ለምን ልጄ…? ለምን..…?ለአንቺማ ይሄ አይገባም…ትቼሽ ስለሄድኩ ይቅርታ ልጄ..ምን ላድርግ የአማላክ ጥሪ ነው….እባክሽ ልጄ ከዚህ በላይ እንድሰቃይ አታድርጊኝ…››

‹‹እንዴ አባዬ እኔ አንተን ማሰቃየት…?››

‹‹አዎ እናቴ… እዚህ እቤቴ ውስጥ በድን አካሌን ታቅፈሽ እንደዚህ ሆነሽ እንዴት እፎይ ብዬ ወደዘላለም የሚወስደኝን  መንገዴን እቀጥላለሁ..…?አልችልም ልጄ ..አካሌ መሬት ሳይገባ ነፍሴ ወደአምላኮ ልትሄድ ይከብዳታል..ልጄ እባክሽ በአምላክ  ስራ ጣልቃ አትግቢ..››

‹‹እንዴት አባ……? እንዴት ጣልቃ ገባሁ……?.››

‹‹እንዴ ሞትን የፈጠረውን አምላክ  እኮ እየተቃወምሽው ነው..ተሳስተሀል እያልሺው ነው››

‹‹አዎ ተሳስቷልማ..እንዴት አንድ አባቴን ይነጥቀኛል..…?እንዴት ባዶዬን ያስቀረኛል….…?.››

‹‹አየሽ ልጄ …ሞት እርግጥ በጥፋታችን ምክንያት የተሸለምነው ቅጣታችን ነው…ይሁን እና በዚህ ምድር ለመኖር እስከመጣን  ድረስ   ሞታችንም በጣም አስፈላጊ ነው..››

‹‹እንዴት አባ .. …?ሞት ደግሞ እንዴት ነው ጠቃሚ የሚሆነው.?››

እግዜር ፈጥሮ ምድር ላይ ቢረሳንስ ምን ይውጠናል….…?አርጅተን መንቀሳቀስ አቅቶን እቤት እስክንቀር…. ቆዳችን እስኪጨማደድ እና  ወበታችን እስኪረግፍ ድረስ አልወስዳችሁም ቢለን ማነው የሚጎዳው……?.ጥርሳችን ረግፎ ገንፎ እንኳን  ማኘክ እስኪያቅተን ቢተወን …አይናችን ለግሞ  የልጅ ልጆቻችንን ከጎረቤቶቻችን ልጆች መለየት እስኪያቅተን ..መኝታ ቤታችን ከሽንት ቤታችን መለየት እስኪሳነን ድረስ ኑሩ ብንባል ሽልማት ነው ቅጣት…ዕርግማን ነው ምርቃት…?››

‹‹እንዴ አባዬ.. …!!!አንተ እኮ ገና ነህ …ሰባ አመት እንኳን አልሆነህም..…?››

‹‹እኮ እግዚያብሄር ይወደኛል ማለት ነዋ..…?ምላሴ ጣዕም መለየት ሳይሳነው፤አይኖቼ ማንበብ ሳያቆሙ ፤እግሮቼ ላምሸው ከዘራ ሳልይዘ አስታወሶኛል…››

‹‹ግን እኮ አባ እኔን ጥለህ ነው የሄድከው…?››

‹‹የሞት መጥፎው ክፍል ያ ነው….አዎ ሁልግዜ የሆነ ነገር ጥለሽ መሄድሽ አይቀርም…ማንም ቢሆን ከዚህ ምድር ሲሰናበት የሆነ ነገር በጅምር ጥሎ መሄዱ የሆነ የሚወደውን ሰው ሳይሰናበት ማምለጡ ያለ እና ግዳጅም ነው….እና ልጄ አንቺ አፈር ካላቀመሺኝ እና በሀዘን መቆራመድሽን እስካላቆምሽ ድረስ ጉዞዬን መጀመር አልችልም… ብጀምርም ቶሎ አልደርስም..ሀዘንሸ ወደኃላ ይስበኛል….ለቅሶሽ  መንገዴን እያጨቀየው ያዳልጠኝ እና አላላውስ ይለኛል…..››

‹‹አባ አረ እኔ እንዲህ የበደልኩህ አልመሰለኝም…?››

‹‹በደልሺኝ እኮ አላልኩም.. ግን  በቃ..አንዳንዴ መሆን ያለበት ነገር እንዲሆን መተው ነው..ታግለሽ ልታሸኝፊው ከማትችይው ነገር ጋር መታገል  ከድካም ውጭ እርባን ያለው ውጤት አያስገኝም ››

‹‹እና ምን ላድርግ አባ…?››