ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
243K subscribers
289 photos
1 video
16 files
239 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹እኮ የምታደርጉትን ነገር አቁሙ ነው እያልንሽ ያለነው  ..በግልጽ እንንገርሽ  መሰለኝ….እርሱ መዳን አይችልም ማለት መዳን የለበትም …..እሱ ከዳነ  እኛ እንጠፋለን ማለት-ነው….ስለዚህ  እረዳሽንም አረዳሽንም እሱን ለመግደል የምናደርገው ጥረት አናቆምም….እኛ በራሳችን ማድረግ  ዳግመኛ  መሞከር ያልፈለግነው  የፖሊሶች አይን እየተከታተለን ስለሆነ ነው፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ አሁን የተመረዘበትን መድሀኒት የሰጣችሁት እናንተ ናችሁ….?››

‹‹እሱን ማወቅ ምን ይጠቅምሻል….?›.›

‹‹አይ እሱማ ምን ይጠቅመኛል..እንዲሁ ተገርሜ እንጂ››

‹‹ምንም የሚገርም ነገር የለም..አሁን ባቀረብንልሽ ሀሳብ
ትስማሚያለሽ ወይስ አትስማሚ..

….?››ይጠይቃታል ሰሎሞን ተብዬው….

ወዲያው  አዕምሮዋን አሰርታና የነገሮችን አካሄድ በፍጥነት በመተንበይ ‹‹አረ  እኔ ምን አገባኝ… እናንተ ለራሳችሁ ሰው ያላሰበችሁ እኔ ምን አስጨነቀኝ..እስማማለሁ…››ብላ ትመልሳለች ሰሚራ፡፡

እነሱም ካሰቡት በጣም በፍጥነት  ስለተስማማችላቸው ተደሰቱ..

‹‹አሪፋ…በጣም ጥሩ ውሳኔ ነው››ሰላም፡፡ 

ሰሎሞን  ‹‹እንግዲህ ስንት ቀን እንጠብቅሽ….?››

ሰሚራ ‹‹አንድ ሶስት ቀን እፈልጋለሁ››

‹‹ሶስት ቀን አይበዛም››

ኮስተር ብላ ‹‹ሰው ለመግደል እኮ ነው እየተስማማን ያለነው ..ሰው ለመግደል ሶስት ቀን እንዴት ሆኖ ነው የሚበዛው….?››

ሰሎሞንም በአሪፍ መስመር  እየሄደ ያለው ጠቃሚ ስምምነት ላለመበረዝ  ለስለስ ብሎ‹‹ያው ሞት አፍፍ ላይ ያለ ሰው ለመግዳል ብዙም አይከብድም  ብዬ ነዋ…በተለይ ላንቺ››

‹‹ላንቺ ስትል …….?ስታየኝ ገዳይ እመስላለሁ….?›› መለሰች ሰሚራ ኮስተር ብላ ፡፡

‹‹አይ አረ በፍጽም እንደዛ ማለቴ ሳይሆን የህክምና ዕወቀቱ ስላለሽ..የትኛው መድሀኒት ሰውዬውን በቀላሉ ሊገድለው ይችላል የሚለውን በደንብ ስለምታውቂ ብዬ ነው፡፡››

‹‹እንዳልከው መግደሉ ቀላል ነው..ግን ግድያውን ማንም  ሊደርስበት የማይችል እና  ፖሊስም በምርማራም ሊያረጋግጠው የማይችል መሆን አለበት››

‹‹አየሽ እኔ ቀልቤን በጣም ነው የማምነው…ገና እንዳየውሽ ለዚህ ስራ እንደምትረጂን እርግጠኛ ሆኜ ነበር..እሷ ግን አይሆንም ብላ በጣም ስትከራከረኝ  ነበር የሰነበተችው….እንድረታት አደረግሸኝ …ጀግና ሴት ነሽ..ስራውን በጥንቃቄ እና በፍጥነት ስሪልን እንጂ 100 ሺ ብር ቦነስ አለሽ››ሰሎሞን በፈገግታ ተሞልቶ   አሞገሳት፡፡

‹‹ችግር የለም..ባይሆን እድር ከሌላችሁ እድር ግቡ….››
‹‹ለእሱ አታስቢ›› ብለው  በደስታ ተሰናብተዋት በፈገግታ እደታጀቡ ይሄዳሉ፡፡

ሰሚራ እነሱ እደወጡ ነበር ምን ማድረግ እዳለባት ማሰብ የጀመረችው‹‹…ሰው እዚህ ድረስ መጨካከን የጀመረው መቼ ነው…….?›› ለዛውም በቤተሰብ ደረጃ…እራሷን በድንጋጤ የጠየቀችው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር… ‹‹…ምን ቢያደርጋቸው ነው የራሳቸውን ሰው እንዲህ ለማስገደል የሚጥሩት..….?››ሰው ሰውን  ከሞት ለማትረፍ‹‹…..የሰውን ህይወት ለማስተካከል ይለፋል ገንዘብን ይከሰክሳል እንጂ እንደነዚህ  የራስ ሰውን ለመግደል ምን አነሳሳቸው...….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 37,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
​​📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ቀጥታ  ለፖሊስ ሄዳ ነገሩን  ማመልከት ፈለገች…ግን በዚህ ሀሳብ  ብዙም አልገፋችበትም.. ሰዎቹን  እንዳየቻቸው ገንዘብን እንደወረቀት የሚበትኑ ናቸው..ስለዚህ ለፖሊስ እንዳመለከተች በሆነ መንገድ ቢደርሱበት በሽተኛውን  በሌላ መንገድ አስወግደው ለእሷም እንደማይመለሱላት እርግጠኛ ነች፡፡አንድ ዜጋ እንዲህ አይነት ፈታኝ  የደህንነት ስጋት አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ወቅት  በሀገሩ ህግ  መተማመን ካቃተውና ፍትህ በጥቂት ገንዘብ እና በትውውቅ በቀላሉ እንደሚጠመዘዝ እያሰበ እና  እያመነ ሲሄድ  አደጋ አለው… ምክንያቱም እንዲህ አይነተ ተመሳሳይ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ  የሚሸሽበት መደበቂያ ይጠፋዋል፡፡

ሰሚራም የዚህ ጥርጣሬ ተጠቂ ስለሆነች ፖሊስን አምና የዚህን አይነት ከባድ ጉዳይ ይዛ ወደፖሊስ መሄድ አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ  በራሷ ነገሩን በሚስጥር ለመወጣት ወሰነች..እራሷንም ከአደጋ ከልላ ይሙት በቃ የተወሰነበትን ሰው ለማዳን…፡፡

እንደዛ በመወሰኗ በወቅቱ እራሷንም አስገርሟት ነበር…የገዛ ዘመዶቹ እና  የራሴ የሚላቸው ሰዎች መኖሩን ሳይፈልጉ እሷ ለምን ተጨነቀችለት..ሰው ስለሆነ ብቻ ወይስ ሰባዊነቷ አሸንፎት…..….?
መቼስ ነርስ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ የሞት መንደር ውላ የሞት መንድር  ውስጥ የምታድር ሰው ነች…ሞት ያንን  ያህል የሰው ልጅ የመጨረሻው ክስረት እንዳልሆነ ትገነዘባለች ታምናለችም....፡፡ከሞት ወዲህ ማዶ የሰው ልጅ በመኖሩ ውስጥ የሚያስተናግዳቸው ብዙ ክስረቶች አሉ… ሰውን ከመኖር በታች ከመሞትም በታች የሚያደርጉ የስብዕና ዝቅጠቶች ……
ምን አልባት ይሙት በቃ የተፈረደበት ወጣት ከሞት ተርፎ በገዛ ሰዎቹ የደረሰበትን ክህደት አውቆ   ስብርብር ከማለት ስለእነሱ ምንም ሳያውቅ እንዳፈቀራቸው እና እንዳመናቸው ቢሞት ይሻለው ይሆናል…
መሰል ነገሮችን  በአዕምሮዋ ውስጥ በማጉላላት ለሳዕታት ብትብሰለስልም ይሙት በቃ የተወሰነበትን እና በኮማ ውስጥ የሚገኘውን መላኩን በቃ የራሱ ጉዳይ ብላ ችላ ልትለው አልቻለችም…ስሜቷ ጠቅላላ ይሄንን ልጅ አድኝው የሚል ነበር…
እርግጥ በሰዎች ሀሰብ  ተስማምታ  የታማሚውን  ህይወት እንዲያልፍ ማድረግ ለእሷ ከሱቅ መስቲካ ገዝቶ እንደማኘክ ቀላል ነገር ነው….ያንን ቀላል ነገር በማድረጓም የተሰጣትና  ቼክ እና የሚጨምርላት ቦነስም ህይወቷን ተአምራዊ በሆነ ቅጽበት እንደሚቀይርላት ታውቃለች….የምትወዳቸውን ሽቶዎች ለማርከፍከፍ፤ከደሞዞ የመግዛት አቅም እጅግ የራቁ ብራንድ ቀሚስ እና ጫማዎችን እየቀያየሩ ለመድመቅ…. ቢኖረኝ ብላ እንደህልም የምትመኘውን  መኪና ገዝታ  ለማሽከርከረር…ጠቅላላ የኑሮ ዘይቤዋን  ፍጥነት ይቀይርላት ነበር…
ግን ‹‹ይሄ ሁሉ ቁሳቁስ እና  ድምቀት  በቀሪው ህይወቴ ውስጥ ደስተኛ ሆኜ  እንድኖር ያደርገኛል ወይ ... ….?››ብላ ስትጠይቅ ዝግንን ነበር ያላት ..በየቀኑ ከጣረ ሞት ጋር ግብ ግብ ስትገጥም ታያት…እንኳን በዚህ አይነት ሁኔታ  አቅዳና   ተከፍሏት ግድያ  ፈፅማ ይቅርና  እሷ ቀጥታ የምትከታተለው በሽኛተኛ ህይወት እንደአጋጣሚ ሆኖ እጆ ላይ ሲያልፍ ..‹‹ማድረግ ሲገባኝ ያላደረኩለት ነገር ይኖር  ይሆን እንዴ….….?›› 
‹‹እንደዚህ አይነት መድሀኒት ቢሰጠው ይድን ይሆን… ….?››እያለች መሰል ጥያቄዎችን  እራሷን በመጠቅ መብሰልሰል እና መፀፀት የሁል ጊዜ  ስቃዮ  ነው…እና ይሙት በቃ የተወሰነበትን ወጣት  በሽተኛ  ልታተርፈወ ወሰነች….እራሷን አደጋ ላይ ሳትጥል እሱን ከገዳዮቹ ማዳን…ግን እንዴት አድርጋ….….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 39,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
​​📕ተአምረተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሰላሳ_ዘጠኝ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

በማግስቱ….
ከምሽቱ 1 በሰዓት አካባቢ ነው ሰሚራም ሆነች ዶ/ር እስክንድር የእለቱ የማታ ተረኛ ሆነው ስራቸው ላይ ተስማርተዋል፡፡
ሰሚራ ለመላኩ ዘመዶች ደወለችላቸው…ሰሎሞን ነበር  ስልኩን ያነሳው

‹‹ሄሎ››

‹‹ሄሎ..ሰላም ነሽ?››

‹‹አዎ ሰላም  ነኝ …እንድትመጡ ፈልጌ ነው››

‹‹ማን…..? ››

‹‹እናንተ ናችሁ…. ሁለታችሁም››

‹‹ለምን…..? ምን ተፈጠረ…..?››

‹‹ላደርገው ነው…ማድረግ የምፈልገው ደግሞ እያያችሁ ነው..እናንተ ባላችሁበት››

‹‹አረ ችግር የለውም ..ሁሉን ነገር ካጠናቀቅሽ በኃላ ብትደውይልን ይሻላል››

‹‹እንደዛ አላደርግም…በቃ አሁን በነፍስ ነው ብዬ እንደደወልኩላችሁ አስቡትና  እቤትም ሆነ መንገድ ላይ ለገኛችሁት ሰው እንዲሁም ለሌሎች ዘመዶቻችሁ እየደወላችሁ በነፍስ ነው ተብሎ ተደውሎልናል እያላችሁ ንገሩ ፣እናንተም በ20 ደቂቃ ውስጥ ድረሱ›

‹‹አዎ… በቃ ገባኝ እንመጣለን..ትክክል ነሽ››ስልኩ ተዘጋ 

ሁለቱ ብቻ ሳይሆኑ በሌሎች ከስድስት በማያንሱ ሰዎች ታጅበው ለመምጣት ከ15 ደቂቃ በላይ አልፈጀባቸውም…..ሰላም ያዙኝ ልቀቁኝ በማለት ሆስፒታሉን አተረማመሰችው….ሰሎሞንም እንባውን እየዘራ ወንድሜን እያለ በማጎራት ግቢውን መዞር ጀመረ…
ለስድስት ቀን በኮማ ውስጥ የሰነበተው መላኩ ምን እንደነካው ከዶክተሩና ከሰሚራ ውጭ ማንም በማያውቀው ምክንያት በጣር ነፍስ ጊቢ ነፍስ ውጭ እያቃተተ ነው…ዶ/ር እስክንድር ሲስተር ሰሚራ እና ሌሎች ሁለት ነርሶች ዙሪያውን ከበው  ሊረዱት እየሞከረ ነው..

‹‹ሲስተር ሰሚራ ቶሎ ብለሽ ይሄንን መድሀኒት ውጊው ››ብሎ በወረቀት ላይ የመድሀኒቱን ስም ጽፎ ሰጣት… እሷም ተቀብላ ቶሎ ብላ ወጥታ ሄደችና በሶስት ደቂቃ ውስጥ ይዛ መጣች… መዳሀኒቱን በተንጠለጠው ግሉኮስ ከረጢት ውስጥ በስሪንጅ መጣ ለቀቀችበት ..ቀስ እያለ በቱቦ ውስጥ በመንጠባጠብ ከደም ስሩ ተቀላቀለ…. ከደቂቃዎች በኃላ የበሽተኛው ጣር  እየቀነሰ …መንፈራገጡም እያቆመ መጣ….ከዛ ፀጥ አለ …ሰው ሲሸነፍ ወይም ሲያፈገፍግ ፀጥ ይል የለ….ዶ/ር እስክንድር በማዳመጫ ትንፋሹ አዳመጠው…እጆቹና እያወናጨፈ አንገቱና ቀብሮ በብስጭት ክፍሉን ለቆ ወጣ …ኮሪደር ላይ እነ ሰሎሞን እና አጃቢዎቻቸው ከበቡት.

‹‹ዶክተር..እንዴት ነው በሽተኛው…..?››

‹‹ዶክተር ይሻለዋል ..ፍቅሬ ይድናል…..?››

ለበራካታ ሰከንዶች ተገትሮ ሰላምን አፍጦ ከማየት ውጭ ምንም መናገር አልቻለም፣‹‹….….ይቺን ላየ ሰው እነ ሰላም እና መሀደር ምኑን አክተር ተባሉት ?››ሲል በውስጡ አሰበ…መለስ ብሎም ስለራሱ አሰበ …ወየው ጉድ እኔም ለካ ሌላ ተዋናይ ሆኜያለሁ…አለም ሰፊ መድረክ እኛም ኑሪዎቾ  ተዋናዬች ነን ያለው ማን ነበር …..? ለካ እውነት ነው…›አለና ወደቀልብ በመመለስ ለእነሱ ጥያቄ  መልስ መስጠት ጀመረ 

‹‹አዝናለሁ የተቻለንን አድርገናል…ግን አልተሳካልንም..አርፏል ››ብሎ በተገተሩበት ጥሎቸው እግሮቹን አንቀሳቀሰ  … ግቢውን በጩኸት እና በለቅሶ ሲያደበላልቁት  በውስጡ እየተጠየፋቸው እና እየረገማቸው ጥሎቸው ወደ ቢሮው ሄደ

ሰላም…
..ፍቅሬ ፍቅሬ…
እንጋባለን ብለሀኝ አልነበረ ወይ…
ሙሽራዬ ነሽ አላልከኝም ነበር ወይ..
ለማን ተውከኝ..ለማን ተውከኝ 

ሰሎሞን……
ወንድም ጋሻዬ ….ወንድም ጋሻዬ
የእኔ ብቸኛ..የእኔ ብቸኛ
የአባቴ ምትክ ..የአባቴ ምትክ 
የዓይን ማረፊያዬ….
/////
ከደቂቃዎች በኃላ ሬሳው እየተገፋ ተመላካቹን በእንባ በሚያራጭ እንግሩጉሮአዊ ዜማ እና አንጀት በሚበላ  ሁኔታ በሚያለቅሱት እና ኩርምት ጭብጥ በሚሉት  በወንድሙ  ሰሎሞን እና በፍቅረኛው ሰላም መካከል አልፎ ወደሬሳው ክፍል ተወሰደ…..ሰሚራም እየተንቀጠቀጠች እና እየዘገነናት እራሷን ለማረጋጋት  በትርምሱ መሀል ተሹለክልካ ከሁሉም ነገር በመሸሽ  ቢሮዋ ገብታ ተሸጎጠች
እስከአሁን የሰራችው ስራ እና የፈጠረችው ተግባር ትልቅ ድንጋጤ ውስጥ ከቷት እየተንቀጠቀች  ነው..የሚገርመውና ይበልጥ የሚጨንቀው ግን ከአሁን በኃላ የምትሰራው ስራ ነው…
በበቀልም ሆነ በጥላቻ ተነሳስቶ ሰውን ድፍት አድርጎ መግደል በጣም ቀላል ነው…ሳያስበው በሆነ ብረት ማጅራቱን መጠቅለል እና ዝርግፍ ብሎ ሲወድቅ ጭንቅላቱን በድልዱም ብረት መድገም ነው…አዎ እንደዛ ማድረግ ቀላል ነው… የሚከብደው ከገደሉት በኃላ ያለው ነገር ነው፡፡ሬሳውን ምን ላድርገው…?ግቢው ውስጥ ቆፍሬ ልቅበረው..….?ረሀብ ያንገላታው ውሻ ቆፍሮ አውጥቶ ቢያጋልጠኝስ…?በጆንያ አድርጌ ከከተማ አውጥቼ ራቅ ያለቦታ በመውሰድ ጫካ ውስጥ ልጣለው…?.መንገድ ላይ ፖሊስ ለፍተሻ ቢያስቆመኝስ……..?እንደዛ ሳደርግ ሰው ቢያየኝስ……..?ስቃይ ነው….በዛን ቅጽበት ከሟቹ በላይ ገዳዩ ያሳዝናል…በተለይ  ገዳዩ እንደእሷ አማትር ገዳይ ሲሆን ......ሁኔታው  እንደቅዣት ሆኖባት፤ በውስጧ ስትብሰለሰል  ስልኳ ተንጫረረ….
ከፈጣሪ የተደወለባት ነው የመሰላት….በርግጋ ከተቀመጠችበት በመነሳት ተፈናጥራ ቆመችና የደዋዩን ማንነት ለደቂቆች አትኩራ ተመለከተች…. በፈራ ተባ ስሜት አነሳችው

‹‹አቤት››

‹‹የት ገባሽ…..?››

‹‹አለው ፈርቼ ቢሮዬ ቁጭ ብዬ ነው››

‹‹ምን ያስፈራሻል.…..?.››

‹‹እንዴ ድመት እኮ አይደለም ሰው ነው ያስገደላችሁኝ…..››

‹‹ማለቴ መግደልሽን  ማን ያውቃል..…..?እንደውም ስትፈሪና ስትንቀጠቀጪ የስራ ባለደረቦችሽ እንዳይጠረጥሩሽ…በተለይ ዶክተሩ እንዴት ሞተ ……..?ይሞታል ብለን አልገመትንም ነበር ሲል ሰምቼዋለሁ››

‹‹እ!! እንደዛ  አለ እንዴ…..? ››

‹‹አዎ ብሏል…ለማንኛውም አሁን ምን እናድርግ.››

‹‹ምን ለማድረግ አሰባችሁ?››

‹‹ሬሳውን አሁኑኑ ብትሰጡንና በጥዋቱ ቶሎ ብለን ብንቀብረው ጥሩ ነው፡፡››

‹‹ሬሳውንማ ላሰጣችሁ አልችልም …ጥዋት ነው መውሰድ የምትችሉት››

‹‹አይ አሁኑኑ መውሰድ አለብን… አሁን ሬሳ ሳጥን ገዝተው እንዲመጡ ሰዎች ልኬያለሁ…አንቺ ብቻ ደክተሩን አሳምነሽ እንዲፈርምልኝ አድርጊ…››

‹‹ዶክተሩ እኮ መሞቱን ብቻ ነው የሚያረጋግጥልህ….ሬሳውን በዚህ ምሽት እንድታወጣ የመፍቀድ ስልጣን ያላቸው  ግን ሌሎች ናቸው››

‹‹ሌሎቹን ተያቸው ..ዶክተሩ ብቻ ካስፈረምሽልኝ ካንቺ ምንም አልፈልገም…..ወደቤትሸ ሄደሽ ተረጋግተሸ በድል መተኛት ትችያለሽ…የስራ ኮንትራታችንን እዛ ላይ ይጠናቀቃል….››

‹‹እዛ ላይማ አይጠናቀቅም … መቶ ሺ ብር ጨምርልሻለው ብለኸኝ ነበር››

‹‹ሀይለኛ ብር ወዳድ  ልጅ ነሽ… አይዞሽ አረሳሁትም ግን እንደምታይኝ አሁን ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡ ከሶስት ቀን በኃላ ያው እንደምንም መጽናናቴ  ስለማይቀር  አቀብልሻለሁ…››

‹‹ዋ እንዳትረሳ››

‹‹አረሳም አሁን ያልኩሽን ጨርሺና ደውይልኝ››
ስልኩ ተዘጋ……

ይቀጥላል

#ክፍል 40,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18