ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
236K subscribers
288 photos
1 video
16 files
233 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ስድስት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹እኮ የምታደርጉትን ነገር አቁሙ ነው እያልንሽ ያለነው  ..በግልጽ እንንገርሽ  መሰለኝ….እርሱ መዳን አይችልም ማለት መዳን የለበትም …..እሱ ከዳነ  እኛ እንጠፋለን ማለት-ነው….ስለዚህ  እረዳሽንም አረዳሽንም እሱን ለመግደል የምናደርገው ጥረት አናቆምም….እኛ በራሳችን ማድረግ  ዳግመኛ  መሞከር ያልፈለግነው  የፖሊሶች አይን እየተከታተለን ስለሆነ ነው፡፡››

‹‹ቆይ እስኪ አሁን የተመረዘበትን መድሀኒት የሰጣችሁት እናንተ ናችሁ….?››

‹‹እሱን ማወቅ ምን ይጠቅምሻል….?›.›

‹‹አይ እሱማ ምን ይጠቅመኛል..እንዲሁ ተገርሜ እንጂ››

‹‹ምንም የሚገርም ነገር የለም..አሁን ባቀረብንልሽ ሀሳብ
ትስማሚያለሽ ወይስ አትስማሚ..

….?››ይጠይቃታል ሰሎሞን ተብዬው….

ወዲያው  አዕምሮዋን አሰርታና የነገሮችን አካሄድ በፍጥነት በመተንበይ ‹‹አረ  እኔ ምን አገባኝ… እናንተ ለራሳችሁ ሰው ያላሰበችሁ እኔ ምን አስጨነቀኝ..እስማማለሁ…››ብላ ትመልሳለች ሰሚራ፡፡

እነሱም ካሰቡት በጣም በፍጥነት  ስለተስማማችላቸው ተደሰቱ..

‹‹አሪፋ…በጣም ጥሩ ውሳኔ ነው››ሰላም፡፡ 

ሰሎሞን  ‹‹እንግዲህ ስንት ቀን እንጠብቅሽ….?››

ሰሚራ ‹‹አንድ ሶስት ቀን እፈልጋለሁ››

‹‹ሶስት ቀን አይበዛም››

ኮስተር ብላ ‹‹ሰው ለመግደል እኮ ነው እየተስማማን ያለነው ..ሰው ለመግደል ሶስት ቀን እንዴት ሆኖ ነው የሚበዛው….?››

ሰሎሞንም በአሪፍ መስመር  እየሄደ ያለው ጠቃሚ ስምምነት ላለመበረዝ  ለስለስ ብሎ‹‹ያው ሞት አፍፍ ላይ ያለ ሰው ለመግዳል ብዙም አይከብድም  ብዬ ነዋ…በተለይ ላንቺ››

‹‹ላንቺ ስትል …….?ስታየኝ ገዳይ እመስላለሁ….?›› መለሰች ሰሚራ ኮስተር ብላ ፡፡

‹‹አይ አረ በፍጽም እንደዛ ማለቴ ሳይሆን የህክምና ዕወቀቱ ስላለሽ..የትኛው መድሀኒት ሰውዬውን በቀላሉ ሊገድለው ይችላል የሚለውን በደንብ ስለምታውቂ ብዬ ነው፡፡››

‹‹እንዳልከው መግደሉ ቀላል ነው..ግን ግድያውን ማንም  ሊደርስበት የማይችል እና  ፖሊስም በምርማራም ሊያረጋግጠው የማይችል መሆን አለበት››

‹‹አየሽ እኔ ቀልቤን በጣም ነው የማምነው…ገና እንዳየውሽ ለዚህ ስራ እንደምትረጂን እርግጠኛ ሆኜ ነበር..እሷ ግን አይሆንም ብላ በጣም ስትከራከረኝ  ነበር የሰነበተችው….እንድረታት አደረግሸኝ …ጀግና ሴት ነሽ..ስራውን በጥንቃቄ እና በፍጥነት ስሪልን እንጂ 100 ሺ ብር ቦነስ አለሽ››ሰሎሞን በፈገግታ ተሞልቶ   አሞገሳት፡፡

‹‹ችግር የለም..ባይሆን እድር ከሌላችሁ እድር ግቡ….››
‹‹ለእሱ አታስቢ›› ብለው  በደስታ ተሰናብተዋት በፈገግታ እደታጀቡ ይሄዳሉ፡፡

ሰሚራ እነሱ እደወጡ ነበር ምን ማድረግ እዳለባት ማሰብ የጀመረችው‹‹…ሰው እዚህ ድረስ መጨካከን የጀመረው መቼ ነው…….?›› ለዛውም በቤተሰብ ደረጃ…እራሷን በድንጋጤ የጠየቀችው የመጀመሪያ ጥያቄ ነበር… ‹‹…ምን ቢያደርጋቸው ነው የራሳቸውን ሰው እንዲህ ለማስገደል የሚጥሩት..….?››ሰው ሰውን  ከሞት ለማትረፍ‹‹…..የሰውን ህይወት ለማስተካከል ይለፋል ገንዘብን ይከሰክሳል እንጂ እንደነዚህ  የራስ ሰውን ለመግደል ምን አነሳሳቸው...….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 37,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
​​📕ተአምረተ_ኬድሮነ

#ክፍል_ሰላሳ_ሰባት

#ተከታታይ ልቦለድ

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ቀጥታ  ለፖሊስ ሄዳ ነገሩን  ማመልከት ፈለገች…ግን በዚህ ሀሳብ  ብዙም አልገፋችበትም.. ሰዎቹን  እንዳየቻቸው ገንዘብን እንደወረቀት የሚበትኑ ናቸው..ስለዚህ ለፖሊስ እንዳመለከተች በሆነ መንገድ ቢደርሱበት በሽተኛውን  በሌላ መንገድ አስወግደው ለእሷም እንደማይመለሱላት እርግጠኛ ነች፡፡አንድ ዜጋ እንዲህ አይነት ፈታኝ  የደህንነት ስጋት አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት ወቅት  በሀገሩ ህግ  መተማመን ካቃተውና ፍትህ በጥቂት ገንዘብ እና በትውውቅ በቀላሉ እንደሚጠመዘዝ እያሰበ እና  እያመነ ሲሄድ  አደጋ አለው… ምክንያቱም እንዲህ አይነተ ተመሳሳይ አጣብቂኝ ውስጥ ሲገቡ  የሚሸሽበት መደበቂያ ይጠፋዋል፡፡

ሰሚራም የዚህ ጥርጣሬ ተጠቂ ስለሆነች ፖሊስን አምና የዚህን አይነት ከባድ ጉዳይ ይዛ ወደፖሊስ መሄድ አልደፈረችም….ከዛ ይልቅ  በራሷ ነገሩን በሚስጥር ለመወጣት ወሰነች..እራሷንም ከአደጋ ከልላ ይሙት በቃ የተወሰነበትን ሰው ለማዳን…፡፡

እንደዛ በመወሰኗ በወቅቱ እራሷንም አስገርሟት ነበር…የገዛ ዘመዶቹ እና  የራሴ የሚላቸው ሰዎች መኖሩን ሳይፈልጉ እሷ ለምን ተጨነቀችለት..ሰው ስለሆነ ብቻ ወይስ ሰባዊነቷ አሸንፎት…..….?
መቼስ ነርስ እንደመሆኗ መጠን በየቀኑ የሞት መንደር ውላ የሞት መንድር  ውስጥ የምታድር ሰው ነች…ሞት ያንን  ያህል የሰው ልጅ የመጨረሻው ክስረት እንዳልሆነ ትገነዘባለች ታምናለችም....፡፡ከሞት ወዲህ ማዶ የሰው ልጅ በመኖሩ ውስጥ የሚያስተናግዳቸው ብዙ ክስረቶች አሉ… ሰውን ከመኖር በታች ከመሞትም በታች የሚያደርጉ የስብዕና ዝቅጠቶች ……
ምን አልባት ይሙት በቃ የተፈረደበት ወጣት ከሞት ተርፎ በገዛ ሰዎቹ የደረሰበትን ክህደት አውቆ   ስብርብር ከማለት ስለእነሱ ምንም ሳያውቅ እንዳፈቀራቸው እና እንዳመናቸው ቢሞት ይሻለው ይሆናል…
መሰል ነገሮችን  በአዕምሮዋ ውስጥ በማጉላላት ለሳዕታት ብትብሰለስልም ይሙት በቃ የተወሰነበትን እና በኮማ ውስጥ የሚገኘውን መላኩን በቃ የራሱ ጉዳይ ብላ ችላ ልትለው አልቻለችም…ስሜቷ ጠቅላላ ይሄንን ልጅ አድኝው የሚል ነበር…
እርግጥ በሰዎች ሀሰብ  ተስማምታ  የታማሚውን  ህይወት እንዲያልፍ ማድረግ ለእሷ ከሱቅ መስቲካ ገዝቶ እንደማኘክ ቀላል ነገር ነው….ያንን ቀላል ነገር በማድረጓም የተሰጣትና  ቼክ እና የሚጨምርላት ቦነስም ህይወቷን ተአምራዊ በሆነ ቅጽበት እንደሚቀይርላት ታውቃለች….የምትወዳቸውን ሽቶዎች ለማርከፍከፍ፤ከደሞዞ የመግዛት አቅም እጅግ የራቁ ብራንድ ቀሚስ እና ጫማዎችን እየቀያየሩ ለመድመቅ…. ቢኖረኝ ብላ እንደህልም የምትመኘውን  መኪና ገዝታ  ለማሽከርከረር…ጠቅላላ የኑሮ ዘይቤዋን  ፍጥነት ይቀይርላት ነበር…
ግን ‹‹ይሄ ሁሉ ቁሳቁስ እና  ድምቀት  በቀሪው ህይወቴ ውስጥ ደስተኛ ሆኜ  እንድኖር ያደርገኛል ወይ ... ….?››ብላ ስትጠይቅ ዝግንን ነበር ያላት ..በየቀኑ ከጣረ ሞት ጋር ግብ ግብ ስትገጥም ታያት…እንኳን በዚህ አይነት ሁኔታ  አቅዳና   ተከፍሏት ግድያ  ፈፅማ ይቅርና  እሷ ቀጥታ የምትከታተለው በሽኛተኛ ህይወት እንደአጋጣሚ ሆኖ እጆ ላይ ሲያልፍ ..‹‹ማድረግ ሲገባኝ ያላደረኩለት ነገር ይኖር  ይሆን እንዴ….….?›› 
‹‹እንደዚህ አይነት መድሀኒት ቢሰጠው ይድን ይሆን… ….?››እያለች መሰል ጥያቄዎችን  እራሷን በመጠቅ መብሰልሰል እና መፀፀት የሁል ጊዜ  ስቃዮ  ነው…እና ይሙት በቃ የተወሰነበትን ወጣት  በሽተኛ  ልታተርፈወ ወሰነች….እራሷን አደጋ ላይ ሳትጥል እሱን ከገዳዮቹ ማዳን…ግን እንዴት አድርጋ….….?

     ይቀጥላል,,,,,,,,,

#ክፍል 39,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄