📕ታምራተ_ኬድሮን
#ክፍል_ሀያ_ሁለት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ይሄ ክስት ከተከሰተ ከ5 ዓመት በኃላ 10ኛ ክፍል ማትሪክ ለመፈተን ዝግጅት ላይ እያለች ድንገት እናትዬው በህይወቷ ለሁለተኛ ጊዜ ክፉኛ ታመመች፡፡ አፋፍሰው ደሎ ሆስፒታል አስገቧት….ወደጎባ ወይም ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ትባላለች ብለው ሲጠብቁ ከሶስት ቀን በኃላ ወደቤት መልሳችሁ ውሰዷት የሚል ትዕዛዝ ተሰጣቸው፡፡
ቀጥታ እየተውረገረገች ዶክተሩ ጋ ገባች፡፡
‹‹አቤት ምን ነበር?›
‹‹ስለእናቴ ጉዳይ ነበር››
‹‹ስለእናትሽ ምን?››
ዝልፍልፍ ብላ ደከማለች እኮ ….በህይወትና በሞት መካከል ሆና እየተመለከታችሁ ወደቤት መልሷት ማለት ምን ማለት ነው...?
ካልቻላቸሁ አልቻልንም ብላችሁ ሪፈር ማለት ነው እንጂ ወደቤት መልሷት ማለት ምን ማለት ነው….?ግልፅ አልሆነልኝም፡፡››
‹እስኪ ተረጋጋግተሸ ተቀመጪና ላስረደዳሽ..እንደው ስታስቢው ይሄንን ቀደም ተከተል ማናውቅ አድርገሽ ነው ምታስቢን ?››
‹‹እኔ እንጃ ግራ አጋባችሁኛ››
‹‹ሁኔታውን እኮ ለአያትሽ አስረድቼቸዋለሁ...እሳቸው ቀስ ብለው ያስረዱሻል፡፡››
‹‹እና እናቴ …የእኔ ውዷ እናት …የሌላ አለም ፈጡርን በፍቅር ጠብ ያደረገችው ተአምረኛዋ እናት እንደቀልድ በአንድ ወር ውስጥ ትሞታለች እያላችሁኝ ነው?››
‹‹አይ እኛ አይደለም እንደዛ ያልነው.. እናትሽ ያለባቸው በሽታ ያለበት ደረጃ እና አሁን ባለው የሳይንስ ግኝት በሽታውን ለማከም ያለንን አቅም ከግምት በማስገባት ነው፡፡››
‹‹እና በቃ ውሳኔያችሁ እንደዛ ነው?››
‹‹አዝናለሁ…ለእሳቸውም የመጨረሻዎቹን ቀናቶች ወዲህ ወዲያ እያሉ ውጤት ለማይኖረው ነገር ከሚንገላቱ በቤተሰባቸው እንክብካቤ ውስጥ ሆነው ቢያሳልፉ ይሻላቸዋል፡፡
‹‹እኔ እናቴን ካዳንኳት…ምን ትላለህ?››
‹‹ስለአንቺ የሰማሁትን ለማመን እገደዳለሁ››
‹‹ስለእኔ ምን ሰማህ?››በመገረም ጠየቀችው፡፡
‹የመላዕክት ዝርያ እንዳለብሽ››
‹‹አይ ያሉህ እንኳን እንደዛ አይደለም…የደቢሎስ ዝርያ አለባት ነው ሊሉህ የሚችሉት፡፡››
‹‹ያው ነው…ዳቢሎስም ሌላ ምንም ሳይሆን መላዐክ ነው…ለዛውም ከዋናዎቹ አንድና ዋነኛው የነበረ.በተወሰነ ያለመግባባት ከእግዚያብር የመኖሪያ ግዛት የተሰደደ…››
‹‹የተናገርከው ከልብህ ስለሆነ አስደስተሀኛል…ለማንኛውም ስለጮህኩብህ ይቅርታ.. እናቴን ወደቤት ወስዳታለሁ...እናም አድናታለሁ።››
‹‹እንግዲህ እንዳልኩሽ ነው….ለማንኛውም እቤት ብቅ እያልኩ አያቸዋለሁ..ድንገተኛ ነገር ተፈጥሮ ከፈለግሺኝም ደውይልኝ› ብሎ ቁጥሩን ሰጣት ተቀበለችውና አመስግናለሁ ብላ ወጣች፡፡
ወዲያው ነበር እናቷን ይዛ ወደቤት የገባችው፡፡ግርግሩ ጋብ ሲል ወደ እናቷ መኝታ ቀረበችና…በቀናቶቸ በሽታ የሰለሉና የደከሙ እጆቾን በእጆቾ ውስጥ አስገብታ እየዳበሰች፡፡
‹‹ሀርሜ አይዞሽ እኔ ምንም እንድትሆኚ አልፈቅድም››
‹‹ልጄ በዚህ ጉዳይ እንድትጨነቂ አልፈልግም…እንደውም መሄድ እፈልጋለሁ።››ስትል መለሰችላት፡፡
እማ ምን ማለት ነው …እኔን ጥለሽ ወደየት ነው የምትሄጂው…አንቺ ከሌለሽ እኮ እኔም መኖር በጣም ነው የሚከብደኝ …ማን ነው የሚረዳኝ?›
‹‹ልጄ አንቺ የአባትሽ ልጅ ነሽ. .በጣም ጠንካራና የማትሰበሪ ነሽ…እኔ ብሄድ ምን አልባት አባትሽን አገኘው ይሆናል፡፡ምን አልባት መልሰን አንድ ላይ የመሆን እድል እናገኝ ይሆናል፡፡
‹አይ እንደዛ አይሆንም…የእሱ አለምና አንቺ ስትሞቺ የምትሄጂበት ቦታ አንድ መሆኑን በምን እርግጠኛ ሆንሽ? እንዲህ አይነት ቁማርማ እንድትጫወቺ አልፈቅድም..በይ አሁን ደክሞሻል.. እረፊ .የሆነ ቦታ ደርሼ መጣሁ…››
‹‹ደግሞ ወዴት ልትሄጂ ነው?››
‹‹እማ ደግሞ የሆነ ቦታ አልኩሽ እኮ›ብላ ግንባሯን በመሳም ወጥታ ሄደች.. ግቢውን እንደለቀቀች ከጀርባዋ ንሰሯ እየተምዘገዘገ መጥቶ ተከሻዋ ላይ አረፈ.እርምጃዋን እልገታችም….በሀሳብ እየተብሰለሰለች ቀጥታ ከተማውን ለቃ ወደ ያዶት ወንዝ ነው የሄደችው…እናትና አባቷ ተገናኝተውበት ወደነበረ ልክ እንደቤተመቅደስ እያየች ወደ አደገችበት ቦታ ነው የሄደችው፡፡እንደደረሰች ንስሯ ከትከሻዋ ለቆ ተነሳና በአካበባቢው ካሉት ብዛት ያላቸው ግዙፉ ዛፎች መካከል አንዱ ላይ አረፈ.እሷም ልብሷን አወላልቃ ዛፉ ላይ እስከግማሽ እየተንጠላጠለችና እየተሳበች ወጣችና አስር ሜትር ከፍታ ላይ ከደረሰች በኃላ ዘላ እየተምዘገዘገች ወንዙ ውስጥ ቦጭረቅ ብላ ገባች…ከዛ ወደውስጥ ሰመጠችና የሆነ ሚስጥራዊ ምርምር እንደሚያካሂድ የባህር ውስጥ አሳሽ ውስጥ ለውስጥ ትንፋሿን ተቆጣጥራ ከወዲህ ወዲያ እየተመላለሰች.፡፡
ግማሽ ለሚሆን ሰዓት ከዋኘች በኃላ የድካም ስሜት ሲሰማት ወጥታ ልብሷን ለበሰች፡፡የመጨናነቅ ስሜቷ አሁን ቀለል ብሏታል…ወደዚህ ቦታ የምትመጠጣው ለመታደስ ነው.ከአባቷ መንፈስ ጋር ለመገናኘት..እሱ የረገጣቸውን የወንዙን ወለል ለመርገጥ ፤እሱ የተነፈሰባቸውን ቦታዎች እሷም ልትተነፍስባቸውና ከእሱ ጋር ያላትን የመንፈስ መስተጋብር ለማጎልበት ነው....እናም ደግሞ ምን አልባት አንድ ቀን ቡልቅ ብሎ ከዚህ ከውሀው መሀል በመውጣት ተጠምጥሞ ይስመኛል…በሚል ድብቅ ምኞትም በመጓጓት ነው እንደዛ የምታደረግው;፡
ለባብሳ እንደጨረሰች ‹‹..ጀግናዬ የት ነህ?››ስትል ንስሯን ጠራችው.. እየተምዘገዘገ መጣና ከፊት ለፊቷ ካለ የዛፍ ቅርንጫፍ ላይ አረፈ..
‹‹እሺ ና ተከተለኝ።›› ብላው ወደጥቅጥቁ ጫካ ተራመደች…ወደ ውስጥ ጠልቃ ገባችና የምትፈልገው ቦታ ስትደርስ ከዛፍ ቅርንጫፎች ላይ ቅጠሎችን እየለመለመች መሬት አነጠፈችና እላዩ ላይ ተደላድላ ተቀመጠች…መጥቶ ከጎኗ ተቀመጠ
‹‹እንድናወራ ነው እዚህ የመጣሁት..››
‹‹እየሰማሀኝ ነው አይደል?›
እየሰማት መሆኑን እንድታውቅ አእምሮን ከፈተላት.
‹‹አዎ እንደዛ ነው…እናቴ እንድትድን አፈልጋለሁ።››
‹‹አይቻልም››የሚል መልስ ሰጣት
‹አይ ይቻላል…አንተ የሆነ ተአምር መስራት አያቅትህም ..ከፈለክ ከአባቴ ጋር ተገናኝና እናቴን ማጣት እንደማልፈልግ ንገረው››
‹‹አይቻልም››ፍርጥም ብሎ መለሰላት፡፡
‹‹ኡፍ..እንግዲያው እሷ ከሞተች እኔም መኖር አልፈልግም…. ይሄንን እወቀው››
‹አንቺ ከሞትሽ እኔም አጠፋለሁ››ብሎ ልክ በሞተችበት ቅፅበት እሱ እንዴት ድርቅርቅ ብሎ እንደሚሞትና ከደቂቃዎች በኃላ መላ አካሉ እንደድቄት ተበታትኖ እንደሚበን አሳያት፡፡ እዝን አላች፡፡
እንዲህ የእሱ ህይወት ከእሷ መኖር ጋር እንደተያያዘና ስትሞት ሟች እንደሆነ ፈፅሞ አታውቅም ነበር..እና እንደዛ በመሆኑ በጣም አዘነች…ቢሆንም ግን ሀሳቧን ለመቀየር ምንም እቅድ የላትም.. መልፈስፈስን አልፈለገችም፡፡
"በጣም እወድሀለሁ.. ታውቃለህ አይደል?.ግን ደግሞ እናቴን ከምንም በላይ ፤ከማንም በላይ ነው ምወዳት እና እንዳልኩህ እናቴ ከሞተች እኛም አብረናት እንሞታለን ማለት ነው።››
የመጨረሻ ውሳኔዋን ከምትናገረው ንግግር ሆነ ከውስጧ ልቧን በማንበብ ከተረዳ በኃላ ከጎኗ ብተት ብሎ ተነሳና ሰማይ ጠቀስ ዛፎችን አልፎ በረረ....ቀጥታ ጭጋጋማውን ደመና አልፎ ተሰወረ.. እዛው በተቀመጠችበት ወደላይ አንጋጣ በአይኖቾ ሸኘችውና ወደትካዜዋ ተመለሰች፡፡

ለሀኪሙ ፏክራ በልበ ሙሉነት እናቷን እንደምታድናት ነግራው ነበር..ለእናቷም ለራሷም አድንሻለሁ ብላ ቃል ገብታላት ነበር…ግን አሁን ምንም ማድረግ እንደማትችል እየተሳማት ነው፡
‹‹እናቴን ማዳን ካልቻልኩ እማ .ዝም ብሎ ሰው ብቻ ነኝ…ተራና ጥበብ አልባ ሰው..ይሄ እንዴት ይሆናል?›
‹‹አባዬ የሆነ ነገር እማ አድርግ… ልጅህ በዕድሜዋ ሙሉ ልትጠይቅህ የምትችለው ብቸኛ ውለታ አድርገህ ውሰደው…እኔም ምን አልባት በዚህ ምድር የሆነ ነገር እንዳደርግልህ ትፈልግና ትጠይቀኝ ይሆናል…ይንን ነገር ካደረክልኝ እኔም በፈለክ ጊዜ ያልከኝን ነገር አደርጋለሁ…ካለበለዚያ ያው አንተ እንደሌለህ ቆጥሬ ብትኖርም ምንም ማድረግ አቅምና ኃይለ እንደሌለህ ቆጥሬ ለማላውቀው እግዚያብሄር መፀለይ ልጀምር ነው፡፡እርግጥ እኔ እግዜያብሄርን ምንም ጠይቄው አላውቅም.. ከእሱ ጋር እንዴት እንደሚወራም አላውቅም..ግን ደግሞ እመነኝ ለእናቴ ስል እንደምንም ብዬ ላወራው እሞክራለሁ…ደግሞ እኮ እኔ ማናችሁ ጥሩ ማናችሁ መጥፎ ትሁኑ አላውቅም…በእናንተ መኖሪያ እግዚያብሄር አላችሁ እንዴ..?.ምን አይነት ጥያቄ ነው…?መቼስ እግዚያብሄር ምንም እንኳን መጠሪያ ስሙ በየቦታውና በየሀይማኖቱ ቢለያይም የጠቅላላው አፅናፍ አለም ፈጣሪ በመሆኑ በጊዜም ሆነ በቦታ የማይወሰን በመሆኑ በእናነተም ምድር በእርግጠኝነት ይገኛል፡፡እናንተንም የፈጠረው እሱ እራሱ ነው፡ለመጠየቅ የፈለኩት በእግዚያብሄር ታማናላችሁ ወ? ነው፡፡
፦፦፦፦ይቀጥላል፦፦፦፦
#ክፍል 23,,እንዲለቀቀ(10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄

#ክፍል_ሀያ_ሶስት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
እዚህ አብሬያቸው ከምኖረው የሰው ልጆች የበለጠ እውቀትና የረቀቀ ጥበብ የሰጣችሁ እሱ መሆኑን ታማናለችሁ ወይ? .በመካከላችሁ ያለው ግንኙነትስ እንዴት ነው ?ማለቴ በእናንተ እና በእግዚያብሄር መካከል…አንድ ጊዜ ስለአንተ ከእማዬ የሰማሁትን ለአንድ ቄስ ብነግራቸው….እነሱ ከእግዚያብሄር ተጣልተው ወደምድር ተወርውረው የነበሩ የመላእክት ዘሮች ናቸው ብለው አስረዱኝ...ወደምድር መጥተው ከሰው ልጆች ጋር ተስማምተው እንዲኖሩ ቢፈቅድላቸውም.እነሱ ግን መላውን የሰው ልጅ በከሉት ..ሰላማዊውን ፍጡር ጦር መሳሪያ አሰራርና ጎራዴ አሞረረድ ከዛም አልፎ የጦርነት ጥበብ እና የዘረፋና ግድያ ስልቶችን በማስተማር እርስ በርስ አጫረሱት ..በስርዓትና ይኖር የነበረውን ግብረሰዶምና ሊዚቢያ አደረጉት..እግዚያብሄር በጥበብና በፍቅር በመፍጠር በምድር የበተናቸውን እንስሳትን አንዱን ከሌላው እያዳቀሉ አስፈሪና አጥፊ ፍጥረታትና መፍጠር ጀመሩ..የጥንቆላና የሞርት ጥበብን ለሰው ልጅ በማስተማር አእምሮውን በከሉት ከዛ አምላክ ተቆጣና የጥፋት ውሀ ላከ ..ምድርንም በውስጦ ያሉትን ከእነሱ ጋር የተባበሩትን ትምህርታቸውንና በጥባቸው የተደሙትን ሁሉ አጠፋ…የሰው ለጅና እንስሳቱ ለዘር እንዲሆን ጥንድ እየሆነ በኖህ መርከብ ተጠልሎ እንደተረፈ ሁሉ.አነሱም የተወሰኑት የረቀቀ ጥበባቸው በመጠቀም ምድርን ለቀው በመሰደድ በጥፋት ውሀው ሙሉ በሙሉ ከመጥፋት እራሳቸውን ያተረፉ ይመስለኛል ….
እንደምገምተው ከሆነ አሁን አባቴ የምትይውና በሌላ አለም እንደሚኖር ለእናትሽ የነገራት ፍጥረት ከእነሱ አንዱ ነው አሉኝ…..፡፡ከእግዚያብሄር ጋረ የሚያቀያይምሽና ሀይማኖትሽ የሚያስክድሽ ከይሲ ፍጥረት ስለሆነ ቢመጣ እንኳን እንዳትቀርቢው.በስመአብ፤ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በማለት ደጋግመሽ በማማተብ ከስርሽ አባሪው ብለው መከሩኝ ..አልተከራከርኮቸውም ምን አልባት ያሉት እውነት ሊሆን ይችላል ብዬ አሰብኩ፡፡እንኳን ሙለ በመሉ የእናንተ ዘር መሆነን ተችሎ ይቅርና እኔ እራሱ ያንተ ደም በውስጤ ስላለ በውስጤ የሚንቀለቀለው የክፋት ኃይልና የወሲብ ጥማት እኔ ነኝ የማውቀው፡፡ከቄሱ ጋር ያልተስማማሁበት አንድ ነገር ቢኖር ቢመጣ እንዳትቀርቢው ብለው ያሉኝን ነው..ወይ ብትመጣ እንዴት እንደምጠመጠምብህ ሳስበው እራሱ ውስጤ በደስታ ይነዝራል፡፡
ይቀልዳሉ እንዴ? ሴይጣንም ሆንክ እግዚያሄር አባቴ ነህ…መርጬ አይደለም ካንተ የተፈጠርኩት..
እና ለማለት የፈለኩት እውነትም ቄሱ ያሉኝ ነገር የእውነት ከሆነ በመጀመሪያ በእናንተና በእግዚያሄር መካከል የነበረውንም አለመጋባባት ምክንያትም የሚያስረዳኝ አካል አላገኘሁም…ስለዚህ ማን ጥፋተኛ ማን ትክክል እንደሆነ መወሰን አልችልም…ደግሞ እግዚያብሄር ይሳሳታል እንዴ?አቦ እኔ እንጃ …ለማኛውም እስከአሁን የዘበዘብኩትን ሁሉ እርሳውና ለእናቴ እባክህ ምትችለውን አድርግ…›ሀሳቧን ሳትቋጭ ዝናቡ ዣ ብሎ መርገፈ ጀመረ….በትላልቅ ዕድሜ ጠገብ ዛፎችና በርካታ ቁጥቆጦችና ሰርጎ የሚረግፍ በመሆኑ ዝናቡ ከላይ በሚረግፈው ልክ ሳይሆን በየቅርንጫፎቹ እየተሹለኮለከ በቅጠሎች ላይ የተንኳለለ ነበር እሷ ጋር ሚደርሰው፡፡ እሷ ግን ግድም አልነበራትም…..ቦታም ቀይራ ለመጠለል አልሞከረችም…. ልክ እዛ ደን ውስጥ ዛፎቹ ስር ተተክላ እንደበቀለች ታዳጊ ችግኝ.. በደስታ ቅርንጫፎቾንና መላ አካሏን ወዲህ ወዲያ እያዋወዘች የሚዘንበውን ዝናብ በፍቅር እንደምትመጥ አይነት እሷም ተመሳሳዩን ነበር ያደረገችው..
ከ20 ደቂቃ በኃላ ዝናቡ ቢያባራም እየተንኳለለ ከቅርንጫፎቹ ቅጠሎች የሚንጠባጠበው ውሀ ግን አልተቋረጠም ነበር….ንስሯ እንደአካሄዷ አካባቢውን እየደረማመሰ መጥቶ ከፊት ለፊቷ አረፈ፤በቅርንጫፎቹ ውስጥ እየሾለከ ሲመጣ አካሉ ላይ ካረፉበት የውሀ እንክበብሎች በስተቀር ሲሄድ እንደነበረው ፍፅም ደረቅ አካል ነው ያለው፡፡ያው ይሄ የእሱ ብቻ ሳይሆን የሁሉም ንስሮች ፀጋ ነው፡ዝናብ ሲዘንብ ደመናውን ሰንጥቀው አልፈው ከበላዩ ይሆኑን ወደታች አዘቅዝቀው በትዝብት ያዩታል..ምድርና በውስጧ ያሉት ሌሎች ፍጥረቶች ሁሉ ግን በሰማይ የሚበሩትን ሌሎች እዋፍቶችም ሳይቀሩ ወደዱም አልወዱም ወይ መሸሸጊያ ዋሻ ይፈልጋሉ ወይ ደግሞ በዝናቡ ይቀጠቀጣሉ፡፡
‹‹እሺ የት ሄደህ መጣህ?››
እምሮውን ከፈተላት.የሄደበትን ቦታ ሳይሆን እናቷ የምትድንበትን ዘዴ ነው የነገራት፡፡መጀመሪያው መድሀኒት ጨካኝ ነፍስ ያላቸው…ከ7 ሰዎች በላይ የገደሉ የሶስት ሰዎችን አንገት ቆርጦ እናትትሽ ቤት ውስጥ መቅበር ነው›የሚል መልዕክት በእምሮዋ ፃፈላት፡
‹‹ምን እያልከኝ ነው….እኔ ሰው ልገድል ነው…?ለዛውም አስፈሪና ጭራቅ የሆኑ ሰዎችን?››
‹‹ለዚህ እኮ ነው….የእናትሽን ሞት በፀጋ ተቀበይ የምልሽ››ሲል በእምሮ መለሰላት፡፡
‹‹አንተ ከእናቴ ነጥለህ ብቻዬን ምን ልታደርገኝ አስበሀል….?ሀዘኔ ያስደስትሀል ማለት ነው..?››
እዕምሮውን በነጭ ቀለም ሞላው …እንዲህ የሚያደርገው ሲያዝንና በንግግሯ ወይም በድርጊቷ ሲበሳጭ እንደሆነ ታውቃለች፡››
‹‹ይቅርታ ላስከፋህ ፈልጌ አይደለም….በቃ አደርገዋለሁ…ሶስት ሰው ጭንቅላት አይደል፡፡ለዛውም የሶስት ጨካኝና ገዳይ የሆኑ ሰዎች ጭንቅላት… .አረ አደርገዋለሁ ደግሞ ለእናቴ››ስትል ፎከረች፡፡
‹‹እንደዛ ከሆነ በ15 ቀን ውስጥ ጭንቅላቱ ተገኝቶ መቀበር አለበት….ይሄ ጉዳይ በትክክል ከተፈፀመ እናትሽን ለአንድ አመት በህይወት ያቆያታል፡፡
‹‹ፈክቶና በተስፋ ተሞልቶ የነበረው ፊቷ በአንዴ ጨለመ››
‹‹ምን ማለት ነው…?እኔ ለእናቴ እኮ መቶ አመት ነው የምመኝላት….ከተቻለም ዘላለም እንድትኖር፡››
‹‹መጀመሪያ ይሄንን ማድረግ ነው የምትችይው ..ከዛ ደግሞ ሌላውን ዕድሜ እናትሽ እንድታገኝ ምን ማድረግ እንዳለብሽ እናወራለን›››
‹‹ለምን ያኔ ?አሁን አትነግረኝም…ምን ያሰደብቅሀል ?››
‹‹የመጀመሪያው ካልተሳካ ሁለተኛውን ማወቅሽ ምንም እርባን የለውም …..››ብሎ ፍቃዷን ሳይጠብቅ ከአካባቢው ለቆ በረረ…ሆዱ ባዶ ስለሆነ የሚበላ ነገር ለማደን ነው ወደ ደኑ በጥልቀት የገባው….እሷም እንዴት አድርጋ ጨካኝና ወንጀለኛ ሰዎችን ጭንቅላት በ3 ቀን ውስጥ ማግኘት እደምተችል እያሰላሰለች ወደቤቷ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
ንስሯ ግን ተከትሏት አልሄደም..በተቃራኒው ሰማዩን ሰንጥቆ በረረ…
✨ይቀጥላል✨
#ክፍል 24,,እንዲለቀቀ(10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅

#ክፍል_ሀያ_አራት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ለሊት ተኝታ በአልጋዋ በላይ ያለው መስኮት ይቆረቆራል…ባነነችና ማዳመጥ ጀመረች..ደጋግሞ ሲቆረቆር ግራ ገባት..ያለምንም ፍርሀት መስኮቱን በርግዳ ከፈተች… ንስሯ ነው፡፡
‹‹እንዴ ምን እየሰራ…?››ዓረፍተ ነገሩን መጨረስ አልቻለችም…የአንድ ሰው ጭንቅላት በመንቀቁሩ አንጠልጥሎ አልፏት ወደ ውስጥ ገባና ከአልጋው ፊት ለፊት ያለው ወለል ላይ ጥሎላት ተመልሶ በሮ ወጣ….ትኩር ብላ አየችው..የተንጨበረረ ፀጉር ..ተጉረጥርጦ ወደ ውጭ የወጣ አይን… በደም የተበከለ የተጎመደ አንገት….አጥወለወላትና አልጋው ጫፍ ላይ ቁጭ አለች…ምን አይነት ተአምር ነው..?ስትል አሰበች፡፡ ይህንን ነገር እራሷ ልታደርገው ትናንትና ወስና ነበር...አሁን ግን እንዳሰበችው ቀላል ስራ እንዳልነበረ ገባት…እርግጥ አሁንም ገና ሁለት የሚቆረጥ ጭንቅላት ይቀራታል….ግን እንዴት አድርጋ ነው የሰውን አንገት እንዲህ ምትከትፈው? ለነገሩ ከባድ ሆኖ የታየኝ ሰው የመሆን ዲኤን.ኤ በውስጤ ስላለ ሳይሆን አይቀርም…?ግን ነው እንዴ? በዚህ ጉዳይ ሰው ከሌላው ከማንኛውም ፍጡር በላይ ገዳይ አራጅ አይደለምን?የሚል ጥያቄ መጣባት..
ከሀሳቧ ሳትወጣ እግሯ ስር …ዷ ብሎ የወደቀ ነገር ተሰማተና ነቃ ብላ ትኩረቷን ሰበሰበች… ቀኝ እግሯ ስር አንድ ከአንገቱ የተቆረጠ ሰው በግራ እግሯ ደግሞ ሌላ ጭንቅላት ቀደም ብሎ ደግሞ የመጣው ትንሽ ከእሷ ራቅ ብሎ በአጠቃላይ በዛች ትንሸ መኝታ ቤት አንገታቸው የተቆረጠና ጭንቅላቻው ብቻ የቀረ ሶስት ሰዎች ተረፍርፈዋል፡፡ የንስሯ መንቁሩ በደም ተጨማልቆ በኩራትና በልበ ሙሉነት አፍጥጦ እያያት ነው፡፡
‹‹ምንድነው የሰራሀው?››
‹‹ልፋትሽን አቃለልኩልሽ››
‹‹እነዚህን ሁሉ በአንድ ቀን ከየት አገኘሀቸው?››
‹‹ምን ደግሞ ወንጀልና ገዳይ በበዛበት ሀገር ሶስት ሰዎች ማግኘት ይከብዳል?››
‹‹አሁን እነዚህ.. በተለይ እኚ ሁለቱ እንኳን ሰው ዶሮ ለሚስታቸው አርደው ያውቃሉ….እንዴ ይህቺኛዋ ደግሞ ሴት ነች እንዴ?››
‹‹አዎ ሁለት ወንድሞቾን ጨምሮ 10 ሰዎችን በመርዝ ገድላለች፡፡››
‹‹ምን ለማግኘት?››
‹ብር ነዋ ሀብታም ለመሆን…ለውርስ ብላ››
‹‹ይገርማል..››
‹‹አሁን መገረምሽን አቁሚና እነዚህን ሶስት ጭንቅላቶች እናትሽ አልጋ ስር ቅበሪያቸው››
‹እንዴት አድርጌ ?››
‹‹ይህቺማ ቀላል ስራ ነች..ለማንኛውም ይንጋ…አሁን ተመልሰሽ ተኚ.. እኔም እነዚህን ጨካኞች ሳድን ድክም ብሎኛል አላት…
‹‹ውይ እውነትህን ነው የእኔ ጀግና ..ና አለችና በደም የጨቀየውን መንቁሩን ታጥቦና ተጣጥፎ በተቀመጠው ነጭ ፎጣዋ ጠራርጋ አፀዳችለትና ወደአልጋው እንዲሄድ አድርገ መስኮቱን በመዝጋት እሷም ወደአልጋዋ በማምራት ወደ ላይ ወጣች. ብርድልብሱን ለበሰችና ንስሯንም አለበሰችው፡፡ከዛ ወዲያው እንቅልፍ ወሰዳት፡
ጥዋት ሳሎን ቤተሰቦቾ ሲንጫጩ ነው ከእንቅልፏ የባነነችው..ከጎኗ ንስሯ እንደተኛ ነው…በርግጋ ተነሳችና ከአልጋ ላይ ወርዳ ቆመች.. ወለሉ ቅንጣት የደም ጠብታ የሌለው ንፅህ ከመሆኑም በላይ ባዶ ነው….ምንም ጭንቅላት የለም፡፡
ንስሯ ተነስቶ እያያት ነበር..
‹‹ምን ተፈጠረ ጭንቅላቶቹስ ?››
ምንም መልስ ላለመስጠት አእምሮውን ዘጋባት
‹‹መልስልኝ እንጂ››ልክ በባሏ ተግባር እንደተበሳጨች ጮሂ ሚስት አንቧረቀችበት፡፡
ንስሩ ግን ዝም
‹‹ቀበርካቸው እንዴ…?››
አሁንም እምሮውን እደቆለፈ ነው፡
በራ ክፍሏን ለቃ ወጣችና እናቷ ወደተኛችበት ክፍል አመራች፡፡
ባልተረጋጋ ስሜትና በተንቀዠቀዠ አነጋገር‹‹ሀርሜ እንዴት አደርሽ?;››አለች
‹ሰላም ነኝ ልጄ.አንቺ ደህና ነሽ ?ምነው የደነገጥሽ ትመስያለሽ?››
‹‹አይ ደህና ነኝ…ንስሬ እዚህ አንቺ ጋር መጥቶ ነበረ..?››
‹‹የት እዚህ.. አረ አልመጣም››
‹‹ከክፍልሽ ወጥተሸ ነበረ…››
‹‹እንዴ ምን ነክቶሻል? እንዴት ብዬ ወጣለሁ…?››
‹‹አይ ማለቴ እንቅልፍ ወስዶሽ መጥቶ ሄዶ ከሆነ ብዬ ነው…››
‹‹አረ ተረጋጊ ለሊት አንቺ ከዚህ ከሄደሸ ጀምሮ እንቅልፍ በአይኔ አልዞረም እና ንስርሽም እልመጣም…ምን አልባት አደን ሄዶ እንዳይሆን?››
‹‹አይ አልሄደም… እሱማ እኔ ክፍል ነው ያለው››
የልጅቷ ቅብዥርዥር ያለ ወሬ ግራ ስላጋባት ‹‹ልጄ ግን ደህና ነሽ?ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ደህና ነኝ ሀርሜ… ››አለችና በርክ ብላ አንገቷን በመድፋት አልጋ ስር ገባችና ወሉን ማየት ጀመረች …ምንም የተቆፈረ …ምንም የተነካካ ነገር የለም…?››
‹‹መጣው እናቴ…ሰላም ነኝ አታስቢ›› ብላ ወደክፍሏ ተመለሰች..ንስሯ አሁንም አልጋው ላይ ተኮፍሶ እንደተቀመጠ ነው፡፡
እንደገባች ‹‹ለምን ታበሳጨኛለህ ?አለችው የእውነትም ተበሳጭታ፡፡
አእምሮውን ከፈተላትና እንድትረጋጋ ወደእምሮዋ መልዕክት አስተላለፈላት
‹‹ዝም ብዬ እንዴት እረጋጋለሁ…?ምንድነው የሆነው…?ለሊት የሶስት ሰዎች አንገት ቆርጠህ አምጥተህልኝ ነበር..እንደውም መንቁርህ በደም ተነክሮ በምወደው ነጭ ፎጣ ነው የጠራረኩልህ .››አለችና በደም የተበከለውን ፎጣ ስታስታውስ ፎጣው ወደተቀመጠበት ጠረጴዛ ስትሄድ እንደተጣጠፈና ግራ እንደመጋባት ብላ አነሳችና ፈታችው… ምንም የደም ጠብታ የለበትም… ከትናንት ወዲያ አጥባ አጣጥፋ እንዳስቀመጠችው ነው…‹‹.እንዴ ህልም ነበር እንዴ?››ብላ ግራ በመጋባት አልጋው ጠርዝ ላይ ተቀመጠች፡፡
‹‹ይሄ የአንተ እና የአባቴ ስራ ነው አይደል….?በል አሁን ተዘጋጅ የሚገደል ሰው ፍለጋ እንሄዳለን… ምን ያህል ቀን እንደሚፈጅብን አላውቅም››አለችው፡
በንስሩ የአእምሮ ሰሌዳ ላይ አያስፈልግም የሚል መልእክት አነበበች፡፡
‹‹እንዴት የእናቴ ህይወት እኮ ነው…?››
‹‹እኮ በሌለ መንገድ አንድ አመት እንድትታገኝ ማድረግ ተችሏል ..በሶስት ቀን ውስጥ ድና ትነሳለች፡፡››
‹‹እውነትህን ነው?››
‹‹እውነቴን እንደሆነ ታውቂያለሽ›› አላት፡፡
በደስታ አቀፈችውና እየሳመች ወደእናቷ ክፍል ይዛው ሄደች፤እናትዬው ከቅድሙ ሁኔታዋ በተቃራኒ እየሳቀችና እየፈነደቀች ንስሯን አቅፋ ሰታገኛት ተደሰተች‹‹ልጄ ከመቼው ወደ ፈንጠዝያ ገባሽ?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹እማ በጣም ደስ ብሎኛል…ለምን መሰለሽ? አንቺ ስለምትድኚልኝ.››
‹‹አይ ልጄ ..ብዙም ተስፋ አታድርጊ››
✨ይቀጥላል✨
#ክፍል 25,,እንዲለቀቀ(10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅

📕ታአምራተ_ኬድሮን
#ክፍል_ሀያ_አምስት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹ነገርኩሽ እኮ… ዛሬ እሮብ ነው አይደል እስከቅዳሜ አልጋሽን ለቀሽ ያልደረሻቸውን ለቅሶዋችና የታመሙ ወዳጆችሽን እየዞርሽ ትጠይቂያለሽ…››
‹‹እንደአፍሽ ያድርገው››
‹‹እማ እኔ እንዲህ በቁም ነገር ተናግሬ ያልሆነ ነገር አለ…ደግሞ ጀግናዬ ነው መልዕክቱን የነገረኝ…ምን አልባት መድሀኒቱን አባቴ ማለቴ የድሮ ፍቅረኛሽ ይሆናል በሚስጥራዊ መንገድ በእሱ በኩል የላከልሽ››
እናትዬዋ በንግግሯ ባለመደሰት ኮስተር ብላ‹‹አባትሽ የድሮ ፍቅረኛዬ ሳይሆን ….የዘላለም ፍቅረኛዬ ነው።››አለቻት፡፡
"እሺ ይሁንልሽ…አሁን ቻው ያዶት ልንሄድ ነው…ደስ ስላለኝ በዚህ በጥዋት ሂጄ መዋኘት እፈልጋለሁ።››
‹‹እንዴ ቁርስ አፍሽ ላይ ጣል ሳታደርጊ?››
‹‹አይ ስመለስ››ብላ ንስሯን እንዳቀፈች ከቤት ወጣችና ግቢውንም ለቃ ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
‹‹ጀግናዬ ስላደረጋችሁት ነገር በጣም አመስግናለሁ...ማለት አንተና አባቴ….ቃል በገባሁት መሰረት የዘላለም ውለታችሁ አለብኝ...ግን እናቴ ከአመት በኃላ ቀጣይ ዕድሜ እንዲኖራትስ ምንድነው ማድረግ ያለብኝ…? መቼስ ከባድ ነገር ነው የሚጠበቅብኝ?››
‹‹አይ ቀላል ነው››
‹‹ቀላል ነው ስትል?
‹ከእናትሽ ጋር መኖር ማቆምሽ ለእሷ ተጨማሪ ዕድሜ ይሰጣታል፡፡
አንቺ ከተፈጥሮሽ የተነሳ ፍቅርሽ እሷን ለመኖር ያላትን ኃይል ይመጣል….አንቺ ስትወጂም ሆነ ስትጠይ እኩል ነው ሰውን ምትጎጂው….በፍቅርም ሆነ በጥላቻ የተለየ ትኩረት ያሳረፍሽበት ማንኛውንም የሰው ልጅ ኃይሉን ነው ምትመጪበት… ያ ኃይል ደግሞ ከዕድሜው ላይ ይጎመዳል..ምን አልባት እናትሽ አንድ ቀን ከአንቺ ጋር ለማሳለፍ ከእድሜዋ ላይ ሀያ ሰላሳ ቀን መገበር ይጠበቅባት ይሆናል…"
የምትሰማውን ዜና ተቋቁማ ወደፊት መቀጠል አልቻለችም …ከመንገድ ጎራ ብላ ቁጥቋጦ ውስጥ ገባችና የተደላደለ ቦታ ፈልጋ ተቀመጠች… ንስሯን ከፊት ለፊቷ አስቀመጠችው…. ከንፈር የማይንቀሳቀስበት ፤አፍ ማይከፈትበት ድምፅ አልባ ንግግሩን ቀጠለ…‹‹.እና አሁን ከእናቴ አልለይም የሆነው ይሁን የምትይ ከሆነ አንድ አመቱን ከእሷ ጋር አሪፍ የምትይውን የደስታ ጊዜ አሳልፊ…አይ እናቴ አርባ ሀምሳ አመት መኖር አለባት የምትይ ከሆነ ግን ዛሬ ነገ ሳትይ ይሄን ሀገር ለቀን መሄድ አለብን፡፡››
‹‹ግን እናቴን ምን እላታለሁ?››
‹‹እውነቱን ንገሪያት..እርግጥ አትስማማም…ግን ቢሆንም ንገሪያትና አንቺ ውሳኔውን ወስኚ።››
‹‹ቆይ ብዋሻትስ?››
‹‹ምን ብለሽ?››
‹‹ለምሳሌ እኔ አብሬአት መኖር ምቀጥል ከሆነ በሽታው ወደእኔ ተላልፎ በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደምሞት እንዳወቅኩ ብነግራት የእኔን መሞት ማሰብም ስለማትፈልግ በፍጥነት የምትስማማ ይመስለኛል›"
ላቀረበችው ሀሳብ ከአእምሮው የድጋፍ ወይም የተቃውሞ መልስ ለማንበብ ስትጠብቅ….እሱ በተለየ ብርሀን የደመቁ አይነት ቀለማትን ረጨ.እንዲህ የሚያደረገው በነገሮች ሲደነቅ ወይም ሲደሰት እንደሆነ ታውቃለች፡፡
‹‹ምነው የማይረባ ሀሳብ ነው እንዴ?››
‹‹አረ አባትሽም እንዲህ አይነት ሸር በዚህ ፍጥነት ማሰብ መቻሉን ስለተጠራጠርኩ አድንቄሽ ነው..››
‹ዲቃላ መሆን ጥቅሙ እኮ ይሄ ነው…ግን አሁን የት ነው የምንሄደው ..ማለቴ የት ሀገር ብንኖር ይሻላል?፡፡››
‹‹ደስ ያለሽ ቦታ..ደስ ያለሽ ሀገር››
‹‹ምን ሰርተን ነው የምንኖረው…ትምህርቴን ገና የ10 ክፍል ማትሪክ እንኳን አልተፈተንኩ..ከብት ከማርባት እና እትክልቶችን ከመንከባከብ ውጭ ምንም ሌላ ማውቀው ሞያ የለኝም››
‹‹ትቀልጂያለሽ እንዴ አንቺ እኮ ማንኛውንም ሞያ ለመልመድ ከሌላው የሰው ልጅ በመቶ እጥፍ በላይ አቅም ነው ያለሽ....በዛ ላይ ታንዛኒያ የሄድን ጊዜ ኬኒያ ድንበር ያገኘነውን ዳይመንድ አለን....በጣም ሀብታም ነሽ እኮ››
‹‹ማለት አባቴ የሌላ አለም ፍጡር ስለሆነ?››
‹‹አዎ ለሰው ልጆች ጥበብ እና እውቀትን ያስተማሩት እኮ አባትሽ እና ከእሱ ጋር ከገነት የወደቁት ጭምር ናቸው››
‹‹ይሄ ነገር እውነት ነው ማለት ነው?››
"አዎ..በከፊል እውነት ነው››
‹‹በከፊል ስትል.ከፊሉስ እውነት?››
‹እሱን ሌላ ጊዜ..እንድነግርሽ ሲፈቀድልኝ?››
‹‹እንዳልክ …ግን የአባቴ ዘመዶች ለሰው ልጆች ያሰተማሯቸው ዕውቀትንና ጥበብን ብቻ ነው …?››
‹‹አይ እሱማ ክፋትና ተንኮልን…ግድያንና ዘረፋንም ጭምር አስተምረዋል፡፤››
‹‹እና የሰው ልጅ ባለውለታ ናቸው ነው የሚባለው ወይስ ጠላት?››
‹‹አይ እኔ ምለው ማንም ቢሆን ማንኛውንም ጥሩ ነገር ለማግኘት መክፈል ሚገባው ክፍያ አለ…አባትሽና ወገኖቹ ለሰው ልጆች ያበረከቱት ጥሩ ጥሩ ነገሮች እንዳሉ ሁሉ ከሰው ልጆችም የነጠቁት መልካምነቶች አሉ››
‹‹ሳስበው ሳስበው የሰው ልጅ ግን ውለታ ቢስ እኮ ነው፡፡
በየቤተክርስቲያኑም ሆነ መስጊዱ ምሰማው የክፋት ሁሉ ምንጭ ሰይጣን እንደሆነ ጥበብና እውቀትን ደግሞ እግዚያብሄር እንዳስተማራቸው ነው የሚያወሩት››
መልስ ብትጠብቅም ምንም አልመለሰላትም. እዕምሮዋን ዘጋባት
‹‹ምነው? አንተም እግዚያብሄርን ትፈራዋለህ እንዴ?›
አሁንም የተቀየረ ነገር የለም..ለንግግሯ ምንም አይነት አስተያየት ለመስጠት እምሮውን እንደቆለፈ በዛው ገፋበት…ተደነቀች፡፡
‹‹የኃያላን ኃያል ፤ የጌቶች ሁሉ ጌታ እሱ እግዚያብሄር ነው..የሚል ስብከት መስማቷን አስታወሰችና መልሳ በልቧ አኖረችው…
ሄዶ ሄዶ የሁሉ ነገር ማሰሪያና የኃይሎች ሁሉ ጥቅል ኃይል እግዚያብሄር ከሆነ ታዲያ የእነ አባቴ ቀድሞ መንፈራገጥ ለምን ይሆን ?ብላ እራሷን ጠየቀችና ..መልሳ ሌላውን ጥያቄ ተወችና
‹‹ በል ተነስ እንሂድ.. ወደየት ሀገር እንደምንሄድ አስብበት.››ብላ መንገዷን ስትቀጥል እሱ ክንፍን አማቶና በአየር ላይ ተርገፍግፎ እሷን በመተው በተቃራኒው ወደ ደኑ ውስጥ ገባ..‹‹እርቧሀል ማለት ነው ?››ብላ እሷ ለመዋኘት ወደ ያዶት ወንዝ ጉዞዋን ቀጠለች፡፡
✨ይቀጥላል✨
#ክፍል 26,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅

📕ተአምራተ_ኬድሮን
#ክፍል_ሀያ_ስድስት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ከሶስት አመት በኃላ..
እናትዬውን አሳምና ከደሎ ለቃ ስትወጣ አንድ ሻንጣ ልብሷን ይዛ በትራንስፖርት ሳይሆን በንስሯ አማካይነት እየበረረች ነበር የተጓዘችው..በእጇ እናቷ ያስጨበጠቻትን 2000 ሺ ብር እና አጎቷ የሰጣትን 5 ሺ ብር .. በቃ ይሄንን ነው የያዘችው፡፡ግን ሻንጣዋ ውስጥ ከአመታት በፊት ኪኒማጀሮን ለመጓብኘት በሄደች ጊዜ ንስሯ ከባህር ወንበዴዎች ነጥቆ የሰጣት ዳይመንድ እንደቀልድ እንዳስቀመጠችው ስለነበረ ይዛው ነበር.። አዲስ አበባ እንደገቡ በደላላ 45 ሚሊዬን ብር ተሸጠ.
በ25 ሚሊዬን ብር ለገጣፎ ከተማ አካባቢ ምታርፍበት የራሷ የሆነ 2ሺ ካ.ሬ ሜትር ግቢ ላይ ጥጉን ይዞ የታነፀ ባለአምስት ክፍል ቢላ ቤት ገዝታ ከንስሯ ጋር የብቸኝነት ኑሮ መኖር ጀመረች፡፡
እንደመጣች ሰሞን ብቸኝነቱ በጣም ከብዷት ነበር.. የምታውቀው ሰው በዙያዋ ካለመኖሩም በተጨማሪ ከደንና ጫካ ውስጥ ወጥቶ በፎቅና በመኪና የታጠረ አካባቢ መኖር በጣም ሚረብሽ ሆኖባት ነበር…ቆይቶ ግን እየለመደችው መጣች፡የገዛችውንም ጊቢ እንደምትፈልገው አደረገችው….እነሆ አሁን ከሶስት አመት በኃላ ከቤቱ ይልቅ በግቢ ውስጥ ያሉ ዛፎች ዕጻዋቶች እና ፍራፍሬዎች ይበልጥ ያስደምማሉ፡፡ በግቢዋ ውስጥ ከ1140 በላይ የዕፅዋት አይነቶች ይገኛሉ፡፡ከነዚህ ውስጥ 83ቱን ከተለያዩ አህጉራት በዞረችባቸው ወቅት ቀልቧን ስበውት ወይም አስደምመዋት አምጥታ የተከለቻቸው ናቸው፡፡እርግጥ አምጥታ የተከለቻቸው ከዚህ አሁን ከተጠቀሰው ቁጥር በሶስት እጥፍ ከፍ ያለ ነበር..ከአዲስ አበባ የአየር ፀባይ ጋር ተላምደው መጽደቅ የቻሉት ግን እነዚህ ብቻ ናቸው፡፡
ግቢዋ ውስጥ ያሉ ዕጽዋቶች ሁሉ አስደማሚነታቸው ለአይን መስብ ከመሆናቸው እና ንጽህ አየር ሚያመርቱ መንፈሳዊ ማሽኖች ስለሆኑ ብቻ አይደለም እዚህ ግቢ የመትከል ተተክሎም የመብቀል እድል ያገኙት…እያንዳንዱ የተለየ ሚስጥር እና ጥበብ የሚገለጽባቸው የእግዚያብሄርን ሚስጥራዊ ሹክሹክታ በቅጠሎቻቸው እና በስሮቻቸው ነስለሚተነፍሱ ነው…::መድሀኒት ናቸው… ታአምራትን የሚሰራባቸው ናቸው..ብዙ ብዙ ነገር…በየዛፎች ቅርንጫፍች ላይ ቁጥራቸውን የማይታወቅ የወፍ ጎጆዎች ሞልተውባቸዋል፤ሶስት ጉሬዛ እና አራት ዝንጀሮዎችም አሏት ..ሁሉንም ያመጣቻው ከሀገሯ ጫካ ነው… ከደሎ መና፡፡እንደዛ ያደረገችው..ልጅነቷን ስለሚያስታውሷት ነው.እንደዛ ያደረገችው..አብራቸው እነሱን እያየች ከእነሱ እየተጫወተች ስላደገች ዘመዷቾ ስለሚመስሏት ነው… ስለምትወዳቸውና ከእነሱ ውጭ ህይወት ስለማይታያት ነው.. ስለምትወዳቸውና የሚወዷትም ስለሚመስላት ነው፡፡
አብረዋት የሚኖሩ አንድ የስልሳ ሁለት አመት አዛውንት ሰውዬ አሉ፡፡ጋሽ ተክለወልድ ይማም ይባላሉ፡፡ይሄንን ጊቢ እንዲህ ያሳመረችውም የምታስተዳድረውም ከእሳቸው ጋር ነው፡፡
እሷ ያው አብዝታ ከአንድ የምድር ጫፍ ወደሌላው መስፈንጠር የዘወትር ድርጊቷ ስለሆነ በሌለችበት ጊዜ እሳቸው ናቸው ሙሉ ሀላፊነቱን የሚወስዱላት፡፡ ዘበኛ ወይም አትክልተኛ አይደሉም፡፡ከዕጽዋቶች ጋር በፍቅር የወደቁ ከሀለማያ ዩኒቨርሲቲ ለ32 ዓመት ያስተማሩና በቅርቡ ጡረታ የወጡ የዕጽዋት ሳይንስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ናቸው፡፡
ሌላው በዋናነት ለብቸኝነቷ መድሀኒት የሆናት ንስሯ ነው ፡፡ የንስሯ እና የእሷ ግንኙነት ለሌላ ሰው ለማስረዳት ቀላል መንገድ የለም፡፡ እያንዳንዱ የሰው ልጅ እንዲጠብቀው እንዲንከባከበው እና ከክፉ ነገር እንዲከልለው ከፈጣሪው የተመደበለት ጠባቂ መልዐክ አለው ተብሎ በአብዛኛው ሰው ይታመናል፡፡ግን እነዚህ ጠባቂ መላዕክቶች አካል አልባ መንፈስ ናቸው ፡፡አይታዩም፤መታየት ብቻ ሳይሆን አብዛኛው ሰውም ጠባቂ መልአኩን በትከሻው ላይ ተሸክሞ እንደሚዞር አያውቅም… አያምንምም፡፡ስለዚህ አይገለገልባቸውም …አያዳምጣቸውም፡፡ሰው በጨለማ ውስጥ ሲጓዝ ማጅራት መቺ ከኃላው ካለ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ሳይሰማ ትከሻዬን ከበደኝ ይላል፤ያ ምን ማለት ነው? ለሚያምንበት ሰው ጠባቂ መላዕክ የማስጠንቂያ ደውል ነው…. እሱ ያልተመለከተውን በጭለማ ውስጥ የተሸሸገውን አጥቂውን ጠባቂ መልአኩ አይቶት ሹክ ብሎታል ማለት ነው፡፡እንግዲህ ያ ሰው ብልህ ከሆነ ማድረግ ያለበት መልዕክቱን አምኖ ተፈትልኮ በመሮጥ ማምለጥ ወይም ጥቃቱን ለመመከት እራሱን ማዘጋጀት ነው፡፡አይ ዝም ብሎ ተራ ፍራቻ ነው ብሎ የደረሰውን መልዕክት ችላ ብሎ በእንዝላልነቱ ከገፋበት ግን ማጃራቱን ተመቶ ይዘረራልም..ይዘረፋልም ማለት ሊሆን ይችላል፡፡
እና ለእሷ ይሄ ንስር አሞራ ጠባቂ መላዕኳ በሉት፡፡በአካል አብሯት የሚንቀሳቀስ የሚያወራት የምታወራው ጠባቂ መልአክ ስላለት፡፡የፈለገችበት የአለም ጥግ አንጠልጥሎ የሚወስዳት...ከሚንቀለቀል እቶን እሳት ውስጥ ብትገባ እንኳን አንጠልጥሎ በማውጣት ሀይቅ ውስጥ ጨምሮ የሚያቀዘቅዘት፡፡ካለሀሪ በረሀ ላይ ወስዶ በጥም ጉሮሮዋ ከደረቀ ከመንቁሩ ወይን አመንጭቶ የሚያጠጣት…..ከፈለገች የሲ.አይ .ኤን የስለላ መረብ በጣጥሶ የዋይት ሀውስ ራት ግብዝ ላይ አስገብቶ የሚጥላት፡፡ሱፐር ሂዩማን እንድትሆን ሱፐር ሆኖ ሱፐር የሚያደርጋት መልዐኳ ነው፡፡የማታውቀው አባቷ ስጦታ፡ከሀገሯ አብሮት የተሰደ የደስታዋም ሆነ የሀዘኗ ጊዜ ተጋሪዋ፡፡
በንስራ አካል ውስጥ ባለው የነቃና የበቃ ነፍስ እገዛ እሱ ያየውን አንደምታይ እና ያሰበውን እንዳምታስብ ታውቃለች፡፡ልክ በአንድ ዲኮደር እንደሚሰራ ሁለት ቴሌቪዝን በሉን….እሷ ቤቷ ቁጭ ብላ እሱ አየሩን ሰንጥቆ በሚበርበት የምድር ጥግ ሁሉ እያየ ያለውን ነገር ጥርት ባለ ምስል በአዕምሮዋ ታያለች…የንስርን አይን ደግሞ የሚታውቅ ነው..እያንዳንዱ ንስር ቅንጣት በቀላሉ በአይኑ ሌንስ ይቀልባታል፡፡ይሄ ገለጻ ለብዙዎችን ግራ ሊያጋባ ይችላል፡፡
ይሄ መልአክ ነው ሰይጣን የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል፡፡መልአክ ከሆነ ለምን በእርግብ አካል ውስጥ አላደረም ወይንም እንደተለመደው ለምን የበግ ስጋና ቆዳ አለበሰም፡፡እሱን የሚያውቀው ይሄ እንዲሆን ያደረገው የማታውቀውና የሌላ አለም ፍጡር የሆነው አባቷ ነው፡፡ለእሷ ግን ምንም ግድም አይሰጣትም፡፡ዋናው በእርግጠኝነት የምታውቀው ነገር የእሷ እኔነት እና የንስሩ ነፍስ የተሳሰረ መሆኑን ነው፡፡ የኖረውን ያህል ኖራ በሚሞትበት ቀን የምትሞት እንደሆነም ይሰማታል፡፡ወይንም የእሱ ነፍስ ከንስር አካሉ ውስጥ ተንጠፍጥበፎ በሚወጣበት ቅጽበት የእሷም ነፍስ ከዚህ የሰው ሰውነት ወይም አካል ውስጥ ተንጠፍጥፎ በመውጣት ከእሱ ነፍስ ጋር በመተቃቀፍ ወደሚሄድበት ሚስጥራዊ ቦታ አብሮት እንደሚነጉድ ታውቃለች… የመዳረሻቸው ፍጻሜም የአምላክ እቅፍ ይሆን የሉሲፈር ጓዲያ ምንም የምታውቀው ነገር የለም ፡፡
አሁን ባሉበት ቦታ ሁለቱምን ደስተኞች ናቸው ፡፡በዚህች ምድር ሚስጥር እየተደመሙበት ነው፡፡
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 27,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅

❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

#ክፍል_ሀያ_ሰባት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ኬድሮን ከዕንቅልፋ የነቃችው 11 ሰዓት አካበቢ ቢሆንም መኝታ ቤቷን ለቃ ወደ በረንዳው የወጣችው 12 ሰዓት ተኩል ካለፈ በኋላ ነው፡፡ለአንድ ሰዓት ያህል ዘወትር እንደምታደርገው ዮጋ እየሰራች ነበር የቆየችው፡፡እቤቷን ለቃ ስትወጣ ንስሯ ተከትሏት ወጣ፡፡እሷ በረንዳ ላይ ቁጭ ብላ ማንበቧን ጀመረች ፡፡
ከ12 ሰዓት እስከሁለት ሰዓት ያለው ጊዜ ግቤዋ ውስጥ ባሉት ዛፎች ላይ የሰፈሩትን የተለያ አይነት የወፎች ህብረ ዝማሬ እየሰማች ንፁህ በሆነ አዕምሮዋ ተረጋግታ በተመስጦ የምታነብበት ሰዓት ነው፡፡ከሀገሯ ወጥታ ለገጣፎ ከከተመች በኃላ ያዳበረችው አዲስ ልምድ ንባብ ነው፡፡ከመፅሀፍቶች ጋር ያላት ቁርኝት ለእሷም ለራሷ እስኪገርማት ድረስ በጣም የጠነከረ ሆኗል፡፡በአጠቃላይ ሱሰኛ ሆናለች ፡፡
አንድ ሰዓት አካባቢ ከእሷ መኝታ ቤት ጎን ያለው የፕሮፌሰሩ በራፍ ተከፈተ ፡፡ያልጠበቀችው ክስተት ነበር፡፡ምክንያቱም ደግሞ የፕሮፌሰሩ ባህሪ ከእሷ የተለየ ስለሆነ ነው፡፡እሳቸው እሰከ ለሊቱ አስር ሰዓት ድረስ ይቆዩና የተለየ ፕሮግራም ከሌላቸው በስተቀር እስከ ጥዋቱ አራት ሰዓት ድረስ ይተኛሉ፡፡እና ስታነብ የነበረውን መጻሀፏን አጠፍ አድርጋ አይኗን ወደፕሮፌሰሩ በራፍ ላከች፡፡ከክፍሉ የወጡት ፕሮፌሰሩ ሳይሆኑ አንድ የ20 ዓመት አካባቢ ሚሆናት መልከ መልካም ሴት ነች፡፡ፈገግ አለች ፡፡
እኚ ሽማጊሌው ሙሁር ከአልማዝ የጠነከረ ጽናት እና የሚያስገርም ስብዕና ቢኖራቸውም ሴት ላይ ያላቸው አመል ግን የተለየ እና የሚገርም ነው፡፡ካሉበት ዕድሜ ጋር የሚቃረን አይነት ነው፡፡እሳቸው ግን ይሄንን ድክመታቸውን እንደድክመት ተመልክተውት አያውቁም፡፡ ለጤነኝነቴ እና በዚህ ዕድሜዬ ላይ ላለኝ ጥንካሬ ሚስጥሩ ሁለት ነው ፤የመጀመሪያው ከእጽዋት ጋር ያለኝ ፍቅር እና ቁርኝት ሲሆን ሌላው ደግሞ ለወሲብ ያለኝ ፍቅር ነው ብለው በድፍረት ለጠየቃቸው ሁሉ ይመልሳሉ፡፡ ጫን ብለው ለጠየቃቸውም ስለወሲብ ጥሩነት ዘርዘር አድርገው ለማስረዳት ይገደዳሉ‹‹…. የወሲብ ብቃት ቀጥታ ከጤነኝነት ጋር ትስስር አለው፣አንድ የወሲብ ብልቱ አልታዘዝ ያለው ሰው የሆነ የጓደለው ነገር አለው ማለት ነው፡፡ብዙ ጊዜ ትልቅ ቢዝነስ ሚያንቀሳሰቅሱ ባለሀብቶች ወይም ትልቅ ድርጅት ሚያሰተዳድሩ የስራ መሪዎች የወሲብ ስሜታቸው ሚቀሰቀሰው ከእለታቶች በአንድ ቀን ፤ለዛውም በብዙ ድካምና የመድሀኒት እገዛ ነው ፡፡ይህ የሚሆነበት ዋናው ምክንያት በጭንቀት የተበረዘ አዕምሮ እና በስራ የዛለ አካል ስላላቸው ነው ለወሲብ ዝግጁ መሆን የማይችሉት:: አልያም ድባቴ ውስጥ ገብተው በጭንቀት በሽታ እየተሰቃዩ ነው፡፡
ጥናተቶች አንደሚያመለክቱት የአንድ ሰው ብልቱ ሲቆም ያለው ጥንካሬ እና የልብ ጥንካሬ ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው…ተገትሮ የሚሰነጥቅ ብልት ያለው ወንድ ልቡም እንደዛው የተደራረበ ጠንካራና ከብረት የደደረ ነው፡፡ በሳምንት 4 ቀን ወሲብ የሚፈጽም ሰው ከማይፈጽም ሰው በልብ ድካም የመያዝ ዕድሉ 58 ፐርሰንት የበለጠ የተሻለ ነው ፡፡…..››እያሉ መሰል መረጃዎችን በመደርደር ያስረዳሉ፡፡
ስለእሳቸው ማሰቧን ገታ አድርጋ ፊት ለፊቷ ወዳለችው ልጅ ትኩረቷን መለሰች፡፡በዛ ተመሳሳይ ሰዓትም ንስሯ ፡፡ ከተቀመጠችበት ወንበር ትክክል ጣራው ላይ ሰፍሮ ዘና ብሎ ቁልቁል እሷንም ጊቢውንም እየቃኘ እና የጥዋቷን ፀሀይ አብሯት እየሞቀ እና የምትመለከታትን ልጅ እየተመለከተ ነው፡፡
ልጅቷ በራፉን መልሳ ዘጋችና ወደውጨኛው በራፍ ለመሄድ እርምጃ ስትጀምር አዕምሮዋን ሰረሰራት፡፡ቀና ብላ ወደ ንስሯ ስታይ እነዛ ሰርሰሪ አይኖቹን ልጅቷ ላይ ሰክቷል…‹‹ ነገር አለ›› አለችና እሷም ትኩረቷን በመሰብሰብ የሚያየየውን ለማየት ሞከረች…. የልጅቷ ልብ ጭልም ብሎ ነው እየታያት ያለው‹‹‹ ..በሀዘን ኩምትርትር ያለ….ደግሞ ግራ የተጋባ የተመሰቃቀለ ነፍስ ነው ያላቻት ›ስትለ አጉረመረመች.. ..ወጣቷ ቆንጆ ለሚያያት ሁሉ በፈገግታ የደመቀ ፊት ስለሚታየው በጨለማ የተሞላች ነፍስ አላት ተብሎ ቢነገረው ማንም አያምንም ፡፡
‹‹የእኔ እህት ››ብላ ጠራቻት
‹‹አቤት››አለችና ባለችበት ቆማ ፊቷን ወደ እሷ አዞረች…
‹‹ደህና አደርሽ …?››
‹‹ደህና ››አለች ግራ በመጋባት
‹‹ምነው በለሊት…?››
በንግግሯ ግራ ተጋብታ በእጇ የያዘችውን ሞባይል አብርታ አየችና‹‹እንድ ሰዓት እኮ ሆኗል…?››አለቻት፡፡
‹‹ካልቸኮልሽ ቁርስ አብረን እንብላና ትሄጄያለሽ›› …..ይህን ስትላት ልጅቱ እንደማትቸኩል እርግጠኛ ነኝ ….በቃ እንደውም የምትሄድበትም ያላት አይነት እንዳልሆነች ተረድታለች፡፡
እንደማቅማማት አለችና ፊቷን አዙራ ወደእሷ መጣች፤እንደዛ ያደረገችው ዝም ብላ አይደለም ….ውስጧ እንደዛ እንዳታደርግ ስለገፋፋት ነው…. ሁሌ ፕሮፌሰሩ የሚያመጧቸውን ሴቶች ወደ ክፍሏ በማስገባት ቁርስ እያበላች ትሸኛቸዋለች ማለት አይደለም፡፡በዛ ላይ እኮ ገና ቁርስም አልሰራችም፡፡ብቻ ይዛት ገባችና ቁጭ እንድትል ነገረቻት ..ያመለከተቻት ቦታ ቁጭ አለች፡፡
‹‹ይቅርታ ቁርሱ አልተሰራም …ግን በፍጥነት ይደርሳል፡፡››ብላ እስቶቩን ለኮሰች
‹‹አረ ችግር የለም…››
ወደ ፊሪጅ አመራችና ከፍታ አንድ ብርጭቆ የማንጎ ጂውስ ሰጠቻት…… አመስግና ተቀበለቻትና መጠጣት ጀመረች ….እሷም እያወራቻት ቁርሱን መስራት ጀመረች…
‹‹እኔ ሶፊያ እባላለሁ…አንቺስ
…?››ሶፊያ የሚለውን ስም ለገጣፎ ከተመች ቡኃላ ደጋጋማ መጠቀም ጀምራለች፡፡ምንያቱም ከአዲስ ሰው ጋር ሁሉ ስትተዋወቅ ኬድሮን እባላለው ስትል‹‹ ኬድሮን ማለት ምን ማለት ነው?›› ብለው ሲጠየቋት እንዴት ብላ እንደምታስረዳ ግራ እየገባት ስለተቸገረች ነው፡ኬድሮን ማለት በማርስና በመሬት መካከል የሚገኝ ፕላኔት ነው ፤አባቴ የዛ ፕላኔት ኑዋሪ ነው…ትርጉሙ የዕውቀት ምድር ማለት ነው .እሱን ለማስታወስ ስትል እናቴ በፕላኔቷ ስም ስሜን ኬዴርን ብላ ሰየመችኝ ብላ ብታስረዳ‹‹እንዴ ኬድሮን የሚባል ፐላኔት መቼ ነው የተገኘው? ብለው ወደጎግል ይሮጣሉ… ምንም ሚጎለጎል መረጃ ሲያጡ እሷን እንደ እብድ ይመለከታቷል …ይሄ ነገር ሲደጋገምባት ሰለቻትና ለምን ሁለተኛ ስሜን አልጠቀምም አለችና ‹ሶፊያ› የሚል ስሞን አብዝታ መገልገል ጀመረች ፤እና ሁለቱንም ስሞቾን እንደአስፈላጊነቱ እየቀያየረች መጠቀም ጀመረች፡
‹‹አለም››
‹‹እሺ አለም….. አይዞሽ..ነገሮች ይስተካከላሉ››አለቻት፡፡
‹‹ ፍጥጥ ብላ አየቻት፡፡ምክንያቱም ስለታሪኳ ምንም አልነገረቻትም፡፡ እንዴት ልታውቅ ቻለች፤ ብላ ግራ ተጋብታ ነው፡፡››
‹‹አልገባኝም ››አለቻት፡፡
‹‹አይ አሁን ያለሽበት ችግር ይፈታል ማለቴ ነው››
በፍራቻም በጥርጣሬም እያየቻት ‹‹ነገርኩሽ እንዴ…? ››ጠየቀቻት …
‹‹አይ እንዲሁ ሳይሽ ውስጥሽ የተጨነቀ እንደሆነ ስለገባኝ ነው፡፡በጣም አዝነሻል፡፡››
እንባዋን መገደብ አቅቷት ዘረገፈችው፡፡
‹‹አዎ ከባድ ሀዘን ላይ ነኝ ፡፡››
‹‹አይዞሽ..እስኪ ንገሪኝ››
‹‹እንደምታስቢው ሸርሙጣ አይደለሁም…ይሄንን ስራ ከጀመርኩ ሳምንትም አይሆነኝም…››
‹‹አይዞሽ ..ተረጋጊና አጫውቺኝ››
‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››

#ክፍል 28,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
#ክፍል 28,,እንዲለቀቀ (5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
የእስልምና እምነት ተከታዮች ለሆናቹ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን ለ 1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ለማለት እኖዳለን በቻናላችን ስም ።
🙏መልካም በዓል ይሁንላችሁ ❤️
🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን!
SUBSCRIBE NOW! 👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18
🙏መልካም በዓል ይሁንላችሁ ❤️
🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን!
SUBSCRIBE NOW! 👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18
👗ለቤተሰብ የሚሆኑ ውብ እና ማራኪ አልባሳትን አሚ ዲዛይን👕
ታዲያ ምን ይጠብቃሉ?
👉ይምጡ 👉ይጎብኙን👉 ይዘዙን!
የተለያዩ የሀገር ባህል አልባሳት እና ዘመናዊ የባህል ልብሶች ለ እርስዎ እና ለወዳጅዎ ለተለያዩ ዝግጅቶች #ለሰርግ🤵🏻♂️👰🏻♀️💍 #ለበዓላት🎆 #ለልደት🎂 #ለፍቅረኞች❤️ #ለቤተሰብ👨👩👧👦 #ለድርጅቶች 🏭 እንዲሁም ለተለያዩ ፕሮግራሞች እኛ ጋር በጥራት ያገኛሉ።
❇️አድራሻችን 📌
🏢 አዲሰ አበባ ቦሌ አዲሱ ስታዲየም በግ ተራ ፊት ለፊት አንበሳ ባንክ ያለበት ህንፃ አንደኛ ፎቅ B26 ያገኙናል።
ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን
☎️ +251951155076 ይደውሉ
+251903524590
የእርሶን ልብስ በጥራት መስራት የኛ ሀላፊነት ነዉ‼️

#ክፍል_ሀያ_ስምንት
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹በነገራችን ላይ ወደሀገር የገባሁትም የዛሬ ወር አካባቢ ነው፡፡ላለፉት ሶስት አመታት ሳውዲ ነበርኩ…በህገወጥ መልኩ ስለሄድኩ በመሹለክለክ ነበር የኖርኩት… የቀን ጎዶሎ ግን ከሶስት ወር በፊት ከቀጣሪዬ ማዳም ጋር ተጣላሁና አስያዘችኝ››
‹‹በባሏ ጠርጥራሽ ነው አይደል …?››ያው እኔ ሳላስበው ነው ቀደም ቀድም የምለው ….ምክንያቱም እሷ ታሪኳን በቃላት አቀናብራ ለሶፊ ከመናገሯ በፊት እሷ ቀድሞ ይታያታል…ንስሯ የበራፍ በረንዳ ላይ ሶፊ ከለቀቀችበት ወንበር ላይ ተፈናጦ ክፍት በሆነው በራፍ ወደውስጥ አጨንቁሮል ….እርግጥ ልጅቷ ጀርባውና ስለሰጠችው እስከአሁን አላየችውም… እሷ ግን ፊት ለፊት ይታያታል ሁለቱም የልጅቷን ታሪክ ላይ አተኩረዋል …ለዛ ነው ቀደም ቀደም የምትለው….ያ ደግሞ ልጅቷን ግራ እያጋባት ስለሆነ መረጋጋት እንዳለባት ለራሷ እየነገረች ነው፡፡
‹‹አዎ ትክክል ነሽ…ብታይ ጭራቅ ሴት ነች፡፡ቅናቷ አያድረስ ነው፡፡በቃ ሰይጣናዊ የቅናት ዛር ነው የሰፈረባት፡፡ኑሮዬን ሁሉ ሲኦል ነው ያደረገችው፡፡››
‹‹ሙሉውን ሶስት አመት እዛው ነው የኖርሺው…?››
‹‹አዎ ሶስት አመት ሙሉ አንድ ቤት ነበርኩ…እርግጥ መጀመሪያውን አንድ አመት አካባቢ ጥሩ ሴት ነበረች…ሁሉ ነገር መልካም ነበር… ደሞዜን በስርአቱ ትከፍለኛለች..እርግጥ እስከመጨረሻውም ደሞዜን ከልክላኝ ወይም አቋርጣብኝ አታውቅም…ለቤተሰቦቼ የምልከው ተጨማሪ ብር ሁሉ ትሰጠኝ ነበር፡፡ከዛ ድንገት ፀባይዋ ተቀያየረ….ለዓይኖቾ ተጠየፈችኝ….
‹‹ለምን ታዲያ አትለቂም ነበር..?ማለት ሌላ ማዳም ጋር ቀይረሽ መስራት ትቺይ ነበር…››
‹‹ያው እንደነገርኩሽ በህገወጥ መንገድ ነው የሄድኩት.. እንደልቤ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሼ ስራ ማማረጥ አልችልም..ሌላው …››ብላ ዝም አለች ..ላውራ ወይስ ይቅርብኝ እያለች ከራሷ ጋ ሙግት የገጠመች መሆኑን አውቃባታለች…
‹‹ሌላው ምን…?››
‹‹ሰውዬው በጣም መልካም ሰው ነው…ልጆቹንም በጣም ነው የምወዳቸው….ለእነሱ ስል ነው ታግሼያት የኖርኩት››
ፈገግ አለች‹‹መጨረሻ ታዲያ እንዴት ሆነ?››
‹‹ቅናቷ ከቁጥጥር በላይ ሆነብኛ››
‹‹ያው ምታደርጉትን እኮ ስለምታይ ነው››
‹‹ማለት…? እንዴት ታውቃለች……?›.
‹‹እርግጥ የእሷን አለመኖር እየጠበቃችሁ ነው ፍቅራችሁን የምትወጡት… ግን እሷ በደንብ ታውቃለች ..እንደውም ጥሩ ሰው ነች››አለቻት
ልጅቷ ግራ ገባት ..ከድንጋጤዋ የተነሳም ከተቀመጠችበት ተነስታ ቤቱን ሁሉ ለቃ መውጣት ፈልጋለች..…
‹‹አይዞሽ አትደንግጪ …እሷን ለማስቀየም ወይም ለመበደል ብለሽ ሳይሆን ፍቅር ላይ ስለወደቅሽ ነው እንደዛ ያደረግሽው…ያ ደግሞ ከሰውዬው ቀረቤታ እና መልካምነት የተነሳ ነው..በዛ ላይ በጣም ቆንጆ እና ዘናጭ ነው…እንደምትወጂው አውቃለሁ ፡፡እሱም በደንብ ነው የሚያፈቅርሽ፡፡በጣም የከፋው ነገር ግን ቅናተኛ ላልሻት ሴት ደግሞ ሰውዬው ሁለመናዋ ነው…እናንተ እርስ በርስ ከምትዋደዱት በላይ እሷ እሱን ትወደዋለች፡፡እና ሴትዬዋ በተፈጥሮዋ መጥፎ ሆና አንቺን በማሰቃየት የምትረካ ስለሆነች ሳይሆን ባሏን ላለማጣት የምታደረግው መፋለም እና ጥረት ነበር፡፡እንደውም አንቺን ባሰቃየች ቁጥር እሱንም የምታስከፋው እና የምታጣው መስሎ ስለሚሰማት በጣም ትጨናነቅ እና ትጠነቀቅ ነበር…አንቺን ጎድታኛለች ብለሽ ከምታወሪው በላይ እሷ እራሷን አሰቃይታለች ….የጨጋራ በሽተኛ ሆናለች….››
‹‹ቆይ አንቺ ይሄን ሁሉ እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…?››
እሱን ልታስረዳት አልቻለችም ‹‹..ትኩረት ከሰጠው አንዳንድ ነገሮችን ማየት እችላለሁ፡፡
በውስጥሽ ይህቺ ልጅ ጠንቆይ ነች እንዴ…? እያልሽ እያሰብሽ እንደሆነ አውቃለሁ..እንደዛ በይው ችግር የለውም››
‹‹አይ ማለቴ ….ልዋሽሽ አልችልም እንዳልሽው ነበር እያሰብኩ ያለሁት…ይገርማል ያልሻቸውን ብዙውን ነገሮች ትክክል ነሽ››
‹‹ምንድነው ትክክል ያልሆንኩት…?››
‹‹እሷ ስለእኛ ግንኙነት በእርግጠኝነት ማወቋን እና..ከእኔ በላይ እሱን ማፍቀሯን››
‹‹ሁለታችሁ ፍቅር የምትሰሩት አንቺ ክፍል አይደል…?››
‹‹አዎ ግን እሷ ስራ በምትሆንበት እና ከቤት እርቃ በሄደችበት ጌዜ ጠብቀንና ተጠንቅቀን ነው››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ …በሁለታችሁ ያልተለመደ መቀራረብ ጥርጣሬ ካደረባት በኃላ ግን ክፍልሽ ውስጥ በስውር ካሜራ ስላስቀመጠች የተቀዳውን በፈለገችው ጌዜ ከፍታ ታየው ነበር፡፡››
‹‹ያማ አይሆንም..…?እንዴት ተደርጎ…?››
‹‹እንደዛ ነበር የሆነው…ከእኔ በላይ አታፈቅረውም ያልሺው ደግሞ ያው በራስሽ ሚዛን ስለምትመዝኚው ነው እንደዛ የምታስቢው እንጂ እንቺ በእሷ ቦታ ብትሆኚ እርግጠኛ ነኝ ወይ ጥለሺው ትሄጂያለሽ ..ወይ ሌላ እርምጃ ትወስጂያለሽ ….እሷ ግን ካንቺ ጋር ብትጨቃጨቅም ….አንቺን ላይ ችግር ለመፍጠር ብትሞክርም አንድ ቀን እንኳን እሱ ላይ ተነጫንጫበት ወይንም ጉዳዩን አንስታበትና ወቅሳው አታውቅም..ለእሷ እሱ ብቸኛው ፍቅሯ ነው..ለአንቺ ግን የመጀመሪያ ምርጫሽ አይደለም..ስለምታፈቅሪው ብቻ ሳይሆን ማዳሞ ከምታውቀው ሌላ ተጨማሪ ብር ስለሚሰጥሽ ነው ..ፍቅርሽ ብቻ ሳይሆን የገንዘብ ምንጭሽም ስለሆነ ነው…ለእሷ ግን እንደዛ አልነበረም…››
‹‹እሱስ እውነትሽን ነው….የእውነት ካሜራው ኖሮ የምናደርገውን ሁሉ እያየች በትዕግስት አልፋን ከሆነ የሚገርም ነው…እኔ ብሆን ልገድለው ሁሉ እችላለሁ…አረ ሁለቱንም ነው በተቃቀፉበት የማጠፋቸው››
‹‹አየሽ..ሴትየዋ የምታስቢያትን ያህል ክፉ አልነበረችም….ከዚህም በላይ ልታሰቃይሽ ምክንያቱን ሰጥተሻት ነበር…ግን እሷ በተቻላት መጠን እራሷን ለመቆጣጠር ሞክራለች፡፡››
‹‹አዎ አንቺ ይገርማል… አሁን ሳስበው በህይወት ስላለውም እድለኛ ነኝ….››
‹‹እና እዚህ ስትመጪ ደግሞ ሌላ ታሪክ አጋጠመሽ››
‹‹አዎ በጣም የሚያንገበግበው እና ስብርብር ያደረገኝ ደግሞ ይሄኛው ነው›› አለች …..አሁን በፍራቻ እና በአድናቆት ነበር የምትመልስልኝ
የተወሰነ ትንፋሽ ወሰደችና ቀጠለች‹‹መቼስ ታውቂዋለሽ…አንድ ቀን ወደ ሀገሬ ስመለስ ቤት ይኖረኛል….አገባዋለሁ..ልጅ ወልድለታለሁ ብዬ ደሞዜንም .ሰውዬው ይሰጠኝ የነበረውንም ብር እልክለት ነበር…ቤት እየሰራው ነው ይለኛል….የቤት ዕቃ እያሞለው ነው ይለኛል..ምን አለፋሽ ከሶስት መቶ ሺ ብር በላይ ነው የላኩለት …..ግን ስደርስ ሌላ ሴት አግብቶ አንድ ልጅ ወልዶ ጠበቀኝ…..ከዛ ምን ልንገርሽ ሁሉ ነገር አስጠላኝ …ክፍለሀገር ወደ ቤተሰቦቼም መሄድ አልፈለግኩም እንዴት ብዬ ምን ይዤ ሄዳለሁ…?……..
‹‹አዎ ለእሱ ያልሽውን ሶስት መቶ ሺብር ስትልኪለት ለቤተሰቦችሽ የላክሺው ብር ሲደመር 50 ሺ ብርም አይሞላም..››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ..የሚያንገበግበኝ እና ሞራሌን እንክትክት ያደረገው እና ዛሬ እዚህ ያስገኘኝ ይሄው ነው….
አይዞሽ እናስተካክለዋለን ..በእኔ ተማመኚ..አልኳትና የደረሰውን ቁርስ አቅርቤ መብላት ጀመርን›…
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 29,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅

#ክፍል_ሀያ_ዘጠኝ
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ከልጅቷ ጋር ሲያወሩ እና ከቤት ሲወጡ ሶስት ሰዓት ሆነ….‹‹ፍቅረኛሽ አሁን የት ነው የሚኖረው?፡፡››ጠየቀቻት፡፡
‹‹እዚሁ አዲስ አበባ ቤቴል አካባቢ እቤተሰቦቹ ያወረሱት ቤት ውስጥ ነው የሚኖረው፡፡››
‹‹ፎቶው አለሽ?››
‹‹አዎ›› ብላት ሞባይሏን ከፈተችና አሳየቻት፡፡ሞባይሏን ተቀብላ ተመለከተችና ከተቀመጠችበት ተነስታ ‹‹ተከተይኝ ››አለቻት እና ወደበረንዳው ወጡ…ንስሯ ተረጋግቶ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ስታየው እንደመፍራትም ግራ እንደመጋባትም አለችና፡፡
‹‹ምን አይነት አሞራ ነው..አይፈራም እንዴ? ››
‹‹የእኔ ነው››
‹‹አሞራው?››
‹‹አዎ…ግን አሞራ ሳይሆን ንስር ነው…የእኔ ንሰር ፡፡››
‹‹ምን ያደርግልሻል?፡፡››
‹‹እሱማ ለእኔ ብዙ ነገሬ ነው… የፈለኩትን ነገር ያደርግልኛል..እኔ እንደውም የሚገርመኝ እኔ ለእሱ ምን አደርግለታለሁ ሚለውን ነው››
‹‹ይቅርታ ግን ያስፈራል…. .በተለይ አይኖቹ እና መንቁሩ…››እሷን ችላ አለቻትና ሞባይሏ ላይ ያለውን የልጅቷን ፍቅረኛ ፎቶ ለንስሯ እያሳየች ‹‹….እንርዳት መሰለኝ…እወነቱን ማወቅ መብት አላት››ስትለው ክንፎቹን አርገፈገፈና መቀመጫውን ለቆ በአየር ላይ ተንሳፈፈ…እሷ በርግጋ ወደኃላዋ አፈገፈገች….ወደላይ ተምዘግዝጎ አየሩን እየሰነጠቀ ከፍታውን ለአይን መታየት እሰከማይችል ድረስ ርቆ ተሰወረ፡
‹‹ቁጭ በይ› አለቻትና በረንዳው ላይ ካለው ወንበር አንዱን እያሳየቻት እሷ ንስሯ በለቀቀላት ወንበር ላይ እየተቀመጠች፡፡
‹‹ሄደብሽ እኮ …እንዲህ እርቆ ሄዶ አሁን አውቆ ተመልሶ ይመጣል?፡፡››
‹‹አዎ የእኔ እወቀት ዘጠና ፐርሰንቱ ከእሱ የማገኘው ነው…ንስሮች በተፈጥሮቸው በጣም ልዩ የሆኑ የአእዋፋት ዝርያዎች ናቸው፡፡እይታቸውም ጥልቅ አስተሳሰባቸውም ስል እና የተሞረደ ነው፡፡ከዛም በላይ ግን የእኔ ንስር የተለየ ነው፡፡እንዴት የሚለውን ነገር ላብራራልሽ አልችልም..ግን አሁን የሚያደርገውን ታያለሽ ..ከዛ እራስሽ ትፈርጂያለሽ››
‹‹እንዴት?››
‹‹አሁን ፍቅረኛሽን ፎቶ እያሳየሁት ሳወራው አላየሽም?››
‹‹አይቻለው.ግን እናቴም ሲጨንቃት እና በሆዷ ነገር ሲገባ ከምታልባት ላም ጋር ታወራ ነበር…እንደውም ለእሱ ስታወሪ እናቴ ነች ትዝ ያለችኝ፡፡››
‹‹አይ ይሄ ይለያል..አሁን ያንችን ችግር ማለት ስለፍቅረኛሽ ትክክለኛ ነገር እንዲያጣራልኝ ነው የላኩት››
‹‹እንዲት አድርጎ››
‹‹በቃ የተለየ ችሎታ አለው… ማንኛውም ነገር ካተኮረበት የውስጡን ሀሳብ እና ጠቅላላ ታሪኩን ማንበብ ይችላል…እኔ ደግሞ ከሱ አዕምሮ ማንበብ እችላለሁ..ወይም እንዳውቀው አዕምሮውን ይከፍትልኛል..ቅድም ያንቺን ታሪክ ላውቅ የቻልኩት ከእሱ ነው፡፡››
‹‹እኔ አላምንም ..ንስር ይሄን ሁሉ…. እንዴት ተደርጎ?››
‹‹አየሽ እንዳልኩሽ የእኔ ንስር ልዩ ነው..ከእኔ ጋር ያለውም ትስስር ከተፈጥሮ ክስተቶች እንደ አንድ ነው..ያም ሆኖ ግን እንዲሁ ንስር እና የሰው ልጅ ከጥንትም ጀመሮ የመንፈስ ትስስር እንደነበራቸው ታሪክ ይመሰክራል፡፡፡ሌላውን ተይና በሀገራችን ጥንታዊ ስነ ጽሁፍ ውስጥ ንስር የትንሳኤ ምልክት ነበር… በምጥቀት ማሰብ እና ወደ ከፍታ የመስፈንጠር መንፈስ ተምሳሌ ተደርጎ ይወሰድ ነበር፡፡በግብጽ ደግሞ መቃብራቸውን ጋንኤል እንዳይደፍረው የንስር ምስል ከመቃብሩ በራፍ ላይ ያስቀምጡ ነበር…ያ የንስር ምስል የጋንኤሉ መንፈስ አልፎት ወደውስጥ ሊጋባ ስለማይችል እሬሳቸው ከጥቃት የተጠበቀ ይሆናል ብለው ያምናሉ..፡፡
የጲላጦስ ሀገር የሆነችው ግሪክ ደግሞ ከአመልክቶቾ ውስጥ አንድ የሆነው የአማልዕክቶች ሁሉ ንጉስ የሆነው ዜዎስ በንስር ይመሰል እንደነበረ ይነገራል፡፡በጥንት ጊዜ አሜሪካኖች ደግሞ እጅግ ለሚያከብሩት የሌላ ወገን ሰው ያለቸውን ጥልቅ ፍቅር ሚገልጽት የንስር ላባ በመስጠት ነው፡፡በመጽሀፍ ቅዱስ ሲራክም ሶስት እራስ እና አስራ ሁለት ክንፎች ሳላለው ንስር በህልሙ ራዕይ አይቶ ነበር….የራዕይው ፍቺ በየተራ ስለሚነግሱ ነገስታት ሲገለጽለት ነበር…ንስር የኃይልን እና የስልጣን ምልክት ነው፡፡…››ስብከት የመሰለ ንግግሯዋን ተናግራ ሳትጨርስ….ዶክተሩ በራፋቸውን ከፍተው ወጡና ወደእነሱ መጡ
…‹‹.ሶፊ ደህና ነሽ?››
‹‹እንዴት አደሩ ዶክተር?››
‹‹አለሁ….ዛሬ እንግዳ ከየት አገኘሽ ?››አለት እንግዳዋ ላይ በማተኮር፡፡
‹‹አያውቋትም?››
‹‹እኔ እንጃ ከዚህ በፊት ግን ያየኋት ይመስለኛል››
‹‹አዎ ከባሌ የመጣች የአክስቴ ልጅ ነች…ከዚህ በፊትም መጥታ ስለነበረ.. ተገናኝታችኋል››
‹‹ለዛ ነዋ ፊቷ አዲስ ያልሆነብኝ….በሉ ተጫወቱ አንዲት ቀጠሮ አላለችብኝ ..ከሰዓት እንገናኛለን ..›ብለው ተሰናብተዋቸው ወደመኪናቸው ማቆሚያ ጥለዋቸው ሄዱ
ሶፊያ ሳቋ አፍኗት ስለነበር እንደራቁላት ለቀቀችው
…‹‹ሳያውቁኝ ቀርተው ነው ወይስ አውቀው ነው?››
‹‹አይ ተምታቶባቸዋል…ያው ማታ መጠጥም ስለሚወሳስዱ ነው ቅር አይበልሽ››
‹‹አረ ምን ቅር ይለኛል ነገራቸው ገርሞኝ እንጂ››ብትልም ቅር እንዳላት ግን በግልፅ ከንግግሯ ቃና በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
‹‹እዚህ ቤት ከጥዋት ጀምሮ የሚያጋጥምሽ ነገር ሁሉ ይገርማል አይደል?››
‹‹ምን መገረም ብቻ ከአዕምሮም በላይ ነው….እኔ እንዲህ….››ንግግሯን ሳትጨርስ ንስሩ እየተምዘገዘገ መጣና ከእነሱ ፊት ለፊት በአምስት ሜትር ርቀት ያህል በሚገኝ የጽድ ዛፍ ላይ ሲያርፍ ስለተመለከተች አቆረጠችና …ምን እንደሚከሰት ለማወቅ መጎጎቷን በሚያስታውቅባት መንፈስ‹‹መጣ ››አለቻት፡፡
‹‹ትንሽ ታገሺኝ ››አለቻትና አዕምሮዋን ሰብሰባ ትኩረቷን በሙሉ ከንስሯ ጋር በማቋራኘት እምሮውን ማንበብ ጀመረች፡፡
‹‹መምጣትሽን ፍቅረኛሽ አያውቅም አይደል?፡፡››
‹‹አዎ..አንዴ በእሱ ክህደትና ዘረፋ የሞትኩት አንሶኝ ጭራሽ መምጣቴን ነግሬው ስሩ ቆሜ ሁለተኛ ሞት ልሙት እንዴ? አላደርገውም ….ፍቅሬን መልስልኝ ብዬ ልማፀነው..?ወይስ ብሬን መልስልኝ ልበለው?››
በንስሯ አእምሮ አሻግራ እያየች ያለችው ታሪክ አሰገርሟት፡፡‹‹ቆይ ቆይ…በዚህ ሰዓት ፍቅረኛሽ ምን እየሰራ እንደሆነ ታውቂያለሽ…?››ስትል ጠየቀቻት፡፡
‹‹ምን እየሰራ ነው..?.ከሚስቱ እየተዳራ ወይም ልጁን እያጫወተ ይሆናል››ብስጭት እና ቅናት በተቀላቀለበት ድምፀት መለሰችላት፡፡
‹‹አይደለም …ትናንትና ወደ ጊኒጪ ሄዶ እናትሽን አምጥቶ ግሩም ጠቅላላ ሆስፒታል እያሳከማቸው ነው…››
‹‹የእኔን እናት .. ?ምን ሆና ነው…?››በድንጋጤና በመገረም .እናም ደግሞ ባለማመን ጠየቀች፡፡
‹‹አትደንግጪ ያው የተለመደው በሽታዋ ነው….ድሮም ከፍተኛ የጨጎራ ቁስለት እንዳለባት ታውቂያለሽ፡፡››
‹‹አዎ ትክክል ነሽ››
‹‹ግን እኔን እንዲህ አድርጎኝ እንዴት ያሰጠጉታል …እናቴ ምንም የሚያስታምማት እና ሚያሳክማት ሰው ብታጣ እንዴት ልጇን ከከዳ ሰው ጋር ትተባበረለች…?እኔ ይሄን ማመን አልችልም …፡፡ሌላው ይቅር እናቴ እንኳን ለስላሳ እና የዋህ ስለሆነች ይቅር ልትለው ትችላለች… እህቴ ግን እርግጠኛ ነኝ ይቅር አትለውም ፤ እርግጥ ሁሉም ለእሱ የላኩለትን ብር አያውቁም …ግን በጣም እንደማፈቅረውና ላገባውም እንደምፈልግ ከዛም አልፎ ቃል እንደተግባባን ግን በደንብ ያውቃሉ፡፡››
‹‹ትክክል ነሽ…በጣም ነው የሚያፈቅርሽ፡፡››

ቢያፈቅረኝ ነዋ እንዲህ የከዳኝ..?ቢወደኝ ነው እንዲህ እራሴን ለማጥፋት እስክመኝ ደረስ ሙልጬን ያስቀረኝ?ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ? ››
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 30,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
ቢያፈቅረኝ ነዋ እንዲህ የከዳኝ..?ቢወደኝ ነው እንዲህ እራሴን ለማጥፋት እስክመኝ ደረስ ሙልጬን ያስቀረኝ?ፍቅር እንዲህ ነው እንዴ? ››
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 30,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን
#ክፍል_ሰላሳ
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
‹‹ምን መሰለሽ ፍቅር በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ከብረሀናማ ቀለማቶች የተሸመነ ጥልቁ ስሜት ነው፡፡ፍቅር ወደ ወደድነው ሰው ልብ ውስጥ ሰተት ብለን የምንገባበትን በር የምንከፍትበት ማስተር ኪይ ነው፡፡ፍቅር ስለእራሳችን በተለየ መልኩ እንድናስብ የሚያስገድደን የተቀደሰ የዕይታ ብሌናችን ነው፡፡በፍቅር የተነደፈ ደሀ በውስጡ የሚሰማው አለም ሁሉ የእሱ ንብረት እንደሆነችና አውቆና ንቆ እንደተዋት ነው …የተናቀ እና መጠጊያ አልባው ሰው በፍቅር እቅፍ ውስጥ ሲወድቅ የንግስና ዙፋኑ የእሱ እንደሆነ እና አለም ጠቅላላ ወደእሱ አጎንብሳ እየሰገደችለት እንደሆነ ነው የሚሰማው፡፡
የስልጣን ማማ ላይ ተቆናጦ ልቡ በትዕቢት ያበጠ በፍቅር አዳልጦት ሲዘረጥጥ ..እንዴ ለካ እኔም ሰው ነኝ…?ለካ ማንበርከክ ብቻ ሳይሆን እንዲህ ለመንበርከክም እገደዳለሁ? ብሎ እንዲያስብ ያደርገዋል፡፡ ….ሰውን ሞት እና መቃብር ብቻ ሳይሆን ፍቅርም ወደ አንድ ተመሳሳይ ስሜት በመጎተት ያቀራርበዋል፡፡…..ግን አሳዛኙ ነገር ይሄ ቅዱሱ ፍቅር ብዙ ጊዜ ድምጥማጡ የሚጠፋው በማይረባ ትርኪ ሚርኪ እውነትነታቸው ባልተረጋገጡ ጉዳዬች ነው…..ባለመደማመጥ እና ባልተጣራ ወሬ የተነሳ ነው፡፡
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹አልገባኝም፡፡››
‹‹ፍቅረኛሽ እንዳገባ ማን ነው የነገረሽ……..? ››
‹‹ከእስር ቤት ወጥቼ ተጠርዥ ልመጣ ስል አንድ እዛ የምትኖር ጓደኛዬ ከአሰሪዎቼ ቤት የነበረኝን ሻንጣዬን አውጥታ እሷ ጋር አድርጋልኝ ስለነበር…ስትሸኝ አቀብላኝ ነበር ፡፡ይቺ ጓደኛዬ ..በጣም ጥሩ ሰው ነች ለኪስ የሚሆነኝን ትንሽ ብር የሰጠችኝም እሷ ነበረች.. ወደ ኢትዬጵያ የገባሁትም በለሊት ስለነበረ ሆቴል ነበር የያዝኩት እና በሰላም መግባቴን ለመናገር ለጓደኛዬ ስልክ ደወልኩላት፡፡ ፖስታ ከኢትዬጵያ መቶልኝ እንደነበረ እና ሻንጣ ኪስ ውስጥ ከታልኝ ሳትነገርኝ እንደረሳችው ነገረችኝ፤ስፈልገው አገኘሁት፡፡
‹‹ስልክ ባልደውልላት እና እሷም አስታውሳ ባትነግረኝ ኖሮ አላየውም ነበር…ቀጥታ ፍቅረኛዬ ቤት ሄጄ ስርፕራይዝ ላደርገው ነበር እቅዴ..እሱ ጋር አንድ ሶስት ቀን አሳልፌ እና አገግሜ ወደጊንጪ ቤተሰቦቼ ጋር ልሄድ ነበር ያሰብኩት..››
ፖስታውን ስከፍተው ግን በቃ የሲኦልን በር እንደመክፍት ቁጠሪው፣…ውስጡ ሲኦላዊ የክህደት እሳት ነበር ያለው..አገባዋለሁ ብዬ ሳልመው የነበረው ሰውዬ የአንድ አመት ህጻን አቅፎ ሲያባብል የተነሳው ፎቶ ነው፡፡ከመከራዬ አገግምበታላሁ ከስባራቴ እጠገንበታላሁ ያልኩት ሰው ጭራሽ መከራዬን የሚጨምር.ስብራቴን የሚያባብስ ሆኖ ጠበቀኝ…..ከፎቶ ጀርባ ላይ….. ናሆም ፍቃዱ እንኳንም ለአንደኛ አመት ልደት አደረሰህ ይላል፡፡ምድር ተሰንጥቃ ብትውጠኝ እወድ ነበር….ምን አይነት ክህደት ነው…?አላስቻለኝም እወነቱን ለማወቅ ጭለማን ተገን አድርጌ ሰፈሩ ሄድኩ….አድፍጬ በአጥር ቀዳዳ አጨንቁሬ ግቢውን ለሰዓታት ቃኘሁ…እውነት ነበረ ፤ልጅ አቅፎ ግቢ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያባብል እና ሲያጫውት አየሁት…በወለብታ ነው እንጂ ሚስቱንም በመጠኑ አይቼያታለሁ››
‹‹ማንነቷን ግን አላየሽም? ››
‹‹ማንነቷ ምን ይሰራልኛል…ሮማንንም አገባ ቦንቱን ለእኔ ምንስ ሲጨምርልኝ ምንስ ሲቀንስልኝ?››
‹‹አይ ማንነቷን እስክታውቂ በደንብ ብታጣሪ..ወይንም እሱን በአካል አግኝተሸ ለምን እንደዛ አደረግክ? ብለሽ ብትጠይቂው ጥሩ ነበረ ….ሁለት ሳምንት ሙሉ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነሽ አትሰቃይም ነበር..በማትፈልጊውን የህይወት መስመር አትጀምሪም ነበር.ብዙ ጊዜ አውነትን ለማደን ብለን እንደ ጀግና መንግድ እንጀምርና ገና የጫካው መግቢያ ጋር ስንደርስ ብርክ ይዞን እንመለሳለን፤ ቀስታችንን እዛው ጨርሰን ወደኃላ እንመለሳለን.ኩልል እና ጥርት ያለውን እውነት ለማግኘት ግን የጫካው እንብርት ድረስ በእሾኩ እየተወጉ እና በፍርሀት እየራዱ መጓዝን ይጠይቃል ››
‹‹አልገባኝም››አለቻት ኮስተር ብላ
‹‹ንብረትሽ..ማለት አንቺ ለፍቅረኛሽ የላክሽው ብር በእጥፍ ጨምሮ አንቺኑ እየጠበቀሽ ነው››
‹‹እንዴት?››
‹‹በላክሽው 300 ሺ ብር ላይ የራሱን ብር ጨምሮ ሚኒባስ ገዝቶበታል››
‹‹እኮ እሱንማ ግቢው ውስጥ ቆማ አይቼያለሁ፡ግን አሁን ንብረትሽ ነው ብሎ የሚመልስልኝ ይመስልሻል…?ልመልስልሽስ ቢል ሚስቱ እሺ ትለዋለች..?እኔስ አሱ ፊት ቆሜ ብሬን ስጠኝ አትስጠየኝ ብዬ የመከራከሩ ጉልበት ይኖረኛል?፡፡›
‹‹ሚኒባሶ በቀን የምትሰራው ብር ያንቺ ድርሻ በስምሽ በተከፈተ የባንክ ደብተር እያስቀመጠልሽ ነው…በጥሬ ብር ደረጃ መቶ ሳላሳ ሺብር ባንክ ተቀምጦልሻል…..ሚኒባሶም ባንቺ ስም ነች፡፡››
‹‹እንዴት ተደርጎ?››
‹‹በቃ በጣም የሚያፈቅርሽ እና ላንቺም ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቦችሽም የሚኖር እና የሚጨነቅ መልካም ልጅ ነው››
‹‹አይ ያደረገው ነገር እወነት እንዳልሺው ከሆነ ዘራፊ አያሰኘው ይሆናል.. ነገር ግን ፍቅሬን ትቶ ሌላ አግብቶ ሌላ ልጅ መውለዱ ግን ከከዳተኛነት ውጭ ሌላ ስያሜ ሊሰጠው አይችልም ፡፡
‹‹አሁን ቀጥ ብለሽ ዛሬውኑ እቤቱ ሂጂ››
‹‹ምን ልፈጥር?››
‹‹ሂጂ አልኩሽ ሂጂ.››
‹‹ሄጄስ?››
‹‹በቃ ግቢውን አንኳኩተሸ ግቢ..ከዛ የሚሆነው ነገር ይሆናል…ይሄንን ካላደረግሽ ግን ህይወትሽን ሙሉ ምትፀፀችበትን ስህተት ነው የምትሰሪው››በብዙ ምክር እና ከማስፈራሪያ በኃላ አሳምናት ሸኘቻት….
….ከዚህ በላይ ልትነግራት አልፈለገችም..እራሷ በሂደቱ ውስጥ እንድታጣጥመው ነው የፈለገችው..ፍቅረኛዋ አሁንም አልወለደም ፤አላገባምም…እሱ በምንም አይነት እሷን አልከዳትም…ለአንድ ቀን እንኳን ወስልቶባት አያውቅም..እንደውም ከዳተኛ መባል ካለበት እራሷ ነች….፡፡
እርግጥ እንዳለችው እቤቱ ውስጥ ሴት አለች…አዎ እቤት ውስጥ ልጅም አለ..የሚወደድ ናሆም የሚባል የአንድ አመት ልጅ…ሴትዬዋ ግን የገዛ እህቷ ነች….ታናሽ እህቷ ..ልጅም የእህቷ ልጅ፡፡ጊንጪ እቤተሰቦቾ ቤት ተቀምጣ የአስራሁለተኛ ክፍል ትምህርቷን በመማር ላይ እያለች አረገዘች….እሱ ሚስጥሩን ሰማ ፤ልጅቷም ህይወቷን እንዳታበላሽ ቤተሰቦቾም በኖሩበት ሀገር እንዳይሸማቀቁ ሁሉንም አሳመናቸውና ዞር አድርጎ አዲስአበባ ወደራሱ ቤት ወሰዳት….ለፍቅሩ ሲል…የእሷ ቤተሰቦች እንዳይሳቀቁ በማሰብ….. ..እሱ ጋር ተሸሽጋ ወለደች..አሁን ትምህርቷንም እየተማረች ነው፡፡››
ታዲያ ፎቶውን ማነው የላከላት..?ማን ነው እንደዛ እንድታስብ የፈለገው›…?መልሱ የገዛ እህቷ ነች፡፡በእዛች ጭንቅ ጊዜዋ ያፈቀረችውና ያረገዘችለት ሰው አፍንጫሽን ላሺ ባላት ወቅት የእህቷ ፍቅረኛ ግን እንደዛ አይዞሽ ማለቱ፤ ሽሽጎ ተንከባክቦ ጭለማውን ጊዜ እንድታልፍ ማድረጉን ..እሷን መንከባከቡ ልጇን መውደዱ ሌላ ነገር እንድታስብ አደረጋት.. የሰው ሀገር በስደት ላይ ባለችው ታላቅ እህቷ እንድትቀና ..እንድታፈቅረው…የራሴ በሆነ ብላ እንድትመኝ …

ስለዚህ እህቷ ተስፋ እንድትቆርጥ ተመልሳ እንዳትመጣና እሱም ጥበቃ ሲሰለቸው ስሩ ያለችውን እሷን እንዲያይ እና የራሱ እንዲያዳረጋት ተመኘች…የመጣላት ዘዴ ፎቶውን እንዲደርሳት ማድረግ ስለነበር ላከችላት..እንጂማ እሱ አሁንም ህልሙ እሷ ነች..አሁንም ረሀቡ እሷ ነች….እሷ እሱን ከምትፈልገው በብዙ እጥፍ በበለጠ ሁኔታ እሱ ያፈልጋታል፡፡እሷ ከምታፈቅረው በእጥፍ እሱ ያፈቅራታል….አሁን ሄዳ ስታገኘውና ስለሁኔታው በግልጽ ስትረዳ ይቅርታ ትጠይቀውና እቅፉ ውስጥ ትገባለች ..ነገሮችም
ይስተካከሉላታል….የተሰባበረውም ልቧ ይጠገናል…..ግን አንድ ፈታና አለባት ፤ እህቷን ከህይወታቸው መሀል ዞር ማድረግ ቀላል ስራ አይሆንላትም.. ቢሆንም ግን ትወጣዋለች፡፡አዎ ኬድሮን በንስሯ አማካይነት የተረዳችው ይሄንን ነው።
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 31,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
ይስተካከሉላታል….የተሰባበረውም ልቧ ይጠገናል…..ግን አንድ ፈታና አለባት ፤ እህቷን ከህይወታቸው መሀል ዞር ማድረግ ቀላል ስራ አይሆንላትም.. ቢሆንም ግን ትወጣዋለች፡፡አዎ ኬድሮን በንስሯ አማካይነት የተረዳችው ይሄንን ነው።
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 31,,እንዲለቀቀ (10) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅
https://youtube.com/@Weygud18
#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰቦች ተባበሩ #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18
❤መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
👇👇👇
@Mtshaf_bicha
@Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩 @Eyos18 አድርሱን
📗📒📕📗📒📕
Join&share
@EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽»🎶••✿••🎶»✽┉┉┄
📕ተአምራተ_ኬድሮን
#ክፍል_ሰላሳ_አንድ
#ተከታታይ ልቦለድ
#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ
ኬድሮን ከምሽቱ 11 ሰዓት አካባቢ ሲሆን ደባበራት እና ከቤቷ ወጣች… ቦሌ አካባቢ ወደሚገኝ ሰሞኑን ወደተከፈተ አንድ ሆቴል ነው እየሄደች ያለችው ..መኪናዋን ሆቴሉ ግቢ ውስጥ በማስገባት ምቹ ቦታ ፈልጋ አቆመችና የለበስችውን ልብስ እዛው ከመኪናዋ ሳትወርድ አወላልቃ የዋና ልብሷን በመልበስ ወደ ዋና ጋንዳው አመራች ..ሰውነቷን ጭፍግግ ስላለት ዘና ማለት ነው የፈለገችው….በዋና ሰውነቷን ማፍታታት……
የዋና ገንዳው አካባቢ እንደደረሰች ዘላ ውሀ ውስጥ ገብታ መንቦጫረቅ አልፈለገችም…የመዋኛ ገንዳውን ዙሪያ ከበው ወደ ተዘረጉ ዘመናዊ ወንበሮች ሄደችና ..ባዳውን ከሆነ አንድ ወንበር ላይ ዘና ብላ በመቀመጥ የሚዋኙትን ታዳሚዎች እያየችና እየታዘበች መዝናናቷን ቀጠለች…..
…..አበሻም ፈረንጆችም…. ሴቶችም ወንዶችም… ህፃናትም፤ ወጣትና አሮጊቶችም በስብጥር ሲዋኙ እና ሲንቦጫረቁ ይታያሉ….
ስሜቷ አንቀልቅሎ ወደ እዚህ ስፍራ ያመጣት ለምን እንደሆነ እስከአሁን አልተገለፀላትም .. …?….. ድንገት ግን ሳታስብ አንድ ወጣት ዕድሜው በግምት በ25 30 ዓመት መካከል የሚገኝ ወንድ ላይ አይኗ አረፈ…ያምራል… በጣም ነው የሚያምረው..፡፡ ከደረቱ በላይ ያለው የሰውነት ቅርጽ ውጥርጥር ያለ እና ሚማርክ ነው…ፀጉሩ በውሀው አቅም ተሸንፎ በሚመስል ሁኔታ ዝልፍልፍ ብሎ ግንባሩ ላይ ተዘናፍሏል፡፡አይኖቹ ከጨረቃ የተዋሳቸው ይመስላሉ…ኪሊማንጀሮ ተራራ ጫፍ ላይ ያገኘችውን አንድሪውን አስታወሳት፡፡.
እሷ ደግሞ ካለ ችግሯ ወይም ድክመት ሊባልም ይችላል ስድስት ወር ወይም አመት ምንም ወንድ ሳያምራት ወይም ከምንም አይነት ወንድ ጋር ሳትነካካ ትቆይና ድንገት በሰከንድ ውስጥ በእይታዋ ውስጥ የሆነ ወንድ ገብቶ ቀልቧን ከሰረቀት በቃ..ስግብግብ ነው የምትለው..፡፡በዛኑ ቀን ወይም ከተቻለም በዛኑ ደቂቃ ማግኘትና አምሮቷን መወጣት አለባት….(ያው የእሷ ፍቅር ከአንድ ጊዜ የወሲብ ፍላጎት አያልፍም ..ከዛ በላይ ፈልጋ አታውቅም ..ለእሷ በፍቅር መነሁለል እና . ወንድን እየተከተሉ መዞር ወይም ወንድ አፈቀርኩሽ እያለ ለሀጩን እያዝረበረበ በዙሪያዋ እንዲሽከረከርባት በፍፅም አትፈቅድም….)
.የእሷ ችግር ጊዜያዊ ነው ..ጊዜያዊም ብቻ ሳይሆን ቅፅበታዊም ጭምር ነው….በፈለገች ጊዜ ማግኘት አለባት… .ካለበለዛ እራሷን ሁሉ መቆጣጠር ስለሚያቅታት ጥፋት ታጠፋለች....የማይሰራ ስራ ትሰራለች…የወሲብ ጠኔም በቀላሉ አዙሮ እና አጥወልውሎ ሊደፋት ሁሉ ይችላል….እና አሁንም ይሄ ሻንቂላ ወንዳ ወንድ ወጣት እፊቷ ያለው ሰማያዊ መዋኛ ገንዳ ውስጥ ጥበባዊ በሆነ ስልት እንደ ዓሳ ነባሪ ብቅ ጥልቅ በማለት እየዋኘ ቀልቧን ስልብልብ አድርጎታል..
‹‹ተይ ይቅርብሽ››እራሷን ለመገሰፅ ሞከረች…እራሷን መገደብ እንደማይሳካላት ግን ከልምድ ታውቃለች… …..ከለበሰችው የዋና ልብስ ስር እግሯ እና እግሯ መካከል ያሳክከት ጀመረ.. እጣቷን ወደ ጭኗ መካከል በመስደድ የሚበላትን አካባቢ አከክ…አከ…ክ አድርጋ ተንፈስ ለማለት አሰበችና ዙሪያዋን በሰዎች መከበቧን ሳታስተውል መልሳ ተወችው....ከተቀመጠችበት መቀመጫ ተነሳችና ወደዋናው ገንዳ ቀረበች…ምን ማድረግ እንዳለባት እያሰበች ነው…ድንገት በትይዩ አቅጣጫ በሰማዩ ላይ በሶስት መቶ ሜትር ርቀት …. ንስራ ሲያንጃብብ ተመለከተችና
‹‹…ወይ ከመቼው ተከትሎኝ መጣ….ግን እንኳን መጣህ.››ስትል በውስጧ አጉረመረመች…. እሱን በአቅራቢያዋ በማየቷ ደስ አላት..አዎ ይሄ ቀልቧ ያረፈበትን ወጣት ከተቻለ አሁን ለመክሰስ..ካልሆነም ለእራት ለማድረስ የእሱ እርዳታ ያስፈልጋታል….ስለደካማ ጎኑ በእነዛ ሰርሳሪ አይኖቹ በማየት ካልነገረራትና በምን ሁኔታ ብትቀርበው የሀሳቧ ሊሳካ እንደሚችል መረጃውን ካላቀበላት ባሰበችው ፍጥነት ሊሰካላት አይችልም ፡፡
ደስታዋ ግን ሀሳቡን አስባ ሳትጨርስ ነው ከውስጧ በኖ የጠፋው….የንስሯን እርዳታ መጠቀም አትችልም…ምክንያቱም ይሄ ሰው ምን አልባት የማይሆን ታሪክ ካለው..ወይም አደጋኛ ሰው ከሆነ ንስሯ የሆነ ተአምር ፈጥሮ ከእሱ ጋር በምንም አይነት ተአምር እንዳትገናኝ ያደርጋታል..በምኞቷ መካከል ጣልቃ ይገባና ያጨናግፍባታል…ያ እንዲሆን ደግሞ አትፈልግም...ስለዚህ እዚህ ታሪክ ውስጥ ንስሯን አታሳትፈውም፡፡እንደዛ ወሰነች፡፡
..እንዳዛ ከሆነ ደግሞ እየበላት ያለውን በገዛ ጣቶቾ ስታክ ማደራ ነው…ፈርዶባት ደግሞ በአንዱ የተቀሰቀውን ስሜቷ በሌላ ወንድ አካክሳ ልታበርደው አትችልም…ይሄ የእሷ የሆነ ልዩ ባህሪ ነው……
ስለዚህ ይሄን ጉዳይ በራሷ መወጣት አለባት….."ንስሯን ምንም እርዳታ አልጠይቀውም….እሱ በሚዋኝበት አካባቢ እስትራቴጂካል ቦታ መርጣ ገንዳው ዳር ተቀመጠችና እግራን ብቻ ውሀ ውስጥ በማስገባት ልክ መዋኘት እንደሚፈልግ … ግን ዋና ስለማይችል መግባቱን እንደፈራ ሰው በመምሰል ማንቦጫረቅ እና በእጇ እየጨለፈች በውሀው መጫወት ጀመረች….
አዎ ልጁ እየዋኘ ወደስሯ ተጠጋ…ተመልሶ ሄደ ..ሶስት አራቴ በሰሯ ተመላለሰ…በአምስተኛው በአጠገቧ ሲያልፍና በጣም ሲጠጋት…
‹‹ታድለህ ››አለችው
‹‹ምን አልሺኝ…?››
‹‹ እንደ ዓሳ ነው የምትዋኘው…ታስቀናለህ…!!! ››
‹‹አመሰግናለሁ…››ብሏት ዋናውን ሊቀጥል ካለ በኃላ መልሶ ወደ እሷ በመዞር..‹‹ለምን አትገቢም…? ››ሲል ጠየቀት
‹‹መግባት እፈልጋለሁ ..ግን ዋና አልችልም፤ ብሰምጥስ…?››
‹‹አይዞሽ እኔ እጠብቅሻለው ግቢ››
‹‹ኸረ ተው ይቅርብኝ››ተግደረደረች
‹‹ግቢ. በእኔ ተማመኚ››
የምትፈልገው ሀሳብ ስለሆነ ቀሰ ብላ ገባችና ልክ እንደጀማሪ ዋናተኛ ተንደፋደፈች..በቅርቧ ስለነበረ ቶሎ ብሎ ከስር ገባና ሰቅስቆ በክንዶቹ
መሀል አድርጎ ወደ ላይ አወጣት …
✨ይቀጥላል✨,,,,,,,,,✍
#ክፍል 32,,እንዲለቀቀ (15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል✅