ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
236K subscribers
289 photos
1 video
16 files
232 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
የክረምት ትዝታ ላለባችሁ

ልጅነት ክፉ ነው...በቃ ትዝታው ከባድ ነው።የሆነ የማይላቀቅ ሰቀቀን ነው።ይሄው ዝናብ ጠብ ባለ ቁጥር ትዝታ ፈረሱን ጭኖ እንደምን አደርክ አንዴት ከረምክ ይለኛል።እርግጠኛ ነኝ የክረምት ትዝታ የብዙ ሰዎች ህመም ነው። ለዛም ይመስለኛል ጌታቸው ካሳ...

"ቀና ብዬ ባየው ሰማዩ ደፈረሰ
ሆዴም ሳር ቅጠሉን ምድሩን አስታወስ
አገሬ ትዝታሽ ነገሰ"

እያለ ያንጎራጎረው። ክረምት ክረምት እኔ እና ወንድሜ መጽሀፍ ተራ በተራ እናነብ ነበር።እሱ "የታንጉት ምስጢርን" ጥርሱን ነክሶ ሲያነብ እኔ ደግሞ "ብርቅርቅታን" እንባዬን እያንጠብጠብኩ አነባለሁ።ያው ስሜታችን ለየቅል ነው። እኔ ሆደ ቡቡ ነገር ነበርኩ።ለሰው ቶሎ የማዝነው ነገር አለኝ።የውሸት ታሪክ ብሰማም እንክዋን ልቤ ድንግጥ ይልና አፍታም ሳይቆይ የሀዝን ድንኩዋኑን ይጥላል። እሱ ደግሞ አይሞከሬ ነው።አይኑን በሽንኩርት ውሃ ቢያጥቡት እንባ አይወጣውም።እንዳንዴ መጽሀፍ እያነበብኩ ሳለቅስ ሲያየኝ "ነፍሴ ለምን ኡራኤል ጀርባ ሄደህ ከአንዱ መቃብር ላይ እርምህን አታውጣም "ይለኝ ነበር።በነገራችን ላይ ሆደ ቡቡ የመሆኔን ያክል ጸብ ሲመጣም አንደኛ ተዋናይ ነኝ።በልጅነት ወራቴ ሶስት ልጆች ፈንክቻለሁ አንድ የማልረሳው ጫማ ጥፊ አስተናግጃለሁ።ልጁን ጠብቄ እንዳልበቀለው አባቱ የፋዘር ጉዋደኛ ስነበሩ ፋዘር ቁልቁል እንደሚሰቅለኝ ስለማውቅ ቂሜን ይዤ ነው የልጅነት ዘመኔን የጨረሰኩት።ከሰው ጋር መዋደድ፣ ስቆ ተጫውቶ፣ተረዳድቶ መኖር ያስደስተኛል::ፈጽሞ እሰው ላይ አልደርስም ከነኩኝ ግን ዛሬም ቢሆን ምላሼ ከእስራኤል የከፋ ነው::በይቅርታ ምናምን አምናለሁ ነገር ግን ከአጸፋ ምላሽ በሁዋላ ነው ታድያ!

የሆነው ሆኖ ብቻ ክረምት ሲገባ የልጅነት ድራማ በሽ ነው።እንደ ዛሬው ፌስቡክ እና ቲክቶክ ስለሌለ ልክ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ጣራውን ሲነርተው ያኔ መጽሀፌን ይዤ ዘልዬ ብርድልብስ ውስጥ መግባትን ያክል የሚያስደስተኝ ነገር አለነበረም።ሻይ በአናቱ ላይ ባገኝ አልጠላም ነበር ነገር ግን ሰራተኛይቱ "የሻይ በጀት ጠዋት ብቻ ነው ከዛ ውጪ ከነ ኢብራሂም ሱቅ ስኩዋር ገዝታችሁ አምጡ" ትላለች።ኮስታራ ጎንደሬ ነበረች።በጣምም ባለሙያ ነበረች።አንድ ቀን ፋዘር "ዶሮ ወጥ እና ጠላን የፈለሰፈችው የብርጌጥ ነች ብሎ አዳንቆዋት"...ከዛ በሁዋላ አረማመዱዋ ሁሉ ተቀይሮ አቴጌ ምንትዋብን ሆናብን ነበር::ለነገሩ ኮራ ካላለች ምኑን ጎንደሬ ሆነችው!:: እቤት ውስጥ እንደ ስራተኛ ሳይሆን እንደ ቁጡ አክስት ነው የኖረችው። ክብሩዋን አታስነካም:: እኛም ቢሆን ለሰው ልጅ ክብር ያለን አዘናት ሳይሆነ ታዘን የምንኖር በስርአት ያደግን ጨዋዎች ነበርን።የብርጌጥ ሞቅ ሲላት "ቀን ጥሎኝ ነው የናንተን ሽሮ የምቀቅለው እንጂ የኮራሁ የገበሬ ልጅ ነኝ" ትላለች።

ከግቢያችን የምንወጣው አንድም ትምህርት ቤት ወይም ቤተክርስትያን ለመሄድ አለያም ሱቅ ተልከን ነው።ከዛ ውጪ ከግቢ ወጥቶ የተገኘ የጸጋዬ መሸሻ ሃያል ክንዶች ያርፉበታል። አንድ ቀን ፋዘር እግሩ ሲወጣ ጠብቄ ጉዋደኛዬ ቤት ሄጄ ለካስ ፋዘር ሀሳቡን ቀይሮ ከመንገድ ተመልሶ ኖሩዋል እናም ለው ለው እያልኩ ስመለስ በመሰላል ግንጣይ ነበር የተቀበለኝ። እውነት እላችሁዋለሁ ሌባ እራሱ እንደዛ አይደበደብም።ግን ደግሞ የልጅነት ግዜዬን ትምህርታት ላይ ብቻ እንዳተኩር የራሱ አስተዋጽኦ አድርጓል።

ይሄው እንግዲህ ባለሁበት ሆኜ ዝናብ ጠብ ባደረገ እና ክረምት በመጣ ቁጥር የልጅነት ትዝታዬ ፈረሱን እየጫነ ብቅ ይላል።እናማ የእናንተስ ትዝታ እንዴት ነው...ቆስቁሱ እንጂ!

#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
👍በጭፍን ተጓዙ!

አንዳንዴ እያወቁ እንዳላቂ፣ እየሰሙ እንዳልሰሙ፣ እያዩ እንዳላዩ መሆን ግድ ነው። የምናውቀውን ነገር ሁሉ መመርመር ብንጀምር እውቀታችን ገደል እንደሚከተን ግልፅ ነው፤ ስለሰማነውና ስላየነው ነገር ሁሉ ብንመራመር ባለንበት መቅረታችን አይቀርም። ምክንያቱም የምንሔደው በእውን ወዳየነውና በእጃችን ወደዳሰስነው ዓለም ሳይሆን አይተነው ወደማናውቀውና በምናባችን ውስጥ ብቻ ወዳለው የማይታወቅ ዓለም ስለሆነ። የቁስ እውቀት ሲደራረብ የምናባዊው ጉዞ መሰናክል መሆኑ አይቀርም። አንዳንዶች እውቀትን እንደ ጉድ ይተነትኑታል ነገር ግን አይኖሩትም፣ ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የህይወት መንገድ ገብቷቸዋል ነገር ግን በእራሳቸው ህይወት ለመተግበር ሲሞክሩ እጅጉን ይቸገራሉ። ብዙ ማወቃችሁ፣ ያወቃችሁትንም አንድ በአንድ ለመተግበር መሞከራችሁ ቀላል ህይወት ለመኖራችሁ ዋስትና ሊሆናችሁ አይችልም። ምንምእንኳን ምድር ላይ ነፍስ ዘርቶ መመልከት ብትችሉም የምታውቁት ሁሉ እውነት አይደለም፣ ምንምእንኳን የሰማችሁትን በእጃችሁ መጨበጥ ብትችሉም የእውነት በእናንተ ህይወት ጠቃሚና አስፈላጊ ስለመሆኑ በእርግጠኝነት መናገር አትችሉም።

አዎ! በጭፍን ተጓዙ! እንዲሁ እንዳላዋቂ፣ እንዲሁ እንዳልሰማ እንዳላየ በጭፍኑ ወደፊት ተጓዙ፣ የምትፈልጉትንና የሚያስፈልጋችሁን ብቻ ማሳደድ ቀጥሉ። በዙሪያችሁ ብዙ ወሬ አለ፣ በአካባቢያችሁ ብዙ ነገር ይከናወናል፣ ብዙ ታያላች፣ ብዙ ትሰማላችሁ ነገር ግን የማይጠቅማችሁና የማያስፈልጋችሁ ከሆነ ጆሯችሁም አይሰማም፣ አይናችሁም አያይም። በጉዟችሁ ላይ መበርታት ከፈለጋችሁ ለሰዎች ፋራ መስላችሁ መታየት አለባችሁ፣ የእውነት ረጅም ርቀት መጓዝ ካለባችሁ እያንዳንዱን የሚያሰናክላችሁን ነገር ቆርጣችሁ መጣል ይኖርባችኋል። ሞዛዛ መሆንን የመሰለ ያሰባችሁበት ስፍራ የሚያደርሳችሁ ነገር የለም፤ ችክ ማለትን፣ የያዙት ላይ ሙጥኝ ማለትን የመሰለ በየጊዜው ተመራጭ የሚያደርጋችሁ ነገር የለም። በገንዘብም ሆነ በተሻለ ህይወት ዙሪያ ብዙ የሚያዋጡ ስራዎች ይኖራሉ፣ የእናንተ ምርጫ ግን የሚያስቀድመው ገንዘብን ወይም የተሻለ ህይወት ሳይሆን ስሜት ነው። እለት እለት ስሜት የሚሰጣችሁን ነገር ማድረግ ከቻላችሁ የጊዜ ጉዳይ እንጂ ሁሉም ነገር መስተካከሉ አይቀርም። ከውስጥ ወደ ውጭ መኖር የውጩን ዓለም ከመቅፅበት ይቀይረዋል። የውጪውን ጫጫታ ዘግቶ፣ ከአስመሳይነት ርቆ ወደፊት መጓዝ ቀላሉንና የተረጋጋውን ህይወት ያጎናፅፋል።

አዎ! ጀግናዬ..! ስለዓለም አሰራር ብዙ ባወክ ቁጥር ብዙዎቹን ክስተቶቿን ወደጎን እያልክና እየሸሸህ ትመጣለህ። የእራስህን ዝግ ዓለም ትፈጥራለህ፣ የውስጥ ፍላጎትህን እንጂ የውጪውን አሉባልታ አትሰማም፣ ተሻሽሎ አድጎና በቅቶ ብዙዎች ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ ማሳደር የሚችለውን አንተ እንጂ በየሰፈሩ ወሬ እያመላለሰ፣ ለትንሹም ለትልቁም ልቡ እየደነገጠ የሚኖረውን አንተ አትመለከትም። ምርጫ እንደሚኖርህ ትረዳለህ። በምርጫህም ከትናንት እየተማርክ ነገህን እያሰብክ ዛሬ በራስህ መንገድ ትኖራለህ። ከሚነገርህ አስፈሪና አስጊ ነገር የሚበልጥ ከየትኛውም ፈተና በላይ ሊያደርግህ የሚችል አቅሙ እንዳለህ አስተውል። ያለህን አቅምም ከማንም በፊት ለእራስህ አሳየው። ቀላል ባይሆንም እንኳን የምትፈልገውን ህይወት በምትፈልገው መንገድ የመኖር መብቱም አቅሙም እንዳለህ እመን። ያ ህይወት ከፈጣሪህ እንደማያርቅህ እርግጠኛ ሁን፣ እርሱን ለመኖርም ዙሪያህን አጥረህ በየቀኑ ወደፊት ተጓዝ። ተዓምራዊው በምናብህ የፈጠርከው የግል ዓለምህ የማንንም ጣልቃገብነት እንደማይፈልግ ተረዳ።

#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ባቡር ውስጥ ነው

✅️ቀይ ጃኬት የለበሰው ሰው ከአንድ ወረቀት ላይ ከተጻፈ ጽሁፍ ጋር ፊቱን እየቋጠረ እና እየፈታ ይታገላል

"ምን እያነበብክ ነው? ግራ የገባህ ትመስላለህ" ሲል ይጠይቀዋል ባለ ጥቁር ጃኬት ለባሹ

"ልጄ የሂሳብ ትምህርት ወድቋል: ድጋሚ ፈተና ስላለው ቤት ገብቼ ላስጠናው ይገባል:: እኔ ደግሞ እድሜዬ 42 አመት ሲሆን ከትምህርት ቤት ከራቅኩኝ ቆይቻለሁኝ:: ስለዚህ ትንሽ ለማስታወስ እየታገልኩኝ ነው"

ባለ ጥቁር ጃኬት ለባሹ ለረጅም አመታት በሂሳብ መምህርነት ያገለገለ መምህር እንደሆነ ነግሮት እያንዳንዱን ጥያቄ እየበተነ ቀላል በሆነ መልኩ እያስረዳው መንገዱን አጋመሱ

በጉዞው ማብቂያ ላይ ሰውዬው ፊት ላይ የታየው እፎይታ ቀላል አልነበረም: ቤት ገብቶ ልጁን እስኪያስጠናው የቸኮለ ይመስል ነበር

ትናንሽ የሚመስሉ ነገሮች ብዙ ፍቅር አላቸው

👇🏾

ሰው መሆኛ መንገዱ ብዙ ነው!! ❤️
🙌🏼

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Z1D7EM0v-uw?si=IxM67RzoSd50NsoW

https://youtu.be/Z1D7EM0v-uw?si=IxM67RzoSd50NsoW

  መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ኦሊምፒክ

የኦሊምፒክ መሪ ቃል 'ሲተስ፣ አስተስ፣ ፎርቲየስ' ሲሆን ትርጉሙም 'ፍጥነት፣ ከፍታና ጥንካሬ' ማለት ነው።

አምስት ቀለበቶች ያሉበት  የኦሊምፒክ የክብር አርማ አምስቱን አኅጉሮች ይወክላሉ። አምስቱም ቀለበቶች የተለያየ ቀለም ያላቸው ሲሆን እያንዳንዱ የዓለም አገራት ባንዲራ ቢያንስ  ከአምስቱ ቀለማት አንዱን ይይዛል።

የኦሊምፒክ ባንዲራን የፈለሰፉት ፈረንሳዊው ፒየር ደ ኩበርቲን ሲሆኑ ለመጀመሪያ ጊዜ የተውለበለበውም በ1920 በብራስልስ - ቤልጅየም ነበር። ፒየር ደ ኩበርቲን የኦሊምፒክ  ቃለ መሃላን እና የኦሊምፒክ መሪ ቃልን ጭምር የፈጠሩ ታላቅ ሰው ናቸው።

በእያንዳንዱ የኦሊምፒክ ትዕይንት ላይ ከአዘጋጅ አገር የተመረጠ አንድ አትሌት የኦሊምፒክ ሰላማዊነትን ለመግለጽ በመላው ተወዳዳሪዎች ስም ቃለ መሀላ እንዲፈፅም ይደረጋል።

የጥንቱ ኦሊምፒክ በግሪክ መዲናዎች ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ776 ዓ.ዓ. ተጀምሮ እስከ 383 ዓ.ም. ድረስ ከተካሄደ በኋላ የአረመኔዎች በዓል ነው ተብሎ ለዘመናት ታግዶ ነበር። እንደገና በዘመናዊ መልክ የተጀመረው በ1896 ዓ.ም. ነበር።

የጥንት አትሌቶች በኦሊምፒክ ትዕይንት ላይ የሚሳተፉት ራቁታቸውን ነበር። በግሪክ ቋንቋ ራቁትን ለመግለፅ የሚጠቀሙት ቃል 'ጂሚኖስ' ነበር። ጂምናዚየም የሚለው ቃል የተገኘውም ከዚሁ ነው።


🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Z1D7EM0v-uw?si=IxM67RzoSd50NsoW

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
አፍቃሪህ አይደለም!

ትኩረት የሰጠን፣ ያሰበልን፣ ጆሮ ሰጥቶ ያዳመጠን፣ የምንፈልገውን ያደረገልን፣ የተንከባከበን፣ ጊዜ የሰጠንና የተጨነቀልን ሰው ሁሉ አፍቃሪያችን አይደለም። በተቃራኒውም የሚገፋን፣ ለስሜታችን የማይጠነቀቅ፣ የማያዳምጠን፣ የፈለግነውን የማያደርግልን፣ የማይንከባከበንና ትኩረት የማይሰጠን ሁሉ ጠላታችን አይደለም። አንድ ሴት እንደምትወድህና እንደምታፈቅርህ ከመደምደምህ በፊት ከእርሷ የምትጠብቀውን ነገር አስቀድመህ እወቅ። የሚቀርብህ ሰው ሁሉ ወዶህና ተማርኮብህ የሚመጣ ከመሰለህ ማንም ቢቀርብህ እንደተፈቀርክ ማሰብህ አይቀርም። ትኩረት ማግኘትህ የመፈቀርህ ዋስትና አይደለም፤ ጊዜ ማግኘትህ ለተለየ ግንኙነትህ የመታሰብህ ምልክት አይደለም። ፍቅር መስፈርቱ ከፍ ያለ ነው፤ ምልክቱም ረቂቅና ከጠለቀው ስሜት ጋር የተገናኘ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! በቀድሞ ህይወትህ ተገፍተህ ከሆነ አሁን ቀረቤታን ማግኘትህ ለተለየ ግንኙነት የተፈለክ እንዲመስልህ ሊያደርግህ ይችላል፤ ለአመታት ትኩረት ተነፍገህ፣ ጆሮ አጥተህ፣ አጋዥ ሳታገኝ ቆይተህ ዛሬ እርሱን ብታገኝ ምናልባትም ካንተ የሆነ ነገር ፈልገው ወይም ለሌላ ግንኙነት አስበውህ እንደሆነ ልትገምት ትችላለህ። ነገር ግን የቀረበህ ሁሉ አፍቃሪህ አይደለም፤ አክባሪህ ሁሉ ለሌላ ግንኙነት የሚፈልግህ አይደለም፤ ትኩረት ሰጥቶህ ያዳመጠህ ሁሉ ካንተ ጋር የረጅም ጊዜ እቅድ ኖሮት ላይሆን ይችላል። የምታስበው ሲሆን፣ የምትጠብቀው ነገር በገሃድ ሲገለጥ የምርም ላንተ እንደሚገባህና ልክህ እንደሆነ ይሰማሃል።

አዎ! የዘመናት ሸክምህ፣ የረጅም ጊዜ ጭንቀትህ፣ የማያባራው ፍላጎትህ፣ ምላሽ ያጣው ጥያቄህ ከአንድ አቅጣጫ በሚመጣ ተግባር የሚገታና የሚመለስልህ ሊመስልህ ይችላል። ነገር ግን እውነት ያስመሰለብህ ሃሳብህ እንጂ መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ ነገር አይደለም። የሚመጣ ሰው ሁሉ ጉድለትህን የሚሞላ፣ ያጣሀውን የሚሰጥህ፣ የተቀማሀውን የሚያስመልስልህ አይደለም። በህይወትህ ትልቅ ስፍራን እንዲኖረው የምትጠብቀው ሰው ቢኖር እርሱም ባንተ ፍላጎት ሳይሆን በእራሱ ምርጫ እንደሆነ አስተውል። ነገሮችን ከፍላጎትህ አንፃር ከመደምደምህ በፊት በሚገባ መርምራቸው፤ ጠንቅቀህ እወቃቸው። በፍላጎትህ ምክንያት እራስህን አጣብቂኝ ውስጥ አትክተት፤ በክፍተትህ በኩል እራስህን ለጉዳት አታጋልጥ።


🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Z1D7EM0v-uw?si=IxM67RzoSd50NsoW

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💗 ወርቃማ አባባሎች 💗

ከልምዶች ሁሉ ጎጂ=ጭንቀት
የሚያኮራ ስራ= ሌሎችን መርዳት
አስቀያሚ ባህሪ= ራስ ወዳድነት
መጥፎ ልማድ =መስረቅ
ትልቅ የተፈጥሮ ሀብት=ወጣትነት
ትልቅ መሳሪያ = ብርታት
መጥፎ ፀባይ = ይሉኝታ
ቆንጆ ጌጥ = ፈገግታ
አደገኛ ስብከት=አሉባልታ
ትልቅ ስጦታ =ምክር
     ይቀጥላል
       LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Z1D7EM0v-uw?si=IxM67RzoSd50NsoW

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ሰላም ቤተሰቦች ዛሬ አንድ የምስራች ልነግራችሁ ነው የ YouTube channel subscribe በማድረግ የሞባይል ካርድ እና🎁የኢንተርኔት ፓኬጅ መሸለም ትችላላችሁ።

ማሳሰቢያsubscribe ማድረጋችሁን ለማረጋገጥ comment ላይ ስልካችሁን አስቀምጡልን ወይ ደሞ የቴሌግራም username አስቀምጡልን።
#ለወዳጅ ለጓደኛዎ #ሼር ያድርጉ አብረው ይሸለሙ🎁

🧑‍💻ከስር ያለውን link በመጫን አሁኑኑ ተሸላሚ ይሁኑ👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/Fxn9M8wu_vw?si=ElBRM5mckhzQDnRE
😳እንዲቆጩ አድርጉ!

በሰው የመገፋትን ህመም ለማወቅ የግድ መገፋት የለባችሁም፣ ከሰዎች መሃል ተመርጦ የመጠቃትን ክብደት ለመረዳት የግድ በግል መጠቃት አያስፈልጋችሁም። ሰዎች መርጠው ይቀርቧችኋል መርጠው ይርቋችኋል፤ ሰዎች ፈልገው ይወዳጇችኋል ፈልገው ይለዩአችኋል። ፍቅር በግዴታ የሚሰራ ነገር አይደለም። መሔድ የሚፈልጉት ይሂዱ ነገር ግን በመሔዳቸው ምን እንዳጡ አሳዮአቸው፤ በምርጫቸው የገፏችሁ ይግፏችሁ ተዎቸው ይሔንን ስላደረጉባችሁ ግን እንዲቆጩ አድርጉ። ለማንኛውም ለሚጠላችሁ፣ ለሚገፋችሁ፣ ለሚጠየፋችሁ ሰው ትክክለኛው በቀል ከእርሱ ተሽሎ በመገኘት በድርጉቱ እንዲፀፀት ማድረግ ነው። ጥሩ የሰራን የማይፈልግ ሰው አይኖርም። ከዚህ ቀደም የነበራችሁ ቦታ ቢነሳችሁና መገፋት ቢደርስባችሁ ብዙ አትደነቁ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ስንባል መዳቡን ስናሳድድ በእጃችን ያለውን ወርቅ መግፋታችን አዲስ ነገር አይደለም። እራሳችሁን እንደ ወርቅ የምትመለከቱ ከሆነ ውድነታችሁን የማሳየት ግዴታ አለባችሁ። ሰው ሁሉ አዙሪት ውስጥ ነው። ከራስወዳድነቱ የተነሳ አጥብቆ የሚፈልገው የሚጠቅመውን ሰው ብቻ ነው።

አዎ! እንዲቆጩ አድርጉ! እናንተን በማጣታቸው፣ እናንተን በመግፋታቸው፣ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ እናንተን በመጥላታቸው እንዲቆጩ፣ በእራሳቸው እንዲያዝኑና አንገት እንዲደፉ አድርጉ። የመገፋት ስቃይ የማንም ሰው እጣፋንታ አይደለም፤ ተመርጦ መጣል፣ መናቅና መንቋሸሽ ማንም ላይ ሊደረግ የሚገባ ነገር አይደለም። በብዙ ፍላጎቶችና ምርጫዎች የታጠረ ቢሆንም ሰውነት ክብር ነው። ማንም ሰው የመጣውን ሰው ሁሉ የህይወቱ አንድ አካል ማድረግ አይችልም፤ ነገር ግን አንዴ ወደ ህይወቱ ካስገባ ቦሃላ ልክ እንደ ሸንኮራ አገዳ አኝኮ የመትፋት መብቱ የለውም። የሰው በደል ዕድሜ ልክ ይከተላል። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ ማንም ሰው ላይ ያደረሰውን ጥፋት መክፈሉ አይቀርም። ከሰው ለመለየት ስታስቡ፣ ሰውን መተው ሰትፈልጉ በቻላችሁት አቅም የሰውዬው ስሜት እንዳይጎዳ ጥንቃቄ አድርጉ፤ እናንተም እንዲሁ የክፋትና የጭካኔ ስም እንዳይሰጣችሁ ተጠንቀቁ። የትኛውም ሰው የሚበጀውን ያውቃልና እጅና እግሩን አስራችሁ ማስቀመጥ አትችሉም። መሔድ ከፈለግ ይሒድ ሲሔድ ግን ምን እንዳጣ ማወቅ አለበት፤ መለያየት የመጨረሻ ውሳኔው ከሆነ ያድርገው ፍቀዱለት ነገር ግን መለያየቱ ከእርሱ በላይ እናንተን እንደጠቀመ በተግባር አሳዩት።

አዎ! ጀግናዬ..! ዋጋህን የማያውቅ ሰው ብዙ ይልሃል፣ ብዙ ያደርግሃል። ረጅም ጊዜ አብረሀው ስትሆን መሔጃ ያጣህ ይመስለዋል፣ የገጠመህን ችግር ሁሉ ስታማክረው ሌላ የምታማክረው ሰው እንደሌለህ ያስባል፣ ከብዙ ሰዎች መሃል መርጠህ ዝቅ ብለህ ስትታዘዘውና ስታገለግለው ሌላ አንተንም የሚያገለግልህ ሰው የሌለህ ይመስለዋል። አንተ ዋጋህን ማሳየት ካልቻልክ ማንም በማቅረቢያው ወይም በአጉሊው መነፅር ዋጋህን ሊያይልህ አይችልም። እንዴትም እራስህን በየበታችነት አዙሪት ውስጥ አታስቀምጥ፤ በምንም መንገድ መሔጃ እንዳጣ ሰው ከሚመርዝህ ሰው ጋር አትቆይ። ሰው ዋጋህን እስካላወቀ ድረስ በፍፁም ቦታ አይሰጥህም፤ ማንም ልክህን እስካልተረዳ ድረስ ሊያከብርህ አይችልም። ዓለም ሰፊ ነች፣ ሰው ይሔዳል ሰው ይመጣል፣ ሰው ይጠላሃል ሰው ይወድሃል፣ ሰው ይገፋሃል ሰው ይቀርብሃል፣ ሰው ይጠየፍሃል ሰው ያፈቅርሃል። ሰው ገፋኝ ብለህ ህይወትህን እንደ ሲዖል አትመልከት፣ ሰው ወደደኝ ብለህም መቼም የማይቀየር የደስታ ዓለም ውስጥ ገባው ብለህ አትመፃደቅ። ከሚጠላህና ከሚወድህ ሰው በላይ ለእራስህ የምታስፈልገው እራስህ እንደሆንክ እወቅ። ከተገፋው ማንነትህ ተሽለህ እስከተገኘህ ድረስ የገፉህን ሁሉ በስራቸው እንዲፀፀቱ የማድረግ አቅሙ እንዳለህ እመን።


       LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ለምሺታችን ተጋበዙልኝ ካነበብኩት🙏

"ራሳችሁን ሁኑ፣ ሁሉም ሰው ተይዟል!"

Oscar Wilde


የራሳችሁን መልክ ለቃችሁ ሌላ ሰው ለመምሰል አትሞክሩ። ሌላ ሰው ሌላ ሰው ነው፣ እናንተም እናንተ ናችሁ። ራሳችሁን በመሆናችሁ የሚቀርባችሁ ነገር ካለ ቀድሞውኑ የእናንተ አልነበረምና ይቅርባችሁ። ናቹ ተብሎ በተሰጣችሁ ማንነት መቼም ሀፍረት አይሰማችሁ።

   LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ፍትህ ..!!!
ገና እንቡጥ ጮርቃ
ሳትጠግብ ቦርቃ
ምኑን ከምኑ ሳትለየው
የአለምን ጣዐም ሳትቀምሰው
እህል በወጉ ጠግባ ሳትበላ
እንዲህ ስትቀር ድፍት ብላ...!
እግዚኦ እግዚኦ ለፍርድህ
ምነው ?ጌታ ሆይ ዝም ማለትህ
ሳጥናኤሎች በዙ ፍርድ ከምድር ጠፋ
እንዲህ ሆነና ሰው ከአራዊት ከፋ
እንደጭዳ ዶሮ አንገቷን ቆልምመው
እንደውሻ ሬሳ ቅዱሱን ሰው ጥለው
ዝንት አለም ያልነበር ለወሬ የከፋ
ስንት ግፍ ተሰራ ስንት ህይወት ጠፋ😭


ለፍትህ ስትሉ ለ100 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ራሳችሁን አድኑ!

ሰውነት ደካማ ነው፤ በምንንና እንዴት እንደሚንሸራተት አይታወቅም። ከምንም በላይ ግን በሰው እጅ ላይ ከወደቀ ቆይታው አደጋ ላይ ነው። ምንምያህል ችግርና ማጣት ቢጠናባችሁ፣ ምንምያህል ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብትወድቁ እንኳን በቻላችሁት አቅም ራሳችሁን ለሰው አሳልፋችሁ አትስጡ። ሰው ወዳለው ያደላል፣ ሰው ለተሻለው ማጎብደዱ አይቀርም፣ ሰው የሚጠቅመውን ይመርጣል። እናንተ የማትረዱትና ከእናንተ ምንም የሚያገኘው ነገር ከሌለ ለትንሽ ጊዜ ቢታገሳችሁ እንጂ ያለምን ጥርጥር በስተመጨረሻ አውላላ ሜዳ ላይ ጥሏችሁ ይሔዳል፣ የናንተ ጉዳትና ህመም ምኑም የማይሆንበት ጊዜ ይመጣል። ከየትኛውም ፍጡር በላይ የጭካኔ ጥግ የሚገለጠው በሰው ልጅ ላይ ነው፤ ሰውም ከየትኛውም ፍጡር በላይ የሚጨክነው አምሳያው በሆነው የሰው ልጅ ላይ ነው። የሰው እጅ ላይ ከወደቃችሁ በትልቁ ጋን ክንችር ተደርጎ እንደተቆለፋባችሁ አስቡት። ሰውየው ሲፈልግ ብቻ በፈለገው ሰዓት ይከፍታችኋል፣ እንደፈለገው ተጠቅሞም መልሶ ቆልፎ ያስቀምጣችኋል።

አዎ! ሁሉም ቢመቸውና ቢሆንለት ሊጠቀምባችሁ ይፈልጋልና ራሳችሁን አድኑ፣ ራሳችሁን ከሰዎች ድራማ ውስጥ አውጡ። ከሰው እጅ እየጠበቃችሁ የተንጣለለ ቪላ ውስጥ ከምትኖሩ እራሳችሁን ችላችሁ በትንሽዬ ጎጆ ውስጥ በነፃነት ብትኖሩ ይሻላችኋል። የሰው ልጅ ፈጣሪ አይደለም ከእናንተ ምንም ሳይጠብቅ የሚያስፈልጋችሁን በሙሉ የሚያሟላላችሁ፣ እርሱን የማድረግ ግዴታም የለበትም። የትኛውም ሰው የመጀመሪያ ሀላፊነቱ እራሱን ማዳን ነው፣ ከርሱም ካለፈ ወዶና ፈቅዶ በዙሪያ ላሉ ሰዎች የአቅሙን ማድረግ ነው። የሰው ነገር ዞሮ ዞሮ የሰው ነው። ከዛም በላይ አብዛኛው ሰው አስመሳይ ነው። ዛሬ አፈር ነገ እሳት ይሆናል፣ አሁን ደግ ቦሃላ ክፉ ይሆናል። ከማን ምን መቀበል እንዳለባችሁ፣ ከማን ጋርስ እስከመቼ እንደምትዘልቁ በሚገባ እወቁ። እድሜ ልካችሁን የሰዎች ተረጂና ተመፅዋች አትሁኑ። ወደዳችሁም ጠላችሁም ብቸኛ ምርጫችሁ ራሳችሁን መቻል ነው። አንድ ቀን ከፍተኛ አውሎ ነፋስ በተነሳ ጊዜ ተገንጥሎ እንደሚወድቀው ቅርንጫፍ አትኑሩ። የራሳችሁን ሰር በጥልቀት ወደምድር አስርጉት፣ በሚገባ ተደላድላችሁ መሬቱን ቆንጥጣችሁ ያዙት፣ የትኛውም ከባድ አውሎ ነፋስ ቢመጣ በቀላሉ እጅ አትስጡት።

አዎ! ጀግናዬ..! ምድር የመፅዋቾች እንጂ የተመፅዋቾች አይደለችም፣ ዓለም የረጂዎች እንጂ የተረጂዎች አይደለችም። የሰው እጅ ላይ ወድቀህ፣ ሰው እየደገፈህና እያገዘህ የምትኖር ግፋ ሲልም ምንም ነገር ሳትሰራ ከሰው እየጠበክ የምትኖር ከሆነ በአደገኛ አጥር በታጠረ ቅጥር ጊቢ ውስጥ እንደሆንክ እወቅ። በምንም መንገድ የነፃነትን አየር መተንፈስ አትችልም፤ እንዴትም ያሰኘህን ነገር ማድረግ አትችልም፤ በምንም ተዓምር ራስህን ልታድን አትችልም። ማውራት፣ መጮህ፣ መንቀሳቀስ ትችላለህ ነገር ግን ሁለቱ እጆችህ በሰንሰለት ታስረዋል፣ አንዳች ተጨባጭ ነገር ማድረግ አትችልም። የሰው ነገር የሰው ነው፣ መቼና እንዴት እንደሚወሰድብህ አታውቅም። ሲኖርህ የሚያሳድድህን ስታጣም የሚያሽሟጥጥብህን ሰው ተማምነህ አትቀመጥ። ራስህን ለማዳን መገንባት ያለብህ ግንብ ካለ ጊዜ አታጥፋ ዛሬውኑ መሰረቱን ጣል፣ ቀስ በቀስ እየገነባሀው ሂድ። ከሰው እጅ ከመጠበቅ ተላቀቅ፣ በሰው መተማመን አቁም። ይብዛም ይነስም የራሴ የምትለውን ነገር መገንባት ላይ አተኩር።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ግዜ ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
👍በሳል ሁኑ!

💚ለውብ ምሺታችን

በሳልና ብልህ የተባሉ ሰዎች ከምንም በላይ የተካኑባቸው ሁለት ጥበቦች አሏቸው። አንደኛው ነገሮችን አርቆመ መመልከት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ስሜትን መቆጣጠር ነው። እንደማንኛውም ሰው የግል ህይወት አላቸው፣ እንዲሁ የሚመሩበትም የግል መርህ አላቸው። ብስለታቸው ምናልባት በእድሜ የመጣ ሊሆን ይችላል፣ ከእዴሜያቸው በፊትም የበሰሉ ግን ብዙ አሉ። እነዚህ ከዕድሜያቸው የቀደሙ ሰዎች ህይወታቸው ያስቀናል፣ በሚያደርጉት እያንዳንዱ ነገር ውስጥ ህይወት አለ፣ ሀሳባቸው በጣም ያስገርማል፣ የገጠሟቸውን ችግሮች የሚመለከቱበትና ሊቀርፉት የሚሞክሩበት መንገድ እጅጉን አስደናቂ ነው። በቅድሚያ ይረጋጋሉ በመቀጠል የገጠማቸው ጉዳይ በእነርሱ አቅም መስተካከል ስለመቻሉ እርግጠኛ ይሆናሉ፣ ከዛም ቀስ በቀስ እርምጃ ይወስዱበታል ደረጃ በደረጃም ችግራቸውን በራሳቸው መንገድ ሲፈቱት ይታያሉ። ብስለትና ብለሀት በገንዘብ አይገዛም፣ በአንድ ሌሊትም ተዋህዶን መገለጫችን አይሆንም። በየቀኑ እራሳችሁን በማሻሻል ስትጠመዱ፣ በየጊዜው እራሳችሁ ላይ ስትሰሩ፣ አዳዲስ ፈተናዎችን ስትጋፈጡ፣ ከሰዎች ውድቀትና ስኬት መማር ስትችሉ ያኔ በሂደት ወደ ብስለት ከፍታ መምጣት ትጀምራላችሁ።

አዎ! በሳል ሁኑ! ዛሬ ስለገጠማችሁ የህይወት ማዕበል ብቻ እያሰባችሁ ህይወታችሁን አትገድቡት። ሩቅ ተመልከቱ፣ የአሁን ገደቦቻችሁን ተሻገሩ፣ የሚወራባችሁን አሉታዊ ነገር እለፉት፣ ለእውቀት ቸኩሉ፣ ጥበብን አሳዱ፣ በሀሳብ ግዘፉ፣ በተግባር ቅደሙ። በቻላችሁት አቅም ህይወት ለእናንተ እንድታዳላ አድርጉ። ቀድመው የነቁ ሁሌም ቀድመው ያተርፋሉ፣ ከሰዎች የተሻሉ ሰዎች ሁሌም የተሻለ ነገር ያገኛሉ። ብስለት ሁነኛው የአሸናፊነት መሳሪያ ነው። ምንም ነገር በስሜት ከማድረጋችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡ፤ ምንም መጥፎ ነገር ከመናገራችሁ በፊት ከጀርባው ስለሚያስከትለው ነገር አስቡ። የህይወትን ሚስጥር ለመረዳት የግድ ችግርና ፈተና እስኪፈራረቅባችሁ አትጠብቁ። ከሰዎች ተማሩ፣ ከተፈጥሮ ተማሩ፣ ከራሳችሁ ተማሩ፣ ሁሌም በእድገት መንገድ ስለመሆናችሁ እርግጠኛ ሁኑ። አስቡ ስታስቡም በትልቁ አስቡ፣ በተለየ መንገድ አስቡ፣ ከመደበኛው አካሔድ ለመውጣት ደፋር ሁኑ። መሪነትን በራሳችሁ ላይ ተማሩ፣ በጫና ውስጥ ተሽሎ መገኘትን ራሳችሁ ላይ ተግብሩት።

አዎ! ጀግናዬ..! የብስለት ተቃራኒ ልጅነት ነው። ልጅ ህይወቱ እንደ ልጅ ነው። ምንም እንኳን ሀሳቡ ነፃና መልካም ቢሆንም ተግባሩ ግን የተገደበ ነው፣ ነገሮችን አርቆ የመመልከት ክፍተት አለበት፣ የሚፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ አሁኑኑ እንዲሆኑ ይፈልጋል፣ ሚዛናዊ እይታና የጠለቀ ግንዛቤ ላይ አጥጋቢ ክንውን የለውም። የብስለትህን ክህሎት ከልጅነት እሳቤዎች ለመውጣት ተጠቀመው። ዕድሜህ ቢያንስም ተግባርህ ግን በጥበብ የተሞላ መሆን ይችላል። ዋናው ጉዳት የቆይታ ዘመን ሳይሆን በትንሿ ዘመን የተረዷትን የህይወት ሚስጥር ምድር ላይ ማውረድ መቻል ነው። ከፍታም ዝቅታም የህይወት አንድ አካል ናቸው፣ ችግርም ድሎት የመኖር ገፆች ናቸው፣ ውድቀትም ስኬትም በፈረቃ የሚመጡ ክስተቶች ናቸው። በብስለት ጎዳና የሚያራምደው ጥበብ ግን እነዚህን ሁሉ ተረድቶ እንደ አመጣጣቸው ምላሽ መስጠት መቻል ነው። አስታውስ ብስለት ከዕድሜ በላይ የአዕምሮ ጫወታ ነው። ህይወትን ቀድመህ በተረዳህ ቁጥር ከዕድሜህ በፊት እየበሰልክና ጥበበኛ እየሆንክ ትመጣለህ። በሳል ሁን፣ ከማንም በላይ ህይወትን ተረዳት።

#LIKE👍👍እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💚ልባችሁን አሙቁት!

ከማንም የሚለያችሁ፣ ከማንም በላይ ከፍታችሁን የሚጨምርላችሁ አንድ ጥበብ አለ። እርሱም ራሳችሁን ከማንምና ከምንም በላይ ማወቃችሁ ነው። እውቀት የታላቅነት መሰረት ነች፤ እውቀት የከፍታው መንገድ ከፋች ነች፤ እውቀት ለለውጥ የመጀመሪያዋ ፈርቀዳጅ ነች። ማንም ስለራሱ በጥልቀት የሚያውቅ ሰው ምርጫዎቹ የተጠኑ ናቸው፤ እርምጃዎቹ በጥንቃቄ የተሞሉ ናቸው፤ ሀሳቦቹ ከፍ ያሉ፣ ድርጊቶቹም ውጤታማ ናችው። አሉባልታ አትስሙ፣ ትርኪሚርኪ ነገር ወደ አዕምሯችሁ አታስገቡ፣ የማይረባ ንትርክ ውስጥ አትግቡ። ራሳችሁን በምታውቁት ልክ ከለላ ሁኑለት፣ ራሳችሁን በተረዳችሁት መጠን ወደፊት ግፉት፣ ከባዱን ትግል አታግሉት፣ ችግር መከራውን አጋፍጡት፣ ልባችሁን አደንድኑት፣ ልቦናችሁን አጠንክሩ። ትክክለኛውን አቅማችሁን ካልተረዳችሁ ወደፊት ልራመድ እንኳን ብትሉ አትችሉም፣ ፍላጎታችሁን ካላወቃችሁ ትልቅ ነገር ላሳካ፣ ህይወቴን ልቀይር፣ ለሰዎች ልድረስ ብትሉ እንኳን አትችሉም። ሀሳባችሁ እውን ይሆን ዘንድ እቅዳችሁም ይሳካ ዘንድ ዋናውን መሰረታዊ እውቀት ወደ ልባችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል።

አዎ! ልባችሁን ክፈቱ፣ ለራሳችሁ ቀናተኛ ሁኑ፣ ውስጣችሁን ተረዱት፣ ልባችሁን አሙቁት። የሚመጣ ሁሉ ሊያውቃችሁ ይሞክራል ነገር ግን ሳያውቃችሁ ተመልሶ ይሔዳል። የሰው ልጅ ረቂቅ ነው። ከርቀቱም የተነሳ አንዳንዴም ራሱ ሰውዬው እንኳን እራሱን በጥልቀት ለማወቅ ሊቸገር ይችላል። ዓለም የምታቀርብላችሁን ጌጣጌጥ መመራመር አቁም፤ በሰዎች ከመስመር የወጣ ድርጊት መበሳጨት አቁሙ፤ የዓለምን አሰራር ለመረዳት መድከማችሁን ተውት፣ አዕምሯችሁን በውጫዊውን እውቀት ዙሪያ ማስጨነቃችሁን አቁሙ። ሁሉም ራስን ከማወቅ ቦሃላ እንደሚመጣ ተረዱት። አሁን ገባችሁም አልገባችሁ፣ አሁን አወቃችሁም አላወቃችሁም በስተመጨረሻ ህይወት በቀዳሚነት የምትፈልገው የእናንተን ህልውና ነው። ጨርቃችሁን ጥላችሁ እስክታብዱለት የምትፈልጉት የትኛውም ምድራዊ ነገር ከእናንተ ህይወት አይበልጥም። አመናችሁም አላመናችሁም ህይወታችሁን የምትመሩት ራሳችሁን በምታውቁትና ለራሳችሁ በሰጣችሁት ትኩረት ልክ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ግብግብ ውስጥ አትግባ። ምንም ቢፈጠርብህ ከሁሉም በፊት የገዛ ስሜትህንና በነገሩ ዙሪያ ያለህን ግንዛቤ ለማወቅ ሞክር። ማንም ያላንተ ፍቃድ እንዲጠቀምብህ ካልፈለክ ከማንም በላይ ራስህን ጠንቅቀህ እወቅ። የትኛውም ሰው ከሚያውቅህ በላይ ራስህን የማወቅ ግዴታ እንዳለብህ አስተውል። ውስጣዊ አቅምህን፣ የመረዳት ችሎታህን፣ ክህሎትህን፣ የደስታህን ምንጭ፣ የወደፊት እርምጃህን፣ ከፈጣሪህ ጋር ያለህን ቅርበት፣ ጥንካሬህን፣ ድክመትህን፣ የልብ ፍላጎትህን በሙሉ ጠንቅቀህ እወቅ። ከራስህ የሚበልጥ የቤት ስራ የለህም። ስሜትህን የመግዛቱ አቅም አለህ፤ ምርጫዎችህን የማስተካከሉ ተሰጥዖ አለህ። ስህተትን እንደ ስህተትነቱ፣ ጥፋትንም እንደ ጥፋትነቱ ተቀበል። ማራኪ ሆነህ ለመታየት ሳይሆን የእውነትም ማራኪ ለመሆን ራስህ ላይ ጨክን፣ ከሰው በላይ ለራስህ ታመን። በጥንቃቄ የተጠናን እርምጃ ተራመድ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተን ተግባር ፈፅም፣ በጥበብ መንገድም በልበሙሉነት ተመላለስ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
"ጦቢያ" የተሰኘው ዘመናዊ ልብወለድ መፅሐፍ የፃፉት ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ከባለቤታቸው ጋር በሀገረ ጣሊያን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተነሱት ፎቶግራፍ ፤

ጳጉሜ 1 ቀን 1927 ዓ.ም
ጣሊያን - ሮም

    LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችው🌼
አዲሱ አመት ሀገራችን ሠላም የምትሆንበት ያድርግልን 🙏
                
    ❤️መልካም
በዓል❤️

    LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
እናቴ በጣም ጎበዝ ነርስ ናት። አንድ ጊዜ በአመት በአል ቀን ተረኛ ሆና ወደስራ ልትሄድ ስትነሳ ሁላችንም ተማርረን አንድትቀር ስንለምናት ያለችን ፈጽሞ አይረሳኝም። '' እኔ እኮ ተረኛ የሆንኩት ስዎችን ለመርዳትና ከደረሰባቸው ስቃይ ነጻ ሆነው ወደቤታቸው እንዲሄዱ ለማድረግ ነው። ለዛውም ከስምንት ሰአት በኃላ ወደቤቴ እመለሳለሁ። እስኪ አስቡ! ዛሬ በሽተኛ ለመሆን ተረኛ ሆነው በህይወትና በሞት መካከል ያሉትን የሌሎች ልጆች ወላጆች። ምናልባት ፈፅመው ወደቤት ተመልሰው ሌላ አመት በአልም ላያከብሩም ይችላሉ።'' ነበር ያለችን። ሁላችንንም የለወጠ አባባል ነበር። እናቴ የምትገርም ደግ ሰው ናት። በእርግጥ ታመው የተሻላቸው ሲያመሰግኑ ያልታመሙት ለምን ይሆን የሚያማርሩት? በህይወትና በሞት መካከል ያሉት አንድ ተጨማሪ ደቂቃ ለመኖር ባለ በሌለ ሃይላቸው ሲፍጨረጨሩ በህይወትና በጤና ያሉት ግን ሞትን የሚያስመኛቸው ምክንያት ግን ሁሌም ይደንቀኛል።

📕ከተቆለፈበት ቁልፍ

በዶክተር ምህረት ደበበ


    ❤️መልካም በዓል❤️

  LIKE👍👍 እና Share
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💚ለውብ ቀናችን🙏

ሁለት በእድሜ የገፉ ባልና ሚስት አንድቀን ከቤት መውጣት ድብር ይላቸውና ..
ባል "የወጣትነት ጊዜያችንን ወደኋላ ብንመልሰው ምን ይመስልሻል?" አላት።
ሚስትም በጣም ደስ ብሏት "እሺ" አለችው።

ባል "በቃ እኔ እታች ሱቁ ጋር ልውረድና ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብዬ አንቺ በዛ በኩል እለፊና ይዤ ላዋራሽ።"
ብሏት ተስማሙና ባል ወርዶ ሱቁ ጋር ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብሎ ሚስቱን መጠበቅ ጀመረ። ቢጠብቅ ቢጠብቅ አትመጣም 4ሰዓት ሙሉ ጠበቃት አልመጣችም።

ከዛን የሆነ ነገር አጋጥሟት ይሆናል ብሎ ወደቤት ሲመለስ ሚስት ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ያገኛታል። ባልም ደንግጦ ..
"ምን ሆነሽ ነው ውዴ? ምን ነካብኝ?" ብሎ ቢጠይቃት
ሚስት "እናቴ አትወጪም ብላ ከልክላኝ ነው😭😭" ብላ እርፍ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም ቀን ተመኘሁ
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
#ሰውና_ተፈጥሮው_እንዲህ_ይልሃል

ሰዎች የቱንም ያህል ልክ ባልሆነ መንገድ ቢያስተናግዱህ ችግር የለውም። መቼም ቢሆን ወደ እነሱ ደረጃ እንዳትወርድ። ረጋ በል፤ ጠንክር እና ትተሃቸው ሂድ!

አንተ እኮ ልዩ ነህ!

#ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ

የሮበርት ግሪን ምርጥ መጽሐፍት👇

#ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ
#የኃያልነት_ሕጎች 3ተኛ ዕትም

ሌሎች የሮበርት ግሪን በእንግሊዝኛ የታተሙ👇

#The_Laws_of_Human_Nature
#The_Daily_Laws
#The_33_strategies_of_WAR

ሁሉንም መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል።

🎀

እነዚህ #የኃያልነት_ሕጎች መጽሐፍ እና #ሰውና_ተፈጥሮው መጽሐፍን፦

#ጄዚ
#ካንዬ_ዌስት
#ፊደል_ካስትሮ
#ጆርዳን_ፒተርሰን
#ባራክ_ኦባማ
#ኤለን_መስክን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ እና ኃያል ግለሰቦች ለስኬታቸው እንደምክንያት የሚጠቅሷቸው ናቸው። እናም አንተም ያቀድከውና ያሰብከው የስኬት መዳረሻ ላይ ለመውጣት እነዚህን መጽሐፍት እንደ መሰላል እንድትጠቀምባቸው አቅርበንልሃል፡፡

 LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
👍ትንሽ አትሁኑ!

ሌሎችን ለመተቸት ጊዜ እስክታጡ ድረስ ራሳችሁን በማሻሻል ተጠመዱ፣ ራሳችሁን በማብቃት ቢዚ ሁኑ። ትልቁ ስራ የሰውን ድክመትና ክፍተት ማውጣት ሳይሆን የራስን አውቆና ተረድቶ እርሱን ማሻሻል መሆኑን እንዳትረሱ። ትቺት የዓለምን ህዝብ እኩል የሚያደርግ በጣም ቀላሉ ስራ ነው፣ በምትኩ ራስን ማሻሻል የዓለምን ህዝብ የሚለይ ትልቁና ዋንኛው ስራ ነው። ማንም ልዩነት ፈጣሪ ሰው ልዩነቱን የፈጠረው ለዓመታት ሰውን ተችቶ፣ በሰው ስራ ተሳልቆ ወይም ሰው ላይ አተኩሮ አይደለም። ይልቅ ራሱን አውቆ፣ ማንነቱን ተረድቶ፣ አቅሙን ተገንዝቦ፣ ያለማቋረጥ ራሱ ላይ ሰርቶ፣ በየቀኑ ራሱን እያስተማረና ራሱን እየፈተነ ነው። ራሳችሁ ላይ ማተኮራችሁን ስትቀጥሉ የሰዎችን ድክመትና ክፍተት የመመልከት እድላችሁ እያነሰ ይመጣል። ጊዜያችሁ እጅግ በጣም ውድ ነው። ከቻላችሁ በገንዘባችሁ ግዙት፣ ሌላ ሰው ማድረግ የሚችለው ጉዳይ ካለ እርሱን ለሰው አሸጋግራችሁ ጊዜያችሁን ለተሻለ ነገር ነፃ አድርጉት።

አዎ! ትናንሽ ነገር እያደረጋችሁ ትንሽ አትሁኑ፣ በአሳፋሪ ተግባር ተሳትፋችሁ በራሳችሁ አትፈሩ። ሰዎች ላይ ያለማቋረጥ የነቀፋ ቃላትን መሰንዘር እውቀት ወይም ስልጣኔ አይደለም። ሁሌም ቢሆን ቁጭ ብሎ ማውራት የትናንሽ ሰዎች ባህሪ ነው፣ የሰው ስራን ሁሉ መናቅ የተናቁ ሰዎች ስራ ነው። አትዘናጉ፣ አይናችሁ ውጪ ውጪውን ሲል ማሻሻልና ማስተካከል የሚችለውን የገዛ ማንነቱን ይዘነጋል፣ ራሱን ይረሳል፣ የት ቆሞ ማንን እንደሚተች ማስተዋል ይሳነዋል። ራስን ማወቅን የሚያክል ትልቅ ምድራዊ ጥበብ የለም። ራሱን የሚያውቅ ሰው ከሁሉም በላይ ፈጣሪውን ይፈራል፣ ራሱን ለእርሱ ትዕዛዝና አስተምህሮ ያስገዛል፣ ቃሉን ያከብራል፣ በሰዎች አይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ከመመልከቱ በፊት የራሱ አይን ውስጥ ያለውን ምሰሶ ያስተውላል፣ ግዞቱ ያልሆነው ውጪ ላይ ከማተኮር ግዞቱና ርስቱ በሆነው ራሱ ላይ ያተኩራል። ከአምላክና ከእናንተ በቀር እናንተን የሚያውቅ ሰው የለም። ማንም ስለእናንተ እንዲነግራችሁ አትጠብቁ። ምንም ዙሪያ ጥምጥም መሔድ ወይም ሰውን ማስጨነቅ አያስፈልግም የራስ ግንዛቤያችሁ ምንጭ እናንተ ብቻ ናችሁ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ዝግጁ ካልሆንክ አንዳች ከውጭ መጥቶ የሚቀይርህ ነገር የለም። ዛሬም እንደ ትናንቱ ዋናው የህይወት አጀንዳህ ሰዎች ከሆኑ ከምታስበው በላይ ለውድቀት እየቀረብክ እንደሆነ አስተውል። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የራሳቸውን ውድቀት በሰዎች ለመሸፈን ይሞክራሉ፣ ሰዎችን በናቁና በተቹ ቁጥር ንፁና ከእነርሱ የተሻሉ ሰዎች እንደሆኑ ያስባሉ። ነገር ግን የትኛውም ከሌላው ሊሻል የሚችለው በወሬ ሳይሆን በስራና በስራ ብቻ ነው። ችሎታው ማውራትና መተቸት ቢቻ የሚመስለው ሰው ስራውን ከመስራቱ ውጪ ትቺቱ የሰውን ስሜት እንደሚጎዳና ህልሙን ሊያደናቅፍበት እንደሚችል አያስብም። ብዙ አውቃለሁ፣ ነገሮችን ተረድቼያለሁ፣ ራሴንም አውቃለሁ ካልክ አፍህን ዝጋ፣ ስለሌሎች አይደለም ስለራስህ እንኳን ከልክ በላይ አታውራ። የምር አዋቂ ከሆንክ ስሜትህን ግዛ፣ ራስህ ላይ ሰልጥን፣ ሰዎችን መተቸት አቅቶህ ሳይሆን ጊዜውን እስክታጣ ድረስ በግል ጉዳዮችህ ተጠመድ፣ ትልቁን ጥበብህንም ገልጠህ ለዓለም አሳይ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💛ተሰፋ

ተስፋ የተሟጠጠበት ቦታ፣ እየታመኑ የሚጠረጠሩበት  ፤እየሰጡ የማይመሰገኑበት፣ እያመኑ በሚካዱበት  ስፍራ መኖር እፈራለሁ፦

ፍቅር  እልቅ እስኪል ፣መከባበር ሙጥጥ እስኪል፣ ተስፋ እሲኪበጠስ ፣ መዋደድ እስኪጠፋ አልጠብቅም ።

የደነበረ በሬ እንደሚከተለው ብርግግ ብዬ እልም እላለሁ..!!

"የደነገጠ እንጂ ያዘነ እንደዚህ ይሸሻል? "  እለዋለሁ እራሴን

"ፍርሃቴ ቀጥሎ ያለውን ላለማየት ነው!!" ይለኛል


LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው
ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/2X-gbw5HnVU?si=Elm9abHXy2eKSmDV

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄