ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
242K subscribers
288 photos
1 video
16 files
237 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
Live stream finished (4 minutes)
📕ተአምረተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ስምንት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ለዓመታት ጎብጦ እና አጎንብሶ የነበረ ትከሻቸው ቋቋቋቋቋ የሚል ድምጽ እያሰማ በመላቀቅ መቃናት ጀመረ…የተጨማደደ እና ተኮመታትሮ የነበረ ቆዳቸው ልክ የሽማግሌ ገፃ-ባህሪ ለመጫወት ጭንብል አጥልቆ እንደነበረ አክተር  ከፊታቸው ተሞሽልቆ በመነሳት መሬት ወደቀ…
ወዲያው መለስተኛ አውሎ ንፋስ ተነሳና እየተሸከረከረ መጥቶ እዚህም እዛም በዙሪያችን የወደቀውን የፕሮፌሰሩን የተወገደ አካል ከአካባቢው ጠራርጎ በአየር ላይ ተሸክሞ ሄደ ..
ከዛ…. ሁሉ ነገር እንዳሰበችው እንደሆነ ካረጋገጠች በኃላ እጆቾን ከጭንቅላታቸው አነሳችና…ወደመቀመጫዋ ተመልሳ ተቀመጠች…

አየቻቸው‹‹…..እንዴት አባቱ የሚያምር ጎረምሳ ሆኖል›ስትል እራሷ በሰራችው ተአምር እራሷ ተደነቀች   …‹‹ውይ እነዛ የአባቴ ዘመዶች መተው ሚወስዱኝ ባይሆን  ኖሮ ይሄን  ፊት ለፊቴ የተቀመጠውን ቆንጅዬ  ጎረምሳ አግብቼ  መኖር ነበር….›ስትል የምፀት ፈግታ ፈገግ አለች፡
ፕሮፌሰሩ ቀስ እያለ ከሰመመኑ ነቃ…
‹‹ወይ ልጄ ምድነው ያደረግሺኝ…….?ራስ ምታቴ እና ጭንቀቴ እኮ ለቆኝ ሄደ››
‹‹አሞህ ነበር እንዴ…….?››
‹‹ምን አልሽኝ…….?››ግራ ተጋብተው
‹‹ ይቅርታ አሞት ነበር እንዴ…….? ለማለት ፈልጌ ነው››
‹‹አንቺን አልረብሽሽም ብዬ ነው እንጂ እንደምትሄጄ ከሰማሁበት ቀን አንስቶ ጤናም የለኝ ነበር..››
‹‹አይ እንኳን ተሸሎት››
‹‹አረ መሻል ብቻ አይደልም …››ንግግራቸውን ሳይጨርሱ አይናቸው እጃቸው ላይ አረፈ..ተጨማዶ ና ተሸብሽቦ የነበረ እጃቸው አሁን በለግላጋ  ጣት እና ለስላሳ ቆዳ ተሸፍኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም… ግራ በመገባት እና  ባለማመን በጃኬታቸው ሸፈኑት..መልሰው ገለጡ…
‹‹ቆይ መጣሁ›› ብለው….ትተዋት ወደቤት በፍጥነት መራመድ ጀመሩ…ከኃላ ተከተለቻቸው…ቀጥታ ወደመኝታ ቤታቸው ሄደው የቁምሳጥናቸው መስታወት ፊት ለፊት  ነው የቆሙት….
‹‹የምን ታአምር ነው.…….?.እኔ የት ሄድኩ……….?ማን ነው ይሄ..…….?እኔ ማነኝ…….…….? ››ፊታቸውን እየዳበሱ ለፈለፉ…
መልስ መስጠት ጀመረች‹‹አሁን የ30 ዓመት ወጣት ሆነዋል..ማለት ሆነሀል፡፡…የሚፀፀቱበት ምንም ነገር የለም..ቀጣይ 45 ዓመት ተሰጥቶታል …. ስዚህ ቅድም እንዳሉት ሚዛናዊ ኑሮ ይኑሩበት..ማለቴ ኑርበት…››
‹‹ምን ጉድ ነው….…….?እኔ ወጣት…አንደገና መወለድ እኮ ነው…….?››
‹‹አዎ ነው..ልክ እንደንስር እንደገና የመታደስ ዕድል..››አለቻቸውና ቤታቸው ለቅቄ ወደራሴ ቤት አመራሁ ..ወደ እናቴ ለመሄድ ልዘጋጅ
////
ንጋት ላይ ነው ጉዞ የጀመሩት፡፡የንጋቱን ቀዝቃዛ አየርን  እየማጉ ሰማዩን ሰንጥቀው ቁልቁል የኢትዬጵያን ደቡባዊዉን መልካ ምድር እየቃኙ እየተጓዙ ነው፡፡እስኪ ትንሽ ከላይ ሆነው ቁልቁል ወደታች ሳያዩ ከፊል ኢትዬጵያ ምን እንደምትመስል አብረናቸው እንመልከት፡

ኢትዬጵያ 12 ታሪካዊ ቅርሶችን በዩኒስኮ በዓለም አቀፍ ቅርስነት አስመዝግባለች፡፡እነዚህም፤ የአክሱም ሀውልቶች፣ የላሊበላ አብያተክርቲያናት፣ የጎንደር ፋሲል ቤተመንግስት፤የሰሜን ብሄራዊ ፓርክ፣ የኮንሶ ሰው ሰራሽ መልካዓ ምድር፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣የታችኛው አዋሽና የታችኛው ኦሞ ሸለቆ፣ የመስቀል ደመራ፣ የሲዳማ ፊቼ ጨንበላላ፣ የኦሮሞ የገዳ ሥርአት ናቸው። ሌሎችም ለማስመዝገብ   ላይ ያለ አሉ  በዩኔስኮ እንዲመዘገቡ በእቅድ ደረጃ የተያዙ ቅርሶችም እንደ የባሌ ተራራዎች ብሄራዊ ፓርክ፣ የድሬ ሼክ ሁሴን መስጊድ፣ የሶፍ ኦመር ዋሻ፣ የጌዲዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መልከዓምድር፣ የመልካ ካንቱሬ የአርኪዮሎጂ ስፍራዎች ናቸው። በማይጨበጥ ባህላዊ ቅርስነት ደግሞ የአማራና የትግራይ የሻዳይና የአሸንዳ በዓላት የጥምቀት በዓል ይጠቀሳሉ። 
ኢትዬጳያ ግን ለቱሪስት ኢነደስትሪው ግብአት የሚሆኑ ሀብቶቾ እነዚህ ብቻ አይደሉም…ሀገሪቱ እራሱ ሙሉ በሙሉ በዩንሰኮ ቅርስነት ብትመዘገብ አያንስባትም…ግን በዛ መጠን የሚያስብ በዛም መጠን የሚሰሩ ልጆች ወልዳ አለማሳደጎ በጣት የሚቆጠሩትን ብቻ ማስመዝገብ ችላለች፡፡

ይገርማችኋል ይህቺ ሀገር ሙሉ ነች፡፡ሙሉ ስላችሁ ለምሳሌ አየር ፀባዮ  ደጋ ጥቂት ፈቅ ስትሉ ወይና ደጋ ..ብዙም ሳትርቁ ቆላ ታገኛላችሁ፡፡ይሄ ድንቅና መድሎ ያለበት የተፈጥሮ ስጦታ ነው…መልካ ምድሯን ስንመለከት  ለጥ ያለ ሜዳ…ደግሞ ቀጥ ያለ ተራራ..እሱ ሲገርማችሁ ጭው ያለ ገደል…በሌላ ጎኑ እንደጣባ አህያ የተራቆተ መሬት…እንደ ደብረብርሀን የሱፍ በግ ጥቀጥቅ ያለ ጫካ…ኩሬ ሀይቅ ወንዝ….አቤት እነዛ አሜሪካኖቹ ይሄን መልካ ምድር ከዚህ የተመጣጠነ ምግብ ከሆነ አየሯ ጋ ቢያገኙት.. አቤት ይሮፖዎች ያ በቆፈን የሚያኮራምት በረዶ ገላግሎቸው እንዲህ ሚዛኑን የጠበቀ አየር ቢያድላቸው ምን ያህል ተአምራዊ ህይወት ይኖሩ ነበር.. ተፈጥሮ ሚዛኗን የምትጠብቅበት የራሷ ቀመር አለት መሰለኝ ለእነሱ ሀብት ከቆፈን ጋር ስታድል ለእኛ ምርጥ አየር ከችጋር ጋር.. ያስቃል….እነሱ በቱሪስት ሆነው መልካምድሯን አይተው ለመደሰት እና አይሯን ምገው ሀሴት ለማድረግ ምቾት ባለው አይሮፕላን መጥተው ገንዘባቸውን ከስክሰው ከረምረም ብለው ይመለሳሉ..እኛ በስደት መልክ ከችግር ለመላቀቅ በእግር ተጉዘን በባህር ተጉዘን ሀገራቸው እንገባና ጉልበታችንን አንጠፍጥፈን አንገታችንን ደፍተን ስንባዝን ስንባዝን እንኖርና በዛው የውሀ ሽታ ሆነን እንቀራለን የእነሱ አንድ ነፍስ በእኛ ስንት ነፍስ እንደሚመነዘር ስሌቱ አይታወቅም ..ምን አልባት የብራችን ምንዛሬ ወይም ዋጋ ልዩነትን ያህል የነፍሳችንም ዋጋ ልዩነት ይኖረው ይሆናል…

….ይሄን ሁሉ ይምታስበው.ይሄን ሁሉ የምትመኘው በአየር ላይ ሆና ንስሯ ጀርባ ላይ ተጣብቆ ነው እየተጓዙ ያሉት… 

ያው ሰው በተፈጥሮ በመጨረሻው የህይወቱ ማብቂያ ሰዓት ቁጭት ውስጥ መግባቱ እና ፀፀቱን መናዘዙ ተለመደ አይደል..እሷም ያው በግማሽም ሰው በመሆኗ መጠን ከሰውም ኢትዬጵያዊ ስለሆነች ያው ያ ደግሞ ክርስቶስም ለስጋው አደላ የእንደሚባለው ለእሷም ለዘመዶቿ ተቆጭታ ነው እንጂማ የእሷ የአባቷ ዘመዶች በምድራዊ ዕውቀት የማይመዘን ብቃት እንዳላቸው ታውቃለች፡፡

ለማንኛውም አሁን ደሎ ደርሰዋል…ግን ቀጥታ ወደእናቷ ቤት መሄድ አልፈለገችም ..በመጀመሪያ ያደገችበትን ጫካ ልትሰናበት ፈለገች..መቼስ የደሎመና ጫካ ጫካ ብቻ አይደልም …ውስጡ  የቡና ተክል የተሰገሰገበት ነው..ልጅ ሆነው እንጨት ለቀማ ከእኩዬቾ ጋር ስትሰማራ ከቡናው ተክል ድፍኑን ሸምጥጠውን ይመጡት ነበር..የቡና ተክል ጥሬ ሆኖ ድፍን አረንጓዴ ነው …እየበሰለ ሲሄድ ቢጫ እየሆነ ይመጣል በስተመጨረሻ ሙሉ ብስል  ሆኗል የሚባለው ሙሉ ቀይ ሲሆን ነው..ታዲያ በዛን ጊዜ ፍሬውን ቀፈው ይመጣሉ…ቀዩ የቡና ገለፈት በወስጡ የያዘው ፈሳሽ ልዩ ጣዕም አለው….ሌላው የሚገርማት ይሄ አሁን ከላይ ወደታች የማታየው የደሎ ጫካ ወይም ሀራና ደን የመንግስት ነው…በውስጡ ከደኑ ጋ ተሰባጥሮ ሚገኘው የቡና ተክል ደግሞ የግለሰብ ነው….የኢትዬጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲህ ተዋህደው በስምም ሲጠቀሙ በዚህ ደን ብቻ ነው ያየችው፡፡
የሆነው…›› ስትል እራሷን ጠየቀች፡ለመሄጃ 3 ደቂቃ ቀረው….ንስሩ ከነበረበት ጉቶ ጥቅልል ብሎ በመንሸራተት  መሬት ላይ ተዘረረ..እናቷም እሷም በደቂቃ ውስጥ ስሩ ደረሱ..አገላበጡት…ከአይኖቹ ደም እየፈሰሰ ነው…‹‹ወይኔ እማ ቅጠሉ….. ቅጠሉ ነው..መርዝ ነው የተጠቀመው..እማ ምን እናድርግ…?››የማሰቢያ ጊዜ ሳያገኙ ግቢያችን በሰማያዊ ብርሀን ተሞላ…ቀና ስትል በሰማይ ላይ ዲስክ መሳይ መንኮራኩር ብርሀን እየረጨች ሰማየ ሰማያትን በመሰንጠቅ እነሱ  ወዳሉበት አቅጣጫ እየወረደች ነው….መጡ ማለት ነው…መጡ መሰለኝ….ወይኔ ንስሬ….

  ተፈፀመ

#በአዲስ ታሪክ እንመለሳል‼️ ከተመቻችሁ 👍👍

ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📍አንዳንዴ ምን ሆነሀል ስትባል የማትመልሰው ብዙ መሆን አለ። ለመናገር የማይመች ለመተው የማይቀል ብዙ ስሜት አለ ..ለአንተ የከበደ ለሌላው የቀለለ ነገር አለ ።

💡እንዴ ይሄ እኮ ቀላል ነው ይሄ እኮ አያስጨንቅም በሚባል ቃል የሚሸነፍ ለአንተ/አንቺ ግን የከበደ ስሜት አለ ።
ምን ሆነሀል ስትባል ምንም ብለክ የምታልፈው ውስጥህ ብቻ የምታንሸራሽረው እያዳመጥክ የምትታመምበት ። ከባድ ስሜት አለ ከባድ.......

✔️ምናልባት የምትፈልገው ስፍራ ላይ አልተቀመጥክ ወይንም የምትመኘውን ነገር አላገኘህ ይሆናል፣ ቢሆንም ተስፋ አትቁረጥ ፣ ተስፋ የመኖር ምክንያት ነውና፣

እየኖርን ነው አይደል? በሰው ሳይሆን በፈጣሪ!!
ትላንት የኖርነው ህይወት በነበር ይተካል፣
ሰዎችም ኖረው ነበሩ ይባላሉ፣
ፈጣሪን ግን ነበር ብለን አናወራውም ፤ ያለና የሚኖር ፣ በዛሬያችን ,በነጋችን አልፎም በዘላለም ውስጥ ኗሪ ነው ።
" የትላንት ነበሮቻችን በእሱ መኖር ተረስተዋል"

እናም  ወዳጄ

✔️አትድከም ፣ አትዘን ። ማንያውቃል ሸክምህ ህመምህ ሁሉ ተራግፎ ሌላ ሰው ሆነህ ትነሳ ይሆናል። ያለን ፈጣሪ እንኳን በአንድ ሙሉ ቀንና ሌሊት፣ በቅጽበት ጊዜ ዉስጥም ብዙ ተዓምር ይሠራል።

💡ንፋስ የማይወዘዉዘው ዛፍ የለም። ችግር ፣ ፈተና ፣ ሀሳብ ወስዶ የማይመልሰው ሰዉም የለም። እንዲህም ሆኖ የማይወድቅ ዛፍ አለ። በፈተና የሚፀና የሚበረታ ሰዉም አለ። ዐሳብህ ጉልበትህ ሥሮችህ ታክቶዋቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ ፈጣሪን ይዞ ይበርታ።


🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ግዜ 🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💚ህይወት ከእናንተ ትጠብቃለች!

ዶ/ር ቪክቶር ፍራንክል (Dr. Victor Frankl) ይባላል። በ20ኛው ክፍለ ዘመን የነበረ ኦስትሪያዊ ታዋቂ ኒዎሮሎጂስት (Neurologist) እና ሳይኮሎጂስት (psychologist) ነው። በህይወትና የህይወትን ትርጉም በማግኘት ዙሪያ በሚያነሳቸው ሀሳቦችና አስተምህሮዎች ይታወቃል። በአንድ ወቅትም እንዲህ ብሎ ነበር፦ "ለምን እንደሚኖሩ ለማያውቁና ከህይወት ምንም ለማይጠብቁ ሰዎች ህይወት በእራሷ ከእነርሱ ሌላ ነገር እነደምትጠብ ማሳወቅ በጣም አስፈላጊ ነው።" የህይወት አላማችሁን ፍለጋ ብዙ ዋጋ ብትከፍሉም ላታገኙት ትችላላችሁ፣ ለዘመናት ስታደርጉት የነበራችሁት ነገር የሆነ ጊዜ ስትነቁ ትርጉም አልባ ሊሆንባችሁ ይችላል፣ ከዚህም በላይ ከእራሳችሁና ከህይወታችሁ ምንም የተሻለ እሴትን መጨመር የሚችል ነገር መጠበቅ ታቆሙ ይሆናል። ነገር ግን ይሔንን አስተውሉ። እናንተ በሰውኛ አዕምሮ አስባችሁ፣ አውጥታችሁ አውርዳችሁ ደክሟችሁና ሰልችታችሁ ያላገኛችሁት የህይወት ትርጉም ዝም ብላችሁ ስትኖሩና እያንዳንዱን ሃላፊነታችሁን ስትወጡ በሒደት ወደ እናንተ ይመጣል። እናንተ የምትኖሩት ህይወት አለ፣ ህይወት ደግሞ እንድትኖሯት የምትፈልግበት መንገድ አለ።

አዎ! ህይወት ከእናንተ ትጠብቃለች! እናንተ በህይወታችሁ ውስጥ ትርጉምን እንደምትፈለጉ ሁሉ ህይወታችሁም ከእናንተ አንድ የተለየና የእናንተ መገለጫ የሆነ ልዩ ነገር ትጠብቃለች። የህይወት አላማን ለማግኘት መውጣት መውረድ፣ እራስን ማታገልና ማስጨነቅ አያስፈልግም። አንዳንድ ክስተቶች እራሳቸው ፍሰት አላቸው፣ ሲጨመቁ ከሚያወጡት መልካም ነገር ይልቅ እንዲሁ በራሳቸው ሲፈሱና በኡደታቸው ሲጓዙ የሚያመጡት ውጤት ይበልጥ ትርጉም ይሰጣል። የትኛውም ትልቅ ነገር መነሻው ትንሽ ነው። "ህይወት ትርጉም አልሰጥ አለችኝ" ከማለት ይልቅ "ህይወት ከእኔ ምን ትጠብቃለች?" ብሎ መጠየቅ ብዙ የተደበቁ አቅማችንን እንድናወጣ ያግዘናል። በየትኛውም ዘርፍ ሊሆን ይችላል፣ በምንም ስራ ውስጥ ሊሆን ይችላል በእኛና በእኛ ብቻ መሞላት የሚችል ክፍተት አለ። ተምረን፣ አውቀን፣ ተረድተንና አስተውለን ወይም በተፈጥሮ በተሰጠን የተለየ ክህሎት ይህንን ክፍተት መሙላት አንችላለን። ዓለማችን በችግር የተሞላች ነች፣ ወረድ ስንል አህጉራችን ውስጥ የችግር መዓት አለ፣ ከዛም ወረድ ስንል ሀገራችን ውስጥ ብዙ ያልተፈቱ እንቆቅልሾች አሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ከምታየውና ከምትሰማው ችግርና ክፍተት ውስጥ ለአንተ የትኛው ጎልቶ ይታይሃል? የትኛውን ለመቅረፍ የቀረብክ ይመስልሃል? በየትኛው ላይ ብትሰማራ ነፍስህ የምትረካ ይመስልሃል? ትንሽ ጊዜ አስብ፣ ለተወሰነ ጊዜ አቅድ፣ በቀጣይ ግን ቀጥታ ትግበራውን ጀምር። ብዙ ሰው የማያየውን ነገር ማየት ስትችል ብቻ ከሰዎች የተለየ አዲስ ነገር ማከናወን ትችላለህ። ህይወትን በዓላማ መኖር ውስጥ እይታ፣ ዝግጁነት፣ ቆራጥነትና የተግባር ሰው መሆን በጣም አስፈላጊዎች  ጥበቦች ናቸው። እይታህ የምትሔድበትን አቅጣጫ ያጠራልሃል፣ ዝገጁነት በማንኛው ሰዓት ወደ ተግባር እንድትገባ ያደርግሃል፣ ቆራጥነት ከሃሳብ በላይ ተግባር ላይ እንድታተኩር ያደርግሃል፣ የተግባር ሰው መሆን ደግሞ በውድቀትና በስህተት ውስጥ አያሳለፍና እያስተማረ ለላቀው ውጤት ያበቃሃል። ቀላል፣ የተረጋጋና ትርጉም ያለው ህይወት ለመኖር እንቅስቃሴዎችህን ሁሉ ትግል አታድርገው። የዓለምን ክፍተት ፈልግ፣ ከፍላጎትህ ጋር አቆራኘው፣ እርሱን ለመሙላትም እንቅስቃሴህን ጀምር


🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
“ደሃ እያለሁ ለምን የድህነቴን ምንጭ አላጣራም?”
*
በ10ሺ ዶላር የተገዛ የወርቅ ጫማ ፣በአልማዝ የተለበጠና 100ሺ ዶላር የተገዛ ሮሌክስ ሰዓት፣ 200ሺ ዶላር ያወጣ ሜርሴዲዝ ቤንዝ ካሉት በርካታ የቅንጦት እቃዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ይህ ሰው የደቡብ ሱዳን ዜጋ ሲሆን በአንድ ወቅት የሀብቱን ምንጭ መንገግስት ለማጣራት ሲሞክር ሀብቱን ሰብስቦ ከሀገሩ አመለጠ፡፡

ታዲያ ይሄን ለምን እንዳደረገ ሲጠየቅ የመለሰው መልስ ሳቅን የሚያጭር ነበር፡፡

የመለሰው መልስ እንዲህ የሚል ነበር…“ደሃ እያለሁ ለምን መንግስት የድህነቴን ምንጭ አላጣራም?”

የአነጋጋሪውን ቢሊየነር ታሪክ በተከታዩ ቪዲዮ ይመልከቱት…

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

  መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Yingalish
Wendi Mak
🎙 JOIN US @Eyosc1

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
ለውብ ቀን

ከዛ በላይ ናችሁ!

ማንም ምንም ይበላችሁ እናንተ ከዛ በላይ ናችሁ፣ ማንም ሰራችሁን ያጣጥል ስራችሁ ግን ከማንም ስራ በላይ ነው፣ ማንም በኑሯችሁ ይፈር ኑሯችሁ ግን ከማንም ኑሮ በላይ ነው፣ ማንም ከፊታችሁ ቆሞ እንደማትችሉ ይንገራችሁ አቅማችሁ ግን ከንግግሩ በላይ ነው። ከውጪ የሚመጣው ጫና ይቅርና በውስጣችሁ እንኳን የሚመላለሰው የገዛ ሃሳባችሁ ከእናንተ በላይ አይደለም። እራሳችሁን በጥራት የምትመለከቱባት የግል መነፅር አላችሁ፣ ለእራሳችሁ የምትሰጡት ቦታ አላችሁ። ውድድራችሁ ከሰዎች ንግግር ወይም ከውስጥ ጩሀታችሁ ጋር ሳይሆን ለእራሳችሁ ከሰጣችሁት ቦታ ጋር እንደሆነ አስተውሉ። ብለሃትንና ጥበብን ትምህርት ቤት ገብታችሁ አትማሩም። እውቀትን ታወሩት ይሆናል ጥበብና ብለሃት ግን በየቀኑ የምትኖሯቸው ናቸው። ጥበበኞች የማይጠቅማቸውን ንግግር አይሰሙም፣ ብልሆች ከጩሀት በላይ በሳል ንግግር ይገዛቸዋል። በየጊዜው ይማራሉ፣ እራሳቸውን በእውቀት መሰረት ላይ ያንፃሉ፣ መንፈሳቸው ጠንካራ ነው፣ ልብና አዕምሯቸው ቅርብ ለቅርብ ናቸው፣ ስለራሳቸው ሚዛናዊ ሀሳብን በማሰብ ይታወቃሉ፣ በእራሳቸው ያምናሉ ከእራሳቸው ጋር ስለሚያወሩት እያንዳንዱ ነገር በሚገባ ይጠነቀቃሉ።

አዎ! እናንተ ከዛ በላይ ናችሁ! ሳትኖሩ ከሚወራባችሁ፣ በጆሯችሁ ከሰማችሁት፣ አዕምሯችሁ ደጋግሞ ከሚነግራችሁ አሉታዊ ማንነት በላይ ናችሁ። ህይወታችሁ በመዳፋችሁ ነች። የትኛውንም ወደ አዕምሯችሁ የሚገባውን አሉታዊ ሀሳብ የማገድ መብት አላችሁ፣ የትኛውንም በአዕምሯችሁ ውስጥ የሚመላለሰውን መጥፎ ሀሳብ ጠራርጎ የማውጣት አቅሙ አላችሁ። የሰዎችን ሀሳብ በማሳደድ አትጠመዱ፣ ስለሚወራባችሁ ነገር ብዙ አትጨነቁ። "ሰዎች ስለእኔ ምን አሉ ሳይሆን እኔ ስለእራሴ ምን እላለሁ?" ብላችሁ ጠይቁ። በማንኛውም ሰዓት በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ እራሳችሁን ልታገኙ ትችላላችሁ፣ በየትኛውም ሰዓት ያልጠበቃችሁት ስፍራ ልትገኙ ትችላላችሁ። ይህም ሁኔታ የህይወታችሁ አንድ አካል እንጂ የህይወታችሁ መጨረሻ እንዳልሆነ አስተውሉ። ሁሉም ነገር በፍጥነት ይቀየራል፣ የትኛውም ከባድ ስሜት እንደ ንፋስ ያልፋል። በተፈጥሮ የደስታችን ጊዜ አጭር የመከራችን ወቅት ግን ረጅም እንደሆነ ልናስብ እንችላለን። ነገር ግን ልዩነቱን ያመጣው አስተሳሰባችን እንጂ በእርግጥም የጊዜው ርዝመት ተለያይቶ አይደለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ከየትኞቹም ከባድ ሁኔታዎችህ በላይ ስለመሆንህ አትጠራጠር። የሚሆነው ይሆናል፣ የሚቀረው ይቀራል፣ የምትባለውን ትባላለህ፣ የሚሰጥህ ስም ይሰጥሃል በስተመጨረሻ ግን ህይወት በእራሷ አቅጣጫ ስትቀጥል ትመለከታለህ። አንተ ተስፋ ቆርጠህ ካልቆምክ ምንም የሚቆም የህይወት ፍሰት የለም። ብዙዎች ሰዎችን ሰምተው ባሉበት ቆመው ቀርተዋል፣ ብዙዎች ለራሳቸው በሰጡት መጥፎ ስም ምክንያት ህይወታቸውን ፈተና አድርገውታል። የምትሰማውም ሆነ የምታየው ነገር ሁሉ እውነት እንደሆነ መቀበል አቁም። እውነት የእምነት ቅጂ ነው። ጉዳዩ የሚያወራው ወይም የሚያሳይህ ሰው ሳይሆን የእራስህ አቀባበል ነው። ሀሳብ ሰውን ይገነባል፣ ሀሳብ ሰውን ያፈራርሳል። ማንም የማይገባበት የግል ዓለም እንዳለህ እወቅ። ያንተ ዓለም ያንተ ብቻ ነው። ከማንም ዓለም አያንስም ከማንም ዓለም አይበልጥም። በልብህ ያኖርከውን ያንኑ እምነት በገሃድ አውጥቶ ያሳይሃል። የግል ዓለምህን ጠብቅ። የማንም ሀሳብ ገብቶ እንዳይረብሸው ተጠንቀቅለት። በህይወት አጋጣሚ ከተገኘህበት ሁኔታ የተሻለ ስፍራ እንደምታደርሰው ቃል ግባለት።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ቀን

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
🆕 What do you want to promote

📌 Advertising services we provide 💸
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

➡️ Channel advertisement
➡️ Music advertisement
➡️ Concert announcement
➡️ Company announcement
➡️ YouTube channel advertisement
➡️ Treatments and other sales announcement

     💻 Also, our door is open for those who want to work with us in various Business 🆕🆕 jobs. 🔸

        🔺 Earn double by making your product and service accessible to the masses at an affordable price. You will enjoy working with us. ❤️

Talk to us now 👇⬇️⬇️⬇️

•    @Eyos18
😀.   +251922788490
😀.   +251933324708‌‌
ለውብ ቀናችን

👍ከዚህ ይበልጣል!

አንዳንድ ሃሳቦች ሃሳብ ብቻ ናቸው፤ አንዳንዶችም ቅዠት ሊሆኑ ይችላሉ። ደጋግመህ ታስበዋለህ ነገር ግን ልታደርገው አትሞክርም፤ ደጋግሞ ይታይሃል፣ ይመጣብሃል ነገር ግን በእውን ልታየው አልቻልክም። ጀርባህ ብዙ ታሪክ፣ ኋላህ ብዙ እንቆቅልሽ፣ ብዙ ሸክም ይኖራል። በምንም ተዓምር በእንቆቅልሽ ማንነት፣ ባልተፈታ ታሪክ ታጅበህ ወደፊት መጓዝ፣ ሃሳብህን መኖር፣ እቅድህን መፈፀም፣ ህልምህን መኖር ሊቀልህ አይችልም። ምንም እንኳን መጠኑና አይነቱ ቢለያይም ሁሉም ሰው በህይወት አጋጣሚ በህመም ውስጥ ያልፋል፤ በስቃይ ይፈተናል፤ በግል አጣብቂኝ ውስጥ ይወድቃል፤ ደፋ ቀና ይላል፣ ይታገላል። የተደላደለ ህይወት ለማግኘት ብዙ ርቀት መጓዝ ይኖርበታል፤ ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ይጠበቅበታል፤ መወጣት የማይፈልገውን ሃላፊነት መወጣት ይጠበቅበታል።

አዎ! ጀግናዬ..! ሃላፊነትህ ቢልቅም፣ ተጠያቂነትህ ቢበዛም፣ ችግሮችህ ቢወሳሰቡም ህይወትህ ግን ከዚህ ይበልጣል፤ መቆየትህ ከዚህ ሁሉ ይልቃል። የሚሆኑ የማይመስሉ ታሪኮች ሊከሰቱ ይችላሉ፣ አጣብቂኞቹ ሊደራረቡ ይችላሉ፣ ፍላጎትና አሁናዊው አቅምህ ሊለያዩ ይችላሉ፣ ምኞትህና የጀመርከው መንገድም ሊራራቁ ይችላሉ። ነገር ግን በዚህ መሃልም ቢሆን መዳረሻህ አንድና አንድ ነው፤ በአዎንታዊነት ዘርፍ ከፍ ማለት፤ ጠቃሚ፣ ችግር ፈቺና አንተ የመጣህበት ከባድ መንገድ ላይ ያሉ ሰዎችን ማብቃት፣ መደገፍና አቅጣጫውን መጠቆም። የሆነው ቢሆንም የሚበልጠው ላይ ማተኮር ይኖርብሃል፤ እውነታውን ተቀብሎ መቆም ሳይሆን ወደፊት መጓዝ፣ መሰናክሎችን ተሻግሮ የተሻለውን ህይወት መፍጠር ይጠበቅብሃል።

አዎ! በጊዜ ብዛት የተገለጡ፣ ጊዜ ወዳንተ ያመጣቸው ጉዳዮች ፈቺው ጊዜያቸው ነው፤ የሚያቀላቸው እራሱ አምጪው አምላክ ነው። ፅናትህ እስከ ጥግ ሲሆን እንቆቅልሾችህ ይፈታሉ፤ ትዕግስትህ ሲበዛ የላቀውን ብለሃት ትጎናፀፋለህ። በደረሰብህ ጉዳይ ፈጥነህ ብይን አትስጥ፤ እራስህ ላይ ለመፍረድ፣ ማንነትህን ለመተቸት፣ መንገድህን ለማንቋሸሽ አትቸኩል። ሁሉም ሰው የተመረጠለት መንገድ በእርሱ በመራጩ በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና እንከን አልባ ነው። ሁኔታህን መቃወም፣ ገጠመኞችህን መተቸት፣ በመጣህበት መንገድ ማፈር ከአምላክህ መቃረን፣ ፈጣሪህን መተቸትና በስራው ማፈር እንደሆነ እወቅ። መሰራት ባለብህ መንገድ ትሰራለህ፤ ብቁ መሆን በሚገባህ አቅጣጫ ብቁ ትሆናለህ። ዋናው ስቃይና ውድቀትህ ሳይሆን ዳግም መነሳትና የፈለክበት ስፍራ መድረስህ ነው።

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ቀን💚💛

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
አይዞህ
Abdu Kiar
👤 Artist: አብዱ ኪያር
📅 Date: 2024
────────
🎙 JOIN US @Eyosc1
🎙 JOIN US @Eyosc1

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18
🌍የዚህ ዓለም እውነታዎች!

ውሾች እና ድመቶች አልጋ ላይ እንዲዘሉ እየፈቀድን ድሆች ግን የግቢያችን ድንጋይ ላይ እንዲቀመጡ አንፈቅድም፡፡

የሰው ዋጋው እየቀነሰ የዶሮ እና የእህል ዋጋ እየጨመረ ሲመጣ በርትተህ ጸልይ፤ ጤናማ አካሄድ አይደለምና፡፡

የውሻ ቡችላ በዋጋ እየተሸጠ ሰውን ግን በነጻ የሚፈልገው ሲታጣ ዘመኑ መክፋቱን እወቀው፡፡

ስለብርቅዬ እንስሳት ብዙዎች እያለቀሱ ይናገራሉ። በምግብ እጥረት ስለሚሞቱት ሕጻናት ግን ቃል አይናገሩም፡፡

ስለ ጠፈር ሳይንስ ብዙ ይወራል (ይሰራል)። የምድር ኑሮ ግን ሲተራመስና ሲጎሳቆል ያስተዋለ የለም፡፡

የወደቁ የታዋቂ ሰዎች ሐውልቶች መልሶ ለመትከል ገንዘብ ይሰበሰባል፤ በየጎዳናው ዳር ስለወደቁት ምስኪን ሕጻናት ግን ምንም አይባልም፡፡

በዚች ምድር ሚሊዮኖች ቤት ሳይኖራቸው በሚልዮን ብሮች እስር ቤቶች ይገነባሉ፡፡

ስለ አየር መበከል ዓለም በሙሉ ይጮሃል። ስለሰው ልጆች ስነ ምግባር መመረዝ ግን ማንም ምንም አይልም፡፡
ሰዎች ሆይ! ... ከዚህ አፍ እና ልብ ከተለያዩበት ትያትረኛ ማንነታችን ፈጥነን እንውጣ ፡፡

☞ ሰዎች ሆይ! ... የሚቀድመውን ብናስቀድም የማይተወን ፈጣሪ ይከተለን ነበር ..።

‌‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‎‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎‌‌‌‌‌‌‎
🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

#መልካም ምሽት💚💛

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Audio
📓ርዕስ፦የመጨረሻው ፍትህ
✍️ደራሲ፦ሊዮ ቶልስቶይ
👤ተራኪ፦ ግሩም ተበጀ

📚@Eyosc1

──────────
📕JOIN US @Eyosc1
📕JOIN US @Eyosc1

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18
✉️ የ ቴሌግራም አዲሱ COIN ነው ልክ እንደ TIKTOK ማለት ነው


✉️ ምንም LISTING ቀን የለውም Distribution ሳያልቅ ቶሎ ስሩ!! ከታች ባለው Link ግቡ Task ስሩ ጓደኞቻቹን ጋብዙ

✉️ ከታች ባለው ሊንክ ስገቡ Telegram premium የሆናቹ 50 Star Coin ሲሰጣቹ! telegram premium ያልሆናቹ 15 Star Coin የሚሰጣቹ ይሆናል

👇👇👇👇👇
ጀምሩት
 https://t.me/major/start?startapp=2101920214
#ቋሚ ነገር የለም

እራሳችሁን ብዙ አታስጨንቁ፣ ያሰብኩት ሁሉ ለምን አልሆነም ብላችሁ ከራሳችሁ ጋር አትጣሉ፣ ከአቅማችሁ በላይ እየታገላችሁ ራሳችሁን አታድክሙ። ሁሉም ነገር በጊዜ እንደሚቀየር አስተውሉ። ተጨነቃችሁ ተጠበባችሁ፣ አወጣችሁ አወረዳችሁ፣ እራሳችሁን ጎዳችሁ አልጎዳችሁ በስተመጨረሻ ነገሮች ሁሉ መቀየራቸው አይቀርም። ስንት ዋጋ የከፈላችሁለት፣ ደጋግማችሁ በይቅርባይነት የጠገናችሁት፣ ለረጅም ጊዜ የተንከባከባችሁት የፍቅር ህይወታችሁ የኋላኋላ እንቅልፍ ሲያሳጣችሁ፣ ከልክ በላይ ሲያስጨንቃችሁና ለከፋ ችግርም ሲያጋልጣችሁ ዝም ብላችሁ አትመልከቱ። የትኛውም ሀሳብ ስልጣን ሰጥታችሁት እንጂ በእናንተ ላይ ምንም አይነት ስልጣን የለውም፣ ሊኖረውም አይችልም። ቅዱስ መፅሐፍ ይህን ይላል፦ "ተጨንቆ በቁመቱ ላይ አንዳች ክንድ የሚጨምር ማነው?" ስለተጨነቅን የሚስተካከል ነገር ቢኖር መልካም ነበር ነገር ግን የለም፤ ስለተዋከብንና ስለተጣደፍን በፍጥነት የሚሳካ ነገር ቢኖረን ጥሩ ነበር ነገር ግን የለም። ሁሉም በሰዓቱ ይቀየራል፣ ሁሉም በጊዜ በእጃችን ይገባል። የእኛ ድርሻ በተቻለ አቅም ነፃ ሆኖ መኖር ነው።

አዎ! ምንም ቋሚ ነገር የለም፣ አንዳች ዘላለም እንደነበር የሚኖር ነገር የለም። ጥቂት የማይባል ሰው ለአንዲት ነፍሱ ብሎ እራሱ የከፋ አደጋ ውስጥ ይጥላል፣ የማያውቀውን ዓለም ናፍቆ ለሞት እራሱን ያጋልጣል፣ የነገሮችን መቀየር መታስ አቅቶት የገዛ ዓለሙን በጨለማ ይሞላል። ዛሬ ላይሆን ይችላል፣ አሁን የታሰበው ነገር ላይሳካ ይችላል፣ በዚህ ሰዓት የተፈለገው ለውጥ ላይመጣ ይችላል ነገር ግን አሁን አልሆነም ማለት ነገም አይሆንም ማለት አይደለም። እስካልቸኮላችሁ ድረስ አይናችሁ እያየ ብዙ ነገር ሲቀየር ትመለከታላችሁ። ለከፋው የህገወጥ ስደት፣ ማንነትን ለሚገድለው መጥፎ ሱስ፣ አንገት ለሚያስደፋው የበታችነትና ፍረሃት እራሳችሁን አሳልፋችሁ አትስጡ። ነፍስን ሸጦ የሚኖር ህይወት የለም። አስቡት ምናልባትም እናንተ ዛሬ እራሳችሁን የሰዋችሁለት ህይወት ውስጥ እናንተ አትኖሩም ይሆናል። እራስን ከማጣት የከፋ ወድቀት የትም የለም። ሰው ሆኖ ሰውነትን መርሳት፣ የተከበሩ ሆኖ እንደ ርካሽ መናኛ መታየት፣ ብርቱ ሆኖ እነተልፈሰፈሱ መኖር የምርም ቅስም ሰባሪና ተስፋ አስቆራጭ ነው። ነገር ግን ነገ ሌላ ቀን ነው። ዛሬ ያቀረቀረው አንገት ነገ ቀና ይላል፣ ዛሬ የተሰበረ ልብ ነገ ይጠቀናል።

አዎ! ጀግናዬ..! ምንም የሚቀየር ነገር የለም ብለህ ቶሎ ተስፋ አትቁረጥ። ታጋሽ ሰው በረዶ ውሃ ሲሆን ያያል። በነገሮች ጊዜያዊነት የሚያምን ሰውም ከክፉው ቀን ማግስት መልካሙን ቀን ለማየት ይበቃል። ፅኑ ልብ የማይሻገረው የህይወት ፈተና የለም፣ በአምላኩ ስራ የሚያምን ሰው በየትኛውም ውድቅ አይሰበርም። ማግኘትና ማጣት፣ ማትረፍና መክሰር፣ መውደቅና መነሳት የህይወት ተቃራኒ ገፆች ናቸው። ለረጅም ጊዜ ሲያተርፍ የኖረ ነጋዴ የሆነ ጊዜ ሊከስር ይችላል፣ እንዲሁ ደጋግሞ ሲከስር የነበረ ነጋዴም አንድ ቀን ከኪሳራው በላይ የሚያተርፍበት ቀን ይመጣለታል። ለብዙዎች ሀብታም መሆን ከባድ አይደለም፣ ሀብታም ሆኖ መቆየት ግን እጅግ ፈታኝ ነው። ምክንያቱም ምንም ቋሚ ነገር የለም። ምን እንዴትና መቼ መቀየር እንደሚችል አይታወቅም። በጊዜያዊ ስሜት አትረበሽ፣ በወቅታዊ ደረጃህ አትከፋ፣ አሁን ስለሆነብህ የከፋ ነገር ከልክ በላይ አትጨነቅ። ምንም ቋሚ ነገር በሌለበት ዓለም የእኔ ህይወት አይቀየርም ብለህ በፍፁም በራስህና በፈጣሪህ ተስፋ እንዳትቆርጥ።

#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
አንድ ዘፋኝ እና መምህር ጎረቤት ሆነው ይኖሩ ነበር

👇🏾

ከእለታት በአንዱ ቀን ዘፋኙ ወደ መምህሩ መጥቶ "ድንገት እግር ጥሎኝ ጎረቤቴ ቤት ስገባ ስለአንተ መጥፎ ነገር ሲወራ ሰማሁኝ:: ምን አይነት መጥፎ መምህር እንደሆንክ እና ልነግርህ የማልችላቸው ሌሎች አፀያፊ ነገሮች ሲይወሩ ነበር:: ይህ ጎረቤትህ ጠላትህ ነው" ሲል ይነግረዋል

መምህሩ በረጅሙ ተንፍሶ "አዎ ጠላቴ ነው" ብሎ ዝም አለ

**

በሌላ ቀን አርቲስቱ በድጋሚ ወደ መምህሩ መጥቶ "ዛሬ ደግሞ ሌላኛው ጎረቤቴ ግሮሰሪው ውስጥ ከሰዎች ጋር ሆኖ ስለ አንተ ባህርይ መጥፎ ሲያወራ ደረስኩኝ: የማይለው ነገር የለም በቃ:: ይህ ሰውዬ ጠላትህ ነው" ሲል ይነግረዋል

መምህሩም "አዎን ጠላቴ ነው: እስካሁን ሁለት ጠላቶች አሉኝ ማለት ነው" ሲል ይመልስለታል

**

በሌላ ቀን ደግሞ "መምህር ሆይ የዛሬውስ ይባስ! ጭራሽ የአንተ ወዳጅ የሆነ ሰው ስለአንተ ክፋት ሲያወራ ሰምቼ አላስቻለኝምና ልነግርህ መጣሁኝ:: ይህ ወዳጅህ ጠላትህ ነው:: ሶስት ጠላቶች አሉህ ማለት ነው" ሲል ይነግረዋል

መምህሩም ቀበል አድርጎ "ሶስት ጠላት ብቻ አይደለም ያለኝ: አራት ናቸው"

"እንዴ መምህር ሶስት እኮ ነው እኔ የነገርኩህ"

መምህሩ መለሰለት

👇🏾

"ራስህን መቁጠር ረስተሃል: አንተ አራተኛ ጠላቴ ነህ:: በቦታው ተገኝተህ ስለ እኔ አንዳችም አልተከራከርክም: የምታውቀኝን ያህል እንኳን ስሜን በክፉ እንዳይነሳ አላደረግክም:: እንደውም ከእነርሱ ይልቅ አንተ ጠላቴ ነህ"

ለምታውቁት እና ለምትወዱት ሰው ዘብ ቁሙ !!❤️🙌🏼


#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
ለውብ ቅዳሜ

📚እውነተኛ ነጻነት...

የሰው አዕምሮ በውሸትና በተጣመመ መረጃ ላይ እንደሚበላሽ በምንም አይበላሽም። በተለይ ውሸትን ስራዬ ብለው በራስ ወዳድነት ስሜት የሚረጩ ሰዎች፣ በክፉና በስግብግብ ውሸተኞች ኑሯቸው ፈርሷል፤ትዳራቸው ተበትኗል፤ ስንት ሥልጣኔዎችን ከጥቅም ውጪ አድርገዋል። አያሌ ጨቅላዎች በውሸት
በተመረዘ ንግግር እንጭጭ አእምሮአቸው ከንቱ ሆኖ ቀርቷል።

ዓለምን በአንደኛነት ያጠፋው ክፉ ሰዎች የዘሩት ውሸት ነው። የሰው ውድቀት የጀመረውም በውሸት ነው። እውነትን በትዕግሥትና በሰከነ ልቦና እንደ መልካም ዘር ካልፈለግናትና ካልተንከባከብናት፣ ውሸት እንደ አረም ከክፉ ሰዎች የልብ ዕርሻ ላይ እየተዛመተ መልካም ልቦችን ማጥፋቱና መውረሱ አይቀርም።

"እውነትን ታውቃላችሁ እውነትም ነጻ ያወጣችሁኋል" የሚለው የትልቁ መጽሐፍ ቃል እንዴት ያለ እውነት ነው? በዓለም ላይ ከሁሉ አስከፊው እስር ቤት የሰው አዕምሮ ባመነጨው ውሸት ሲፈጠርና በዚያ ቀንበር ውስጥ ሲኖር ነው።


እውነተኛ ነጻነት የኅሊና ነጻነት ነው። የኅሊና ነጻነት ደግሞ እውነትን በማወቅና በመኖር ነጻ ከወጣ አዕምሮ ብቻ የሚገኝ ፀጋ ነው።

የብዙ አዕምሮዎች መቆለፍና መዛጋት መንሥኤው፣ ባንድም በሌላም መንገድ ወደ ውስጣቸው የገባው ውሸትና ነጻ የሚያወጣቸውን እውነት አለማወቃቸው
የፈጠረው ገደል ነው። ከእውነት በፊትም ሆነ በላይ ለአእምሮ ጤንነትና ነጻነት ምን መድኅኒት ይገኛል? እውነትን ማወቅ ነጻ ቢያወጣም፣ እውነት ዋጋዋ እጅግ ውድ የሆነ መድኅኒት ናት።

📚የተቆለፈበት ቁልፍ መጽሐፍ 📚

#ውብ ቀን ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
⭐️ለምሺታችን ይሄን ተጋበዙልኝ🙏

ድንግል ሴት አምላክም መፍጠር አቁሟል እስከሚባል ደረጃ በደረስንበት በኛ ዘመን ማን እንዲህ ደፍሮ ይጽፋል ካለ ደራሲ አዳም ረታ በስተቀር።

አዳም ሆይ የት ነው ያልከው?!🤔

"……ሁሉ ሰው በእግዜር ዐይን እኩል እንደሆነ ማንም ይነግርሀል። ልክ አይደለም። በሰውም ሆነ በእግዜር አይን ሰዎች ሁሉ እኩል አይደሉም። ማባበያ ነው። ከአፈር ብንፈጠርም ሲመስለኝ ከተለያየ አፈር ነው። ሚስት ስታገባ ወንድ የማታውቅ አግባ። ሀብት ይኑራት አይኑራት አይደለም። መጠንቀቅ ያለብህ ለትዳር ድፍን ሴትን የመሰለ የለም። ለምን?' በለኝ ለምን? ማለት ጥሩ ነው። ድፍን ሴት ማለት ላይና ታቿ ልክ እንደ ሸንኮራ አገዳ የተዘጋ ነው። ውስጧ ምንም ያልሆነ መረቅ ነው። በማሕፀኗ ያለው አየር ክፋት ያልገባው ነው። ምድርና ሰማይ ሲፈጠር አዳምን ያቆመው፣ ከእግዜር ጋር የማገው አየር እዛ ነው ያለው። ዮሀንስ አፈወርቅ: የሀጢያት ምንፃፍ የማታውቅ ነውር የሌለባት ድንግል ሴት ክብር ናት። እንዲህ ያለችቱ ሴት ነፍሳት በጸጋና በክብር በተገኙበት ጊዜ ዋጋዋን ታገኛለቸ ይላል። በዘመኑ እኮ የበኩር ልጅ እየጠፋ ነው። ለምን ሀሞተ ቢስ ሆነ ዘመኑ? ለምን ደደብነት ይነካካዋል? ለምን ጅል እየበዛ ሄደ? ለምን ፈሪ ተትረፈረፈ? ሀሞት ቢኖረው አእምሮ፣ አእምሮ ቢኖረው ሀሞት ለምን ሙሉውን አጣ? የበኩር ልጅ ስላልሆነ ነወ። ሴቶች ዘመናዊ ትምህርት ለመማር ሲሉ ትዳር ለመመስረት ሲዘገዩ ዕድሜያቸው ሲገፋ አያስችላቸውምና ከወንድ ይገናኛሉ። ይሳሳታሉ፣ ከዚያ በተገኘው በዘመኑ ወይ በባሕል መድሀኒት ያስወርዳሉ። እንዲህ ካልሆነም ዘግይተው ያገባሉ። ትዳር ሲይዙም ማህፀናቸው ደንግጧልና እንደ ልጃገረድ ዘር አይበቅልም። ይሰንፋል። የበኩር ልጅ መጀመሪያ የተወለደ ወይም የተወለደች ማለት አይደለም። ቁጥር አይደለም። ያለ ድንግልና መበከር የለም። የዛች ዓይነት ሴትና ትንሽ ሀብት ደስታ ነው። ልጆችህ ጠንካራ ይሆናሉ። ከግዜር ጋር። ፍቅር የሁዋላ ጉዳይ ነው። ሲለማመዱ፣ ሲተሳሰቡ። ከሌላ ወንድ ጀምራ የመጣች ሴት አትሆንህም፣ ትዝታዋ ባልሆነ ጊዜ እየተነሳ ይረብሽሀል። ባሏ የሞተባት ሴት እማ ይብስባታል። ባትችልበትና ባይሆንልህ ባይሆንልህ ባልዋ ያሰቃያትን ምረጥ። ትዝታዋን ትፈራለች። እመርቅሀለሁ የበኩር ልጅ ይስጥህ ብዬ። ሌላም ሌላ ጉዳይ አለው እሱስ። ሌላው የራስህ አብራክ ሲጣፍጥህ ነው። ሰማህ? ሰማህ ልጄ? ማስተዋል የጎደለውን ወጣት ብስለት ከሌላቸው መሃል አገኘሁት ይላል ምሳሌ።

ምርቃቱ ትደርስህ ዘንድ ቢጠራህ
አቤት ቢልክህ ወዴት? ብለህ አባትህን አክብረው ይላል ሲራክ በምዕራፍ ሶስት።

አዳም ረታ _መረቅ #እውይይ

#ውብ ምሽት ይሁንልን💚💛❤️

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@Weygud18
https://youtube.com/@Weygud18

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄