ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
247K subscribers
290 photos
1 video
15 files
243 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
‹‹ኤርሚየስ››
‹‹ኤርሚያስ …እዚህ ጋር ታቆምልኝ..….?››
ዳር ያዝኩና አቆምኩላት…ወረደችና የመኪናዋን የኃላ ኮፈን ከፍታ ምንጣፍ በማውጣት አንድ ጠርሙስ ያልተከፈተ ውስኪ በመያዝ ከመኪናው እርቃ ወደአንድ ዘርፋፋ ቅርንጫፍ ወደተሸከመ ዛፍ ሄደችና ጥላው ባለበት አቅጣጫ ምንጣፍን አንጥፋ እንደቡዲስት መለኩሴ እግሮቾን አነባብራ  በመቀመጥ የጠርሙሱን ክዳኑን ተታግላ ከፈተችና አንዴ በመጎንጨት ወደ ፅሞናዋ ተመለሰች…..
እኔን  ልክ እንደ ግኡዙ  መኪናዋ ነበር የቆጠረችኝ… እስከመፈጠሬም እረስታኛለች…20 ለሚሆኑ ደቂቃዎች  ከመኪናው ሳልወርድ የተለያዩ ኤፍ. ኤም ጣቢያዎችን እየቀያየርኩ ሳረብሻት ለመቆየት ሞከርኩ… ከዛ በላይ ግን አልቻልኩም… መኪናውን ከፍቼ ወጣሁና በዝግታ እርምጃ ወደእሷ በመሄድ አንድ ሜትር ከእሷ ርቄ ከፊትለፊቷ  ሳር የለበሰ ሜዳ ላይ ቁጭ አልኩ……በሁለት ጉንጮቾ እንባዋ ያለምንም ድምጽ ትረጫዋለች….ደነገጥኩ…. ምን እንደምላትም ሊገለፅልኝ አልቻለም፡፡
‹-በህይወትህ መሞት ፈልገህ ግን ደግሞ እንዴት መሞት እንዳለብህ ግራ ገብቶህ ያውቃል….?፡፡››ስትል ጠየቀችኝ 

‹‹ብዙ ጊዜ አዎ…….?››መለስኩላት

‹‹እና እንዴት አደረግክ….?››

‹‹ቆይ ዛሬ…ቆይ ነገ…በገመድ ተንጠልጥዬ ብሞት ይሻላል ወይስ መድሀኒት ልጋት……….?ከፎቅ ላይ እራሴን ልፈጥፍጥ ወይስ የሚበር መኪና ውስጥ እራሴን ወርውሬ ይጨፍልቀኝ….? ብዬ ሳማርጥ በአንዱ መወሰን አቅቶኝ ስዋልል ቆይና ሁለት የምወዳቸው ሰዎች ወደአዕምሮዬ ሲመጡ ደግሞ እስኪ ቢያንስ ለእነሱ ስል  ብዬ  እታገሳለሁ..ከዛ ቀስ በቀስ ያ ስሜት ይጠፋል ወይም ይደበዝዛል…ቢያንስ ለጊዜውም ቢሆን ››
‹‹ለሁለት ሰዎች ስትል….?››


            ይቀጥላል

#ክፍል 53,,እንዲለቀቀ 👍(5) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
📕ታምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ሶስት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ



‹‹አዎ…እናቴ እና ሰላም ያልኩሽ የማፈቅራት ልጅ ትዝ ሲሉኝ››
-‹‹በዛ ሰዓት ላይ ሁለቱም ባይኖሩ ኖሮ…..መቼም እንዳማታገኛቸው እርግጠኛ ሆነህ ቢሆን ኖሮስ….?››ዘግናኝ ጥያቄ ጠየቀችኝ

‹‹እኔ እንጃ…እንዳልሞት የሚያደርገኝ ምንም ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም››ስል በታማኝነት መለስኩላት፡፡

‹‹ለምን….?››ጠየቀችኝ
‹‹ሁለቱ መላ አለሜ ናቸው…እነዚህ የነገርኩሽ ሁለቱ ሴቶች እና ሌላው ዓለም እኔንም ጨምሮ በሌላ ሚዛን ቢሆን ሚዛን ሚደፉት እነሱ ናቸው…..ስለዚህ እነሱ  የሌሉበት  ዓለም ምን ይረባኛል…››

‹‹አየህ ትክክል ብለሀል..እኔ አሁን ያለሁበት ሁኔታ አንተ አንደገለጽከው ነው…እስከአሁን እራሱ ለምን እንደቆየሁ አላውቅም…….?››ብላ የሆነ አዲስ ነገር እንደተገለጽላት ተመራማሪ  ፈገግ ብላ ከተቀመጠችበት  ተነሳች ‹‹ እንሂድ ›› ብላ ጠርሙሷን ይዛ ምንጣፉን ባለበት ጥለ መራመድ ጀመረች…

-‹‹እንዴ ወዴት….? ››

‹‹ወደቤት ….ወደቤት መልሰኝ››

ደነገጥኩ…. ሳላስበው የማይሆን ነገር እንደተናገርኩ ገባኝ…ገደል አፋፍ ላይ ያለን ሰው ከኃላ መግፋት አይነት የቀሺም ሰው ተግባር ነው የሰራሁት..

‹‹ምንጣፉስ..››

ግዴለሽ በሆነ የድምፅ ቃና‹‹ከፈለከው ያዘው›› አለችኝ፡፡ጠቅለል ጠቅለል አደረኩና ወስጄ ኮፈን ውስጥ ከተትኩት፡፡ከዛ ወደመኪናው ገባሁና ወደኃላ አዙሬ የመልስ ጉዞ ….ብራዩ እንደደረስን የሆነ ነገር ማድረግና አሁን ካለችበት ስሜት እንድትዘናጋ ማድረግ እንዳለብኝ   ወሰንኩ…

‹‹..በጣም አመመኝ..››አልኳት …ቀና ብላ አየችኝና ምንም ሳትናገር መልሳ ወደ ሃሳቧ ተመለሰች…..መኪናዋን ወደዳር አውጥቼ አቆምኩ

‹‹ምነው….?››ኮስተር ብላ

‹‹ሆዴን ቆረጠኝ ››

‹‹ማለት….?››

‹‹እኔ እንጃ እራበኝ መሰለኝ..ከነጋ ምንም አልቀመስኩም… ለዛ ይሆናል..ረሀብ ደግሞ አልችልም››

‹‹እና ምን ይሻላል ….?››አለች እንደመበሳጨት ብላ

‹‹በቃ እኔ ሳልበላ መንዳት አልችልም….››

‹‹እሺ ጥሩ  ቁልፉን ስጠኝ…. እኔ ጊዜ ማባከን አልፈልግም …አንተ ብላና በትራንስፖርት ና››የሚል ሀሳብ አቀረበች

‹‹ለምን የሚሆን ጊዜ ነው ማባካን የማትፈልጊው….?››ስል ጠየቅኳት፡፡

‹‹እቤት ተመልሼ በፍጥነት ማድረግ ያለብኝ ነገር አለ››

‹‹እሺ ነይ…አልኩና ቁልፉን ነቅዬ ከመኪናው ወረድኩ.. እሷም ካለችበተ የኋላ ወንበር ወርዳ ወደጋቢናው ስታመራ ፈጠን ብዬ ሁሉንም በር ጠረቀምኩትና ቁልፍን እያንቀጫጨልኩ   በአካባቢው ወደአለ ሆቴል ጉዞ ጀመርኩ

‹‹ምን እያደረክ ነው….?››

‹‹ምሳ በልቼ እቤትሽ አደርስሻለሁ..አንቺ ስለጠጣሽ መንዳት አትችይም…››

‹‹ምኑ ነህ..….?አሁን ለአንድ ቀን ባትበላ አትሞት…ደግሞ ብትሞትስ ከመኖር ምን ሲገኝ…››

‹‹ግድ የለም.. ልብላና አብሬሽ እሞታለሁ››

‹‹መቀለድህ  ነው..….?››ተከተለችኝና ከፊት ለፊቴ ወንበር ስባ ተቀመጠች…ምግብ አዘዝኩ እስኪመጣ ወሬ ጀመርን 
‹‹በነገራችን ላይ አባትሽን በቅርብ አይቼው አላውቅም..?››

‹‹የለም››

‹‹የት ሄዱ….?››

‹‹ወደ ውጭ ሄዷል››

‹‹አሀ …ለዛ ነዋ እንዲህ ዓለም ድብልቅልቅ ያለችብሽ….?››

‹‹እንዴት እንዲህ ልትል ቻልክ….?››

‹‹በአባትሽ እና በአንቺ መካከል ያለውን ግንኙነት እና ቀረቤታ እኮ ሙሉ ሰፈሩ ነው የሚያውቀው.. እንኳን እኔ ቀርቶ የዛሬ አመት እዛ ሰፍር የገባ ሰው ሳይቀር ያውቃል…››

‹‹አንዴ አንተም እኛ ሰፈር በቅርብ የገባህ መስሎኝ….  ባልሳሳት ሁለት  አመት ..ከዛ ይበልጥሀል..?››

‹‹የእውነትሽን ነው..አታውቂኝም….?›› በእድሜዬ  ከደነገጥኩት በበለጠ መጠን ደንግጬና ተሸማቅቄ ጠየኳት

‹‹ማለት አንተ ታውቀኛለህ እንዴ….?››

……የምመልሰው ነገር ሲጠፋኝ  ሳቅኩ

‹‹የሚያስቅ ነገር ተናገርኩ እንዴ…››

‹‹አይ ታውቀኛለህ ስትይ ገርሞኝ ነው….ራስህን ታውቃለህ ወይ ብለሽ ብትጠይቂኝ ይሻላል..ግንባርሽ ላይ ያለውን ስንጥቅ ጠባሳ ምን እንደሆነ ልንገርሽ…….?››

‹‹እንዴት ልትነግረኝ ትችላለህ..….?

እሱ እኮ እፃን ሆኜ የሆነ ነገር ነው››

‹‹አዎ ቄስ ትምህርት ቤት አባ ገብረክርስቶስ ጋር ስንማር ድብብቆሽ በምንጫወትበት ጊዜ ልትደበቂ ስትሮጪ  አደናቅፎች ወድቀሽ ብረት ግንባርሽን ሰንጥቆሽ አይደል…?››

አይኖቾ ፈጠጡ ‹‹እንዴ !!!አዎ ትክክል ነህ ..ማነህ አንተ….?..››

‹‹ኤርሚያስ››

‹‹ኤርሚያስ ..ኤርሚያስ እንዴ ኤርሚያስ ካሳ እንዳትሆን……….?››የሆነ የቆየ ህልም የማስታወስ ያህል ተደንቃ

‹‹አዎ ነኝ››

‹‹ታዲያ በጣም እኮ ነው የተቀያየርከው…አረጀህ… በጣም…ደግሞ ከሀገር  ወጥተህ አልነበር…..….?››

‹‹ኦዋ ሁለት  ዓመት አለፈኝ  ተመልሼ   ከመጣሁ..››

‹‹እና ይሄን ሁሉ ጊዜ   ሳታናግረኝ…….?››

‹‹እኔ እንጃ እንደመጣው ጥሩ ስሜት ላይ ስላልነበርኩ ላናግርሽ ጉልበቱ አልነበረኝም….››

‹‹ትክክል አልሰራህም…ጓደኛች ነበርን አይደል….….?.››መገረሟ ሳይገታ የታዘዘው ምግብ መጣ..እሷ ለምግቡ  ደንታም ሳይሰጣት ብላክ ሌብል ታመጣልኝ አለችው አስተናጋጁን….

‹‹አይቻልም..››አልኳት ቆፈጠን ብዬ
‹‹ለምን…….?ዝም በለውና አምጣልኝ ››አምጣላት …ግን ከበላሽ ነው የምትጠጪው..

‹‹አረ ባክህ ››

‹‹እውነቴን ነው››

‹‹እሺ ..››አለች.. እየቆነጠረች ከምግቡ ለመቅመስ ሞከረች እኔ እየለመንኩም እያስገደድኩም አንድ ሶስት ደህና ጉርሻ አጎረስኳት…
ከዛ መጠጧን ጀመረች ‹‹….ይገርማል  ..ዱርዬ ነበርክ እኮ …አሁን የተለየ እና የተረጋጋ ሰው ሆነሀል››

‹‹ምን ታደርጊዋለሽ ህይወት ትገራሻለች… ኑሮ ይሞርድሻል…መከራ ያስተካክልሻል ወይም ያበላሽሻል፡፡››

‹‹ለምን አንተም አትጠጣም….?››

‹‹ጥሩ ሀሳብ ነው..ግን መኪናውን ማን ይነዳል…….?››

‹‹ግድ የለም ..የሆነ መላ እንፈልጋለን..….?››ልክ ቅድም ላንቺ ታዝዤ አብሬሽ መጠጣት እንደጀመርኩ ..ለእሷም ተስማምቼ አዘዝኩ …የልጅነት ነገር ምንም ሳይነሳ የቀረ ትውስታ የለም..ከማስበው በላይ ስለልጅነታችን ታስታውሳለች…ያ ደግሞ ደስታ ፈጠረብኝ….እሷም ከነበረችበት ስሜት በሆነ ጠብታ ቢሆንም የመረጋጋት ሁኔታ  ታየባት
ተመልሰን ቅድም ለቀነው ወደወጣነው ቤት የሄድን
 
‹‹እየተቆነጠረ የሚመጣው ውስኪ ሊያረካን ስላልቻለ..ሙሉውን አዘዝን…››

ኬድሮን ቆይ ቆይ ..››ብላ አስቋመችው 

‹‹ምነው ደከመሽ..እንተኛ?››

‹‹አይ አንዴ ሽንቴን….›› አለችና ከመኝታዋ ወርዳ ወደሽንት ቤት ሳይሆን ወደሳሎን ሄደች….ይህቺ ታሪኳ ለሊቱን ሙሉ የተነገረላት  ፍቅረኛው የሆነ ችግር ላይ እንደሆነች እየተሰማት ነው ..አዎ ስሜቷ እየነገራት ነው….ለዚህ ነው ወደሳሎን የሄደችው …ንስሯን ፈልጋ..‹‹አይ የኔ ነገር ..››አለች . የዚህ ባለ ላዳ ታሪክ ንስሯንም እንድትዘናጋ ስላደረጋት እራሷን ታዘበች…ሳሎን ሶፋ ላይ ኩርምት እንዳለ ተኝቷል….አስነሳችው….‹‹ ‹‹አብሮኝ ያለው ልጅ ፍቅረኛ..ማለቴ የሚወዳት ልጅ ችግር ላይ ትመስለኛለች..አሁኑኑ ሄደህ ያለችበትን ሁኔታ አጣራልኝና  ና…አሁኑኑ……ትንሽ ከዘገየን የሚረፍድብን ይመስለኛ…››
ነቃ ለማለት እዲረዳው  ክንፉን አርገፈገፈ …..የሳሎኑን በር ከፈተችለት… ከሶፋው ላይ ተንሳፎ ጭንቅላቷ ላይ አረፈ…ክንፉን እያማታ ከጭንቅላቷ ላይ ተነስቶ በሩን አልፎ ጭለማ ውስጥ ሰመጠ…..
ወደመኝታ ቤቷ ተመለሰችና  ወደአልጋው ሳይሆን  ወደ  ሻወር ቤት ገባች …

ሻወር ቤት ገብታ ሽንቷን ብቻ ሸንታ አልወጣችም..የሻወሩን ውሀ ከፈተችና ልብሷን አወላልቃ ገባችበት….አዎ በሆነ መንገድ መረጋጋት ፈልጋለች……. ‹‹ምንድነው ያጣሁት ነገር…….?.ከሁለት የተለያዩ  ፍጥሮች መፈጠሬ ስለፍቅር ያለኝን ስሜት አበላሽቶብኛል እንዴ….….?ለምንድነው እኔስ መላኩ  ሰሚራን ባፈቀረበት መጠን ላፈቅር  ማልችለው..….?ለምንድነው ይሄ አልጋዬ ላይ ሆኖ የሚጠብቀኝ ኤርምያስ ሰላምን ባፈቀራት መጠን በዚህ የህይወቴ ረጂም ጊዜ ሁሉ ቢያንስ ለአንድ ጊዜ እንኳን  ማፍቀር ያልቻልኩት….….?››በአዕምሮዋ እያተረማመሱ ያሉ ጥያቄዎች ነበሩ….

ውሃው ከላይ እየተወረወረ ሰውነቷ ላይ እያረፈ ነው..ዝም ብላ ቆማ በሀሳብ ውስጥ እየነሆለለች ነው….አሁን እነሱ ታሪካቸውን ለማንም ሰው ቢናገሩ ሰሚው ሰው ውስጡ በሀዘን ይተረማመሳል..እንባ አውጥቶም ሊያለቅስ እና  በዛም  መጠን ሊያዝንላቸው ይችላል…እሷ ግን ቀናችባቸው እንጂ ልታዝንላቸው አልቻለችም …ለምን በዚህ መጠን የማፍቀር ስሜት ከውስጧ መብቀል አቃተው…….?እንዴት ሰው በህይወት ዘመኑ ቢያንስ አንዴ በፍቅር ፍላፃ ልብ አይሰነጣጠቅም….?እንዴት በእድሜው አንዴ እንኳን በፍቅር እቅፍ አጥቶና ምቾት ነስቶት ሲነፈርቅ አይታይም…….?ለፍቅር መሸነፍ እኮ ድክመት አይደለም ሰዋዊነት እንጂ…..እሷ የወሲብ ረሀብ ያንን ተከትሎ የጭን መብላት አባዜ ብቻ ነው የሚያሰቃያት….ሙላት ያለው የፍቅር   ስሜት ሳታጣጥም ይህችን ምድር ልትለቅ አራት ቀን ቀራት ..!!!አራት ቀን ብቻ…

ይቀጥላል።

አብዛኞቻቹ ወይም ባጠቃላይ ማለት ይቻላል የአገልግሎት ክፍያ እየከፈላቹ አደለም ክፍያውም አንብባቹ ስትጨርሱ👇👇👇

#ክፍል 54,,እንዲለቀቀ 👍(15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Today's Combo...🚫
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_አራት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


የንስሯ ጭንቅላቷ ላይ ማረፍ ነበር ከእንቅልፏ ያባነናት….በመከራ አይኗን ገልጣ ዙሪያዋን ስትቃኝ እራሷን  እዛው ቅድም የተዘረረችበት ወለል ላይ እርቃኗን አገኘችው….ባለ ላደውም የሞተ እስኪመስል ድረስ ትንፋሹ ጠፍቶ እግሮቾ  መካከል ጭንቅላቱን ቀብሮ በተመሳሳይ እርቃኑን ተዘርሯል ….ቀስ ብላ ከላዮ ላይ ገልበጥ  አደረገችውና እና እራሷን በማላቀቅ  ሾልካ ወደ ሻወር በመሄድ ለ5 ደቅቃ ውሃ በላይዋ ላይ አፈሰሰችና..
ከዛ ወደመኝታ  ቤቷ ተመልሳ ቢጃማ ለበሰችና ባለ ላዳውን እንደምንም እየጎተተችም እየደገፈችውም ወስዳ አልጋው ላይ በማስተኛት ብርድልብስ ካለበስችው በኋላ ወደሳሎን አመራች…..ንስሯም ተከተላት..፡፡
አዎ ሊነጋ  መሆኑን ከውጭ የሚሰማውን የወፎች  ዝማሬ በማዳመጥ ተረዳች …ሳሎኖ እንደደረሰች ተስተካክላ ከተቀመጠች በኋላ ንስሯ ያየውን  እንዲያሳየት… ያወቀውን እንዲያሳውቃት አዕምሮዋን ከእሱ ጋ አቆራኘችው…
ሰላምና አባቷ…ፍቅራቸው ከአባትና ከልጅም የዘለል አይነት ነው..ኤርምያስ እንዳለው እናትም አባትም ወንድምም እህትም ሆነው ነው ያሳደጎት…ግን አሁን ስላለችበት ሁኔታ ብቻ ያለውን ታሪክ ከንስሯ በተረዳችው የሚከተለውን ነው
ቀጥታ ቤታቸው ገባች… መኝታ ቤት ወደመሰላት ክፍል ተጓዘች… አዎ ትክክል ነች ያልተነጠፈ እና የተዝረከረከ አልጋ … አልጋው ላይ የተዘረረች ውብ ለጋ  ሀዘን የሰበራት ወጣት ተኝታለች…..ወለሉ ጠቅላላ በመጠጥ ጠርሙሶች እና በተበታተኑት ልብሶች ተሞልቷል..አንድ ግዙፍ  አራት መአዘን  ፍሪጅ አልጋውን ተደግፎ   ይታያል…ትኩረቷን ወደፍሪጁ አመዘነበት… ውስጡን አየችው… .ህልም ውስጥ ነኝ እንዴ ያስብላል… …ነጭ ሱፍ ለብሶ ነጭ ሸሚዝና ቀይ ከረባት ያደረገ  እንቅልፍ የተኛ የሚመስል ሰው ፍሪጅ ውስጥ ይታያል.. ..አባቷ ነው ….የሰላም አባት..አሁን የሆነ ነገር የገባት ነው..ልጅቷ እንደጠረጠረችውም  አደጋ ላይ ነች…ሰላም አባቷን አጥታለች..ሰላም አባቷን መሬት ውስጥ ቀብራ ለዘላላም ለመለየት ድፍረቱንም ጭካኔውንም ለማግኘት አልቻለችም….
/////
ነገሩን በዝርዝር ለመረዳት  አምስት ቀን ወደኃላ እንመለስ 
እንደማንኛውም ቀን እየተጎራረሱ እራት በሉ…እያተሳሳቁ ዜናና ፊልም አዩ…አራት ሰዓት አካባቢ ወደመኝታቸው አመሩ….ሰላም አባቷን መኝታ ቤት አስገብታ እንዲተኙ ካደረገች  በኃላ ግንባራቸውን ስማ ተሰናብታ ወደመኝታዋ ልትሄድ ስትል

‹‹ሰላሜ››ሲሉ ጠሯት

‹‹አቤት አባ›››

‹‹አብረሺኝ ተኚ››
ዘላ አልጋው ላይ ወጣችን ብድርብሱን ገልጣ ከውስጥ በመግባት እቅፋቸው ውስጥ ገባች…..ይህ አዲስ ነገር አይደለም..ተለያይተው ከሚተኙበት ይልቅ አንድ ላይ የሚተኙባቸው ቀናቶች የበዙ ነበሩ..ሁለቱም ትንሽ ሲከፋቸው ወይንም አመም ሲያደርጋቸው..ወይንም እንዲሁ ለብቻ መተኛት ሲደብራቸው ዛሬ እኔ ጋር ትተኚ..?ዛሬ አብረሀኝ ትተኛ..? እየተባባሉ አንድ ቀን እሷ ክፍል አንድ ቀን እሳቸው ክፍል ይተኛሉ..እና የተለመደ ነው፡፡
ችግሩ ንጊ ላይ ከእንቅልፏ ባና ከእቅፋቸው ስትወጣ ነበር የተፈጠረው….እጃቸውን ከሰውነቷ ላይ ሳታነሳ በተለየ ሁኔታ ቀዘቀዛት…..ቀስ ብለ ወጣችና አየቻቸው..ጸጥ ያለ ፊት ነበር..ዝም ያለ ፊት…እጇን ወደ አንገታቸው ላከች ….ትንፋሽ አልባ ሆነዋል..

‹‹አባዬ ..አባዬ›› ወዘወዘቻቸው…ጮኸች……..ወደመኝታ ቤቷ  በሩጫ ሄደችና የልብ ማዳመጫ መሳሪዋን አመጣች…ምንም  የለም..?…ጮኸች…ሁሉ ነገር ረፍዶ ነበር..ፀሀይ በጠለቀችበት ቀርታ ነበር…ጨረቃ በደመናው ሙሉ በሙሉ ተሸንፋ ከስማ ነበር…ምጽአት ደርሶ  ነጋሪት እየተጎሰመ እና መለከት እየተነፋ ነበር…..
አባቷ እርግጥ ህመም ላይ ከነበሩ ወራት አልፏቸዋል….ግን እየተንከባከበቻቸው እና በትክክል የህክምና ክትትል እያደረገችላቸው ነበረ…ምንም የተለየ እና ለሞት የሚያሰጋ ምልክት አልተመለከተችም….የት ጋር ነው የተሸወደችው…..?ማወቅ አልቻለችም…፡፡ ለሳዕታት እሬሳውን ላይ ተኝታ ስትነፈርቅ ቆየች…ስልክ ደውላ ለወዳጆቾ ልትናገር ፈለገችና መደወል ከጀመረች በኃላ መልሳ ተወችው

‹‹አባቴን ልቀብር…..?አባቴንም ፈጽሞ አልቀብርም…….ለሳዕታት ካሰበች በኃላ ወሰነች‹‹..አብሬው እሞታለሁ..ግን ለመሞት እስክቆርጥ ድረስ እሱም አይቀበርም›› አለችና…ባላት የህክምና እውቀት በመጠቀም ሬሳው እንዳይበሰብስ አድርጋ በባለመስታወት ፍሪጅ ውስጥ በማድረግ መኝታ ቤት ውስጥ ሬሳውን ደብቃ አስቀመጠች….እና ይሄ ነው የሚያስጨንቃት…እና በዚህ ጊዜ ነበር ኤርምያስ ላዳ ውስጥ የገባችው….ይሄን ችግር ነበር እሱ ሊያውቅና ሊረዳላት ያልቻለው…..በዚህ ከቀጠለች  በጥቂት ቀናት ውስጥ ወይ አዕምሮዋ ተነክቶ ጨርቋን ጥላ ይለይላታል ወይንም እዛው መኝታ ቤት ውስጥ እራሷን አጥፍታ ከአባቷ ጋር ወደመቃብር ትጓዛለች..ከሁለቱ የተለየ የነገ ዕጣ ፋንታ የላትም….
ንስሯ ይዞላት የመጣው ታሪክ ይሄ ነው..በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው…‹‹እና እንዴት ልረዳት እችላለሁ…...?›ስትል እራሷን ጠየቀች፡መቼስ ምንም  ተአምረኛ ብትሆን ከሞተ  አራት ቀን የሆነው እና በፍሪጅ ውስጥ በቅዝቃዜ የደረቀ ሬሳን  ህይወቱን ካሄደችበት መልሳ በማዋሀድ ነፍስ  ልትዘራበት አትችልም…ይሄ የማይቻል ነው… ቢሆንም ቢያንስ ልጅቷ የአባቷን ሞት አምና እንድትቀበል እና እንድትቀብረው…ከዛም እንድትጽናና የሚያስችል አንድ ዘዴ መዘየድ እንዳለባት ተሰማት…አዎ ያንን ማድረግ ትፈልጋለች…
ሀሳቧን ሰብስባ ውሳኔ ላይ ሳትደርስ በፊት የሳሎኗ  በራፍ ተንኳኳ..ግራ ገባት …በዚህ ጥዋት ማን ነው የሚያንኳኳው .. ..?ገና አንድ ሰዓት እንኳን አልሆነም፡፡

‹‹…ማነው..?››ከተቀመጠችበት ሳትነሳ

‹‹እኔ ነኝ ..››

የፕሮፌሰር ድምጽ ነው..ተነሳችና ከፈተችላቸው‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..በጥዋት እንዴት ተነሱ..?››

‹‹አረ ጨርሶውኑም አልተኛሁም…ከሰው ጋር ስለሆንሽ ነው እንጂ  ለሊቱን አብሬሽ ስጫወት ማደር ነበር የፈለግኩት››

‹‹ምነው በሰላም..?››

‹‹እኔ እንጃ ብቻ  ትናፍቂኛለሽ…ከፍቶኛል››

‹‹እንዴ ፕሮፌሰር..እስቲ ግቡ››

‹‹አሁን አልገባም.. በኋላ ግን እፈልግሻልሁ››

‹‹ለምን አይገቡም..?››

‹‹አይ አሁን እንግዳ ይፈልግሻል››

‹‹ማንን እኔን....?››ግራ ገብቷት 

‹‹አዎ አንቺን››ብለው ከበራፍ ላይ ገለል ሲሉ ከጀርባቸው በአዕምሮዋ ውስጥም የሌለ ሰው ብቅ አለ…አንድ ጥቁር ሻንጣ በእጁ አንጠልጥሎ አንገቱን ደፍቶ ቋማል..ፕሮፌሰሩ  ወደክፍላቸው ተመለሱ….

‹‹እንዴ መላኩ ..ምነው ሰላም አይደለህም እንዴ....?ሰሚራን አመማት እንዴ..?››

‹‹አረ እሷስ ደህና ነች››

‹‹ታዲያ ምነው በለሊት....?››እስቲ ግባ ብላ ወደውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ አደረገችው…

‹‹ምን ሆንክ..?››ፊት ለፊቱ ቆማ በገረሜታ እያየቸችው ዳግመኛ የመጣበትን ምክንያት ጠየቀችው፡፡

‹‹ምን ያልሆንኩት ነገር አለ..አሸንፈሻል …ሰሚርን አስመርምሬያታለሁ..ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ሆናለች..››

‹‹አሪፍ ነዋ .ታዲያ ደስ አላለህም..?››

‹‹አዎ ብሎኛል…››
‹‹እና ታዲያ አሁን ለምን መጣህ..?››

‹‹ስምምነታችንን ላከብር ነዋ..በሶስት ቀን ውስጥ ትተሀት ካልመጣህ ብለሽ ፎክረሻ አድራሻሽን ሰጥተሸኝ ነበር  እኮ..የሆነ ነገር ለማድረግ ኃይል እንዳለሽ አሳይተሸኛል…እንቢ ብዬ በዛው ብቀር ደግሞ ፍቅሬን  መልሰሽ በሽተኛ ብታደርጊብኝስ..?››
ሳቋ አመለጣት ..ከፊት ለፊቱ ቁጭ አለች……

‹‹ይሄውልህ…››ብላ የውስጧን ልትግረው ስትጀምር ባለ ላዳው ማለት ኤርሚያስ ሆዬ ከመኝታ ቤት ውልቅልቁ የወጣውን ሰውነቱን እየጎተተ ሳሎን ደረሰና ግራ በመጋባትና በድንጋጤ አንዴ እሱን አንዴ እሷን እያየ  ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ በመጋባት ሲዋልል እሷንም ንግግሯን እንድታቆርጥ አደረገት ….

     ይቀጥላል።

አብዛኞቻቹ ወይም ባጠቃላይ ማለት ይቻላል የአገልግሎት ክፍያ እየከፈላቹ አደለም ክፍያውም አንብባቹ ስትጨርሱ👇👇👇

#ክፍል 55,,እንዲለቀቀ 👍(15) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Today's Combo...🚫
Today's Combo...🚫
😎ተአምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_አምስት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

‹‹ልሄድ ነበር››አላት ሚለው ጠፍቶት..አንዴ ኬድሮንን  አንዴ ከፊት ለፊቴ የተቀመጠውን መላኩን እያየ

‹‹አይ መኝታ ቤት ተመልሰህ ትጠብቀኝ..አብረን ነው ምንወጣው››

ግር አለው‹‹ይቅርታ አልሰማሁሽም..?››

‹‹እሱን ልሸኝና እመጣለሁ …መኝታ ቤት ተመልሰህ ጠብቀኝ…››

ባለማመን ወደኋላው ዞረና.. ወደመኝታ ቤት ተመለሰ

ከመላኩ ፊት ላይ ግራ የመጋባት  ጥያቄ  ስላነበበች‹‹ባለቤቴ ነው..?›› አለችና  ሳይጠይቃት መለሰችለት….

‹‹እንዴ….ባለቤቴ…ታዲያ እኔን…....?››

‹‹እኔ ለቀልድ ነበር እደዛ ያልኩህ ..የእውነት ታዳርገዋለህ አላልኩም ነበር…..››ከተቀመጠበት ተነስቶ ተንደርድሮ ጉንጯን እያገላባጠ ሞጨሞጫት

‹‹በእውነት በጣም ነው ደስ ያለኝ…በቃ ሁለቴ ህይወት ሰጥተሸኝል….ሰሚርን  አዳንሺልኝ አሁን ደግሞ ነፃነቴን ስትሰጪኝ››

‹‹አይ ግድ የለም››አለችና ከእቅፉ እየወጣች…ጭምቅ አርጎ ሲያቅፈትና ሲስማት መተንፈስ አቅቶት ነበር…በቃ በሽታዋ ሁሉ ሊነሳባት እና ሀሳቧን ልትቀይር ትንሽ  ነበር የቀራት….. 

እንደመደንገጥ አለና ወደመኝታ ቤቱ ገልመጥ በማለት ሲስማት ማንም እንዳላየው ለማጣራት ሲሞክር በቆረጣ አይታ ለራሷ ፈገግ አለች   ..‹‹በቃ ልሂድ.. ሌላ ቀን ከሰሚር ጋር መጥተን እንጠይቅሻለን ….በቃ ዘመድ እንሆናለን..››እያለ ይዞ የመጣውን ሻንጣ ይዞ ለመሄድ አንጠልጠሎ ተዘጋጀ፡፡

‹‹ሰላም በልልኝ..ግን እኔን ለመጠየቅ አትልፉ.. ዛሬ ለሊት ወደውጭ ልበር ነው….››ስትል ዋሸችው

‹‹ዉይ !!!ምነው?በሰላም..?››እንደመደንገጥ ብሎ፡፡

‹‹አይ በሰላም ነው …ቤተሰብ እዛ ስለሆነ እዛ ለመኖር ነው››

‹‹እሺ በቃ እግዜር ካንቺ ጋር ይሁን …ዕድሜ ልክ ከፍዬ የማልጨርሰው ውለታሽ አለብኝ ››እያለ ሳሎኑን ባለማመን  ለቆ ወጣ……

‹‹ምን ያህል መስዋዕትነት እንደከፈልኩልህ ብታውቃው..ባንተ ምክንያት ይህቺን አለምና ንስሬንም ጭምር እንደአጣሁ ብትሰማ›› ስትል አሰበች

….ይህን ሁሉ ልትነግረው ያልፈለገችው ቢያንስ በስተመጨረሻ ጥሩ ልሁንለት ብላ ነው ….በፀፀት ያልደፈረሰ የፍቅር ህይወት ይገባዋል ብላ ስላሰበች ነው….አሁን  የእነሱን ሰሚራ ለማዳን የሆነችውን እና  ያጣችውን ዘርዝራ ባታወራው ከማዘን በስተቀር ለእሷ ምንም አይፈይድላትም..በእሱ ህይወት ላይ ግን ቁጭትን ይፈጥርበታል…..ደስታው ላይ ደመና ያጠላል…. ያንን አስባ ነው እውነቱን የደበቀችው፡፡
/////

ሀሳቧን ሰብስባ ቀጥታ ወደመኝታ ቤቴ ሄደች…. ስትደርስ ባዶ ነው..ግራ ገባት….‹‹ እንዴ በጓሮ በር ሾልኮ ፈረጠጠ እንዴ..? ››ብላ ሳታሰላስል ከሻወር ቤት የውሃ መንሾሾት ድምጽ ሰማችና ወደ እዛው ሄደች..ደረሰችና ብርግድ አድርጋ  ከፈተችው…. ድንገት መሳሪያ እንደተደቀነበት ምርኮኛ ኩም ብሎ ደነገጠ..እጆቹን የተንዘላዘለ እንትኑ ላይ ሸፈናቸው….
‹‹አረ ልቀቀው ..ለሊቱን  እስክጠግብ እኮ ሳየው ነው ያደርኩት››

‹‹እብድ ነሽ..አስደነገጥሸኝ እኮ …››አለና ቀስበቀስ ለቀቀው
‹‹ህፃን ሆነህ እናትህ በቂቤ በደንብ ያሹልህ እና ይጎትቱልህ ነበር እንዴ..? ›› 

‹‹‹ምን እንዲሆን ነው የምትጎትትልኝ..?››

‹‹እንዲህ እንዲንጀላጀል ነዋ….ሜትር ከምናምን እንዲሆንልህ››

‹‹ትቀልጂያለሽ..ቆይ ማን ነበር ሰውዬው… ውሽማሽ መስሎኝ እኮ ተበላሁ ብዬ ነበር››

‹‹አይደለም ዘመዴ ነው…እንዴት ነው እኔም አወላልቄ ልግባ እንዴ..?››

‹‹ወዴት....?››

‹‹ወደሻወር ነዋ..እጠበኝ ልጠብህ››

‹‹ኸረ በፈጠረሽ..ስወደሽ እንዳታደርጊው››

ሳቋ አመለጠት‹‹እንዴ !!ይሄን ያህል…...?››

‹‹እንዴ…እሳት እኮ ነሽ…እኔ እንጃ የዛሬ ወር ድረስ ተከፍቶ ባገኝ እንኳን ለመክደን አልሞክርም…እንዴት እንዴት አይነት የወሲብ ጥብብ ነው..የሆነ ህልም ውስጥ እኮ ነው ያስገባሺኝ..በአየር ላይ ሁሉ እየተንሳፈፍኩ ይመስለኛል…አሁን ሳስበው ደግሞ እንዴት በአየር ላይ መንሳፈፍ ይቻላል እላለው....?ከግድግዳ ጋር ግን እዳጣበቅሺኝ በእርግጠኝነት አውቃለሁ..ግን አጥንቶቼ ስብርባራቸው ለምን እንዳልወጣ እንቆቅልሽ ነው የሆነብኝ…ብቻ ግራ ተጋብቻለሁ.፡፡እኔ በህይወት ፍቅር እንጂ ያጣሁት የወሲብ ችግር ገጥሞኝ አያውቅም….ቁጥራቸውን ከማላስታውሳቸው ሴቶች ጋር ወሲብ ፈጽሜያለሁ..በአንድ ለሊት ስድስት ሰባቴ …ግን ከንቺ ጋር ያደረኩት አንድ ዙር ወሲብ እድሜ ልኬን ከደረኩት ጋር የማይነፃፀር እና የተለየ ነው››

‹‹ወሲብ ደጋግመን የምፈፅመው ለምን እንደሆነ ታውቃልህ..?››

‹‹እኔ እንጃ››

‹‹እኔ ግን ስገምት ..ለኮፍ ለኮፍ ከሆነ ወዲያው ወዲያው ያምርሀል…በሁለት ደቂቃ በራፍ ላይ ደፍቶ ተልኮውን የሚያጠናቅቅ  ሰውና በ20  ደቂቃ  ውስጠ ውስጥ በርብሮ ግዳጁን ያጠናቀቀ እኩል መልሶ አያሰኛቸውም….ለዛ ነው ››
‹‹ይሁንልሽ ››አለና የሻወሩን ውሃ ዘግቶ… ፎጣውን አገለደመና ከሻወሩ ቤት ወጣ …ተከተለችውና አልጋው ጠርዝ ላይ ቁጭ አለች፡፡

‹‹እሺ ቁርስ ትጋብዘኛለህ አይደል..?››አለቸው

‹‹አንቺን ለመሰለች ቆንጆ እንኳን ቁርስ አራሴንስ ብጋብዝሽ ቅር አይለኝም..››

‹‹እራስህንማ  እንዴት ልትጋብዘኝ ትችላለህ…..?››

‹‹ለምን አልችልም..?››ሲል ጠየቃት  ኮስተር ብሎ

‹‹እኔ ልቡን ለሌላ ሰው ጠቅልሎ ያስረከበና ቀፎውን ብቻ ያለ ሰው ምን ያደርግልኛል…....?››

‹‹አይ የምታወሪው ስለ ሰላም ከሆነ ተስፋ  ቆርጬያለሁ….አሁን የምፈለገው ምን እንደሆነች ብቻ አውቄ ልረዳት ነው…ያንን ማድረግ  ከቻልኩ ይበቃኛል…ካዛ….››

‹‹ከዛ ምን…..?››

‹‹እኔ እንጃ… የላዳ ሹፌር ነው ብለሽ ካልናቅሺኝ በጣም ነው ያፈቀርኩሽ..?››

‹‹ያፈቀርኩሽ ስትል..?››
‹‹ያፈቀርኩሽ ነዋ..በጣም ነው የተመቸሺኝ ….የሆነ የማላውቀውን አለም ነው ያሳየሺኝ…ላጣሽ አልፈልግም….››

‹‹ስለእኔ ምንም እኮ አታውቅም....?››

‹‹ማወቅ አልፈልግም..አንቺ ብቻ እሺ በይኝ እንጂ…..››ንግግሩን ሳይጨርስ ንስሯ እየበረረ የመኝታ ቤቱን በር በርግዶ  በመግባት  እንደቀናተኛ አባ ወራ አልጋ ላይ ተኮፍሶ  ጉብ አለ….

ይሄንን በድንገት ያየው ባለ ላዳው ከተቀመጠበት በርግጎ ወድቆ ነበር..

‹‹አይዞህ አይዞህ…›››ሳቋ እያመለጣት
‹‹አይዞህ….!!›

‹‹የማታው ንስር አይደል..?››

‹‹አዎ ነው››

‹‹ምን ይሰራል  እዚህ..?››
‹‹እዚህ ምን ትሰራለህ ..?ብሎ መጠየቅ ያለበት እሱ ነው..ምክንያም እሱ የገዛ ቤት ውስጥ ነው ያለው››

‹‹ማታ የእኔ ነው ያልሺው እወነትሽን ነው እንዴ..?››

‹‹አይ የእኔ አይደለም..እኔ ነኝ የእሱ….››

‹‹እኔ እንጃ ግራ ይገባል..››እያለ ልብሱን መልበስ ጀመረ……..
‹‹ሰላምን እንድትረዳት ልናግዝህ እንችላለን››አልኩት  

‹‹ልናግዝህ ስትይ....?አንቺና ማን..?››

‹‹እኔና ንስሬ››

ፈገግ አለ….‹‹ትቀልጂብኛለሽ አይደል..?››

‹‹የምሬን ነው…›

‹‹አንቺ እሺ ይሁን …ይሄ እንስሳ እንዴት አድርጎ ነው የሚረዳኝ..ደግሞስ አንቺስ ብትሆኚ በምን መልኩ ልትረጀኝ ትችያለሽ .. ..?እኔ እንኳን ገና ችግሯን  ማወቅ አልቻልኩም››
‹‹እኔ ግን  አውቄያለሁ››
ሱሪውን ለብሶ ከላይ እራቃኑን እንደሆነ አጠገቡ ያለ ወንበር ላይ ቁጭ አለ‹‹እንዴት ልታውቂ ቻልሽ…..?እንኳን የእሷን  ታሪክ ይቅርና እኔን  ካወቅሽ እራሱ 24 ሰኣት አልሞላውም››
‹‹የፈለኩትን ነገር ማወቅ እችላለሁ…ንስሬ ከረዳኝ የፈለኩትን ነገር….››

‹‹አላምንሽም››

‹‹እሺ ጥቂት ደቅቃ ታገሰኝ ››አልኩና ወዲየው ትኩረቴን ወደንሰሬ በመመለስ ከአዕመሮው ጋር ተቆራኘው…..ለሶስት ደቆቃ ከቆየሁ በኃላ

‹‹እሺ ስማኝ …እንድታምነኝ አንተ ብቻ የምታውቀውን የራስህን ሚስጥር ነግራሀለው….ደቡብ አፍሪካ ለ2 ወር ታስረህ ነበር….ከሶስት ሴቶችና ከእንድ ተካልኝ ከሚባል ልጅ ጋር በደባልነት አንድ  ቤት ውስጥ ትኖሩ ነበር…ከሶስቱ ሴቶች  መካከል  ሁለቱን ሴቶች ታወጣቸው ነበር…..››

‹‹በቃ በቃ…..››

‹‹ያው እንድታምን ብዬ ነው…..››
‹‹አመንኩ እኮ …አደገኛ ጠንቆይ ነሽ….ምክንቱም ይሄንን ታሪኬን ለማንም ተናግሬ አላውቅም ..በተለይ የሁለቱ ሴቶችን ጋር ያለኝን ግንኝነት››

‹‹ምክንያቱም መንታ እህትአማቾች ስለሆኑ ትክክለኛ ስራ እንዳልሰራህ ስለሚሰማህ እና ፀፀት ስላለብህ..››ብላ ጨመረችለት፡፡

‹‹አዎ..ትክክል ነሽ…ግን አሁን ሰላም ምንድነው ችግሯ..ከፍቅረኛዋ ጋር ተጣልታ ነው…..?››

‹‹ፍቅረኛ የላትም….ማለቴ በፊት  ነበራት… ከተለያዩ ግን  አመት አልፏቸዋል…እረስታዋለች››

ፈገግ አለ‹‹ይሄንን በመስማቴ ደስ አለኝ….እሺ ሌላ ታዲያ ምን ሆና ነው…..? ስራ ተበላሽቶባት ነው..?››
‹‹ያለችበትን ችግር ምትገምተው አይደለም..››

‹‹እሺ ንገሪኛ..? ››

‹‹አባቷ ሞቶባት  ነው..››

መጀመሪያ ተደናግጦ ከተቀመጠበት ተነሳ..ከዛ መልሶ ቁጭ አለ..ለደቂቃ ተከዘ

‹‹እስከአሁን ያልሺው ሁሉ ትክክል ነው..ይሄ ግን የማይመስል ነው..አልነገርኩሽም እንዴ አንድ ሰፈር እኮ ነው የምንኖረው ..ዕድራችንም አንድ ነው….ቢያንስ እኔ ባልሰማ እናቴ ሰምታ ትነግረኝ ነበር..በዛ ላይ   እሷን የሀዘን ልብስ ለብሳ አያት ነበር ….››
‹‹አባቷ እንዲቀበሩባት ስለማትፈልግ ..መኝታ ቤቷ ውስጥ እንዳይበሰብሱ በማድረግ  ድብቃቸዋለች››

‹‹እንዴ!!!! ታዲያ ዝም ትያለሽ እንዴ....?እራሷን ብታጠፋስ....?ይሄንን ሁሉ ቀን የአባቷን እሬሳ ታቅፋ ለብቻዋ ስታድር ጄኒ ቢያጠናግራስ .. ..?እንዴ በቃ ብታብድስ…..?››ይሄን ሁሉ ሚናገረው በጥድፊያ ልብሱን እየለበሰና በተመሳሳይ ጊዜ ወደውጭ እየተንደረደረ ነው….እሷም ከኃላው  ኩስ ኩስ እያለች   ሚለውን ታዳምጣለች…

‹‹እውነት ከሆነ በጣም ነው የማዝንብሽ…..እንዳወቅሽ ልትነግሪኝ ይገባ ነበር…አንድም ሰከንድ ማባከን አልነበረብሽም ..አባቷን እንዴት እንደነፍሷ እንደምትወዳቸው ብታውቂ እንደዚህ ቸልተኛ አትሆኚም ነበር….››ወቀሳውን ሳያቆርጥ ከግቢው ወጥቶ በእግሩ ሊነካ ሲል…

‹‹ና በመኪና ላድርስህ….››ስትለው በደመነፍስ ተከተላትና ማጉረምረሙን ሳያቆርጥ  መኪና ውስጥ ገባ….ሞተሩን እስነስታ መንዳት ጀመረች..ፀጉሩን ይነጫል ….ጨንቅላቱን ይቀጠቅጣል..ከንፈሩን ይነክሳል
‹‹እንዲህ ከሆንክማ እንዴት ልንረዳት እንችላልን....?››አለችውት የእሱም ከቁጥጥር ውጭ መሆን አሳስቧት

‹‹እንዴት ልሁን ታዲያ …..?ሳለምዬ የአባቷን ሬሳ ታቅፋ አምስት ቀን ብቻዋን ባዶ ዝግ ቤት ውስጥ አድራለች እያልሺኝ እኮ ነው…››

‹‹እኮ አሁን ካለችበት ሁኔታ ይልቅ ወደፊት የሚከሰተው ነገር ይበልጥ ይጎዳታል… ስለዚህ እንዴት ልንረዳ እንደምንችል ለማሰብ ያንተ መረጋጋት ያስፈልጋል እያልኩህ ነው››

‹‹እሺ ንጂው…በእግዚያብሄር ፍጠኚ …ደግሞ ንስርሽ ከኃላ እየተከተለን ነው››

‹‹አዎ እሱ በጣም ያግዘናል…››

‹‹በፈጠረሽ …ምንም ነገር እንድትሆንብኝ እልፈልግም›››

‹‹አይዞህ…. ምንም አትሆንብህም…››

ከ25 ደቂቃ በኃላ ሳሪስ ደረሱ ..መኪናውን አቁመው ወደበራፍ  በመከተታል ተንደርደረው ደረሱ... ንስሯ ቀድሞ ግቢው ውስጥ ገባ..መጥሪያውን ተጫኑ..ደጋግመው  ተጫኑ…. እጃችን እስኪዝል በየተራ አንኳኩ ..ከውስጥ ከፋች ሊመጣ አልቻለም..

‹‹ትግስቴ አልቆል…  የግንቡን አጥር ዘለዬ  ልገባ ነው….››አላት በጭንቀት 

‹‹ግንቡ ላይ የተሰካውን የጠርሙስ ስብርባሪ እንዴት አድርገህ ታልፈዋለህ..?››

‹‹የራሱ ጉዳይ…የቆራረጠኝን ያህል ይቁረጠኝ… ››

‹‹ቆይ የተሻለ ዘዴ አለኝ ››አለችው
‹‹ምንድነው....?››

ንስሯን ጠራችው … ከገባበት ግቢ እየተመዝገዘገ መጣና  የፈለገችውን ሳትነግረው በመረዳት የለበሰችውን ልብስ አንገቷ አካባቢ በመንቁሯ ይዞ እያሽከረከረ ወደአየር ላይ ይዞት በመውጣት አጥሩን አሻግሮ ጊቤው ውስጥ ወለል ላይ አሳረፈት…  ከውስጥ የተቀረቀረውን በራፍ  ከፈተችለት…ኤርምያስ ተንደርድሮ ገባ..

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው....?ምንድነሽ አንቺ..?›› እያለ ገፍትሯት ወደሳሎን ሮጠ… ሊያንኳኳ ሲሞክር ብርግድ ብሎ ተከፈተለት..ተከትላው ገባች..ወደየት እንደሚሄድ ግራ ገብቶት ሲደነጋገር ቀደመችውና ወደመኝታ ቤቱ አመራች..ምክንያቱም ቅድም ንስሯ በምናብ  እቤቱን በደንብ ስላስቃኛት ስለነበር  ታውቀዋለች..፡፡

መኝታ ቤት ሲገቡ …ሰላም ወለል ላይ ተዘርራ ግንባሯን ግዙፉ ፍሪጅ ላይ እስደግፋ በአንድ  እጇ የመጠጥ ጠርሙስ ጨብጣ በሌላ እጇ  የተለኮሰ ሲጋራ  ወደ ከንፈሯ በመላክ ወደውስጥ እየመጠጠች  ጭሱን  ወደውጭ እያትጎለጎለች  ትታያለች  …ከጎኖ 10 ሜትር የሚሆን የተጠቀለለ ሰማያዊ ሲባጎ ገመድ ይታያል….. ኤርምያስ ከእሷ ቀድሞ እሷንም ተራምዶ ወደፍሪጁ ሄደና ውስጡ ያለውን አየ…….

ወደኬድሮን በመዞር  ‹‹…እውነትሽን ነው…..››በማለት ከወገቡ ሽብርክ ብሎ ሰላም ጎን ወላሉ ላይ ተዘረፈጠ..እሷ በቃ ትንኝም በአካባቢዋ ያለ አልመሰላትም.. ፍጽም ደንዝዛለች…ጭርሱኑ ጠፍታለች…..


     ይቀጥላል።

አብዛኞቻቹ ወይም ባጠቃላይ ማለት ይቻላል የአገልግሎት ክፍያ እየከፈላቹ አደለም ክፍያውም አንብባቹ ስትጨርሱ👇👇👇

#ክፍል 56,,እንዲለቀቀ 👍(20) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Live stream finished (3 minutes)
#HAMSTER KOMBAT #COMBO ♨️

Upgrade 📤
"GameFi tokens"
"Margin trading x30"
"Trading bots"

After Upgrading This Cards You will GET 5 MILLIOM HAMSTER♻️

Dont Forget To like and Share This #post With your #Friends To Let them know the Combo❤️‍🔥

Click Here to Start Hamster🐹

Click Here For Tapswap♋️

Other Channel📮

#HamsterKombat #Tapswap #Airdrop
#Friday
14 June 2024
📕ተአምራተ_ኬድሮን

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ስድስት

#በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ

ወደቀልቧ እስክትመለስ እና መኝታ ቤቷ ውስጥ ያልጋበዘቻችው ሰዎች እንደገቡ ለመገንዘብ ከአንድ ሰዓት በላይ ወሰደባት ….

‹‹እንዴት ብትደፍረኝ ነው ግን ሰተት ብለህ መኝታ ቤቴ ድረስ  ሚስትህን ይዘህ የገባኸው……?.›

ኤርሚያስ ግራ ተጋባ … ተርበተበተ……‹‹ይቅርታ..ማለት ሚስቴ አይደለችም…. አላውቃትም..ይቅርታ ማለቴ አውቃታለሁ ግን ይሄውልሽ እሷ….››
አቋረጠችው ‹‹…ውጣልኝ …ውጡልኝ..››ጭንቅላቷን በእጆቾ ይዛ ጩኸቷን ለቀቀችው….

‹‹እሺ እንወጣለን..አንቺ ብቻ ተረጋጊ… እንወጣለን…ይሄው እየወጣን ነው…››የሚያደርገው ጠፍቶት ክፍሉን ለቆ ለመውጣት ወደበራፉ ፊቱን አዞረ…

ኬድሮን‹‹አባትሽን ላገናኝሽ ነው የመጣሁት››አለቻት

ከተቀመጠችበት ወንበር ንቅንቅ ሳትልል
ከትከት ብላ ሳቀች..የምፀት ሳቅ…..የእብደት ሳቀ..የንዴት ሳቅ

‹‹እንዴት አድርገሽ ነው ከሞተው አባቴ ጋር ምታገናኚኝ….…?ነው ወይስ ከበድኑ ነው ልታገኛኚኝ ያሰብሺው…..አመሰግናለሁ በድኑ በእጄ ስለሆነ አትልፊ  ….››

‹‹አይ እዲያናግርሽ ማድረግ እችላለሁ››

‹‹እንዲያናግረሽ አልሽ…..ኤርሚያስ ምን በድዬሀልው..…?››አለችው ወደእሱ ዞራ

እየተርበተበተ‹‹..ሰላም አንቺ ምን በወጣሽ.. አረ ምንም አልበደልሺኝም  …ለምን እንደዛ ልትይ ቻልሽ…?››

‹‹እንዴ ያንተ ሳያንስ ሌላ ሰው ይዘህ መጥተህ እድታሾፍብኝ ታደርጋለህ……?በሀዘኔ እንዴት ታላግጣላችሁ….…?በቁስሌ እንዴት ጨው ትነሰንሳላችሁ…?ይሄ ምን አይነት ጭካኔ ነው …?…››

‹‹አረ በፍፅም እንደዛ አይደለም….አንቺን ለመርዳት እንጂ ሌላ ምንም አላማ የለንም››

‹‹እና ታዲያ እንዴት ነው ከአባቴ የምታገናኘኝ……?.››

‹‹እሱን አንዴት እንደሆነ አላውቅም ..ግን ታደርገዋለች ››አለ አንዴ ኬድሮንን አንዴ ሰላምን በማፈራረቅ እያየ
ልታስረዳት ሞከረች‹‹እመኚኝ  የሙት መንፈስ ማናገር እና ከሚወዶቸው ሰዎች  ጋር የማገናኘት ችሎታ አለኝ…መቼስ ስለዚህ ጉዳይ ሰምተሸ አታውቂም  ለማለት አቸገራለው….››

‹‹ሰምቼማ አውቃለው..በመጽሀፍ ቅዱስ ላይም አንብቤያው..ግን ..››>

‹‹ምንም ግን የለም…››ብላ ንስሯን እንዲመጣ በአዕምሮዬ መልዕክት አስተላለፍችለት ….. ክንፉን እየማታ መጣና  አልፎን ፈሪጁ ላይ ጉብ  ሲል  ሰላም  በድንጋጤ ተንደርድራ ልትሰፍርበት ስትል ቦታ ቀየረና አመለጣት….

‹‹አባቴን ..አግዙኝ…. አባቴን አንዳይነካብኝ››

‹‹አይዞሽ የእኔ ንስር ነው ..ምንም አያደርግም…››

‹‹እርግጠኛ ነሽ ……?አባቴን አይነካውም…?››አለች… በእሷ ግምት የኬድሮን ንስር  የአባቷን በድን አካል ለመዘንጠል ይዳዳል ብላ ነው

‹‹እንዴ ንስር የሞተ ነገር እንደማይነካ አታውቂም…››

‹‹አላውቅም››አለች

‹‹እኔም አላውቅም ››በማለት ድጋፍ ሰጣት  ኤልያስ

ማብራሪያዬን በኩራት ቀጠልኩ ‹‹ንስር ኩሩ ነው…እራሱ አባሮ… እራሱ ታግሎ …እራሱ ገድሎ ካልሆነ ነክች አያደርግም…ለማንኛውም አሁን ተዘጋጂ ቁጭ በይ ››….ቁጭ አለች…
‹‹ይሄሁልሽ አሁን ንስሬ ያግዘኝና ከአባትሽ መንፈስ ጋር አገናኝሻለሁ...ማለት የእኔን አንደበት ተጠቅመው አባትሽ ቀጥታ ያናግሩሻል..በእኔ አንደበት በራሳቸው ድምፅ››

‹‹እሺ››

‹‹ኤርምያስ አንተ ደግሞ ካለህበት እንዳትነቃነቅ..ምንም የሚረብሽ ነገር ካለ ትኩረቴን ስለሚበታን መሀል ላይ ግንኙነቱ ሊቋረጥ ይችላል››

‹‹አረ በፍጽም ይሄው ንቅንቅ አልልም..ትንፋሼ እራሱ አይሰማም››አለና በተቀመጠበት ጭብጥብጥ አለ

ሁሉም ነገር ዝግጁ መሆኑን ሳታረጋግጥ አዕምሮዋን ከንሰሯ ጋር አገናኘቸው..ለደቂቃዎች ተመሰጠች …ይሄን ነገር ከዚህ በፊት አድርጋው አታውቅም ‹‹..ግን ማድረግ አያቅተኝም›ስትል በራሷ ተማመነች….አዎ ንስሯ የአባቷን ነፍስ ካለችበት እንድትመጠ እየጋበዘ  ነው..ወይ ብዙም አላስቸገራትም ….ቀጥታ አባትዬው በኬድሮን አንደበት ልጃቸውን ማናገር ጀመሩ……

‹‹ልጄ ሰላሜ…››

ባለማመን መለሰች‹‹ወይ አባዬ..››ተንደርድራ ሬሳውን እያየች
‹‹እዛ ለምን ትፍልጊኛለሽ….…?አይ ልጄ ስጋዬ ውስጥ አይደለሁም.. …ግን ደግሞ ወደዘላለም ማረፊያዬም መሄድ አልቻልኩም..ከሁለቱም ሳልሆን በአየር ላይ ተንጠልጥዬ አለሁልሽ፡፡

‹‹ምነው አባዬ……? እኔ ልሰቃይልህ…..እኔ በአየር ላይ ለዘላለም ተንጠልጥዬ ልቅር››

‹‹አይ ለምን ልጄ…? ለምን..…?ለአንቺማ ይሄ አይገባም…ትቼሽ ስለሄድኩ ይቅርታ ልጄ..ምን ላድርግ የአማላክ ጥሪ ነው….እባክሽ ልጄ ከዚህ በላይ እንድሰቃይ አታድርጊኝ…››

‹‹እንዴ አባዬ እኔ አንተን ማሰቃየት…?››

‹‹አዎ እናቴ… እዚህ እቤቴ ውስጥ በድን አካሌን ታቅፈሽ እንደዚህ ሆነሽ እንዴት እፎይ ብዬ ወደዘላለም የሚወስደኝን  መንገዴን እቀጥላለሁ..…?አልችልም ልጄ ..አካሌ መሬት ሳይገባ ነፍሴ ወደአምላኮ ልትሄድ ይከብዳታል..ልጄ እባክሽ በአምላክ  ስራ ጣልቃ አትግቢ..››

‹‹እንዴት አባ……? እንዴት ጣልቃ ገባሁ……?.››

‹‹እንዴ ሞትን የፈጠረውን አምላክ  እኮ እየተቃወምሽው ነው..ተሳስተሀል እያልሺው ነው››

‹‹አዎ ተሳስቷልማ..እንዴት አንድ አባቴን ይነጥቀኛል..…?እንዴት ባዶዬን ያስቀረኛል….…?.››

‹‹አየሽ ልጄ …ሞት እርግጥ በጥፋታችን ምክንያት የተሸለምነው ቅጣታችን ነው…ይሁን እና በዚህ ምድር ለመኖር እስከመጣን  ድረስ   ሞታችንም በጣም አስፈላጊ ነው..››

‹‹እንዴት አባ .. …?ሞት ደግሞ እንዴት ነው ጠቃሚ የሚሆነው.?››

እግዜር ፈጥሮ ምድር ላይ ቢረሳንስ ምን ይውጠናል….…?አርጅተን መንቀሳቀስ አቅቶን እቤት እስክንቀር…. ቆዳችን እስኪጨማደድ እና  ወበታችን እስኪረግፍ ድረስ አልወስዳችሁም ቢለን ማነው የሚጎዳው……?.ጥርሳችን ረግፎ ገንፎ እንኳን  ማኘክ እስኪያቅተን ቢተወን …አይናችን ለግሞ  የልጅ ልጆቻችንን ከጎረቤቶቻችን ልጆች መለየት እስኪያቅተን ..መኝታ ቤታችን ከሽንት ቤታችን መለየት እስኪሳነን ድረስ ኑሩ ብንባል ሽልማት ነው ቅጣት…ዕርግማን ነው ምርቃት…?››

‹‹እንዴ አባዬ.. …!!!አንተ እኮ ገና ነህ …ሰባ አመት እንኳን አልሆነህም..…?››

‹‹እኮ እግዚያብሄር ይወደኛል ማለት ነዋ..…?ምላሴ ጣዕም መለየት ሳይሳነው፤አይኖቼ ማንበብ ሳያቆሙ ፤እግሮቼ ላምሸው ከዘራ ሳልይዘ አስታወሶኛል…››

‹‹ግን እኮ አባ እኔን ጥለህ ነው የሄድከው…?››

‹‹የሞት መጥፎው ክፍል ያ ነው….አዎ ሁልግዜ የሆነ ነገር ጥለሽ መሄድሽ አይቀርም…ማንም ቢሆን ከዚህ ምድር ሲሰናበት የሆነ ነገር በጅምር ጥሎ መሄዱ የሆነ የሚወደውን ሰው ሳይሰናበት ማምለጡ ያለ እና ግዳጅም ነው….እና ልጄ አንቺ አፈር ካላቀመሺኝ እና በሀዘን መቆራመድሽን እስካላቆምሽ ድረስ ጉዞዬን መጀመር አልችልም… ብጀምርም ቶሎ አልደርስም..ሀዘንሸ ወደኃላ ይስበኛል….ለቅሶሽ  መንገዴን እያጨቀየው ያዳልጠኝ እና አላላውስ ይለኛል…..››

‹‹አባ አረ እኔ እንዲህ የበደልኩህ አልመሰለኝም…?››

‹‹በደልሺኝ እኮ አላልኩም.. ግን  በቃ..አንዳንዴ መሆን ያለበት ነገር እንዲሆን መተው ነው..ታግለሽ ልታሸኝፊው ከማትችይው ነገር ጋር መታገል  ከድካም ውጭ እርባን ያለው ውጤት አያስገኝም ››

‹‹እና ምን ላድርግ አባ…?››
‹‹በቃ አልቅሰሽ ቅበሪኝ….ከዛ በኃላ ሞተ የእያንዳንዱ ሰው ዕጣ ፋንታ መሆኑን አምነሽ ተቀበይና ወደ ህይወትሽ ተመለሺ…የራስሺኝ ሰው ፈልገሽ ኑሮሽን  ኑሪ….የእኔ በድን ታቅፈሽ እዚህ ቤት ባሳለፍሽው ስድስት ቀናት ውስጥ ስራ ላይ ብትሆኚ ኖሮ ሰንት ነፍስ  እንደምታታርፊ አስበሽዋል….… ?ስንት ያንቺን ክትትል የሚፈልጉ ህመምተኞችን እርግፍ አድረግሽ በመተውሽ  በያሉበት ምን ያህል እየተሰቃዩ እንደሆኑ ታውቂያለሽ….…?ያባትሽን መንፈስ ለዘላለም ለማስደሰት እውነታውን ተቀብለሽ  ፈገግ በይ ..በእኔ ስም የአዛውንቶችን ጤንነት ተንከባከቢ…እኔን እያሰብሽ ሞያሽን በጥንቃቄ እና በታማኝነት ስሪ..እያንዳንዱ ሰው ባንቺ እጅ ታከሞ በመዳኑ ተደስቶ ፈገግ ሲል  እኔም ባለሁበት  ፈገግ እንዳልኩ በማሰብ ውስጥሽ ሀሴት ታድርግ….›.

‹‹አዎ አባ እውነትህን ነው..እንዳልከው አደርጋለሁ››

‹‹ስለዚህ ተስማምተናል››

‹‹አዎ አባ ..ተስማምተናል››

‹‹በቃ ደህና ሁኚ ልሄድ ነው

‹‹አባ ከመሄድህ በፊት ››

‹‹እሺ ምንድነው…?››

‹‹ግን ገነት ነው ምትገባው አይደል…?››

‹‹አይ ልጄ..መች ሄድኩና አውቀዋለሁ ..ግን ምንም አይት ፍራቻ እየተሰማኝ አይደለም….እረፍትና እፎይታ ነው ዙሪያዬን የከበበኝ….የሚታየኝ  አንፀባራቂ ብርሀን እንጂ ፅልመት አይደለም….እና ፈጥኜ የመሄድ ፍላጎት ነው ያለኝ…ባከሽ ልጄ እንድዘገይ አታድርጊኝ..››

‹‹እሺ አባ ..አንድ የመጨረሻ ጥያቄ››

‹‹ምን ልጄ…?››

‹‹እማዬን ታገኛታለህ…?››

‹‹አዎ ልጄ ተስፍ አደርጋለሁ..በጣም መቸኮሌ አንድም ለዛ ይመስለኛል››

‹‹እንደምወዳትና በጣምም እንደናፈቀቺኝ ንገርልኝ››

‹‹እሺ ነገርልሻለሁ››
ደግሞ ቀኔ ደርሶ ወደእናንተ  ስመጣ ከእናንተ ጋር አብሬያችሁ መኖር ነው የምፈልገው››

‹‹እሺ ልጄ  እንዳልሽ…ደህና ሁኚልኝ…››

‹‹እሺ አባ ደህና ሁን››

     ይቀጥላል።

#ክፍል 57,,እንዲለቀቀ 👍(20) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
❇️ተአምረተ_ኬድሮነ

#ተከታታይ ልቦለድ

#ክፍል_ሃምሳ_ሰባት

በዘሪሁን_ገመቹ_ዋቤ


ቫይብሬት ላይ የተደረገ ሞባይል ስልክ ላይ ሲደወል እንዳለ ንዝረት ተንቀጠቀጥችና አዕምሮዋን ከንስሯ ጋር አላቀቀች…
ሰላም ወደኬድሮን ተንደርድራ መጥታ እግሯ ሰር ድፍት አለችና‹‹በጣም አመሰግናለሁ….እግዜር ይስጥሽ››

‹‹ተነሺ ..እኔን አታመስግኚ…እሱ በጣም ስለለመነኝ ነው እንዲህ ያደረኩልሽ…››አለቻት

‹‹ኤርሚ እግዜር ይስጥልኝ….አንተንም በጣም  ነው የማመስግንህ..ምን አይነት ሰላም በውስጤ እንደተሰራጨ አትገምትም››አለች ወደመቀመጫዋ ተመልሳ በመቀመጥ

‹‹በነጋራችን ላይ በጣም ነው የሚያፈቅርሽ …እንደነገረኝ ከሆነ ከልጅነቱ ጀምሮ አንቺን ሲያፈቅርሽ ነው የኖረው….አንድም ቀን አንቺን ማፍቀር አቁሞ አያውቅም..ግን በኑሮ ደራጃ ስለምትለያዩ እሺ አትለኝም የሚል ፍራቻ በውስጡ ስላለ  ካንቺ ሲሸሽ ነው የኖረው››አፈረጠችለት

ባለማመን አንዴ ኬድሮንን አንዴ እሱን በማፈራረቅ ማየት ጀመረች..ኤርምያስም የተቀመጠበት ወንበር ላይ አንገቱን ወደወለሉ እንደደፋ ሚገባበት ጠፍቶታል እጆቹን እያፍተለተለ ነው…

‹‹አላውቅም ነበር…ኤርምያስ እኔን ማፍቀር….…?››

‹‹አዎ….ኤርምያስ አንቺን…››

‹‹እሺ ጥሩ ነው…አሁን ምን እናደርግ …ኤርሚ እርዳኝ ለእድር ሰዎች ንገራቸው…አባቴ ዛሬውኑ እንዲቀበር እፈልጋለሁ….››

‹‹አረ እሺ… ችግር የለውም… አሁኑኑ ነግሬያቸው ልምጣ …ስልካቸውን ስለማላውቅ እናቴ ጋር ሂጄ …››ብሎ ተነሳ 

ኬድሮን የተለየ ሀሳብ አመጣች‹‹ቆይ መጀመሪያ የሬሳ ሳጥን እንግዛና አባትሽኝ  በሳጥኑ ውስጥ በማድረግ  ማዘጋጀት አለመብን..አሁን ዕድርተኛው መጥተው ጓደኞቸው ተሰብስበው እንገንዝ ማለታቸው አይቀርም …እንደዛ ከሆነ ደግሞ ሌላ ሀሚት ላይ ይጥልሻል…በህግም ሊያስጠረጥርሽ ይችላል››

‹‹ታዲያ ምን እናድርግ››አለች ግራ ገብቷትና ያለሳበችውን ነገር ስላነሳው ደንግጣ

‹‹ግድ የለም እኔና ኤርሚ ሳጥኑን ይዘን እንምጣ..ሁሉንም ከጨረስን  ብኃላ ለሌላው ሰው እንናገራለን….››

‹‹አስቸገርኮችሁ አይደል…?›› 

‹አረ አትጨነቂ …እኔን እንደእህትሽ ቁጠሪኝ… ኤሪሚም  ያው ያንቺው ነው..››አለችና ምትናገረው ጠፍቷት በመቁለጭለጨ ላይ ሳለች የደነዘዘውን ኤርሚያስን ይዛው ወጣች…

መኪናው ውስጥ ገብተን የሬሳ ሳጥን ወደሚሸጥበት ቦታ  እያመሩ ሳለ…

‹‹ምን አይነት ተአምር ነው ያደረግሽው……?.››ሲል ጠየቀት

‹‹ያው ላንተ ስል ነው››

‹‹በጣም ነው የማመሰግንሽ….ግን  እንደማፈቅራት ለእሷ ባትነግሪያት ጥሩ ነበር››

‹‹ለምን…?››

‹‹ያው አንደኛ መንገሩ ምንም ውጤት አይኖረውም ሁለተኛ እኔ እና አንቺ……››

‹‹አይ እኔና አንቺ የሚባል ነገር የለም…አኔን እርሳኝ…እኔ ሁለት ቀን ብቻ ነው የቀረኝ..››

‹‹ምን ለመሆን…?››

‹‹ለመብረር…››

‹‹እንዴ የት አሜሪካ ወይስ አውሮፓ……?››

‹‹በለው ከሁለት አንዱ….ስለዚህ እሷኑ ጠበቅ አድርግ.ደግሞ በትክክል ይሳካልሀል….

እንደምታፈቅራት ስነግራት የልቧን ምት በደንብ ታዝቤያለሁ. ዋናው ከዚህ ሀዘን እስክትወጣ ከስሯ አትለይ …….

‹‹እንዴ ወዴት ነው የምለየው….ከእሷ የሚበልጥ ምን ሌላ ጉዳይ ይኖረኛል››

‹‹ምንም ››

‹‹አንቺ ልትበሪ መሆንሽን መስማቴ  ግን ቅር አሰኝቶኛል››

‹‹እኔን እርሳኝ አልኩህ እኮ››

‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ልርሳሽ…?››
/////

የሰላምን አባት የቀብር ሁኔታ ካመቻቸችና ከተጠናቀቀ በኃላ ሁለቱንም አንድ ላይ ከለቀስተኞች ጋር ጥላቸው እናም በውስጧ ለመጨረሻ ጊዜ ተሰናብታቸው መልካሙን ሁሉ እየተመኘችላቸው ወደቤቷ ነው የተመለሰችው…ድክምክም ብሏት ነበር…ግቢውን አስከፍታ ስትገባ ግን ድካሟን ሁሉ ከላዮ የሚያበንላት አስደሳች ሁኔታ ነው የጠበቃት…

ግቢው መሀል ላይ ባለች ክፍት ቦታ ጠራጴዛ እና ወንበር ወጥቷል፤…ጠረጵዛው በልዩ ሌዩ ምግቦችና መጠጦች ተሞልቷል …ከዛ አልፎ ዙሪያው በየጥጋጥጉና በየቦታው የዛፍ ቅርንጫፎች ላይም ሳይቀር የተለያዩ የምግብና የፍራፍሬ አይነቶች ተቀምጠዋል…የተለያዩ ጥራጥሬዋች በየቦታው ተበትኗል….በጊቤዋ ውስጥ ያሉ እንስሳት ብቻ ሳይሆኑ እንግዳ የሆኑ ወፎች ሳይቀሩ ግቢውን ወረውት የተበተነላቸውን ጥራጥሬ በደስታ ይለቅማሉ… ጦጣና ዝንጆሮዎቾም ሙዙን እየላጡ ይውጣሉ …የማይፈነጭ እና የማያስካካ ፍጥረት በግቢው አይታይም..  የሆነ እንስሳት አግብቶ ሌሎቹ ሠርግ ተጠርተው አሼሼ ገዳሜ ላይ ያሉ ነው የሚመስለው….ሌላው ይቅር እያንዳንዱ  ተክል   ስሩ ተኮትኩቶና አፈር ታቅፎ ውሃ ጠግቦ እስኪተፋ ድረስ ጠጥቶ ይታያል….በቃ በግቢው አንድም ያልተደሰተ ፍጥረት አልነበረም..ይሄ ሁሉ በፕሮፌሰሩ የተደረገው እነሱ በተደሰቱበት መጠን እኔ እንደምደሰት በደንብ ስለሚያውቁ ነው፡፡

‹‹አትመጪም…  ይሆን ብዬ በስጋት ላይ ነበርኩ …እንኳን በሰላም መጣሽ››አሏት ከእድሜ ጫና የተነሳ ያጎበደድት ፕሮፌሰር…

‹‹አይ እፈልግሻለሁ ብለውኝ የለ..…….?በዛ ላይ  አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረኝ …ማታ ወደ እናቴ  እሄዳለሁ.አዎ ነገ ሙሉውን ቀን ከእሷዋ ጋር ነው ማሳለፍ የምትፈልገው………››

‹‹ጥሩ ጥሩ..ነይ እዚህ ጋር ቁጭ በይ›› ብለው ምግብ በሞላበት ጠረጴዛ ዙርያ ከበው ከተቀመጡ ወንበሮች ውስጥ አንድን ሳቡላት… አመስግና ተቀመጠች፡፡

የእጅ ውሀ አመጡላት …‹‹አረ እራሴ እታጠባለሁ›› ብላ በራሷ ተጣበች… ሳሀን ስባ ምንም እንኳን የምግብ ፍላጎት ባይኖራትም እሷቸውን ለማስደሰት ስትል ብቻ መብላት ጀመረች… እሳቸውም ከፊት ለፊቷ ተቀምጠው በስስት እያዮት መመገብ ጀመሩ…

‹‹የሚጠጣ ምን ልቅዳልሽ…….?››

‹‹ውሀ ››

‹‹ወይን ወይም ሌላ ነገር አይሻልሽም…….?››ካለወትሮዋ ዉሀ ማለቷ አስገርሞታል

‹‹አይ ውሀ ነው የምፈልገው….››

‹‹እሺ ካልሽ ››ብለው ውሀ ቀዱላት፡፡

‹‹ጋሼ በዚህ ምድር በኖርኩበት ዓመት የተረዳሁት ነገር ቢኖር  ምድር መተኪያ የሌላቸው ሁለት ነገሮች መታዳሏን ነው ….አዎ  እናትና ውሃ የዚህ ዓለም ሁለት ልዩዎች  ናቸው…››

‹‹እንዴት ልጄ..…….?እንዴት እንደዛ ተረዳሽ…?››

‹‹እናታችን መጀመሪያ ገነታችን ነች..ከተፈጠርንበት ቀን አንስቶ እስክንወለድበት ቀን ድረስ በእናታችን መሀፀን ውስጥ ገነታዊ ኑሮ ነበር የምነኖረው… ያ ስፍራ ሁሉ ነገር በፍፅምና  እንከን አልባ  ስፍራ  ነበር..ሁላችንም ከዛ ያለፍላጎታችን ተገፍትረን ስንወጣ(ስንወለድ) እሪ ብለን ለቅሶችንን የምንለቀው  ምን እንዳጣን በደመነፍስ ስለሚገባን ነው…አዳም እና ሄዋን በሰሩት ሀጥያት ከገነት ወደምድር ተባረሩ የሚባለው ሌላ አይደለም ከእናት መህፀን ወደምድር ተገፍትሮ መውጣት ነው…ከዛ በኋላም ቢሆን  እናት ምን ጊዜም እናት እንደሆነች ነው ምትቀጥለው… እንዳላረጀን እና እንዳላበቃልን የሚሰማን እናታችን በሰላሳ አመታችንም እንደ ህፃን ስትቆጣን ስናይ ነው..ጭንቅላታችንን ስትዳብስልን…ተይ አንቺ ልጅ ብርድ ይመታሻል ስትለን  ነው፡፡
ግን ክፋቱ በፈለግናት  ጊዜ ስለምናገኛት…በጣራናት ጊዜ ሮጣ ስራችን ስለምትገኝ ዋጋዋን ብዙም አናውቀው…. እንደድንገት ስትነጠለን  እና ከእጃችን ተንሸራታ ስናጣት ግን  አንድ ሰው ብቻ እንዳልነበረች ይገለጽልናል…መላ ዓለም እሷን እንደማይተካልን  ትምህርት እናገኛለን…ግን ትምህርት ቀድሞ ያጣኸው ነገር ወደፊት ዞሮ መጥቶ እንድታስተካክለው እድሉን ካላገኘህ ጥቅም የለውም..በደንብ ስትፀፀት እድትኖር ብቻ ነው የሚያግዝህ፡፡

ውሃም በቀላሉ ነው የምናገኘው..እኛ እራሱ በዋናነት የተሰራነው ከውሀ ነው ..ምድርም ሶስት እጆ ውሀ ነው….በቀላሉ ብቻ ሳይሆነ በርካሽም እናገኘዋለን.. ሰውነታችን ከየትኛውም መጠጥ በተሻለ በውሀ ይረካል…በውሃ ጤነኝነት ይሰማዋል…የውስጥ መጠማታችንን ብቻ ሳይሆን በአካልም መዛላችንን በውሀ ነው የምናክመው….ሰውነታንን የምንታጠበው የቆሸሸ ሰውነታችንን ለማጽዳት ብቻ አይደለም ውኃው በሰውነታችን ላይ ሲያርፍ መነፍስን የማረጋጋት እና የአዕምሮ ውጥረትን የማከም ኃይል ስላለው ነው…ግን ‹‹ወይ ስታጠብ ቀለል ይለኛል›› በማለት ያገኘነውን ጥቅም እናቃልለዋለን እንጂ ውሀ መድሀኒት ነው ብለን ዕውቅና መስጠት አንፈልግም ..ወሃ የደም ግፊት መድሀኒት ነው..ውሀ የኩላሊት መድሀኒት ነው…ውሃ የራስ ምታት መድሀኒት ነው…..ወሃ የበሽታዎች ሁሉ ፈውስ ነው…
‹‹የእኔ ውሃ ግን  አንቺ ነበርሽ…››አሏት እዝን እንዳሉ፡፡
‹‹ማለት……….?››አለቻቸው አሳዝነዋት፡፡
‹‹አዎ እኔ ጡረታ እስክወጣ ድረስ በዚህች ሀገር ላይ በጣም ስኬታማ ከሆኑ ጥቂት ሰዎች መካከል አንድ  ነኝ ብዬ አስብና እመፃደቅ ነበር….አምስት ስድስት ዲግሪዎች ስላሉኝ አንቱ የምባል ፕሮፌሰር ስለሆንኩ በቃ እታበይ ነበር….ልክ ጡረታ ስወጣ ግን ግማሽ ህይወት ብቻ ስኖር እንደነበር ተገለጽለኝ..እንደው ወደኃላ ተመልሶ የኖሩትን ህይወት ማስተካከል ቢቻል ካሉኝ ዲግሪዎች መካከል አንድን ብቻ አስቀርቼ ሌሎቹን በልጆች እና የልጅ ልጆች መቀየር ብችል ደስ ይለኝ ነበር..ከዛሬ 40 አመት በፊት አግብቼ ዛሬ የ35 ዓመት ልጅ እና የአምስት አመት የልጅ ልጅ ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ በጣም ስኬታማ እና ሙሉ እሆን ነበር..ይሄን ቁጭቴን ባንቺ ነበር እየተፅናናው ለመኖር እውተረተር የነበረው…አሁን ግን….››
‹‹እንዲህ እማ አይዘኑ››
‹‹ተይኝ ልዘን…እነዛ ሁሉ ያገኘዋቸው ግኝቶች …እነዛ ሁሉ የተሸለምኮቸው ሽልማቶች እኔ ካለፍኩ በኃላ ማን ይረከባቸዋል..ማን ነው ሊኮራባቸው የሚችል የእኔ ሰው  ……….?
‹‹አሁን ወደኃላ ተመልሰው አድሉን ቢያገኙ እኮ መልሰው ተመሳሳዩን ነው የሚያደርጉት››
‹‹በፍጽም አላደርገውም..ህይወት ሚዛን መጠበቅ አላባት…እድሜሽን ሙሉ ገንዘብ ለማካበት ሰትባክኚ ቆይተሽ ካረጀሽ እና ጥርስሽ ከረገፈ በኃላ ልዝናና ብትይ አያምርብሽም… ደስታ ሚያመነጨው የሰውነትሽ ዕጢም እንዘይሙን ማምረት ስለሚያቆም አትቺይም….ወንደላጤ ሆነሽ ስትንዘላዘይ ኖረሽ በእኔ ዕድሜ ላግባ ብትይ እንዴት ተደርጎ..እንደው ሚስትዬዋ ተገኝታ ማግባት ቢቻል እንኳን እንዴት መውለድ ይቻላል..…….?ቢወለድ እራሱ የማያሳድጉትን ልጅ  እንዴት ….?ሁሉ ነገር በጊዜው ነው የሚያምረው››
‹‹እና እንዴት መሆን አለበት ይላሉ…….?››ጠየቀቻቸው
‹‹የተወሰነ መማር..የተወሰነ ገንዘብ መስራት… የተወሰን ቁጥር ያለው ቤተሰብ መመስረት…በቃ ከሁሉም የሚያስፈልገውን እና የምትጠቀሚበትን ያህል መውሰድ ነው…አየሽ አኔ አሁን ተማርኩ ከምላቸው ትምህርቶች መካከል ሁለቱን ዲግሪዎች ለአንድ ሰምንት እንኳን አልሰራሁባቸውም…እንዲሁ ለጉራ ካልሆነ በስተቀር  ያን ያህል ፋይዳ አልነበራቸውም …
በልተው እንደጨረሱ እጇን ታጥባ  እሳቸው ቢራቸውን እየጠጡ እሷ ደግሞ ወኃዋን ይዛ ወሬውን ቀጠሉ
‹‹እቤቱን እንግዲህ  ሰጥቼዎታለሁ…..››
‹‹አይ እንደዛማ አይሆንም ….እኔ እኮ ለራሴ የሚበቃ የጡረታ ብር አለኝ..ተከራይቼ ሌላ ቦታ እኖራለሁ..ቤቱ የሚገባወ ለዘመዶችሽ ነው..››
‹‹አይ ይሄ ቤት የሚገባው ለእናቴ ነበር..ግን እናቴ ከተወለደችበት አካባቢ ንቅንቅ ማለት አለትፈልግም….››
‹‹እንደዛ ከሆነ ይሸጥና ብሩን ይጠቀሙበታ››
‹‹አይዞት ለእሷ አያስቡ …በቂ የሆነ ብር ሰጣታለሁ..ይሄ ቤት ግን የሚሸጥ አይደለም…እሺ ጣሪያና ግድግዳው መሸጥ ቀላል ነው…እነዚህ ግቢውን የሞሉትን ዛፎች በስንት ብር ተምኜ ልሽጣቸው…?እነዚህ ዛፎቹን የወረሯቸውን በሺ የሚቆጠሩ ወፎች ስንት ስንት ብር ያወጣሉ...?ዝንጀሮዬን ስንት ልሽጠው..…?ጉሬዛዬንስ….?አዩ አንዳንድ ነገሮች ከሚሰጡት ጥቅም አንፃር ብቻ ሳይሆን ካለቸው ትርጉም  በመነሳት ዋጋ ሊወጣላቸው አይቻልም….አሁን ለአንድ ሀብታም ብሸጠው እኚ አሁን የጠቀስኩሎትን ሁሉ አንድ ሰምንት የሚያቆያቸው ይመስሎታል….?.ዛፎቹን ጨፍጭፎ መሬቱን ነፃ በማድረግ ፎቅ ነው ሚገነባበት…ወፎችስ እድሜ ለክንፋቸው በስደት  በመሸሽ  ነፍሳቸውን ለማቆት ይሞክራሉ..፤ሎሎቹስ….?

‹‹እሱስ ከባድ ነው››
‹‹ስለዚህ ቤቱ አይሸጥምም… ለሌላ ዘመድም ቢሆን ተላልፎ አይሰጥም…ይሄ ቦታ የሚገባው ለእርሷ ብቻ ነው..የእያንዳንዶን ዕጽዋት ሚስጥር የሚያውቁትና የሚረዱት እርሶ  ኖት… ስለዚህ የእርሶ ነው››
ፈገግ አሉ..
‹‹ምነው .. …….?ተሳሳትኩ እንዴ..…….?››አለቻቸው ፈገግታቸው የምፀት ስለነበረ ገርሞት
‹‹ስንት ዓመት ልኖር ብለሽ..…….?በተለይ አንቺ በሌለሽበት..ሁለት አመት ሶስት አመት..ከዛስ ያው የፈራሽው  መድረሱ አይቀርም..እነዚህ ሁሉ የለፋንባቸው ነገሮች አጥፊ እጅ መግባታቸው እና መውደማቸው አይቀሬ ነው…››
‹‹ስለዚህ አንድ ነገር እናድርጋ››
‹‹ምን…….?››
ከመቀመጫዋ ተነሳች..ንስሯ ለማድረግ የፈለገችውን ቀድሞ ገብቶታል ፤ ካለበት ዛፍ ላቆ ልክ ትሪኢት እደሚያሳይ የአየር ኃይል የጦር ጄት መገለባበጥ ጀመረ… እንዲህ የሚያደረግው ሲደሰት ነው…በስንት ቀኑ ፈታ አለ….. 
ወደእሳቸው ቀረበች… ግራ ገብቷቸው በዝምታ ያዩታል…. ከጀረባዋ ቆማ  ፀሎት እንደሚያደሰርስ   የፕሮቴስታንን ፓስተር ሁለት እጇን በጭንቅላታቸው ላይ ጫነችና አይኖቾን ጨፈነች…በፍጽም መመሰጥ ውስጥ ገባች….ቀስ እያለ ሰውነቷ ሲግል ይታወቃታል..አዎ ከልቧ ጀምሮ ኃይል እየተሰበሰብ በደምስሯ በመራወጥ ወደ እጆቾ እየፈሰሰ ነው…ከዛ ወደ ፕሮፌሰሩ ጭንቅላት መተላለፍ  ጀመረ…አይኖን የጨፈነች ቢሆንም እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ይታያታል… ኃይል የሞላው ሀመራዊ ቀለም  ከፕሮፌሰሩ ጭንቅላት አንስቶ ወደ አንገታቸው..ከዛም  ትከሻቸው እያለ ወደመላ ሰውነታቸው ተሰራጨ… መንዘፍዘፍ ጀመሩ….ኦ.. ሽበት የወረረው ነጭ ፀጉራቸው...ከግንባራቸው እየተነሳ ወደ መሬት ይረግፍ ጀመር…በዛው ቅፀበት ሌላ ደማቅ ጥቁር ሉጫ ፀጉር ከእያንዳንዱ የራስ ቅል ቀዳዳቸው በመብቀል ወደ ውጭ በመውጣት ጭንቅላታቸውን ሞላው…

ይቀጥላል
#ክፍል 58,,እንዲለቀቀ 👍(20) ሰው ከስር ያለውን ሊንክ #Subscribe🔔ካረገ ይለቀቃል
https://youtube.com/@Weygud18

#Subscribe እያደረጋቹ ቤተሰብ ስለምትሆኑ እናመሰግናለን #Subscriber
YouTube link👇
https://youtube.com/@Weygud18

መልካም ሰንበት ተመኘሁ🙏