ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
236K subscribers
289 photos
1 video
16 files
231 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
Live stream finished (9 minutes)
👍በሳል ሁኑ!

💚ለውብ ምሺታችን

በሳልና ብልህ የተባሉ ሰዎች ከምንም በላይ የተካኑባቸው ሁለት ጥበቦች አሏቸው። አንደኛው ነገሮችን አርቆመ መመልከት ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ስሜትን መቆጣጠር ነው። እንደማንኛውም ሰው የግል ህይወት አላቸው፣ እንዲሁ የሚመሩበትም የግል መርህ አላቸው። ብስለታቸው ምናልባት በእድሜ የመጣ ሊሆን ይችላል፣ ከእዴሜያቸው በፊትም የበሰሉ ግን ብዙ አሉ። እነዚህ ከዕድሜያቸው የቀደሙ ሰዎች ህይወታቸው ያስቀናል፣ በሚያደርጉት እያንዳንዱ ነገር ውስጥ ህይወት አለ፣ ሀሳባቸው በጣም ያስገርማል፣ የገጠሟቸውን ችግሮች የሚመለከቱበትና ሊቀርፉት የሚሞክሩበት መንገድ እጅጉን አስደናቂ ነው። በቅድሚያ ይረጋጋሉ በመቀጠል የገጠማቸው ጉዳይ በእነርሱ አቅም መስተካከል ስለመቻሉ እርግጠኛ ይሆናሉ፣ ከዛም ቀስ በቀስ እርምጃ ይወስዱበታል ደረጃ በደረጃም ችግራቸውን በራሳቸው መንገድ ሲፈቱት ይታያሉ። ብስለትና ብለሀት በገንዘብ አይገዛም፣ በአንድ ሌሊትም ተዋህዶን መገለጫችን አይሆንም። በየቀኑ እራሳችሁን በማሻሻል ስትጠመዱ፣ በየጊዜው እራሳችሁ ላይ ስትሰሩ፣ አዳዲስ ፈተናዎችን ስትጋፈጡ፣ ከሰዎች ውድቀትና ስኬት መማር ስትችሉ ያኔ በሂደት ወደ ብስለት ከፍታ መምጣት ትጀምራላችሁ።

አዎ! በሳል ሁኑ! ዛሬ ስለገጠማችሁ የህይወት ማዕበል ብቻ እያሰባችሁ ህይወታችሁን አትገድቡት። ሩቅ ተመልከቱ፣ የአሁን ገደቦቻችሁን ተሻገሩ፣ የሚወራባችሁን አሉታዊ ነገር እለፉት፣ ለእውቀት ቸኩሉ፣ ጥበብን አሳዱ፣ በሀሳብ ግዘፉ፣ በተግባር ቅደሙ። በቻላችሁት አቅም ህይወት ለእናንተ እንድታዳላ አድርጉ። ቀድመው የነቁ ሁሌም ቀድመው ያተርፋሉ፣ ከሰዎች የተሻሉ ሰዎች ሁሌም የተሻለ ነገር ያገኛሉ። ብስለት ሁነኛው የአሸናፊነት መሳሪያ ነው። ምንም ነገር በስሜት ከማድረጋችሁ በፊት ቆም ብላችሁ ደጋግማችሁ አስቡ፤ ምንም መጥፎ ነገር ከመናገራችሁ በፊት ከጀርባው ስለሚያስከትለው ነገር አስቡ። የህይወትን ሚስጥር ለመረዳት የግድ ችግርና ፈተና እስኪፈራረቅባችሁ አትጠብቁ። ከሰዎች ተማሩ፣ ከተፈጥሮ ተማሩ፣ ከራሳችሁ ተማሩ፣ ሁሌም በእድገት መንገድ ስለመሆናችሁ እርግጠኛ ሁኑ። አስቡ ስታስቡም በትልቁ አስቡ፣ በተለየ መንገድ አስቡ፣ ከመደበኛው አካሔድ ለመውጣት ደፋር ሁኑ። መሪነትን በራሳችሁ ላይ ተማሩ፣ በጫና ውስጥ ተሽሎ መገኘትን ራሳችሁ ላይ ተግብሩት።

አዎ! ጀግናዬ..! የብስለት ተቃራኒ ልጅነት ነው። ልጅ ህይወቱ እንደ ልጅ ነው። ምንም እንኳን ሀሳቡ ነፃና መልካም ቢሆንም ተግባሩ ግን የተገደበ ነው፣ ነገሮችን አርቆ የመመልከት ክፍተት አለበት፣ የሚፈልጋቸው ነገሮች በሙሉ አሁኑኑ እንዲሆኑ ይፈልጋል፣ ሚዛናዊ እይታና የጠለቀ ግንዛቤ ላይ አጥጋቢ ክንውን የለውም። የብስለትህን ክህሎት ከልጅነት እሳቤዎች ለመውጣት ተጠቀመው። ዕድሜህ ቢያንስም ተግባርህ ግን በጥበብ የተሞላ መሆን ይችላል። ዋናው ጉዳት የቆይታ ዘመን ሳይሆን በትንሿ ዘመን የተረዷትን የህይወት ሚስጥር ምድር ላይ ማውረድ መቻል ነው። ከፍታም ዝቅታም የህይወት አንድ አካል ናቸው፣ ችግርም ድሎት የመኖር ገፆች ናቸው፣ ውድቀትም ስኬትም በፈረቃ የሚመጡ ክስተቶች ናቸው። በብስለት ጎዳና የሚያራምደው ጥበብ ግን እነዚህን ሁሉ ተረድቶ እንደ አመጣጣቸው ምላሽ መስጠት መቻል ነው። አስታውስ ብስለት ከዕድሜ በላይ የአዕምሮ ጫወታ ነው። ህይወትን ቀድመህ በተረዳህ ቁጥር ከዕድሜህ በፊት እየበሰልክና ጥበበኛ እየሆንክ ትመጣለህ። በሳል ሁን፣ ከማንም በላይ ህይወትን ተረዳት።

#LIKE👍👍እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💚ልባችሁን አሙቁት!

ከማንም የሚለያችሁ፣ ከማንም በላይ ከፍታችሁን የሚጨምርላችሁ አንድ ጥበብ አለ። እርሱም ራሳችሁን ከማንምና ከምንም በላይ ማወቃችሁ ነው። እውቀት የታላቅነት መሰረት ነች፤ እውቀት የከፍታው መንገድ ከፋች ነች፤ እውቀት ለለውጥ የመጀመሪያዋ ፈርቀዳጅ ነች። ማንም ስለራሱ በጥልቀት የሚያውቅ ሰው ምርጫዎቹ የተጠኑ ናቸው፤ እርምጃዎቹ በጥንቃቄ የተሞሉ ናቸው፤ ሀሳቦቹ ከፍ ያሉ፣ ድርጊቶቹም ውጤታማ ናችው። አሉባልታ አትስሙ፣ ትርኪሚርኪ ነገር ወደ አዕምሯችሁ አታስገቡ፣ የማይረባ ንትርክ ውስጥ አትግቡ። ራሳችሁን በምታውቁት ልክ ከለላ ሁኑለት፣ ራሳችሁን በተረዳችሁት መጠን ወደፊት ግፉት፣ ከባዱን ትግል አታግሉት፣ ችግር መከራውን አጋፍጡት፣ ልባችሁን አደንድኑት፣ ልቦናችሁን አጠንክሩ። ትክክለኛውን አቅማችሁን ካልተረዳችሁ ወደፊት ልራመድ እንኳን ብትሉ አትችሉም፣ ፍላጎታችሁን ካላወቃችሁ ትልቅ ነገር ላሳካ፣ ህይወቴን ልቀይር፣ ለሰዎች ልድረስ ብትሉ እንኳን አትችሉም። ሀሳባችሁ እውን ይሆን ዘንድ እቅዳችሁም ይሳካ ዘንድ ዋናውን መሰረታዊ እውቀት ወደ ልባችሁ ማስገባት ይኖርባችኋል።

አዎ! ልባችሁን ክፈቱ፣ ለራሳችሁ ቀናተኛ ሁኑ፣ ውስጣችሁን ተረዱት፣ ልባችሁን አሙቁት። የሚመጣ ሁሉ ሊያውቃችሁ ይሞክራል ነገር ግን ሳያውቃችሁ ተመልሶ ይሔዳል። የሰው ልጅ ረቂቅ ነው። ከርቀቱም የተነሳ አንዳንዴም ራሱ ሰውዬው እንኳን እራሱን በጥልቀት ለማወቅ ሊቸገር ይችላል። ዓለም የምታቀርብላችሁን ጌጣጌጥ መመራመር አቁም፤ በሰዎች ከመስመር የወጣ ድርጊት መበሳጨት አቁሙ፤ የዓለምን አሰራር ለመረዳት መድከማችሁን ተውት፣ አዕምሯችሁን በውጫዊውን እውቀት ዙሪያ ማስጨነቃችሁን አቁሙ። ሁሉም ራስን ከማወቅ ቦሃላ እንደሚመጣ ተረዱት። አሁን ገባችሁም አልገባችሁ፣ አሁን አወቃችሁም አላወቃችሁም በስተመጨረሻ ህይወት በቀዳሚነት የምትፈልገው የእናንተን ህልውና ነው። ጨርቃችሁን ጥላችሁ እስክታብዱለት የምትፈልጉት የትኛውም ምድራዊ ነገር ከእናንተ ህይወት አይበልጥም። አመናችሁም አላመናችሁም ህይወታችሁን የምትመሩት ራሳችሁን በምታውቁትና ለራሳችሁ በሰጣችሁት ትኩረት ልክ ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ግብግብ ውስጥ አትግባ። ምንም ቢፈጠርብህ ከሁሉም በፊት የገዛ ስሜትህንና በነገሩ ዙሪያ ያለህን ግንዛቤ ለማወቅ ሞክር። ማንም ያላንተ ፍቃድ እንዲጠቀምብህ ካልፈለክ ከማንም በላይ ራስህን ጠንቅቀህ እወቅ። የትኛውም ሰው ከሚያውቅህ በላይ ራስህን የማወቅ ግዴታ እንዳለብህ አስተውል። ውስጣዊ አቅምህን፣ የመረዳት ችሎታህን፣ ክህሎትህን፣ የደስታህን ምንጭ፣ የወደፊት እርምጃህን፣ ከፈጣሪህ ጋር ያለህን ቅርበት፣ ጥንካሬህን፣ ድክመትህን፣ የልብ ፍላጎትህን በሙሉ ጠንቅቀህ እወቅ። ከራስህ የሚበልጥ የቤት ስራ የለህም። ስሜትህን የመግዛቱ አቅም አለህ፤ ምርጫዎችህን የማስተካከሉ ተሰጥዖ አለህ። ስህተትን እንደ ስህተትነቱ፣ ጥፋትንም እንደ ጥፋትነቱ ተቀበል። ማራኪ ሆነህ ለመታየት ሳይሆን የእውነትም ማራኪ ለመሆን ራስህ ላይ ጨክን፣ ከሰው በላይ ለራስህ ታመን። በጥንቃቄ የተጠናን እርምጃ ተራመድ፣ በእውቀት ላይ የተመሰረተን ተግባር ፈፅም፣ በጥበብ መንገድም በልበሙሉነት ተመላለስ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/fpn1FQlM_X4?si=VgYsjN8SaeD4KRDr

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇
       
@Mtshaf_bicha
       
@piyasa188
❤️ለወዳጅዎ
#ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ 📩
@Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                 
@EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
"ጦቢያ" የተሰኘው ዘመናዊ ልብወለድ መፅሐፍ የፃፉት ነጋድራስ አፈወርቅ ገብረኢየሱስ ከባለቤታቸው ጋር በሀገረ ጣሊያን በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተነሱት ፎቶግራፍ ፤

ጳጉሜ 1 ቀን 1927 ዓ.ም
ጣሊያን - ሮም

    LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችው🌼
አዲሱ አመት ሀገራችን ሠላም የምትሆንበት ያድርግልን 🙏
                
    ❤️መልካም
በዓል❤️

    LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
እናቴ በጣም ጎበዝ ነርስ ናት። አንድ ጊዜ በአመት በአል ቀን ተረኛ ሆና ወደስራ ልትሄድ ስትነሳ ሁላችንም ተማርረን አንድትቀር ስንለምናት ያለችን ፈጽሞ አይረሳኝም። '' እኔ እኮ ተረኛ የሆንኩት ስዎችን ለመርዳትና ከደረሰባቸው ስቃይ ነጻ ሆነው ወደቤታቸው እንዲሄዱ ለማድረግ ነው። ለዛውም ከስምንት ሰአት በኃላ ወደቤቴ እመለሳለሁ። እስኪ አስቡ! ዛሬ በሽተኛ ለመሆን ተረኛ ሆነው በህይወትና በሞት መካከል ያሉትን የሌሎች ልጆች ወላጆች። ምናልባት ፈፅመው ወደቤት ተመልሰው ሌላ አመት በአልም ላያከብሩም ይችላሉ።'' ነበር ያለችን። ሁላችንንም የለወጠ አባባል ነበር። እናቴ የምትገርም ደግ ሰው ናት። በእርግጥ ታመው የተሻላቸው ሲያመሰግኑ ያልታመሙት ለምን ይሆን የሚያማርሩት? በህይወትና በሞት መካከል ያሉት አንድ ተጨማሪ ደቂቃ ለመኖር ባለ በሌለ ሃይላቸው ሲፍጨረጨሩ በህይወትና በጤና ያሉት ግን ሞትን የሚያስመኛቸው ምክንያት ግን ሁሌም ይደንቀኛል።

📕ከተቆለፈበት ቁልፍ

በዶክተር ምህረት ደበበ


    ❤️መልካም በዓል❤️

  LIKE👍👍 እና Share
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም አዲስ አመት ተመኘሁ🙏
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌻
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Live stream finished (2 hours)
💚ለውብ ቀናችን🙏

ሁለት በእድሜ የገፉ ባልና ሚስት አንድቀን ከቤት መውጣት ድብር ይላቸውና ..
ባል "የወጣትነት ጊዜያችንን ወደኋላ ብንመልሰው ምን ይመስልሻል?" አላት።
ሚስትም በጣም ደስ ብሏት "እሺ" አለችው።

ባል "በቃ እኔ እታች ሱቁ ጋር ልውረድና ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብዬ አንቺ በዛ በኩል እለፊና ይዤ ላዋራሽ።"
ብሏት ተስማሙና ባል ወርዶ ሱቁ ጋር ድንጋዩ ላይ ቁጭ ብሎ ሚስቱን መጠበቅ ጀመረ። ቢጠብቅ ቢጠብቅ አትመጣም 4ሰዓት ሙሉ ጠበቃት አልመጣችም።

ከዛን የሆነ ነገር አጋጥሟት ይሆናል ብሎ ወደቤት ሲመለስ ሚስት ስቅስቅ ብላ ስታለቅስ ያገኛታል። ባልም ደንግጦ ..
"ምን ሆነሽ ነው ውዴ? ምን ነካብኝ?" ብሎ ቢጠይቃት
ሚስት "እናቴ አትወጪም ብላ ከልክላኝ ነው😭😭" ብላ እርፍ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

🌼መልካም ቀን ተመኘሁ
🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
👉 ለማስታወቂያ ፈላጊዎች በሙሉ መልካም ዜና አለን

ከ230 ሺ በላይ ተከታታይ ባለዉ እና ተወዳጅነትን ባተረፈዉ  ቻናላችን ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ በሙሉ ምርት እና አገልግሎትዎን ለብዙዎን መድረሻ አማራጭ በሆነው ገፃችን ላይ ማስተዋወቅ እድትችሉ እዱሉን አመቻችተንላቹሁዋል።

እንግዲያውስ ይፍጠኑ ምርቶን ያስተዋውቁ በብዙ ያትርፉ ለብዙሃን ተደራሽ ያድርጉ እንላለን።

ከእኛ ጋር አብሮ ለመስራት እውነተኛ ፍላጎቱ ያላቹሁ ሰዎች ብቻ ከስር በአሉት አማራጮች ማናገር ትችላላቹሁ።

👉 📥 @eyos18

+251922788490
+251933324708

SHARE ፦ 👇👇👇👇
@Eyosc1
@Eyosc1
🐣የሁለት እንቁላሎች ታሪክ

የት እንዳነበብኩት የማላስታውሰው የሁለት እንቁላሎች ታሪክ ነው ። እንቁላሎቹ የተለያየ ቦታ ቢጣሉም፣ ንፋስ ገፍቶ ገፍቶ አጠጋጋቸው። ወንድና ሴት ናቸው፡፡ (እንቁላል ፆታ አለው እንዴ?) ገና በቅርፊት እንዳሉ ወሬ ይጀምራሉ።
“ድምፅሽ ያምራል” አላት።
“ያንተም ውብ ነው” አለችው።
“ምን እግር ጣለሽ? ከየት መጣሽ ውዴ?” ጠየቃት።
“የእህል ውሃ ነገር፣ አንተን ሳታውቂው አትሙቺ ሲለኝ” ትመልሳለች፤ ሆድ በሚያባባ ድምጽዋ።
እንዲሁ ሳር ላይ እየተንከባለሉ፣ የረባ ያልረባውን ሲጨዋወቱ ይዋደዳሉ። ፍቅር ይጠናል። አልፈው ተርፈው ቃል ይገባባሉ።
“እኔ እንደተፈለፈልኩ፣ አንተን ነው የማገባው” ትለዋለች፡፡
“እኔስ ካላንቺ ማን አለኝ!” ይላታል።
እንዲያውም ለጫጉላ ሽርሽር በሰዓታት በረራ ተጉዘው፣ አሰብና ምፅዋ ለመዝናናት ሁሉ ተመኝተዋል። (በረራው በክንፍ ይሁን በአውሮፕላን አንድዬ ይወቀው!)
በፍቅሩ ጥናትና ጊዜዋም ደርሶ ሴቷ ቀድማ እንቁላሏን በርቅሳ ወጣች - ርግብ ነበረች።
የውጪው አለም እንዴት እንደሚያምር ...
ስለ ፀሐይ ድምቀት ...ስለ ነፋሻው አየር...መብረር እንዴት ደስ እንደሚል-- ሁሉንም እየተረከች ገና በቅርፊት ያለውን ወዳጇን አጓጓችው።
ቶሎ እንዲፈለፈልላት በላባዎቿ አቅፋ፣ ሙቀት በመስጠት ትዘምራለች... “የጓሮዬ አባሎ - አብብ ቶሎ
የጓሮዬ ጦስኝ - አብብልኝ” እያለች።
ውብ ዜማዋ ልቡን ሰውሮታል ... ሙቀቷ የልብ ልብ ሰጥቶታል ... ፍቅሯ ጉልበት ሆኖት፣ ቅርፊቱን ሰብሮ ተጠመጠመባት - እባብ ነበር።
👉ውስጣዊ ማንነታቸውን ሳናይ እባቦችን እያቀፍን ጉድ እያደረጉን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።


🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO
#ሰውና_ተፈጥሮው_እንዲህ_ይልሃል

ሰዎች የቱንም ያህል ልክ ባልሆነ መንገድ ቢያስተናግዱህ ችግር የለውም። መቼም ቢሆን ወደ እነሱ ደረጃ እንዳትወርድ። ረጋ በል፤ ጠንክር እና ትተሃቸው ሂድ!

አንተ እኮ ልዩ ነህ!

#ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ

የሮበርት ግሪን ምርጥ መጽሐፍት👇

#ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ
#የኃያልነት_ሕጎች 3ተኛ ዕትም

ሌሎች የሮበርት ግሪን በእንግሊዝኛ የታተሙ👇

#The_Laws_of_Human_Nature
#The_Daily_Laws
#The_33_strategies_of_WAR

ሁሉንም መጽሐፍት በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ያገኟቸዋል።

🎀

እነዚህ #የኃያልነት_ሕጎች መጽሐፍ እና #ሰውና_ተፈጥሮው መጽሐፍን፦

#ጄዚ
#ካንዬ_ዌስት
#ፊደል_ካስትሮ
#ጆርዳን_ፒተርሰን
#ባራክ_ኦባማ
#ኤለን_መስክን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ እና ኃያል ግለሰቦች ለስኬታቸው እንደምክንያት የሚጠቅሷቸው ናቸው። እናም አንተም ያቀድከውና ያሰብከው የስኬት መዳረሻ ላይ ለመውጣት እነዚህን መጽሐፍት እንደ መሰላል እንድትጠቀምባቸው አቅርበንልሃል፡፡

 LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
👍ትንሽ አትሁኑ!

ሌሎችን ለመተቸት ጊዜ እስክታጡ ድረስ ራሳችሁን በማሻሻል ተጠመዱ፣ ራሳችሁን በማብቃት ቢዚ ሁኑ። ትልቁ ስራ የሰውን ድክመትና ክፍተት ማውጣት ሳይሆን የራስን አውቆና ተረድቶ እርሱን ማሻሻል መሆኑን እንዳትረሱ። ትቺት የዓለምን ህዝብ እኩል የሚያደርግ በጣም ቀላሉ ስራ ነው፣ በምትኩ ራስን ማሻሻል የዓለምን ህዝብ የሚለይ ትልቁና ዋንኛው ስራ ነው። ማንም ልዩነት ፈጣሪ ሰው ልዩነቱን የፈጠረው ለዓመታት ሰውን ተችቶ፣ በሰው ስራ ተሳልቆ ወይም ሰው ላይ አተኩሮ አይደለም። ይልቅ ራሱን አውቆ፣ ማንነቱን ተረድቶ፣ አቅሙን ተገንዝቦ፣ ያለማቋረጥ ራሱ ላይ ሰርቶ፣ በየቀኑ ራሱን እያስተማረና ራሱን እየፈተነ ነው። ራሳችሁ ላይ ማተኮራችሁን ስትቀጥሉ የሰዎችን ድክመትና ክፍተት የመመልከት እድላችሁ እያነሰ ይመጣል። ጊዜያችሁ እጅግ በጣም ውድ ነው። ከቻላችሁ በገንዘባችሁ ግዙት፣ ሌላ ሰው ማድረግ የሚችለው ጉዳይ ካለ እርሱን ለሰው አሸጋግራችሁ ጊዜያችሁን ለተሻለ ነገር ነፃ አድርጉት።

አዎ! ትናንሽ ነገር እያደረጋችሁ ትንሽ አትሁኑ፣ በአሳፋሪ ተግባር ተሳትፋችሁ በራሳችሁ አትፈሩ። ሰዎች ላይ ያለማቋረጥ የነቀፋ ቃላትን መሰንዘር እውቀት ወይም ስልጣኔ አይደለም። ሁሌም ቢሆን ቁጭ ብሎ ማውራት የትናንሽ ሰዎች ባህሪ ነው፣ የሰው ስራን ሁሉ መናቅ የተናቁ ሰዎች ስራ ነው። አትዘናጉ፣ አይናችሁ ውጪ ውጪውን ሲል ማሻሻልና ማስተካከል የሚችለውን የገዛ ማንነቱን ይዘነጋል፣ ራሱን ይረሳል፣ የት ቆሞ ማንን እንደሚተች ማስተዋል ይሳነዋል። ራስን ማወቅን የሚያክል ትልቅ ምድራዊ ጥበብ የለም። ራሱን የሚያውቅ ሰው ከሁሉም በላይ ፈጣሪውን ይፈራል፣ ራሱን ለእርሱ ትዕዛዝና አስተምህሮ ያስገዛል፣ ቃሉን ያከብራል፣ በሰዎች አይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ከመመልከቱ በፊት የራሱ አይን ውስጥ ያለውን ምሰሶ ያስተውላል፣ ግዞቱ ያልሆነው ውጪ ላይ ከማተኮር ግዞቱና ርስቱ በሆነው ራሱ ላይ ያተኩራል። ከአምላክና ከእናንተ በቀር እናንተን የሚያውቅ ሰው የለም። ማንም ስለእናንተ እንዲነግራችሁ አትጠብቁ። ምንም ዙሪያ ጥምጥም መሔድ ወይም ሰውን ማስጨነቅ አያስፈልግም የራስ ግንዛቤያችሁ ምንጭ እናንተ ብቻ ናችሁ።

አዎ! ጀግናዬ..! አንተ ዝግጁ ካልሆንክ አንዳች ከውጭ መጥቶ የሚቀይርህ ነገር የለም። ዛሬም እንደ ትናንቱ ዋናው የህይወት አጀንዳህ ሰዎች ከሆኑ ከምታስበው በላይ ለውድቀት እየቀረብክ እንደሆነ አስተውል። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች የራሳቸውን ውድቀት በሰዎች ለመሸፈን ይሞክራሉ፣ ሰዎችን በናቁና በተቹ ቁጥር ንፁና ከእነርሱ የተሻሉ ሰዎች እንደሆኑ ያስባሉ። ነገር ግን የትኛውም ከሌላው ሊሻል የሚችለው በወሬ ሳይሆን በስራና በስራ ብቻ ነው። ችሎታው ማውራትና መተቸት ቢቻ የሚመስለው ሰው ስራውን ከመስራቱ ውጪ ትቺቱ የሰውን ስሜት እንደሚጎዳና ህልሙን ሊያደናቅፍበት እንደሚችል አያስብም። ብዙ አውቃለሁ፣ ነገሮችን ተረድቼያለሁ፣ ራሴንም አውቃለሁ ካልክ አፍህን ዝጋ፣ ስለሌሎች አይደለም ስለራስህ እንኳን ከልክ በላይ አታውራ። የምር አዋቂ ከሆንክ ስሜትህን ግዛ፣ ራስህ ላይ ሰልጥን፣ ሰዎችን መተቸት አቅቶህ ሳይሆን ጊዜውን እስክታጣ ድረስ በግል ጉዳዮችህ ተጠመድ፣ ትልቁን ጥበብህንም ገልጠህ ለዓለም አሳይ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
💛ተሰፋ

ተስፋ የተሟጠጠበት ቦታ፣ እየታመኑ የሚጠረጠሩበት  ፤እየሰጡ የማይመሰገኑበት፣ እያመኑ በሚካዱበት  ስፍራ መኖር እፈራለሁ፦

ፍቅር  እልቅ እስኪል ፣መከባበር ሙጥጥ እስኪል፣ ተስፋ እሲኪበጠስ ፣ መዋደድ እስኪጠፋ አልጠብቅም ።

የደነበረ በሬ እንደሚከተለው ብርግግ ብዬ እልም እላለሁ..!!

"የደነገጠ እንጂ ያዘነ እንደዚህ ይሸሻል? "  እለዋለሁ እራሴን

"ፍርሃቴ ቀጥሎ ያለውን ላለማየት ነው!!" ይለኛል


LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/2X-gbw5HnVU?si=Elm9abHXy2eKSmDV

#መልካም ምሽት ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
❇️የማይታየው ላይ አተኩሩ!

እጅግ በጣም ፈታኙ፣ እጅግ በጣም ወሳኙ፣ እጅግ በጣም ተፅዕኖ ፈጣሪው እንዲሁም ደግሞ ከፍተኛ ጥረትን ፈላጊውና በጣም ከባዱ ተግባር ማንም ሳያያችሁ የምታደርጉት ተግባር ነው። ታዛቢ በሌለበት ብዙ ጊዜ ምን ታደርጋላችሁ? ማንም ሳያያችሁ ጊዜያችሁን እንዴት ታሳልፋላችሁ? በድብቅ ምን ታደርጋላችሁ? እንዳለመታደል ሆኖ ሰው የሚያየው ውጤታችሁን እንጂ ጥረታችሁን አይደለም። የሚዳኛችሁም በውጤታችሁ ነው። መሬት ውስጥ የተቀበረ የሰብል ፍሬ እንዴት ከመሬት ወጥቶ ግንድ አብቅሎ ብዙ ፍሬዎችን እንደሚያፈራ ሁሉንም ደረጃውን የሚመለከት የለም። መሬት ውስጥ ምን ሲካሔድ ነበር? ምን አይነት ምግቦችን ሲመገብ ነበር? የተጠቀማቸው ንጥረ ነገሮችስ ምን ምን እንደሆኑ ማን አየ? ማንም። ሁላችንም እኩል የምንመለከተው ከመሬት ከፍ ብሎ የሚታየውን ያፈራውን ፍሬ ብቻ ነው። የሰው ልጅ ህይወትም ይሔው ነው። ብቻችሁን ስትሰሩት የነበረውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማንም አያየውም፣ የእንቅስቃሴው ውጤት የሆነውን ውብ ተክለ ሰውነት ግን ሁሉም ሰው ይመለከተዋል። ላይብረሪ ገብታችሁ ስታጠኑ፣ ቤታችሁ ልብቻ ስታነቡ ምን እንደምታጠኑ፣ እንዴት እንደምታጠኑና እንደምታነቡ ማንም አያውቅም፣ ያመጣችሁት ከፍተኛ ውጤት ግን የጥረታችሁን ከፍተኛነት ያሳያችኋል።

አዎ! የማይታየው ላይ አተኩሩ፤ አይን የማይበዛበትን ተግባር በአግባቡ ፈፅሙ፣ ለብቻችሁ ስትሆኑ ለምታደርጉት ነገር ተጠንቀቁ። ራሳችሁን የመገምገም፣ ከግምገማውም ቦሃላ በአፈፃፀማችሁ ላይ ተመስርታችሁ ራሳችሁን የመቅጣትና የመሸለም ልማድ ይኑራችሁ። ማነቃቂያችሁ ማየት የምትፈልጉት ውጤት ሳይሆን የምትጓዙበት ሒደት እንዲሆን አድርጉ። ለውጥና እድገታችሁን ሰው ከመመስከሩ በፊት ራሳችሁ ለራሳችሁ መስክሩ፣ ለእያንዳንዷ ጥቃቅን መሻሻል እውቅና ስጡ። ህይወት የምንለው ሁሌም ሰው ፊት የምንኖረው ህይወት አይደለም፣ ይልቅ ህይወት የሚባለው ብቻችንን የምንኖረው፣ ስለራሳችን የሚሰማን እውነተኛ ማንነትና ለራሳችን የምንሰጠው ቦታ ነው። ሰው ፊት እውነተኛ ማንነቱን የሚገልጥ ሰው በጣም ጥቂት ነው። በውሸትና በአስመሳይ ማንነት የሚኖር ህይወት ደግሞ የለም። በፍፁም እንዳትዘናጉ። ከሰው በላይ ለራሳችሁ ይሉኝታ ይያዛችሁ፣ ሰው ፊት ከምትገልጡት ማንነት በላይ ራሳችሁ የምታውቁት እውነተኛ ማንነታችሁ ያሳስባችሁ። የህይወታችሁን አቅጣጫ በዋናነት የሚቀይረው አደባባይ የሚታየው ውጤት ሳይሆን ለብቻ በድብቅ የምታደርጉት ትናንሽ የየእለት ተግባራት እንደሆኑ እወቁ።

አዎ! ጀግናዬ..! ዓለምን የሚስደምመው ውጤትህ መና አይደለም በአንዴ ከሰማይ የሚወርድ፣ ዱብእዳም አይደለም በአንድ ቀን የሚመጣ። ከየትኛውም የሚታይ ውጤት በስተጀርባ እጅግ በጣም ብዙ የማይታይ ጥረትና ልፋት አለ። ብዙ ሰው ስኬትን አጥብቆ ይፈልጋል፣ ነገር ግን ስኬታማ የሚያደርገውን ስቃይና ዲሲፕሊን አይፈልገውም፤ ብዙ ሰው የተረጋጋና ደስተኛ ህይወትን መኖር ይፈልጋል፣ ነገር ግን በፍፁም ራሱ ላይ መስራትን አይፈልግም ወይም ለእንደዚህ አይነት ነገር ጊዜ የለውም። ለዓመታት በሰው ዘንድ ቦታ ለማግኘት ሮጠህ ያገኘሀው ውጤት ምን እንደሆነ አስተውል። ለረጅም ጊዜ ብቻህን ስትሆን ስትፈፅማቸው ከነበረው ውጤት አልባ ከንቱ ተግባራት ምን እንዳተረፍክ አስብ። ለሰው ከመኖርህ በፊት ለራስህ እየኖርክ እንደሆነ እርግጠኛ ሁን። የብቸኝነት ጊዜህን በአላስፈላጊ ነገሮች ማሳለፍ አቁም። አስደሳች ውጤት ከፈለክ ውጤታማ የሚያደርጉህን ወሳኝ ልማዶችን ለማዳበር አታመንታ። ህይወትህን ለብቻህ ገንባው።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/2X-gbw5HnVU?si=Elm9abHXy2eKSmDV

#መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
🆕 🆕 ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ

📌 የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች 💸
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

➡️ የ ቻናል ማስታወቂያ
➡️ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
➡️ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
➡️ የ ድርጅት ማስታወቂያ
➡️ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
➡️ ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ

     💻 እንዲሁም የተለያዩ የ Business  🆕🆕  ስራወችን ከእኛ ጋ መስራት ለምትፈልጉ በራችን ክፍት ነው🔸

        🔺 ምርትና  አገልግሎቶን በተመጣጣኝ ዋጋ ለብዙሀኑ ተደራሽ በማድረግ በእጥፍ ያትርፉ። ከኛጋ በመስራትዎ ይደሰታሉ❤️

አሁኑኑ ያናግሩን 👇⬇️⬇️⬇️

•    @Eyos18
☎️.   +251922788490
☎️.   +251933324708
🙏ትወጣዋለህ!

ያንተን ቦታ የሚተካ ማንም የለም፤ የተቋቋምከውን የሚቋቋም፣ የተወጣሀውን የሚወጣ ማንም የለም። ምንም ሳትፈተን ዛሬ ያለህበት እንዳልደረስክ አስታውስ። ይቺን አለም ከተቀላቀልክ ጀምሮ የህይወት ፈተናህ አቁሞ አያውቅም፤ ከአሁን ቦሃላም ይቀጥላልና ጠንካራ ሁን። ያለፍካቸውን ከባድ ጊዜያት እያስታወስክ ለመጪዎቹ ተዘጋጅ። በፍፁም አንተን ብሎ ለመጣ ችግር አትንበርከክ፤ እጅ አትስጥ። በሚከተለው አዎንታዊ ማረጋገጫም ብርታትህን ለእራስህ አረጋግጥ፤ በእራስ መተማመንህን አጎልብት፤ በተስፋ ተሞላ፣ ስሜትህን አድስ፣ ስብረሃትህን ጠግን።

" የደረሱብኝን እያንዳንዱን ፈተናዎች በድል ተወጥቼያቸዋለሁ፣ የቀሩትንም እወጣቸዋለሁ፤ ችግሮቼን እቀርፋለሁ፤ ወደፊት እራመዳለሁ፤ የጎዱኝን፣ ያቆሰሉኝን ሰዎች በትልቁ ይቅርባይነት ረስቼያቸዋለሁ፤ በእነርሱ ምክንያት ለመደንዘዝም ሆነ ለመቆዘም ጊዜ የለኝም። ሙሉ ትኩረቴ ህሌሜ፣ ራዕዬና ግቤ ላይ ነው። ለዚህም የማምነው አምላኬ በሚገባ ይረዳኛል።

አዎ! ያበቃን ታሪክ አልቀሰቅስም፣ ያለፈ ትዝታን አላስታውስም። አዲስ ታሪክ፣ አዲስ ጀብድ ግን መስራትና መፈፀም እችላለሁ፤ አቅሙ አለኝ።በብዙ ችግሮች የተሞላው ዶሴ ተዘግቷልና አዲሱን የእራሴን አስደሳች ዶሴ እከፍታለሁ። ላጠፋሁት ጥፋትና ለሆነብኝ ነገር ሙሉ ሃላፊነት እወስዳለሁ። ለውድቀቴ ተጠያቂ ነኝ፤ ለመበደሌ ተጠያቂ ነኝ፤ ለሆነብኝ ሁሉ ሃላፊነት ስለምወስድ ምንም የሚያስፈራኝ ነገር የለም። እራሴን ተቀብዬዋለሁ፤ እራሴን እወደዋለሁ፤ እራሴን አከብረዋለሁ፤ ዘወትር የሰላም እንቅልፍ እተኛለሁ። ድንቅ ስላዳረገኝ፣ መልካም ስላደረገኝ ከማመስገን ውጪ ምርጫ የለኝም።

አዎ! ያሰብኩትን አደርጋለሁ፤ የገጠመኝንም አልፈዋለሁ፤ አምላኬን ተደግፌ፣ ፈጣሪዬን ይዤ መቼም ተስፋ አልቆርጥም። በሆነብኝ አልፀፀትም፣ ባደረኩት አልቆጭም። እርሳስ ለስህተቱ ማረሚያ ላጲስ እንዳለው ሁሉ እኔም ሁለተኛ እድል አለኝና በጥፋቴ አልረበሽም፤ በስህተቴ አልታወከም። በእርግጥም ሁለተኛ የቀድሞ ስህተቴን አልደግመውም፤ ጥሩ ተማሪ መሆኔን ለማረጋገጥ በፍፁም በተደጋጋሚ ስህተት ረጅም ጊዜ አልወስድም። ከፈጣሪ ፍቃድ ቀጥሎ ህይወቴ በእጄ ናትና በምፈልገው መንገድ እኖራታለሁ፤ ደስታዬንም ከውስጤ አመነጨዋለሁ። "

አዎ! ጀግናዬ..! ትችላለህ፤ ትወጣዋለህ፤ ታልፈዋለህ። ነገ ሌላ ቀን ነው፤ እራስህን ለማፅናናት አትስነፍ፤ ለእራስህ ጊዜ አትጣ። በአዎንታዊ ማረጋገጫ ደጋግመመህ እራስህን አበርታ፣ ያረጋጋህ ዘንድ ለውስጠ ህሊናህ ተርክለት፤ አዎንታዊ ሃሳቦችን ለእራስህ ንገር። የማያሻማውን የሰላም አማራጭ በነፃነት ተጠቀም፤ ከፈተናዎችህ ተላቀህ ብሩህ ነገን አልም፤ በጎውን ተመኝ፣ ደጉን አድርግ። ከምንም በላይ በእራስህና በአምላክ ተማመን። መልካም ጊዜያት እንደሚመጡ አትጠራጠር። ዘወትር በተረጋጋ መንፈስ፣ በሰከነ አዕምሮ፣ በማይናወጥ ተስፋ መጪዎቹን የተሻሉ ድንቅ ጊዜያት ጠብቅ።
አይዞህ! በርታ! ተበራታ።

LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት
🙏🙏

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtube.com/@weygud18?si=2HdpprkkNeXryDsO

#መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

🎙ግሩፑን ለማግኘት
              👇👇👇

        @Mtshaf_bicha
        @piyasa188
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
📩 @Eyos18     አድርሱን
             📗📒📕📗📒📕
                Join&share
                  @EyosC1
       📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
Forwarded from Quality Button
ሴት ልጅ አንተን እንዳፈቀረችክ የምታቅበት 10 ምልክቶች ከታች #JOIN ብለክ ተተቀምበት እና ህዝቤ ሆይ ምን ትተብቂያለሽ ገብተህ አንበዋ😋😋😋😋
👇👇👇👇👇👇👇
Forwarded from quality botton
ወላሂ ለአዚም አላህ ሽሀዳዬ ነው ይሄንን ቻናል  ተቀላቅዬ 87455ብር በልቺያለሁኝ ,ሰዎችን ሁሉ ሀብታም እያደረገ ነው።
👉ገንዘብ ለጠረረባቹህ ብቻ አሪፍ መፍትሄ በቀላለሉ ገንዘብ ለማግኘት ምርጥ ቻናል
💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯💯
Join በሉ👇👇👇👇👇