ፒያሳ መሃሙድ ጋ ጠብቂኝ
242K subscribers
290 photos
1 video
16 files
238 links
እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
ተከታታይ ልቦለድ
ግጥም
ወግ
ሳይኮሎጂ
ምክር
መነባንብ

#ማንኛውም አይነት ፅሁፎች📕 ከፈለጉ ይቀላቀሉን
የተለያዩ PDF መፅሐፍት ከፈለጉ @Eyosibooks
አስተያየት ካሎት👇👇
+251933324708
☎️ +251922788490
📩@Eyos18
Download Telegram
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_አምስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ናንሲ ባህሩ ዳር ቁጭ ብላለች፡፡ መርቪን ላቭሴይ አጠገቧ ተቀምጧል፡፡
የባህሩ ውሃ በማዕበል እየተገፋ ይመጣል፣ ይመለሳል፡፡ ናንሲ ዓይኗን
ጨፍናለች፡ ሌሊት በደምብ አልተኛችም:: መርቪንና እሷ
እሷ ማታ መጋጨታቸው ትዝ አላትና ፈገግ አለች ከእሱ ጋር የምር ግንኙነት
አለመመስረቷ ደስ ብሏታል፡ ለወሲብ መቻኮሉ ጥሩ
አይደለም፡፡የመጣችበትን ዓላማ ከግብ ማድረስ አለባት፡፡

ሼዲያክ የዓሳ ማጥመጃ ፤መንደርና የባህር ዳር መዝናኛ ከተማ ናት፡፡
በባህሩ ዳርቻ ላይ የዓሳ
ማጥመጃ ጀልባዎች፣ መርከቦች፣ ሌሎች ሁለት
አይሮፕላኖችና እነሱ የመጡበት አይሮፕላን ይታያል፡፡ ብዙዎቹ የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች በባህሩ ዳርቻ ላይ ወዲያ ወዲህ ይላሉ፡፡

ሁለት የፖሊስ መኪኖች እየበረሩ መጥተው ጎማቸውን ሲጢጥ
አድርገው ሲቆሙ የአካባቢው ፀጥታ ታወከ፡፡ ከመኪኖቹም ውስጥ ሰባት
ስምንት ያህል ፖሊሶች እየዘለሉ ወጡ፡፡  በቀጥታ ወደ ተሳፋሪዎቹ
ማስተናገጃ ሲያመሩ የሆነ ሰው ሊይዙ የመጡ ይመስላል›› አለች ናንሲ፡
እሱም በመስማማት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ማንን ይሆን?›› አለ፡፡
‹‹ምናልባትም ፍራንኪ ጎርዲኖን››
‹ሊሆን አይችልም እሱ እንደሆነ እንደታሰረ ነው፡፡››
አይሮፕላን ውስጥ ሲገቡ ሁለቱ ወደ ባህሩ ዳርቻ ሲያመሩ ሁለቱ ደግሞ
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ፖሊሶቹ ከመናኸሪያው ወጡና ሶስቱ መንደሩ ውስጥ መንጎራደድ ጀመሩ፡፡

ፖሊሶቹ የሆነ ሰው እንደሚፈልጉ ያስታውቅባቸዋል፡ አንዱ
የአይሮፕላኑ ሰራተኛ ከአይሮፕላኑ ሲወጣ አየችና ናንሲ ‹ፖሊሶቹ ማንን ነው የሚፈልጉት?›› ስትል ጠየቀች:

ሰውየው ምስጢር ለማውጣት እየተጠራጠረ ሄሪ ቫንዴርፖስት
የተባለውን ሰው ነው የሚፈልጉት፤ ስሙ የሀሰት ነው›› አለ፡፡

ናንሲ ግንባሯን ከሰከሰችና ይሄ ልጅ ከኦክሰንፎርድ ቤተሰብ ጋር ተቀምጦ የነበረው ነው፡ ልጁ የማርጋሬትን ልብ ሳይሰርቅ አልቀረም›› ስትል
ገመተች ናንሲ፡

መርቪን ‹‹ከአይሮፕላኑ ወጥቶ ሄዷል እንዴ? እኔ ከአይሮፕላኑ ሲወጣ
አላየሁትም›› አለ፡፡

‹‹እኔም አላስተዋልኩም›› አለች ናንሲ፡

‹‹ልጁ አጭበርባሪ ይመስላል››

‹‹እውነት?›› አለች ናንሲ፡ እሷ ልጁ ከጥሩ ቤተሰብ የተገኘ ነበር የመሰላት፡ ‹‹ጥሩ ባህሪ አይቼበታለሁ: ማርጋሬት ከልጁ ጋር ፍቅር ሳይዛት አልቀረችም፡፡ ፖሊስ እንደሚፈልገው ስታውቅ ታዝናለች›› አለች

‹‹ወላጆቿ ፖሊስ እጅ መውደቁ ደስ ሳያሰኛቸው አይቀርም›› አለ
መርቪን፡፡ናንሲ ስለወላጆቿ ግድ የላትም፡ በአይሮፕላኑ መብል ክፍል ውስጥ
ሎርድ ኦክሰንፎርድ ያሳዩት የነበረው ጋጠወጥ ባህሪ መርቪንና ናንሲ
ያስታውሳሉ፡ ለእንደዚህ አይነት ሰው ውርደት ሲያንሰው ነው ናንሲ ከእንደዚህ አይነት ወመኔ ጋር ማርጋሬት ፍቅር ስለያዛት አዘነችላት፡

መርቪንም ቀጠለና ‹‹እኔ ስለሌላ ሰው ማውራት አልፈልግም›› አለ፡
ናንሲ ጆሮዋን ቀሰረች፡
መርቪን ቀጠለና ‹‹የተገናኘነው ከጥቂት ሰዓታት በፊት ስለሆነ በደምብ ላውቅሽ እፈልጋለሁ፡›› ናንሲም እርግጠኛ መሆን አትችልም አንተ ደደብ አለች በሆዷ
ሆኖም ይህን ማለቱ አስደስቷታል፡ ምንም መልስ አልሰጠችውም፡፡

‹‹ብፊት አንቺን ኒውዮርክ አድርሼ ወደ ማንቼስተር መመለስ ነበር የማስበው፡፡ አሁን ግን አላደርገውም›› አላት፡

ናንሲ ፈገግ አለች ይህን እንዲል ነበር ስትጠብቅ የነበረው:፡ እጇን ሰደደችና እጁን ያዝ አደረገች፡፡ ‹‹ይህን ስላልክ ደስ ብሎኛል›› አለችው፡

‹‹ደስ ብሎሻል? ችግሩ ከዚህ በኋላ አትላንቲክን ማቋረጡ የሚቻል አይሆንም፡፡ የጦር መርከቦች ብቻ ናቸው ይህን ማድረግ የሚችሉት፡››ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡
አሁን ከተለያየን ምናልባትም የምንገናኘው ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው፡፡።
እኔ ግን ላጣሽ አልፈልግም›› አለ መርቪን፡፡

‹‹እኔም እንደዚያው›› አለች ናንሲ፡፡

‹‹ከእኔ ጋር ኢንግላንድ ትሄጃለሽ?›› ሲል ጠየቃት፡፡
ናንሲ ፈገግታዋ ከፊቷ ላይ ጠፋ፡፡ ‹‹ምን አልክ?››
‹‹ከእኔ ጋር ወደ ኢንግላንድ እንመለስ፡፡ ሆቴል ውስጥ ትቆያለሽ ወይም ቤት ትገዣለሽ ወይም አፓርትማ ትከራያለሽ››

ናንሲ ያቀረበላት ሃሳብ በጣም አስቆጣት፡፡ ጥርሷን በንዴት አፋጨች፡፡
‹‹አብደሃል እንዴ?›› አለችው፡፡ መርቪንን ፊት ለፊት ማየት ጠልታ
ፊቷን አዞረች፡፡ በእጅጉ አዘነችበት፡፡
መርቪን አባባሏ አስደነገጠው ግራ አጋባው፡፡ ‹‹ምነው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹እኔ አሜሪካ ውስጥ የራሴ ኑሮ፣ ቤት፣ ሁለት ልጆችና በሚሊዮንዐየሚቆጠር ዶላር ገቢ የሚያስገኝ ፋብሪካ አለኝ፡፡ አንተ እንዴት ይህን ሁሉ እርግፍ አድርጌ ትቼ በማንቼስተር ሆቴል እንድቀመጥ ትጠይቀኛለህ?››

‹‹ይህን ካልፈለግሽ ከእኔ ጋር ተጠቃለይ››

‹‹እኔ እኮ ባገሬ የተከበርኩ ሴት ነኝ እንደ ቅምጥ ልኖር አልችልም፡››

‹‹ይኸውልሽ ልንጋባ እንችላለን፤ ይህን አረጋግጥልሻለሁ፧ እኔ አሁን
በዚህ ደቂቃ ውስጥ እንድትወስኚ አይደለም የጠየቅሁሽ››

‹‹ይህ አይደለም ዋናው ነጥብ መርቪን›› አለች ‹‹እኔን የገረመኝ ሁሉን
ጣጥለሽ ተከትለሽኝ ኢንግላንድ ነይ ያልከኝ ነው፡፡››
‹‹ታዲያ እንዴት ነው አንድ ላይ ልንኖር የምንችለው?››
‹‹ታዲያ ጥያቄውን መጠየቅ ሲገባህ ወደ መልሱ ሄድክ››
‹‹አንድ መልስ ስላለ ብቻ ነው ይህን ያልኩት››
‹‹ሶስት መልሶች ናቸው ያሉት፤ አንተ እንዳልከው አንተን ተከትዬ ወደ
ኢንግላንድ መመለስ ወይም አንተ ወደ አሜሪካ መጥተህ ከእኔ ጋር መኖር
ወይም ሌላ ቦታ ለምሳሌ ቤርሙዳ እንኖራለን›› አለች፡፡
በአባባሏ አልተደሰተም፡፡ ‹‹አገሬ ጦርነት ላይ ነች፤ እኔም የድርሻዬን ማበርከት አለብኝ፤ ጦርነት ውስጥ ገብቼ ለመዋጋት እድሜዬ ቢያልፍም ለአየር ኃይሉ የአይሮፕላን ሞተሮች ሰርቼ አቀርባለሁ፡፡ በእዚህ መስክ ከእኔ የተሻለ እውቀት ያለው የለም፡፡ አገሬ በጣም ትፈልገኛለች››

አሁን ያላት ነገሩን አባባሰው፡ ‹‹ለምንድነው የእኔ አገር እኔን
እንደማትፈልገኝ አድርገህ የምታስበው?›› አለች እኔ የወታደር ጫማ አመርታለሁ፡፡ አሜሪካ ጦርነቱ ውስጥ ከገባች ብዙ የወታደሮች ጫማ
ያስፈልጋታል››
‹‹እኔ ማንቼስተር ውስጥ ፋብሪካ አለኝ››
‹‹እኔ ደግሞ ቦስተን ውስጥ ካንተ የበለጠ ፋብሪካ አለኝ››
‹‹ታዲያ ሴት እንደ ወንድ እኮ አይደለችም››
‹ሴት ከወንድ እንዴት ታንሳለች አንተ ጅል!›› ብላ ጮኸችበት፡፡
ጅል› ማለቷ ወዲያው ጸጸታት፡፡ ፊቱ ቅጭም ሲል ታያት፡፡ በጣም
እንዳበሳጨችው ገባት፡፡ ከወንበሩ ተነሳ፡፡ እንደከፋው እንዳይሄድ አንድ ነገር
ማለት ብትፈልግም ትክክለኛው ቃል አልመጣላት አለ፡፡ እሱም አፍታም ሳይቆይ ጥሏት ሄደ፡፡

ምን ማለቴ ነው? አለች ምርር ብሏት፡ አባባሉ  ቢያበሳጭም ስላስከፋችው ደግሞ ተናደደች፡፡ በዚህ ሁኔታ እንዲርቃት አልፈለገችም ወዳዋለች፡ ወንዶችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ለውጥ ማምጣት እንደማይቻል
እያደር ገብቷታል፡፡ ወንዶች ከወንዶች በኩል
የሚመጣውን ጠብ ለምደውታል፡ ከሴቶች የሚመጣውን ግን መቀበል ይከብዳቸዋል፡፡ በንግድ
ስራዋ ላይ ከሰራተኞች የሚመጣ ችግር ሲገጥማት ድምጿን አለስልሳና
አለዝባ ትመልሳቸዋለች እንጂ አታካሮ አትገጥምም፡፡ አሁን ግን ያ ባህሪዋ ሸሽቷት በአስር ዓመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ልቧን የወሰደውን ሰው
አበሳጭታ አባረረችው፡
‹ጅሏ እኔ ነኝ! ኩሩ መሆኑን አውቃለሁ፡ አንዱ የወደድኩት ባህሪው
ይሄ ነው፡፡ የጥንካሬው ምልክት ነው፡፡ ብርቱ ቢሆንም ብዙ ብርቱ ወንዶች
እንደሚያደርጉት ውስጣዊ ስሜቱን አፍኖ ቁጭ አላለም፡፡ ያቺን ፈርጣጭ
ሚስቱን ግማሽ ዓለም እንዴት ተከትሏት እንደመጣ ተመልክቻለሁ፡ ሎርድ
ኦክሰንፎርድ ይሁዳውያኑ ላይ እንደዚያ ቡራ ከረዩ ሲሉ እንዴት ለይሁዳውያኑ ጥብቅና እንደቆመላቸው በዓይኔ በብረቱ አይቻለሁ፡ እኔንም እንዴት ግጥም አድርጎ እንደሳመኝ እኔ ነኝ የማውቀው› አለች በሆዷ፡

ታዲያ ይሄ ሁሉ በህይወቷ ላይ ለውጥ ማምጣት እንዳለባት አመላካች
ነው፡

ዳኒ ሪሌይ የነገራት ነገር በህይወቷ ላይ አዲስ ለውጥ እንደሚያጭርባት
ታይቷታል፡ ፒተር ከእሷ ጋር የሚጣላው በችሎታ  ስለምትበልጠው ይመስላት ነበር፡ እንደዚህ አይነት የታላቅና የታናሽ መቀናቀን በጉርምስና ጊዜ ይጠፋል፡ ሁለቱ ወንዶች ልጆቿ ለሃያ ዓመት ያህል እንደ ድመትና
ውሻ እንደተጣሉ ነው ያደጉት፡ አሁን የማይነጣጠሉ ጓደኛሞች ሆነዋል የእሷና የፒተር መቀናቀን ግን በጉልምስናቸውም ጊዜ ቀጥሏል፡ ለዚህም
ተጠያቂው አባታቸው እንደሆኑ አውቃለች፡፡

አባቷ በህይወት በነበሩ ጊዜ የድርጅቱ የበላይ ኃላፊነት በእሷ እጅ እንደሚሆን ፒተር ደግሞ ምክትሏ እንደሚሆን ነው የነገሯት፡፡ ለፒተር
ደግሞ የነገሩት የተገላቢጦሹን ነው፡፡ ስለዚህ ሁለቱም የኃላፊነቱ ቦታ የኔ ነው› ብለው ነው የሚያስቡት፡፡ አሁን ግን ሁኔታው ከዚያም በላይ ሄዷል፡
አባታቸው ሁልጊዜ የሁለቱን ተግባርና ኃላፊነት በተመለከተ ግልጽ ደምብ
አያስቀምጡም ነበር፡፡ ልጆች ሆነው አንድ አሻንጉሊት ይገዙና ልጆቹ ሲናቆሩ ያያሉ እንጂ የሚታረቁበትን መንገድ አያመቻቹም፡፡ ካደጉ በኋላ ደግሞ መኪና ይገዙና ለጋራ እንዲጠቀሙበት በመስጠት እንዲናቆሩ ያደርጋሉ፡

የአባታቸው ስልት የጠቀመው ናንሲን ነው፡፡ ጠንካራና አቋመ ጽኑ
እንድትሆን አድርጓታል፡፡ ፒተር ደግሞ ደካማ፣ ሸረኛና ለሰው ጉድጓድ የሚምስ አድርጎ አሳደገው፡፡ ስለዚህ በአባትዬው ዕቅድ ጠንካራው ልጅ
የኩባንያውን የኃላፊነት ቦታ ነጥቆ ይወስዳል፡፡

ይሄ ነው እንግዲህ ናንሲን አዕምሮዋን እረፍት የነሳው፡፡ ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው በአባታቸው ዕቅድ መሰረት ነው፡፡ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ አባታቸው እነሱ ሳያውቁ በነደፉት ዕቅድ መሰረት መሆኑ የሚገኘውን ድል ጣዕም አሳጥቶታል፡ ስለዚህ ኑሮዋን በራሷ ዕቅድ ለመምራት ታላቅ ጉጉት አደረባት፡፡

ናንሲ ከመርቪን ጋር ስለሚኖራት የወደፊት
ዝግጁ ነበረች፡፡ እሱ ግን ሁሉን ነገር ጣጥላ ተከትላው እንድትመጣ
ስለጠየቃት ተበሳጨች፡፡ እሷም ተነጋግሮ ችግሩን እንደመፍታት አፉን
አስይዛ አባረረችው፡

መቼም መርቪን ተንበርክኮ እንጋባ ብሎ ይጠይቀኛል ብላ አትጠብቅም፡፡

እሷ ከካቶሊክ ቤተሰብ የተገኘች እንደመሆኗ እንዲያው ዝም ብሎ እንደ
መንገድ ሴት እጇን ጎትቶ ወደ ቤቱ እንዲያስገባት አይደለም ምኞቷ በአገር
ልማድ ለጋብቻ በክብር እንዲጠይቃት እንጂ፡

በመሃከላቸው የተፈጠረው ጥል ጊዜያዊ እንደሆነ ገምታለች፡ መርቪን
በዚያው ይቀር ይሆን ብላ ማሰብ ጀምራለች፡፡ ምን ያህል መርቪንን
እንደምትፈልገው ያወቀችው አሁን ነው፡፡

ከዚህ ቀደም ልቧን የወሰደው ነገር ግን ጥሏት የሄደው ሰው መምጣት
ከሃሳቧ አባነናት፡፡

ፊቷ ቆሞ ባርኔጣ በትህትና አውልቆ ‹‹ድል ሳታደርጊ አልቀረሽም እንደገና›› አላት፡፡

ናትን በአትኩሮት አየችው፡፡ አባቷ የብላክ ጫማዎች ኩባንያን ከትቢያ
አንስቶ አሁን የደረሰበት ደረጃ ማድረስ ናት እንደማይችል ታውቃለች፡፡ ናት እንዲህ ለማድረግ ራዕዩም ሆነ ዓለማ የለውም፡፡ የእሱ ችሎታ አንድን ትልቅ ኩባንያ መምራት ነው፡፡ ናት ብልህ፣ ትጉህና ጠንካራ ሰራተኛ ነው፡፡

‹‹ለማስተዛዘን ከሆነ የመጣኸው፤ ከአምስት ዓመት በፊት ስህተት
መፈጸሜን አውቄያለሁ›› አለችው:

‹‹የንግድ ስራ ወይስ የግል ስህተት?›› ይህን ሲል የለበጣ እንደሆነ ያውቃል
‹የንግድ ስራ›› አለችው፡፡ ጅምር ፍቅሯን በማጣጣም ላይ እያለች ነው
ጥሏት የሄደው፡ ስለዚህ መነጋገር ደግሞ አትፈልግም ‹‹እንኳን ደስ ያለህ ስለ አዲሱ ትዳርህ›› አለች፡ ‹‹የሚስትህን ፎቶ አየሁት፤ ቆንጆ ናት››

‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ‹‹ወደ ንግድ ስራችን እንመለስና የምትፈልጊውን ለማግኘት ወደ ስም ማጥፋት ዘመቻ ማዘንበልሽ ገርሞኛል››

‹‹ይሄ የሻይ ግብዣ ሳይሆን ኩባንያ በቁጥጥር ስር ማዋል ነው›› ብለሃል ባለፈው ጊዜ፡››

‹‹ትክክል ብለሻል፤ ልቀመጥ?››

አባባሉ አናዷታል፡ ‹‹ለብዙ ዓመታት አብረን ሰርተናል፡፡ ለጥቂት ቀናት አብረን ወጥተናል፡፡ ስለዚህ ለመቀመጥ የኔን ፍቃድ የምትጠይቅበት ምክንያት የለም››

ናት ፈገግ አለና
‹‹አመሰግናለሁ> አለ ናት እሷን ፊት ለፊት ማየት
እንዲችል መርቪን ተቀምጦበት የነበረውን ወንበር አዞረው፡፡ ‹‹የብላክ
ጫማዎች ኩባንያን ያላንቺ ድጋፍ ለመጠቅለል ሞከርኩና አልተሳካልኝም:
ይሄ አላዋቂነቴን ያሳያል፡ ይሄ እንደማይሆን አስቀድሜ ማሰብ ነበረብኝ››

‹‹አሁን ክርክር አያስፈልግም›› አለች ናንሲ ‹‹እኔም በዚህ አድራጎትህ
ቂም አልያዝኩም››

‹‹እንዲህ ማለትሽ አስደስቶኛል ምክንያቱም ኩባንያሽን ለመግዛት ዝግጁ ስለሆንኩ።

ናንሲ አባባሉ አስገረማት፡ ‹‹ምንድነው ልታቀርብልኝ ያሰብከው?››ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹እንደገና መነጋገር አለብን›› አለ፡ ‹‹አሁን ይዤ የመጣሁት ሀሳብ
ከበፊቱ በጣም የተሻለ ነው፡፡ ዋናው ነገር ግን ከኩባንያው ሽያጭ በፊትም
ሆነ በኋላ ከኔ ጎን እንድትቆሚ ነው የምፈልገው፡፡ የጄኔራል ቴክስታይልስ ዳይሬክተር እንድትሆኚ የአምስት ዓመት ኮንትራት እንድንፈራረም
እፈልጋለሁ፡፡››

ናንሲ ይህን ፈጽሞ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህም ራሷን አላዘጋጀችም፡ ጊዜ
ለማግኘትና ሀሳቡን ለማውጣጣት ‹‹የምን ኮንትራት? ምን ለማድረግ?››ስትል ጠየቀች፡፡

‹‹ብላክ ጫማዎች ኩባንያን በጄኔራል ቴክስታይልስ ስር እንደ አንድ መምሪያ ለማስተዳደር››

‹‹ነጻነቴን አጥቼ እንደሰራተኛ?!››
‹‹እሱ በምናደርገው ስምምነት ይወሰናል፡፡ ምናልባትም የአክሲዮን ድርሻ ይኖርሻል፡፡ ድርጅቱን አትራፊ ካደረግሽው የምትፈልጊው ነጻነት ይሰጥሻል፡እኔ በአትራፊ ኩባንያዎች ስራ ውስጥ ጣልቃ መግባት አልፈልግም፡፡ አክሳሪ
ከሆነ ግን ነጻነትሽን ታጫለሽ፡፡ ውድቀትን መታገስ አልችልም፡፡ አንቺ ደግሞ ውድቀት አይገጥምሽም:››

ናንሲ የናትን ሃሳብ ውድቅ  እንደምታደርገው ጥርጥር የለውም፡፡አባባሉ የሚጣፍጥ ቢሆንም የመጨረሻ ሃሳቡ ኩባንያውን ከእሷ ለመንጠቅ መሆኑ ግልጽ ሆኗል፡፡ አባቷ ቢሆኑ በቀጥታ ይህን ሀሳብ አልቀበልም ነው የሚሉት፡፡ እሷ ደግሞ በአባቷ አስተሳሰብ መመራት ጀምራለች፡ ሆኖም
እውነቱን በሆዷ ደብቃ ‹‹አስብበታለሁ›› አለችው፡፡

‹‹ይህን ነው እኔም ማወቅ የፈለኩት›› አለና ተነሳ፡፡ ‹ምን ዓይነት ስምምነት ብታደርጊ እንደምትጠቀሚ አስቢበትና ወስኚ፡፡ መቼም ሁሉን ማድረግ የምትችይበት ስልጣን እሰጥሻለሁ ብዬ እኔም ቃል አልገባም፡፡ ነገር ግን አንቺን ለማስደሰት ስል የተቻለኝን አደርጋለሁ፡››

ናንሲ በመጠኑ ልቧ ከጀለ፡፡ አነጋገሩ አሳማኝ ነው፡፡ የመደራደርን ጥበብ
እየተካነው መጥቷል፡፡ ናት በናንሲ ጀርባ አሻግሮ ተመለከተና ‹‹ወንድምሽ
ካንቺ ጋር መነጋገር ይፈልጋል፡››
አንገቷን ዞር አድርጋ ስታይ ፒተር ወደ እነሱ አቅጣጫ ሲመጣ አየች በዚህ ጊዜ ናት ባርኔጣውን አደረገና ተነስቶ ሄደ፡ የፒተርን መምጣት ስታይ
ሁለት በኩል ጥቃት እንደተከፈተባት ሰው የሆነች መሰላት፡ በንዴት ፒተር ላይ አፈጠጠችበት፡፡ ወንድሟ ስለከዳትና ስላታለላት ልታነጋግረው አትፈልግም፡፡ የናት ሪጅዌይ ድንገተኛ ሃሳብ በህይወቷ ላይ የሚያመጣውን
ለውጥ ለማብላላት ብትወድም ፒተር ጊዜ አልሰጣትም፡፡ ፒተር እንደ ልጅነቱ አንገቱን ዘምበል አድርጎ ፊቷ ተገትሮ ‹‹መነጋገር ይቻላል?›› አላት፡

‹‹አይመስለኝም›› አለች በንዴት፡፡

‹‹ይቅርታ ልጠይቅሽ ነው የመጣሁት››

‹‹በፈጸምከው እምነት ማጉደል ይቅርታ ልትጠይቅ ነው፤ ስለተነቃብህ››
‹‹ሰላም እንዲወርድ ነው የምጠይቅሽ››
ዛሬ ሁሉም ሰው ከኔ ጋር ሰላም ለማውረድ ይፈልጋል አለች በሆዷ፡
‹‹ያደረስክብኝን በደል እንዴት ነው የምትክሰኝ?››
‹‹አልችልም›› አለ ከአፏ ነጥቆ ናት የለቀቀው ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ
‹‹ሪፖርትሽን ሳነበው ምን ያህል አቅም እንደሌለኝ ተረዳሁ፡፡ ኩባንያውን
ልመራ እንደማልችል ይገልጻል፡ እኔ እንደ አባታችን አይደለሁም፡ እህቴ የተሻለ እንደምትሰራ አውቃለሁ፡ ልቦናዬ እውነት መሆኑን ስለሚያውቅ እፍረት ተሰማኝ፡፡››

ይህም አንድ እርምጃ ነው አለች በሆዷ

‹‹እውነታው እብድ አድርጎኛል ናን፡›› ልጅ ሆነው እሱ ‹‹ናን›› ሲላት
እሷ ‹‹ፔቲ›› ትለው ነበር፡፡ ይህ አባባሉ የድሮውን አስታወሳትና ጉሮሮዋ ሳግ
ተናነቃት፡ ‹‹የማደርገውን አላውቅም›› አላት፡፡
ናንሲ ራሷን ወዘወዘች። ይሄ የተለመደ የፒተር ይቅር በሉኝ አነጋገር ነው፡ የምታደርገውንማ ታውቃለህ›› አለች አሁን ግን ከመናደድ ሀዘን ነው የተሰማት፡፡

ሰዎች በአየር መንገዱ ህንጻ አጠገብ ሲንጫጩ ፒተር ተናደደና
‹‹በባህሩ ዳርቻ እየተንጎራደድን እናውጋ›› አላት፡፡

ናንሲ ሲቃ ተናነቃት፡፡ ምንም ቢሆን ታናሽ ወንድሟ
ከተቀመጠችበት ተነሳች፡ ፒተር ይህን ሲያይ ፊቱ በደስታ በራ፡፡ ከዚያም
ወደ ባህር ዳርቻው ቀስ እያሉ መሄድ ጀመሩ፡፡ ናንሲ ታኮ ጫማዋን አውልቃ
በስቶኪንግ አሸዋው ላይ ትሄዳለች፡፡

ነፋሱ የፒተርን ጸጉር ሲገልጠው ጸጉሩ እየሸሸ መሆኑን አይታ ደነገጠች፡ ከዚህ በፊት ይህን ባለማየቷ ፒተር በራውን ለመሸፈን ጸጉሩን ወደፊት እያበጠረ መሆኑን ተረዳች፡፡ ይህም በተዘዋዋሪ የእሷን ማርጀት
ይጠቁማል፡

አጠገባቸው ማንም የለም፡፡ ‹‹ዳኒ ሪሌይ አንድ እንግዳ ነገር ነገረኝ፡፡
አባባ አንተና እኔ እንድንጣላ በማሰብ አንድ ሴራ ጠንስሷል››
ፒተር ግምባሩን ከሰከሰና ‹‹ለምን?›› ሲል ጠየቃት፡
‹‹ብርቱ እንድንሆን››
ፒተር በብሽቀት ሳቅ አለና ‹‹ታዲያ አመንሺው?››
‹‹አዎ ሳይሆን አይቀርም፡፡ እኔ ግን ቀሪው ህይወቴን በአባባ ተጽዕኖ
እንደማልኖር ወስኛለሁ››
ፒተር ራሱን ነቀነቀና ‹‹ምን ማለት ነው?›› አላት፡
‹‹ገና ያወቅሁት ነገር የለም፡፡ ምናልባት የናትን ጥያቄ ተቀብዬ የእኛን
ኩባንያ ከእሱ ኩባንያ ጋር እናዋህደዋለን››
ኩባንያው የጋራችን ሳይሆን ያንቺ ነው ናን››
ናን ወንድሟን አጤነችው፡፡ እውነቱን ይሆን? ወዲያው ለወንድሟ ክፉ እንደሆነች አላግባብ እንደጠረጠረችው ተሰማት፡ ጥርጣሬውን እንዲፍቅ ማድረግ እንዳለባት አወቀች
አሁን አሁን የተገነዘብኩት እኔ ለንግድ ስራ የተፈጠርኩ አለመሆኔና እንዳንቺ ላሉት ችሎታ ላላቸው ሰዎች መተው መሆኑን ነው››

‹‹ታዲያ ምን ልትሰራ አሰብክ?››

‹‹ያን ቤት መግዛት ነው የማስበው፡ አንድ ነጭ ቀለም የተቀባ ቤት አልፈው  ሄዱ፡ ‹‹እኔ እየዞርኩ  መዝናናት ነው የምፈልገው  አገር መጎብኘት››

ናንሲ ወንድሟን ክፉኛ በመጠራጠሯ አዘነች፡፡ ‹‹ቆንጆ ቤት ነው›
አለች፡፡ ‹ይሽጥ ይሆን?››
ቤቱ አጠገብ የሆነ የማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ አለ፡፡ ‹‹ቅድም እዚህ
መጥቼ ነበር፧ እንሂድና እንይ፡››

ቤቱን ዞረው ሲያዩ ተቆልፏል፡፡ የመስኮቶቹ ሻተሮች ስለተዘጉ ውስጡን
ማየት አልቻሉም ቤቱን ከውጭ ሲያዩት ቤቱ ደስ ይላል፡ በረንዳው በጣም ሰፊ ነው፡፡ ቤቱ ከጀርባው የቴኒስ ሜዳ አለው፡፡ ከቤቱ አጠገብ አንድ መስኮት
የሌለው አነስተኛ መጋዘን አለ፡፡ የጀልባ ማስቀመጫ ይመስላል፡ ‹‹ጀልባም
ሊኖርህ ይችላል›› አለች፡፡ ፒተር በጀልባ መዝናናት እንደሚወድ ታውቃለች፡፡
መጋዘኑን ከፈተና ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ትንሽ ቆየና ‹‹ወይኔ!›› ሲል ተሰማ
እሷም ወደ ውስጥ ስትገባ ጨለማው ተቀበላት፡፡ ‹‹ምንድነው ፔቲ?
ምን ሆነሃል?››
ፒተር ከኋላዋ ብቅ አለና እጇን ለቀም አድርጎ ያዘው፡፡ ፊቱ በድል ማድረግ ሲፈካ ስታይ እንደተታለለች አወቀች፡፡ ከዚያም እጇን እየጎተተ ወደ ውስጥ ወሰዳት፡፡ ናንሲ  ትጮሃለች፡፡ ጫማዋና ቦርሳዋ እዚህና እዚያ ወድቀዋል፡፡ አቧራማ ወለል ላይ ጥሏታል  ፒተር፡
‹‹ፒተርl›› ስትል ተጣራች በጭንቀት፡፡ ፈጠን ፈጠን እያለ ከመጋዘኑ ወጥቶ በሩን ዘጋባትና በጨለማ ተዋጠች፡፡ በጨለማ ውስጥ ሆና ‹‹ፒተር!
ፒተር!›› ብትል ማን ሊሰማ! ፍርሃት ወረራት። ከወደቀችበት ብትነሳም በሩ
ሲቀረቀር ተሰማት ‹‹ፒተር!›› ስትል ተጣራች ደጋግማ፡፡
መልስ የለም፡፡
ጨለማው የፈጠረባት ፍርሃት ጉሮሮዋን ተናነቃትና ጩሂ! ጩሂ አላት፡ ጨለማው ውስጥ ድንግር ብሏት ቆማለች፡፡ ፒተር ይህን ሁሉ ሲያቅድ እንደቆየ ተገነዘበች፡፡ ይህን ቤት ፈልጎ ተስማሚነቱን ካረጋገጠ በኋላ
አይሮፕላኑ ጥሏት እንዲሄድ አታሎ አምጥቶ ቆለፈባት፡፡ በዚህ ምክንያት ስብሰባው ላይ ስለማትገኝ ድምጽ መስጠት አትችልም፡ ይቅርታ መጠየቁ፣
መጸጸቱ፣ ስራውን ለመተው ማሰቡና ሃቀኛ መስሎ መታየቱ በሙሉ የሀሰት
ነበር፡ የበለጠ ሆዷን ለማራራት የልጅነት ትዝታቸውን አንስቶ አወራ፡
ታዲያ አመነችውና ሸጣት፡፡ ይህ ሁሉ ተደራርቦ ለለቅሶ ዳረጋት፡፡
ከለቅሶዋ መለስ ስትል ዓይኗም ጨለማውን ለመደና በበሩ ስንጥቅ
ብርሃን ታያት፡ ከሆነ ነገር ጋር እንዳትጋጭ ሁለት እጇን ወደፊት ዘርግታ የእውር ድምብሯን ወደ በሩ ተጠጋች፡፡ በሩጋ ስትደርስ ግድግዳውን በእጇ
እየደባበሰች ማብሪያ ማጥፊያ አገኘችና ስትጫነው የመጋዘኑ መብራት ወገግ አለ፡፡ የበሩን እጀታ ይዛ በሩን ለመክፈት ብትሞክርም አልሆነም: በሩን
ደህና አድርጎ ጠርቅሞታል፡ ባለ በሌለ ሀይሏ በትከሻዋ በሩን ገፋችው፡፡ በሩ
ግን ፈቀቅ አላለም፡፡

መጋዘኑ ውስጥ አምጥቶ ሲወረውራት ክርኗና ጉልበቷ በመጎዳቱ ቁስሉ ጠዘጠዛት፡፡ ‹‹አንተ አሳማ!›› ብላ ፒተርን በሌለበት ተሳደበች፡፡.....

......ይ🀄️ጥላል......

#መልካም ቀን ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት

      @Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን
       📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
Live stream finished (15 minutes)
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ስድስት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


መጋዘኑ ውስጥ አምጥቶ ሲወረውራት ክርኗና ጉልበቷ በመጎዳቱ ቁስሉ ጠዘጠዛት፡፡ ‹‹አንተ አሳማ!›› ብላ ፒተርን በሌለበት ተሳደበች፡፡
ጫማዋን አጠለቀችና ቦርሳዋን አንስታ ዙሪያውን ቃኘች። ሌላ በር አገኘችና ለመክፈት ብትሞክርም በጥብቅ የተዘጋ በመሆኑ መክፈት አልቻለችም::

ቤቱ ከባህር ዳርቻው የራቀ ቢሆንም የአይሮፕላኑ ተሳፋሪዎች ወይም
ሌላ ሰው በዚያ በኩል ሊያልፍ ይችላል፡፡ ናንሲም ጉሮሮዋ እስኪሰነጠቅ
‹‹የሰው ያለህ!›› ስትል ጮኸች፡

ጉሮሮዋ ደርቆ ድምጿ እንዳይዘጋ በየአንድ ደቂቃ ልዩነት አንድ ጊዜ
መጣራቷን ቀጠለች፡
ሁለቱም በሮች በወፍራም እንጨት የተሰሩና ግጥም ያሉ በመሆናቸው
ዲጂኖ ወይም ሌላ ብታገኝ ሰብራ ወይም ፈልቅቃ ትከፍተው ነበር፡፡
ምናልባትም አንድ የሆነ የእጅ መሳሪያ አገኝ ብላ አካባቢውን ቃኘች፡፡ የቤቱ
ባለቤት ዕቃውን በስርዓት የሚይዝ ኖሮ የእጅ መሳሪያዎቹን መጋዘኑ ውስጥ አልተዋቸውም፡፡ መጋዘኑ ውስጥ አንድም የሚታይ የአትክልት መኮትኮቻም ሆነ አካፋና ዶማ የለም፡፡

እንደገና ‹‹የሰው ያለህ!›› መልስ የለም፡፡

ቁጭ ብላ መተከዝ ሆነ ያላት አማራጭ፡ ኮቷን ይዛ በመምጣቷ ብርዱ
ብዙም አላስቸገራትም፡፡ መጣራቱን ባታቆምም ጊዜ እያለፈ ሲሄድ ተስፋዋ
እየተሟጠጠ ሄደ፡ ይሄን ጊዜ ተሳፋሪዎቹ አይሮፕላኑ ላይ እንደገና እየገቡ
ይሆናል፡፡ ጥቂት ቆይቶ እሷን ጥሎ ይበራል፡፡
በአሁኑ ሰዓት እያስጨነቃት ያለው ኩባንያውን ማጣቱ አይደለም፡፡አይበለውና ለሳምንት ያህል ሰው ወደ መጋዘኑ ዝር ባይል ምን ይውጣታል፡ እዚሁ ልትሞት አይደል፡፡ ይህም ጭንቀት ላይ ስለጣላት ያለማቋረጥ
ጩኸቷን አስነካችው፡፡

ጥረቷ ሁሉ አለመሳካቱን ስታውቅ ዝም ብላ ቁጭ አለች፡፡ ፒተር ክፉ
ሰው ቢሆንም ነፍሰ ገዳይ ስላልሆነ እዚህ እንድሞት አይተወኝም ብላ ገመተች፡፡ ሼዲያክ ፖሊስ መምሪያ ስልክ ደውሎ ከመጋዘኑ እንዲያወጧት ይነግራቸው ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከቦርድ ስብሰባው በፊት
አይነግራቸውም፡፡ ያለችበት ቦታ የማያሰጋ ቢሆንም ስጋት መፍጠሩ አልቀረም፡ ፒተር ካሰበችው በላይ ጨካኝ ቢሆንስ! ቢረሳትስ? ቢያመውስ?
ወይም የሆነ አደጋ ቢገጥመውስ? ታዲያ ከዚህ ማጥ ውስጥ የሚያወጣት
መቼም ማነው?

የአይሮፕላኑ ሞተሮች ሲያስገመግሙ ስትሰማ የነበራት ተስፋ ሁሉ ጨለመ  የገዛ ወንድሟ ለክፉ እንደዳረጋት መርቪንም ሊደርስላት እንደማይችል አወቀች፡፡ መርቪን ይህን ጊዜ አይሮፕላኑ ውስጥ ቁጭ ብሎ የአይሮፕላኑን መነሳት እየጠበቀ ይሆናል፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ሲያጣት ‹ምን ሆና ይሆን?› ማለቱ ባይቀርም በመጨረሻ የተለያዩት ‹‹አንተ ጅል!›› ብላ ሰድባው ስለሆነ ከእሷ ጋር አብቅቷል ብሎ ያስብ ይሆናል፡፡እንግሊዝ አገር ተከትለሽኝ  ነይ ማለቱ ብልግናውን ያሳያል፡ ሆኖም
ማንም ወንድ ይህን ስለሚል መናደድ አልነበረባትም፡፡ የተለያዩት በጥል ስለሆነ ካሁን በኋላ እንደማታገኘው ተገነዘበች፡፡ ‹‹ኩባንያዬንም ተነጠቅሁ፣
መርቪንንም ተነጠቅሁ፣ በረሃብም እሞታለሁ›› ስትል አላዘነች፡፡

ጉንጯ ላይ የፈሰሰውን እንባ በእጅጌዋ ጠረገች፡፡ ከእዚህ ችግር ለመውጣት ወገቧን ጠበቅ ማድረግ እንዳለባት ተገነዘበች፡፡ ከዚህ መውጪያ መንገድ መኖር አለበት፡፡ በዙሪያዋ በሩን ለመስበር የሚጠቅም አንዳች መሳሪያ ካለ ቃኘች፡ ግድግዳውን በጥፍሮቻቸው ፍቀው ከእስር ያመለጡ እስረኞች እንዳሉ  አስታወሰች፡፡ እሷ ደግሞ የዓመታት ጊዜ
የላትም፡፡ ከጥፍር የጠነከረ መሳሪያ ያስፈልጋታል፡፡ ቦርሳዋን ፈታተሸች፡፡
ከዝሆን ጥርስ የተሰራ ማበጠሪያ፣ ሊፒስቲክ፣ መሃረብ፣ የባንክ ቼክ ቡክ፣
ገንዘብ፣ ከወርቅ የተሰራ ብዕር አላት፡፡ ሁሉም በር ለመክፈት አይጠቅሙም
የለበሰችውን ልብስ ተመለከተች፡፡ ቀበቶ ታጥቃለች: የቀበቶ ማያያዣው
ምናልባት በሩን ለመቦርቦር ሊጠቅም ይችል ይሆናል፡ ቡርቦራው ረጅም ጊዜ
ሊወስድ ይችላል ነገር ግን ከዚህ ሌላ አማራጭ የለም፡፡

ወደ በሩ አመራች፡፡ በሩ ከወፍራም እንጨት የተሰራ ነው፡፡ በሩን በሙሉ መቦርቦር አይኖርባትም፡፡ የተወሰነ ጥልቀት ከቦረቦረች ሊሰበር ይችላል፡፡ እንደገና ለእርዳታ ተጣራች፡፡ የሚሰማ የለም፡፡ቀበቶዋን ስትፈታ ቀሚሷ ወለቀ፡  ከዚያም ቀሚሷን አጠፈችና
አስቀመጠችው፡ የሚያያት ሰው ባይኖርም የሚያምር ፓንት አድርጋለች፡፡

በአራት ማዕዘን ቅርጽ ቦረቦረች፡ የቀበቶው ማያያዣ ጠንካራ ባለመሆኑ
ተጣመመ: ቢሆንም ቡርቦራዋን ቀጠለች፡፡ በመሃል በመሃል የድረሱልኝ
ጥሪዋን ታሰማለች፡፡ በትዕግስት ስትፈቀፍቅ የእንጨት ፍግፋጊ መሬቱ ላይ መርገፍ ጀመረ፡፡ እንጨቱ ለስለስ ያለ ነው፡፡ አየሩ እርጥበት ስላለው
ቡርቦራዋን በተስፋ ቀጠለች፡፡ ስትቦረቡር የቀበቶው ማያያዣ እየወለቀ
ያስቸግራታል፡፡ እያነሳች ትቀጥላለች፡፡  አምስት  ስድስት ጊዜ እየወደቀ
እያነሳች ብትቦረቡርም ስራው ፈቀቅ አልል ሲላት ለቅሶዋን ለቀቀችው፡
በሲቃ በሩንም በጡጫ ደበደበች፡፡

ከውጨው ድምጽ ተሰማ፡፡ ‹‹ሰው አለ እዚህ›› አለ ድምጹ፡፡

ድምጹን ስትሰማ በሩን መደብደቧን አቆመች፡፡ በትክክል ድምጽ
ሰምታለች፡፡ ‹‹የሰው ያለህ! ከዚህ አውጡኝ›› አለች፡፡
‹‹ናንሲ አንቺ ነሽ?››
ናንሲ ልቧ በደስታ ዘለለ፡፡ የሰማችው ድምጽ የእንግሊዛውያን ቅላጼ
ያለው ነው፡፡ ድምጹንም አወቀችውና ‹‹መርቪን! ተመስገን አምላኬ!›› አለች፡፡
‹‹አንቺን ያልፈለግሁበት ቦታ የለም፡፡ እዚህ ምን ትሰሪያለሽ?››
‹‹ከዚህ ማጥ አውጣኝ መርቪኔ››

መርቪን በሩን ነቀነቀው፡፡ ‹‹ተዘግቷል!›› አላት
‹‹በጎን በኩል ና››
‹‹መጣሁ››
‹‹መርቪን?!››
‹‹በሩ ተቀርቅሯል፡፡ ትንሽ ጠብቂኝ›› አለ መርቪን፡፡
‹‹በፓንትና በስቶኪንግ ብቻ መሆኗ ትዝ አላትና ገላዋን በኮቷ ሸፈነች፡
ጥቂት ደቂቃ ቆይቶ በሩ ወለል ብሎ ተከፈተ፡፡ ሮጣ መርቪን ደረት ላይ
ተለጠፈች፡፡ ‹‹እዚህ ሞቼ እቀር ነበር›› አለችና ለቅሶዋን ለቀቀችው::
መርቪንም ደረቱ ላይ እንደተለጠፈች ጸጉሯን እያሻሽ ‹‹አይዞሽ
አይዞሽ!›› አላት፡፡
‹‹ፒተር ነው እዚህ የዘጋብኝ›› አለች ዓይኗ እምባ አቆርዝዞ::
‹‹ይሄ ወንድምሽ የሆነ በድብቅ የሚሰራው ነገር ሳይኖር አይቀርም፡፡
ወንድምሽ ርጉም ሰው ነው፡፡››
በአሁኗ ደቂቃ ናንሲ  ስለወንድሟ ሳይሆን ስለመርቪን ነው
የምታስበው፡፡ በእምባ በተንቆረዘዙ ዓይኖቿ መላ አካላቱን ቃኘችና ጊዜ
ሳታጠፋ ፊቱን አገላብጣ ሳመችው፡፡ ለጠቀችና ከንፈሮቹን በስሜት
ጨመጨመቻቸው፡ በዚህ ጊዜ የወሲብ ፍላጎቷ በእጅጉ ተነሳሳ፡፡ እሱም
አላሳፈራትም፡፡ እጆቹን ሰደደና ደረቱ ውስጥ ከቶ እቅፍ አደረጋት፡ እሷም
የእሱን ገላ ስለተራበች ከእቅፉ ውስጥ መውጣት አልፈለገችም፡: እጆቹን ወደ
ቂጧ ሲሰድ ፓንቷን ነካና ደንገጥ ብሎ አቆመ:

‹‹ቀሚስሽ የት ሄደ?›› ሲል ጠየቃት፡፡

‹‹በሩን ለመፈግፈግ ብዬ ቀበቶዬን ፈትቼው ስለነበር ቀሚሴም ያለቀበቶ
ወገቤ ላይ መቆም ስላልቻለ አሽቀንጥሬ ጣልኩት›› አለች እየሳቀች፡፡
‹‹እንዴት ጥሩ አጋጣሚ ነው›› አለና እጁን ሰዶ ቂጧንና ጭኗን መደባበስ ያዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ብልቱ ቆሞ ሆዷን ሲነካካት ታወቃት፡ እሷም ሱሪው ውስጥ እጇን ከታ ብልቱን ታሻሸው ጀመር፡
ሁለቱም በወሲብ ፍላጎት ጦዙ፡ ናንሲ እዚሁ ሴክስ ማድረግ ፈለገች፡፡
እሱም እንደዚሁ በግዙፍ መዳፉ ትናንሽ ጡቶቿን ይጎነታትላል፡፡ እሷም
እፍረቷን ጥላ እጇን ሰዳ የሱሪውን ዚፕ ከፍታ ብልቱን ጎትታ አወጣችው፡፡
ይህን እያደረገች እያለች ከዚህ ሰው ጋር ወሲብ ብፈጽም ምን ችግር
አለው፤ ሞቼ አልነበር! ከሞት ያተረፈኝ እኮ ይሄ ሰው ነው› አለች በልቧ፡
ይህ ሃሳቧ የበለጠ ሴክስ የማድረግ ፍላጎቷን አናረው:፡ አሁን ሁለቱም
በመሻፈዳቸው እያለከለኩ ነው፡፡ ትንሽ ፈንጠር አለችና ትንሿ እጇ ውስጥ
የተጋደመውን የመርቪንን ግዙፍ ብልት አየች፡፡በወሲብ ጉጉት እየተነዳችም
ላታቅማማ በጉልበቷ ተንበረከከች
ከተንበረከከችበት አንስቶ አቀፋትና ጣቶቹን በወሲብ ስሜት የረጠበው
ብልቷ ውስጥ ከቶ አፍተለተለው፡ ‹የት ጋ እንሂድና እናድርግ›› ስትል
ጠየቀችው።

‹‹እጆችሽን አንገቴ ላይ ጠምጥሚያቸው›› ሲላት እንዳላት አደረገች፡፡
እሱ ደግሞ በእጆቹ የቂጧን ፍንካቾች ያዝ አደረገና አንጠልጥሎ አነሳት፡
እሷ ለእሱ እንደ ገለባ የቀለለች ናት፡፡ ከዚያም ሁለቱን እግሮቿን ወገቡ ላይ
ጠምጥማ ከኋላው ቆልፋቸው ቀስ እያለች በተገተረው ብልቱ ላይ ተሰካች፡ወደላይ ወደታች እያለች ብልቱን ብልቷ ውስጥ እያጠለቀችና እያወጣች ታሾረው ጀመር፡ በዚህ ሁኔታ አስር ዓመት ብትቆይ በወደደች፡፡
እሱም ከላይ ሆና ስትጋልበው ባገኘው ደስታ ማቃሰት ጀመረ፡ ለዚህ
ደስታው እሷ ምክንያት መሆኗን ስታውቅ የበለጠ ስሜቷ ጨመረ፡ እሷም
ብዙ ከማታውቀው ሰው ጋር እንዲህ ያለ ወሲብ ያለ እፍረት መፈጸሟ
ሳይገርማት አልቀረም፡ በመጀመሪያ በቁሙ ተሸክሞ ሲያደርገኝ ይደክመው ይሆን?› ብላ አስባ ነበር፡፡ እሷ ከአፍ የወደቀች ጥሬ የምታክል መሆኗን እሱ ደግሞ ግዙፍ መሆኑን ስታውቅ ፍርሃቷ ለቀቃት፡፡ እሱም የቂጧን
ብርጭቆዎች አጥብቆ ይዞ ወደ ላይና ወደ ታች እየናጣት ይወስባታል፡
እግሮቿ በወገቡ ዙሪያ ተጠምጥመው ስለነበር በተከፈተው ብልቷ ውስጥ
ብልቱን ሲያስገባና ሲያወጣ  ስሜቷን መቆጣጠር
አቅቷት ትጮሃለች፡

ትንሽ ቆየችና ዓይኖቿን ከፈተቻቸው፡፡ እንደምትወደው ልትነግረው
ፈለገች፡፡ ነገር ግን አዕምሮዋ መልሶ ተይ ገና ካሁኑ› ሲል ሸነቆጣት፡ ያም
ሆነ ይህ እየወደደችው መጥታለች፡፡ ‹‹አንተ ነፍስ ነገር ነህ›› ስትል በጆሮው
አንሾካሾከች በሲቃ: እሱም በስሜት ስሟን እየጠራ ቶሎ ቶሎ ይከትባታል።
ዓይኖቿን ከደነቻቸውና ብልቷ አካባቢ ስለሚካሄደው የወሲብ ማዕበል ብቻ ትኩረቷን አደረገች፡፡ ብልቱን ሲከትና ሲያወጣ በሚነዝራት ስሜት
እየጮኸች መሆኗ ይታወቃታል፡፡

እሷን በቁሙ ተሸክሞ ሲወስባት ቢያለከልክም ምንም የመዛል ስሜት
አይታይበትም፡፡ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ የእሱን ስሜት እየጨመረው መሆኑን
ስታውቅ በደስታ ሲቃ ታቃስታለች፡፡ ላይ ታች እያለች ስትጋልበው
ስሜታቸው ጫፍ ደረሰና ፈነዳ፤ ሰውነታቸው በደስታ ተንቀጠቀጠ፡፡
በመጨረሻም ቀስ በቀስ እየቀዘቀዙ ሲመጡ ሰውነታቸው ተፍታታ፡ እሷም
ደረቱ ላይ ተለጥፋ አንገቱ ስር ተወሸቀች፡
እሱም ደረቱ ላይ እንደለጠፋት ‹‹አንቺ ሁልጊዜ እንደዚህ ነው ሴክስ የምታደርጊው?›› ሲል ጠየቃት፡፡

ጥያቄው ቢያስቃትም መልስ አልሰጠችውም::

ከዚያም መሬት ሲያወርዳት ተንገዳገደች፡፡ ልብሷን የለበሰችው እሱን
ተደግፋ ነው፡ ልብሷን የለበሰችው በፍላጎት አልነበረም፡፡ ዝንት ዓለም ከእሱ ጋር ራቁቷን ብትሆን በወደደች፡:

ከዚያ በኋላ ወጥተው ሲሄዱ እየተያዩ መሳሳቅ ብቻ፡፡ በዚህ ሁሉ መሀል ናንሲ ‹መርቪንን አግብቼ ኢንግላንድ መኖር እጣ ፈንታዬ ይሆን?
እያለች ታስባለች። ኩባንያውን በእጇ ለማስገባት የገጠመችው ጦርነት በእሷ ሽንፈት ተጠናቋል፡፡ የቦርዱ ስብሰባ ላይ በጊዜ መገኘት የምትችልበት ምንም
መንገድ የለም፤ ፒተር ደግሞ ድምጹን በድምጽ በመሻር መብቱ አክስታቸውን ቲሊንና ዳኒ ሪሌይን ስለሚያስከነዳ ኩባንያውን መቆጣጠሩ
አይቀርም፡፡ ልጆቿም በአይነ ህሊናዋ ድቅን አሉባት፡ እነሱ እንደሆነ አድገዋል፡ ከዚህ በኋላ የእሷን ድጋፍ አይሹም፡ አሁን ባለው ሁኔታ
መርቪን ፍቅረኛዋ እንዲሆን እንደምትፈልግ ተገንዝባለች፡፡ ከጥቂት ጊዜ
በፊት በፈጸሙት ወሲብ ትንሽ ድካምና መዛል ተሰምቷታል፡፡ ‹ኢንግላንድ
ውስጥ ምን ልሰራ እችላለሁ? የቤት እመቤት ልሆን አልችልም!›› ትላለች
በሆዷ፡
ባህሩ ዳርቻ ላይ ሆነው አሻግረው ይመለከታሉ፡፡ መርቪንን ስለምታስበው ነገር ልትጠይቀው ስትል እሱም አንድ ነገር ላይ አትኩሮ ይመለከታል፡፡ ምንድነው እንዲህ አትኩረህ የምታየው?› ስትል ጠየቀችው፡
በጣቱ አሻግሮ እየጠቆማት ‹‹እዚያ ጋር ባህር ላይ የሚያርፍ አይሮፕላን አይታይሽም? አዲስ የወጣ አይሮፕላን ነው፡፡ እነዚህ
አይሮፕላኖች ስራ ከጀመሩ እንኳን ሁለት ዓመት አልሆናቸውም፡:
ከመጣንባቸው አይሮፕላኖች ጋር ሲነጻጸሩ እነዚህ ፈጣን ናቸው›› አላት
ናንሲ አይሮፕላኑን ቃኘች፡፡ ዘመናዊ ነው፡፡ መርቪን የሚያስበው ገብቷታል፡፡ በዚህ አይሮፕላን ከተሳፈረች የቦርዱ ስብሰባ ላይ ትደርሳለች፡

‹‹አይሮፕላኑን መከራየት እንችል ይሆን?›› ስትል መርቪንን ጠየቀችው፡
‹‹እኔም ይህንኑ ነበር የማስበው››
‹‹እንጠይቅ?›› አለችና ወደ አየር መንገዱ ቢሮ በፍጥነት ገሰገች፡
መርቪንም በረጅም ቅልጥሙ ተፍ ተፍ እያለ ተከተላት፡ ልቧ ይመታል
ኩባንያዋን የማዳን እድል ይኖራት ይሆን? ሆኖም ደስታዋን በገደብ
ማድረግ አለባት፤ ላይሳካ ይችላል፡፡

አየር መንገዱ ቢሮ ሲደርሱ አንድ የፓን አሜሪካን አየር መንገድ ዩኒፎርም የለበሰን ሰው ‹‹አይሮፕላኑን አስመለጣችሁኝ አይደል?›› አለችና ‹‹ባህሩ ላይ የቆመውን አይሮፕላን የማን እንደሆነ ታውቃለህ?›› ስትል ጠየቀችውና
‹‹አውቃለሁ፡ አልፍሬድ ሳውዝቦርን ይባላል ባለቤቱ››
‹‹ያከራየዋል?››
‹‹አዎ፤ ልትከራዩት ትፈልጋላችሁ?››
ናንሲ ልቧ ክፉኛ መታ ‹‹አዎ›› አለችው፡
‹‹hፓይለቶቹ ውስጥ አንዱ እዚህ አለላችሁ›› ከዚያም ቀጥሎ ያለው ክፍል ውስጥ ገባና ‹‹ኔድ አይሮፕላንህን ሰዎች ሊከራዩት ይፈልጋሉ››
አለው፡፡
ኔድ ከጓዳው ክፍል ወጣ፡፡ እድሜው ወደ ሰላሳ የሚሆነው ጥርሱ
የማይከደን ሰው ነው፡፡ በአክብሮት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ልወስዳችሁ ዝግጁ ነኝ፧
ረዳት ፓይለቱ ግን እዚህ የለም፡፡ አይሮፕላኑ ደግሞ በሁለት ሰው ነው
የሚነዳው›› አላቸው፡
የናንሲ ልብ በደስታ የደለቀውን ያህል በድንጋጤም መታ፡
መርቪን ቀበል አደረገና ‹‹እኔ ፓይለት ነኝ›› አለው።
ኔድ በጥርጣሬ አየውና ‹‹ባህር ላይ የሚያርፍና ከባህር የሚነሳ
አይሮፕላን አብርረህ ታውቃለህ?›› ሲል ጠየቀው፡፡
ናንሲ ትንፋሿን ዋጠች፡
‹‹አዎ የውድድር አይሮፕላን አብርሬያለሁ›› አለው፡፡
‹‹ትወዳደራለህ ማለት ነው?››
‹‹ወጣት እያለሁ አዎ፧ አሁን ለመዝናናት ነው የማበረው፤ እኔም ትንሽ አይሮፕላን አለችኝ››
የውድድር አይሮፕላን ካበረርክ ለዚህ አይሮፕላን ረዳት አብራሪ
መሆን አያቅትህም፡፡ ባለቤቱ ነገ ነው የሚመጣው፡፡ የት ነው መሄድ የምትፈልጉት?››
‹‹ቦስተን››
‹‹አንድ ሺ ዶላር ትከፍላላችሁ››
‹‹እንከፍላለን›› አለች ናንሲ ቶሎ ብላ፤ ‹‹ነገር ግን አሁኑኑ መብረር
እንፈልጋለን፡፡››
ፓይለቱ የናንሲ ቀደም ቀደም ማለት ገርሞታል፡ ሰውየው ነው የጉዳዩ
ኃላፊ የመሰለው፡፡ ‹‹አሁን እንበራለን፤ እንዴት ነው ክፍያ የምትፈጽሙት?››
‹‹ቼክ እፈርምልሃለሁ፤ ከፈለክ ደግሞ ለኔ ኩባንያ የክፍያ ኢንቮይስ
መላክ ትችላለህ፡፡ ብላክ ቡትስ የጫማ ፋብሪካ ይባላል፡››
‹‹ብላክ ቡስት ፋብሪካ ነው የምትሰሪው?››
‹‹የኔ ንብረት ነው››
‹‹እኔም ያንቺን ጫማ ነው ያደረኩት››
ጫማውን ተመለከተችና ‹‹እንዴት ነው ተስማምቶሃል?›› ስትል
ጠየቀችው፡፡
‹‹በጣም ይመቻል፤ ጥሩ ጫማ ነው፡፡››
ናንሲ ፈገግ አለች፡፡....

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት

      @Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን
       📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ሰባት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ከሼዲያክ ወደ ቤይ ኦፍ ፈንዲ

አይሮፕላኑ ከካናዳ ወደ ኒውዮርክ ሲያቀና ማርጋሬት በጭንቀት ተወጥራለች ሄሪን ምን ዋጠው?› እያለች ታስባለች፡፡

ፖሊሶች ሄሪ በሃሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ አውቀዋል፡፡ ተሳፋሪዎቹም
ይህን ነው የተገነዘቡት፡ ፖሊሶቹ እንዴት እንደደረሱበት አልገባት ብሏታል ከያዙት ምን እንደሚያደርጉት ነው ያልታወቀው:: ምናልባትም ወደ እንግሊዝ አገር ይመልሱትና ጌጣጌጦቹን በመስረቁ እስር ቤት ይወረውሩት ይሆናል፤ ወይም ወደ ጦር ሰራዊት ውስጥ ይጨምሩታል። ታዲያ እንዴት ልታገኘው ነው?

እስካሁን እንዳልያዙት ግን አውቃለች፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ያየችው ሼዲያክ ላይ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ወደ መታጠቢያ ቤት ሲገባ ነው፡ ታዲያ ያኔ ይሆን ያቀደው? ችግር እንደደረሰበት አውቋል ማለት ነው፡፡
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን በሙሉ ቢያስሱም አላገኙትም፡፡ አይሮፕላኑ ሲያርፍ ሾልኮ ጠፍቷል ማለት ነው:: ታዲያ የት ሄደ? ምናልባትም
ከአይሮፕላኑ ወርዶ ጫካ ጫካውን እያሳበረና ሊፍት እየጠየቀ ሄዶ ይሆናል፡
ታዲያ ከዚህ በኋላ በዓይነ ስጋ ታየው ይሆን?

በዚህ ተስፋ መቁረጥ እንደሌለባት ተገንዝባለች፡፡ ሄሪን በማጣቷ ብትጎዳም ናንሲ አለችላት፡፡

አባቷ  ዓላማዋን ከማሳካት አያግዷትም፡ ለራሳቸው  ሁሉ ነገር የጠመመባቸውና ስደተኛ ስለሆኑ የማስገደድ ኃይላቸው ተዳክሟል፡ ሆኖም እንደ ቆሰለ አውሬ እንደገና አገርሽቶባቸው ዓላማዋን የሚያሰናክል ነገር ያደርጉ ይሆናል፡፡
አይሮፕላኑ ሽቅብ መጎኑን ጨርሶ የመቀመጫ ቀበቶዋን ፈትታ ናንሲን ለማነጋገር ሄደች።

አስተናጋጁ ለምሳ ጠረጴዛ እያዘጋጀ ነው፡፡ አባቷ ቦታቸው ላይ ቁጭ
ብለዋል ኦሊስ ፊልድ ከፍራንክ ጎርደን ጋር በካቴና ተጠፍሮ ቁጭ ብሏል፡
ማርጋሬት ወደ ሙሽሮቹ ክፍል ሄዳ ደጋግማ አንኳክታ ምላሽ ስታጣ በሩን
ከፈተች፤ ማንም የለም፡፡

በድንጋጤ ክው አለች፡፡

ምናልባትም ናንሲ መታጠቢያ ክፍል ውስጥ እየተቆነጃጀች ይሆናል፡
መርቪን ላቭሴይ የት ሄደ? ወደ መታጠቢያ ክፍል የሄደ ከሆነ ታየው ነበር ክፍሉ ውስጥ አንድ ቦታ ተደብቀው እንደሆን ቃኘች፡፡ ነገር ግን ምንም መደበቂያ የለም፡፡

የናንሲ ወንድም ፒተርና ጓደኛው የሙሽሮቹ ክፍል አጠገብ ተቀምጠዋል፡ ‹‹ሚስስ ሌኔሃን የት ነች?›› ስትል ጠየቀችው ፒተርን

‹‹ሼዲያክ ላይ ነው የወረደችው››

‹‹ምን አልክ?›› ስትል ጠየቀችው ‹‹አንተ እንዴት አወቅህ?››

‹‹ነግራኛለች››

‹‹ለምን ግን?›› ስትል ጠየቀችው ‹‹ለምንድነው የወረደችው?››

ፒተር የተሰደበ ያህል ተሰማው፡ ‹‹እኔ እንጃ›› ሲል መለሰላት፡ ‹‹ወደ ኒውዮርክ እንደማልሄድ ለፓይለቱ ንገርልኝ ነው ያለችኝ›› አላት ፊቱን አኮሳትሮ፡፡

ማርጋሬት ፒተርን በጥያቄ ማጣደፍ ነውር መሆኑን ብታውቅም አጥብቃ መጠየቁን አላቋረጠችም:፡ ‹‹ናንሲ የት ሄደች?››

ፒተር በዚህ ጊዜ አጠገቡ ያለውን ጋዜጣ አነሳና ‹‹እኔ የማውቀው ነገር የለም›› ሲል መልስ ሰጥቷት ማንበቡን ቀጠለ

ማርጋሬት ሆድ ባሳት፡ ናንሲ እንዴት እንዲህ ታደርጋለች አለች ምን ያህል በእሷ ላይ ተስፋዋን እንደጣለች ታውቃለች፡ ሆኖም
ነገር ሳይገጥማት ከመንገዷ አልተስተጎለችም መልእክት ትታ ይሆናል።

ከአስተያየቱ የነገራት ውሽቱን እንደሆነ ጠረጠረች ማርጋሬት እንደ ፖሊስ ስለመረመረችው ደስ አላለውም፡፡ በደመነፍስ ‹‹እውነቱን አይደለም
የነገርከኝ›› ስትል አፈጠጠችበት፡፡ አባባሏ ትክክል ባይሆንም ምላሹን ግን ትጠብቃለች፡፡

ፒተር ፊቱ በንዴት ቲማቲም መስሏል፡ ‹‹እንደ አባትሽ ጋጠወጥ ነሽ ከፊቴ ጥፊ!›› አላት፡

የፒተር ስድብ አንገቷን አስደፋት። ያባትሽን መጥፎ ባህሪ ይዘሻል ከሚል ስድብ በላይ የምትጠላው ነገር የለም፡፡ ምንም ሳትተነፍስ ውልቅ ብላ ሄደች፤ በዓይኗ እንባ እንደሞላ አልፋ ስትሄድ ውቧን የመርቪንን ሚስት ዳያና ላቭስሌይን አየቻት። አይሮፕላኑ ውስጥ ያለው ተጓዥ በሙሉ ባሏን
ከድታ ከፍቅረኛዋ ጋር ስለኮበለለችው ሚስትና መልሶ በእጁ ለማስገባት አገር አቋርጦ ስለተከተላት ባሏና ቦታ አጥቶ ባሏ ከሞተባት ሴት ጋር በሙሽሮች ክፍል ውስጥ ለመዳበል የመገደዱን ወሬ በደስታ እየተቀባበለ ሲያወጋ ነው የሰነበተው፡፡ ማርጋሬት ባሏና ናንሲ የት እንደገቡ ዳያና ታውቅ እንደሆን መጠየቅ ፈለገች፡፡ በርግጥ ይህን ጥያቄ መጠየቅ የሚያሳፍር ቢሆንም መጥፋታቸው አሳስቧታል፡፡ ዳያና አጠገብ ተቀመጠችና ‹‹ይቅርታ መርቪንና ናንሲ የት እንደገቡ ታውቂ ይሆን?›› ስትል ጠየቀቻት፡ ዳያና ጥያቄው አስገርሟት ‹‹ምን ሆኑ? በሙሽሮች ክፍል ውስጥ የሉም እንዴ?››

‹‹ጭራሽ አይሮፕላኑ ውስጥ የሉም፡፡ እኛ ስንሳፈር እነሱ ቀርተዋል››

‹‹እውነት?›› ዳያና ደነገጠች አጠፋፋቸውም እንቆቅልሽ ሆኖባታል፡
‹‹እንዴት ሊሆን ይችላል? አይሮፕላኑ አመለጣቸው እንዴ?››

‹‹የናንሲ ወንድም ጉዞውን ለማቋረጥ ወስነዋል ቢልም አላመንኩትም›› አለች ማርጋሬት፡፡

ሁለቱም ለኔ የነገሩኝ ነገር የለም›› አለች ዳያና፡፡ ‹‹ብቻ ክፉ ነገር.አይድረስባቸው::››

‹‹ምን ማለትሽ ነው ማርዬ?›› ሲል ጠየቃት ፍቅረኛዋ፡፡

‹‹ክፉ አይንካቸው ነው ያልኩት?››

ማርጋሬትም የዳያናን ሃሳብ መቀበሏን ራሷን በመነቅነቅ ገለጸች፡

‹‹ወንድምየውን ግን አላመንኩትም፡፡ የተናገረው ውሸት ይመስለኛል››

ማርክም ቀበል አደረገና ‹‹እኔም ይመስለኛል፡፡ አሁን አየር ላይ ስለሆንን የሚሆነውን ከመጠበቅ በስተቀር ማድረግ የምንችለው ነገር የለም››
‹‹ከዚህ በኋላ የሚያደርገው ነገር አያገባኝም›› አለች ዳያና መናደዷ በግልጽ እየታወቀባት፡፡ ‹‹የአምስት ዓመት ባሌ ስለሆነ ግን ክፉ እንዲያገኘው አልፈልግም፤ ያስጨነቀኝ ደግሞ ይኸው ነው››

‹‹አሜሪካ ስንደርስ ከእሱ መልእክት እናገኝ ይሆናል›› አለ ማርክ በማስተዛዘን አይነት፡፡

‹‹እስቲ እሱ ይሁነና›› አለች ዳያና፡፡

አስተናጋጁ የማርጋሬትን ክንድ ነካ አደረገና ‹‹ክብርት ማርጋሬት ምሳ ደርሷል፧ ቤተሰቦችሽ ለመብል ተሰይመዋል›› አላት

‹‹አመሰግናለሁ›› አለች ማርጋሬት ‹የምግብ አፒታይቴ ተዘግቷል፡፡››

ማርጋሬት ለመሄድ ስትነሳ ዳያና ‹‹ከናንሲ ጋር ወዳጅ ናችሁ?›› ስትል ጠየቀቻት፡፡
በፋብሪካዋ ውስጥ ስራ ልትቀጥረኝ ቃል ገብታልኝ ነበር›› አለች ማርጋሬት በምሬት፡፡ ከንፈሯን እንደነከሰች ዞራ ሄደች፡፡

እናትና አባቷ እንዲሁም እንዲሁም ፔርሲ የመጀመርያው ዙር ምግብ
ቀርቦላቸዋል፡ ማርጋሬትም እንደተቀመጠች ‹‹ይቅርታ አባባ ስለዘገየሁ››
አለች፡፡ የቀረበላትንም ምግብ ትቆነጣጥራለች፡ አልቅሽ አልቅሽ አላት፡ ሄሪና
ናንሲ ሳይነግሯት እብስ ብለዋል፡ አሁን የሚረዳት የለም፡ እንደ እህቷ
ኤልሳቤት ለመኮብለል አስባ ነበር አሁን ግን ሁሉ ነገር ተበላሽቶባታል፡

ሁለተኛው ዙር ምግብ ቀረበ፡፡ ሾርባ ነው፡፡ ሾርባውን አንድ ጊዜ ፉት
አደረገችና ተወችው: ድካምና ንዴት በአንድ ላይ ተሰማት አሟታል፡ የምግብ ፍላጎቷ ተዘግቷል፡ ምቹው አይሮፕላን እስር ቤት
ሆኖባታል፡ ለሃያ ሰባት ሰዓት ስለበረሩ ጉዞው ሰልችቷቸዋል፡ እናቷ
ፊታቸው ገርጥቷል፡፡ ድካም ይነበብባቸዋል፡ ድብርት ተጫጭኖአቸዋል።
ዓይኖቻቸው በእንቅልፍ እጦት በርበሬ  መስለዋል፡፡ ፔርሲ ቅዥቅዥ ያደርገዋል፡፡ አባቱን በክፉ ነው የሚያያቸው፡ ለጠብ ያሰፈሰፈ ይመስላል
ከፊት ለፊቷ ያሉትን ደባሪ ቀኖች አሰበች ማርጋሬት፡፡ በኒውዮርክ ሆቴል ከአባት ከእናቷ ጋር ነው የምትቆየው፡፡ ሄሪ ወደ መኝታ ክፍሏ አሸምቆ ሊመጣ አይችልም፡፡ እሱን እያሰበች ብቻዋን ትተኛለች፡፡ ከእናቷ ጋር ገበያ ለገበያ ትዞራለች፡ ከዚያ ወደ መኖሪያቸው ኮኔክቲከት ስቴት ይሄዳሉ።እሷን ሳያማክሯት የፈረስ መለማመጃና ቴኒስ ክለብ ያስመዘግቧታል፡
ፓርቲም እንድትሄድ ያዟታል፡፡ ከዚያ በኋላማ እናቷ ከከተማው ትላልቅ
ሰዎች ልጆች ጋር እንድትወዳጅ የሻይ ግብዣ በመጋበዝ ያስተዋውቋታል፡
አገሯ እንግሊዝ የጦርነት ወላፈን እየገረፋት እንዴት ነው እሷ እዚህ
የምትምነሸነሸው? ይሄን ባሰበችው ቁጥር ሀዘኗ ይበረታል፡፡

ማርጋሬት የቀረበላትን አይስክሬም ልሳ ጨረሰች፡፡

አባቷ ብራንዲና ቡናቸውን ጨልጠው ሲያበቁ ጉሮሯቸውን እህህ እህህ
በማለት አጸዱ፡ አንድ ነገር ማለት ፈልገዋል፡ መቼም ትናንትና ራት ላይ ለፈጸሙት አሳፋሪ ድርጊት ይቅርታ ሊጠይቁ እንዳልሆነ መገመት አያስቸግርም::

‹‹እናትሽና እኔ ስላንቺ ተነጋግረናል›› ሲሉ ንግግራቸውን ጀመሩ፡
‹‹ልክ ትዕዛዝ እንደማትቀበል ገረድ ቆጥራችሁኛል›› ስትል ማርጋሬት ጮኸች::

እናትም ቀበል አደረጉና ‹‹ሞገደኛ ልጅ ነሽ›› አሏት

«አስራ ዘጠኝ ዓመት ያለፈኝ ወጣት ነኝ እንዴት እኔን ልጅ
ትሉኛላችሁ?››

‹‹ዝም በይ!›› ሲሉ እናት ተቆጡ፡፡ አባባሏ አስደንግጧቸው ‹‹እንዲህ
አይነት የብልግና ቃል በአባትሽ ፊት ከተናገርሽ ገና ህጻን ልጅ ነሽ ማለት
ነው›› አሉ፡
‹‹በቃ ተዉኝ!›› አለች ማርጋሬት፡፡
አባትም ቀበል አደረጉና ‹‹የምታሳይው ጋጠወጥ ባህሪ የምንለው
እውነት መሆኑን ያመለክታል፡ በደህናው ህብረተሰብ መካከል ገብተሽ ትኖሪያለሽ ብለን አናምንም››

‹‹ለዚህ አምላክ ይመስገን!›› አለች ማርጋሬት፡

ፔርሲ ይህን ሲሰማ ከት ብሎ ሳቀ፤ አባት በፔርሲ አድራጎት ቢናደዱም
እሱን ናቅ አድርገው ማርጋሬትን ‹‹ብትበጠብጪም አንድ ብዙም ችግር
የማትፈጥሪበት ቦታ እንልክሻለን››

‹‹ገዳም ልትልኩኝ ነው?››

እንደዚህ የብልግና መልስ ሰጥታ ባታውቅም ንዴታቸውን እንደምንም
ዋጥ አድርገው ‹‹እንዲህ አይነት ንግግር አይረባሽም›› አሏት፡፡

‹‹አይረባሽም! ለመሆኑ ለእኔ ጥሩ የሆነው የቱ ነው:፡ የሚወዱኝ ወላጆቼ የእኔን ፍላጎት በማክበር የወደፊት ህይወቴን ይወስኑብኛል፣ ሌላ
ምን እፈልጋለሁ›› አለች በምሬት፡፡

‹‹ማርጋሬት አንቺ ጨካኝ ነሽ›› አሉና እናት ለቅሷቸውን ለቀቁት፡፡

ማርጋሬት በዚህ ጊዜ ልቧ ተነካ። እናቷ ሲያለቅሱ ስታይ ጉልበቷ ተብረከረከባት፡፡ ከዚያም ድምጿን አለሳልሳ ‹‹ታዲያ ምን ላድርግ እማማ?››
ስትል እናቷን ጠየቀች፡፡

‹‹አክስትሽ ክሌር ዘንድ ትኖሪያለሽ›› አሉ አባት፡ ‹‹ቬርሞንት ስቴት
ውስጥ ቤት አላት፡፡ የምትኖሪው ተራራ ስር እና ሩቅ ስለሆነ የምታሳፍሪው
ሰው አጠገብሽ የለም››
እናትም ጨመሩና ‹‹እህቴ ጥሩ ሴት ናት፡: ባል አላገባችም፡፡ የአካባቢው
ኤጵስ ቆጶስ ቤተክርስቲያን ዋና አባል ናት፡፡››

ማርጋሬት እንደገና ብስጭት ቢወራትም ንዴቷን ዋጥ አድርጋ ‹‹አክስቴ ክሌር ስንት አመቷ ነው?›› ስትል ጠየቀች።

‹‹ከሃምሳ ዓመት በላይ ይሆናታል››

‹‹ብቻዋን ነው የምትኖረው?››

‹‹ገረዶች ካልተቀጠሩ አዎ››
ማርጋሬት በንዴት ተንዘፈዘፈች፡፡ ‹‹ለብቻዬ ልኑር ባልኩ ነው ይሄ
ሁሉ ቅጣት!›› አለች ድምጿ እየተንቀጠቀጠ፤ ‹‹ምን ባጠፋሁ ነው ቆማ ከቀረች መበለቲት ጋር ተራራ ስር እንድኖር የተፈረደብኝ፤ ለመሆኑ ምን ያህል ጊዜ ነው እዚያ የምቆየው?››

‹‹አደብ እስክትገዥ ድረስ›› አሉ ‹‹አንድ አመት ያክል››
‹‹ዓመት!›› እድሜ ልክ መሰላት ማርጋሬት ‹‹ጅል አትሁኑ፤ ልታግቱኝ
አትችሉም ወይ አብዳለሁ ወይ ደግሞ እሞታለሁ ወይ ደግሞ አገር ጥዬ እጠፋለሁ›› አለች፡፡
‹‹ያለኛ ፈቃድ የትም ንቅንቅ አትይም፤ከፈቃዳችን ውጭ ብትሆኚ ደግሞ. . ›› አሉና ንግግራቸውን አቋረጡ፡፡

ማርጋሬት አባቷን ገረመመቻቸው ሊል ያሰበው ነገር አሳፍሮት
መናገር አቃተው› አለች በሆዷ፤ ምን ሊል ፈልጎ ነው?›

ከዚያም ከንፈራቸውን ሸርመም አድርገው ‹‹ከአክስትሽ ቤት ብትኮበልይ አዕምሮዋ በሽተኛ ናት ብለን የእብዶች ሃኪም ቤት እናዘጋብሻለን››

ማርጋሬት በንዴት ትንፋሿን በረጅሙ ለቀቀች መናገር አቃታት እንዲህ አይነት ጭካኔ አባቴ ይፈጽምብኛል ብላ አስባ አታውቅም፡ ወደ
እናቷ ፊቷን ስታዞር ዓይኗን ማየት አቃታቸው፡፡

ፔርሲ ከመቀመጫው ተነስቶ የአፍ መጥረጊያ ሶፍቱን ጣለና ‹‹አንተ
ጅል ሽማግሌ! አላበዛኸውም አሁንስ!›› አለና ጥሎ ሄደ፡ ፔርሲ ይህን ያለው ከሳምንት በፊት ቢሆን አልቆለት ነበር፡፡ ነገር ግን ስድቡን ናቅ አድርገው ምንም ሳይሉት ተዉት፡፡

ማርጋሬት አባቷ ላይ አፈጠጠች፡፡ ፊታቸው ላይ የሚነበበው የጸጸት
ስሜት ነው፡፡ የተናገሩት ተገቢ እንዳልሆነ ቢያውቁም ከአቋማቸው ንቅንቅ አላሉም፡፡

ከዚያም ስትረጋጋ ‹‹አባባ በቁሜ ቀብረኸኛል›› አለች፡፡
እናትም ድምጽ ሳያሰሙ አነቡ፡፡

ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡

#መልካም ቀን ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት

      @Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን
       📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ስምንት

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ድንገት የሞተሩ ድምጽ ተለወጠ፤ሁሉም ተሳፋሪ የሆነውን ሁሉ ባለማወቁ በፍርሃት ረጭ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ተንቀጠቀጠና ወደ ታች መውረድ ጀመረ፡

አራቱም ሞተሮች በአንድ ጊዜ ሲጠፉ የኤዲም ዕጣ ፈንታ አብሮ ተዘጋ።

ችግር ከመከሰቱ በፊት ሃሳቡን ቢለውጥ ኖሮ ይሄ ችግር አይመጣም፡፡
ሃሳቡ በውጥን ላይ ብቻ ቢቀር አይሮፕላኑ ሰላማዊ መንገዱን ይጓዝ ነበር
አሁን ግን ምንም ሆነ ምን ችግሩ ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጦ መጥቷል፡፡ ከዚህ በኋላ እንደተሳፋሪ መብረር ካልሆነ በስተቀር የበረራ መሀንዲስ መሆን አይችልም፡፡ አልቆለታል። በንዴት ስህተት እንዳይሰራ
መጠንቀቅ አለበት፡ ይህን ዕቅድ በርጋት መከወን አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ
ህይወቱን ያመሰቃቀሉበት ርጉሞች ላይ ይዘምታል።

አይሮፕላኑ በድንገት ባህር ላይ ማረፍ ሊገደድ ነው: ሚስቱን ያገቱበት ወሮበሎች አይሮፕላኑ ላይ ይወጡና ፍራንክ ጎርዲኖን ያስፈታሉ፡ ከዚያ በኋላ የሚሆነው አይታወቅም:፡ ካሮል አን ደህና ስለመሆኗ ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ወሮበሎቹ ወደ አይሮፕላኑ ሲመጡ የጠረፍ ጠባቂ
ፖሊሶች አደጋ ይጥሉባቸው ይሆናል፡፡ ኤዲ በዚህ ስራ ውስጥ ለፈጸመው እስር ቤት ይወረወር ይሆናል፡፡ እሱ እጣ ፈንታው ሆኖ እዚህ ውስጥ በመግባቱ ነው
ለእስር  የሚበቃው።ካሮል አንን በደህና እጁ እንዳስገባ ሌላ የሚፈልገው ነገር የለም::

የአይሮፕላኑ ሞተሮች ቀጥ ካሉ ከአፍታ በኋላ የካፒቴን ቤከር ድምጽ በጆሮ ማዳመጫው መጣና ‹‹ምንድነው ነገሩ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ኤዲ በድንጋጤ አፉ ስለደረቀበት ከመናገሩ በፊት ሁለት ጊዜ ምራቁን ዋጥ አደረገ ‹‹ገና አላወቅሁትም›› አለና  መለሰ፤ ነገር ግን መልሱን ያውቃል፡ ሞተሮቹ መስራት ያቆሙት ነዳጅ ስላለቀ ነው፡፡ እሱ ነው ነዳጅ
ወደ ሞተሮቹ እንዳይደርስ ሆን ብሎ ያደረገው። አይሮፕላኑ ስድስት የነዳጅ
ታንከሮች ያሉት ሲሆን ነዳጅ ወደ ሞተሮቹ የሚያደርሰው ክንፉ ላይ ባሉት
ታንከሮች አማካይነት ነው፡፡ ወደ ሞተሮቹ ነዳጅ
የሚያመጡትን ፓምፖች ሆን ብሎ እንዳይሰሩ አድርጓቸዋል፡፡ ሌላ ኢንጂነር
ቢያየው ሆን ብሎ እንዳይሰሩ እንደተደረጉ ያውቅበታል፡

ረዳት ኢንጂነሩ ሚኪ ፊን ተራው ባይደርስም ድንገት ሊመጣ ይችላል ብሎ ተጨንቋል፡ ነገር ግን ሚኪ እንቅልፉን እየለጠጠ ይሆናል ይህን ጊዜ፡
በረራው ረጅም ጊዜ የሚወስድ በሚሆንበት ጊዜ ከስራ ውጭ ያሉ
የአይሮፕላኑ ሰራተኞች ይተኛሉ፡

ሼዲያክ ላይ ሁለት ጊዜ አስፈሪ የፖሊስ ምርመራዎች ነበሩ፡
የመጀመሪያው ፖሊሶች አይሮፕላኑ ላይ የተሳፈረውን የፍራንኪ ጎርዲኖ
ግብረ አበር ስም ማወቃቸውን ገልጸው ነበር፡፡ ኤዲ ሉተርን ማለታቸውን
ገምቷል በዚህም ምክንያት ሉተር  አልቆለታል ብሎ  ካሮል አንን የሚያስለቅቅበትን ሌላ ስልት ማውጠንጠን ጀምሮ ነበር፡፡ በኋላ ደግሞ
ፖሊሶቹ ሄሪ ቫንዴርፖስትን እንደሚፈልጉ ሲገልጹ ኤዲ ጮቤ ረገጠ፡፡ከድንጋጤው መለስ ሲል ከሃብታም ቤተሰብ የተወለደ የሚመስለው ቫንዴርፖስት ለምን በሀሰት ፓስፖርት እንደሚጓዝ ገርሞታል፡የፖሊሶችን ትኩረት ከሉተር ወደ ራሱ እንዲዞር በማድረጉ ቫንዴርፖስትን በሆዱ እግዚአብሔር ይስጥህ  ብሎታል፡።
ፖሊሶችም በምርመራው  ብዙም ሳይገፉበት ርግፍ አድርገው ተዉት፡ ስለዚህ ሉተር ተረዳና በዕቅዱ መሰረት እነ ኤዲ የጀመሩትን ሊያከናውኑ ተነሱ፡፡
የፖሊሶችን

ለካፒቴን ቤከር ግን የተፈጸመው ሁሉ ጥርጣሬን የሚቀሰቅስ ሆኖበታል፡፡ ኤዲ ገና ከድንጋጤው ሳያገግም አንድ ድንገተኛ ሃሳብ ይዞ ብቅ አለ፡፡ አይሮፕላኑ ላይ ጎርዲኖ
ተባባሪ አለው ማለት እሱን ነጻ ለማውጣት የተዘጋጀ ሰው አለ ሲል ደመደመ፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖን ከአይሮፕላኑ ላይ ማስወረድ ፈለገ፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የኤዲ እቅድ ውሃ በላው ማለት ነው፡፡

ህግ እንዳይከበር በማድረጉ በህግ እንደሚጠይቀው የኤፍ.ቢ.አዩ ኦሊስ ፊልድ ካፒቴን ቤከር ላይ ዝቶ ነበር፡፡ በመጨረሻ ካፒቴኑ ኒውዮርክ ለሚገኘው ለፓን አሜሪካን አየር መንገድ መስሪያ ቤት ስልክ ደውሎ ለችግሩ መፍትሄ እንዲሰጡ ነገራቸው፡፡ አየር መንገዱም ጎርዲኖ በአይሮፕላኑ
መጓዙን እንዲቀጥል ሲፈቅድለት ኤዲም በእፎይታ ተነፈሰ፡፡

ሼዲያክ ላይ አንድ አስደሳች መልዕክት ደረሰው፡፡ የመጣው የኮድ
መልዕክት ከጓደኛው ስቲቭ አፕል ባይ መሆኑ አያጠራጥርም፡ መልዕክቱም አንድ የባህር ኃይል ጀልባ አይሮፕላኑ የሚያርፍበት አካባቢ ጥበቃ እያደረገ መሆኑንና እንዳይታወቅ ከእይታ ውጭ ሆኖ ወደ አይሮፕላኑ የሚጠጋ ማንኛውንም ጀልባ ለመምታት የተዘጋጀ መሆኑን ይገልጻል፡

ይሄ ለኤዲ ትልቅ ነገር ነው፡፡ በኋላ ወሮበሎቹ ከህግ እንደማያመልጡ
ማረጋገጫ ቢሰጠውም ዕቅዱ ግን ያለምንም እንከን ባሰበው መልኩ
እንዲጠናቀቅ እንቅፋት እንዳይፈጠር ምኞቱ ነው፡፡
ካፒቴን ቤከር ወደ ኤዲ መጣ፡፡ ኤዲ እጁ እየተንቀጠቀጠ ለሞተሩ ነዳጅ የሚመግበውን ፓምፕ ከፈተውና ‹‹ታንከሩ ባዶ ስለሆነ ሞተሩ አልነሳ አለ›› አለው::

‹‹ለምን?›› ሲል ካፒቴኑ ተቆጣ፡፡

ኤዲ መልስ አልነበረውም፡፡
የአይሮፕላኑ መሳሪያዎች በመጠባበቂያ ነዳጅና በመጋቢ ቧንቧዎቹ
መካከል የነዳጅ እንቅስቃሴ ወይም ግፊት መኖሩን አያሳዩም፡ ፓይለቶቹ ጋ
ግን የነዳጅ ሁኔታን የሚያሳዩ የነዳጅ መቆጣጠሪያዎች አሉ ካፒቴኑ ሁሉንም በየተራ አየና ‹‹ምንም ነዳጅ የለም›› አለ፡፡ ‹‹በክንፉ ላይ ባለው
ታንከር ውስጥ ምን ያህል ነዳጅ አለን?›› ሲል ጠየቀ፡፡
‹‹ትንሽ ነው የቀረው - የተወሰኑ ኪሎ ሜትሮች ብቻ የሚያስኬድ››
‹‹እንዴት ነው ይህን ያላስተዋልከው?›› ሲል ጠየቀ በቁጣ፡

‹‹እኔ ፓምፕ እያደረገ ነው የመሰለኝ›› አለ ኤዲ በተቆራረጠ ድምጽ
ይህ መልስ ግን ካፒቴኑን አላጠገበውም፡፡

‹‹ሶስቱም ፓምፖች እንዴት ባንድ ጊዜ ስራ ሊያቆሙ እንደቻሉ አልገባኝም›› አለ ካፒቴኑ።

‹‹ቶሎ ባህር ላይ ካላረፍን የቀረው ነዳጅ ተንጠፍጥፎ አይሮፕላኑ ሊወድቅ ይችላል›› አለ ኤዲ፡፡

‹‹ባህር ላይ ልናርፍ ስለሆነ ሁላችሁም ተዘጋጁ›› አለ ቤከር፡፡ ጣቱንም ኤዲ ላይ እያወዛወዘ ‹‹አንተ አታስፈልገኝም አላምንህም›› አለው፡

ኤዲ ሞቱን ተመኘ፡፡ ካፒቴኑ ላይ ክህደት ለመፈጸም በቂ ምክንያት እንዳለው ቢያውቅም የፈጸመውን ድርጊት አልወደደውም፡ ህይወቱን በሙሉ
ሃቀኛ ሆኖ ነው የኖረው:: አጭበርባሪዎችንና አታላዮችን አጥብቆ ይጠላ
ነበር፡፡ አሁን ግን የሚጠላውን ነገር ለማድረግ ተገዷል፡
ካፒቴኑ ናቪጌተሩ ጋ በመሄድ ቻርቱ ላይ ዓይኑን ተከለ፡፡ ናቪጌተሩ ጃክ
አሽፎርድ ኤዲን በግርምታ ገረመመውና ‹‹አሁን ያለነው እዚህ ላይ ነው››
ብሎ ቻርቱ ላይ በመጠቆም ለካፒቴኑ አሳየው፡፡

የኤዲ ዕቅድ ሊሳካ የሚችለው አይሮፕላኑ እሱ ባሰበው ቦታ ከወረደ
ነው፡፡ ወሮበሎቹ እዚህ ቦታ ላይ ነው የሚጠብቁት፡፡ ነገር ግን ድንገት
የሚፈጠር ነገር ካለ ከታሰበው ውጭ ሊደረግ ይችላል፡፡ ካፒቴኑ ሌላ ቦታ
ከመረጠ ግን ኤዲ እሱ ያለው ቦታ የተሻለ ስለሆነ እዚያ ማረፍ እንዳለበት
ካፒቴኑን ማሳሰቡ አይቀርም፡፡ ካፒቴኑ ሊጠረጥር ቢችልም እዚህ ቦታ ከማረፍ የተሻለ ነገር እንደሌለ በሎጂክ መቀበል ይኖርበታል፡ ሌላ ቦታ
እንዲያርፍ የሚያደርግ ከሆነ ግን ትክክል የማይሆነው እሱ ነው፡፡ ስለዚህ የእሱ ጣልቃ ገብነት አያስፈልግም ማለት ነው፡፡ ትንሽ ቆየና ‹‹እዚህ ጋ ነው የምናርፈው›› አለ ካፒቴኑ፡
ኤዲ በተቀዳጀው ድል መደሰቱን ካፒቴኑ እንዳያውቅበት ዞር አለ፡፡
ለካሮል አን እየደረሰላት መሆኑን አረጋገጠ፡፡ ኤዲ በመስኮት ወደ ታች ባህሩን ሲቃኝ አንድ ነጭ መርከብ ውሃ ላይ እንደተጣለ ኳስ ሲዋልል አየ፡፡ ባህሩ ማዕበል አዘል ስለሆነ ለአይሮፕላን አይመችም፡፡

ልቡን ቀጥ ሊያደርግ የሚችል ድምጽ ከአንድ አቅጣጫ መጣ::
‹‹አይሮፕላኑ በድንገት ሊያርፍ ነው›› አለ ሚኪ ፊን፡፡

ኤዲ ሚኪ ፊን ላይ በፍርሃት አፈጠጠ፡ ሚኪ የእጅ ፓምፑ ላይ ያለው ቫልቭ እንደማይሰራ አውቋል፡፡ ስለዚህ እሱን ከዚህ ቦታ ማራቅ ይኖርበታል፡ ካፒቴን ቤከር ደረሰለት፡ ‹‹ሚኪ ከዚህ ጥፋ!›› ሲል ተቆጣ
ፈረቃቸው ያልሆኑ ሰራተኞች አይሮፕላኑ ድንገት ሲያርፍ የመቀመጫ
ቀበቷቸውን አስረው ነው መቀመጥ ያለባቸው እንጂ የማይረባ ጥያቄ
ለመጠየቅ እዚህ እዚያ አይሉም: ሚኪ ከአካባቢው በሮ ሲጠፋ ኤዲ እፎይ አለ፡፡

አይሮፕላኑ ወደ መሬት ማዘቅዘቅ ጀመረ፡ ነዳጁ ከተጠበቀው ጊዜ
በፊት አልቆ አይሮፕላኑ ከመከስከሱ በፊት ማረፍ የተሻለ ነው ብሎ አምኗል፡፡

ደሴቷን አልፎ ላለመሄድ ሲሉ ወደ ምዕራብ አጠመዘዙ፡፡ ነዳጅ
አልቆባቸው አይሮፕላኑ መሬት ላይ ከወደቀ ለወሬ ነጋሪ የሚተርፍ አንድም
ሰው አይኖርም ባህሩ ላይ አራት ሜትር ያህል ከፍታ ያለው ከባድ ማዕበል ይታያል በዚህ ሁኔታ አይሮፕላኑን ማሳረፍ አስቸጋሪ ነው፡፡ ኤዲ በፍርሃት ጥርሱ ተፋጨ
ኤዲ ለህይወቱ ፈራ፡
አይሮፕላኑ አየር ላይ ቢሆንም የሞተሩ  አለመስራት ፍጥነቱን
በመቀነሱ ከፍታውን ጠብቆ መብረር አልቻለም፡፡ በተቃራኒው የመሬት ስበት
ወደ ታች ይስበዋል፡፡ ስለዚህ ሲያርፍ መንሸራተት ሳይሆን ውሃው ላይ
በሆዱ ይወድቃል፡ የአይሮፕላኑ ሆድ በስስ አሉሙኒየም የተሰራ በመሆኑ እንደ ካርቶን ሊበጫጨቅ ይችላል፡
እስኪያርፍ በጭንቀት ጠበቀ፡፡ አይሮፕላኑ ወርዶ ከውሃው ጋር ሲላተም ሰቀጠጠው፡፡ የአይሮፕላኑ መስኮቶች በውሃ ተሸፈኑ። ወደ አንድ ጎን ሲያዘነብል ወምበሩ ላይ በቀበቶ ባይታሰር ኖሮ ይጋጭ ነበር፡
ውሃው ላይ ለማረፍ ሲነሳ ሲወድቅ በፍርሃት የተዋጠው የተሳፋሪዎች
ጩኸት በረታ፡

ትንሽ ቆየና አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ቀጥ ብሎ መሄድ ጀመረ፡ በኋላም
ባህሩ ላይ ቆሞ ላይ ታች ማለት ያዘ፡፡ ሞተሮቹ እያጓሩ ነው፡፡ ትንሽ በትንሽ
ኤዲ ፍርሃቱ እየለቀቀው መጣ፡፡

ኤዲ ጀልባ ይኖር እንደሆን ለማየት በመስኮቱ አሻግሮ ተመለከተ ጸሃይ የወጣ ቢሆንም ደመና እያንዣበበ ነው፡፡ በአካባቢው ጀልባ አይታይም ወደ መቀመጫው ተመለሰና ሞተሮቹን አጠፋቸው፡፡ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ
የድረሱልኝ ጥሪውን እያሰማ ነው፡፡ ‹‹እስቲ ልሂድና ተሳፋሪውን ላረጋጋ››
አለ ካፒቴኑ፡

የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ለድረሱልኝ ጥሪው ምላሽ ያገኘ ሲሆን ኤዲ ምላሽ የሰጡት የጎርዲኖ ሰዎች እንዲሆኑ ተመኘ፡

ለማወቅ ጓጓ፡፡ ኤዲ የአይሮፕላኑን በር ከፈተ፡፡ የባህር ሞገዱ የሚረጨው ውሃ ጫማውን እያራሰው ነው፡፡ ጀምበር ከደመናው ኋላ ገባች፡ አይሮፕላኑን ቃኘው ምንም አልሆነም፤ ጭረት እንኳን የለበትም፡፡
ኤዲ መልህቁን ባህሩ ላይ ጣለና ዙሪያ ገባውን ቃኘ - የሆነ ጀልባ አይ ይሆን ብሎ፡፡ የሉተር ሰዎች የት ደረሱ? የሆነ እክል ተፈጥሮ ይሆን?ካልመጡስ ምንድነው የሚደረገው? ሲል ተጨነቀ፡፡ ትንሽ ቆይቶ አንድ የሞተር ጀልባ በሩቅ ታየች፡፡ ልቡ ደለቀ፡፡ ይሄ ይሆን ጀልባው? ካሮል አን
ውስጡ ትኖር ይሆን? በድንገት የወረደውን አይሮፕላን ሊታደግ የመጣ
ጀልባ ሊሆን ይችላል ሲል ተጨነቀ ውጥኑን ሊያበላሽ የመጣ፡፡

ጀልባው ወደ እነሱ መጣ  በማዕበሉ ላይ ታች እያለ እየቀረበ ሲመጣ
ትልቅ ጀልባ መሆኑን አየ፡ ጀልባው ላይ አራት ለዎች ይታያሉ፡ ሶስት ወንዶችና አንዲት ሴት ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች ካሮል አን ደግሞ
ሰማያዊ ቀሚስ አላት፡፡

እሷ ናት ብሎ ገምቷል፡፡ ነገር ግን ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ ሴትየዋ
ጸጉሯ ነጣ ሰውነቷ ቀጠን ያለ ነው፡፡ እሷም እንዲሁ ናት፡፡ ከወንዶቹ ፈንጠር ብላ ነው የቆመችው፡፡ ጸሃይ እንደገና ስትመጣ ሴትየዋ እጇን ወደ ወታደር ሰላምታ ሰጪ ግምባሯ ላይ አደረገች፡፡ ጀልባው እየተጠጋ ሲመጣ
ሚስቱ መሆኗን አወቀ፡

‹‹ካሮል አን›› ሲል ተጣራ፡፡

ደስታ ወረረው፡፡ የገቡበትን አደጋ ለጊዜው ረስቶ ዳግም ሲያገኛት ደስታው ወደር አጣ፡፡ ምድር ጠበበችው፡፡ ‹ሮል አን›› ‹ሓሮል አን›› ሲል
ደጋግሞ ተጣራ::

ድምጹን ስትሰማ ለየችው፡፡ እሱ ይሆን አይሆን እያለች በመጠራጠር እጇን ቀስ እያለች ነበር የምታውለበልበው፡፡ በኋላ እሱ መሆኑን ስታውቅ
ግን ክንዷ እስኪገነጠል እጇን አወናጨፈች፡፡
‹እጇን ማወናጨፍ የቻለችው ደህና ብትሆን ነው የኔ ካሮል› አለ በሆዱ
ደስታው ሆዱን እያሞቀው፡፡
ሆኖም ገና ነገሩ እንዳላለቀ ተረዳ፡ ብዙ የሚሰራው ነገር ስላለ እጁን እንደገና አውለበለበና አይሮፕላኑ ውስጥ ገባ፡፡ደ

ወደ ውስጥ ሲገባ ከካፒቴን ቤከር ተገናኙና ‹‹አይሮፕላኑ ጉዳት ደርሶበታል?›› ሲል ጠየቀው ቤከር፡

‹‹ምንም አልሆነም››
ካፒቴኑ ወደ ሬዲዮ ኦፕሬተሩ ሲዞር ‹‹የድረሱልኝ ጥሪያችንን ሰምተው
ብዙ መርከቦች እየመጡልን ነው፡፡ አንድ ጀልባ ግን አይሮፕላናችን ጋ
እየቀረበች ነው፤ እያቸው›› አለ ኦፕሬተሩ፡፡ ቀጠለና ‹‹ጀልባዋ ላይ ያሉት
ሰዎች አይሮፕላኑ ውስጥ እንግባ እያሉ ነው›› አለ፡፡
‹‹አይሆንም›› አለ ካፒቴኑ፡ በዚህ ጊዜ ኤዲ ተበሳጨ፡ ‹መግባት አለባቸው አለ ኤዲ በሆዱ፡፡ ቤከርም ቀጠለና ‹‹ጀልባውን ከአይሮፕላኑ ጋር እንዳታስሩት፤ የአይሮፕላኑ ውጫዊ ክፍል ይጎዳል፡፡ በዚህ ማዕበል ውስጥ
ከአይሮፕላኑ ወደ ጀልባው ሰው ስናዛውር ባህሩ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ
ልትረዱን ስለመጣችሁ እናመሰግናለን፤ ነገር ግን እርዳታችሁ አያስፈልገንም
በላቸው›› አለው፡
ኤዲ ያልጠበቀው ነገር ተከሰተ፡ ጭንቀቱንም ለመደበቅ ሲል ምንም
ያልመሰለው ለመምሰል ሞከረ፡ አይሮፕላኑ ከፈለገ ግንጥልጥሉ ሊወጣ
ይችላል፡ የሉተር ወዳጆች አይሮፕላኑ ላይ መውጣት አለባቸው ይህ ሊሆን
የሚችለው ግን አይሮፕላኑ ውስጥ የሚረዳቸው ሰው ካለ ነው፡፡ አንድ ሰው
ገመድ ወጥሮ ካልያዘላቸው ሊገቡ አይችሉም ታዲያ እንዴት ብለው አይሮፕላኑ ውስጥ ይግቡ› አለ በሆዱ፡፡
ሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹መግባት እንደማይችሉ ብነግራቸው በጀ አላሉም›› አለ ለካፒቴኑ

ኤዲ ወደ ውጭ ሲመለከት ጀልባዋ አይሮፕላኑን ትዞራለች፡

‹‹ከምንም አትቁጠራቸው›› አለ ካፒቴኑ፡

ኤዲ ወደ ውጭ ሊወጣ ሲሄድ የት ነው የምትሄደው?› ሲል ተቆጣ
ካፕቴኑ።

መልህቁን በትክክል ጥዬው መሆኑን ላረጋግጥ ነው አለና ከካፒቴ መልስ ሳይጠብቅ ከአይሮፕላኑ ወጣ፡፡

‹ይሄ ሰው በቅቶኛል›› አለ ቤከር፡፡

እኔም አውቄዋለሁ ይህን አስቀድሜ አለ ኤዲ በሆዱ፡ ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ብዙም አትርቅም፤ ካሮል አን በደምብ ትታየዋለች፡፡ ስራ
ስትሰራ የምትለብሰውን አሮጌ ቀሚስና ጫማ ለብሳለች ሊወስዷት ሲመጡ በስራ ልብሷ ላይ አለኝ የምትለውን ኮት ደርባለች ፊቷ ገርጥቷል፤ ኤዲ በዚህ ጊዜ ደሙ ፈላ፤ አልለቃቸውም! አለ በሆዱ። ከዚያም እጁን ጀልባዋ
አሳያቸው:፡ ሰዎቹ የሚያደርገው እስኪገባቸው ድረስ ብዙ ጊዜ ገመዱን
ላይ ላሉት ሰዎች አውለበለበና ገመዱን እንዲወረውሩለት በምልክት
አወዛወዘ ልምድ የሌላቸው መርከበኞች መሆናቸው ወዲያው ነው የገባው፡
የለበሱት ሙሉ ልብስና ንፋሱ ኮፍያዎቻቸውን እንዳይወስድባቸው በእጃቸው ተጭነው መያዛቸው ለአካባቢ እንግዳ እንደሆኑ ያሳያል፡ የጀልባው ነጂ በባህር ሞገዱ ምክንያት ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ጋር እንዳትጋጭ ለማድረግ
ስራ በዝቶበት ይታያል፡፡ በመጨረሻ ከሰዎቹ አንዱ የኤዲ ገመድ የማወዛወዝ
ምልክት ገባውና ገመዱን አነሳ፡፡ ልምድ የሌለው ገመድ ወርዋሪ በመሆኑ
ኤዲ ገመዱን የቀለበው ከአራት የውርወራ ሙከራ በኋላ ነው፡፡

ኤዲ ገመዱን ቀለበው፡ የጀልባው ነጂ ጀልባዋን ወደ አይሮፕላኑ ለማስጠጋት እየሞከረ ነው:፡ ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ጋር ስትነፃፀር ትንሽ በመሆኗ በማዕበሉ ውዝዋዜ ምክንያት በጣም ላይና ታች ትል ነበር፡ ስለዚህ ከአይሮፕላኑ ጋር ማሰር ከባድ ስራ ሆኖ ነበር፡
ኤዲ ገመዱን ለማሰር ሲታገል ሚኪ ፊን አየውና

‹‹ኧረ ለመሆኑ ምን
እያደረግህ ነው?›› ሲል ጠየቀው፡፡

ኤዲም ዞር አለና ‹‹አያገባህም ሚኪ ተጠንቀቅ ጣልቃ እገባለሁ ብትል አይሮፕላኑ ውስጥ ያሉት ሰዎች ይጎዳሉ›› አለው፡፡

ሚኪ ፈራ ‹‹እሺ እንዳልክ›› አለና ተመለሰ ኤዲ አብዷል ብሎ እያሰበ፡፡ ጀልባዋ አይሮፕላኑን ተጠግታለች፡፡ ሶስቱን ሰዎች አያቸው: አንዱ ዕድሜው ከአስራ ስምንት አይበልጥም፡፡ ሌላው ደግሞ አርጀት ብሎ ቀጨጭ ያለ ሲሆን አፉ ላይ ያለው ሲጋራ ማዕበሉን ተከትሎ ይወዛወዛል፡፡ ሶስተኛው ሰው ባለመስመር ሙሉ ልብስ የለበሰ ሲሆን አዛዣቸው ይመስላል፡፡

ጀልባውን ከአይሮፕላኑ ጋር በደንብ ለመጠፈር ሁለተኛ ገመድ እንደሚያስፈልግ ኤዲ ተረዳ፡፡ ‹‹ሌላ ገመድ ወርውሩልኝ›› ሲል እጁን አፉ ላይ ደቅኖ ተናገረ ድምጹ በደንብ እንዲሰማቸው፡፡
ባለ መስመር ልብስ የለበሰው ሰው ሌላ ገመድ አነሳና ለኤዲ አሳየው፡
‹‹ኤዲ እሱ አይሆንም! ሌላ ጠንካራ ገመድ  ወርውርልኝ›› አለ፡፡
ሰውዬው ኤዲ ያለው ገባውና ሌላ ገመድ ሲወረውር ኤዲ ቀለብ አድርጎ ጀልባውን አይሮፕላኑ ጋር ጠፈረው፡፡ ጀልባዋ ቀስ እያለች ወደ አይሮፕላኑ
ተጠጋች፡፡ ከዚያም የጀልባዋ ሞተር ጠፋና ቱታ የለበሰ ጀልባ ነጂ ገመዱን
ወጥሮ ያዘ፡፡ ይህ ሰው በእርግጥም መርከበኛ ነው፡፡

ኤዲ ከወደ አይሮፕላኑ ድምጽ ሰማ፡፡ ድምጹ የካፒቴን ቤከር ነው፡፡
‹‹ቀጥታ ትዕዛዝ ጥሰሃል›› አለው ኤዲን፡፡

ኤዲ የካፒቴኑን ትዕዛዝ ከምንም አልቆጠረውም፡፡ ለተወሰነ ጊዜም
ጣልቃ እንዳይገባ ነው ፍላጎቱ፡

ቤከር ኤዲን ‹‹ና አሁኑኑ›› ሲል ጮኸ፡፡

ባለመስመር ሙሉ ልብስ የለበሰው የወሮበሎቹ መሪ ዘሎ ወደ አይሮፕላኑ ለመግባት ሲዘጋጅ ከኋላው የቆመው ቤከር ጃኬቱን ሲጎትት ወሮበላው ሽጉጡን ለመምዘዝ ኪሱን ደባበሰ፡፡

ኤዲ ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች መካከል አንዱ ነሽጦት ወሮበሎቹን እተናነቃለሁ ቢል ሊሞት ይችላል ብሎ ነው የሚፈራው፡፡
ወዳጁ ስቲቭ አፕልባይ የባህር ኃይል ጀልባ ይዞ እየመጣ መሆኑን
ቢነግራቸው በወደደ፤ ነገር ግን አይሮፕላኑ ላይ ያለው የወሮበሎቹ ግብረ
አበር ሰዎቹን ሊያስጠነቅቅ ይችላል ብሎ ገምቷል፡ ወደ ቤከር ዞር አለና

‹ካፒቴን ዞር በል ከዚህ እነዚህ ሰዎች መሳሪያ ይዘዋል››

ቤከር ይህን ሲሰማ ደነገጠ፡ ወሮበላውን አየና ወደ ኋላ አፈገፈገ፡
ሰውየው ቤከር ወደ ኋላ መመለሱን ሲያውቅ ሽጉጡን መልሶ ኪሱ
ከተተው፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ጋር አታካራ ብገጥም ተሳፋሪዎቹ ሊሞቱ
ይችላሉ› ሲል አሰበ፡፡

የወሮበሎቹ መሪ ኤዲ የያዘለትን ገመድ ይዞ ወደ አይሮፕላኑ መግቢያ
ዘለለ፤ ኤዲም ሰውየው እንዳይወድቅ ያዝ አደረገው፡፡

‹‹አንተ ነህ ኤዲ?›› ሲል ጠየቀ፡፡

ኤዲ ይህን ድምጽ ወዲያው ለየው። በስልክ የሰማው ድምጽ ነው፡፡

‹‹ቪንቺኒ›› ብሎ ጠበቅ አድርጎ ተናገረ የስድብ ያህል፡ በኋላ ግን በአባባሉ
ተፀፀተ፡፡ ይህ ሰው ሚስቱን በማዳን በኩል እንዲተባበረው በእጅጉ
ይፈልጋል፡፡ ‹‹ሁሉ ነገር እንዳሰብነው ያለ እንከን እንዲፈፀም መተባበር
አለብን››

ቪንቺኒ ፊቱን እንዳኮሳተረ ‹‹እሺ ነገር ግን ሌላ ነገር አደርጋለሁ ብለህ
የምትሞክር ከሆነ ህይወትህን ታጣለህ›› አለ አነጋገሩ ቀጥተኛ ሲሆን
ድምጹም አስፈሪ ነው፡፡

‹‹ጓደኞችህን እስካስገባ ድረስ ውስጥ ቆየኝ›› አለው ኤዲ ቪንቺኒን፡፡

‹‹እሺ›› አለ ቪንቺኒ ወደ ጀልባዋ ፊቱን አዞረና ‹‹ጆ መጀመሪያ አንተ ና
ቀጥሎ ትንሹ ልጅ በመጨረሻ የኤዲ ሚስት፡፡›› ወደ ውስጥ ሲያዩ ካፒቴኑ ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ሲሄድ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ቪንቺኒ ሽጉጡን
መዘዘና ‹‹አንተ ባለህበት ቁም›› ሲል አዘዘው ቤከርን፡፡

#መልካም ቀን ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት

      @Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን
       📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_አርባ_ዘጠኝ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ

‹‹እሺ›› አለ ቪንቺኒ ወደ ጀልባዋ ፊቱን አዞረና ‹‹ጆ መጀመሪያ አንተ ና
ቀጥሎ ትንሹ ልጅ በመጨረሻ የኤዲ ሚስት፡፡›› ወደ ውስጥ ሲያዩ ካፒቴኑ ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ሲሄድ አየው፡፡ በዚህ ጊዜ ቪንቺኒ ሽጉጡን
መዘዘና ‹‹አንተ ባለህበት ቁም›› ሲል አዘዘው ቤከርን፡፡
ኤዲም ካፒቴን እንደሚልህ አድርግ እባክህ እነዚህ ሰዎች ቀልድ አያውቁም›› አለ ቤከር ባለበት ቆመና እጁን ወደ ላይ አነሳ፡፡

ጆ የተባለው ወሮበላ ‹‹እዚህ ውስጥ ብወድቅ መዋኘት አልችልም›› አለ
ከጀልባው ወደ አይሮፕላኑ መዝለል ፈርቶ፡፡

‹‹መዋኘት አያስፈልግም›› አለ ኤዲ እጁን ዘረጋለት፡፡

ጆም እንደምንም ዘለለና አይሮፕላኑ ውስጥ ገባ፡፡
ከእሱ በፊት ሁለት ሰዎች በደህና መዝለላቸውን አይቶ ትንሹ ልጅ ኮራ ብሎ ዘለለ፤ ነገር ግን ሲዘል ሚዛኑን ሳተና ወደኋላው ሊወድቅ ሲል ኤዲ የልጁን ቀበቶ ይዞ አዳነው ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ ልጁ፡፡

አሁን የካሮል አን ተራ ደረሰ ለመዝለል ፈርታ የኤዲን አይን አይን ታያለች በተፈጥሮዋ ፈሪ ሆና ሳይሆን ከእሷ በፊት ትንሹ ልጅ ተንገዳግዶ ባህር ውስጥ ሊገባ ሲል ስላየች ነው የፈራችው፡፡ ኤዲም ፈገግ አለና
‹‹እንደነሱ ዝለይ ማርዬ›› አለ ‹‹አይዞሽ ውሃ ውስጥ አትወድቂም::››

ኤዲ በፍርሃት ልቡ እየደለቀ በጉጉት ጠበቀ ሚስቱ እስክትዘል፡፡ ካሮል
አን መዝለል መቻሏን ተጠራጠረች፡፡ ‹‹ተዘጋጂና ዝለይ!›› አላት እሱም የእሷ
ፍርሃት ተጋብቶበት፡፡

ካሮል አን ጥርሷን ነክሳ እንደ ምንም ዘለለች፤ ነገር ግን ግማሽ አካሏ ባህሩ ውስጥ ሆኖ ገመዱን ለመያዝ ተፍጨረጨረች፤ ‹‹ገመዱን አጥብቀሽ
ያዥ አይዞሽ›› አለ ወደ ባህሩ የምትወድቅ ከሆነ ለመዝለል ተዘጋጅቶ
ኤዲ ተንበረከከና እጇን ለመያዝ እጁን ሰደደ፤ ሆኖም ሚዛኑን ሳተና ወደ
ባህሩ ሲወድቅ እጇን መያዝ አልቻለም፤ የባህሩ ሞገድ ጎትቶ ውሃ ውስጥ
ሲያስቀራት በተስፋ መቁረጥ ጮኸች፡፡

ያለ የሌለ ሀይሏን ተጠቅማ ወደ ኤዲ እየዋኘች ተጠጋች፤ ኤዲ ጥርሷ
ሊንገጫገጭ አየ፧ እንደ ምንም ብሎ እግሯን ያዘ፤ ሆኖም የባህሩ ሞገድ
ሃይለኛ በመሆኑ ከእጁ አፈተለከችና እንደገና ባህሩ ላይ ወደቀች፤ ካሮል አን
እየሰመጠች ነው እሱም እጁን ሰደደና ወገቧን ያዘ፡፡

‹‹አይዞሽ የኔ ማር ይዤሻለሁ›› አለና እንደምንም ተሸክሞ ወደ
አይሮፕላኑ አስገባት፡፡ ካሮል አን ባሏ  እቅፍ ውስጥ ገብታ ማንባቷን ቀጠለች፡፡ እምባ ቢተናነቀውም እንደምንም ዋጥ አደረገው፡፡የምትንቀጠቀጠውን
ሚስቱን ለማረጋጋት አጥብቆ ደረቱ ላይ ለጠፋት
‹‹ደህና ነሽ የኔ ማር? እነዚህ ሰዎች አንገላቱሽ?›› ሲል ጠየቃት

‹‹ደህና ነኝ›› አለች ጥርሷ እየተንገጫገጨ፡፡

የካፒቴኑን ዓይን ለማየት ፈርቶ እየሰረቀ ያየዋል፡፡ ቤከር ወደ ካሮል
አን አማተረና
‹‹ያደረግኸው ሁሉ ለምን እንደሆነ አሁን እየገባኝ መጣ›› አለ፡፡
‹‹ይበቃል የምንሰራው ስራ አለን›› አለ ቪንቺኒም፡፡
ኤዲ ካሮል አንን ለቀቃትና ‹‹እሺ ወደምትፈልጉት ሰው እወስዳችኋለሁ››
‹‹እሺ›› አለ የወሮበሎቹ መሪ፡
‹‹ተከተሉኝ›› አላቸውና ወደ ውስጥ ገቡ፡ ሰራተኞቹ ምንም ነገር ለማድረግ እንዳይሞክሩ ኤዲ አስጠነቀቃቸው:
‹‹ሁላችሁም አደብ ግዙ፡፡ እነዚህ ሰዎች አድርጉ የሚሏችሁን ማድረግ
ብቻ ነው ያለባችሁ አለበለዚያ በጥይት ከመግደል ወደ ኋላ የሚሉ ሰዎች አይደሉም፡ ሰው እንዲጎዳ አልፈልግም፡ ካፒቴኑም ይህንኑ ነው የሚላችሁ አለ ኤዲ፡

‹‹ትክክል ነው›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ጎበዝ! እነዚህ ሰዎች መሳሪያ የያዙ ናቸው፤ ብትወራጩ በጥይት ነው የሚሏችሁ ››
ኤዲ ወደ ቪንቺኒ ዞረና ‹‹እንሂድ እንግዲህ፤ ካፒቴን ተሳፋሪዎቹን ማረጋጋት ይኖርብሃል›› አለ፡፡

ቪንቺኒ በኤዲ አባባል መስማማቱን በራሱ ንቅናቄ አሳየ፡
‹‹ካሮል አን ከአይሮፕላኑ ሰራተኞች ጋር ሁኚ፧ እሺ›› አላት፡፡

ኤዲ ሚስቱ ከወሮበሎቹ ጥይት መራቋን ወዶታል፡ በተጨማሪም ባሏ
ለምን እነዚህን ሰዎች ሊተባበር እንደወሰነ ለተሳፋሪዎቹ ታስረዳለታለች፡
ኤዲ ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ጠመንጃህን ከተሳፋሪዎች ብታርቅልኝ፧ ይፈራሉ››
‹‹ተነፋ!›› አለ ቪንቺኒ ‹‹እንሂድ›› ሲል አዘዘ ጓደኞቹን፡ ኤዲ ትከሻውን
በንዴት ነቀነቀ፡፡ ሁሉም ቦታ ቦታቸው ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡ ሁለቱ አስተናጋጆች ምንም እንዳልተፈጠረ ሁሉ ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ ነው፡፡
ኤዲ አይሮፕላኑ ውስጥ እየተዘዋወረ ሲያይ መብል ክፍሉ ትርምስምስ
ብሏል፡፡ ወለሉ በሸክላ እና በብርጭቆ ስብርባሪ ተሸፍኗል። ምግብ ተበልቶ
ስላለቀና ተሳፋሪዎች እየጠጡ ስለሆነ የተደፋፋ ነገር አይታይም፡:
ተሳፋሪዎቹ የቪንቺኒን ሽጉጥ ሲያዩ በፍርሃት ድምጻቸውን አጠፉ፡፡ ካፒቴን
ቤከር ወደ ፊት መጣና ‹‹ክቡራንና ክቡራት ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ
እጠይቃለሁ፡ ከመቀመጫችሁ እንዳትነሱ፡ አሁን ያለው ችግር ከተወሰነ
ደቂቃ በኋላ መፍትሄ ያገኛል›› አለ፡፡

ኦሊስ ፊልድና ፍራንኪ ጎርዲኖ አብረው ቁጭ ብለዋል አሁን ነፍሰ
ገዳይ እንዲያመልጥ ላደርግ ነው አለ ኤዲ ለራሱ፡ ወደ ጎርዲኖም ጣቱን እየጠቆመ ‹‹ያውልህ ሰውዬህ ውሰደው›› አለ፡፡
ኦሊስ ፊልድ ከተቀመጠበት ተነሳና ‹‹ይሄ የኤፍ ቢ አይ መርማሪ ቶሚ ማክ አርድል ነው›› አለ ‹‹ፍራንኪ ጎርዲኖ ትላንት በመርከብ ኒውዮርክ ደርሶ ወህኒ ገብቷል››
‹‹የአምላክ ያለህ!›› ሲል ኤዲ በግርምት ጮኸ፡፡ ይህን ሁሉ እኩይ ተግባር ሲፈጽም የነበረው ለአስመሳይ ሰው ነው?!

‹‹እኛ ከፍራንኪ ጉዳይ የለንም፡፡ ጀርመናዊው ሳይንቲስት የታለ?›› አለ ቬኒቺኒ

ኤዲ ተገርሞ ቪንቺኒ ላይ አፈጠጠ፡፡ ጎርዲኖን አይፈልጉትም፡፡ ታዲያ
ማንን ነው የሚፈልጉት?ተ

የቶም ሉተር ድምፅ ተሰማ ‹‹እዚህ ነው ያለው፤ በእኔ ቁጥጥር ስር  ነው›› አለ ሉተር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን እየደገነ፡፡ተ

ኤዲ የበለጠ እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡ የፓትሪያርካ ማፊያ ቡድን ለምንድን ነው ካርል ሃርትማንን ማገት የፈለገው?› ‹‹ሳይንቲስቱን ለምንድን ነው የምትፈልጉት?› ሲል ጠየቀ፡፡

ቀበል አድርጎ ‹‹ተራ ሳይንቲስት እንዳይመስልህ የኒኩሊየር ፊዚስት
ነው›› አለ ሉተር፡

‹‹እናንተ ናዚ ናችሁ?›› ሲል ጠየቀ ኤዲ፡፡

‹‹አይደለንም፧ እኛ ዲሞክራቶች ነን፡፡ እነሱ ሳይንቲስቱን አግተን
እንድንሰጣቸው ስራ አዘውን ነው፡ ረብጣ ገንዘብ ይከፍሉናል›› አለና ቪንቺኒ
ተንከተከተ፡

ሉተርም ‹‹እኔ ዲሞክራት አይደለሁም፡፡ የጀርመን አሜሪካን ትብብር
ማህበር አባል ነኝ፡፡ ይህ ማህበር በናዚ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ
የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው፡፡ ሂትለር ራሱ ነው ከአገር አምልጦ የወጣውን
ሳይንቲስት አፍኜ ወደ ጀርመን እንዳመጣው ያዘዘኝ›› አለ፡፡ ሉተር ይህን
ሲናገር በኩራት ነው፡፡ ‹‹እነዚህ ሰዎች ከፍዬ የማሰራቸው እኔ ነኝ፡፡ ስለዚህ ዶክተር ፕሮፌሰር ሃርትማንን ወደ ጀርመን መልሼ እወስደዋለሁ፡
ሳይንቲስቱ እዚያ በጣም ይፈለጋል›› አለ፡

ኤዲ ከሃርትማን ጋር ዓይን ላይን ግጥም አለ፡፡ ሰውዬው ፍርሃት
ጨምድዷቸዋል፡ ኤዲ ወዲያው ፀፀት ገባው፡፡ ሳይንቲስቱ ወደ ጀርመን
ሊመለሱ ነው፡፡ ይሄ ደግሞ የኤዲ ጥፋት ነው፡፡

‹‹ምን ላድርግ ባለቤቴን ስላገቱብኝ ነው የተባበርኳቸው›› አለ፡፡

የሃርትማን አስተያየት ተለወጠ ‹‹ይገባኛል›› አሉ ሳይንቲስቱ ‹‹እንደዚህ
አይነት ክህደቶችን ጀርመን ውስጥ ለምደናቸዋል፡ አንዱን ለማዳን ስትል
ሌላውን አሳልፈህ ትሰጣለህ፡ ምንም ምርጫ አልነበረህም፡፡ በዚህ ራስህን አትውቀስ›› አሉት፡፡
ኤዲ ሳይንቲስቱ በዚህ ወቅት ሊያጽናኑት በመሞከራቸው ተገርሟል፡

ኤዲ ወደ ኦሊስ ፊልድ ዞሮ ‹‹ለምንድነው አስመሳይ ሰው አይሮፕላን ውስጥ ያሳፈራችሁት?››

‹‹ጎርዲኖ ለፖሊስ መረጃ እንዳይሰጥ ሊገድሉት እንደሆነ መረጃ ደረሰን፡፡ አሜሪካ እንደደረሰ ይመቱታል፡፡ ስለዚህ ጎርዲኖ በዚህ አይሮፕላን
እንደሚሄድ የሀሰት መረጃ ለማፊያዎቹ አቀበልናቸውና እሱን አስቀድመን
በመርከብ ላክነው፡፡ ጎርዲኖ እስር ቤት መግባቱን የማፊያ ቡድኑ ሲሰማ
መሸወዱን ያውቃል››

‹ለምንድን ነው ለካርል ሃርትማን ጥበቃ ያላደረጋችሁላቸው?,,

እሳቸው በዚህ አይሮፕላን ላይ እንደሚሳፈሩ አናውቅም፡፡ የነገረን
ሰው የለም፡፡››

ጆ የሚባለው ወሮበላ በአንድ እጁ ሽጉጡን በሌላ እጁ የሻምፓኝ ጠርሙስ ይዞ ‹‹እዚህ ያሉት ተሳፋሪዎች በፍርሃት ረጭ ብለዋል፡ ስለዚህ
ትንሹ ልጅ እነሱን መቆጣጠር ይችላል›› አለው ቪንቺኒን፡፡

ቪንቺኒም ‹‹የታለ የባህር ጠላቂው መርከብ?›› ሲል ሉተርን ጠየቀው፡

‹‹በጥቂት ጊዜ ውስጥ እዚህ ይደርሳል›› አለ ሉተር፡

‹‹በል እንግዲህ ሉተር ስራችንን ጨርሰናል ገንዘቡን ስጠን›› አለ ቪንቺኒ፡፡

ሉተር ሳምሶናይት ቦርሳ አወጣና ለቪንቺኒ አቀበለው: ቪንቺኒ
ቦርሳውን ሲከፍተው ረብጣ ገንዘብ አለበት፡፡

‹‹አንድ መቶ ሺህ ዶላር ነው›› አለው ሉተር፡፡

‹‹እስቲ ቼክ ላድርግ›› አለና ቪንቺኒ ሽጉጡን አስቀምጦ ቦርሳውን ጉልበቱ ላይ አኖረና ገንዘቡን መቁጠር ጀመረ፡፡ ሉተርም ሲቆጥር አይቶ
‹‹ይሄን ሁሉ ለመቁጠር ብዙ ሰዓት ይወስድብሃል›› አለው

ሁሉም ሰው ቪንቺኒን ገንዘቡን ሲቆጥር አፍጦ ያየዋል፡፡ ጆ ተዋናይዋን
ሉሉ ቤልን አወቃትና ‹‹አንቺ የፊልም ተዋናይ  አይደለሽም?›› ሲል
ጠየቃት፡፡ ሉሉ ፊቷን አዞረች፡፡ ጆ ከጠርሙሱ ላይ መጠጡን ተጎነጨና
ዳያና ላቭሴይን ‹‹ጠጪ›› ብሎ ጠርሙሱን አቀረበላት፡፡ እሷ በጥላቻ ፈንጠር አለች፡፡ ‹‹አዎ ይሄ ያሰክርሻል›› ብሎ ቀሚሷ ላይ መጠጡን ሲደፋው ዳያና ጮኸችና እጁን ገፋ አደረገች፡፡ በመጠጥ የራሰው ቀሚሷ ሰውነቷ ላይ
ተጣብቆ ገላዋን በግልጽ ያሳያል፡፡

እንዲህ አይነት ነገር ጠብ ሊያጭር መቻሉን ኤዲ ተገነዘበና ‹‹ተው››
ሲል ተቆጣ፡፡ ወሮበላው የኤዲ ቁጣ ምንም አልመሰለውም፡፡ ጠርሙሱን
ጣለና ጡቷን ያዝ ሲያደርገው ዳያና ጮኸች፡፡
ወዳጇ ማርክ ‹‹ተዋት አንተ ወንበዴ!›› ሲል ተሳደበ በመቀመጫ ቀበቶው ታስሮ እንደተቀመጠ፡ ወሮበላው ታዲያ ቀልጠፍ አለና ማርክን በሽጉጡ አፉን ሲለው ደሙ ተንፎለፎለ፡፡
ኤዲም ቪንቺኒን ‹‹እባክህ ተው በላቸው›› ሲል ለመነው፡፡

‹‹እንደዚህ ያለች ሴት ከዚህ ቀደም ጡቷን አልተዳሰሰች ከሆነ የመዳበሻ ጊዜዋ አሁን ነው›› አለ ቪንቺኒ፡፡
ጆ በዳያና ቀሚስ ስር እጁን ሲሰድ እጁን ለማስጣል ታገለች፡፡ ነገር ግን
እሷም ወንበሯ ላይ በመቀመጫ ቀበቶ ታስራ ስለነበር እጁን ማስጣል
አልቻለችም::

ማርክ የመቀመጫ ቀበቶውን ፈታና ሲነሳ ሰውዬው እንደገና አይኑን
መታው፡፡ ቀጠለና ሆዱንና ፊቱን በሽጉጡ እጀታ እየደጋገመ ሲመታው
ማርክም በሚፈሰው ደም ዓይኑ ስለተጋረደ ማየት አቃተው፡፡ ሴቶቹ
ይጮሃሉ፡

ኤዲ የደረሰው ሁኔታ አስደንግጦታል፡ ምንም ደም ሳይፈስ የእገታው
ድራማ እንዲጠናቀቅ ነው የሚፈልገው፡፡ ከዚህ በላይ ግን መታገስ አልቻለም: ጆ እንደገና ማርክን ሊመታ ሲል ኤዲ ህይወቱን ሸጦ
ወሮበላውን እጁን ለቀም አድርጎ ያዘው፡፡

ጆ ራሱን ለማስለቀቅና ሽጉጡን ኤዲ ላይ ለመደገን ቢሞክርም ኤዲ አጥብቆ እጁን ስለያዘው መፈናፈን አልቻለም፡፡ በዚህ ጊዜ ጆ የሽጉጡን ምላጭ ሳበው የጥይቱ ጨኸት ጆሮ ይሰነጥቃል፡ ነገር ግን ሽጉጡ የያዘውን
የጆን እጅ ታግሎ ወደ ታች ስለያዘው የወጣው ጥይት ወለሉን በሳው የመጀመሪያ ጥይት ሲተኮስ ሁኔታው ከእጅ እየወጣ መሆኑ ኤዲ
ታወቀው፡፡ እዚህ ላይ ካልቆመ ደም መፋሰስ ይከተላል በመጨረሻም ቪንቺኒ ጣልቃ መግባት ግድ ሆነበትና ‹‹ጆ ይበቃሃል
አቁም!›› ሲል ጮኸ፡
ጆ ትግሉን ሲያቆም ኤዲም ለቀቀው፡

ጆ በጥላቻ ኤዲን አየው ነገር ግን ምንም አላለም፡

ቪንቺኒም ‹‹መሄድ እንችላለን ገንዘቡን ተቀብለናል›› አለ፡፡

ኤዲ ተስፋው ለመለመ:፡ አሁን ከሄዱ ደም መፋሰስ አይኖርም› አለ
በሆዱ፡ቪንቺኒ ቀጠለና ‹‹ጆ ሴትዬዋን ከፈለካት አምጣት እኔም ልነፋት እፈልጋለሁ፡፡ ከኢንጂነሩ ሰናና ሚስት እሷ ትሻላለች›› አለና ተነሳ፡፡

ዳያና ጮኸች ‹‹እባካችሁ ተዉኝ!››

ጆ የዳያናን የመቀመጫ ቀበቶ ፈታና ፀጉሯን ጎትቶ አነሳት፡ ዳያና የአቅሟን ያህል ታገለች ማርክ ደሙን ከዓይኑ ላይ እየጠራረገ ለጠብ ሲነሳ ኤዲ አየና ‹‹ይገሉሃል›› አለው በለሆሳስ፡፡ ‹‹አይዞ ችግር አይኖርም፡››የባህር ኃይሉ መርከብ እየመጣ መሆኑን እንደሚደርስላቸው ሊነግረው ፈልጎ ነበር፡፡ ነገር ግን ቪንቺኒ ሊሰማ ይችላል ብሎ ተወው፡

ጆም ቀጠለና ማርክ ላይ ሽጉጡን ደግኖ ዳያናን ‹‹አንቺን እንወስድሻለን፧ አለበለዚያ ወዳጅሽ ዓይን ላይ ጥይት እንለቅበታለን›› አለ ዳያና በድንጋጤ ቆመችና ማልቀስ ጀመረች፡
‹‹እኔ ከእናንተ ጋር እመጣለሁ፡፡ የባህር ጠላቂው መርከብ መምጣት ያስቸግረዋል››
አለ ሉተር

ቪንቺኒ ስለ ጠላቂ መርከብ የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ ምናልባትም ጠላቂው መርከብ ያልመጣው የስቲቭ አፕልባይን የጦር መርከብ አይቶ ሊሆን ይችላል፡ ስለዚህ ጀልባው ራቅ ብሎ እስኪሄድ ሊጠብቅ ይችላል፡

‹‹አንሂድ›› አለ ቪንቺኒ፡፡ ‹‹በመጀመሪያ እኔ እወጣለሁ፡፡ ቀጥሎ ኤዲ፡፡
በመጨረሻ ጆ ከቆንጆዋ ጋር ትወጣለህ፡፡››

ማርክ ኦልደር ከኤዲ እጅ ለማምለጥ ይታገላል፡፡ ቪንቺኒም ቀጠለና
ሌላውን መርማሪ ‹‹ይህን ሰው አደብ እንዲገዛ
ኦሊስ ፊልድንና ታደርጉታላችሁ ወይስ ጆ በጥይት ይበለው?›› ሲል ጠየቀ፡፡ እነሱም ማርክን
እንዳይንቀሳቀስ አድርገው አጥብቀው ያዙት
ኤዲ ቪንቺኒን ተከትሎ ሲሄድ ሚስተር መምበሪ ሽጉጡን መዞ

‹‹ቁም!›› አለና ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን ደገነ፡፡ ‹‹ወሮበላ ሁሉ ጸጥ በይ!
አለበለዚያ አለቃሽን በጥይት እደፋዋለሁ›› አለ፡ ቪንቺኒም ይህን ሲያይ
ደንግጦ ‹‹ሁላችሁም እንዳትንቀሳቀሱ!›› ሲል ጓደኞቹን አዘዘ፡፡ ነገር ግን
ትንሹ ልጅ የሚባለው ሰውዬ ፈንጠር አለና ሁለት ጊዜ ሲተኩስ መምበሪ
ወደቀ፡ ቪንቺኒም ትንሹ ላይ ጮኸ ‹‹አንተ የማትረባ! ሰውዬው ሊገለኝ
ይችል ነበር እኮ!›› አለው፡
‹‹አነጋገሩን አልሰማኸውም?›› ሲል ትንሹ ልጅ መለሰ ‹‹እንግሊዛዊ እኮ
ነው››
‹‹ታዲያ ቢሆንስ?›› ሲል ቪንቺኒ አምባረቀ፡፡

‹‹በርካታ ፊልም አይቻለሁ ነገር ግን በእንግሊዛዊ ጥይት የተመታ ሰው
የለም፡፡››

ኤዲ መምበሪ አጠገብ ተምበርክኮ ሲያይ ጥይቶቹ ደረቱን በስተው
ገብተዋል፡፡ ደሙ እየተንፎለፎለ ነው ‹‹ማነህ አንተ?›› ሲል ጠየቀው
መምበሪን፡፡

‹‹የእንግሊዝ ልዩ ፖሊስ አባል ነኝ›› አለ መምበሪ በደከመ ድምፅ፡፡‹‹ሳይንቲስቱን ሃርትማንን ለመጠበቅ ነው የተመደብኩት አልሆነልኝም››
አለና አይኑን ዘጋ፤ ትንፋሹም ቆመ:፡

ኤዲ አንድ ሰው ሳይሞት ወሮበሎቹ ከአይሮፕላኑ እንዲወጡ ፈልጎ
ነበር፡ ያሰበው ሊሳካለትም ትንሽ ነበር የቀረው፡፡ ነገር ግን ይሄው አንድ ፖሊስ ተገደለ፡ በትዕግስት ሊታለፍ ይችል ነበር፡፡ ለሰው ህይወት መጥፊያ
የሆነው ደግሞ እሱ ነው፡፡

የእነ ቪንቺኒ ጀልባ ነጂ ሲሮጥ መጣና ‹‹የሬዲዮ መልእክት መጥቷል››
አለው፡:

የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ለአስቸኳይ ጉዳይ ካልሆነ መገናኛ እንዳይጠቀም
ነግሬው አልነበረም?›› አለ ቪንቺኒ፡፡
‹ይሄ በጣም አስቸኳይ ነው፡፡ አንድ የባህር ኃይል መርከብ እየመጣ ነው።
የኤዲ ልብ ሊቆም ምንም አልቀረውም፡፡ የወሮበላው ቡድን መልዕክት አስተላለፊ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ቪንቺኒ ወጥመድ ውስጥ እንደወደቁ አውቋል፡

‹‹ከዳኸኝ›› አለ ቪንቺኒ ኤዲን፡፡ ‹‹ለዚህ ክህደትህ ደግሞ እገልሃለሁ››

ኤዲ የካፒቴኑን ዓይን ሰረቅ አድርጎ ሲያይ ካፒቴኑ ጥረቱን እንደተረዳለትና ባደረገው አክብሮት እንዳለው ከካፒቴኑ አይን ላይ አነበበ፡

ቪንቺኒ ኤዲ ላይ ሽጉጡን ደገነ፡፡

‹‹የቻልኩትን ያህል እንዳደረኩ ሁሉም አውቆልኛል፡ አሁን ብሞትም
አይቆጨኝም›› አለ ኤዲ፡
ሉተርም ለጠቀና ቪንቺኒን ‹‹አንድ ድምጽ  አይሰማህም?›› ሲል
ጠየቀው፡

ሁሉም ጸጥ አለ፡፡ የሌላ አይሮፕላን ድምጽ ነው፡፡

ሉተር በመስኮቱ አሻግሮ ሲመለከት ባህር ላይ የሚያርፍ አይሮፕላን
መሆኑን አወቀ፡ አጠገባቸው ሊያርፍ ነው፡

ቪንቺኒ ሽጉጡን ወደ ታች አደረገ፤ ኤዲ ጉልበቱ ተብረከረከ፡፡ ‹‹ቢሆንስ
አናስኬድም ካሉን በጥይት ነው የምንረፈርፋቸው›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ሌላ ነገር አይታይም›› አለ ሉተር በደስታ በዚህ አይሮፕላን ከባህር ሀይሉ መርከብ በላይ በረን እናመልጣለን›› አለ፡፡

ቪንቺኒ በመስማማት ራሱን ነቀነቀና ‹‹ጥሩ አስበሃል እንደዚያ ነው የምናደርገው›› አለ፡

#መልካም ቀን ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት

      @Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን
       📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሃምሳ

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ



ናንሲ ሌኔሃን በተከራየችው አይሮፕላን በካናዳ ጠረፍ ላይ ስትበር ለችግሯ መፍትሄ ታያት፡ ወንድሟን መርታት ብቻ ሳይሆን አባቷ
ካስቀመጡላት የህይወት መርህ መውጣት ትፈልጋለች፡ ከመርቪን ጋር
መሆንም ትፈልጋለች፡ ሆኖም የጫማ ፋብሪካውን ትታ መርቪንን ተከትላ
እንግሊዝ ሃገር ሄዳ ብትኖር እንደ ዳያና የባሏን እጅ መጠበቅ የሰለቻት
ሚስት መሆኗ ነው፡

ናት ሪጅዌይ ኩባንያውን በተሻለ ዋጋ እንደሚገዛና በጄኔራል ቴክስታይል ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ እንደሚሰጣት ነግሯታል፡ ጄኔራል ቴክስታይልስ ደግሞ አውሮፓ ውስጥ ባብዛኛው በተለይም እንግሊዝ ውስጥ በርካታ ፋብሪካዎች አለው፡፡ ናት ሪጅዌይ ደግሞ ጦርነቱ ካላበቃ ፋብሪካዎቹን መጎብኘት አይችልም፡፡ ስለዚህ እሷ የፋብሪካ
ዎቹን የአውሮፓ የበላይ ሀላፊነት ቦታ ይሰጣታል፡፡ ይህ ደግሞ በራሱ
ከመርቪን ጋር ለመሆንና ስራ መስራት የሚያስችላት በመሆኑ ጥሩ ነው፡

መፍትሄው ጥሩ ይመስላል፡፡ አንድ የሚያስፈራ ነገር አውሮፓ ጦርነት ውስጥ ስላለች ልትሞት ትችላለች፡፡ ናንሲ ይህን ስታወጣና ስታወርድ
መርቪን ባህሩ ላይ የቆመውን አይሮፕላናቸውን አሳያት፡፡
መርቪን ከአይሮፕላኑ ጋር በሬዲዮ መገናኛ ለመገናኘት ቢሞክርም ምንም ምላሽ አላገኘም፡፡ ናንሲ አይሮፕላኗ ስታንዣብብ አዕምሮዋ ውስጥ የሚመላለሰውን ነገር ተወችው፡፡ ምንድን
ምንድን ነው የተፈጠረው?
አይሮፕላኑ ውስጥ አሉ? አይሮፕላኑ ሲታይ ምንም አልተጎዳም፡፡ ሆኖም
የሰው ዘር ያለበት አይመስልም፡፡

መርቪን ‹‹ምናልባትም ችግር ደርሶባቸው ከሆነ አርፈን ብናያቸው›› አለ፡፡ ናንሲ በመስማማት ራሷን ነቀነቀች፡፡

‹‹የመቀመጫ ቀበቶሽን በደምብ እሰሪ፡፡ ባህሩ ማዕበል ያለበት ስለሆነ
ስናርፍ ይንገጫገጫል፡››
ፓይለታቸው እንደ ፈረስ የሚጋልበው ባህር ላይ አይሮፕላናቸውን
አሳረፈ፡ ናንሲ እንደገመተችው ማዕበሉ አስቸጋሪ አልነበረም፡፡
አንድ የሞተር ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር ታስሯል፡፡ ትልቁ አይሮፕላን በር ላይ አንድ ሰው እጁን ያውለበልባል። ከዚያም እነ መርቪን አይሮፕላናቸውን ከግዙፉ አይሮፕላን ጋር አሰሩት፡፡

ኔድ ‹‹እኔ አይሮፕላኔ ውስጥ እቆያችኋለሁ›› አለ ‹‹እናንተ ውጡ አይሮፕላኑ ምን ችግር እንደደረሰበት አጣሩ›› አላቸው፡፡

‹‹እኔም እመጣለሁ›› አለች ናንሲ፡፡

መርቪን መጀመሪያ ወደ አይሮፕላኑ ዘለለና ለናንሲ እጁን ዘረጋላት፡

በሩ ላይ የቆመውን ሰው ‹‹ምንድን ነው የተፈጠረው?›› ሲል ጠየቀው፡

‹‹ነዳጅ ስላለቀባቸው ነው ባህሩ ላይ ያረፉት›› ሲል መለሰ፡፡

‹‹በሬዲዮ መገናኛ ላገኛቸው ሞክሬ ነበር፡፡

ሰውዬውም ‹‹ወደ ውስጥ ግባ›› አለው፡

መርቪን ከገባ በኋላ ‹‹ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አይሮፕላኑ ድንገት ነው ያረፈው›› አለ ወጣቱ ሰው ‹‹እኛ አሳ አጥማጆች ነን ስለዚህ ችግሩን ለማጣራት መጥተን ነው››

‹ካፒቴኑን እጠይቀዋለሁ›› አለ መርቪን፡፡

ወጣቱ ሰው በአለባበሱ አሳ አጥማጅ አይመስልም፡፡ ክራቫት አድርጓል፡፡
ናንሲ ሁኔታው አሳቃት፡፡

ወደ ውስጥ ገብተው ሲመለከቱ መምበሪ በደም ተለውሶ ወለሉ ላይ
ተዘርግቷል፡፡ አፏን ያዘች በድንጋጤ
‹ወይ አምላኬ! ምንድን ነው ችግሩ?›› ሲል መርቪን ጠየቀ ከኋላቸው ያለው ወጣቱ ሰው ‹‹ቀጥሉ ወደፊት›› አለ በቁጣ፡

ናንሲ ዞር ብላ ስታየው ሰውዬው ሽጉጥ ደግኗል፡፡ ‹‹አንተ ነህ እንዲህ ያደረከው?›› ስትል ጠየቀች
‹‹አፍሽን ዝጊና ቀጥ ብለሽ ሂጂ›› አላት፡፡

መብል ክፍል ውስጥ ገቡ፡፡
ሌሎች ሶስት ሽጉጥ የያዙ ሰዎች አሉ፡፡ አዛዣቸው የሚመስል አራተኛ
ሰው ቆሟል፡፡ ትንሹ ልጅ ከመርቪን ሚስት ኋላ ቆሞ ጡቷን ይጎነትላል፡
መርቪን ይህንን ሲያይ ተናደደ፡፡ ሶስተኛው ሰው የአይሮፕላኑ ተሳፋሪ
የሆነው ሉተር ሲሆን በፕሮፌሰር ሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡
ካፒቴኑና የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ዓይናቸውን
ያቁለጨልጫሉ፡ በርካታ ተሳፋሪዎች ወምበራቸው ላይ እንደተቀመጡ
ሲሆን ወለሉ ላይ የብርጭቆና የሰሃን ስብርባሪ ይታያል፡፡ ናንሲ ዙሪያውን ስታማትር በፍርሃት የተዋጠችው ማርጋሬት አይኗ ገባች፡፡
‹‹ላቭሴይ አምላክ ፊቱን አዙሯል፡፡ አይሮፕላን በምንፈልግበት ጊዜ
ደርሰህልናል፡ እኔን ቪንቺኒንና የእሱን ሰዎች በአይሮፕላን ይዘኸን ትሄዳለህ፡ ኤዲ ዲኪንማ ፖሊስ እጅ ሊጥለን ወጥመድ ሲያሰናዳልን ነው
የከረመው›› አለ ሉተር፡
መርቪን ከመገላመጥ በስተቀር ምንም መልስ አልሰጠውም፡፡

ባለመስመር ሱፍ ልብስ የለበሰው ሰው ‹‹የባህር ኃይል ወታደሮች
መጥተው ችግር ከመፍጠራቸው በፊት እንሂድ፡፡ ትንሹ ልጅ አንተ ላቭሌይን ይዘህ ና፡፡ ገርል ፍሬንዱ እዚሁ ትቆይ›› አለ፡፡
‹‹እሺ ቪኒ›› አለ ትንሹ ልጅ፡፡
ናንሲ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ባታውቅም ወደኋላ መቅረት ግን አልፈለገችም፡፡ መርቪን ችግር ውስጥ የሚገባ ከሆነ ከጎኑ ትሆናለች፡፡

ቪንቺኒ ሌላ ትዕዛዝ ሰጠ፡፡ ‹‹ሉተር አንተ ሳይንቲስቱን ይዘህ ና፡›› ወደ ጆ ዞር አለና ‹‹በመጨረሻ ቆንጆዋን ሴት ይዘህ ና›› ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፡፡

ሰውየው ዳያና ላቭሴይ ላይ ሽጉጡን ደግኖ ‹‹እንሂድ›› አላት እሷ ግን ከቦታዋ ንቅንቅ አልልም አለች፡፡ ናንሲ ሌላ ጥያቄ ጭንቅላቷ ውስጥ አጫረ፡ ዳያናን ለምንድን ነው የሚወስዷት? በኋላ ግን መልሱ ተከሰተላት
ጆ ቀጠለና በሽጉጡ አፈሙዝ የዳያናን ጡት ወጋ ሲያደርገው ጮኸች፡፡

‹‹ቆይ እስቲ›› አለ መርቪን፡፡

ሁሉም እሱ ላይ አፈጠጡ፡፡

‹ሁላችሁንም በአይሮፕላን እወስዳችኋለሁ። ነገር ግን አንድ ነገር ማሟላት አለባችሁ›› አላቸው

ቪንቺኒም ‹‹አፍህን
ዝጋና ተንቀሳቀስ፡፡ ምንም ቅድመ  ሁኔታ ማስቀመጥ አትችልም›› አለው፡፡

መርቪን እጁን ዘረጋና ‹‹እንግዲያውስ ግደሉኝ›› አለ፡፡

ናንሲ በፍርሃት ጮኸች፡
እነዚህ ሰዎች የሚዳፈራቸውን ሰው
ከመግደል ወደኋላ የሚሉ አይደሉም መርቪን  አላወቃቸውም አለች በሆዷ

‹‹ምንድነው ቅድመ ሁኔታው?›› ሲል ጠየቀ ሉተር

መርቪን ወደ ዳያና
አመለከተና ‹‹እሷ እዚሁ ትቆይ›› አለ ጆ በንዴት መርቪን ላይ አፈጠጠ፡፡

‹‹አንፈልግህም ብዙ የፓን አሜሪን ፓይለቶች ሞልተዋል፡፡ እነሱም
እንዳንተ ማብረር ይችላሉ›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ሁሉም እንደዚህ አይነት ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ›› አለ መርቪን፡፡
‹‹ጠይቋቸው ጊዜ ካላችሁ፡፡›› ወሮበሎቹ እነሱን ያመጣው ፓይለት መኖሩን እንዳላወቁ ተገንዝቧል፡

‹‹ሴትዬዋን ተዋት›› አለ ሉተር፡፡

ጆ በንዴት ፊቱ ቀላ፡፡

‹‹ለምን?››

‹‹እሷን ተዋት›› ሲል ጮኸ ሉተር፡፡ ‹‹እኔ ገንዘብ የከፈልኩህ ሃርትማንን እንድታፍንልኝ ነው እንጂ ሴት እንድትደፍርልኝ ነው እንዴ››

‹‹ሉተር ልክ ነው ጆ፡ በኋላ ሌላ ሴት ታገኛለህ›› አለው ቪንቺኒም:

‹‹እሺ›› አለ ጆ፡

ዳያና በእፎይታ አለቀሰች።

‹‹ጊዜ የለንም ከዚህ እንውጣ›› ሲል ቪንቺኒ አዘዘ፡፡

ናንሲ ‹መርቪንን ዳግመኛ አየው ይሆን?› አለች በሃሳቧ
ከውጭ ክላክስ ተሰማ፡፡ የጀልባው ነጂ ነው ክላክስ ያደረገው።
ትንሹ ልጅ ‹‹አለቃ እስቲ በመስኮት ተመልከት›› አለው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሄሪ ማርክስ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ለማረፍ ከውሃ ጋር ስለተጋጨ ወደ
አንድ ጎን ወድቆ ነበር፡ በመጀመሪያ ተወርውሮ ከሻንጣዎቹ ጋር ተጋጨ፡
እንደገና ለመነሳት ሲሞክር ከአይሮፕላኑ ግድግዳ ጋር ተጋጨና ራሱን ሳተ፡
ሲነቃ ምንድን ነው የሆነው? አለ በሆዱ፡ ፖርት ዋሽንግተን እንዳልደረሱ
አውቋል፡፡ ገና ከሚቀራቸው የአምስት ሰዓት በረራ ሁለቱን ሰዓት ብቻ ነው
የተጓዙት፡፡ ስለዚህ ይሄ ከፕሮግራሙ ውጭ
ይሄ ከፕሮግራሙ ውጭ የተደረገ ቆይታ ነው፡፡
ምናልባትም አይሮፕላኑ ችግር ገጥሞት ድንገት ይሆናል ያረፈው::
አሁን ተመቻችቶ ቁጭ
ሲል ቁስሉ ተሰማው፡፡  አይሮፕላኖች የመቀመጫ ቀበቶ ለምን እንደሚያስፈልጋቸው የተረዳው አሁን ነው
አፍንጫው እየደማ ነው፡፡ ራሱን ይፈልጠዋል፡፡ ሰውነቱን ሁሉ ቁስል
ይሰማዋል፡፡ እጅ እግሩ ግን ደህና ነው፡፡ አፍንጫውን በመሀረብ ጠረገና
ለመትረፉ አምላኩን አመሰገነ፡፡

የአይሮፕላኑ ሻንጣ ማስቀመጫ ክፍል መስኮት ስለሌለው ውጭ ምን
እንደተፈጠረ ማየት አልቻለም፡፡ በጸጥታ ቁጭ አለና ሲያዳምጥ የአይሮፕላኑ ሞተር ጠፍቷል፡ ሁሉ ነገር ፀጥ ረጭ ብሏል፡፡

ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፡፡

የሽጉጥ ተኩስ ካለ ወሮበሎቹ አሉ ማለት ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ
ካሉ ደግሞ ጎርዲኖን ነው የሚፈልጉት፡፡ ሌላም ነገር አለ፡፡ የሽጉጥ ተኩስ
ካለ ግርግር ስለሚኖር በዚያ መሀል ሾልኮ ለመውጣት ይመቻል፡፡ ስለዚ, ከሻንጣ ክፍል ወጥቶ ለማየት ወሰነ፡፡

በሩን ትንሽ ከፈት አደረገና አየ፡፡ ምንም የሚታይ ነገር የለም

ኮሪደሩ ላይ ወጣና ወደ አይሮፕላኑ መንጃ ክፍል ሄደ፡ ከዚያም በሩ
ጋር ተለጥፎ ድምፅ ይሰማ እንደሆነ ጠበቀ፡፡ ምንም የለም፡ ከዚያ ቀስ ብሎ
በሩን ከፈተና አጮልቆ አየ፡፡
የአይሮፕላኑ መንጃ ክፍል ውስጥ የሰው ዘር አይታይም፡፡ ከዚያም ወደ
ፊት ሲሄድ ሰዎች ሲጨቃጨቁ ሰማ፡፡ ምን እንደሚሉ አይሰማውም፡ በአይሮፕላኑ መስኮት አሻግሮ ሲመለከት አንድ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር ታስሮ አየ፡፡ አንድ ሰው ይታየዋል፡፡ ለማምለጥ ትንሽ እንደቀረው ሄሪ ተገነዘበ፡፡
ውጭ ሰው ወደሌለበት የባህሩ ዳርቻ የሚወስደው ጀልባ አለ፤ አንድ ሰው ብቻ ስለሆነ ሰውዬውን አባሮ ጀልባውን መውስድ ይችላል።

ከኋላው የጫማ ኮቴ ሰማ፡፡ ልቡ እየደለቀ ዞረ፡ ከኋላው የመጣው ፔርሲ ኦክሰንፎርድ ነው፡፡ ልጁ በፍርሃት ተውጧል።

‹‹የት ነው የተደበቅኸው?›› ሲል ፔርሲ ጠየቀው

‹‹ተወው እሱን›› አለ ‹‹ይልቅ እዚያ ምን እንደተፈጠረ ንገረኝ›› ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ሚስተር ሉተር የናዚ ደጋፊ ነው፡፡ ፕሮፌሰር ሃርትማንን መልሶ ወደ ጀርመን ሊወስዳቸው ይፈልጋል፡፡ ለዚህም ስራው በመቶ ሺህ ዶላር ወሮበሎችን ቀጥሮል
ሻንጣ ሙሉ ገንዘብም ሰጥቷቸዋል ወሮበሎቹ መምበሪን ገደሉት፡ ከእንግሊዝ ፖሊስ መምሪያ ሃርትማንን ሊጠብቅ
የተመደበ ፖሊስ ነበር››

‹‹እህትህ ደህና ነች?››

‹‹እስካሁን ደህና ነች፡፡ ሚስስ ላቭሴይ ቆንጆ ስለሆነች ሊወስዷት ነው፡፡
ማርጋሬትን ከሰውም አይቆጥሯት!›› አለ ፔርሲ ‹‹ተደብቄ ሰው ሳያየኝ ነው
ወደዚህ የመጣሁት››

‹‹ለምን?››

‹‹የኦሊስ ፊልድን ሽጉጥ ለመውሰድ፡፡ ካፒቴን ቤከር ከሚስተር ፊልድ ነጥቆ እዚህ ጠረጴዛ ኪስ ውስጥ ሲያስቀምጥ አይቻለሁ›› አለና ሽጉጡን አንስቶ ያዘ።

‹‹ሄሪ አንተ ልጅ ነህ ሽጉጥ መያዝ የለብህም፧ ባርቆብህ ሊመታህ ይችላል›› አለና ሽጉጡን ነጥቆ የጠረጴዛ ኪስ ውስጥ ከተተና መሳቢያውን ዘጋው፡:

እውጭ የሚያስገመግም ድምጽ ሰሙ፤ በመስኮቱ ሲመለከቱ የእነሱን
አይሮፕላን ከላይ ሆኖ የሚዞር አይሮፕላን አዩ አይሮፕላኑም ትንሽ
ሲያንዣብብ ቆይቶ ለማረፍ መውረድ ጀመረ ከዚያም ባህሩ ላይ አረፈና
ወደ እነሱ አይሮፕላን እንደ ጀልባ እየተነዳ መጣ:፡

‹‹አሁን ምን እናድርግ?›› አለና ፊቱን ወደ ፔርሲ ሲያዞር እሱ የለም፧
የጠረጴዛው መሳቢያም ተከፍቷል፡ ሽጉጡም የለም፡፡

ጊዜ ሳያጠፋ ከሻንጣ መያዣ ክፍሉ ወጥቶ ሄደና ሌላ ክፍል ዳር ተለጥፎ አየ፡፡ ፔርሲን አሁን ማስቆም አልቻለም ጥሎት ሄዷል፡
ማርጋሬት ሁሉም ቤተሰቡ  በሙሉ ሽጉጥ መተኮስ እንደሚችል የነገረችው ትዝ አለው፡፡ ልጁ ግን ስለማፊያዎች የሚያውቀው ነገር የለም፧ ሊያስቆማቸው ከሞከረ ደመ ከልብ ይሆናል፡፡

ወደ አይሮፕላን መንጃው ክፍል ገብቶ ወደ ውጭ ሲያይ አሁን ያረፈው አይሮፕላን ከእነሱ አይሮፕላን ጋር በገመድ ሲታሰር አየ፡ ወደ
አይሮፕላኑ ጭራ አካባቢ ድረስ ሄዶ በሩን ትንሽ ከፈት አድርጎ ምን እየተደረገ እንደሆነ ለማወቅ ፈለገ፡፡
የአንድ ሰው ኮቴ ይሰማዋል፡፡ ሌሎች ሁለት ሰዎች ሲመጡ ኮቴ ሰማ፤
አልፈው መሄዳቸውን አረጋገጠና ወጣ፡፡
ማፊያዎችን የሚይዝ የፖሊስ ሀይል መጣ ይሆን?› ሄሪ የሚነግረው
አጣ ቀስ እያለ ኮቴውን ሳያሰማ ወደ ፊት ሄደ፡፡ በመሀል በመሀሉ ቆም
ይልና ያዳምጣል፡፡ አሁን ድምጽ በደምብ ይሰማዋል፡፡ የቶም ሉተር ድምጽ እንደሆነ አወቀ፡ አነጋገሩ ትንሽ የአውሮፓ ቅላጼ ያለው የጨዋ አሜሪካዊ አነጋገር ነው፡፡

ወሮበሎቹ ሲጨነቁበት የነበረው የማምለጥ ጉዳይ አሁን መፍትሄ አግኝቷል፡፡ በመጣው አይሮፕላን ሚስተር ሃርትማንን ይዘው ሊጠፉ ነው፡

ሄሪ በእግሩ እየዳኸ ቀረበ
ምስኪኑን ሳይንቲስት ለናዚዎች አሳልፎ
መስጠት በእርግጥም ልብ ይሰብራል፡፡ መቼም ለሳይንቲስቱ ብሎ አንገቱን
ለካራ አይሰጥም፡፡ ሆኖም ፔርሲ አንድ ነገር ሊያደርግ ይችላል፡፡ እሱ ደግሞ
እንዲሞት አይፈልግም፡፡ ለማርጋሬት ሲል አንድ ነገር ማድረግ አለበት፡፡
ከሄሪ ቀድሞ በመገኘት ወሮበሎቹን እርምጃ እንዳይወስዱ ለማደነጋገር
ወይም ሊሰሩት በተዘጋጁት ላይ ጋሬጣ በመፍጠር ሊያዘናጋ ነው፡፡
በአይሮፕላኑ በኩል ወጣና
ጀልባዋ ከአይሮፕላኑ ጋር
🙄፡£የታሰረችበትን ገመድ ፈታው፡ ነገር ግን ጀልባዋ በሌላ ገመድ ከአይሮፕላኑ
ተናደደ፡፡
ስለዚህ
ገመዱን ለመፍታት ወደ
ጋር መታሰሯን ሲያይ
አይሮፕላኑ መግቢያ መሄድ ሊኖርበት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ደግሞ አንዱ
ያየዋል፡ ሆነም ቀረ የመጣው ይምጣ ብሎ አንድ ነገር ማድረጉ አይቀርም ጊዜም ስለሌለው ቶሎ ማድረግ አለበት፡፡

ሁለተኛውንም ገመድ ፈታና ጣለው፡፡

ጀልባው ውስጥ ያለው ሰው ‹‹አንተ ምን እያደረግህ ነው?›› ሲል ጠየቀው ሄሪን፡፡

ፊቱን አዙሮ ሲያይ የጀልባው ነጂ ነው ያናገረው። መሳሪያ
አልታጠቀም ሰውዬው ገመዱን ለማሰር ሲጎትት ከእጁ አመለጠውና ባህሩ
ውስጥ ገባ፡፡ የጀልባው ነጂ ወደ ውስጥ ገባና ሞተሩን አስነሳ፡ በዚህ ጊዜ
ወሮበሎቹ ጀልባው እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ማየታቸው አይቀርም፡፡ ጉዳዩም አስገራሚም አስደንጋጭም ይሆንባቸዋል፡፡ ሄሪ ወደ አይሮፕላኑ ተመልሶ
ገብቶ የሻንጣ መያዣ ክፍል ውስጥ ገብቶ ተደበቀ።

ከማፊያዎቹ ጋር እሰጣ እገባ ውስጥ መግባት አደገኛ መሆኑን ያውቃል፡ ከያዙት ምን እንደሚያደርጉት ሲያስበው ፍርሃት ይወረዋል
ሄሪ ተደብቆ አንድ ነገር ይፈጠራል ብሎ ጠበቀ፡፡

በመጨረሻ ወደ አይሮፕላን መንጂያው ክፍል የሚሄድ የተቻኮለ የእግር ኮቴ ተሰማው፡ በኮቴው ድምጽ ሁለት ሰዎች እንደመጡ አውቋል፡ እሱ ከሁለት ሰዎች ጋር ሊጋፈጥ እንደሚችል አልገመተም::
ትንሽ ራቅ ብለው ሄደዋል ብሎ በመገመት በሩን ከፈት አድርጎ ሲያይ ምንም ሰው የለም፡፡ ትንሽ ወደፊት ሄዶ ሲመለከት ሁለት ሰዎች ሽጉጥ ያልያዙ ቢሆንም ዓይን የሚስቡ ልብሶች በመልበሳቸው ብቻ ማፊያዎች መሆናቸውን መገመት ችሏል፡ አንዱ አስቀያሚና ክፉ መልክ ያለው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጣም ወጣት ነው፤ ምናልባትም ከ18 ዓመት የማይበልጥ ጎረምሳ፡፡
ተመልሼ ልደበቅ ይሆን› ሲል አሰበ፡፡

ሁለቱ ወሮበሎች ጀልባውን ከአይሮፕላኑ ጋር ለማሰር እንደገና ትግል ጀምረዋል፡ ለማሰር ደግሞ የግድ ሽጉጦቻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው ሄሪም መሳሪያቸውን እስኪያስቀምጡ ጠበቃቸው፡፡

ሁለቱ ሰዎች ሽጉጦቻቸውን በኪሳቸው ከተቱና ወደ ውጭ ወጡ የጀልባው ነጂ የሚወረውርላቸውን ገመድ ለመያዝ ትግል እያደረጉ ስለሆነ በመጀመሪያ ሄሪን አላዩትም ነበር፡፡

አንደኛው ማለትም ወጣቱ ገመዱን ሲይዝ ሁለተኛው ሰው ዞር ሲል ሄሪን አየው፡፡ ልክ ሄሪ ሲደርስበት ሽጉጡን ከኪሱ አወጣ፡፡ በዚህ ጊዜ ሄሪ ሞቱ እንደቀረበ ስለተረዳ ጊዜ ሳያጠፋ የሰውየውን እግር ለቀም አድርጎ ጎተተው፡፡ በዚህ ጊዜ አንድ ጥይት ጮኸች ሰውዬው ሲንገዳገድ ሽጉጡ
ቢወድቅበትም ላለመውደቅ ብሎ ጓደኛውን ያዘው፡፡ ወጣቱ ሰው ሚዛኑን ሳተና ገመዱ ከእጁ ወጣ፡፡ ለተወሰነ ጊዜ አንዱ አንዱን ለመያዝ ወዲያ ወዲህ ተንጠራወዙ፡፡ ሄሪ የአንደኛውን ሰው እግር ይዞ እንደገና ጎተተው፡፡
በዚህ ጊዜ ሁለቱ ሰዎች በማዕበል በሚጋልበው ውሃ ውስጥ ወደቁ፡፡ ሁለቱ ስዎች አንዴ ውሃ ውስጥ እየጠለቁ አንዴ ወደ ጠለሉ እየወጡ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ይጣጣራሉ፡፡ ሄሪ ከሁኔታቸው ዋና እንደማይችሉ አውቋል፡

‹‹ይህን የማደርገው የክላይቭ መምበሪን ደም ለመበቀል ነው›› አላቸው ሄሪ፡፡ ከዚያ በኋላ ይሙቱ ይዳኑ አያውቅም፡፡ ቢሞቱም ግድ አልነበረውም ከዚያም ኮቴ ሳያሰማ በፍጥነት ወደ አይሮፕላኑ ተመለሰ።

ማርጋሬት የራሷ ልብ ድውድውታ ይሰማታል፡፡ ልቧ ልክ እሳት ላይ
እንደተጣደ ጀበና ይንደቀደቃል፡፡ ያለማቋረጥ በጣም ስለሚመታ አጠገቧ ያሉ ሰዎች የሚሰሙ መሰላት፡፡

በህይወቷ እንደዚህ ፈርታ ስለማታውቅ ፍርሃቷን ሌሎች ያውቁብኝ ይሆናል ብላ ሰግታለች።
የፍርሃቷ ምንጭ እንዲሁ የመጣ አይደለም፡፡ አይሮፕላኑ ድንገት
መሃል ባህር ላይ ማረፉ፣ ፍራንኪ ጎርዲኖ፣ ሚስተር ሉተርና የበረራ መሀንዲሱ ኤዲ ዲከን እየሰሩ ያሉት ስራ፣ ሱፍ የለበሱ ማፊያዎች ድንገት ከዚህም ከዚያም ብቅ  ብለው የአይሮፕላኑን ህብረተሰብ ቁም ስቅል ማሳየታቸውና ሚስተር መምበሪ በጥይት ተመትቶ ወለሉ ላይ መዘረሩ ተደማምሮ ፍርሃቷን ጣራ አድርሶታል፡

ለዓመታት ፋሺዝምን እንዴት እንደምትታገል ስትናገር ኖራለች፡፡ አሁን ዕድሉ በሯ ድረስ መጥቷል፡ የፋሺስት ቡድኑ ሳይንቲስቱን ካርል
ሃርትማንን ወደ ጀርመን አፍኖ ለመመለስ እየተውተረተረ ነው፡፡ እሷ ደግሞ በፍርሃት እጅ እግሯ ስለተሳሰረ ምንም ማድረግ አትችልም፡፡ ነገር ግን
መሞከር ይኖርባታል። ምክንያቱም እሷም ፋሺዝምን ለመዋጋት
የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝና በሞት የተነጠቀችውን ኢያንን
ለማስታወስ ስትል ትግል መግጠም እንዳለባት ታስባለች፡፡

ጀግና ነኝ እያለች ስታስመስል አባቷ የስድብ ናዳ እሷ ላይ ማውረዳቸው
ትክክል ነው፡፡ እሷም ይህን ታውቃለች፡ ጀግንነት በአፍ ብቻ ነው፡፡ በጦር ሜዳ በሞተር ሳይክል እየተመላለሰች ለጦሩ ዕቃ አጓጉዛለሁ ማለቷ ህልም
ነው፡ አንድ ጥይት ቢተኮስ የሆነ ነገር ውስጥ መወሸቋ አይቀርም፡፡ ከባድ ጥቃት ከተፈጸመማ ዋጋ አይኖራትም፡፡

ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡

#መልካም ምሽት ተመኘሁ!!💚💛❤️

🎙ግሩፑን ለማግኘት

      @Mtshaf_bicha
      @Mtshaf_bicha
❤️ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ
👉አሰተያየት ካላችሁ
@Eyos18 አድርሱን
       📗📒📕📗📒📕
            Join&share
             @EyosC1
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
😎ጠላፊዎቹ

#ክፍል_ሃምሳ_አንድ

#የመጨረሻው ክፍል

#በኬንፎሌት

#ትርጉም_ወንዳየሁ_ንጉሴ


ጎረምሳውና ጆ ውሃ ውስጥ እየሰጠሙ ስታይ ጮኸች፡፡
ወጣቱ ልጅ ወደ ላይ ለመውጣት ሲሞክር ጆ ደግሞ ህይወቱን ለማትረፍ ወጣቱን ወደ ታች ይጎትታል፡፡ በጣም አስፈሪ ሁኔታ ነው የሚታየው፡፡
ማርጋሬት መጮኋን ሰምቶ ሉተር በመስኮት ተመለከተና ‹‹ባህሩ ውስጥ ወድቀዋል››› ሲል ጮኸ በጭንቀት፡፡

‹‹እነማ ናቸው?›› አለ ቪንቺኒ፡፡

‹‹ጎረምሳውና ጆ›› አለ ሉተር፡

የጀልባው ነጂ ገመድ ቢወረውርላቸውም ሁለቱ ሰዎች አላዩትም፡፡ እነሱ
የሚይዙትን አጥተው በፍርሃት ውሃ ውስጥ እየተንቦራጨቁ ሲሆን ጆ
ጎረምሳውን ልጅ ወደ ባህሩ ውስጥ እየደፈቀው ነው፡፡

‹‹እባክህ እርዳቸው›› አለ ሉተር እሱም በፍርሃት እየተንቀጠቀጠ፡፡

‹‹ምን?›› አለቪንቺኒ ‹‹ምንም ልንረዳቸው የምንችለው ነገር ያለ
አይመስለኝም፡ እነሱም ራሳቸውን ለማዳን አቅም የላቸውም፡፡›› በመጨረሻም
ሁለቱን ሰዎች ጨካኙ ባህር ሰለቀጣቸው፡

‹‹እንዴት ሊሆን ቻለ?›› ሲል ጠየቀ ሉተር ‹‹በመጀመሪያ ውሃ ውስጥዐእንዴት ሊወድቁ ቻሉ?››

‹‹ምናልባት የሆነ ሰው ገፍቷቸው ይሆናል›› አለ ቪንቺኒ፡

‹‹ማን?››

‹‹እዚህ አይሮፕላን ውስጥ የሆነ ሌላ ሰው ይሆናል፡›› ማርጋሬት የሁለቱን ሰዎች ንግግር ስትሰማ ስለነበር ሄሪ ሊሆን ይችላል› ስትል
ገመተች፡ ሄሪ ጀልባው ውስጥ ይኖር ይሆን?
ፖሊሶቹ አይሮፕላኑን
ሲፈትሹ እሱ የሆነ ቦታ ተደብቆ አይሮፕላኑ ባህሩ ላይ ሲያርፍ ከተደበቀበት
ወጥቶ ይሆን? ሁለቱን ወሮበሎች ውሃ ውስጥ ገፍቶ የጨመራቸው እሱ
ይሆን? እያለች መልስ የሌለው ጥያቄ በአዕምሮዋ ተጉላላ፡፡

በኋላ ደግሞ ወንድሟ ትዝ አላት ፔርሲ የወሮበሎቹ ጀልባ ከአይሮፕላኑ ጋር በሚታሰርበት ጊዜ ነው የጠፋው፡፡ ‹ምናልባትም መጸዳጃ ቤት ሄዶ ግርግሩ እስኪያልቅ እዚያው ሊቆይ አስቦ ይሆናል› አለች በሆዷ፡
እሱ ደግሞ እንዲህ አይነት ባህሪ የለውም፡፡ እሱ እንደውም ሁሉን ነገር
ለማወቅ ስለሚፈልግ ችግር አይፈራም፡፡

ሉተር ‹‹ሁሉ ነገር ከእጃችን እየወጣ ነው ምን ብናደርግ ይሻላል?›› ሲል ጠየቀ፡

‹‹አሁን በመጣችው አይሮፕላን እንሄዳለን እንዳቀድነው፡፡ አንተ፣ እኔና
ሳይንቲስቱ›› አለ ቪንቺኒ፡ ‹‹መንገዳችንን ሊያሰናክል የሚሞክር ሰው ካለ
በሆዱ ጥይት ልቀቅበት፡ አሁን ረጋ ብለን እንውጣ፡፡››
ማርጋሬት ወሮበሎቹ ፔርሲን ደረጃው ላይ ያገኙትና በሆዱ ጥይት
ይለቁበታል ብላ ሰጋች፡
ሶስቱ ሰዎች ከምግብ ቤቱ ሲወጡ የፔርሲ ድምጽ ከበስተኋላቸው
ተሰማ፡፡ ድምጹንም ከፍ አድርጎ ‹‹እንዳትነቃነቁ!›› አለ፡፡
ፔርሲ ቪንቺኒ ላይ ሽጉጡን መደገኑን ስታይ ማርጋሬት ዓይኗን ማመን አቃታት፡፡ የሽጉጡን አፈሙዝ አይታ ካፒቴኑ ከኤፍ.ቢ.አዩ ሰውዬ
ላይ የነጠቀው መሆኑን ገመተች፡

ቪንቺኒ ቀስ ብሎ ወደ ፔርሲ ዞረ፡፡

ማርጋሬት የወንድሟ ህይወት አደጋ ላይ ቢሆንም በፔርሲ ኮራች፡፡

የመብል ክፍሉ በሰው
ተሞልቷል፡፡ ከቪንቺኒ ኋላ ማርጋሬት ከተቀመጠችበት አጠገብ ሉተር በሃርትማን ላይ ሽጉጡን ደግኗል፡ በሌላኛው በኩል ናንሲ፣ መርቪን፣ ዳያና፣ ኤዲ እና ካፒቴኑ ቆመዋል ቪንቺኒ ፔርሲን ዘለግ ላለ ጊዜ አየውና ‹‹ልጅ ከዚህ ጥፋ›› አለው፡፡

‹‹ሽጉጥህን ጣል!›› ሲል ፔርሲ አዘዘ፡፡

በመሃል አንድ ጥይት ጮኸች፡፡ የጥይቱ ድምጽ ጆሮ ያደነቁራል፡
ማርጋሬት ጩኸቷን አቀለጠችው: ማን ማን ላይ እንደተኮሰ አላወቀችም:: ፔርሲ ምንም አልሆነም፡፡ ትንሽ ቆይቶ ቪንቺኒ ከደረቱ ላይ ደም እየተንፎለፎለ ተንገዳገደና መሬት ዘፍ አለ፡፡ በዚህ ጊዜ ቦርሳው
ሲወድቅ ተበረገደና ብሮቹ በደም ታጠቡ፡

ፔርሲ ቪንቺኒን ሲያይ ሽጉጡን ጣለ፡፡ ደንግጧል፡
ሁሉም ሰው ሽጉጥ የያዘው የመጨረሻው ወሮበላ ላይ አፍጧል፡

ካርል ሃርትማን በተፈጠረው
ሁኔታ ከተዘናጋው ሉተር መንጭቀው ራሳቸውን ነጻ አደረጉና መሬት ያዙ ማርጋሬት ሳይንቲስቱን ይገድላቸዋል ብላ ሰግታለች ፔርሲንም እንዲሁ፡ ነገር ግን ወዲያው የሆነው ግን
አስደንግጧታል፡፡

ሉተር አፈፍ አድርጎ ያዛት፡ ከወንበሯ ጎትቶ አነሳትና ጭንቅላቷ ላይ ሽጉጡን ደገነባት፡፡ በዚህ ጊዜ ሁሉም በድንጋጤ በድን ሆኑ።

ማርጋሬት ፍርሃት ስለገባት መንቀሳቀስ መጮህ አልቻለችም፡ የሉተር
ሽጉጭ ጭንቅላቷን እየወጋት ነው፡ ሉተር ራሱ ይንቀጠቀጣል፡፡ ከዚያም
ሳይንቲስቱን ‹‹ውጣና ጀልባ ውስጥ ግባ፡፡ ትዕዛዜን ካልፈጸምክ ልጅቷ
ጭንቅላት ላይ ጥይት እቀረቅርበታለሁ›› አለ፡፡
ወዲያው ፍርሃቷ ሲለቃት ታወቃት፡፡ ሉተር  ብልህ መሆኑን ተገንዝባለች፡፡ ሽጉጡን ሃርትማን ላይ ደግኖ ቢሆን ኖሮ ሃርትማን ግደለኝ ጀርመን አገር ከምመለስ ሞቴን እመርጣለሁ› እንደሚሉ እርግጠኛ ሆኗል፡ አሁን ግን የእሷ ህይወት አደጋ ላይ ነው፡ ሃርትማን ምናልባት
ህይወታቸውን ለመስጠት ዝግጁ ይሆኑ
ይሆናል፡፡

ሃርትማን ቀስ ብለው ተነስተው ቆሙ፡፡

ሁሉም ነገር በማርጋሬት ላይ የተጣለ ነበር፡ ራሷን ሰውታ ማዳን ትችላለች፡ ሆኖም ይህ አድራጎት ጥሩ አይደለም፡፡ እሷም ይህን አደርጋለሁ ብላ አልጠበቀችም፡፡ ለዚህ ራሴን አላዘጋጀሁም፡፡ ማድረግ አልችልም› አለች
በሆዷ፡
ከአባቷ ጋር ዓይን ላይን ግጥም አሉ፡፡ አባቷ በጣም ደንግጠዋል ሲያበሻቅጧት እንደኖሩ ምን ያህል
አቅመቢስ እንደሆነች ጦሩንም ተቀላቅላ አንድ ቀን እንኳን እንደማትቆይ
የነገሯት ሁሉ ትዝ አላት፡፡
አባቴ ያለው እውነት ይሆን?› አለች ለራሷ፡
ስለዚህ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለባት ወሰነች፡፡ ሉተር ሊገላት ይችላል ነገር ግን አንድ ነገር ከማድረጉ በፊት ሌሎች ሰዎች ዘለው ይረባረቡበታል ጊዜው እየሄደ ነው፤ አንድ ነገር ማድረግ አያቅተኝም, አለች በሆዷ፡

ከዚያም ‹‹ሁላችሁም ደህና ሁኑ›› አለች፡፡ አፍታም ሳይቆይ የሄሪን ድምጽ ከኋላዋ ሰማች፡፡

‹‹ሚስተር ሉተር ጠላቂው መርከብህ ደርሷል›› አለ፡፡

ሁሉም ሰው በአይሮፕላኑ መስኮት ተመለከተ፡፡ ማርጋሬት ሄሪ በተናገረው ነገር ሉተር ልቡ መወሰዱን አወቀች፡፡ ከዚያ አንድ ጥይት ጮኸች፤ እሷ ግን ምንም አልሆነችም፡፡ ሁሉም አንድ ጊዜ ተንቀሳቀሰ፡፡ ኤዲ ዘለለና እንደ ተቆረጠ ዛፍ ሉተር ላይ ወደቀበት፡፡ ሄሪ የሉተርን ሽጉጥ
መንጭቆ ወሰደ፡፡

ፔርሲ ወደ ማርጋሬት ሄደና አቀፈችው፡፡ ‹‹አንተ ግን ደህና ነህ?››ቸ ስትል ጠየቀችው፡፡

‹‹አዎ ይመስለኛል››
‹‹በጣም ጎበዝ ነህ››
‹‹አንቺም እንዲሁ››
‹አዎ እኔ ጎበዝ ነኝ አለች ለራሷ፡
ፀጥ ብሎ የቆየው ተሳፋሪ ሁሉ በአንድ ጊዜ ተንጫጫ፡፡ በዚህ ጊዜ
ካፒቴኑ ‹‹ፀጥታ እባካችሁ ዝም በሉ›› አለ፡፡
ማርጋሬት ዙሪያውን ቃኘች፡፡
ሉተር ኤዲ እና ሄሪ ላዩ ላይ ወጥተውበት ከመሬቱ ላይ እንደተደፋ ነው፡፡ አይሮፕላኑ ውስጥ ያንዣበበው አደጋ ተወግዷል፡ ሃርትማንና
ሉተርን ሊወስድ የመጣው ጠላቂ መርከብ ተንሳፎ ይታያል፡

ካፒቴኑም የባህር ኃይል መርከብ በቅርብ ርቀት ይታያል፡ ‹‹ጠላቂ
መርከብ እዚህ እንዳለ የሬዲዮ መልእክት እናስተላልፋለን፡፡››
‹‹ቤን›› ሲል ተጣራ፡
‹‹አቤት ጌታዬ›› አለ የሬዲዮ ኦፕሬተሩ ‹‹የጠላቂው መርከብ አዛዥ
ሬዲዮ መልእክት ማስተላለፋችንን ካወቀ ወደ እኛ ሊተኩስ እንደሚችል
ተገንዝበኸዋል?›› አለ ቤን፡፡

‹‹ደህና ይቅር›› አለ ካፒቴኑ ‹‹ተሳፋሪዎቻችን እስካሁን የደረሰባቸው መከራ
ይበቃል፡››
ጠላቂው መርከብ መግቢያው እንደተዘጋ ነው አዛዡ  አንድ ነገር
ይሆናል ብሎ እየጠበቀ ነው፡፡

‹‹ቤከር አንድ ያልተያዘ ወሮበላ  ይቀረናል፡ እዚህ እንዲመጣ እፈልጋለሁ፡፡ የጀልባዋ ነጂ፡ ኤዲ ሂድና ቪንቺኒ እንደሚፈልገው ንገረው አለው
ኤዲ ሉተርን ለቀቀና ወጥቶ ሄደ፡

ካፒቴኑ ናቪጌተሩን ጠራና ‹‹እነዚህን ሽጉጦች ሰብስብና ጥይቶቹን
አውጥተህ አስቀምጥ›› ሲል አዘዘ፡፡

ካፒቴኑ ሉተርን በጫማው ወጋ አደረገውና ሌላውን የአይሮፕላኑ ሰራተኛ የሆነውን ጆኒን ‹‹ይህን ወንበዴ ውሰድና አንድ ክፍል ውስጥ ቆልፍበት ጠብቀው›› ሲል አዘዘው፡
ሄሪ ሉተርን ለቀቀውና ጆኒ ይዞት ሄደ፡

ሄሪና ማርጋሬት ተያዩ፡
ሄሪ ትቶኝ ሄዷል ብላ ደምድማ ነበር፡፡ እስከወዲያኛው ዓይኑን
አላየውም ብላ ነበር ያሰበችው: ህይወቴ ይተርፋልም ብላ አልገመተችም፡ ሆኖም ግን በአምላክ ቸርነት በህይወት መገናኘታቸው ደንቋታል፡
ማርጋሬት ሮጠችና እቅፉ ውስጥ ገባች፡፡ አንድ ሰው እስኪመስሉ ድረስ
ተጣበቁ፡፡

ትንሽ ቆይቶ ‹‹ወደ ውጭ ተመልከች›› አላት፡፡
ጠላቂው መርከብ ቀስ እያለ እየሰመጠ ነበር፡፡
ማርጋሬት ፈገግ አለችና ሄሪን ከንፈሩን መጠመጠችው፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ሁሉ ነገር ካበቃ በኋላ ካሮል አን ባሏ ጫፌን አይነካኝም ብላ መሸሽ ጀምራለች፡ አስተናጋጁ ዴቪ ያፈላላትን ማኪያቶ እየጠጣች ነው፡ ፊቷ ገርጥቷል፡፡ ሰውነቷ አሁንም ይንቀጠቀጣል፡፡ ኤዲ ባለፈ ባገደመ ቁጥር
ሲነካት ድንግጥ ትላለች፡፡

አጠገቧ ቁጭ ብሎ ያያታል፡፡ እሷ ግን የባሏን ዓይን ትሸሻለች፡፡ ምን
እንደተፈጠረ ያወራሉ፡፡ ሰዎቹ በሩን በርግደው ገብተው ወደ መኪናቸው
እየጎተቱ እንደወሰዷት ደጋግማ ትነግረዋለች ታሪኩ ይሄ ብቻ እንደሆነ
ሁሉ፡፡

‹‹አሁን ክፉው ነገር ሁሉ አልፏል›› ይላታል ኤዲ ደጋግሞ፧ እሷም ራሷን ትነቀንቃለች ነገር ግን እሷ ከዚህ በሰላም እስካልወጣች ድረስ
አታምንም::
በመጨረሻ እንደምንም ብላ ቀና ብላ አየችውና ‹‹በሚቀጥለው ጊዜ መቹ
ነው የምትበረው?›› ስትል ጠየቀችው፡፡

ጥያቄዋ ገባው፡፡ እሱም ‹‹የበረራ ስራ አቆማለሁ›› አላት ‹አሁኑኑ ስራዬን እለቃለሁ፡ እኔም ስራዬን ባልለቅ እነሱ ማባረራቸው አይቀርም::የተሳፋሪዎቹን ህይወት አደጋ ላይ ጥሎ ድንገት አይሮፕላን ባህር ላይ እንዲያርፍ የሚያደርግ እንደ እኔ ያለ አይቆይም፡፡››

ካፒቴን ባልና ሚስቱ የሚነጋገሩትን ሰምቶ ኖሮ
‹‹አንድ ነገር ልነግርህ
ወደድኩ፡፡ ያደረከው ነገር በሙሉ አሁን ገብቶኛል፤ የገጠመህን ችግር በድል
ለመወጣት የምትችለውን አድርገሃል፡፡ አንተ ካደረግኸው የተሻለ ነገሩን
የሚያስኬድ ሰው አለ ብዬ አላምንም፧ በጣም ጎበዝ ስለሆንክ ከአንተ ጋር
መብረሩ ያኮራኛል›› አለ፡፡

‹‹አመሰግናለሁ አለቃ›› አለ ኤዲ፡፡ ኤዲ በካፒቴኑ አነጋገር ልቡ ተነካና ሳግ ጉሮሮውን ተናነቀው፤ ‹‹ያልከው ነገር ምን ያህል ችግሬን እንዳቀለለልኝ
መናገር ያቅተኛል›› አለ፡ ዞር ብሎ በድንጋጤ የተሸማቀቀውን ፔርሲን
ተመለከተና ‹‹ጌታዬ ወጣቱ ፔርሲን ማመስገን ይገባናል፤ እሱ ነው ከጉድ
ያወጣን›› አለ

‹‹ጥሩ ብለሃል›› አለ ካፒቴኑ የኤዲን ጀርባ በአድናቆት ቸበቸበና፡ ወደ ፔርሲም ሄዶ

‹‹አንተ ጎበዝ ልጅ ነህ ፔርሲ›› አለና ጨበጠው፡፡
ፔርሲም ወዲያው ድንጋጤው ለቀቀውና ‹‹አመሰግናለሁ›› አለ፡
ካሮል አን ‹‹መብረር የምታቆም ከሆነ ምን አይነት ስራ ልትሰራ
አስበሃል?›› ስትል ጠየቀችው ኤዲን፡፡

‹‹የተነጋገርነውን ስራ እጀምራለሁ፡››

ዓይኗ ላይ ተስፋ አነበበ፤ ነገር ግን ለማመን ስለቸገራት ‹‹እንችላለን?››
ስትል ጠየቀችው፡

‹‹አየር ማረፊያውን ለመግዛት የሚያስችለኝን ገንዘብ ባንክ አስቀምጫለሁ። ቀሪውን ከባንክ እበደራለሁ፡፡››

ካሮል አን ወዲያውኑ በደስታ ዓይኗ በራና ‹‹አብረን እንሰራለና›› አለች
‹‹አንተ ለጥገና ወይም ነዳጅ ለመሙላት ስትሄድ እኔ ሂሳብ እሰራልሃለሁ
የስልክ ጥሪም እቀበላለሁ፡››
ኤዲም ፈገግ አለና ‹‹ልጅ እስከምትወልጂ ድረስ›› አለ፡፡

እጁን ሰደደና እጇን ለቀም አደረገው:፡ በዚህ ጊዜ በድንጋጤ ድንብር
አላለችም፡፡ እንደውም እሷ አጥብቃ እጁን ያዘች፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ናንሲ መርቪንን እንቅ አድርጋ ስትይዘው ዳያና ልታናግረው ፈልጋ
ጀርባውን ነካ አደረገችው፡፡

ናንሲ የእሷና የምትወደው ሰው ህይወት መትረፍ በፈጠረላት ደስታ
ተውጣለች፡ ዳያና በዚህ ጊዜ የመጣላትን ደስታ እንዳትነጥቅባት ተመኘች፡፡
ዳያና ከባሏ ለመለየት እስካሁን ቁርጥ ውሳኔ ላይ አልደረሰችም ነበር፡ አንዴ
መጣ አንዴ ሸሸት ስትል ነበር እስካሁን የቆየችው የእሷን ህይወት ለማትረፍ ከወረበሎች ጋር መደራደሩ እስካሁን ለእሷ ያለውን ፍቅር ያሳያል፡፡ ‹ታዲያ መልሰህ ውሰደኝ ትለው ይሆን?,

መርቪን ወደ ሚስቱ ዞር አለና ‹‹አቤት ዳያና›› አላት፡፡ ዓይኗ በእምባ የተሞላ ቢሆንም ውሳኔ ላይ እንደደረሰች ያስታውቃል፡ ‹‹ከዚህ በኋላ ታናግረኛለህ?›› አለች

ዳያና ያለችው ለናንሲ ግልፅ አልሆነላትም፡፡ የመርቪን ሆድ አልቆርጥ ማለቱም ወደ እሷ ይመለሳል የሚል ጥርጣሬ አጭሮባታል፡

እሱም እጇን ለመጨበጥ እጁን ዘረጋና ‹‹በሚገባ›› አላት፡፡

ዳያና በሁለት እጇ እጁን አጥብቃ ያዘችው አሁንም ታነባለች፡፡

ናንሲ ይህን ስታይ ዳያና ‹ወደቤት እመለሳለሁ› ትላለች ብላ ጠበቀች
የተገላቢጦሽ ግን ‹‹መልካም ዕድል ይግጠምህ መርቪን፡፡ ቀሪው ህይወት በደስታ የተሞላ እንዲሆን እመኝልሃለሁ›› አለች፡፡

መርቪን ፊቱን እንደከፋው ‹‹አመሰግናለሁ ዳያና፤ እኔም እንደዚሁ መልካም ዕድል እንዲገጥምሽ እመኝልሻለሁ›› አለ፡፡

ናንሲ ሁለቱም ለሆነው ነገር ይቅር ሊባባሉ እንደሆነ ገባት መለያየታቸው አይቀርም፧ ሆኖም የሚለያዩት ቂም በሆዳቸው ቋጥረው አይደለም፡፡

በደመነፍስ ናንሲ ጣውንቷን ‹‹መጨባበጥ እንችላለን?›› አለቻት፡

ዳያናም ‹‹አዎ›› አለችና ተጨባበጡ ‹‹መልካም ዕድል ይግጠምሽ››
አለቻት፡፡

‹‹አንቺም እንዲሁ›› አለች ናንሲ፡፡

ዳያና ዞረችና ወደ መቀመጫዋ ተመለሰች፡፡
መርቪንም ‹‹እንዴት ነው የወደፊት አኗኗራችን?›› ሲል ናንሲን ጠየቃት፡፡

ናንሲ ጊዜ አግኝታ ያሰበችውን አለመንገሯን ተገነዘበች፡፡ ‹‹የናት
ሪጅዌይ ኩባንያ የአውሮፓ ሀላፊ ሆኜ እሰራለሁ››
መርቪን አባባሏ ገረመውና ‹‹ይህን ኃላፊነት የሰጠሽ መቼ ነው?›› ሲል
ጠየቃት፡፡

‹‹አልሰጠኝም ነገር ግን ይሰጠኛል›› አለችና በደስታ ተፍነከነከች፡

ትንሽ ቆየና የሞተር ጩኸት ተሰማ፡፡ ይህ ድምጽ ግን የግዙፉ አይሮፕላናቸው ድምጽ እንዳልሆነ ይታወቃል፡ የባህር ኃይሎች የመጡ መስሏት ናንሲ በመስኮት አየች፡፡

የወሮበሎቹ ጀልባ ከትልቁ
አይሮፕላን ጋር የታሰረበት ገመድ መፈታቱንና ጀልባው ሊሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን አየች፡:

ታዲያ ጀልባውን ማነው የሚነዳው?

ማርጋሬት በፍጥነት ጀልባውን ነዳችው፡፡

ንፋሱ ጸጉሯን ወደ ኋላ ይገፋዋል፡፡

በደስታ ‹‹አሁን ነፃ! ነፃ!›› አለች፡፡

እሷና ሄሪ ይህ ሀሳብ የመጣላቸው ሳይነጋገሩ ነው፡

‹ወደፊት እንዴት ነው የምንኖረው?› እያሉ በየግላቸው ሲያስቡ ኤዲ
ወሮበሎቹን ይዞ የመጣውን ጀልባ ነጂ አግቶ ሲያመጣው ጀልባውን ይዞ
መጥፋት የሚባል ሀሳብ መጣላቸው፡፡

ተሳፋሪዎቹ ከሞት አደጋ ስለተረፉ እርስ በእርሳቸው ‹‹እንኳን ደስ ያለህ ደስ ያለሽ›› ሲባባሉ ሄሪና ማርጋሬት ሾልከው ወጥተው ነው ጀልባው
ላይ የወጡት፡፡ የጀልባው ሞተር አልጠፋም ነበር፡ ሄሪ ጀልባው ከትልቁ አይሮፕላን ጋር የታሰረበትን ገመድ ሲፈታ ማርጋሬት በበኩሏ የሞተሩን ማንቀሳቀሻ መሳሪያዎች እንዴት እንደሚሰሩ እየቃኘች ነበር፡ ጀልባው ደግሞ ከአባቷ ጀልባ ጋር ብዙ ልዩነት የለውም፡፡