Exit Exam Preparation
38.3K subscribers
79 photos
1 video
6 files
17 links
Exit Exam በከፍተኛ ውጤት ለማለፍ የሚረዳ ፣ ከዚ በፊት የነበሩ የExit Exam ጥያቄዎችን ከነ መልስና ማብራሪያቸው የያዘ Quiz Bot


@Exit_Exam_preparationbot
Download Telegram
#DebreBerhanUniversity

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1008 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

ተመራቂዎቹ 919 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 87 በሁለተኛ ዲግሪ እና ሁለት ተማሪዎች ደግሞ በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን በመደበኛ እና በተከታታይ መርሐግብር ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
42👍7😁6
51A+ ያስመዘገበችው ተመራቂ 👏👏

ቃልኪዳን ታዘብ ከመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ባዮሎጅ ትምህርት ክፍል የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ ናት።

ተማሪ ቃልኪዳን CGPA 4.00 አጠቃላይ ውጤት ብቻ አይደለም ያስመዘገበችው። በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ ከወሰደቻቸው ኮርሶች 51A+ እና 6A በማምጣት ያጠናቀቀችው።

በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ቃልኪዳን፤ ከአጠቃላይ ተመራቂ ተማሪዎች አንደኛ በመውጣት የሁለት ዋንጫዎች ተሸላሚ ሆናለች፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ተመራቂ ቃልኪዳን በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት ተቀጥራ እንድታገለግል መወሰኑ ተገልጿል።

የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉 @Exit_Exam_prep
👍5835🥰11😭5🔥1
#ማሳሰቢያ

የዲግሪ ሰርተፍኬት ለዩንቨርስቲዎች መላኩ የተረጋገጠ ሲሆን ዩንቨርስቲዎች ከዛሬ ጀምሮ ቴምፖ መስጠት ጀምረዋል የመውጫ ፈተና በተመለከተ ላለፉ ተማሪዎች ብቻ ይሰጣል ተብሏል።


የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉 @Exit_Exam_prep
👏5748😭18👍11🥰2🤔2
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ ነገ መጋቢት 15/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ላይ ይጠናቀቃል።

በተሰጠው ጊዜ ያልተመዘገበ ተማሪ ለፈተናው መቀመጥ አይችልም። ያልተመዘገበ ተማሪ በቀጣይ ዓመት የሚፈተን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ ከ9-11 ክፍል የተማሩበት ውጤት
➫ አሁን ላይ የ12ኛ ክፍል ተማሪ መሆን

በድጋሜ ተፈታኝ ከሆኑ https://register.eaes.et ላይ ከዚህ በፊት የተፈተኑበትን አድሚሽን ካርድ በማስገባትና 750 ብር ክፍያ በመፈጸም መመዝገብ ይችላሉ።

ተፈታኞች በመረጡበት የፈተና ማዕከል መፈተን እንደሚችሉ ተገልጿል።

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚሰጥበት ትክክለኛ ጊዜ ባይገለፅም፤ ፈተናው ሰኔ ወር ውስጥ እንደሚሰጥ ይጠበቃል። 

የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
52🤔3👍1
#TVTI #ExitExam

የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና አርብ መጋቢት 18/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ፣ የሳተላይት ካምፓሶች እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የጨርቃ ጨርቅ ቴክኖሎጂ የክረምት ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ለመውሰድ እየጠበቁ እንደሚገኙ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡

የመውጫ ፈተናው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ጋር በመተባበር በተመረጡ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አርብ መጋቢት 18/2018 ዓ.ም ከጠዋት 2፡30-5፡30 ይሰጣል፡፡

የተመዘገቡ ተማሪዎች በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ፈተናውን መውሰድ ያለባቸው ሲሆን፤ ህጋዊ መታወቂያ (የዩኒቨርሲቲ መታወቂያ፣ የቀበሌ መታወቂያ ወይም የፋይዳ መታወቂያ) መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

Username and Password ተፈታኞቹ በየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የተለጠፈ መሆኑን ኢንስቲትዩቱ ገልጿል፡፡


የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
53👍1
ባለፈው ወር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 48,692 (23.8 በመቶ) የሚሆኑት ተፈታኞች ብቻ ፈተናውን ማለፋቸው ተሰምቷል።

ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡ 236,460 ተማሪዎች ውስጥ 204,028 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

32,000 በላይ ተማሪዎች ተመዝግበው 'በግል ምክንያት' ሳይፈተኑ መቅረታቸውን አንድ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን ጠቅሶ መረጃ አጋርቷል።

በአጠቃላይ 342 ተቋማት ማለትም 70 የመንግሥት እና 272 የግል ተቋማት በፈተና አሰጣጡ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል።

የመውጫ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 48,692 ተፈታኞች ብቻ ያለፉ ሲሆን፤ በቅሬታ ሂደት ላይ ያሉ ውጤቶች አሐዙን ሊያሳድጉት ይችላሉ ተብሏል።


የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
51😢13🥰1👏1
#coc

የብቃት ምዘና ፈተና በተመለከት አጠቃላይ ማብራሪያ

የ coc ፈተና ከ 2019 Gc ጀምሮ በጤና ሚንስትር ለጤና ዘርፍ ተመራቂ ተማሪዎች የሚሰጥ ፈተና ነው ። በ 13 የጤና ዘርፎች የሚሰጠው ፈተናው ከ2015ዓ.ም ጀምሮ ደሞ የመውጫ ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ብቻ እንዲወስዱት ተደርጓል ። ፈተናው በከፍተኛ ትምህርት መምህራን ሚዘጋጅ ሲሆን ሁሉም ጥያቄዎች scenario based ናቸው ፈተናው ለ የ department በተመረጡ standard text book እና updated guide lines ላይ ተመስርቶ ነው ሚዘጋጀው ከመውጫ ፈተና ያለው ልዩነት ተማሪው understand ማድረጉን ላይ ሳይሆን knows how ወይ ደሞ evaluate አድርጎ ለታካሚ ሚወስደውን decision ላይ በብዛት ማተኮሩ ነው።

ፈተናውን ለመፈተን ቴምፖ ግዴታ ነው!

ምዝገባው በዚህ ወር ጀምሮ እስከ ቀጣይ ወር መጀመሪያ እንደሚቀጥል ሲጠበቅ ፈተናው በሚያዚያ ወር መጨረሻ አሊያ ደሞ በግንቦት መጀመሪያ ይሰጣል ።


ፈተናውን እንድታልፉ ሚረዳቹ ከዚ በፊት የነበሩ ጥያቄዎችን ከነ መልስና ማብራሪያው ተዘጋጅቶላቹሀል ይሄን በመንካት እራሳችሁን ለፈተናው አዘጋጁ
👉@Exit_Exam_preparationbot



ያለፉ ተማሪዎች ሊስት ወደ ከተማ መስተዳድር ስማቸው ተልኮ license ከዛው ሚወስዱ ይሆናል።



የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
108👍21🔥5😁4🤔4👏1💔1🖕1
#exit_exam

ለቅሬታ የሚሰጡ ምላሾች ዛሬ ነው ሚጠናቀቁት።
ከ15 ሺህ በላይ ቅሬታዎች ገብተው የተወሰኑት በአግባቡ ተስተካክለዋል። አቶ ተፈሪ(eaes)

የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
61👍22😢18😁6🕊6
#JigjigaUniversity

ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 907 ተማሪዎች አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው 17ኛ ዙር ተመራቂዎች በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሕክምና ዶክትሬት እና በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።


የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
21
#AdigratUniversity

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 167 ተማሪዎች አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 16ቱ የሕክምና ዶክተሮች መሆናቸው ተገልጿል።

የተቋሙ 12ኛ ዙር ተመራቂዎች 121 በመጀመሪያ ዲግሪ እና 46 በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ  ናቸው።


የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
23
#WolaitaSodoUniversity

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 352 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን ከ2,300 በላይ ተማሪዎች ትናንት ማስመረቁ ይታወቃል።

የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
34👍2🥰2
በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተሰማሩ 52 የግል ኮሌጆች ታገዱ

የኢ. ፌ. ዲ. ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር መሰረት በማድረግ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ባደረገው የክትትልና ቁጥጥር ስራዎች 52 የግል ኮሌጆች ከዘርፉ እንዲወጡ ማድረሱን አስታወቀ፡፡

ተቋማቱ  በዳግም ምዝገባ ስርዓት ውስጥ ባለመግባታቸው ምክንያት ከከፍተኛ ትምህርት ሴክተር እንዲወጡ የታዘዙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት  ዝርዝር አሳውቋል፡፡

ባለስልጣኑ እንዳታወቀው ተቋማቱ  አራት ጊዜ በደብዳቤ፣ አንድ ጊዜ በስልክ እንዲሁም  አንድ ጊዜ በአካል ቀርበው እንዲያስረዱ በስልክ ጥሪ በተደጋጋሚ ጥሪ ባለማክበራቸው ህጋዊነታቸው ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም ተቋማቱ የተላለፈውን ውሳኔ ተግባራዊ እንድያደርጉ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ህጋዊነታቸው የተቋረጠ ሰለሆነ  በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ተሰማርተው ዜጎች ላይ  ጉዳት እንዳያደርሱ የከፍተኛ ትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ እና አስፈላው የህግ እንደሚወሰድባቸው መገለፁን ብስራት ሬዲዮ ከኢ. ፌ. ዲ. ሪ ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የደረሰው መረጃ ያመላክታል፡፡

የ University  መረጃ የምትገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
80👍8😁7🔥5🤨2