Exit Exam Preparation
50.9K subscribers
237 photos
1 video
11 files
60 links
Exit Exam በከፍተኛ ውጤት ለማለፍ የሚረዳ ፣ ከዚ በፊት የነበሩ የExit Exam ጥያቄዎችን ከነ መልስና ማብራሪያቸው የያዘ Quiz Bot


@Exit_Exam_preparationbot
Download Telegram
#NGAT
 
አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ረቡዕ ሐምሌ 29/2018 ዓ.ም መከናወኑ ይታወቃል፡፡  
 
የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን Update እያደረጋችሁ ያላችሁ ተፈታኞች፣ በፈተና ሲስተሙ ላይ የሚገኝ የትኛውንም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ በፈተና ማዕከልነት መምረጥ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡
 
🔔 የተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket የ GAT ፈተና ከሚሰጥበት ሁለት ወይም ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ በእያንዳንዳችሁ Dashboard ላይ የሚመጣላችሁ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ዳሽቦርዳችሁን ቶሎቶሎ ቼክ እንድታደርጉ ተብሏል፡፡

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
57🥰6👏4
COC ተፈታኝ ለሆኑ በሙሉ share አርጉላቸው።

ይሄ የቴሌግራም ቦት ከዚ በፊት የነበሩ የ COC ጥያቄዎችን ከነ መልስና ማብራሪያቸው የያዘ ነው።

ጥያቄዎቹ ለመስራት አመቺ ስለሆኑ የትም ቦታ ሆነው መስራት ይችላሉ
የተካተቱ Health Department
1, Pharmacy
2, Bsc Nursing
3, Medical Laboratory
4, Public Health HO

ለማግኘት👇
@Exit_Exam_Preparationbot
49👍21🤔2
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና መርሐግብር
 
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡
 
ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም
Medicine, Pharmacy, Anesthesia, Environmental Health, Human Nutrition, Emergency and Critical Care Nursing, Dental Medicine and Optometry.

ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም
Medical Laboratory Science, Public Health, Midwifery, Medical Radiology Technology, Pediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing, Physiotherapy and Surgical Nursing.

ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም - Nursing

ተፈታኞች ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አጠቃላይ ቅድመ ገለጻ (Orientation) መከታተል ይጠበቅባችኋል፡፡
 
የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
38👍1
#ተጨማሪ
 
ከነሐሴ 13-15/2018 ዓ.ም በሚሰጠው የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ወቅት ተፈታኞች የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡

ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡

በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ-ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል፡፡



ተመዛኞች ስማችሁ ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ እንደማይፈቀድላችሁ ተገልጿል፡፡
 
የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
42
All Examinee Nehase 2018.zip
7.2 MB
ተመዛኞች የመረጧቸው የፈተና ማዕከል

@Exit_Exam_prep
20
#NGAT
 
አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡  
 
ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket ለማግኘት የኢሜይል አድራሻችሁን መጎብኘት አትዘንጉ።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
23👍14
የብቃት ምዘና ፈተና ተመዛኞች በሙሉ

የጤና ሚኒስቴር ከነሀሴ 13 እስከ 15 /2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተናን በ17 የሙያ አይነቶች ተመዝግባቸሁ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ ተመዛኞች ነገ ማክሰኞ ነሃሴ 12/2018 ዓም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት በየመፈተኛ ጣቢያችሁ በመገኘት ቅድመ ፈተና ገለፃ እንድትከታተሉ እናሳስባለን።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉 @Exit_Exam_prep
46🔥2👍1
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ዛሬ መሠጠት ጀምራል፡፡

ፈተናው በ31 የመፈተኛ ጣቢያዎች እየተሠጠ ሲሆን፣ እስከ አርብ ነሐሴ 15/2018 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።

ፈተናው ነገ ነሐሴ 14/2018 ዓ.ም ሲቀጥል፤ የMedical Laboratory Science, Public Health, Midwifery, Medical Radiology Technology, Paediatric and Child Health Nursing, Psychiatric Nursing, Surgical Nursing ሙያ ተመዛኞች ጠዋት ከ3:00 ሰዓት ጀምሮ እና ከሰዓት ከ8:00 ሰዓት ጀምሮ ፈተናቸውን የሚወስዱ ይሆናል።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
17
COC ተፈታኝ ለሆኑ በሙሉ share አርጉላቸው።

ይሄ የቴሌግራም ቦት ከዚ በፊት የነበሩ የ COC ጥያቄዎችን ከነ መልስና ማብራሪያቸው የያዘ ነው።

ጥያቄዎቹ ለመስራት አመቺ ስለሆኑ የትም ቦታ ሆነው መስራት ይችላሉ
የተካተቱ Health Department
1, Pharmacy
2, Bsc Nursing
3, Medical Laboratory
4, Public Health HO

ለማግኘት👇
@Exit_Exam_Preparationbot
41🔥6
#NGAT
 

የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ለአገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) በፈተና ጣቢያነት ባለመካተታቸው ቅሬታ ለትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ማቅረባቸው ተሰምቷል፡፡
 
አገልግሎቱ ቅሬታ ላቀረቡ ዩኒቨርሲቲዎች በሰጠው ምላሽ፤ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ጣቢያነት ያልተመረጡት ከፌዴራል ተቋሙ የማስፈፀም አቅም ውስንነት ጋር በተያያዘ መሆኑን ገልጿል፡፡
 
"ፈተናውን ለማስፈፀም ከማዕከል የሚጠቀሟቸው አስተባባሪዎች እና የፌዴራል ፖሊስ ፀጥታ ኃይሎች ማሰማራት የማይችልባቸው ሁኔታዎች ስላሉ ብቻ" የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ጣቢያነት አለመካተታቸውን አገልግሎቱ አስረድቷል፡፡
 
የ NGAT ምዝገባ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሲከናወነ መቆየቱ ይታወሳል። አሁን ላይ የተወሰኑ ተፈታኞቹ ወደ ሌሎች ዩነቨርሲቲዎች እንዲዘዋወሩ መደረጉ ታውቋል፡፡
 
በመሆኑም ተፈታኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉና በተመደቡበት አቅራቢያ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ፈተናቸውን እንዲወስዱ አገልግሎቱ ጥሪ አድርጓል፡፡
 
አገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
 
የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
31👍7🔥1😁1
#National_Exam_Result

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 12.8% ተማሪዎች ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ።

ለፈተና ከተቀመጡ 560,210 ተማሪዎች 70,544 ወይም 12.8% የሚሆኑት ማለፋቸውን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

በመላ አገሪቱ የመልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ውስጥ 88 ትምህርት ቤቶች 100% ያስፈተኗቸውን ተማሪዎች ማሳለፋቸውን የገለፁ ሲሆን፣ 585 ትምህርት ቤቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ገልፀዋል።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
12🔥1
#National_Exam_Result

| የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ወይም ማክሰኞ ለተማሪዎች ይላካል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምልመላ እና ቅበላ ካደረጉ በኋላ ሌሎቹም ዩኒቨርሲቲዎች ቶሎ ጥሪ እንዲያደርጉ እየሠራን ነው። መስከረም 05/2019 ዓ.ም ትምህርት ይጀመር የሚለውን ለመጠበቅ እንፈልጋለን።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
8
#National_Exam_Result

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት፦

ተፈጥር ሳይንስ
ወንድ - 591.6 ኦዳ ልዩ አዳሪ ት/ቤት (አዳማ)
ሴት - 583 አገው ምድር ት/ቤት (እንጅባራ)

ማኅበራዊ ሳይንስ
ወንድ - 576.2 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት
ሴት - 569.1 ቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
11👏1
|| የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወደ ፈተና ማዕከል ከመግባት ጋር በተያያዘ የዲሲፕሊን ችግር የተገኘባቸው 265 ተማሪዎች ከፈተናው እንዲባረሩ ተደርጓል።

ከኮምፒውተር ፈተና አሰጣጡ ጋር በተያያዘ Irregularities ጉዳያቸው እየታየ የሚገኙ ተማሪዎችም አሉ።

ዘንድሮ በኦንላይን ፈተናው ከወሰዱ 18.37% ተማሪዎች አልፈዋል፤ በወረቀት ከተፈተኑት ውስጥ 4.2% አልፈዋል።

ዘንድሮ በኦንላይን ፈተናው የወሰዱ ተማሪዎች በአጠቃላይ 60 በመቶ አካባቢ ነበር። በሚቀጥለው ዓመት ፈተናውን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ዕቅድ ይዘናል።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
6
ለ2019 የትምህርት ዘመን የሪሚዲያል ተማሪዎች ቅበላ እንደሚኖር የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አረጋግጠዋል።

ይሁን እንጂ በ2019 ዓ.ም ወደ ሪሚዲያል ፕሮግራም የሚገቡ ተማሪዎች እንደቀደሙት ዓመታት ብዙ እንደማይሆን ገልፀዋል።

"ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ወደ ዩኒቨርሲቲ ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሪሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል" ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ምን ያህል ተማሪ ወደ ፕሮግራሙ ይገባል የሚለው ግን አጠቃላይ የውጤቱ ሥራ ከተጠናቀቀ በኋላ የመቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለፅ ይሆናል ብለዋል።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
31😁5
#NGAT

የሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket አሁን ላይ ማግኘት እንደምትችሉ ተገልጿል።

በመሆኑም ፕሮፋይላችሁ ላይ በመግባት 'Exam Credentials' በሚለው ስር 'Download Entry Ticket' የሚለውን በመጫን ወደ ፈተና ማዕከል መግቢያ ትኬትዎን አውርደው ፕሪንት ያድርጉ።

ፈተናው ከሚጀመርበት ሰዓት 30 ደቂቃ ቀድማችሁ መድረስ ይጠበቅባችኋል።

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል፡፡

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
31👍5
#NGAT_Schedule

የ2018 ዓ.ም መጨረሻ ዓመት ብሔራዊ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) የፈተና መስጫ መርሐግብር፦

ፈተናው በጠዋት እና በከሰዓት ፈረቃ ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
48👍3😁2
#MoH

ነሐሴ 13/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የሙያ ፈቃድ የፅሑፍ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ሙያ ተመዛኞች፣ ውጤታችሁን ከዛሬ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

የፅሑፍ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች የተግባር ፈተና ለመውሰድ ነሐሴ 23 እና 24/2018 ዓ.ም ብቻ ምዝገባ የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል።

በመሆኑም በተገለፁት ቀናት https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት መፈተኛ ጣቢያ በመምረጥ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ ተብሏል።

ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ ሲስተሙ የሚሰጣችሁን QR Code የያዘ ስሊፕ ይዛችሁ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
42
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ምዝገባ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ-ምረቃ በቀን መደበኛ መርሐግብር (በመንግሥት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሐግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

መስፈርቶች
➻ በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ
➻ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) ይወስዳሉ

የምዝገባ ጊዜ 👇
እስከ ነሐሴ 29/2018 ዓ.ም ድረስ

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇
https://admission.aau.edu.et

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ፈተና (UAT) ከጳጉሜን 02-04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡


የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉 @Exit_Exam_prep
36🔥3👏3
#RemedialResult

በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ተማሪዎች ውጤት ተለቋል።

https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Examination ከሚለው ስር View Results የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።

ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን ሀገር አቀፍ የሪሚዲያል ፕሮግራም ፈተና 53,620 ተፈታኞች መውሰዳቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወሳል።

የ University  መረጃ የምታገኙበት 
👉
@Exit_Exam_prep
32👍2