EvaSUE |ኢቫሱ
8.17K subscribers
2.23K photos
15 videos
5 files
477 links
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎችና ምሩቃን ማሕበር [ኢቫሱ] -ከ1950ዎቹ ጀምሮ

#ተቀዳሚ_ዐላማ፤የምንኖርለት:-

<<ተማሪዎችን በማገልገል የእግዚአብሔርን መንግስት ማስፋት>>

ኢቫሱ፣ በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ #176 የዩኒቨርሲቲና ኮሌጅ ወንጌላውያን ክርስቲያን ተማሪዎች ሕብረቶችን በማቀፍ ያገለግላል።

#በዚህ_ቻናል:-
☞ለካምፓስ ሕብረቶች የሚጠቅሙ መልእክቶች ይተላለፉበታል!
Download Telegram
ቅዱሣን፣ ሰላም ለእናንተ ይሁን።

ዛሬ ስለ #የወንጌል_ተልዕኮ የምናስብበት ቀን ነው!

ባለፉት ጊዜያት #ተልዕኮ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ያለው ብቻ ሳይሆን መፅሐፍ ቅዱስ #እራሱ መሰረቱ ተልዕኮ እንደሆነ አይተናል።

እራሱን ለሰው ልጆች በመግለጥ ተልዕኮ ላይ ያለው እግዚአብሔር እራሱን የገለጠበት መንገድ አንዱ #ቃሉ እንደሆነ አይተናል።
በሌላ በኩል ደግሞ ያለመጽሐፍ ቅዱስ #ተልዕኮው የማይታሰብ ነገር እንደሆነ አይተናል! የተልዕኮ ሀላፊነት፣ የምስራቹን መልዕክት፣ የመልዕክቱን ማወጃ መንገድ እና የሀይሉን ተስፋ የሚሰጠን መጽሐፍ ቅዱስ ነው እንደሆነ ተመልክተናል።
------- ------ ------ -------
#ዛሬ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ #ከዘፍጥረት_እስከ_ራዕይ ስለእግዚአብሔር ተልዕኮ እንደሚናገር መጽሐፍ የምናይበትን አስተዋጾ [Outline] እናያለን። በተጨማሪም #በፍጥረት_እና_ውድቀት የታየውን የእግዚአብሔር ተልዕኮ እንመለከታለን።

👉🏿 ስለዚህም በሚከተሉት ጥያቄዎች እና ምንባብ ላይ እንድታሰላስሉ (Reflect) እና ሀሳባችሁን እንድታካፍሉ እጠይቃለሁ!

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ዘፍ 1፡26-28፣ ዘፍ 2፡15፣ ዘፍ 3፡15፣ ዘፍ 9፡1፣ ዘፍ 11፡3-9 እና ሐዋ. ስራ 17፡26-27

▪️ በውኑ የሰው ልጅ ህይወት ትርጉም እና ዐላማ አለው?

▪️ የሰው ልጅ ትልቁ ግቡ ምንድነው? ሊረካ የሚችለው በምንድነው?

▪️ ከውድቀት በፊት እና በኋላ ባለው አለም ውስጥ ያለው ልዩነት ምንድነው?

▪️ የሰው ልጅ አለመታዘዝ እና አመጻው ውጤት ምንድነው?

▪️ እግዚአብሔር ህዝቦችን በባቢሎን ግንብ ግንባታ ወቅት ለምን በተናቸው?

ጌታ ይባርካችሁ፤ ለበረከትም ያድርጋችሁ!
-------------------
👉🏿 @EvaSUE58
ፍጥረት፣ ውድቀት እና መበተን - ክፍል 1
ተልዕኮአዊ የመጽሐፍ ቅዱስ #አስተዋጽኦ [ Outline ]

👉🏿 ክፍል #አንድ [1]

#መጽሐፍ_ቅዱስ
#ከዘፍጥረት_እስከ_ራዕይ ስለእግዚአብሔር #ተልዕኮ እንደሚናገር አንድ ወጥ መጽሐፍ አድርገን ብንመለከተው ብለን እናስብ እና #አስተዋጾ [Outline] እናውጣለት።

ቀላል አስተዋጽኦ (Outline)፡
-----------------
1. መግቢያ፡ ከዘፍጥረት 1 - 11፡ ፍጥረት እና ውድቀት

2. ሀተታ፡ ከዘፍጥረት 12 እስከ ይሁዳ መጽሐፍ፡ የመዋጀት/የድነት ታሪክ

2.1. የእግዚአብሔር ዕቅድ በእስራኤል
2.2. የእግዚአብሔር ዕቅድ በክርስቶስ
2.3. የእግዚአብሔር ዕቅድ በቤተ ክርስቲያን

3. መደምደምያ፡ የራዕይ መጽሐፍ

▪️#ያድምጡት
▪️ለሌሎችም #ያካፍሉት

👉🏿 መጽሐፍ ቅዱስን #ከተልዕኮ አንፃር ለማንበብ ይጠቅምዎታል፣

👉🏿 ለተግባራዊ #የተልዕኮ_ሕይወት ይሞገቱበታል፣
------------------------
#Missio_Dei

▪️በአቤኔዘር ሽመልስ
-------------------
👉🏿 @EvaSUE58
ፍጥረት፣ ውድቀት እና መበተን - ክፍል 2
ተልዕኮአዊ የመጽሐፍ ቅዱስ #አስተዋጽኦ [ Outline ]

👉🏿 ከክፍል
#አንድ [1] #የቀጠለ

#መጽሐፍ_ቅዱስ
#ከዘፍጥረት_እስከ_ራዕይ ስለእግዚአብሔር #ተልዕኮ እንደሚናገር አንድ ወጥ መጽሐፍ አድርገን ብንመለከተው ብለን እናስብ እና #አስተዋጾ [Outline] እናውጣለት።

ቀላል አስተዋጽኦ (Outline)፡
-----------------
1. መግቢያ፡ ከዘፍጥረት 1 - 11፡ ፍጥረት እና ውድቀት

2. ሀተታ፡ ከዘፍጥረት 12 እስከ ይሁዳ መጽሐፍ፡ የመዋጀት/የድነት ታሪክ

2.1. የእግዚአብሔር ዕቅድ በእስራኤል
2.2. የእግዚአብሔር ዕቅድ በክርስቶስ
2.3. የእግዚአብሔር ዕቅድ በቤተ ክርስቲያን

3. መደምደምያ፡ የራዕይ መጽሐፍ

▪️#ያድምጡት
▪️ለሌሎችም
#ያካፍሉት

👉🏿 መጽሐፍ ቅዱስን
#ከተልዕኮ አንፃር ለማንበብ ይጠቅምዎታል፣

👉🏿 ለተግባራዊ
#የተልዕኮ_ሕይወት ይሞገቱበታል፣
------------------------
#Missio_Dei

▪️በአቤኔዘር ሽመልስ
-------------------
👉🏿
@EvaSUE58